"…ቻዎ ቻዎ ጥልያን… ቻዎ ቻዎ ሮማ… ጉዞ ወደ ስደት ሀገር ወደ ራየን ወንዝ ማዶ ወደ አጎት አገር ጀርመን…!
"…በጢያራው ለመብረር፣ ሮጲላውን ለመሳፈር ሰከም፣ ሰከም እያል እየመጣን ነው…!
• እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ እሑድ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር እንገናኛለን።
እህም ነው ገና…
"…እኔ ዘመዴ ምኞቴ ይህ ነበር። ዝም ብሎ በብላሽ ታርዶ ከመሞት ቢያንስ ገዳይን መክቶም ከፍ ሲልም አንክቶ መሞት።
"…እንደ እብድ የጮህኩበት፣ እንደ ውሻ ያላዘንኩበት፣ በቄስ በሼኩ፣ በዶፍተር በፍሮፌሰሩ፣ በትግሬ በኦሮሞው፣ በፎለቲካው ቅማንት በአገው ሸንጎው፣ በወሃቢ በጴንጤው ስሰደብ የከረምኩት ዐማራን እንዲህ እንዲታጠቅ፣ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ወሳኝ፣ ፈራጅ፣ ለነገዱ ሞጋች ጠበቃ እንዲሆን በመቀስቀሴ ነበር።
"…አሁን ዐማራን በብላሽ መግደል፣ ማታለል፣ ማጭበርበርም አይቻልም። እየመጣ ያለው ዐማራ በመኖርና ባለመኖር መካከል ወስን ተብሎ ምርጫ ቀርቦለት በሕይወት መኖርን ምርጫው አድርጎ በመነሣት ይሄንኑ በተግባር እያሳየ ነው ያለው።
"…ዛሬ ላይ በዐማራ ክልል ትምህርት የለም። ዝግም ነው። የሥራ እንቅስቃሴም የለም። ታዲያ ዐማራ ይሄን የመከራ ጊዜ ወደ በጎ ነገር እየቀየረው ነው። አጋጣሚውን ተጠቅሞም ከትንሽ እስከትልቅ ራሱን በወታደራዊ ሥልጠና እየገነባ ነው።💪
"…ወዳጄ አኬር ይገለበጣል። ፍቅርም እንዲሁ ይገለባበጣል። ምንአልባትም አሁን ዐማራ ክልልን በጦርነት አድቅቀን ኦሮሚያን በልማት ሰማይ ላይ እንሰቅላታለን ብለው ቆምረው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አኬር ይገለበጣል። ዐማራ ደቅቆ፣ ትግሬ ወድሞ፣ አፋር ፈርሶ፣ ኦሮሚያ ብቻውን ገነት ሊሆን አይችልም። ተፈጥርአዊም አይደለም።
"…ቢዘገይም ዐማራ በአንድ ዓመት ውስጥ የደረሰበት የትግል ደረጃ በየትኛውም ዓለም ያለ የትጥቅ ትግል የሚያደርግ ድርጅት አሳክቶት አያውቅም። ያውም አሜሪካ ሳትረዳው፣ አረቦች ሳይደጉሙት፣ አውሮጳውያን ሳይደግፉት ከዜሮ ተነሥቶ ጀግና፣ ከባዶ እጅ ተነሥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ ባለ ዙ 23 ታጣቂ የሆነ ከዐማራ በቀር ሌላ ሰምቼም፣ ዓይቼም አላውቅም።
• አዛኜን የጮህኩለት ዐማራ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።
"…ቆይ ደግሞ ሌላ ጥያቄ… ባለፈው ለታ የሆነ ቀን ላይ… ጠቅላይ አቡቹ አድማጭ ተመልካች አጨብጫቢ ሚንስቴሮችን ሰብስቦ… ሦስት ክላሽ ይዞ የብልጥግናን መንግሥት መቀየር አይቻልም አላለም ነበር እንዴ?
• እናስ ይሄ የማየው ነገር ምንድነው…?
• ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ አርብ።
"…ይዞትስ እንደመጣ ሰዱስ ቢል በቀና ነበር። ወደ ምስጢር ሄዶ አርብ አለ እንጂ። አርብ ማለት የፍጥረት መካተቻ ማለት ነው። ስድስቱን ቀን ሲፈጥር ሰንብቶ በሰባተኛው ቀን በዕለተ ቀዳሚት አልፈጠረም። "ወአእረፈ እግዚእነ እምኵሉ ዘአኀዘ ይግበር" እንዲል። አንድም መካተቻ ማለት ነው። ሰባቱን መና ሲያዘንብላቸው ሲለቅሙ ሰንብተው በስድስተኛይቱ ቀን በዕለተ ቀዳሚት አይዘንምም የቀዳሚቱን ዓርብ ደርበው ያገባሉና የመና መካተቻ ማለት ነው። አንድም የሥራ መካተቻ ማለት ነው ሠላሳ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በዚህ ዓለም የሰውነት ሥራ ሲሠራ ኖሮ በዚህ ቀን ሥራውን ፈፅሞ ዐርፏል።
"…ወአርበ ፋሲካሆሙ ለአይሁድ እንዲል። አለፈ ተከተተ ሲል ነው። በዚህ ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፣ የብርሃን ምንጣፍ ይነጸፋል፣ ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦ ፍቁርዬ ኤፍሬም ትለዋለች። እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል። ወድሰኒ ትለዋለች ክርክር በሰኞ አልቋልና ባርክኒ ይላታል። በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይህድር በላእሌከ ትለዋለች። እሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀመራል። ውዳሴ ዘአርብ ውዳሴ በአርብ ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በእለተ አርብ ይላል። ቃል ጸሐፊ ነው እሱ ግን ምስጋናዋን ቡርክት አንቲ ብሎ ይጀምራል።
"…በአዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ከፈጠረን ልጅሽ ፅንኢት በድንግልና እመቤታችን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…እጠይቃለሁ… ሁሌ ለምንድነው የትግራይ ነፃ አውጪዋ ወዩ እና የኦሮሞ ነፃ አውጪው ወነግ አክ እንቲፍስቶች እስክንድር ነጋ ለምን ይተቻል? ለምን ይነካል ብለው ጓ የሚሉት እል ነበር። በፊት በፊት ነው።
"…ሀብታሙ አያሌው ተሾመ አፍራሳን ሳይ፣ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራን ሳይ፣ በዚህ ላይ ብዙዎቹ በሚስት በኩል ትግሬና ኦሮሞ ማግባታቸውን ስመለከት፣ ዘራቸው ብቻ ሳይሆን ከቤትም ጫና ሊኖርባቸው ይችላልም ብዬ እል ነበር።
"…አርበኛ አሰግድን ሀብታሙ ሰድቦ፣ መከታው አዋክቦ ለመከላከያ አሳልፈው ከሰጡት በኋላ ማጀቴን የመከታው ማሞ ፈቄ ልጆች ተቆጣጥረው ቆይተው ነበር። እናም ዛሬ የመከታው ቡድን ለመከላከያ ማጀቴን ሁላ ለቅቆ ፈርጥጧል አሉኝ።
"…የመከታው ማጀቴን ለመከላከያ አስረክቦ መውጣት ያየው እስክንድር ነጋ ከኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባው ጋር ወደ ደቡብ ጎንደር ወደ ዶር አምሳሉ ሀገር በመሸሽ በዚያ አርበኛ ውባንተ በተሰዋበት ምድር ፋፍዴኖችን ሊቀላቀሉ ነው የሚል ጭምጭምታም ተሰምቷል። እነ ዶፍተር ምስጋናው አንዱአለም ከጎደር ዳያስጶራ ብር ለመሰብሰብ እየዳከሩ ነውም ተብሏል። ዶለር ግን ወፍ የለም።
"…አሁን ለዐማራው እጅግ ጥሩ ጊዜ ነው። ሁሉ ነገር በጊዜ መገለጡም ሸጋ ነው። ሸዋም በጊዜ ድክመቱን ከለየ በጊዜ ይጠነክራል። ጎጃም እንደሁ ከወዲሁ የብረት ግድግዳ ሆኗል። ጎንደር ተወዛግቧል። ዶላሩ እና መሃላው ወደ እስኬው አስጠግቶ ነበር። የሆነው ሆኖ እነ ፋኖ ደረጄ ይሄን ውርደት እንደ ጎንደር የሚቀበሉት አይመስለኝም። ወሎም ከወዲሁ ፈርጥሟል። እሾሁን ከመሃሉ ነቅሎ ጥሏል። የፈለገ ይሁን የደፈረሰው ነገር በጊዜ ጠርቶ ዐማራም በጥራት በኩራት ያሸንፋል።
• እኔ ዘመዴ የሚታየኝ እንዲህ ነው። ቦግ ብሎ የሚበራ የድል ችቦ ብቻ ነው የሚታየኝ። እንኳንም በጊዜ ተገለጠ።
• እስኬው ግን አይገርምላችሁም…?
