zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አገዛዙ አጀንዳ ለማስቀየስ አይደለም ዓመት ያለፈው አሰቃቂ ወንጀል ገና ወደፊት ራሱ በራሱ ደራሲነት እና ተዋናይነት አረመኔ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ አጀንዳ በመሆን መንጋውን እያላቀሰ ይቀጥላል ባይ ነኝ። የዛሬ 150 ዓመት ሚኒሊክ ጡትህን ቆርጧል ብሎ ሃውልት የሠራ አገዛዝ ከዚህም ሌላ ነገር ባይፈጽም ነው የሚገርመው።

"…በዚህ ላይ አስተያየታችሁን ስጡና ወደ ሌላ መርሀ ግብራችን እንለፍ። በጨዋ ደንብ ተንፒሱ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዎ ስለ ሕፃን ሔቨን ሰምቻለሁ።

"…ከትናንት ጀምሮ ከምር ደንግጠው ስለ ወንጀሉም አረመኔነት ዓለም እንዲያውቀው በቀና ልብ የወንጀል ድርጊቱን የሚቃወሙ፣ ወንጀለኛው እንዲቀጣ፣ ቤተሰብ ፍትሕ እንዲያገኝ የሚጮሁ አሉ። ነገር ግን በእነዚህ ኑፁሐን ፍትሕ ፈላጊዎች ጀርባ ተከልሎ በተለይ የራሱ የብልጽግና አክቲቪስትና የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ከላይ በወረደለት መመሪያ በሚመስል መልኩ ማኅበራዊ ሚዲያውን ከላይ እስከታች ተቆጣጥሮ ቲክቶኩን በሉት ዩቲዩቡን እና ፌስቡክ ቴሌግራሙን ሁሉ እንደ ሱናሚ ማዕበል አጥለቅልቀው የአዞ እንባቸውን ሲያነቡም ታይተዋል። እኔን የሚገርመኝ እነዚህ ከንቱዎች ሌላውን ማጀዘባቸው ሳያንስ አዛኝ አንጓች መስለው እኔንም ለማጀዘብ ሲላላጡ መታየታቸው ነው። ለወትሮው በፔጄ ላይ "እግዚአብሔር ይመስገን" ለማለት አገዛዙን የሚፈሩና ወኔያቸው የተሰለበባቸው መበለቶች ሳይቀር በድፍረት ወደ ፔጄ መጥተው "ዘመዴ ምነው ዝም አልክ? ዘመዴ ሴት ልጅ የለህምን ምነው ጨከንክ? ዘመዴ አንተን ብዙ ሰው ያነብሃልና እባክህ የሆነ ነገር በል እንጂ? ሕፃኗ ፍትሕ እንድታገኝ ድምፅ ሁናት? ሲሉኝ ውለው አድረዋል። ብልፅግና ያሸንፋል! አቢይ ይግዛን ሲሉኝ የከረሙ ሁላ "ዘመዴ ምነው ዝም አልክ? ሲሉኝ ነው የዋሉ ያደሩት።

"…የዛሬ ዓመት ሐምሌ 25/2015 ዓም የተፈጸመን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ዓመት ጠብቆ ልክ በዓመቱ ሐምሌ 12/2016 ዓም ወደ አደባባይ አምጥተው አጀንዳም አድርገው ለምን በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እንዲጮህ ተፈለገ? ዓመት ሙሉ ለምን ተደብቆ፣ ተከድኖ፣ ተሰውሮ ቆየ? ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው የአገዛዙ ደጋፊ የሆኑ ሚዲያዎች እና የአገዛዙ ተቃዋሚ ነን የሚሉት ሳይቀር የኦሮሞ ነፃ አውጪ እና የትግሬ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ጭምር አንድ ላይ ቆመው ዋይ ዋይ የሚሉት? ብልፅግና፣ ህወሓት እና ኦነግ አንድ ላይ ሆነው እኮ ነው በግፍ የተገደለችን ሕጻን ሲያዝኑላት የሚታዩት። ታየኝ እኮ። ኧረ አልሰማህም።

"…ወላሂ ከዛሬ ጀምሮ ዐማራ አልሆንም እያለች የታረደችዋን የዐማራ ሕፃን ባላየ በዝምታ አልፈህ ስታበቃ፣ የዘጠኝ ወር እርጉዝ ድርስ ነፍሰ ጡር ማኅፀኗ በሳንጃ ተዘክዝኮ በኦሮሚያ ስትገደል እያየህ ዝም ብለህ ስታበቃ፣ የዐማራ ልጅ በኦሮሚያ ምድር አይወለዳትም ብለው በሻሸመኔ ያችን የዐማራ ሴት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል በዓይንህ እያየህ፣ በጆሮህ እየሰማህ ስታበቃ፣ በመተከል፣ በወለጋ የዐማራ ሕፃናት በጅምላ ተጨፍጭፈው አስከሬናቸው ተከምሮ እያየህ እኔ ስጮህ እየታዘብክ፣ ስትሰድበኝ ጭምር ከርመህ፣ በፍርሃት ቆፈን ተይዘህ ዝም ጭጭ ብሎ ኖረህ ኖረህ፣ ዛሬ መንጋ ሙሉ አድርባይ ሁላ ዛሬ ድንገት ተነሥተህ "ፍትሕ ለሕፃን ሔቨን" እያልክ የአዞ እንባህን ስታፈስ ብትውል እንዳንተ ባልቃወምህም ግን አብሬህ አልጮህም፣ ደግሞም አልሰማህም። እኔ ምኔ ሞኝ ነው መንግሥትም፣ ፍትሕም በሌለበት ሀገር መንግሥትም ፍትሕም እንዲመጣ እየተዋደቀ ካለው አካል ጋር ቆሜ ለፍትሕ እታገላለሁ እንጂ ምን ይሁነኝ ብዬ ነው የአረመኔነት መፈልፈያ ማሽን የሆነውን ብልፅግና ስለ ፍትሕ የምጨቀጭቀው? ለሕፃኗ ቤተሰቦች ፍትሕ ያስፈልጋቸዋል? አዎ ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን ከአቢይ አሕመድ አገዛዝ ችግኝ እንጂ ፍትሕ ኢንጂሩ። እናም አንተን አስመሳዩን ሰሞነኛ ጯሂ አበደን አልሰማህም። አልሰማሕም አልኩህ።

"…ጭራሽ አንዱ ፔጅማ የብዙ ሰዎችን የቴሌግራም እና የፌስቡክ ፔጆችን፣ ታዋቂ አክቲቪስቶችን በስም ዝርዝር እየጠራ፣ እየዘረዘረም እነ እገሌ እኮ ጽፈዋል፣ እነ እገሌ ቪድዮ ሠርተው ለቀዋል፣ እነ እገሊት ድምጽ እያሰሙ ነው። ሌሎችም ብዙ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ድምጻችሁን ታሰሙ ዘንድ እየጠበቅን ነው እያለ በጉዳዩ ላይ ያልጻፉትን የፍትሕ ጠላት፣ የወንጀለኛው ተባባሪ አድርጎ ለማቀሳሰር ሲላላጥ ሁላ አይቼው ሞኝህን ብላ ብዬው ነው ያለፍኩት።

"…በግፍ፣ በጭካኔ የተገደለችዋ ሕፃን ከምር እውነት ነው ታሳዝናለች። ፍትሕም ማግኘት አለባት። ነገር ግን ከዚህ አረመኔ አገዛዝ ፍትሕ አይጠበቅም። የዚህችን ሕፃን አረመኔያዊ አሰቃቂ ግድያና ሞት ባለፉት 6 ዓመታት ውስጥ አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በሌሎች የኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ እየተፈጸመ ካለው አሰቃቂ፣ አረመኔያዊ ወንጀሎች የተለየ አያደርገውም። እንደ ሕዝብ ነው አቢይ አሕመድ እየጨፈጨፈን ያለው። ሚልዮን ትግሬ በአቢይ አልቋል። ዐማራም እንደዚያው። ኦሮሞም አገዛዙን መንቀፍ ይሆንብኛል ብሎ አፍሮ ነው እንጂ በሸኔ ሰበብ እያለቀ ነው። አረመኔነት የሥርዓቱ መገለጫ ነው። ሕጉ አረመኔነትን የሚያበረታታ ነው። ሕፃናትን ያረደች ወንጀለኛ ኦሮሞ ስለሆነች ብቻ  መርማሪ ፖሊሱ "አይዞሽ አታልቅሺ፣ ተረጋጊ" እያለ ሚሪንዳ እየሰጠ ቪድዮ ቀርጾ እንዲበተን የሚያደርግ ነው። በሕፃናት ላይ ግበረ ሰዶም የሚፈጽሙ የሚሸለሙበት ሥርዓት ነው። ሥልጣኑ በሙሉ በዓረመኔዎች፣ ልቡሣነ ሥጋ በሆኑ ጋኔሎች የተሞላ፣ የተያዘ ነው። እናም ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው እኔ ከያዝኩት የዐማራ ፋኖ ተጋድሎ ንቅንቅ ብዬ ያውም በብልፅግና ካድሬዎች መሪነት የሚንጫጫን አጀንዳ ይዤ አብሬ የምንጫጫው። ክላልኝ የእንጭቅ ልጅ…

"…እኔ ዘመዴ የሕፃኗ አጀንዳ መራገቡን አልቃወምም። የምቃወመው አጀንዳ ፈጣሪዎቹ ራሳቸው መልሰው እኔን የአጀንዳው አራጋቢ ለምን አልሆንክም ብለው ሲጋተቱኝ ሳይ ብቻ ነው። ትግሬዎቹ የጮሁት ለሞተችዋ ሕጻን አዝነው ነው ብዬ አላስብም። ኦሮሞዎቹም እንደዚያው። ሁለቱን ያስጮሃቸው ድርጊቱ የተፈጸመው ዐማራ ክልል ያውም ባህርዳር ላይ መሆኑ ብቻ ነው። ይሄ ነው እነሱን የሚያስጮሃቸው። ትግሬዎቹ ድርጊቱ ባህርዳር ከመፈጸሙም ሌላ የልጅቷ አባት ትውልዱ ወይም ዘሩ ትግሬ ስለሆነም ጭምር ነው። ለሥጋቸው ማድላታቸው መሆኑ ነው። ኦሮሞዎቹ አክቲቪስቶችም ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ ለማጉላትና ትግሬዎቹን አክቲቪስቶች ለማጽናናት ብለው ነው። ሌላ ምንም ኀዘኔታ ኖሯቸው አይደለም። አጭቤ ሁላ።

"…ልብ በሉ የኢዜማ አመራር የነበረው የፖለቲከኛው ዳንኤል ሽበሺ ሕፃን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የተደፈረችው እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ወንጀሉ ተፈጽሞባት ፖሊስ ጣቢያ ስትሄድ ግን ፖሊስ የአባቷን ስም አይቶ አንቺማ የአገዛዙ ተቃዋሚ የዳንኤል ሽበሺ ልጅ ነሽ፣ ጥፊ ከዚህ ያላት እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ይሄንን ዜና እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት አይዘግቡትም። የኦሮሞ እና የትግሬ አክቲቪስቶች አይጮሁለትም። መንጋው ገተቴ የማኅበራዊ ሚዲያ አዛኝ አንጓችም ትንፍሽ አይላትም። እነ ያሬድ ያያ ዘልደታም በቪዲዮ ወጥተው "ደፋሪዎቹን ገድላችሁ አሳዩን ብለው አይጮሁም" ፍትሕ ለሕጻን ሔቨን ግን ደግሞ ፍትሕ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊባል ይገባል።

"…እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው መሰላችሁ? ወንጀለኛው በብአዴን እጅ ነው። የተያዘውን ወንጀለኛ አሁኑኑ ስቀሉት። ግደሉትም። ሥልጣኑ ሁሉ በእናንተ እጅ ነው ያለው። ሌባ ተይዞ እኮ ዱላ አይጠየቅም። ከምታጯጩሁ። አጀንዳ ለማስቀየስ የቆየ የተረሳ ወንጀል አጀንዳ አድርጋችሁ ፒፕሉን ከምታንጫጩ፣ ወንጀለኛውንም፣ ወንጀለኛውን ለማስፈታት የሚዳክሩ ፖሊሶችን፣ ዳኞችን ሁሉ ሰብስባችሁ ስቀሉ። ስቀሉናም አሳዩን። እኔ እያልኩ ያለሁት ግን እናንት መርጦ አልቃሾች ራሳችሁን ችላችሁ ጩሁ ነው። ለምን ከእኛ እኩል አትጮህም ብላችሁም አታዝጉኝ ነው። አሁን እኔ ዘመዴ ሥራ ላይ ነኝ። ይህን ሰው መሳይ በሸንጎ አረመኔ ወንጀልን የሚያበረታታ አገዛዝ ለመጣል እየተዋደቀ…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ፀምር ዘጌዴዎን
የጌዴዎን ብዝት አንች ነሽ።
      "መሳ 6፥ 36-40"

"…ጌዴዎንን መልአኩ ጌታ ባንተ አድሬ እስራኤልን ከምድያም ሰዎች አድናቸዋለሁ ብሎሃል ሂድ አለው፡፡ እንኪያስቆየኝ መሥዋዕት ልሠዋ ብሎት ሄደ። መሥዋዐት ሰውቶ ሥጋውን በቅርጫት ደሙን በብርት አድርጎ አቀረበ። ደንጊያውን ጸፈጸፈ አንጨቱንም ረበረበ። ሥጋውን እዚያ ላይ አደረገው። መልአኩ በዘንግ ቢነካው ተቃጥሏል፡፡ እሳት የመቅሰፍተ እግዚአብሔር፣ ሥጋው የአሕዛብ ሕለት የኩናተ ጌዴዎን ምሳሌ ነው፡፡ ሁለተኛ ጸምር ልዘርጋ ጠል ከብዝት ላይ ይውረድ ዳርና ዳሩ ይቡስ ይሁን ሲለው ይሁንልህ አለው፡፡ ሦስተኛ ፀምር ልዘርጋ ጸምር ይቡስ ይሁን ጠል በዳርና በዳር ይውረድ አለው ይሁንልህ አለው፡፡ ሁሉም ሆኖለታል፡፡ ለጊዜው ፀምር የእስራኤል ጠል የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ፣ ጠል ከፀምር መውረዱ እስራኤልን የመርዳቱ፣ በዳርና በዳር አለመውረዱ አሕዛብን ያለመርዳቱ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ፀምር አይለወጥም የእስራኤል ጠል የመቅሰፍተ እግዚአብሔር፣ ጠል ከፀምር አለመውረዱ እስኤልን ያለማጥፋቱ፣ በዳርና ባዳር መውረዱ አሕዛብን የማጥፋቱ ምሳሌ ነው። ፍጻሜው ግን ፀምር መውረዱ ጌታ በእመቤታችን የማደሩ ምሳሌ ነው፡፡ በዳርና በዳር አለመውረዱ ጌታ በሌሎች ሴቶች ያለማደሩ ፀምር ይቡስ መሆኑም እመቤታችን እንበለ ዘርዕ የመውለዷ ምሳሌ ነው። በዳርና በዳር መውረዱ ሌሎች ሴቶች በዘር በሩካቤ የመወለዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ጌዴዎን ማለት ጽንዕ ጽንዕ እግዚአብሔር ኀያል ማለት ነው። ትውልዱ ምድረ ርስት ከገቡት ከመንፈቀ ነገደ ምናሴ ነው፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እንደማመጥ…!

"…ወያኔ ያ ሁሉ ጣት ተዋጊዎቿ እንደ ሕዝብ ያለቁት እንደ መንጋ አንድ ላይ እጅብ ብለው ሲግተለተሉ ነው። እናም ፋኖዬ ድሮን የሚባል ነገር አለ እሺ።

• የመጨረሻው ባይሆንም ድሉ ግን ደስ ይላል። ቢሆንም፣ ቢሆንም ግን እየተደማመጥን። ስሜት በልኩ ይገለፅ፣ ደግሞም ተበተን፣ ሰብጠርጠር በል። አትዘናጋ ለማለት ነው።

• ስላዳመጣችሁኝ አስመሰግናላሽ 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐማራ ፋኖ ሆይ…!