አደራ፣ አደራ…አዳራ…
"…ይሄን ቪድዮ በእስክንድር ዶላር ለተንበረከኩት ለጎንደሬዎቹ ለእነ ጋሽ መሳፍንት ቡድን ለእነ ሀብቴ እና ለጎንደሬዎቹ ለፋፍዴኖቹ ቡድን ለእነ ፍሮፌሰር ጌታ አስራደ፣ ለሸዋው መከታውና ለወሎዬው ኮ/ል ፈንታሁን ሙሀባ አድርሱልኝ።
"…ዐማራ ባለመሆኑ ፋኖ ብሎ አስረግጦ መናገር የማይችለው እስኬው… ፋኖ የሚያስፈልገው ይላል…
1ኛ፦ ወያኔን ለመበተን
2ኛ፦ ጭፍጨፋውን ለማስቆም ብቻ ነው ይለናል።
"…ልብ በሉ አስታውሱም ድሮ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ ፋኖዎች ከደርግ ጋር ተዋጉና ወያኔን ከደደቢት በረሀ አውጥተው ተሸክመው 4ኪሎ አስገብተው እነሱ ተመለሱ።
"…ቀጠሉና የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ ፋኖዎች ከወያኔ ጋር ተናንቀው ሥርዓት ለወጡ፣ ዐማራ መስሏቸው ደመቀ መኮንን አንተ ምራ ሲሉት "እኔ እኮ ብአዴን ነኝ። እኛ ብአዴናውያን ስንፈጠር ለመሪነት አልተቀባንም፣ ስለዚህ ኦሮሞዎቹ ይምሩ ብሎ ሥልጣን አሳልፎ ሰጥቶ ዐማራ ባዶውን ተመለሰ።
"…እስኬ ብልጧ አሁንም ፈኖ እንደ ኩሊ፣ እንደ አጋሰስ መሆን ነው የሚያምርበት፣ ፋኖን መጠቀም ያለብን እንደ ጓንት፣ እንደ ኮንዶም ነው። ፋኖ እኛን ቤተ መንግሥት ካስገባ በኋላ እሱ ወደ ግብርናው መመለስ ነው ያለበት ነው የሚለው።
"…እሺ አረጋዊው ጎንደሬ ጋሽ መሳፍንትን፣ ሽማግሌው ኮረኔል ፈንታሁንን፣ ኡንበርስቲ ባለመበጠሳቸው ሀብቴንና መከታውን ዶላር አቅምሶ ሸወዳቸው ማለት በቃ ሌላውንም መሸወድ ይችላል ማለት ነው እንዴ?
"…አበበ በለው በእናቱ ትግሬ በአባቱ የፖለቲካ ቅማንት ነው አሉ፣ ሀብታሙ አፍራሳ፣ ብሩኬ ጉራጌ ናት፣ ጄሪ እንኳ እንጃ እነዚህን ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎጃም ኮተቶችን ይዞ ከሕዝብ በተሰበሰበ ዶላር ምኒልክ ብሎ ቲቪ ከፍቶ ዐማራን ማሞኘት ይቻላል ወይ?
•እንደ እስክንድር አባባል በእውነት ፋኖ ኮንደም ነው ወይ? ተወያዩ✍
ከዚያ…
"…በታች በመስቀል አደባባይ በኩል፣ ከፒያሳ፣ ከሜክሲኮ፣ ከሽሮሜዳና ከመገናኛ አካባቢ በሚመስል መንገድ ወደ ቤተመንግሥቱ የተመሙት የባንግላዲሽ ዜጎች ቤተ መንግሥቱ ጋር ሲደርሱ በአጥሩ ላይ እየተንጠላጠሉ ውስጥ ድረስ ገቡ።
"…ጠቅላይ ሚንስትሯም የሕዝቡን ቢገደልም ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ ብሎ ግግም ማለቱን ባየች ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የቀረበላትን ምግብ ሳትቀምስ፣ ውኃ እንኳ ሳትጠጣ ብድግ ብላ ነው ወደ ዱባይ ማነው ወደ ሕንድ የተሰደደችው። 😂
"…ሕዝቡ ቤተ መንግሥት ሲገባ ባየው ነገር ተደመመ፣ እነ ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ፣ እነ ዳኒ ክብረት፣ እነ ጫልቱ ሳኒ፣ እነ ጌቾ ረዳ፣ እነ ግርማ ብሩ፣ እነ በለጠ ሞላ፣ እነ ብራኑ ነጋን የመሰሉ ባለ ሥልጣናት ሁለዜ በነፃ የሚቀለቡትንና ቦርጭ ያወጡበትን የቤተ መንግሥት ምግብ ተደርድሮ አገኙት። አገኙትናም ገሚሱ በቁሙ፣ ገሚሶቹ ተቀምጠው ይመገቡት ጀመር። አንዳዶቹም በጠቅላይ ሚንስትሯ አልጋ ላይ ጋደም ሁላ ብለዋል።
"…ወዳጄ ይሄን የሚያደርገው በጣም የራበው፣ የጨነቀው፣ ኑሮ የከበደው ሕዝብ ነው። በሴፍቲኔት መኖርን ጌጥ ያደረገ፣ ቀበሌ ሄዶ 2ኪሎ ዱቄትና 30 ብር አበል ስለተቀበለ ለአገዘዙ አቃጣሪ የሚሆን ዜጋ በፍጹም ሊደፍረው አይችልም። ሾካካ፣ አቃጣሪ፣ አስመሳይ፣ ፈሪ፣ ሽንታም ይሄን ሊያደርግ አይችልም።
"…በአገዛዙ የተዘረፈን የነጋዴ ንብረት በርካሽ መብላት የለመደ ሕዝብ ይሄን ሊያደርግ አይችልም። የአምባገነኖችን ቀንበር የሚሰብረው የተራበ፣ ፍትሕ የተጓደለበት፣ ኑሮ፣ በደል የከበደው፣ ጭቆና ያንገሸገሸው ሕዝብ ነው። ለአስመሳይ፣ አቃጣሪ፣ አስጠቋሪ፣ አውርቶ አደር፣ በወንድሙ ሞት እሱ ኗሪ ሕዝብ አይሞክረውም።
"…የዝናሽን ዳቦ ካገኘህ ምን ትፈልጋለህ? እኔ የጻፍኩት ስለ ባንግላዴሽ ሕዝብ ነው። ስለ አንተ አልተነፈስኩም። ሚልኢላልኢሄ…
በባንግላዴሽ እንዲህ ነው የሆነው አሉኝ…
በመጀመሪያ…
"…በአገዛዙ ሹመኞች ያለቅጥ በሙስና መዘፈቅ፣ በአምባገነንነታቸው፣ ጨፍላቂና ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ ዜጎች በሕይወት ለመኖር በጣም ከበዳቸው አሉ። በየቤታቸው መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ የሚባሉት እንደ ሩዝ፣ ዘይት፣ ስኳር የመሳሰሉት ተወደው ከገበታቸው ላይ ጠፉባቸው አሉ። የቤት ኪራይ ጨመረ፣ የትራንስፖርት፣ የህክምና፣ የትምህርት ቤት ዋጋ ሰማይ ነካባቸው አሉ። እናም ወላጆች ልጄን ምን ላብላው? ምንስ ላጠጣው? እያሉ በየቤታቸው በጭንቀት በሽታ ላይ መውደቅ ጀመሩ አሉ። (እንደ ዳባት ጎንደር ራሳቸውን አንቀው የገደሉ፣ መርዝ ጠጥተው የሞቱ ስለመኖራቸው ግን አልሰማሁም።) ብቻ የወላጆቻቸውን ሰቆቃ ልጆቻቸው አዩ። ተመለከቱም አሉ።
"…ሰላማዊ ሰልፍ፣ መንግሥትን መቃወም በሚያስገድልበት ሀገር "የራባቸው ጥቂት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለምን ይሄን አምባገነን ገዳይ ዘራፊ መንግሥት በልተን አንገረስሰውም፣ እንብላውና እንቀደስ በማለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንቅስቃሴ ጀመሩ አሉ። ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው ነውና ከነተረቱ ሆድ የባሰው፣ የራበው፣ የጠማው፣ የጨነቀው ሁላ የወጣቶቹን ጥሪ ተቀብሎ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ወጣ። በቃ ወጣ።
"…ከዚያ…
• ሰዓሊ ለነ ቅድስት
"…ሰዓሊ ለነ ቅድስትን ቅዱስ ኤፍሬም አልተናገረውም። ይኸውም ሊታወቅ በሀገራቸው ከመጽሐፍ ቢፈልጉ በቃል ቢጠይቁ አይገኝም፡፡ ቅዱስ ያሬድ የዜማ መክፈያ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ እርሱም ከአፍኣ አምጥቶ ከልቡ አንቅቶ የተናገረው አይደለም። ከዚያው ከውስጥ ሰአሊ ካለው ሰአሊን ቅድስት ካለው ደግሞ ቅድስትን አምጥቶ ተናግሮታል፡፡ አንድም የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል።
"…ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በግብርናተ ዲያብሎስ ተይዞ የነበረ አዳምን ነጻ ያወጣው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ለብዎውን ሰላሙን ፍቅሩን በልቡናችን በአእምሯችን ሳይብን አሳድሪብን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
እናንተስ አልታዘባችሁምን…?
"…ዐማራው በራሱ የቤት ሥራ መጠመዱን ያየሁት ዘንድሮ ነው። ከምር ከጉብኝት መልስ እንዲህ አረፍ ስል የዐማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬና የብልጽግና ፔጆችን ዞር ዞር ብዬ በወፍበረር ለማየት እሞክራለሁ።
"…ድሮ ድሮ የዐማራ አክቲቪስቶች መንደር ብዙ ዝብርቅርቅ ያለ ጫጫታ ነበር የምመለከተው። በተለይ እንደ ኦሎምፒክ አትነቱ ዓለምአቀፍ የስፖርት ውድድር ሲመጣ ዓይኑም፣ ጆሮውም እዚያው ተክሎ ፍጥጥ ብሎ ነበር የሚከርመው።
"…ዘንድሮ ግን አባቴ ወፍ የለም። ወርቅ ቀረ ብር ቀረ፣ ነሃስ የለ ሰርተፊኬት ትንፍሽ የሚል የለም። አስተያየት ሓሳብ አይሰጥ፣ አይተች፣ አይሞቀው አይበርደው። ዝም። ጭጭ።
"…እናቴ ዐማራው መነሻዬም መድረሻዬም ዐማራ ነው ብሎ ሥራ ላይ ነው። ትግል የጀመረበትን 1ኛ ዓመት ድምቅምቅ አድርጎ እያከበረ ፌስቡኩን በትግሉ ፎቶና ቪዲዮ ጥልቅልቅ አድርገው ነው የሰነበቱት። ቪቫ ዐማራ
"…የኮሪደር ልማቱ ጀልባ ሲያስፈልገው እያየ ዐማራ አይናገር፣ አይጋገር። መምህራን ደሞዝ አጡ፣ ጤፍ 20 ሺ ገባ፣ ሕወሓትና ሕወሓት ተጣሉ፣ አቶ ገዱ ይቅርታ ጠየቀ፣ ሀብታሙ እና እስክንድር ነጋ የአሜሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጎጃም ይግባ ብለው እየዬ አሉ፣ ዶላር ጨመረ፣ ቀነሰ ዐማራው እሱ እቴ ዝም ጭጭ።
"…የዐማራ አክቲቪስቶች ገፅ ስገባ የማየው መረጃ ሲሰጡ፣ ፋኖ ሲያበረታቱ፣ ሲመክሩ፣ ሲመካከሩ ነው። ዐማራው ሌላ ደረጃ ላይ ደርሷል አባቴ ሌባውን ከደኅናው፣ አጭቤውን ከሰገጤው እየለየ ነው። ይሄ መታደል ነው። የኦሮሞ ፔጆች ለሲፈን ሲያሽቃብጡ ያውም በአማርኛ እኔ በሳቅ።
"…እናም እኔ ዘመዴ ከመደነቄ የተኗ የሮማ ጥልያን የእረፍት ቀኔ ውብ ሆኖልኛል። አሁን ዐማራን አጀንዳ ሰጥቼ አንጫጫዋለሁ አይሠራም። በዚሁ ከቀጠሉ እኔም ባለቤቶቹን ለማንቃት ብዬ እንደ እብድ ውሻ መጮሄን እቀንሳለሁ።
የአሕፋድ ድፍረት
አፋሕድ፦ ሃሎ ብፁዕ አባታችን እንደምን አሉ? ቡራኬዎት ይድረሰን። ከኢትዮጵያ ነው የምንደውለው።
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ማን ልበል?