"…የብህትውና ቦለጢቃ፣ ጻድቅ ጻድቅ መጫወቱም ይብቃህ። አንተ ገዳይህን፣ አራጅህን፣ አነዋሪ ደፋሪህን፣ የፈለገውን አሟልተህለት፣ ወርቅ አንጥፈህ፣ ወርቅ አልብስህ ብትልከው፣ ብትሸኘው እሱ መልሶ አንተን ማረዱን፣ መግደሉን አይተውም።

"…ኦሮሙማው፣ የህወሓት መርዝ ትውልዱ አእምሮ ላይ የሞላው፣ የተጠቀጠቀው፣ ዐማራ ኦርቶዶክሱም፣ እስላሙም ጠላት ተደርጎ ነው። ህወሓት እና ኦህዴድ ኦነግ ሃውልት ቀርጸው ልጆቻቸውን በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ቀርጸው እያስተማሩ በሐሰት ትርክት፣ በኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ አብባ ድርሰት ያሳደጉት ዐማራ የተባለን ፍጡር ስለመበቀል፣ ከምድረ ገፅ ስለማጥፋት ነው።

"…ጥይት መግዣ አጥቶ የሚሞተው ፋኖ አያሳዝንህም ይሄን ደም መጣጭ አረመኔ ስምንት ሺ ብር ሰጥተህ ድጋሚ እንዲገድልህ ከምትልከው? አዝመራውን ሊያይ የመጣ ገበሬ አባትህን እና ወንድምህን እንዲህ ረግጦ ሲጨፈጭፍ የከረመን አረመኔ ተንከባክበህ መልሶ እንዲወጋህ ማድረጉስ ተገቢ ነው ወይ?

"…አሜሪካ እንድትራራልህ፣ አውሮጳ አይ ዐማራ እንዴት ያለ ደግ ፍጥረት ነው እንዲልህ ፈልገህ ነው? ሞኝ አትሁን። ገዳይ የብአዴን አባላትን አንበርክከህ ስለቀጣህ አሜሪካ በአምባሳደሯ በኩል፣ ሀብታሙ አያሌው እና እስክንድር ነጋ አምባሳደሩን ደግፈው እንደውም ሰላም አስከባሪ፣ አጣሪም ቡድን ጎጃም ይግባ እኮ ነው ብለው በድፍረት የፈረዱብህ። አትሞኝ። አታብዛውም።

"…ምርኮኛ ሁሉ ይገደል፣ ይታረድ አይባልም። ምርኮኛን ግን እንደ ሻአቢያ መንገድ፣ እርሻ ታሰራዋለህ። እንደ ወያኔ ዋሻ ታስቆፍረዋለህ፣ እርከን ታስደረድረዋለህ። ይሄን የመሰለ ወጠምሻ አራጅ ጎረምሳ ማርከህ፣ ቀልበህ፣ ከዚያም በላይ የአንተን እናት ገድሎ የእሱ እናት ስለናፈቀችው ገንዘብ ሰጥቶ መልቀቅ መሰልጠን፣ ደግነት አይደለም። ይሄ እልም ያለ ፋርነት ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው። አዎ በተቀበላችን መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ ሕጻናት፣ ነፍሰጡሮችና የደም ግፊት፣ የልብ ድካም ያለባቸው ዐማሮች እንዳያዩት የሚመከር አንድ ዘግናኝ በዐማራ ወጣቶች ላይ የፀጥታ ኃይሉ የሚፈጽመውን ዘግናኝ ቪድዮ ላሳያችሁ ነኝ እና ዐማሮች የሆናችሁ በሙሉ ለማየት ተዘጋጁ።

"…አላችሁ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ያለፈው ሰኞ ዕለት ባወጣሁት ሳምንታዊ የቴሌግራም መርሀ ግብራችን መሠረት ከዛሬዋ ዕለተ ቅዳሚት ሰንበት፣ እሁድ እና ሰኞ ከማክሰኞ እስከ አርብ ድረስ የሚኖረን "ርዕሰ አንቀጽ" አይኖረንም ማለት ነው። ከምር እኔማ በማየው፣ በምሰማው የዐማራ ሁኔታ ከወዲሁ ኩራትም፣ እረፍትም እየተሰማኝ ነው። እንዲያውም ባይገርማችሁ ከቤተሰቦቼ ጋር ሁሉ ወጣ ብዬ ከራየን ወንዝ ማዶ በሚገኝ የጸሎት ቤት በመገኘት በስንት ዓመቴ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም ትርጉም ከካህናት አባቶቼ አንደበት ስኮመኩም አርፍጄ መምጣት ሁላ ጀምሬአለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ስለ እውነት ዛሬ እጅግ በጣም ነው ደስስ ያለኝ። በዓይነ ሕሊናዬ ሁላ በልጅነት ክብር ባገኘሁበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም፣ ብዙ ፀጋ ባገኘሁባቸው የፍልሰታን ጾም ያሳለፍኩባቸው የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ መንዝ እመጓ ኡራኤል እና እመቤታችን በዓይኔ ላይ ሲዞሩ ነው የዋሉት። ምንአልባትም ማን ያውቃል ብልፄ ወድቆ፣ ሾተላዩ ስኳድ ከዐማራ ትግል ተነቅሎ ወድቆ፣ በሚቀጥለው ዓመት…?

"…ለማንኛውም በመርሀ ግብራችን መሠረት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለጥቂት ወራት ተቋርጦ የነበረው የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችን በይፋ ይጀምራል። እናም እንደተለመደው እናንተም ከወዲሁ ግጥማችሁን አዘጋጁና ለባለ ማሰንቆው ለመስጠት ተዘጋጁ። ዛሬ ትንቢት፣ ትንቢት የመሰለ ግጥም ነው ከእናንተ የምጠብቀው።

"…ተዘጋጁ እሺ። ጻፉ። ሞክሩ። ግጥሙ ግሩም የሆነውን እኔ ራሴ አውጥቼ እለጥፈዋለሁ። ዘመኑን የዋጀ ቅኔያዊ ግጥም በብዛት ይጠበቃል።

• ሰምታችኋል አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…21 ሺ ሰው አንብቦት 14 ሰው 😡 ብው ብሎ መናደዱን፣ መበሳጨቱን የገለጸበት የዛሬውም ርዕሰ አንቀጻችን ይህን ይመስል ነበር። ቀጣዩ ደግሞ እኔና ብዙ የዚህ መንደር ኗሪዎች በጉጉት የምንጠብቀው የአድማጭ ተመልካቾቻችን አስደማሚ ብስል ያለ አስተያየት የሚኮመኮምበት ሰዓት ነው።

"…የሚገርመው ነገር አንድም ከመሬት የሚጣል አስተያየት የሚሰጥ ሰው የለም። ሁሉ ገራሚ ሆኗል። ከጦማሩ አስተያየቱ ይልሃል ይሄ ነው።

"…ብዙዎች እኔ ፔጅ ላይ ሲመጡ እረፍት ይሰማቸዋል። ባለጌ ስድአደግ ቦታ የለውም። አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ለቅላሚ ቦታ የለውም። አጀንዳ አስቀያሾች ቦታ የላቸውም። በጨዋ ደንብ ተቃውሞአቸውን የሚገልጹ የሚበረታቱበት ቤት ነው። እንደነ ዳንኤል ክብረት፣ ምስጋናው አንዷለም፣ አያሌው መንበር፣ ሙላት አድኖ የኮመንት መስጫ ሳጥን ተዘግቶ ራስ ብቻ ለፍልፎ ሌላው እንዳይተነፍስ አይደረግም። ሁሉም ከአጀንዳው ሳይወጣ በጨዋ ደንብ ሓሳቡን ተንፍሶ ከጨጓራ ህመም ይገላገላል። እናም ቀጥሎ ዛሬ በተጻፈው ርዕሰ አንቀጽ ላይ ያላችሁን አስተያየት በጨዋ ደንብ ግለጹ። ተንፒሱ።

• 1…2…3…ጀምሩ ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …የሰሊጥ ብር፣ በኡጋንዳው ስኳድ አማካኝነት እስክንድርን ተጠቅመው በኃይለኛው ሞከሩ አልተቻለም። ጎጄ መለኛው አስቀድሞ ስለነቃ የእስክንድር ነጋን ሴል ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ጠራርጎ ነው ሰብስቦ የመከረው። ከጎጃም የስኳድ ሴል መጽዳቱን ያየው ወሎም አስቀድሞ ነው በሩን የዘጋው። እናም አሁንም አልረፈደም። ረጅሙ የስኳድ እጅ ከዐማራ ፋኖ ትግል መቆረጥ አለበት። ስኳድ ከጀርባው ብዙ ኮተት፣ ከግንቦት ሰባት እስከ መዓት ድረስ የተሸከመ ባንዳ ስለሆነ መላ ሊፈለግለት ይገባል።

"…እመኑኝ መጨረሻ ላይ ይሄ ቀርጣፊ ፀረ ዐማራ የወያኔ ዲቃላ ቡድን ራሱ ጅሉን እስክንድርን ነጋ እና መሃይሙን መከታው ሞሞን ቀርጥፎ ነው የሚበላው። ባለፈው ሳምንት ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው ማንገራገር ሲጀምር በመከላከያ እንዲከበብ እና እንዲደመሰስ ተወስኖ ነበር የነበረው። ኮሎኔሉ መውጪያ ሲያጣ በር የተከፈተለት ወደ ደቡብ ጎንደር ወደ ጋይንት መሄጃ ቀጭን መንገድ ብቻ ነበር። የኮሎኔሉን ጋይንት መግባት ተከትሎ እስክንድርም ወደ ደቡብ ጎንደር ይሻገራል መባልን ሰምቼም ነግሬአችሁ ነበር። ታዲያ አጅሬ እስክንድር ምን እንደሰማ አይታወቅም በፍጹም ወደ ደቡብ ጎንደር አልሄድም ማለቱ ነው የተሰማው። ስኳድ አደገኛ ነው ብዬ ተናግሬአለሁ። ኡጋንዳ የመሸገው ጎንደር አሰዳቢ ስኳድ የተባለው ቡድን አደገኛ ነው አልኳችሁ። ግን አሁን የዐማራ መከራ የነጠላው ጫፍ ላይ ስለሆነ ይጨመቃል። ይራገፋል። ይደርቃል።

"…ሰሞኑን አያ መከታውን ሽማግሌዎች ቀርበው እንዲህ ይሉታል። "አንተ ግን ለምን ከእስክንድር አትለይም? ምንድነው እንዲህ ከእሱ ጋር ያጣበቀህ? ለምን የሸዋን ትግል በእስክንድር ምክንያት ታዳክማለህ? በአስቸኳይ ከእሱ መለየት አለብህ" ይሉታል። እናም ሞኙ ሰው አማኙ፣ መሃይሙ መከታው (ማይም አላልኩም መሃይም እንጂ፣ ሰደበው እንዳትሉኝ ነው) መሃይሙ ምን ብሎ ለጠየቁት ጥያቄ ቢመልስ ጥሩ ነው። "እኔ እኮ የጨነቀኝ ራሱ እስክንድር ቤተ ክርስቲያን ወስዶ ላንከዳዳ ብሎ እስምሎኛል። እናም እኔ እንዴት ላድርግ? አሁን ያለው ሴራ ቆይቶም ቢሆን ገብቶኝ ነበር። ግና  መሃላውን፣ ቃልኪዳኑን እንዴት ላፍርስ? ብሎ ቃሉን መስጠቱን ነው የሰማሁት። አይ ዐማራ በእውነት አንዳንዴ እኮ ሃይማኖቱ ገራሚ ነው። አሁን ስኳዶች መከታውን ከሸዋ ልጆች አራርቀው ራሳቸው ዙሪያውን ከበውታል። የሆነ ቀን ያው እንደለመዱት ራሳቸው ይበሉታል። የሚሻለው በጊዜ ዘመድ፣ ከወገኖቹ መቀላቀል ነው።

"…አሁን በሸዋ ያለው መከታው ማሞ የሚቆጣጠረው የጎንደር ስኳድ ምን እያደረገ ነው? አዎ ሸዋን እያስጨነቀ ነው። የሸዋ ሕዝብ በፋኖ እንዲማረር እያደረገ ነው። በማታለል የሸዋ ዳያስጶራን ገንዘብ እየተቀበለ ትግሉን ቆርጥሞ ሲበላ የከረመው የመከታው ጦር ርዳታው ስለተቋረጠበት አሁን በሚዲያ ወጥታ ስትለፈልፍ የምትውለው ፋኒት ባርች ሳትቀር የሞዴስ መግዣ፣ የካርድ መግዣ ሁሉ አጥተው ተጨንቀዋል። ይሄ መፈጠሩን የየው የስኳድ ቡድን የዐማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ በሙሉ ከነጋዴው ማኅበረሰብ ከ50 ሽህ እስከ 500 ሽህ ብር እያስገደዱ እንዲቀበሉ አዝዞ እነ ጅሉ አበበ ጢሞ፣ እነ ሞኙ መከታው ማሞ የራሳቸው ወገን እየጋጡት፣ እያስጨነቁት ይገኛሉ። የሸዋ ዐማራ እንዲጎሰቁል ከገጠር አርሶ አደር ማኅበረሰብ ጭምር በአባወራ ብዙ ሽህ ብር እያስከፈሉ ይገኛሉ። ካላመናችሁኝ ደውላችሁ አረጋግጡ። እነ ምስጋናው አንዷለም ካሸነፉንማ ሞተናል ማለት ነው። የእንጭቅ ልጅ ሁላ።

"…እስክንድር በምርጫ ቦርድ ኦዲት የተረጋገጠ 20 ሚልዮን ብር የባልደራስ ገንዘብ አስዘርፎ ነው ፈርጥጦ ጫካ የገባው። ቀለብ ስዩም፣ አስቴር አሁን ኡጋንዳ የሄደችው ልጅ ለእኔ ሲበዛ ወዳጄ ናት። አሁን አሁን ቁጭ ብዬ ግን ነጥቦችን ማገጣጠም ስጀምር ደነገጥኩ። ቀለብ የአርማጨሆ ልጅ ናት። ያዙልኝ። እስክንድር ደግሞ በባልደራስ የሰበሰባቸው በሙሉ አብዛኛዎቹ ጎንደሬና ትግሬዎችም ጭምር ናቸው። በአሜሪካ ገንዘብ ያዡ ዶር አምሳሉ ደቡብ ጎንደሬ ነው። ኦሮሞዎቹ እነ ኤርሚያስ ዋቅጅራን ሳትዘሉ ማለት ነው። የመሳይ መኮንን ተንታኝ ገለታው ዘለቀ ግን ዘሩን ዐላውቀውም። ባልደራስን በገንዘብ የደገፈው፣ በዶላር ያንበሻበሸው ደግሞ ሞኙ ዐማራ ነው። የፈረንጅ ላሙ ዐማራ። ቀለብ አስቴር ስዩም የፖለቲካ ፓርቲዋ ግንቦት ሰባት ነበር። የታሰረች፣ የተፈታችውም በግንቦት ሰባትነት ነበር። ወዲያው ከእስር እንደተፈታች በቀጥታ የገባችው ወደ ባልደራስ ነበር። ጎንደሬዋ የአርማጨሆ ልጅት የደቡብ ጎንደሬው እስክንድር ነጋ የቀኝ እጅ ነው የሆነችው። ጎንደር ድረስ ከእስክንድር ጋር ሄዳ ከአርበኛ መሳፍንት ጋር ቃል ሲገባቡ በዚያው ነበረች። እናም የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ ተወላጅ፣ የጉራጌም ተወላጅ የባልደራስ አባላት ተለቅመው ተመንጥረው ሲባረሩ እስከመጨረሻው ድረስ በባልደራስ ቆይታ አሁን ኡጋንዳ ገብታ ትልቅ የጎንደር ስኳድ ሚዲያ ልትከፍት ነው መባልን ስሰማ የማልደብቃችሁን ነው የደነገጥኩት። የእስክንድር የአክስቱ ልጅ የጃጀው ቀማቴ ጫታሙ ተብታባው ጋዜጠኛ ወንደሰን ተክሉም ከኬንያ ወደ ኡጋንዳ የተወሰደው እንግዲህ ለዚህ ነበር ማለት ነው። ነገር ግን አይሳካም አፈርሰዋለሁ።

"…ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና የዛሬውን ርዕሰ አንቀጽ እንዝጋው። አሁን የእስክንድር የዶላር ፌስታል እየተቀደደ ነው። በአሜሪካ የታገደው ዶላር ሲለቀቅ ድርሻዬን አገኛለሁ ብሎ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ የሆነበት የጋሽ መሳፍንት ተስፉው አርበኛ ሀብቴ ከሚመራው ብርጌድ እና የደቡብ ጎንደር የወልቃይት መሩ በጎንደር ስም ከሚያጭበረብረው የእነ ጌታ አስራደ እና የኮሎኔል ታደሰ የእስክንድር ገባሪ ስኳድ በቀር የወሎ ፋኖዎች አንድ አንድ እያሉ እየወጡ ነው። ጎንደር ላይ ያሉትም ሊንጠባጠቡ እንደሆነ ነው የምሰማው። ሲወስኑ እነግራችኋለሁ። ከወሎ ትናንት ፋኖ ድርሳን ብርሐኔ ዛሬ ደግሞ ፋኖ ሲሳይ እና ፋኖ እስራኤል ከስኳድ ቡድን መለየታቸውን በይፋ አውጀዋል። መላው ወሎዬ ቤተ ዐምሓራ ነው ጮቤ እየረገጠ ያለው። ገንዘብ ያደነቆራቸው እነ ሀብቴና መከታው ካልሆኑ በቀር ሌሎችም የሀብታሙ አያሌውንና የእስክንድርን የዶላር ዕዝ በቅርቡ ፍርስርሱን አወጣዋለሁ። ለሕዝብ የሚታገል ሕዝብን ሲሰማ ለዶላር የሚታገል ቀጣሪውን ነው የሚሰማው። እርግጠኛ ነኝ የእስክንድር ሴራ፣ የስኳድ ሴራ ከከሸፈ፣ ሁሉም እንደ ጎጃም አንድ ወጥ ከሆነ፣ አራቱም ክፍላተ ሀገራት አንድ ሆነው፣ በአንድ ቀን ዘመቻ ድባቅ መምታት አያቅታቸውም። እስከዚያው ግን ስኳድን እኔ ብቻዬን የገባበት ገብቼ እወቅጠዋለሁ። እረፍት ነው የማሳጣው። የዳዊት ጠጠር ሆኜ እንደ ጎልያድ እገነድሰዋለሁ።