አሕፋድ፦ እኔ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፋኖ ሻለቃ መከታው፣ እስክንድር እና ወልደ ገብርኤል ነን።
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ እሸ ምን ልታዘዝ? በደህናችሁ ነው?
አሕፋድ፦ በደህና ነው ብፁዕ አባታችን። ያው በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የዐማራ ፋኖ አንድነት ዛሬ በዲሞክራሲያዊ መንገድ፣ በድምፅ ብልጫ አሳክተናል፣ አንድ መሪም መርጠናል። እናም ይሄን የምሥራች ነግረንዎ ጸሎተ ቡራኬ እንዲሰጡንና እኛም ቡራኬዎን ለመቀበል ነው የደወልነው።
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፦ መልካም ከጎጃምም፣ ከጎንደርም፣ ከወሎና ከሸዋ ከሁሉ ተስማምታችሁ ነው አንድ የሆናችሁ?
አፋሕድ፦ አዎ ብፁዕ አባታችን። ጋዜጠኛ እስክንድርን በድምጽ ብልጫ መሪ አድርገን መርጠነዋል። አሁን የእርሶ ቡራኬ ብቻ ነው የምንፈልገው።
"…መሸ ነጋ፣ ሁለተኛም ቀን ሆነ። እኔ ዘመዴ ምርጫ እንዳልተደረገ፣ ስብሰባው ዕጩ ሆነው በቀረቡት በአርበኛ ዘመነ ካሤና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ለእጩነት ለመቅረብ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላሉ ወይስ አያሟሉም በሚለው ላይ እየተነጋገሩ እንደነበር እና ይሄንኑ ሳይግባቡ አምስቱ ረግጠው ወጥተው አራቱ እንደቀሩ፣ እነዚህ የቀሩቱ በድብቅ በውሸት መሪ እንደመረጡ የስብሰባውን የድምፅ ቅጂ በመረጃ ቴሌቭዥን ለቅቄው በእነ አፍራሳ የልጅ ልጅ ሴራ ላይ ቀዝቃዛ በረዶ ቸለስኩበት። ብፁዕ አባታችንም ዝግጅቱን አይተው ደወሉልኝ። ጉድ ጉድ ተባብለንም ተለያየን። ሌባ ሁላ አለ ዘፋኙ። ድፍረታቸው ለጉድ ነው። ጭራሽ ጳጳስ ለመሸወድ መዳፈር።
• ጎዶኞቼ እኔ ሮም ጥልያን እረፍት ላይ ነኝ። አየሩ ይሞቃል። አረፍ ስል ነው ብቅ ብዬ የምጎበኛችሁ።
• አይገርሙላችሁም ግን?
"…ድንግል ሆይ! …ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ። ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ። መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ። ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ፡፡
"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"
"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን። እንኳን ለፆመ ማርያም (ፍልሰታ) በሰላም አደረሰን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ኦቦ ቢቲኔም ሞተ አሉኝ።
"…በለንደኑ የኦሮሞ ምሁራን ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ማደሞክረስ ሳይሆን መደርመስ፣ መበታተን ነው ያለብን። ኦሮሞ ታጥቆ፣ ተዋግቶ ኢትዮጵያን መበታተን ነው ያለበት። የምትበታተን ኢትዮጵያን ስንፈጥር ብቻ ነው ኦሮሞ ሰላም የሚያገኘው፣ ኦሮሞም ነፃ የሚወጣው" ሲል የነበረው ኦቦ ቢቲኔ ኦቦ ሊበን ዋቆም ኢትዮጵያ ሳትሞት፣ ሳትበታተንም በፊት እሱ ቀድሞ ተበተነ፣ ሞተ፣ ከአፈርም በታች ተቀበረ አሉኝ።
"…እረፍት ላይ ሆኜ እኮ ነው ይሄን መርዶ የሰማሁት። የሚደንቀው ነገር ኢትዮጵያ ግን እስከአሁን አለች። ከነ ሕመሟ፣ ስቃይዋ፣ ከነ ቁስሏ አለች። እስከአሁን አልሞተችም። ወደፊትም አትሞትም። ገዳዮቿ ጆሮአቸው እየሰማ፣ አይናቸው እያየ እሷ ቆማ እነሱን እየቀበረች። ከአፈርም እየቀላቀለች፣ ወደፊት ትቀጥላለች።
"…እረፍት ላይ ብሆንም አንደዜ ልጸልይ እስቲ። አምላኬ ሆይ እባክህ ተለመነኝ፣ ደግሞ ሌላ አንድ ፀረ ኢትዮጵያ ገንድስልኝ። 🙏🙏🙏 እባክህ አምላኬ ሆይ ጸሎቴን ስማ።
"…በሰኔ 15ቱ ቀውስ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ሰበብ ለረጅም ጊዜያት ወኅኒ ቤት ቆይተው የተፈቱትና መጀመሪያ ምሥራቅ ዐማራ ፋኖን ምሬ ጋር፣ ከምሬ ተለይተው ከኮ/ል ሞገስ ጋር፣ ከኮረኔሉም ተለይተው በደቡብ ወሎ ሲንቀሳቀሱ የቆዩትና ኋላላይ ከእናት ድርጅታቸው ጋር ተዋሕደው የዐማራ ፋኖ በወሎ ም/ል ወታደራዊ አዛዥ የነበሩት ኮ/ል ፈንታሁን ሙሀቤ በዛሬው ዕለት ከድርጅቱ መባረራቸው ታውቋል።
"…ነገርየው እየለየ መጥቷል። የዐማራ ፋኖ ሀገር ይበትናል ሲል የቆየውና በእነ ዶር ምስጋናው እና ሲሳይ አልታሰብ የሚታዘዘው ተገንጣዩ የጎንደር ፋኖ ቡድን ሦስተኛ አንጃ ሆኖ ተከስቷል። እስክንድር ነጋ ጋሽ መሳፍንትን አስምሎ፣ ጋሽ መሳፍንት ፋኖ ሀብቴ ወልዴን ወክሎ ከእስኬው ጋር ከተጣበቀ ወዲህ ለዚህ ታማኝነቱ እስክንድር ለ6ተኛ ጊዜ በፈጠረው ድርጅት የራሱ የእስክንድር ምክትል አድርጎ መርጦ ጮቤ አስረግጦታል።