"…የእስክንድር ነጋን ክፍለጦር በእስክንድር ነጋ ስም የመሠረተው ፋኖ እንድሪስ ከማንም በፊት የሚያውቀው እኔን ነበር። ከግንባር የሚልክልኝን መረጃም በመረጃ ቲቪ የምለቅለት እኔው ነበርኩ። ኋላ ላይ እነ ሀብታሙ አያሌው አግኝተውት ሲያሸፍቱትም አንዲት ክፉ ቃል ተናግሬው አላውቅም። ደውሎ እንኳ ሲያናግረኝ ሳላውቀው እንደ ወንድም ነበር ትክክል አይደለህም እለው የነበረው። እነ ሀብታሙ ብዙ አስለፈለፉት። አሁን ግን ዛሬ ስሰማ እነ ፋኖ እንድሪስም ከእስክንድር እና ከስኳዱ መውጣታቸውንም ሰማሁ። በእስክንድር ነጋ ስም የመሰረቱትን ክፍለጦር ስሙን መቀየራቸውን ሰማሁ። ይሄ በእውነት ለእኔ ትልቅ ድል ነው። ኑረዲን ወንድሜ እንኳን በሰላም መጣህ ለማለትም እፈልጋለሁ። 👇③ ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን የዐማራ ፋኖ በጎጃም አንድ የዐዋጅ ታናሽ ወንድም የመሰለ ቀጭን መመሪያ ለጎጃም ዐማራ ሕዝብ አስተላልፎ ነበር። በሦስት ጀነራሎች የሚመራ ቁጥሩ እጅግ ከፍ በርከት ያለ የኦሮሙማው ገዳይ ጦር ከወትሮው በተለየ መልኩ ወደ ጎጃም ስምሪት ተቀብሎ በዘመቻ መልክ እየመጣ ነው። አገዛዙ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የጎጃሙን የፋኖ አደረጃጀት አፈር ደቼ ካበላሁት የሌላው ቀላል ነው ከሚል ግምገማ ተነሥቶ ነው። እናም ይሄንን መንጋ ገዳይ አራዊት ሠራዊት የገባው ሳይወጣ አፈር ከደቼ ለማብላት ያመቸኝ፣ መክቼም ለማነከት ይቀለኝ ዘንድ ማንኛውም ተሽከርካሪ በጎጃም ምድር እንዳይንቀሳቀስ ዐውጆ ነበር። እናም ዐዋጁ በታወጀ በሰዓታት ውስጥ በመላዋ ጎጃም ትእዛዙ ተግባራዊ ሆኖ ትራንስፖርት የተባለ በሙሉ ቀጥ ብሎም ቆመ። ተመልከቱ ይህ የሆነው በጎጃም አንድ የፋኖ አደረጃጀት በመኖሩ ምክንያት ነው። በአንድ አመራር ውስጥ መሆን ያለውን ጥቅም አያችሁልኝ አይደል? ጎንደር፣ ሸዋ ይሰማል?

"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም ይሄን ቀጭን ወፍራም ዐዋጅ ሲያውጅ በመጀመሪያ ቀድሞ የተቃወመው ኡጋንዳ የመሸገው የትግሬዋ የህወሓት ቻናል የሆነ የትግሬ ሚዲያ ነው። "የጎጃም ፋኖ እንዴት በሕዝቡ ላይ መንገድ ይዘጋል? እንዴት ትራንስፖርት ይቋረጥ ይላል? ብሎ የጮኸው የትግሬ ሚዲያ ነው። እኛ ትግሬዎች መንገድ ተዘግቶብን የደረሰብንን እናውቃለን። እናም ልክ አይደለም ብሎ ነው ጓ ያለው።" ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሽዋን ምች አጠናገራት ማለት ይኽም አይደል? በመቀሌ ሁለት ቦታ እንደ አሜባ ተቆራርጠው የራያና የዓድዋ ህወሓቶች ሲፈሳፈሱ ዓይቶ እንዳላየ ዝም የሚለው ትግሬ አክቲቪዝም፣ በወለጋ፣ በጎጂ፣ በምዕራብ ሸዋ እርስ በእርሱ የሚጣለዘው የኦሮሞ አክቲቪስትም የጎጃም ፋኖ ዐዋጅ አሳስቦት ጨንቆትም ዐማራን ሲመክር ፈጣሪ ያሳያችሁ። እነሱን ተከትሎ ነው የብልፄም፣ የኦነግም አክቲቪስቶች ዋይ ዋይ ማለት የጀመሩት። በተለይ ራዕየ እስክንድሮች ተንጫጩ አይገልጸውም።

"…ጎጃም መዋቅራዊ ሥሪቱ በመጠንከሩ ከላይ ወደታች የሚወርዱ መመሪያዎች ወዲያው ነው ተፈጻሚ የሚሆኑት። በጎጃም ፋኖ ወደ አንድ መምጣቱ በፋኖ ስም የሚሠሩ ወንጀሎችን ይቀንሣል። ያጠፋልም። ተጠያቂነትንም ከፍ ያደርጋል። የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ አርበኛ ዘመነ ካሤ ለክፍለጦር መሪዎቹ ያስተላለፈውን መልእክት ስሰማ የተረዳሁትም ይሄንኑ ነው። በቃ ጎጃም አስደማሚ ሆኗል። ጎጃም እንደ ሕዝብ ነው የተነሣው። ይሄ ነው የሚፈለገውም። ጎንደር እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? ሸዋ እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? ወሎም እንደ ጎጃም ለምን አልሆነም? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም። ችግር ስላለባቸው፣ ፈተና ስለገበባቸው፣ ደንቃራ በውስጣቸው፣ ሾተላይ በመሃላቸው ስላለ ብቻ ነው እንደ ጎጃም ያልሆኑት። መልሱ ይሄው ነው። ጎጃም ይሄን አጽድቶ ነው ወደ ሥራ የገባው። ጎጃም እስክንድር ነጋን ከመሃሉ አባርሮ ወደ ሸዋ ሰድዶ፣ እስክንድር ሸዋ ተቀምጦ ገንዘብ እየከፈለ ጎጃምን ይበጠብጡ ዘንድ ያሰማራቸውን በሙሉ ከጎጃም ምድር ለቃቅሞ ይዞ መክሮ "በአንድ ቤት አንድ አባወራ" ብሎ አንድ ሁኖ ነው ውጤታማ የሆነው።

"…ጎንደር እንዲህ እንደ ጎጃም እንዳይሆን ጎንደሬው ራሱ ምልክት የሚያደርገው ፀረ ዐማራው ስኳድ በየት በኩል ያላውሰው? በለሳ፣ ጋይንት መከላከያ ጋር ደም የሚፋሰሰው የጎንደር ዘአማራ ፋኖ፤ ወልቃይት ላይ ከመከላከያው ጋር ቢራ እየጠጣ፣ መሬት የሚቸበችብ፣ የዐማራን ሴቶች የሚያነውር፣ የሚያማግጥ ወንበዴ ከሃዲ ስኳድ በየት በኩል ያንቀሳቅሰው? የወልቃይቱ ዐማራ ነኝ ባይ የሰለጢ ነጋዴ ፀረ ዐማራ ስኳድ የጎንደር ዐማራን እየገደለ፣ እየጨፈጨፈ ያለውን መከላከያ ፋኖ ከነካው ቀይ መስመራችን ተነክቷል። ፋኖ መከላከያን መውጋቱ ትክክል አይደለም ብሎ ስንቅና ተተኳሽ ጭምር ሰጥቶ የሚያሰማራው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እያለ በየት በኩል የጎንደር ዐማራ አንድ ይሁን? የማይካድራውም፣ የመራዊም ጭፍጨፋ የማይሰቀጥጠው የጎንደር ነቀርሳው ስኳድ እያለ በየት? ጎጃምን አልፎ ጎንደር የማይገባው መከላከያ በትግራይ በኩል ወልቃይት ገብቶ ነው እኮ ራሳቸው ጎንደሬዎችን የሚጨፈጭፈው። በጣም አስቂኝ ነገር እኮ ነው ጎበዝ።

"…ጎንደር እንደ ጎጃም አንድ እንዳይሆን በአሜሪካ የተያዘው፣ የታገደው የእስክንድር ዶላር ተለቅቆ የድርሻችንን እስኪሰጠን ለእስክንድር ነጋ እንገረዳለን ባሉ ጎንደር አሰዳቢ እዞች ምክንያት፣ በተለይ በታላቁ አርበኛ ክቡር አቶ መሳፍንት በአፄ ቴዎድሮስ አጽም የገዘቱት አርበኛ ሀብቴ የሚመራው ጦር ለእስክንድር ነጋ አልታዘዝም፣ እነ ሀብታሙ አያሌው እና ሻለቃ ዳዊት አያዙኝም ባዩን ሻለቃ አርበኛ ባዬ የሚመራውን ጦር በመደምሰስ ለእስክንድር ነጋ ለማስገበር ስለሆነ የሚሠሩት አልተሳካላቸውም። ጎንደር አንድ ባለመሆኑ ምክንያት መከላከያው ከወልቃይት እየተነሣ ጎንደሬ ዐማሮችን በዘዴ ይጨፈጭፋል። ያርዳል። በቃ ሊባል ይገባል። የጎንደር ዐማራ ሲሞት ሲጨፈጨፍ ጭጭ እያሉ ወልቃይት ቀይ መስመራችን ነው ማለት ትርጉሙ አይገባኝም። እንዱገባኝም አልፈልግም።

"…አሁን ጎንደር ሦስት የፋኖ አደረጃጀቶች ተፈጥረዋል። አንደኛው የእስክንድር ነጋ የተያዘው፣ የታገደው ዶላር ሲለቀቅልን የተወሰነ ዲላር እናገኛለን ብሎ ለእስክንድር ነጋ የተከበረ ጎንደሬ ማንነቱን ለገንዘብ ብሎ የሸጠ፣ የሸቀጠውና እስክንድር ነጋ መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ እንዳልከዳው በመሃላ አስሮ ይዞኛል በሚሉት በአርበኛ መሳፍንት ተስፉ የበላይ ጠባቂነት፣ በአርበኛ ሀብቴ የሚመራው ዕዝ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በጎንደር ዐማሮች የሚመራው፣ አርበኛ ውባንተን የመሰለ ጎንደሬ ጀግና ለእስክንድር ነጋ አልገብርም በማለቱ በአርበኛ መሳፍንት ርግማን፣ ኡጋንዳ ባለው ስኳድ በሙላት አድኖ አርቃቂነት በኢትዮ 251 ሚዲያ፣ በመረጃ ቲቪ በታወጀ የሞት ዐዋጅ ምክንያት በግፍ የተገደለውና ከእርሱ ሞት በኋላ በአርበኛ ባዬ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ነው። ሦስተኛው ደግሞ አሁን ከዐማራ ፋኖ በጎንደር በስኳዱ ምክንያት የተገነጠለው እና ወደፊት ክልል ሀገር ወይም ራሷን የቻለች ክልል ትሆናለች ብለው የሚቃዡት ስኳዶች ጎንደርን በፕሬዘዳንትነት ትመራለህ ተብሎ ቃል እንደተገባለት በሚነገረው የእናት ፓርቲ መሥራች፣ ኋላም ፋፍሕዴን አሁን ተገንጣይ የሆነው እና ለእስክንድር የገበረው ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ የሚመራው ፋኖ ነው። ታላቋ ጎንደር ሦስት ፋኖ አደረጃጀት ነው ያላት። አያሳዝኑም ወይ?

"…ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ። አሁን የምነግራችሁንም ደጋግማችሁ መርምሩት። እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ ጌታ አስራደ፣ እነ ፋኖ ተስፋሁን እና ኢያሱ የነበሩት ከአርበኛ ውባንተ ጋር ነበር። እነዚህ ሰዎች የሚደገፉት ደግሞ በእነ ዶር ምስጋናው አንዷለም ነበር። ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ። እነ ሀብቴና ጋሽ መሳፍንት ደግሞ ውባንተን ከሰውት በሚዲያ የሞት ዐዋጅ ያወጁበት ምክንያቱ እንዴት እነዚህን ሰዎች አንተ ጋር ታስጠጋለህ ተብሎ ነበር። ውባንተ ይመልስላቸው የነበረውም "እነዚህ ልጆች ጎንደሬ ናቸው። የጎንደር ዐማራ፣ ብአዴንም፣ ፋፍዴንም ቢሆኑ ያለፈ ታሪክ ነው። አሁን ያሉት በዐማራ ፋኖ በጎንደር ድርጅት ውስጥ ነው። እንኳን ጎንደሬ፣ የጎንደር ዐማራ ሆነው ይቅርና ኦሮሞም፣ ወላይታም አብሬአችሁ ልታገል ብሎ ቢመጣ መቀበል ነው ያለብን። እናም ልጆቹን አታሳዱአቸው" ነበር የሚለው። አሁንም ተከተሉኝ። 👇① ከታች ይቀጥላል… ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዘወትር ያመሰግን ዘንድ የምንጠብቀው 1ሺ አመስጋኝ ሞልቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…እንደተለመደው ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው ወደ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን አጠር ያለች ነው የምትሆነው። አጠር ብላ ወፈር፣ ደልደል ያለች ለብላቢ ሚጥሚጣ በቃሪያ ናት። እሷን ገምጦ ለመቃጠል አብረን እንሂድ አይደል?

"…እህሳ…ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሕወሓት ተሰነጠቀች፣ ደብረ ጺዮንና ጌታቾ ረዳ ተጣሉ፣ ተቃቃሩ፣ ለገሰ ቱሉ ደነፋ፣ ምርጫ ቦርድ ተቆጣ ለደንታቸው ነው። አያደርጉትም እንጂ ለምን እርስ በርሳቸው በዳጣ በሚጥሚጣ እያጠቀሱ አይበላሉም። አይናጩም። ዐማራ አይመለከትህም።

"…የፋኖ ትግል ከጎመራ፣ ከአሸተ ወዲህ ነው ተጣሉ ተጣሉ ሲባል የሚሰማው። ጠቡ ቧልት ነው። ከአቢይ ጋር በነበረው የትግሬ መቀነሻ፣ አፋር እና የዐማራን ማውደሚያ፣ ነባሩን የመከላከያ ጦር ቆርጥሞ የመብያ የፌክ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ አንተ እንዲህ አደረክ፣ በፕሪቶሪያ እንዲያ ብለህ ተስማማህ ወዘተ ነው ንትርካቸው። ፌክ ነው ጸብ የላቸውም። ወዳጄ የትግሬ ነፃ አውጪን ማመን ቀብሮ ነው። አሁን እየተጣሉ ነው ሲባል ድንገት አዙረው ዐማራ ላይ ጉብ ሊሉም ስለሚችሉ ዐማራ መጠንቀቅ ነው ያለበት።

"…አሁን ትግሬ ከሆነ አካል ጋር ካልተጣበቀ ማንንም መውጋት አይችልም። ከአቢይ ጋር ተሞዳምደው አዘናግተው የሆነ ነገር አይሞክሩም ማለትም አይቻልም። አሁን እነ ህወሓትን ምን ያጣላቸዋል? ራያ እንደሆነ ተሰጥቶአቸዋል። ጠገዴ ተመልሰዋል። ወልቃይት ነው የሚቀረው እሱንም መላ እየፈለጉለት ነው። እና ምኑ ነው የሚያጣላቸው? ጌታቸውና ደፂ ሁለቱም ለአቢይ ወዳጆች ናቸው። አቢይ ጨክኖ ጓ ቢል እንኳ ማይክ ሐመር በርሮ መጥቶ ፓርላማውን ሰብስቦ፣ አቢይን ጆሮውን ጠምዝዞ ሂዊ የፈለገችውን ሕግ ያጸድቅላታል። እና ምን አጣላቸው? መልሱ ምንም ነው።

"…ፋኖ ይህችን ክረምት በአንድነት እንዳይገጥም የጎንደሩ የወልቃይት ስኳድ በእስክንድር በኩል ደንቃራ ሆኗል። ትግሬ ሲያይል ትግሬ ዐማራ ሲያይል ዐማራ ነኝ የሚለው ዐማራ ጠሉ የወልቃይት ስኳድ እንደሁ ወያኔ ዕለቱን ብትመጣ ደስተኛ ነው። ጀትና ድሮኑም በዚህ ጭጋግ ስለማይሠራለት ድራማ እየሠሩ ነው ባይ ነኝ።

• እናም ዐማራ አይመለከትህም ለማለት ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ዶር ምስጋናው አንዷለም ከነ ሀብቴ ጋር፣ ከጋሽ መሳፍንት ቡድን ጋር አብረው እስክንድርን መሪ አድርገው በይፋ ወጥተዋል። የጠንቋይ ልጅ ሁላ። አርበኛ አሰግድ መኮንን አዋክቦ ለአገዛዙ አሳልፎ የሰጠው ይሄ ስኳድ የተባለ የጎንደር ሾተላይ ቡድን ነው። አሰግድን በአቶ መሳፍንት በኩል አሰድቦ፣ አዋርዶ፣ አሳድዶ ያስያዘው ይሄ ነውረኛ ቡድን ነው። ምሬ ወዳጆን እንዴት በድርጅቱ ዓርማ መሃል የጄነራል አሳምነው ጽጌን ፎቶ ይጠቀማል ብሎ ምሬ ወዳጆ አሁኑኑ ካልተገደለ እያለ የሚፎክረውም ይሄ ስኳድ የተባለ የሰኔ 15ቱ ተቸንካሪ ቡድን ነው። ዘመነ ካሤ ጎጃሜ ነው። ጎጃም እኛ እያለን እንዴት የዐማራ ፋኖን ይመራል? አይደለም ዘመነ፣ ከነ ዘመነ ጋር የሚተባበር፣ ከጎጃም ሕዝብ ጋር የሚሠራ የጎንደር ፋኖ ካለ መጥፋት አለበት፣ መገደል አለበት ብለው ዋይ ዋይ የሚሉት ስኳዶች ናቸው። አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ክፍለ ጦሩን የዓድዋ ክፍለጦር ብሎ የሰየመው ትግሬ ስለሆነ ነው ብለው ካልተገደለ የሚለው ይሄ እስኳድ የተባለ ቡድን ነው። የውባንተ ምትክ አርበኛ ባዬን፣ አርበኛ ሳሚን በኮሎኔል ደመቀ የተከዜ ዘብ ጦር፣ በአቶ መሳፍንት እና በሀብቴ ጦር፣ በወደፊቱ የጎንደር ክልል ፕሬዘዳንት ተብሎ በእጩነት የተያዘው፣ የእናት ፓርቲ መሥራቹ፣ በፋፍዴኑ ሊቀመንበር በደቡብ ጎንደሩ ጌታ አስራደ የእስክንደር ነጋ ጦር ከበባ አስድርገው ዐማራ የሆነውን የጎንደር ዐማራ ፋኖ ለመደምሰስ እየተፍጨረጨረ ያለውም ይሄው ስኳድ የተባለ ክፉ የዐማራ ነቀርሳ ነው። ጎንደር፣ የጎንደር ዐማራ ግን ለእዚህ ከሀዲ ቡድን እጁን ይሰጣል ብዬም ለሰከንድም አላምንም። ጎንደሬ ብልህ ነው። ጎንደሬ የፖለቲካ ነቢይ ነው። ውባንተን ሳያውቅ ሳይደርሰልት የበሉትን አውሬዎች አሁን ደግሞ እነ ሳሚን እነ ባዬን ያስበላቸዋል ብዬም አላምንም። ለእነ ዘመነ ካሤ ጎጃም ሕዝቡ፣ ለእነ ምሬ ወዳጆም ወሎ ሕዝቡ ተገን፣ ከለላ እንደሆናቸው ጎንደርም ለእነ ባዬ ተገን በመሆን ከስኳድ ሰይፍ ይታደጋቸዋል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።

"…ኡጋንዳ የሰፈረውና በስኳድ ማስተር ማይንድ በእነ ሙሉዓለም ገብረ መድህን የሚመራው የሚዲያ ሠራዊትም ይበተናል። በእነ መላኩ ፈንታ በእነ መልካሙ ሹምዬ የሚመራውም፣ በደመቀ ዘውዱ የሰሊጥ ብር የሚታገዘውም የስኳድ ቡድን ምንጩ ይደርቃል። እኔ ደግሞ እንዴት ጎጃሜ ነው ብለው የፈረጁትን ማማር ጌትነትን እንዳረዱት አሳያችኋለሁ። ያበጠው ይፈነዳታል እንጂ እኔ ዘመዴ እነዚህን ሾተላይ የዐማራ ትግል ደንቃሮች ሳላሸንፋቸው እረፍት አላደርግም። እነ ሙላት አድኖ፣ እነ ሙሉዓለም ገብረ መድህን፣ የደቡብ ሱዳን ኤርትራ የመሣሪያ ንግዳችሁን ውኃ ነው የማበላው። ምድረ የጠንቋይ ልጅ ሁላ የዐማራን ትግል፣ የአማኙን የጎንደርን ስም ስታረክስ ዝም ብዬም አላይህም። ከወልቃይትም ከዐማራም ትግል ላይ ትመነቀላላችሁ። ወልቃይትም ከፖለቲካው ቅማንትና ከትግሬ ልጆች እጅ ወጥታ በጎንደር ዐማሮች እጅ ትተዳደራለች። የምጽፈው ይመራል ነገር ግን ጨክነህ ጠጣው ያሽርሃል። ይሄ ወቅት ስህተት የማይፈቀድበት ወሳኙ የዐማራ የትግል ወቅት ነው። የሞት ሽረት የሚደረግበት የዐማራ የትግል ወቅት ነው። ደፈር ብለን አይነኬ የሚመስሉ የዐማራን ሰንኮፎች ለመንቀል እንዘጋጅ። ትግሉ ዐማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ኡጋንዳም ጭምር ነው። በዚያም ያላችሁ ተዘጋጁ። ልብ በሉ እነዚህ የስኳድ ስብስቦች የሚመሩት ደግሞ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል አይደለም። ሰዎች ናቸው ለማለት ነው።

"…ትዝብቴን ተናግሬ የዛሬውን በዚህ ላብቃ።

"…ታስታውሱ እንደሆን የሆነ ወቅት የሕዝቡን ሙቀት ለመለካት ብዬ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በስሱ ተንኮስ አደረግሁት። 50% ከመቶው ሕዝብ ጮኸብኝ። ነገር ግን ሲተኛ ሲነሣ እንዲያንሰላስል፣ እንዲያስብ እርሾ ነበር አእምሮው ውስጥ ያስቀመጥኩት። አልደገምኩም። ቆይቼ የዛሬ ዓመት አካባቢም ኮሎኔሉን ሸንቆጥ አደረግኩት። ስኳዱ ብቻና ጥቂት ሰው ነበር የተንጫጫብኝ። ሌላው በሆዱ እያማ፣ ዘመዴ ልክ ነው እያለ ቆየ። እኔ ደመቀን ስጎነትል ስኳዱን አልነካውም ነበር። ስኳዱ ግን አካሄዴን ስለሚያውቅ በጊዜ በስድብ ሊያስቆመኝ ነበር ይውተረተር የነበረው። ከትናንት ወዲያ ግን ኮሎኔሉንም፣ ስኳዱንም አውቶሚክ ቦንብ በሆነው ጦማሬ በስሱ ስሸነቁጥ ሕዝቡ ከእኔ በላይ ነው መረጃ መዘርገፍ የጀመረው። እኔ ጠላትን እንዲህ ነው አመንምኜ የማሾቀው። በአንደዜ አልላተምም፣ ጦርነት ተጀምሯል ብዬ ካርታ ሙሉ ጥይቴን አልጨርስም። እየቆጠብኩ ነው የምተኩሰው።

"…አሁን ስኳድ ሲሰድበኝ ምላሽ የሚሰጠው ጎንደሬ ነው። ጎንደሬ የእኔ ወዳጅ። እኔ ለጎንደር የሠራሁትን ያህል ስኳድ አልሠራም። ዋልድባ ዳልሽሃ ኪዳነ ምህረት ገዳምን ያለማኋት እኔ የሀረርጌው ቆቱ ዘመዴ ነኝ። ለወላድባ አብረንታት 23 ሚልየን ብር ለምኜ ገቢ ያደረግኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። ለጎንደር መድኃኔዓለም፣ ለጎንደሮች ዳቦ ቤት አልቅሼ ለምኜ የከፈትኩት እኔ ዘመዴ ነኝ። ከፈለግክ የኔታ እዝራን ጠይቅ። ደቡብ ጎንደር ዙርአምባ አቡነ አረጋዊን ያለማሁት እኔ ዘመዴ ነኝ። ፎገራ ደብረ ጓንጉት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ያሳነፅኩ እኔ ዘመዴ ነኝ። ጣና ቂርቆስ፣ ማንዳባ፣ ጎርጎራ ማርያም ብትሄድ አሻራዬ ጉብ ብሎ ነው የምታየው። የጎንደርንና የትግራይን ያህል በወሎና በጎጃም፣ በሸዋ አሻራዬ ያረፈበት ሌላ ስፍራ የለም። የማንም የጠንቋይ ልጅ ጀዝባ ስኳዳም ሁላ በጎንደር ጉዳይ ከፊቴ ሊቆም አይችልም። አጥብቀህ ስትይዘው ትግሬ ሲያይ ዐማራ ለማኝ ነው እያለ፣ ዐማራ ሲያይ ትግሬ ቆማል እያለ አንዴ ትግሬ አንዴ ዐማራ ሆኖ ጎንደርን ከመላው ዐማራ ለማቆራረጥ ሲዳክር ከሚውለው ሰገጤ ወልቃይትን ጥገት ላሙ ካደረገ ነውረኛ እስኳድ ጋርማ እንዳታመሳስለኝ። በጭራሽ እንዳታስበው። ስኳዳም፣ የጎንደርን አጥንቷን አስቀርቶ ሲግጥ የከረመ የቀን ጅብ ሁላ እኔ ዘመዴ ለምኜ የገነባኋትን ጎንደርን ሲያዋርዳትማ ቆሜ አላይም። ደግሞ እኔ እኮ የሀረርጌ ቆቱ ሆኜ በጎንደር ጉዳይ ብጎርር፣ ብበጠረቅ ያምርብኛል። ይኸው ሚልዮኖች ፊት ቆሜ በኩራት ደረቴን ነፍቼ ነው የምመሰክረው። ወንድ የሆንክ ሆዳም ስኳድ ናና ተቃወመኝ እስኪ። ሰገጤ ሁላ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …በል እንግዲህ በሦተኛው ቀን ስትነሳ እንይህ ብለው በሰይፍ ቀልተው እሱም ሳይነሣ፣ ደሙ በከንቱ ፈስሶ የቀረውን ሰውዬ ታሪክ ይነግረናል። መምህር ግርማና፣ ቅባቅዱስ በአፍንጫ ሄኖኬ እኮ ተከታዮቻቸው ነፍ ናቸው። ሄኖክ አሁን የት ነው ያለው? ስንዱ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ ሥራዋን እየሠራች ሄኖክ እንግሊዝ ምን እየሠራ ነው? አሁን ገልቱ ሞኝ ደናቁርት ተከታዮቹ ፀበል እያጠመቀ፣ በፈረንጅ ሀገር ትብታብ፣ ዛር፣ ቡዳ አይነ ጥላ እያወጣ ይመስላቸዋል። ጅል ሁላ። እናም ከአንተ የሚጠበቀው ወለላይቱ ማርያም እያልክ ይሄን ወለላ መንጋ ዩሮ፣ ዶላርና ፓውድ ማጠብ ነው።

"…እስክንድር ነጋ በየወሩ አንድ ፓርቲ የሚመሠርተው በነፃ ፈቃዱ ተጠቅሞ ነው። ለሚመሰርተው ፓርቲም ተከታይ ሰው እስካላጣ ድረስ ደንታው አይደለም። ነፃ ፈቃድ የሚባል ነገር ስላለ ደግሞ ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ለእስክንድር የሚገረዱ ሰዎች አይጠፉም። የምትመሠርተው ፓርቲም ይሁን ሃይማኖት ገንዘብና ሰባኪ ካለው ገንዘቡ እስኪያልቅና ሰባኪም እስክታጣ ድረስ በጥሩ ሁኔታ ይዘልቃል። መንደር ውስጥ ያለ ጠንቋይ ተከታይ ካፈራ፣ በሁላችን ግንበኝነት የተገነባ መልካም ስም ያለው ስመ ጥሩው እስክንድር ነጋማ እንዴት አይከብር አይከበር? የቀደመ የእስርቤት ስሙን በመጠቀም፣ በመታሰር ብቻ የጀገነን፣ የገነነ ሰው በዚያ ላይ በባልደራስና በግንባሩ ስም የሰበሰበውን ሚልዮን ዶላር ይዞ ማኅበርተኛ፣ ተከታይ፣ ሰባኪ ጭምር ቢያጣ ነበር የሚገርመው። እንደ መምህር ሀብታሙ አያሌው፣ እንደ ጭንብሴ ጄሪ፣ እንደ ብሩክ ይባስ (አቤት የብሩኬን ስም ስጠራ አፌን እንዴት እንደሚመረኝ። ምን ላድርግ ቡሩኬ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ሆንክብኝ) እንደ አርቲስት ሽመልስ አበራና፣ እንደ እስክስ አበበ በለው ያሉ ዳንኪረኛ ይዞማ እንዴት አይከብር። የሳታላይት ቴሌቭዥን ዲስኩር ጨምሩበት። እናም እስክንድር ገንዘብም ሰባኪም ስላለው ለጊዜው እንዘጭ፣ እንዘጭ ማለት ይችላል። ችግሩ ገንዘቡ ያለቀ ቀን ነው ጉድ የሚፈላው።

"…ወተቴ ማሬ የፈረንጅ ላሟ ወልቃይትን የሚመራው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከእስክንድር እና ከእስኳዱ ጋር ነው የሚሠራው። የአሜሪካው ዶላር ለእስክንድር ሲቋረጥበት መረጃዎች የሚጠቁሙት የወልቃይት መሬት የሰሊጥ ሽያጭ ለእስክንድር ቡድን እንዲደርሰው መወሰኑ ነው የሚሰማው። የጌታ አስራደ ወልቃይት መክረምም አንደኛው ተልእኮ ለዚሁ ነው ተብሏል። ሁለት ባንኮችም በዚህ የእስክንድር በጥባጭ ፀረ የዐማራ ፋኖዎች ውስጥ ለእስክንድር አካላት ስንቅ እንዲያቀርቡ መደረጉም ነው የሚነገረው። እነ አቶ መላኩ አለበልም በዚህ ፈንድ ማሰባሰብ ውስጥ ንቁ ተሳታፊም ናቸው የሚሉ አሉ። እስኳዱ ቀደም ሲል ሀብታሙ አያሌውን አሁን በመጽሐፍ ጭምር መሠረተ ኦሮሞ መሆኑን የኦቦ አፍራሳ የልጅ ልጅ መሆኑን እስኪያውጅ ድረስ በወሎዬነት በአሳምነው ጽጌ የትውልድ ሀገርነት ፈርጀው ጎጃሜነትም አለው በማለት ከዘመነ ካሤም ጋር እንደማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ሲማማል ስለሚያዩት "ቀበቶ ሻጭ" የሚል ስም አውጥተው ይሞልጩት የነበረውን ሰው አሁን በእናቱ የደቡብ ጎንደር የሊሞ ከምከም ተወላጅ ነው ብለው ወደ ግሩፓቸው ያቀረቡት፣ የሳቡት የእስክንድር ነጋ ደንገጡር አገልጋይ ሆኖ ስላገኙት ስኳድ ሀብታሙን ለዐማራ ፋኖ ማፍረሻ መዶሻነት ይጠቀሙበት ይዘዋል። 360 ከዩቲዩብ ሲባረር ገንዘብ ያለው እስክንድር ነበር የገዛቸው።