"…ይሄ ስኳድ የተባለ የጎንደሩ ተገንጣይ ቡድን በአባ ዶላር እስክንድርን ነጋ መሪነት ከወሎ ኮ/ል ፈንታሁንን፣ ከሸዋ መከታው ማሞን በመያዝ በእነ አበባው ታደሰ ድጋፍ ሰጪነት በጎንደር በአርበኛ ባዬና በአርበኛ ሳሙኤል ባለድል ላይ፣ በወሎ በእነ የዋርካው ምሬ ላይ፣ በሸዋ በእነ ኢንጂነር ደሳለኝም ላይ ጦርነት ይከፍታል ተብሎም ይጠበቃል።
"…ስኳድ ተብዬው ጎንደር አሰዳቢ ቡድን በእነ ዶር አምባቸው ግድያ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበር ተብሎ የነበረውን ኮ/ል ፈንታሁንን አቅፎ ተጠርጣሪ ነው በተባለው አርበኛ ዘመነ ካሤ ላይ ልቅ ዘመቻ መክፈቱም አስገምቶታል። ስኳድ በዘመነ ስም ዘመቻ የከፈተው ጎጃምና የጎጃም ሕዝብ ላይ ሲሆን መከታውንና ኮረኔሉን ይዞም ጎጃምን ጦርነት ለመግጠም ሳያስብ ሁላ አይቀርም እየተባለም ነው።
• አታስመስሉ። አትፍሩም ደፈር ብላችሁ ተነጋገሩ። ስኳድንና እስክንድርን በግላጭ ሞግቱና ተፈወሱ።
"…ውዳሴ ዘቀዳሚት፣ ውዳሴ በቀዳሚት፣ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ይላል አንድ ነው ቃለ ጸሐፊ ነው። እርሱ ግን (ቅዱስ ኤፍሬም) "ንጽሕት ወብርህት" ብሎ ያመጣል። ይጀምራል። ከአባቱ ጋር ካስታረቀን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን።
"…ቅድስት አለ። ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ሲል ነው። ንጽሕትም አለ። ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም። እርስዋ ግን ከነቢብ ከገቢር ከሐልዮ ንጽሕት ናትና። "ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ እንዲል። ጽንዕትም አለ። ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው። እርሱዋ ግን፥ ቅድመ ጸኒስ፣ ጊዜ ጸኒስ፣ ድህረ ጸኒስ፣ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናትና። ክብርትም አለ። ሌሎችን ሴቶች ብናከብራቸው ጻድቃንን ሰማዕታትን ወለዱ ብለን ነው። እርሱዋን ግን ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና። ልዩም አለ። እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የተገኘች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና።
• ዓይኑ "ዓ" ቢሆን አዕምሮውን ለብዎውን ሳይብን።
• አልፋው "አ" ቢሆን ለምኝልን ማለት ነው። "…ልመናስ ከዚያ በኋላ ስንኳን በሱዋ በሌሎችም የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ የምታስምረን ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ። ይህን ሲጨርስ ባርካው ተነስታ ታርጋለች እርሱም እጅ ነሥቶ ይቀራል ይቆየን።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…እነ አቢይ አመድ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ብራኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አረጋ ከበደ ወዘተ ይሄንንም እያዩ አሁንም ፋኖ አሞሌ ጨው ነው፣ ከክልሉ 97% ያህል አፅድተን የቀረን በኪስ ቦታ ላይ ያሉቱ ብቻ ነው። ፅንፈኛውን፣ ጃውሳውን፣ ቀማኛ፣ ዘራፊ ወዘተ ያሉትን የዐማራ ፋኖ ኃይል አጽድተነዋል፣ ቀበቶውንም አስፈትተነዋል ወዘተ ይሉ ይሆን…?
• የዐማራ ስብእናው የሚገርመኝ የጠላቱን አስከሬን ራሱ አክብሮ መቅበሩ… 👏👏👏
"…መከላከያን የምመክረው "…አባዬ ከሕዝብ ጋር ተዋግተህ ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም።"
"…ሽርሽር ላይ ሆኜ እኮ ብዙ ወሬ አምልጦኛል። ቆይ እኔምለው ሽርሽር ጥልያን ሮማ ከመሄዴ በፊት በአዲስ አበባ በብሽክሊሊት መንገድ ላይ በእግሩ የሚሄድ ሰው ብዙ ብር ይቀጣል አልተባለም ወይ…?
Читать полностью…"…እኔና ቤተሰቦቼ በጥልያን ሮማ ስናደርግ የነበረውን ቤተሰባዊ ጉብኝት ዛሬ አጠናቅቀናል። ነገ ወደ ማታ ላይ ወደ አጎት ሀገር ጀርመን ለመመለስ እንበርራለን። መቼም እንዴት ያለ ግሩም የቆይታ ጊዜ እንደነበረን በቃላት ልገልጽላችሁ አልችልም። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…በነገራችን ላይ የዶላር የምንዛሪ ዋጋ በብር ስንት ደረሰ ይሆን? ከወሬው ዓለም ስለራቅኩ በቃ ምንም ልሰማ አልቻልኩም።
"…አንድ ዶላር በሰማንያ ሁለት የኢትዮጵያ ብር መመንዘር ጀምሯል የሚባለው እውነት ነው ወይ…? በመንግሥት ሰማንያ ሁለት ብር ከሆነ በጥቁር ገባያው ስንት ደረሰ ማለት ነው?
በሉ ደኅና እደሩልኝ…
"…በጥልያን ሀገር በሮም ከተማ በዚህ ካቴድራል ውስጥ በዚህ ጠንካራ መስታወት ውስጥ ከሚታዩት ሁለቱ አንደኛው ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል ነው አሉኝ። አጭር አራት ማዕዘኗ ደግሞ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለው የክስ ጽሑፍ የተቀረጸበት ነውም አሉኝ። እዚያው ክፍል ውስጥ ክቡር ሥጋው ተጠቅልሎ ወደ መቃብር የወረደበት ጨርቅ ነው የተባለም ዋናውን ሳይሆን ቅጂውን በመስታወት አድርገው አስጎብኝተውናል።
"…ብርክክ ብዬ ዕለተ አርብን በማሰብ በዓይነ ህሊናዬ ኢየሩሳሌም ቀራንዮ አደባባይ ሄድኩኝ። ዞር ስል ሁለት ፈረንጆችም እንደኔው ብርክክ ብለው ይጸልዩ ጀመር። ለካ የበኩር ልጄ ጎረምሳው በስልኩ የካሜራ ዓይን ቀለብ አድርጎ አስቀርቶኝ ኖሯል።
"…በሉ ነገን በጥልያን ሮማ ቀሪ ቦታዎችንና የሜዲትራንያን ባህር ዳርቻዎችን ስንጎበኝ እንውልና ቅዳሜ አመሻሹን ወደ አጎት ሀገር ጀርመን በጢያራ በርረን እንገባለን። እስከዚያው እየተወያያችሁ ቆዩኝ። በጥባጭ ካለ ግን በመሃልም ቢሆን ገባ ብዬ ጆሮውን በመመልዘግ አደብ ማስገዛቴ አይቀርም። 😂
"…በሮም ፀሐይዋ ከነ ልጅ ልጆቿ ነው የወጣች የመሰለኝ። ምግባቸውም ጣፋጭ አይገልፀውም። የቤት ጠላ ነው ብለው ለውኃ ጥም መቁረጫ ይሁንህ ብለው ያጠጡኝ ደንበጃን ሙሉ ድራፍት ያሉት ጠላ መሳይ ነገርም በዓይነ ኅሊና አሸተን ማርያምን እና ዙር አምባ አቡነ አረጋዊን ነው የወሰደኝ። የቤት ጠላ የመሰለው ድራፍት ያሉኝ ነገር እዚህ ጀርመንስ ዞር ዞር ብልም የማጣው አይመስለኝም። እስቲ ጾሙ ይፈታና እማማ ብሪጅ እስቶንን ጠይቄ እሞክራለሁ። ሞጥዬ ብሊስ ብሪጅ ጠላ ቤቱን በመጠቆም እንድትተባበረኝ እርዳኝ። አደራ።
"…የሰማነውንና ያነበብነውን በልቦናችን ያሳድርልን፣ የተሰወረውን ምስጢር ይግለጥልን፣ የተኙትን ያንቃልን፣ ደኅና እደሩልኝ።
"…ሀብታሙ አያሌውና ተሾመ አፍራሳ እና እስክንድር ነጋ የብአዴን ገዳይ አስገዳዮች ለምን በእንብርክክ ተቀጡ? ስለዚህ አሜሪካ አጣሪ ኃይል ወደ ክልሉ ታስገባ፣ ጎጃሜዎች በአስቸኳይ ብአዴንን ከማሳደድ ይቆጠቡ፣ እምቢና አላርፍ ካሉ "…ከጎንደር ጋሽ አባባ መሳፍንትን፣ ሀብቴንና የምወደውን ደሬን፣ ከጎጃም ማስረሻ ሰጤን፣ ከደቡብ ጎንደር ፍሮፌሰርን ጌታአስራደን እና ኮረኔልን ታደሰን፣ ከወሎ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባን እና ፋኖ መከታው ማሞን ይዤ ነው የምዝምትበት፣ በብሮባጋንዳው አበበ በለው፣ ሀፍታሙ አያሎ፣ ብሩኬ፣ ጄሪ አሉልኝ፣ የሚል ድምጸት ያለው መግለጫ ሲሰጥ አሁን ሰምቼ የሆነ ነገር መጣብኝ እና እሱን ነገር ላሳያችሁ ወይስ ይቅር እያልኩ ነበር።
"…የእኔ ነገር ደግሞ ዶፍቶር ምስጋናው አንዱአለም፣ አመዶ ሲሳይ አልታሰብ፣ ማናት ጩጬዋ አያሌው መንበር ደግሞ ቅር እንዳይሰኙብኝ ብዬም ፈራሁ። እኔ ስፈራ መቼም እኮ ጤናም የለኝ።
"…እድሜ ለእኔ ለእኔ ለዘመዴ ይስጥልኝ እንጂ 😂 ሁሉም ዐማራ በጊዜ ነቃ እንጂ እነ አበበ በለው፣ እነ ሀፍታሙ አያሌው፣ እስኬ ብረቷም እኮ በአቅማቸው ፋኖን ሊከፋፍሉት ፍርግጥግጥ እኮ ነበር ያሉት። ከእንግዲህ ሀብታሙ ጮኸ፣ እስክንድር እሪሪ አለ፣ አባቴ ወፍ የለም። ወፍ የለም ስልህ።
"…ለማንኛውም ሁሉንም ነገር ለኦሮሙማውና ለትግርሙማው የሚያመቻቸው እስኬ ብረቷ፣ እስኬ ፌሮዋ በኦሮሙማው ላይ መጨከን ትታ ዘመነ ካሤ ንግሥናዬን አኮላሸብኝ በሚል ምክንያት እንዲህ ጎጃምን መጥመዱ ደስ ባይለኝም ፋኖን በዚህ መጠን ለመክሰስ መጋጋጥ የፈለገበትን ምክንያት የሆነች ቪድዮ ብለቅባችሁስ? 😂
"…አደራ የቦለጢቃው ቅማኔቴዎች፣ አገው ሸንጎ፣ ወነግ፣ ወዩ፣ ብልፄ እንዳትንጫጩብኝ። እኔ እናንተ እስክንደርን በተቸሁት ቁጥር ስትቆጡኝ እየተሳቀቅኩ ተሸግሬአለሁ።
• ልጠይቅ አይደል?
"…መልካም…
"…አሁን ደግሞ ስለዚ ሶዬ… በብሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምትክ አቢይ አሕመድ ቦታ እንደሚሰጠው ቃል እንደገባለት ዳንኤል ክብረት ለወዳጆቹ ሲናገር ስለተሰማው ስለ አባ ዶላር ዳዲ ስለ ፀረ ዐማራው፣ ስለ አባ ከፋፍሌ እስኬው የሆነ ነገር ልል ነኝ። መቼም እናንተ እንደ እነ እስክስ አበበ በለው፣ እንደ ሀፍታሙ አፍራሳ አይደላችሁም ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። የዛሬው የጥልያን እረፍቴን በደንብ ልጠቀምበት ብዬ ነው። ደግሞም…
"…በዚያውም እግረመንገዳችሁን ለሸዋው ፋኖ ለእስክንድር አምላኪው ለወደፊት ለክቡር ብሬዘዳንቱ የጥበቃ ሓላፊ ሆኖ ቃል ለተገባለት ለፋኖ መከታው ማሞ፣ ለጎንደሬዎቹ፣ ለእነ ጋሽ አባባ አርበኛ መሳፍንት፣ ለፋኖ ሀብቴ ወልዴ፣ እጅግ ለማከበረው ለፋኖ ደረጀ፣ ለፍሮፌሰር ጌታ አስራደ፣ ለኮረኔል ታደሰ፣ ለወሎዬው ለኮረኔል ለፈንታሁን ሙሀባው ታደርሱልኝማላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
"…ልቀጥል አይደል?
ከዚያ…
"…ጠቅላይ ሚንስትሯ… የበለጸገውን ባርቲያቸውንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ አደባባይ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥት ለመግባት የተሰባሰበውን ሱናሚ የሕዝብ ማዕበል ያስቆምላቸው ዘንድ በሀገራቸው አጠራር እንደ ኦሮሚያ ፎሊስ፣ እንደ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ እንደ አዲስ አበባ ፎሊስ፣ እንደ ፌደራል ፎሊስ፣ እንደ ጋቸነ ሲርና ያለ፣ እንደ መከላከያ ሠራዊት፣ እንደ ሰላም ሠራዊት፣ እንደ ደንብ ማስከበር፣ እንደ ሚሊሻ ያሉ የሀጋሪቱን የፀጥታ ተቋማት አዘዙ።