"…ስኳድ ተብዬው ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ወሎ ቡድን ሟቾች ጎጃሜዎች ስለሆኑ የመርዓዊን ጭፍጨፋ የፈጸመውን መከላከያ ተብዬ የኦሮሙማ ጦር አያወግዝም። እንዲያውም ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? በወሎ፣ በሸዋ ጭፍጨፋ ሲፈጽም፣ ዐማራን ሲያርድ የሚውልን የአገዛዙን አራዊት መንካት ቀይ መስመሬን ማለፍ ነው ብሎ ነው በሙሉዓለም ገብረ መድኅን አጽፎ፣ በበለጠ ካሣ በኩል ያስነበበው። ይሄ የሰሊጥ ብር ናላውን ያደነዘዘው ሆዳም ቡድን ጎንደር ያሉ ዐማሮች መከላከያን ሲዋጉ መከላከያን መንካት የወያኔ ተላላኪነት ነው፣ ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ እንደመስጠት ነው። መከላከያን መንካት ከእኔ ጋር ያጣላችኋል ብሎ እንደ ብርሃኑ ጁላ በትግርኛ አክሰንት በአማርኛ በድፍረት እስከመናገር፣ መግለጫ እስከማውጣት የደረሰ ድፍረት ሁላ ነው ያየነው። ይሄን ቆሻሻ፣ ግማታም፣ ክርፍ ጥንባታም የበሰበሰ ፀረ ጎንደር፣ ፀረ ዐማራ የበለፀገ አካል በጊዜ መቁረጡ ላይ ካልፈጠንክ ዐማራ ሆይ የስኳድ ጥንባቱ የዐማራን ትግል ማሽተቱ፣ ለሳይነስና ለጉንፋን ማጋለጡም አይቀርም። ስኳድ ጨካኝ ነው። ስኳድ የሰፊ ድንግል መሬት ሀብት ለብቻው ተቀራምቶ የያዘ ቡድን ነው። ስኳድ የመሳሪያ ነጋዴ ነው። ስኳድ ከሻአቢያ ጋር ወዳጅ ነው። ስኳድ ኔትወርኩ ሰፊና እጁ ረጅም ነው። ስኳድ ከኤርትራ ተነሥቶ ደቡብ ሱዳን የሚዘልቅ የመሳሪያ ንግድም ላይ ተሳታፊ ነው። ስኳድ በኡጋንዳ ቢዝነስ ከፍቶ፣ ሚዲያና ጋዜጠኛ ሰብስቦ፣ በሙሉዓለም ገብረ መድኅን አቅጣጫ ሰጪነት፣ ጽሑፍ አርቃቂነት ጎንደርን ከሌላው ዐማራ ጋር በማላተም ጎንደርን ለብቻው ክልል እናደርጋለን በማለት ዐማራ ከጎንደር መውጣት አለበት ብሎ የሚደክም ፀረ ዐማራ የትግሬዋ ህወሓት እና የፖለቲካው ቅማንት የበድኑ ብአዴን ኮንዶም የሆነ ቡድን ነው።

"…እነ ሙክታሮቪች እንኳ የሱማሌውን መንገድ እንዲይዙ፣ እነ ጠበቃ አንዷለም በቆቶ ኦሮሞውን እንዲይዙ ከእስኳዱ ጋር ተመልምለው የሚሠሩ ነበሩ። ስኳድ የአሥራት ቲቪን ለትግሬው ዓምደማርያም እዝራ ሰጥተው ያስፈረሱ፣ እነ አያሌው መንበር ጎጃምን እንደሕዝብ ለማናከስ ገብተው ያፈረሱ ጨካኝ የዐማራ ሾተላዮች ናቸው። ከአንድ ጎንደሬ የጎንደር ፋኖ ይልቅ የኦሮሞውን የአንዳርጋቸው ጽጌን እህት ወልቃይት ድረስ ጋብዘው መሬት ተሰጥቷት፣ ከእነ ጋሻው መርሻ ጋር በሰሊጥ እርሻ ላይ እንድትሳተፍ ሀብት እንድታፈራ ሲያደርጉ የከረሙ ናቸው። ዶር ወንደሰን ከእስክንድር ጋር መግጠሙ ታይቶ እንዲታሰር ከተደረገ በኋላ ነው የአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ከወልቃይት የወጣችው። ተተኳሽ ጥይት ሁለት ስማቸውን ለጊዜው የማልጠቅሳቸው ሰዎችና ለባዬ ይደርሳል ብሎ ለጌታ አስራደ ከሻአቢያ 52 ሺ ፍሬ ጥይት አምጥቶ ሰጥቶ ውባንተ ጋር ሆኖ ለሀብቴ የሚያከፋፍል ሸፍጠኛ ቡድን ነው ስኳድ። እንዲህ እንደ ቀላል እንዳትመለከቱት። የጎንደር ኤሊቶች በጊዜ ካልመከራችሁ ፍዳ መከራችሁን ነው ይሄ ቡድን ይዞባችሁ የሚመጣው። አሁን ሰሞኑን ነካ ነካ ስላደረግኩት ግርር ብሎ ቢመጣም እንደ በፊቱ በጎንደር ስም መነገድ አልቻለም። የኮመንት ሳጥኑን ሁሉ ዘግቶ ነው እዬዬውን የሚያቀልጠው?

"…የኦሮሙማው የጀነራሎች የትግሬ ጀነራሎችን አባርረው ከፀረ ፋኖው ኮሎኔል ደመቀ ጋር ሆነው የወልቃይትን መሬት እንዴት እንደሚቸበችቡት ብታዩ ትደነቃላችሁ። አንድም ጎንደሬ ግን በወልቃይት ተጠቃሚ አይደለም። ጭራሽም አያቀርቡትም። የጎንደር ዐማራ ከወልቃይት መሬት ሃባ ቅንጣት ታህል አይጠቀምም። ወልቃይትን የሚግጧት ሻአቢያ፣ በግማሽ ጎናቸው ቅማንትና ትግሬ የሆኑ ሰዎች ናቸው የሚዘውሩት። ሙሉ ዐማራ የሆነ ጎንደሬ ግን በወልቃይት አካባቢ ድርሽ እንዲል አይፈቀደልተም። ወልቃይት ለጎንደር ዐማራ ላምአለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ናት። ወልቃይት ከወያኔ ጋር ችግር ገጠመው ሲባል ነው የዋሁ ጎንደሬ የአፄ ቴዎድሮስ፣ የመልኬ ጎቤ ስም እየተጠራበት፣ በጎንደር አዳራሽ የስኳዱ መሪ ኮሎኔል ደመቀ እና…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…ያመሰግን ዘንድ ይጠበቅ የነበረው 1ሺ አመስጋኝ ቁጥሩ አልፎ 1ሺ 6 መቶን አልፏል። እግዚአብሔር የምሰግን።

"…በነገራችን ላይ የእኔ የልብ ጓደኞች፣ ወዳጆች ቁጥራቸው ይሄው ነው። 300 ምናምን ሺው ታዛቢ ነው። በተለይ 1ሺዎቹን በስም ሁላ እየለየሁአቸው መምጣት ጀምሬአለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን ብለው ካልጻፉ እንኳ ከምር ምን ሆነው ይሆን ብዬ ማሰብ፣ ቅር ይለኝ ሁላ ጀምሯል። ከሥራ ቦታቸው ሁኔታ፣ ካሉበት ሓላፊነት አንጻር በእኔ ጦማር ላይ ሲጽፉ ባይታዩም በጀርባ ሆነው ስለ እኔ የሚጸልዩም ከሺ በላይ የሚሆኑ ወዳጆች እንዳሉኝም ይሰማኛል። ለማንኛውም እኔ እንቅልፍ አጥቼ የምተጋው ለእነዚህ ትጉህ አመስጋኝ ወዳጆቼ ጭምር ነው።

"…ከምስጋና በኋላ በቀጥታ የምንሄደው እንደተለመደው ወደ ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ርዕሰ አንቀጻችን ነው። መቼም ርዕሰ አንቀጼ እንደ ጠበል የምታስለፈልፈው ብዛቱ ለጉድ ነው። እናም ዛሬም ስስ አውቶሚክ ቦንብ በጀመርኩት ስኳድ ላይ በተን ላደርግ ነኝ። የነብሩን ጭራ ይዤው የለ? አዎ አልፋታውም። እመ አምላክ ምስክሬ ናት የስኳድን ኔትወርክ ሳልበጣጥሰው ራሱ ተበጣጥሶ ወድቆ እንዳይቆጨኝ ጸልዩልኝ። ማርያምን አልፋታውም። የነብሩን ጭራ ይዤዋለሁ። ገደል ሃንቁፍቱ ሳልከተው አልመለስም። አይደለም ወልቃይት፣ ሸዋ ኡጋንዳም ድረስ ዘልቄ ከስኳድ ጋር ጦርነት ነው የምገጥመው። ሙላት አድኖ ጋብዘኸኛል እንግዲህ እንሞካከራለን። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ያዋጣህ እንደሆነ እናያለን። ውባንተን አስገድለህ እንዲሁ በዋዛ የምንፋታስ ይመስልሃልን?

"…እናስ ጎደኞቼ ስኳድ ላይ ልተኩስ ነኝ። እናንተስ ተኩሱን ለመስማት፣ ሰምታችሁም የሰማችሁትን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁን?

• እደግመዋለሁ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②…ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ካለው ዐማራ ሕዝብ ጎን ቆሜ ድምጼን ካለው ዐማራ ሕዝብ ጎን ቆሜ ድምጼን

እያሰማሁ ነኝ። ዐማራው እንደ ሕዝብ ትግል ላይ ነው ያለው። እኔ እየጻፍኩ፣ እየጮህኩ ያለሁት እናንተ መርጦ አልቃሾች በምትፈሩት ርዕስ፣ መንካት በማትፈልጉት ጉዳይ ላይ ነው። በጎንደር የጎንደር ጀግኖች እየፈጸሙ ያሉትን ተጋድሎ፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ ያለውን ትንቅንቅ። ጥሎ መውደቅ፣ የጎንደሩን አረም የብልፅግና ስኳድ ሴራ፣ የግምባሩን ሾተላይነት እየጻፍኩ በብዕሬ እየታገልኩ ነው። እናም ወጉ ደርሷችሁ፣ ስለ ፍትሕ መከበር ድምፅ ለማሰማት ወኔ አግኝታችሁ የእናንተን ለሕፃን ሔቨን መጮህ አልቃወምም። ግን ራሳችሁን ቻሉ ለማለት ነው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ዐማራ ሕዝብ…!
• ሞት ለአረመኔው የብልፅግና ሥርዓት…!
• ፍትሕ በግፍ ተደፍረው ለሚገደሉ ለኢትዮጵያ ሕጻናትና ሴቶች።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዕለቱ አመስጋኞች ቁጥር እንደተለመደው 1ሺህ ሞልቶም አልፏል። ያው ሁለዜ ለዓመታት ያህል ከምስጋና በኋላ ዘወትር ሳምንቱን ሙሉ አቀርብ የነበረውን ተወዳጁን "ርዕሰ አንቀጽ" የሚለው ጦማሬን ከትናንት ቅዳሜ ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀን ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ብቻ እንደማቀርብም የዛሬ ሳምንት ሰኞ መግለፄ ይታወቃል። እናም ዛሬም እንደ ትናንቱ ቅዳሜ እንደ ነገው ሰኞ ርዕሰ አንቀጽ አይኖረንም ማለት ነው። ሆኖም ግን ለዛሬ ርዕሰ አንቀጻችንን የሚመስል ጦማር ወደ እናንተ ላቀርብላችሁ ወደድኩ።

"…ስለዚህች ሕፃን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት በተለይ የብልፅግና አባላት፣ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ አባላት ጭምር "ምነው ዘመዴ ዝም አልክ? በማለት ስለጨቀጨቁኝ ከነበርኩበት አጀንዳ ወረድ ብዬ የማውቀውንና የደረስኩበትን ላካፍላችሁ ወደድኩ።

"…ለማታው የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ዝግጅት ላይ ስለሆንኩ እረፍት ቢያስፈልገኝም። ጭቅጨቃው ስለበዛብኝ የሆነ ነገር ልተነፍስ ነው። እናስ ጎዶኞቼ አላችሁ አይደል?

• እስቲ አንድ 100 ያህል ሰው ጮክ ብሎ "አለነ ዘመዴ" ይበል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ንሳ ተቀበልማ አንተው…

ጎንደር እንዴት አለህ?
የውባንተ ወንድም የነሳሚ ሀገር
የእነ ደሬ ሀገር
ጎጃም እንዴት አለህ?
የሳሙኤል ወንድም የዘመነ ሀገር
ወሎ ገራገሩ የአሳምነው ወንድም የነምሬ ሀገር
ሸዋስ እንዴት አለህ?
የሀገር ማገሩ
የምጡቁ አእምሮ የእወቀት መንደሩ
የእነ አሥራት ወልደየስ የእነ አስግድ ሰፈር
እንዲህ የተማረ
ለዐማራ ሕዝብ ሲል የተመራመረ

• ያዝ እንግዲህ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…

እስኪ ዘራፍ ብዬ ልጀምር ግጥም
ወኔን በሚያሞቀው እጅግ በሚጥም
ሸዋ ተነስቼ ልገስግስ ጎጃም
ወሎም ተነስቼ ጎንደር ላይ ልክተም
ከሠርጉ ጠርቶኛል ፋኖ ክንዳለም

አውድማ ተጥሎ ምርቱ እየታፈሰ 
በ 4ኪሎ ሰፈር ሙሾ ተደረሰ።

ሙሾው እንዲህ ይላል…

በሸዋው ምኒልክ ካሣ የጎንደሩን
የጎጃሙን በላይ የወሎ ራስ ሚካኤልን
ከሴት የጣይቱን ስሟን እየጠራ
በነበልባል ክንዱ መጣብን ዐማራ!!

እያለ ያለቅሳል በፍርሃት ርዶ
ፋኖ የ'ርሳስ ዝናብ ሲያወርድበት ማልዶ።

"…እንዲያ ነው…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በተቀበል መሃል…!

"…ይድረስ በአራቱም የዐማራ ጠቅልይ ግዛት ውስጥ ለምትገኙ የፋኖ አባላት…ይሄን ቪድዮ በውጊያ ላይ በትግል ሜዳ ለሚገኙ ፋኖዎች አድርሱልኝ። ይድረስ የዐማራ ፋኖን ሳትቀላቀል አንተ የተለየህ ሁነህ ይምርህ ይመስል በየከተማው በየመንደሩ ለምታውደለድል ለዐማራ ወጣት። ልብ ብለህ ስማኝ ቪድዮውንም ሰብሰብ ብለህ እየው፣ ተመልከተውም።

"…በፀረ ዐማሮቹ፣ በፖለቲካው ቅማንት፣ በአገው ሸንጎና በወሎ ኅበረት፣ በአንዳንድ ማይም ዐማሮች የተሞላው የዐማራ ልዩ ኃይል ተብዬውና የሀገር መከላከያ ተብዬው የኦሮሙማ አራዊት ሠራዊት ወደ ዐማራ ክልል ከፋኖ ጋር ለመግጠም ሲገቡ፣ ፋኖን ቢያጡት በዚያ ያገኙትን የዐማራ ወጣት እንዲህ አድርገው ነው የሚበቀሉት።

"…ዐማራ ጠሉ የብልግና መንግሥት ሥርዓት በዐማራ ላይ ይፈጽም ዘንድ የሚታዘዘው በምታዩት መልክ የሚታየውን አስፀያፊ ድርጊት በመፈጸም ነው። የብልጽግና አራዊት እንዲህ አይነቱን ፀያፍ ድርጊት በትግሬ ሕዝብ ላይ ፈጽሞታል። በኦሮሞ፣ በሱማሌ፣ በደቡብ ሕዝብ ላይም ፈጽሞታል። የዐማራው ግን ይከፋል።

"…እናስ ወዳጄ ልቤ… ይሄን በዳንኤል ክብረት ፅንፍ የረገጠ፣ ጥግ በሌለው የዐማራ ጥላቻ የሰከረን የዐቢይ አሕመድ እና የብራኑ ጁላን ጦር ማርኮ መቀለብስስ ተገቢ ነው ወይ?