"…የሀገሪቱ የጸጥታ ተቋማትም የጠቅላይ ሚንስትሯን ትእዛዝ ተቀብለው። እንደ ብራኑ ጁላ፣ እነ አበባው ታደሰ፣ እንደ ደመላሽ ገበረ ሚካኤል የመሰሉ የባንግላዴሽ የጸጥታውና የወታደሩ ሊቃነ መናብርት በሉት ይሄን ሕዝብ ብለው አዘዙ። ወታደሩም ግራ ቀኝ ሳያይ የገዛ ወንድሙን፣ የአጎትና የአክስቱን ልጅ፣ በእጁ ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ያላዘን ሰላማዊ ዜጋ ግንባር ግንባሩን ይለው ጀመር። ወንዶች፣ ሴቶች እንደ አግአዚ ያለ ጦር በመሰሉ ጨካኝ ወታደሮች አናታቸው በስናይፐር እየፈረሰ በግራም በቀኝም ይወድቅ ጀመር። ሕዝቡ ግን የራበው፣ የመረረው፣ ራሱን እንደ ደባርቅ ነዋሪ መርዝ ጠጥቶና በገመድ ራሱን አንቆ ሞቶ በመንግሥተ ሰማያት ከሚኮነን በመንግሥት ሰይፍ ተሰይፌ ሰማእትነትን ልቀበል ብሎ በወደቁት አስከሬኖች ላይ እየተረማመደ ዋናውን ሰንኮፍ ለመንቀል ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመሄድ ወታደሮቹን ገትሮ ያዘ።
"…በመጨረሻም… ሆቴል ተቀምጠው፣ ቁርጣቸውን እየቆረጡ፣ ልጃገረድ ተማሪ ወጣቶች በጨረታ እየቀረቡላቸው የሚያመነዝሩት፣ በጠቅላይ ሚንስትሯ ኮንትሮባንድ እንዲሠሩ፣ እንዲዘርፉ፣ መሬትና ቪላ በነፃ እንዲታደላቸው የተፈቀደላቸው ጀነራሎች ፈሩ። ፈሩና ለወታደሮቻቸው መመሪያ ሰጡ አሉ። ግድያ አቁሙ፣ መንገዱን ልቀቁላቸው…
"…ከዚያ…
"…ለእሁዱ የመረጃ ተለቭጅን ተናፋቂው "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" መርሀ ግብሬ ለመድረስ ስል ወደ ሀገሬ መመለሻ ድልድዩ በተሰበረብኝ ወቅት የክፉ ቀን መሸሸጊያዬ ወደሆነችው ወደ አጎት ሀገር ጀርመን መመለሻ ቀኔም ስለደረሰ ዛሬን በጥልያን ሮማ ከተማ ከሰዓት በኋላ በማረፊያ ቤቴ የእረፍት ሰዓት ይኖረኛል። በዚያን በእረፍት ሰዓቴ እስከ ምሽት እስከ መኝታ ሰዓታችን ድረስ የልብ የልባችንን እናወጋ ዘንድም አስቤአለሁ። እናንተም በያላችሁበት በጨዋ ደንብ ለመወያየት ተዘጋጁ።
"…እስከዚያው ድረስ የሰላሌዋ ኦሮሞ ሚስቱ አባራው አሁን ከብሪጅእስቶን ጋር በቤልጂየም ብራስልስ ዓለሙን እየቀጨ ላለው ለባለ አንጓ ንቅሴው ለአባባ ሞጣና ለእማማ ብሪጅስቶን የዕለቱ የቲክቶክ ማሳመሪያ፣ ለግንቦቴ፣ ለግንባሩ፣ ለኦነግ እና ለሂዊ፣ ለብልፄ፣ ለፖለቲካው ቅማንቴና ለአገው ሸንጎ አክቲቪስቶች ራሳቸውን በራሳቸው ለስሜታቸው ማርኪያ ይሆን ዘንድ ይህቺን ፎቶ ከጥልያን ሮማ ልኬላቸዋለሁ።
"ሰበር ዜና"
"…አጭበርባሪው፣ ሌባው፣ ዱርዬው፣ ክፍትአፉ፣ እብድ ውሻው፣ ሰካራሙ፣ መራታው፣ ቀማቴው፣ ተሳዳቢው፣ አረም ነቃዩ፣ አያስዋሼው፣ አፍራሹ ዘመድኩን ነቀለ በጥልያን ሮማ ከተማ በፎሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ" ብላችሁ ትሸቅሉብኝ ዘንድ ይህችን ፎቶ ለጥፌላችኋለሁ። 😂😂😂
"…አዛኜን እኔ እኮ ለሚጠሉኝ እንኳ ለዕለት እንጀራ ይሆናቸው ዘንድ የሚያበላቸውን አጀንዳ በምስል አስደግፌ የማበረክት ደግ፣ ለጋስ፣ ቸርና ርህሩህ ነኝ። 😁 አይ ዘሙካ፣ ዘመዴ፣ ዘምነት፣ ዘሙ፣ ዘሜ፣ ዘምዬ፣ ዘመዳችን፣ ዘመድ ዘር…✍✍✍
"…አዳሜና ሔዋኔ ሆይ እንደ ንሥር ታድሼ እየመጣሁልሽ ነው።
በመጨረሻም…
"…ከብር የመግዛት አቅም መዳከም በኋላ በገበያው ላይ ምን ታዘባችሁ?
• ጤፍ በኪሎ ስንት ገባ…?
• 1 ኪሎ ሥጋስ
• ሽንኩርትስ?
• 1 ሊትር ዘይትስ?
"…ትራንስፖርት ጨመረ ወይስ በዚያው ነው። ከአዲስ አበባ ሀረር፣ ድሬደዋ፣ ከአዲስ አበባ መቀሌ፣ ደሴ፣ ጎንደር ባህርዳር የአውቶብስ የትራንስፖርት ዋጋ ስንት ገባ? ከአዲስ አበባ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ጋምቤላ በአውቶቡስ ይኬዳል ወይ? ከአዲስ አበባ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት፣ ደብረ ብርሃን፣ አምቦና ፎቼስ ስንት ገባ ትራንስፖርቱ?
"…አንድ ዳቦ ጨመረ ወይስ ቀነሰ? በየአይነቱ፣ ሽሮ ራሱ፣ ሻይና አንድ ተቆራጭ ኬክ ስንት ገባ? እኔ የምጠጣው ቅሽር ሻይ ስንት ደረሰ? ብርቱካን በኪሎ? አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ስንት ደረሰ?
"…ከአዲሱ ገበያ ፒያሳ ታክሲ እንደ ድሮው 3 ብር ነው ወይ? ከጊዮርጊስ ጎጃም በረንዳ 1ብር ከ50 ላይ ተጨመረ ወይ? ሸሚዝ፣ ካልሲ፣ ግልገል ሱሪስ ዋጋቸው እንዴት ነው?
"…የልጆች ትምህርት ቤት ዋጋ ጨመረ ቀነሰ? የደብተር ዋጋስ? የሰርቢስ ዋጋ? የህክምና ለካርድ እንደ ድሮው 30 ብር ነውን? ፊልም እና ቲያትር መግቢያቸው ስንት ሆነ? የቤት ኪራይስ? ደሞዝስ ጨመረ ቀነሰ?
• ኮሪደር ልማቱስ ምንሁኖ ነው መለስተኛ ሀይቅ የሆነው? የብሽክሊሊት መንጃው ቀዩ አፈር ምን አጠበው? እስቲ ትንሽ አጫውቱኝ። ለስላሳና ቢራስ በጠርሙስ ስንት ገቡ?
"…አሁን እኮ እንደ ድሮ ብዙም የሚያስቸግር ነገር የለም። ሁሉም ነገር ጥርት እያለ ወደፊት እየመጣ ነው። ተኩላው ከበጉ፣ ብርሃን፣ ከጨለማ፣ ኃጥኡ ከጻድቁ፣ እውነት ከሐሰት እየተለየ ነው። የብዙዎች ሜካፕ እየለቀቀ የአፈር ገንፎ እየመሰሉ ነው። አሁን ያልነቃውን ሳይሆን የነቃውን ነው ቆጥረህ የማትደርስበት፣ ሁሉም ነገር መልክ መልኩን ይዟል።
"…አሁን እኮ ያ በሁሉም የተናቀው ፋኖ፣ የትም አይደርስም የተባለው፣ ባለ ሦስት ፍሬ ክላሽ ባለቤት፣ በሦስት ቀን ሱሪውን እናስወልቀዋለን፣ ጃዊሳ፣ አሞሌ ጨው፣ ጽንፈኛ፣ ሽፍታ፣ ዘራፊ የተባለው ፋኖ ዙ 23 መታጠቅ ጀምሯል። ክፍለጦር እያደራጀ ያለ እኮ ነው ፋኖ። ዕህእ።
"…እናም በፊት በፊት ብአዴንን አንበርክከህ ቅጣው፣ ዘር ማንዘሩንም አጥፋው፣ አቶ ግርማ የሺጥላ አሬሮ ኦሮሞ ነው። ከዐማራ ምድር መነቀል አለበት እያለ ሲደነፋ የነበረው የአፍራሳ የልጅ ልጅ ዛሬ ድንገት ተገልብጦ ብአዴኖች ለምን ተንበረከኩ? ይሄ እኮ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው በማለት ከብአዴን በላይ ብአዴን፣ ከብልፅግናም በላይ በልፅጎ የተንበረከኩትን ሰዎችን ሰብዓዊ ጥሰት ለማጣራት አሜሪካም ጦሯን ይዛ ትግባ ምናምን ካለህ በቃ ቲሽ እና ድር የመጨረሻ ተሸንፈዋል ማለት ነው። ማንቁርታቸው ላይ እንደቆምክ ዕወቅ።
"…ዘመነን በመጥላት ሰበብ ዘመነን መሸወድም፣ መግደልም ሲያቅትህ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ዘምተህበት ስታበቃ፣ አርበኛ ባዬ፣ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ላይ ይገደሉ፣ ይጥፉ ብለህ ካወጅክ በኋላ፣ ግዙፉን የምሬ ወዳጆን ጦር እያናናቅክ፣ አሰግድን አሳልፈህ መስጠትህ ሳያንስ የአሰግድን ይዞታ ለመከላከያ ለቀህ እየወጣህ፣ ከመከላከያ ጋር በመናበብ የሸዋ ፋኖ ላይ እየዘመትክ የፋኖ መሪ ነኝ አድምጡኝ፣ ተረዱኝ፣ እርዱኝ ስትል አለማፈርህ። ወዳጄ ዐማራ ሥራ ላይ ነው አልኩህ።
• አልቅስ 😭
• ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
•ቅዱስ ጴጥሮስ
"…ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ ከነገደ ሮቤል፣ በእናቱ ከነገደ ስምዖን ሲኾን፣ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ስምዖን" ነበር፡፡ ኋላ ላይ ጌታ "ጴጥሮስ" ብሎ ጠርቶታል፡፡ ትርጕሙም በግሪክ ቋንቋ ዓለት ወይም መሠረት ማለት ነው፡፡
"…ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ በዋና መዲናቸው በኢየሩሳሌም ፩ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን በዕጣ ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሮም ደርሶታል። በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣ በቀጳዶቂያና በቢታኒያም ዙሮ አስተምራል። በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በስሙ የተመዘገቡ ፪ መልእክታትንም ጽፏል።
•ቅዱስ ጳውሎስ
"…ቀዳሚ ስሙ ሳውል ነበር። ትውልዱም ከነገደ ቢኒያም ነው። የተወለደውም ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ሲሆን ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከገማልያል እግር ስር ሕገ ኦሪትን ተምሯል።
"…በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በስምንተኛው ዓመት ነበር። ለሐዋርያን የተመረጠውም ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ሲጓዝ የዓይኑን ብርሃን በሳጣው የጌታ ጥሪ በደማስቆ ሜዳ ላይ ነው። ስሙም ከሳውል ወደ ጳውሎስ ተቀይሮ ዓለምን ዙሮ ወንጌልን በብዙ ድካም አስተምሯል። ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።
"…ታዲያ ሁለቱም ሐዋርያነ አበው በርትዕት ሃይማኖታቸው ምክንያት በ69 ዓም በጣኦት አምላኪው በሮሙ ንጉሥ ኔሮን ቄሳር በተሰጠ የሞት ፍርድ ቅዱስ ጴጥሮስን የቁልቁል ሰቅሎ፣ ቅዱስ ጳውሎስን ሰይፎ ሁለቱም በአንድ ቀን በሰማዕትነት አርፈዋል። በረከታቸው ይደርብን።
"…ለእኔ ሁለተኛዬ፣ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ የሆነው የጣሊያን ጉብኝታችን በሮማ ወዳጆቼ ክብካቤ በስኬት እየተጓዘ ነው። 🙏🙏🙏
“…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ሊቀ መንበር እስክንድር ነጋ ምክትል ሊቃነ መናብርቶቼን መርጫለሁ ብሏል።
፩ኛ፦ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ከጎንደር (ዕዙ)
፪ኛ፦ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሀባ ከወሎ (ዕዙ)
፫ኛ፦ አርበኛ መከታው ማሞ ከሸዋ (ዕዙ)
፬ኛ፦ ኮረኔል ታደሰ እሸቴ ከጎንደር (ፋፍህዴን)
፭ኛ፦ ፍሮፌሰር ጌታአስራደ ከጎንደር (ፋፍህዴን)
፮ኛ፦ መስፍን አባተ (ከየት እንደሆነ እንጃ)
፯ኛ፦ አርበኛ ደረጀ በላይ ከጎንደር (ዕዙ)
፰ኛ፦ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ከጎጃም (ዕዙ)
፱ኛ፦ መምህር ምንተስኖት ወንዳፈረ ከሸዋ (ዕዙ) ከኢዜማ ናቸው።
"…እንግዲህ የእነዚህ ሁሉ አለቃቸው ማን ሆነ? ጋሽ እስክንድር ነጋ። አዎ ጋሽ ሁሌ ሊቀመንበር አሁንም ሊቀመንበር ሆነዋል። በዚህ በጋሽ ሁሌ ሊቀመንበር ድርጅት ውስጥ ደግሞ ጎንደርን ወክለናል ያሉቱ በስፋት የሥልጣን ቦታ ሲያገኙ፣ ግዙፍ ጦር ያላቸው ከጎጃም እነ አርበኛ ዘመነ ካሤ፣ የጦሩ ሊቅ እነ ሻለቃ ዝናቡ፣ እነ ኢንጂነር ማንችሎት ጎጃሜ ስለሆኑ እግራችሁን ብሉ ተብለዋል።
"…ከዚያው ከጎንደር እነ አርበኛ ባዬ፣ እነ አርበኛ ፋኖ ሳሙኤል ባለድልና ሌሎቹም ጥፉ ከዚህ ድራሻችሁ ይጥፋ ተብለዋል። የምሥራቅ ዐማራው አብሪ ኮከብ፣ የጦሩ ገበሬ የዋርካው ምሬ ወዳጆም በባልደራሱ ሊቀመንበር በጋሽ እስክንድር አያስፈልግም ተብሏል። ሸዋ የአሰግድ ጦር፣ ኢንጂነር ደሳለኝ የሚመራው ጦር፣ ከሰም፣ ቡልጋ፣ አሳግርትን የመሰሉ ግዙፍ ጦር ያላቸው በጋሽ ዶላር ዕዝ ውስጥ አልተፈለጉም።
"…የጎንደሩ እስኳድ ከጎጃም፣ ከወሎ፣ ከራሱ ወንድሞች ከጎንደሮቹ፣ ከሸዋዎቹም ውጪ በእስክንድር መሪነት አራት ኪሎ ለመግባት ከአሁን ተሿሹመው ጨርሰዋል። ያለ ጎጃም፣ ያለ ወሎ፣ በዚያው በጎንደር፣ ደግሞም በሸዋ ስምም ሳትሆን ዝም ብሎ ድል ለዲሞክራሲ ብሎ በመፎከር 4ኪሎ መግባት አለ እንዴ?