"…እባክዎ ለሽ ብሎ ለተኛው፣ ለዳተኛው፣ ለሰነፉ፣ ለአቃጣሪው፣ ለአስጠጪው፣ ለሾተላዩ፣ ለስኳዱ፣ ለሆዳሙ ዐማራ አሳዩልኝ። ወንድምሽ፣ ወንድምዎ፣ ልጅህ፣ ልጅሽ እንዲህ ሲደረግ ቢያዩ ቢመለከቱ ምን ይሰማዎታል? የዘራውን አዝመራ ሊያይ፣ ሊያርም፣ ሊኮተኩት የመጣን ገበሬ እንዲህ ማሰቀያት ያውም ከወታደር አይጠበቅም ነበር።

• ተበቀል ዐማራ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል አንተው…

ቀሳውስቱ ጎንደር ጳጳሱ ጎጃም ነው
ዲያቆናቱ ወሎ ተማሪው ሽዋ ነው
የዚህ ሁሉ መምህር ዐማራ ፋኖ ነው
ጨቅላውን አውርዶ ቀሚስ ሊያለብሰው ነው
ተጉዞ ተጉዞ ማረፊያው ሸገር ነው
ይዘገያል እንጂ ድሉ የፋኖ ነው።

በሮቹ ቆፍጣና ስማቸው ፋኖ ነው
አራሹም ዐማራ ሞፈሩ ጎንደር ነው
ማረሻው ወልቃይት ወገሉ ጎጃም ነው
ድግሩ ወሎ ሁኖ መርገጨው ሽዋ ነው
ቀንበሩ ዳሞት ማነቂያው ደንብያ ነው
የዘሩ መጫኛ አህያው ጁላ ነው።

ዘሪታው ዘመነ አራሹ ምሬ ነው
አራሚው ባየ አጫጁ ሳሚ ነው
ደሳለኝ ከማሪ ማንችሎት ወቂ ነው 
ሰለሞን አይዞህ ባይ ዝናቡ ከፊት ነው
ጋይንት እያጨደ መሬ እየወቃው ነው
የምርቱ መክተቻ አዲስ አበባ ነው
አትጠራጠሩ ድሉ የፋኖ ነው💪

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት።

"…እርሱን ከወለድሽ በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኑረሻልና የክርስቶስ እናቱ ተባልሽ፡፡ ድንቅ በሚያሰኝ ተዋሕዶ አማኑኤልን ወልደሸዋልና ባለመለወጥ አጸናሽ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ “ ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋን ያለመለወጥ አጸና፡፡ ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ” በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ እርሷ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል እንደምትኖር አካላዊ ቃል ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ (ሰው የኾነ አምላክ) ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል "ሃይማኖተ አበው.66፥32"፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ነገር ግን እኔ እነ ድርሳን መጡ፣ እነ ኑረዲን ወጡ ሲባል ሰፍ ብዬ አልቀበልም። እነ ድርሳን ወሎን አንድ ለማድረግ ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ተቀላቅለው አንድ ጠንካራ የወሎ ፋኖ ለመፍጠር ከሆነ እቀበላለሁ። አልያ እስክንድርና እስኳዱ ሲመቱ ከእነሱ ጋር ሆነን ከምንወድቅ ተገንጥለን ፕላን ቢ እንጠቀም ብለው ከመጡም አልፋታቸውም። እኔ አስቀድሜ ድርሳንን ሸንቆጥ ለማድረግ ስፈልግ እነ አቤ ናቸው እነ ምሬ ዘመዴ ድርሳን እኮ የዋህ ናት፣ በእውነት አሳስተዋት እንጂ ጀግና ወሎዬ ቤተ ዐምሓራ ናት። በትእግስት መጠበቅ ነው የሚሻለው እያሉኝ ነው ሸንቆጥ ሳላደርጋት የተውኳት። አሁንም ድርሳን ሌላ መሠሪ ተንኮል ይዛ ከሆነ የመጣችው አምላከ ዐምሓራ ያጋልጣታል። የንፁሐን ደም ይፋረዳታል። የሚወዷትን ወንድሞቿን ዳግም ትከዳለች ብዬ አላስብም የሆነው ሆኖ ብትከዳ ግን ያው አይማረኝ አልምራትም። ታላቁ አሳምነው ጽጌ እንዳለው አንድ ሁኑ። መድኃኒቱ አንድ መሆን ብቻ ነው። አለቀ።

"…አሁን ኡጋንዳም፣ አሜሪካም ያለውን የስኳድ ስልክና ፎቶ እለቃለሁ ብዬ ስላልኩ ነው መሰል ስኳዶች አስቀድመው ራሳቸውን መግለጥ ጀምረዋል። በኤርትራ በኩል አቋርጦ ኡጋንዳ የከተመው የስኳድ ማስተር ማይድ ተብሎ የሚነገርለት በትውልድ ዘር ትግሬ ነው ተብሎ የሚታማው፣ ከወልቃይት በቀር ስለ ሌላው የዐማራ ፋኖ ግድ የማይሰጠው፣ በፌስቡክ ገጹም ከወልቃይት በቀር ሌለላው ብዕሩ የማይታዘዝለት ስኳድ ሙሉአለም ገብረ መድኅንም በአካል ተገልጦ ለስንት ግዜ ዘግቶት የነበረውንም የፌስ ቡክ አካውንቱን ከፍቶ ሽምቅ ውጊያውን መቀላቀል እንደሚፈልግ በግልጽ ዐውጇል። ተብታባው ጆሮ ቆሮቆራሙ ሲሳይ አልታሰብም ልክ ተአምረኛ የፖለቲካ ልሂቅ የመጣ ይመስል የተደበቁት ወድሞቻችን ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል ብሎ ሲፈነድቅ አይቼው በሳቅ ነው ፍርፍር ያማረኝ። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ኡጋንዳ ያሉትን በሚዲያ ስም የተሰገሰጉትን ወንበዴ ስኳዶች ነው ማዘዝ፣ መምራት የሚችለው። ሙሉዓለም ገብረ መድኅን የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴን ማኅተም በኪሱ ይዞ እየዞረ፣ መግለጫ ለደመቀ ዘውዱ እየጻፈ ከመንበጫበጭ በቀር አሁን ምንም ማምጣት አይችልም። እርግጥ ነው እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ከሙላት አድኖ ጋር ሆነው አርበኛ ውባንተን አስበልተውታል። አሰግድ መኮንንን አስበልተውታል። ጎጃምና ወሎን ግን አልቻሉም። የጎንደር ዐማራ ራሱ ነቅቷል። ወልቃይት ገብቶ እንዳያርስ የተከለከለ የጎንደር ዐማራ እንዴት እነዚህን ጥቂት ወንበዴዎች አምኖ ይከተላል? የማይሆነውን። ጎንደር እኮ ታላቅ ሕዝብ ነው። ሙሌ ግን እንኳን ደኅና መጣህ። እኔም ዝግጁ ነኝ።

"…እኔ አሁን እዚህ ቦታ ፋኖ ድል አደረገ፣ አሸነፈ፣ ማረከ፣ አልልም። አልጽፍምም። በአሩሲ ዐማራ ታረደ፣ ተገደለም ብዬ ትንፍሽ አልልም። አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እየተመዘበረ ነው። የደብር እልቅና ለመሆን ጉቦው 1ሚልዮን ብር ገባ ምናምን ብዬም ለቄሶቻችን ጥብቅና አልቆምም። እኔ አሁን ደረጃዬን ከፍ አድርጌአለሁ። እኔ ሰንኮፍ ነቀላ ላይ ነኝ። እኔ አይነኬ፣ አይደፈሬ ምሽግ እየደረማመስኩ ለዐማራ ፋኖ ትግል ምቹ የመጫወቻ ሜዳ በመፍጠር ላይ ነኝ። ባህርዳር እንዲህ ሆነ፣ ጎንደር በዚህ ወጣ፣ በዚህ ገባም አልልም፣ የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የሸዋ፣ የላስታዎችን፣ የጎንደርን፣ የጎጃምን ድላቸውን ሌሎች የዐማራ ሚዲያዎች ይመስክሩ። እኔግን ዋናውን መርግ፣ የዐማራን እርግማን በማፍረሱ ሥራዬ ላይ እቀጥላለሁ። እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ የሐረርጌው ቆቱ መራታ፣ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ የዐማራን የመርገም ጨርቅ በጦማሬ በሥላሴ ስም ቀዳድጄ አወድመዋለሁ። ማርያምን የጣንቋይ ልጆች አያሸንፉኝም።

"…ከምር እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። በአንድ በእኔ በዘመዴ በኃጢአተኛው፣ በወራዳው፣ በጎስቋላው፣ በወንበዴው፣ ከሁሉ በማንስ በእኔ በጭንጋፉ ላይ አድሮ ያለምንም በጀት እና ጀት የዐማራን ሰንኮፍ እየነቃቀለ ነው። በሜዳ፣ በበረሃ ያሉ ፋኖዎች፣ ጠላትም ወዳጅም እንዲያነበኝ፣ እንዲሰማኝ እያደረገ ነው። ለሰማይ ለምድር እንደከበደ ሰው የሚቆጠረው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ራሱ በትህትና ራሱን ዝቅ አድርጎ "እንዳንተ ያለ አንድ ሰው መኖሩ ጥሩ ነው። መረጃ ይኑርህ እንጂ ጥፋት ከተገኘብኝ እኔንም ቢሆን አትማረኝ፣ በእኔ ጉዳይ መረጃ ሲደርስህ አስቀድመህ ከመጻፍህ በፊት ብትጠይቀኝ ለመመለስ ዝግጁ ነኝም" ብሎ እንዲጽፍልኝ ያስደረገው የድንግል ልጅ ራሱ መድኃኔዓለም ነው። እኔም መልሼ አልኩት… "እንኳን አንተን ጎምቱ ቦለጢቀኛ የአደባባዩን ሰው ይቅርና አልኩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን "እንኳን አንተን የአደባባዩን ሰው እኔ ለራሴም ቢሆን ጥፋት ሲገኝብኝ ራሴን ከማጥረግረግ አልመለስ" ይኸው ነው። ለወዳጅ ማር፣ ወተት፣ ለጠላት ሬት ስላደረገኝ አምላኬን አመሰግነዋለሁ።

• ማርያምን ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው፣ አስነቀልቲው ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍✍ "…ጌታ አስራደ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር ወልቃይት ነው የከረመው። ውብአንተ ለእነ ጌታ አስራደ ነበር ይከራከር የነበረው። የውባንተ ሞት የሚቆጨው አሁን እዚህ ጋር ነው። ተመልከቱ እነ ጌታ አስራደ፣ እነ ዶር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ ሲሳይ አልታሰብ፣ እነ ሙሉዓለም ገብረ መድኅን ጦርነቱ አልቆ በስናይፐር ተነጥሎ እንዲመታ የተደረገው ውብአንተ ከተገደለ በኋላ በቀጥታ ያደረጉት ምንድነው ያልን እንደሆነ በቀጥታ ወደ እስክንደር ዕዝ ነው የገቡት። እስክንድርን ነው መሪያችን ብለው የመረጡት። ልብ በሉ። ፍረዱም። ስለዚህ አርበኛ ውባንተ የሞተው የተገደለውም በጠላት ነው ማለት ይቻላል ወይ? እስኪ ንገሩኝ? የውባንተ አርባው እንኳ ሳይወጣ እኮ ነው እነ ኮሎኔል ታደሰ እስክንድር ነጋ መሪያችን ነው ብለው ያወጁት። ይሄ ብቻ አይደለም ቀጥሎም እኮ አርበኛ ባዬ ቆስሎ በመከራ ነው የዳነው። ቀጥሎም አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ይገደል የሚለው ይሄው ስኳድ እኮ ነው። አያችሁ የስኳድን ሰርጎ ገብንት።

"…ስኳድ ጎንደሬዎችን እንዲህ ቀርጥፎ ከበላ በኋላ በቀጥታ ያመራው ወደ ሸዋ ነው። ሸዋ ላይ አስቀድሞ የጎንደር ተወላጅ ነን ያሉ ልጆችን ልኮ በአሰግድ መኮንን በኩልም፣ በአርበኛ መከታው ማሞም በኩል የሸዋ ፋኖ አመራርነት ቦታን አስይዞ ሸዋን በእጁ የማስገባት ያህል ነበር የሠራው። አሁንም ልብ ብላችሁ ተከተሉኝ ሸዋ ላይ እነ መከታው ማሞ የሚመሩት የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ  የሻለቃ እና የብርጌድ መሪዎቹ በአብዛኛው የጎንደር ተወላጅ የሆኑ ናቸው። በስም ዝርዝር ላስቀምጥላችሁ እችላለሁ። እነዚህ የጦር መሪዎች ደግሞ ተጠሪነታቸው ለእስክንድር ነጋና ከወልቃይት በኡጋንዳ እስከ አሜሪካ ለተዘረጋው ለአደገኛው የብአዴን ስኳድ ቡድን ነው። ተመልከቱ ብቻ እጃቸው ርዝመቱን።

"…ይሄ ወልቃይቴ ስመ ጎንደሬ ስኳድ በፊት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ባለማገዝ ቀርጥፎ የበላ ብአዴናዊ አፍቃሬ ወያኔ ቡድን አሁን ደግሞ በወልቃይት የሰሊጥ ብር፣ በደቡብ ጎንደር ወያኔያዊ የብአዴን ስኳድ ቡድን ረጅም እጁን በደቡብ ጎንደሬው እስክንድር ነጋ አማካኝነት ውድና እንቁ የሸዋ ልጆችን መሪ እንዳይሆኑ ተመርጠው በሴራ እየተመቱ ነው። በሸዋ የሌለ ጭካኔ ነው ስኳድ የሸዋ ፋኖዎች ላይ እየፈጸመ ያለው። የፋኖ አለቆችን በጩቤ፣ በሳንጃ ዓይናቸውን ሁሉ ጎልጉሎ፣ አንጀታቸውን ዘርግፎም ነው እየገደለ ያለው። ጭካኔው የዐማራ አይመስልም። ማርያምን እውነቴን ነው።

"…ይሄ የስኳድ እጅ አይደለም እነ መከታው ጋር ራሱ አርበኛ አሰግድ ከሚመራው ፋኖ ውስጥ የሦስት  ብርጌድ መሪዎች ትውልደ ገንደሬዎች እንደነበሩና መጨረሻ ላይ ግጭቱ አድጎ ጦርነት ሲገጥሙ እነመከታው ውስጥ ያሉት እስኳዶችና አሰግድ ጦር ውስጥ የነበሩት እስኳዶች እንዴት እንደተናበቡ ብትመለከቱ ትደመማላችሁ። ለምሳሌ ሰኔ 23/2016 ዓም ማጄቴ በነበረው ግጭት ሰኔ 24 ለጋሽ አሰግድ ደውሎ አሰግድ የነገረውን አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን ልንገራችሁ። "የጦር መሪዎችን ስም ዝርዝር እየጠራሁ  አለ ጋሼ እነማን አብረውህ አሉ? ስለው አሁን የሸዋ ተወላጆች ብቻ ናቸው አብረውኝ ያሉት አለኝ። ከምርህ ነው? ጋሼ ስለው…ተወውማ "ዐማራ አንገቱ አንድ ነው" ብዬ ተሸወድኩ አለኝ። እኔም ይህን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ነው የሚለኝ ይሄ ወዳጄ። ከዚህ ተነሥታችሁ ሌሎች የሸዋ ፋኖዎችም በአመራርነት ቦታ ያሉትን ሰዎች ከወዲሁ ልትፈትሹ ይገባል። በተለይ ሸዋ አስቡበት። ስኳድ ሸዋ ላይ የሠራውን ሌላ ቦታ የትም አልሠራም። ሸዋን ሽባ አድርጎ ነው ነው ያስቀመጠው። ለዚህ ነው ሸዋ ደብረ ብርሃን ሊገባ መንገድ ሲጀምር መከላከያ ሲፈረጥጥ ከኋላ በጎንደር ስኳድ የሚመራው የእነ መከታው ጦር የሸዋ ልጆች ላይ ተኩስ የሚከፍተው። ደቡብ ጎንደር ያለው የወያኔ መርዝ ስኳድ አደገኛ ነው ነው የምልህ። ጎንደርን ሦስ ቦታ የከፈለ ስኳድ ሸዋን ሁለት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ ቢከፍል አትገረም ልልህ ነኝ።

"…መረጃው ውሸት ነው የሚል ካለ ወጥቶ ይሟገተኝ። እኔ ገና የቁስሉን ዳርዳር እያከኩት እንጂ አላፈረጥኩትም። ደግሞም አሁን አላፈርጠውም። ገና መዝምዤ፣ መዝምዤ ነው የማፈነዳው። አሁን ሸዋ ላይ ካሉት የፋኖ የታችኛው እርከን መሪዎች 80% በጎንደር ልጆች ነው የተያዘው። ይሄን ሴራ ሸዋ ካፈረሰው አለቀ ሁሉ ነገር አሸወይና ነው የሚሆነው። ሴራው እየተገለጠላችሁ ነው አይደል? እነ ስኳድ እያሉ ያሉት ምን መሰላችሁ በሸዋ ያሉትን የነቁ ዐማሮች በእነ አቤ ጢሞ፣ በእነመከታው እጅ ተቀርጥፈው ይበሉ። ጅሉ መከታው፣ ሞኙ አቤ ጢሞ ሸዋ ላይ ያሉትን የነቁ ዐማሮች በእኛ ሳይሳበብ፣ ሳይነቃም በልተው ከጨረሱልን መጨረሻ ላይ አያስፈልጉንም እና እኛ ራሳቸውን በልተን ነው የምንጨርሳቸው ነው ብለው የወሰኑት። ናሁሰናይ የተገደለው እኮ ናሁሰናይ በእነ ባዬ፣ በእነ ውባንተ ጦር ውስጥ ስላለ ነው። ናሁሰናይ ሲሰዋ እኮ ቀድሞ መግለጫ የሰጠው የእነ መከታው ቡድን ነው። የእነ መከታው ቡድን ደግሞ አሁን በእስክንድር ነጋ እጅ ወድቋል። በተዘዋዋሪ ስኳዱ ነው የመከታውን ጦር የሚመራው። ተመልከቱ የሰሞኑን የሸዋ ተጋድሎ ስትሰሙ ስኳድ ድባቅ ስለተመታ በሸዋ የኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ጦር ብዙ አካባቢዎችን ነፃ እያወጣ ነው። ምክንያቱም የስኳድ እጅ እየተቆረጠ ስለሆነ ነው። በደንብ ደግሞ ሳንቲምና ሚዲያ ሲያጣ ሸዋ ብቻውን ያሸንፋል።

"…አሁን ደስ የሚለው ነገር በስሙ የሚነገድበት የጎንደር ዐማራ ከምንጊዜውም በላይ ነቅቷል። ሁል ጊዜ አበበ በለው በጎንደር የሆነ ነገር ሲሠራ ሩጦ የሚጠራው የምወደው፣ የማከብረውን አርበኛ ደረጀ በላይ መሆኑ ይገርመኝ ነበር። እርቅ ሲፈጸም የሚያጣጥለው አበበ በለው ነበር። ኋላ ስጠይቅ አበበ በለው እናቱ ትግሬ፣ እሱ ደግሞ ቅማንቴ ነው ነው አሉኝ። ነው እንዴ ብዬ መገረም፣ መደነቄን ትቼ ልግጠመው እንጂ ብዬ ቆርጬ ተነሣሁ። አበበ በለው ከሸዋ ሁል ጊዜ የሚያቀርበው የመከታውን ጦር ሰዎች ነው። ቀላል ይናበቡታል እንዴ? አበበ በለው ከሀብታሙ አያሌው ጋር ሆኖ መረጃ ቲቪን በጥበብ ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ መረጃ ቲቪ በጊዜ ነቅቶ መንግሎ ነው የጣለው። አበበ በለው አሁን ገንዘብም፣ ተመልካችም ሲያጣ ሁል ጊዜ ወጥቶ የሚለፈልፈው "መረጃ ቲቪ በአስቸኳይ ዘመድኩን በቀለን ከቴሌቭዥን ላይ ያውርድ" እያለ ነው። እኔን ማውረድ ብቻ ሳይሆን ዘመድኩን መረጃ ቲቪ ላይ ከቆየ "ኡጋንዳ ሆነው ሙሉዓለም ገብረ መድህን እየጻፈ የሚሰጣቸውን መግለጫ የሚያነቡት የስኳድ አባላትም ይጎዳሉ ነው የሚለው። ተመልከቱ እስኳድ ሰንኮፉ ሲነቃነቅ።

"…አሁን ጎንደርና ሸዋ እንዳይጋጭ በጥንቃቄ መጓዝ አስፈላጊ ነው። ሾተላዮቹ ቢጨመቁ 30 አይሞሉም። እነዚህን አረሞች በጥበብ ከስንዴ ምርቱ ጎንደርና ሸዋ መሃል ነቅሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ ናቸው በአንድነታቸው እንዲቀጥሉ ማድረግ ይገባል። በዚህ በኩል የሁለቱም ምሑራን ጨክናችሁ ምከሩ። ሸዋን በሸዋ ምድር በሸዋ ልጆች በዘዴ እያስወገዱ ያሉት የጎንደር ስኳዶች ሸዋን ለቅቀው በጊዜ ቢወጡ መልካም ነው። ይሄ ሰሊጣም ወልቃይትን ጋጭ የብአዴን ህወሓት ብልፅግና ስኳድ ዘመነ ካሤን በመጥላት ስም ጎጃም ላይ እንደ አበደ ውሻ ለሃጩን የሚያዝረከርከውም እኮ ወደ ጎጃም እንደ ሸዋ ሰተት ብሎ መግቢያ መስመርና ቀዳዳም ስላጣ እኮ ነው። በኮሎኔል ደመቀ…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… ርዕሰ አንቀጹን ለመጻፍ የዘገየሁት ጎጃም ሄጄ የተዘጋውን መንገድና ተጋድሎ፣ ጎንደርም ዘልቄ ትንቅንቁን፣ ሸዋም ሔጄ ነፃ የወጡ መሬቶችን ስቆጥር፣ ወሎ ሄጄ የእነ እስክንድር ነጋንና እስኳድ ዶር ምስጋናውን የህልም ዣት የሆነው አዲሱ ፌስታሌ ድርጅታቸው ተቀድዶ ሹመት የተሰጣቸው በሙሉ "ወራጅ አለ" በማለት ተንጠባጥበው ሲፈርሱ እያየሁ ስለነበር ነው።

• ፋኖ ድርሳን ብርሃኔ
• ፈኖ ሲሳይ ሳተናው
• ፋኖ እስራኤል እሸቴ ከእስክንድ ከኩርቱው ተንጠባጥበው መውጣታቸው ታይቷል።

"…በዚያው በወሎ በወዳጄ በእነኑረዲን አማካኝነት በእስክንድር ነጋ ስም ተቋቁሞ የነበረው እስክንድር ነጋ ክፍለጦር መፍረሱንና አዲስ ክፍለጦር ማቋቋማቸው ተሰምቷል።

"…አሁን ከእስክንድር ጋር የቀሩት በአሜሪካ መንግሥት የተያዘው ዶላር ሲለቀቅ የድርሻችንን እናገኛለን ብለው ዶላር ተስፋ አድርገው ጎንደር አንድ ሆኖ እንዳይታገል በእስክንድር መሃላ ተጠፍረው ለጎንደር ዐማራ ትግል እንቅፋት የሆኑት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በበላይ ጠባቂነት የሚመሩት የሀብቴ ጦር፣ እንዲሁም የወልቃይት የሰሊጥ ብር እና እነ ስኳድ የሚመሩት የጌታ አስራደ የደቡብ ጎንደሩ የፋፍዴን ጦር፣ ከወሎ ሸሽቶ ጋይንት የገባው ኮሎኔል ሙሀባው፣ ሠራዊቱ እየከዳው፣ የሸዋ ሕዝብ አንቅሮ እየተፋው የመጣው የመከታው ሚሊሻ ብቻ ናቸው። እነሱም የሕዝብ ጫና ሲበረታ ወደ ቀልባቸው ይመለሳሉ።

"…በነገራችን ላይ እነ ድርሳን፣ እነ ፋኖ እስራኤል፣ እነ ሲሳይ ሳተናው ከእስክንድር ስር ወጥተው ሌላ ዕዝ ከመሰረቱ መጠርጠር ነው። አስቀድሜ የሰማሁት ነገር ስላለ መጠርጠር ደግ ነው። ብዙ ጊዜ ፋኖ ድርሳን ላይ ተግሳጽ ልጽፍ መረጃ ሳሰባስብ እነ ምሬ፣ እነ አቤ ግዴለም ዘመዴ "ድርሳንን እንታገሳት" ስለሚሉኝ ተንፍሼባት አላውቅም።

• ርዕሰ አንቀጽ ልለጥፍ ነኝ። አላችሁ አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ አርብ።

"…ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን። በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን "ፊል.3፥10-11። ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ "ሉቃ 1፥28።" ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሻልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰው (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል ዮሐ.6፥37፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርዕሰ አንቀጻችንን 20 ሺ ሰው አንብቦት 25 ሰው ብው 😡 ብሎ መበሳጨቱን እያየሁ ነው። ቀጥሎ በቀጥታ የምንሄደው በርዕሰ አንቀጹ ላይ በጨዋ ደንብ ሓሳብ ወደ መስጠቱ ነው።

"…የእኔ ቤት ያው የታወቀ ነው። አግድም አደግ፣ አምቡሌያም፣ ስድአደግ ባለጌ እንደ ሌሎች ፔጆች ዘው ብሎ ገብቶ አፉን መክፈት አይችልም። የእኔ ቤት የአስተያየት መስጫ ሰንዱቅ ለሁሉም ክፍት ነው። ክልከላ የለበትም። ሙግትም፣ ተቃውሞም ይስተናገዳል። ታዲያ ሁሉ ነገር በጨዋ ደንብ ነው። አልያ ያስቀስፋል።

"…እኔንም ይሁን ሌላ ሰው ነውር በምንለው በባህላችን ፀያፍ በሆነ ስድብ መሳደብ አይቻልም። እሱም ያስቀስፋል። ለእኔም ሆነ ለሌላ ሰው አግዛችሁ፣ እናንተም መልሳችሁ ሌላ ሰው በገፄ ላይ ብትሳደቡ ያ የመጀመሪያው ተሳዳቢ የገጠመው ዕጣ ፈንታ ነው የሚገጥማችሁ፣ የሚደርስባችሁም። ማንም ይሁን ማን ፀያፍ ቃል ከአፉ በፔጄ ላይ የሚያወጣ ይቀሰፋል። ለእኔ አግዞ ስለተሳደበልኝ አልሸልመውም።

"…ባለጌ ስታዩ ጠቁሙኝ። ዘመዴ 👈…👉🏿 Block ብላችሁ መጠቆም ብቻ ነው። በፆም ምን አፍ አካፈታችሁ። ከዚያ እኔ ወገብ ዛላ መቁረጫ የብሎክ ሰይፌን ይዤ እመጣና እቀስፈዋለሁ። ይኸው ነው።

"…በሉ ስለ እስኳድ ደፈር ብለን መነጋገር እንጀምር። ጎንደርን እንደ ሕዝብ በእስኳድ ስም የሚናገር ካለ እቀስፈዋለሁ። ስኳድን ብቻ ለይተህ ተች። አጋልጥ። ሞግት።

"1…2…3… ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ከላይኛው የቀጠለ… ✍✍✍ …አሸተ ደምለው ሕዝብ ሰብስበው ወልቃይት ከተያዘ በቃ አለቀልህ። ዐማራ የሚባል ይጠፋል፣ ጎንደር ያበቃለታል። የአባ አመሀ ኢየሱስ ትንቢት ይፈጸማል ብለው ቀስቅሰው ለሞት የሚማግዱት። በወልቃይት ጉዳይ ጎንደሬ ዐማራ የሚፈለገው እንዲሞት ብቻ ነው። አዎ ሞት ብቻ ነው ለጎንደር ዐማራ የሚፈቀድለት።

"…እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለወልቃይት የስኳር ፋብሪካ መሥሪያ ነው ተብሎ የመጣን ብረታ ብረት፣ ጄኔሬተር ሁላ አውጥተው ነው የሸጡት። ኮሎኔል ደመቀ ጎንደር ከተማ እኔ ነኝ ያለ የራሱን ህንፃ እየሠራ ነው ያለው። ዐመዳም የትግሬ ወታደር እያለ ያላመጣውን ሀብት ከየት አምጥቶ ነው አሁን ህንፃ ፎቅ በዐማራ ምድር፣ ፋኖን እየሰደበ፣ እያሳደደ የሚገነባው? አዎ ከየት አምጥቶ ያልከኝ እንደሆነ ወልቃይት የተባለ ዐማራ ሞቶ ያስከበረው የዐማራን ርስት የግሉ የነዳጅ ጉድጓድን የሚያስንቅ ሀብት ስላደረገው ነው። በወልቃይት ጉዳይ ደቡብ ጎንደሮች ተለይተን ነው የተገደልነው የሚሉ አልቃሾች በሟች ብአዴኖች ሰበብ በጎጥ ተደራጅተው በማኅበር ነው የሚግጡት ወልቃይትን። የመሳሪያ፣ የሰሊጥ ንግድ ነፍ ነው። ገቢ ዘጭ ነው። ወልቃይቴ እንጂ ጎንደሬ መባልንም አይፈልጉም። እንደ ድሬደዋ ራስገዝ እንድትሆን ነው የሚፈልጉት። የጎንደር ዐማራን አጥፍተው በፖለቲካው ቅማንት ነው መተካት የሚፈልጉት። አዎ ደመቀ ዘውዱ ሽፍታ ከሀዲ ፀረ ፋኖ ፀረ ዐማራ ነው። ደመቀ ዘውዱና ካቢኔው ከገዳዩ መከላከያ እኩል መወቀጥ ያለበት አደገኛ ፀረ ዐማራ የተቀበረ ፈንጂ ነው። አባቱ ትግሬ ነኝ እያሉ እሱ ዐማራ ነኝ የሚለው ለምን ይመስልሃል? ተንጫጫ፣ እበድ፣ ስኳድ ፀረ ዐማራ ሁላ።

"…ራያ ሲወረር ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? ስኳዱስ ምን አለ? ምንም። ስለ ሸዋ ደራ ኮሎኔል ደመቀ ምን አለ? ስኳዱስ ምን አለ? ምንም ምንም አላሉም። በመተከል ለሚጨፈጨፈው ዐማራ ስኳዱ ምን አለ? ኮሎኔሉስ ምን አለ? ምንም ምንም አላለም። አሁን በዐማራ ምድር ይሄ ሁሉ ዐማራ ሲረግፍ ስኳዱና ግማሽ ትግሬው የብልጽግና የወልቃይት ተወካይ ደመቀ ዘውዱ ምን አለ? ፋኖ መከላከያ ላይ መተኮስ የለበትም ነው ያለው። ደመቀ ዘውዱ ከራያ፣ ከመተከል፣ ከደራ አስመላሽ ኮሚቴ ጋር ተባብራችሁ ሥሩ ሲባል ምንድነው ያለው? አይ እኛ ከኦህዴድ መጣላት አንፈልግም። ሁሉም በራሱ ይንቀሳቀስ። ወልቃይት ሲነካ ብቻ ግን ሁሉም ለእኛ ይሙት ነው ያለው። ደመቀ ዘውዱ ስለ ጄነራል አሳምነው ጽጌ ምንድነው ያለው ትክክል አላደረገም፣ አጥብቄ ነው የምቃወመው ነው ያለው። እናም ይሄ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ፋኖ ስብስብ አደብ መግዛት አለበት። ወልቃይት ሲነካ ግርር ብሎ መጥቶ፣ ሚዲያውን ሙልት አድርጎ ዋይዋይ የሚለው አጭቤ ቡድን ልሣኑ መዘጋት አለበት። ወልቃይት የሚወረር ሲመስለው ዐማራ አለቀለት፣ ዐማራ ሊጠፋ ነው፣ ዐማራ ጉዱ ፈላ፣ የደብረ ማርቆስ፣ የጎጃም ዐማራ ተነሥ፣ ናና ሙትልኝ፣ ተቀበርልኝ፣ ተሰዋልኝ። ወሎዬዎች ኑና ሙቱ፣ ዐማራ ተጠቃ፣ ሸዋ ዝም አትበል፣ ወልቃይትን ትግሬ ከወሰደው የዐማራ አንገት ተቆረጠ፣ ዋይዋይ፣ ቀይመስመራችን ተደፈረ የሚልን ራስወዳድ ፀረ ዐማራ ቡድን በጊዜ ሃይ መባል አለበት። ጋሽ መሳፍንት በሰፈሩ ከመከላከያ ጋር ሲጣላ እስኳድ ወጥቶ ጎጃሞች መንገድ ዝጉልኝ እንጂ ይላል። ሰው ላኩልኝ፣ አግዙኝም ይላል። ጎጃም መከራው ውስጥ ሲገባ ግን ስኳድ ድምጹም አይሰማም። ጎጃም ጎንደር ተሻግሮ ሲያግዝ ስኳድ ጎጃምና ጎንደር እንዳይገናኝ ድልድዩን ይሠብራል።

"…እደግመዋለሁ የትኛውም የጥፋትም ይሁን የልማት ማኅበር አንተ መስርተው እንጂ ገንዘብና ሰባኪ ካለህ ተከታይ አታጣም። በተለይ ገንዘብና መሳሪያ ካለህ ተከታይህ ነፍ ነው የትየለሌም ነው የሚሆነው። ባህርዳር ላይ የእኛ ወዳጅ፣ የአገልጋዮች እንግዳ ተቀባይ፣ እነ አበበ እና ሌሎች ጎጃሜዎች "ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብለው መፈክር ይዘው ወጥተው በአግአዚ ጥይት ሞተው ስኳድ የጎጃሜውን አበበን ባነር እየለጠፈ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ሲሳደብ ይውላል። ሌላው ቢቀር እቤተሰባቸውን እንኳ የጠቀመው ነገር የለም። በወልቃይት የተጠቀሙት ጎንደሬዎች እንኳ አይደሉም። በወልቃይት ጉዳይ በቃሊቲ በስብሶ ከተፈታ በኋላ እንደገና ተገድሎ ሚስቱ ይኸው ራበኝ ብላ ለእኔ ነው ቪድዮ ሠርታ የምትልከው። ስኳድ ጨካኝ ነው። የስኳዱ መሪዎች ግማሽ ቅማንት እና ግማሽ ትግሬ መሆናቸው ደግሞ ችግሩን ያብሰዋል። ያጎላዋልም። አሁን እስኳድ የሰሊጥ ብር ይዞ እስክንድርንና መከታውን ቼ ፈረሴ ብሎ እየጋለበም ነው። የመከታው ልጆች ሰሞኑን እነ አዶናይ "እናትዋ ጎንደር፣ እህልዋ ጎንደር" ብለው ፌስቡክ ላይ መለጠፍ የጀመሩት እጀ ረጅሙ የስኳድ የሰሊጥ ብር ሸዋ ገብቶ በእስክንድር በኩል ሸዋ ቀድሞ 4ኪሎ እንዳይገባ አንቆ ስለያዘላቸው ነው። አብዛኛው የመከታው ጦር አዛዦች ትውልደ ጎንደሬዎች መሆናቸውን ስታይ ትጠረጥራለህ። አንድ ላይ መታገሉ ችግር ባይኖረውም ሸዋ ተቀምጦ አሰግድ ይገደል የሚል ጎንደሬ የጦር መሪ ስታይ መጠርጠር ግድ ነው።

"…ተመልከት ጎንደር በውኃ ጥም እየተቃጠለ እስኳድ ሥልጣኑን በእጁ ይዞ እየታየ፣ ሀብቱ በእጁ መሆኑ እየታየም ለጎንደር ሕዝብ ደንታ አይሰጠውም። በዓመት አንድ ጊዜ ጎንደር ለጥምቀት እያለ ሄዶ አረቄውን፣ አምቡላውን፣ ዳሽን ቢራውን እየተጋተ፣ ጮማ ቆርጦ፣ በቢራ እና በውስኪ ታጥቦ፣ ደሀ የጎንደር ዐማራ ምስኪን ሴቶችን አማግጦ፣ አነውሮ፣ በየ አዝማሪው ቤት የሰሊጥ ብር፣ የግፍ ብር ለአዝማሪና ለሸርሙ* በትኖ፣ የካህናቱን፣ የቅዱሳኑን ሀገር በዝሙት፣ በግልሙትና አርክሶ፣ አውራ ጎዳና ላይ እናትዋ ጎንደር፣ እህልዋ ጎንደር እያለ ጨፍሮ፣ ተዝረክርኮ ነው የሚመለሰው። አዎ ጎጃምን ከጎንደር ለማጣላት፣ ሕዝብን ከሕዝብ ለማፋጀት፣ ፕላን አውጥቶ ነው የሚለያየው። ስኳድ ቁጥሩ ትንሽ ነገር ግን እጁ ረጅም የሆነ ድንጉጥ፣ አቅመቢስ ስብስብ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ ጆሮውን ቆንጥጦ የሚያዘው፣ ሻአቢያ ቁጭ ብድግ የሚያደርገው፣ አቢይ አሕመድ በየአይነት አቅርቦ በሆዱ የሚያንበረክከው ሆዳም ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ ስብስብ ነው። ለጎንደርም፣ ለጎንደሬም ጠብ ያለ ነገር የማያመጣ ስብስብ ነው። ከደቡብ ጎንደር ለሄደው ለጋሻው መርሻ የመሬት ባለቤት፣ ባላባት ያደረገው ስኳድ ለወልቃይት ደማቸውን ካፈሰሱ፣ አንድያ ነፍሳቸውን ለሰጡ የጎንደር ዐማራ ፋኖዎች ግን ወፍ የለም። አሁን እስኳድ ሲቀጠቀጥ ጎንደር ተነካ ማለት አይሠራም። እኔ ለጎንደር ዐማራ መስሎኝ ጥብቅና ቆሜ ሽንጤን ይዤ የምሟገተው? ሃኣ?

"…ውባንተን የገደለው ይሄ ስኳድ የተባለ ሾተላይ ቡድን ነው። ለአቶ መሳፍንት ብር ሰጥቶ ውባንተ ፋፍዴን ነው ብሎ፣ ውባንተ ብአዴን ነው ብሎ፣ ሻለቃ ዳዊት፣ ሀብታሙ አያሌው እስክንድር ስር እንደነ ሀብቴ ካልገባህ ብለው፣ ሰድበው፣ አዋርደው፣ ጦርነት ካለቀ በኋላ በስናይፐር ያስደፋው ይሄ ስኳድ የተባለ ቡድን ነው። ልብ በሉ ውብአንተን እስኳድ ያስባለው እነ ጌታ አስራደ፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ ኢያሱ ፋፍዴን ናቸው፣ ለምን እነሱን አንተ ጋር አስጠጋህ ተብሎ ነው። ዛሬስ ውብአንተን ካስገደሉት በኋላ እነ…③ 👇ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…እኔ ዘመዴ ዛሬ ድንገት ብድግ ብዬ ተነሥቼ አዲስ ሃይማኖት መሥርቻለሁ እና ተከተሉኝ ብዬ ባውጅ በአንደዜ ሚልዮን ተከታይ አላፍራ አላግኝ እንጂ ቀስ በቀስ እየዋለ እያደረ የሚበዛ አሜን ብሎም የሚከተለኝ ሰው ግን አላጣም። ሃይማኖት ብቻ አይደለም፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የውይይት፣ የምክክር ማኅበር፣ የሌብነት፣ የዝርፊያ፣ የቅሚያ ማኅበር፣ የቢዝነስ ድርጅት ብመሠርት ተከታይ ማኅበርተኛም አላጣም። ጠንቋይ፣ አስማተኛ ነኝ ብዬ ስር እየማስኩ፣ ቅጠል እየበጠስኩ እፈውሳለሁ ብዬ ባውጅም እንዲሁ ተከታይ፣ አድናቂ እና አምላኪም አላጣም። እንዲያውም ስለ እኔ ሌት ተቀን የሚሰብኩ ደቀ መዛሙርትም ሁላ ላፈራ እችላለሁ። ተከታይ የማገኘው እኔ ጎበዝ፣ ቆንጆ፣ ውብ፣ አንደበተ ርቱዕ ስለሆንኩ፣ ባለፀጋ፣ ሀብታም ዲታም ስለሆንኩ አይደለም። ሰዎች ስንባል ነፃ ፈቃድ ከፈጣሪ የተሰጠን ስለሆነ በዚያ ነፃ ፈቃዳችን ነጻነታችን ተጠቅመን የፈለግነውን፣ የፈቀድነውን የማመን፣ የመከተል ተፈጥሮአዊ መብት ስላለን ነው። እንደየሀገራቱ መንግሥታት ሕግ በሕግ የተከለከለ ነገር ካልሆነ በቀር የሆነ ነገር መስርቶ ተከታይ ማፍራት እጅግ ሲበዛ ቀላል ነው። እግዚአብሔር እንደሁ ፍጹም ዲሞክራት አምላክ ስለሆነ እኛን አስገድዶ የሚያሳምን የሚያስመልክ አምላክ ስላልሆነ እሳትና ውኃ ያቀርብልናል የእኛ ሥራ እጃችንን ወደ ወደድነው መዘርጋት እና መንከር ብቻ ነው። አለቀ።

"…በዓለም ላይ ሀሺሽ፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ የጦር መሣሪያ የሚያዘዋውሩ፣ የሚሸጡ፣ የሚለውጡም ማኅበራትና ቡድኖች አሉ። ህጻናትን ለወሲብ ንግድ የሚያሰማሩ፣ የሚያዘዋውሩ የሚሸጡ፣ ሴቶችን ለወሲብ ንግድ የሚሸጡ፣ የሚገዙ፣ የሚያዘዋውሩም አሉ። በሲና በረሃ የሰደተኞችን ልብና ኩላሊት ያለማደንዘዣ ቀደው የሚሸጡ የተማሩ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የህክምና ዶክተሮችም አሉ። ጄነራሎች፣ ኮሎኔሎች፣ ወታደራዊ አዛዦች ሆነው በኮንትሮባንድ የከበሩ፣ የሚከብሩም ግለሰቦች አሉ። እነዚህ ሁሉ ቡድኖች ናቸው። ተከታይ፣ ሰባኪ፣ ሠራተኛም አላቸው። የሀገር፣ የታሪክ መውደም ደንታቸው ያልሆነ፣ አንድ ሚልዮን ትግሬ ቢሞት ጉዳያቸው ያይደለ፣ ዐማራ ከምድረገጽ ቢጠፋም የማይሞቃቸው የማይይበርዳቸው ነፍ ናቸው። ይሄ ሁሉ ሲሆን ከሀገር ውስጥ እስከ አውሮጳና አማሪካ እስከ ቻይናም ድረስ የተዘረጋ አደገኛ በሆነ መረብ ውስጥ ተሳትፈው የሚሠሩቱ የሰዎች ልጅ የተባሉ የመንጋ ስብስብ ናቸው።

"…በየመንደሩ ያለ ጠንቋይም እኮ ካዳሚ አለው። ገባሪም አለው። ሰባኪም፣ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛለት፣ የአፍ ማስታወቂያ የሚነግርለት አለው። አቤት እሳቸው እኮ ዐዋቂ ቢሉሽ ዐዋቂ አይምሰሉሽ፣ ለከሰረው ሱቅህ ዐዋቂ እገሌ ጋር ብትሄድ ብለው የሚሰብኩ ደላሎችም አሉ። ጠንቋዩ ሳትጠራጠር አድርግ የሚለውን ዘግናኝ አፀያፊ የወንጀል ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የአብራካቸውን ክፋይ ለአጋንንት እስከመሰዋት ድረስ የሚደርሱ አንቱ የተባሉ ሰዎች እኮ ያለምንም አስገዳጅ ሁኔታ ነው የዚህ ማኅበር አባል የሚሆኑት። ጠንቋይ ያዘዛቸውን ፈጽመው ለመክበር ሲሯሯጡ የምታዩአቸው እኮ በነፃ ፈቃዳቸው ተጠቅመው ነው። ፎጋሪ ጠንቋዮች እንዳሉ ሁሉ አጋንንቱ ሰፍሮባቸው የሚጠቀምባቸው ጠንቋዮችም አሉ። የእኔ መነሻ ነጥብ ጠንቋይም ይሁን መተተኛ የፈለገው ይሁን የቁጥር መብዛትና ማነስ እንደሁ እንጂ ተከታይ ሰው ግን አያጣም።

"…የፖለቲካ ፓርቲም እንደዚሁ ነው። የሆነ ሰውዬ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ቀን ተኝቶ በልቡ ያሰበውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ያስባል። ያን ያሰበውን ጉዳይ ደግሞ የእኔ ለሚላቸው ሰዎች ጥቅሙን ዘርዝሮ በማስረዳት የፖለቲካ ፓርቲ አብረውት እንዲመሠርቱ ይወሰውሳቸዋል። ነገርየውን የሰሙ ወዲያው እሺ ብለው የሚስማሙ የኖራሉ፣ ቆይ ነገርየውን ልመርምር ብለው የደመራውን አወዳደቅ የሚጠብቁ ይኖራሉ። የታቀደው ነገር ከተሳካ እምቢ በማለታቸው የሚቆጩ፣ ካልተሳካ ደግሞ እግዚአብሔር ነው ያወጣኝ ብለው ስለት የሚያስገቡም ይኖራሉ። እናም የሆነ ሰው ሓሳብ የሆነ ሰው ያመነጫል። ከዚያ 6 ትግሬ አንድ ጎንደሬ ዐማራ ሆነህ ደደቢት በረሀ ወርደህ ህወሓትን ትመሠርታለህ። ከዚያ 17 ዓመት በረሃ ቆይተህ፣ ሚልዮኖች ገድለህ፣ ሚልዮኖች ተገድለውብህ አንተ 6 ሚልዮን ሆነህ ትወጣለህ፣ ከዚያ 27 ዓመት ሙሉ ሀገር ትገዛለህ፣ ትበዘብዛለህ። ከዚያ ሲበቃህ ተዋርደህ ትባረራለህ። ሰማኸኝ አይደል? ሁሉ ነገር የሚጀመረው በሆነ ሰው ሓሳብ አመንጪነት ነው።

"…ጭካኔው የሚወደድለት፣ በጭካኔው የሚፈቀር ሰው አለ። ጀግንነት የሚል ቅጽል ስም ይሰጠውና ወዳጅ፣ ተከታይ በጭካኔው የሚያፈራም ሰው አለ። እንደ አቢይ አሕመድ ሚልዮን ትግሬ አርዶ በልቶ በሚልዮን ትግሬ የሚፈቀር፣ የሚወደድ፣ የሚከበርም ሰው አለ። ቦዘኔ ዱርዬን ውድድ፣ ፍቅር የሚያደርጉ ፀባየ ሸጋ፣ የተከበሩ ቤተሰቦች ፍሬ፣ መልከ መልካም ቆንጆ ሴቶች አጋጥመውኛል። ይሄ ነፃ ፈቃድ ነው። ቦዘኔው፣ ወያላው፣ ደሀው፣ ዱርዬው አስደግሞባት ነው፣ መተት ውሎባት ነው የሚሉ የምቀኛ ሰፈር መልከጥፉ ፉንጋ ሴቶች እና ወንዶች ቢኖሩም ነገርየው ግን ሰዎች በነፃ ፈቃዳቸው ተጠቅመው የሚተገብሩት ነገር ነው። ዱርዬ፣ ተደባዳቢ፣ ሰካራም፣ አጫሽ ቃሚ የሚያፈቅሩ፣ አፍቅረውም ብቻ አይቀሩም ሀገር ጉድ እያላቸው አግበተዋቸው ልጅ ወልደው አብረው የሚኖሩ አሉ። ዘወትር በባሏ በቦክስ እየተጠለዘች፣ አይኗ እየበለዘ፣ ገላጋይ ሽማግሌ ሲመጣ ምን አገባችሁ በባሌና በእኔ መካከል ብለው ኩም የሚያደርጓችሁ ነፍ ናቸው። የትየለሌ። ወዳጄ አንተ ነህ በጤናማ አእምሮ እያሰብክ ይህ እንዴት ይሄ ይሆናል? እያልክ በቅናት፣ በምቀኝነት፣ በየዋህነትም ስትብሰለሰል የምትኖረው እንጂ ነገርየው የነፃ ፈቃድና የምርጫም ጉዳይ ነው።

"…ጥሬ ሥጋ በዳጣ በላተኞች፣ የጠጪዎች ማኅበርም እንዳለ አውቃለሁ። የቃሚ በደቦ ሺሻ የሚያጨሱ ማኅበራትም እንዳሉ ሰምቻለሁ። የትኛውም ነገር በአንድ ሰው ተጠንስሶ በጥቂት በትንሽ ሰው ይጀመርና ቀበሌ ሙሉ ሊዳርስ፣ ሀገር ሙሉ ሊያካልልም ይችላል። የሰው ልጅ ሞራል ካልከለከለው በቀር ምንም ነገር ለማድረግ ነፃ ፈቃድ አለው የምንለው ለዚህ ነው። አዚህ አውሮጳ ውስጥ አለ ተብሎ የሰማሁት ደግሞ በግሩፕ በማኅበር ተሰባስበው ልቅ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት የሚፈጽሙ እንዳሉ ነው። አሁን ይሄን ጽሑፍ የሚያነብቡ አስቀዳሽ፣ ጿሚ ጸሎተኛ ምእመናን አስር ጊዜ አማትበው ሊሆን ይችላል። በማማተብ እውነታውን ግን አይቀይሩትም። ጥቂቶች የጀመሩት ቀስ በቀስ ሚልዮኖች የተቀላቀሉት ብዙ ድርጅቶችን ማንሳት ይቻላል። እርስዎ አንድ ሰው ጀምሮት አሁን ብዙ የሆናችሁበትን የሚያስታውሱት ማኅበር ወይ የሆነ ነገር እስቲ ይንገሩን። ጀማሪው ይሄኔ ሞቶ ሁላ ሊሆን ይችላል።

"…እህተ ማርያም ስንዱ የደብረ ዘይት እለት በእኩለ ጾም ፋሲካ ነው ብላ ሰንጋ አርዳ የምታባላው እኮ የሰዎችን ስብስብ ነው። እንቁጣጣሽ የሰኔ ሚካኤል ቀን ነው። መስቀል ህዳር ጽዮን ላይ ነው የሚከበረው ብላ ተነሣች ይኸው ከመቶ በላይ ሰው አምኖ ይከተላታል። ባለሀብቶችም፣ የእንግሊዝ የስለላ ድርጅትም ፈንድ ይሰጣታል አሉ። ደመቀ መኮንን ወልቃይት ላይ አስሯት እንድትፈታ ያደረጋት ብልፅግና ከእንግሊዝ በደረሰበት ጫና ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ኦሮሚያ ውስጥ እኔ ማርያም ነኝ ብላ የተነሣች ሴት በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርባ ተከታዮቿ በመያዟ ሲያለቅሱም አይቻለሁ። ጎንደር ውስጥ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ 12 ሐዋርያት ሁሉ መርጦ፣ በመጨረሻ ንጉሡ ሰምተው… 👇 ① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ

"…ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናውን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች፡፡

"…ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች። “ዘጸ 3፥ 1-3” አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኹኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ 

"…ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኀተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢኾንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል፡፡ ሰውም ቢኾን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ኾኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው።

"…ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel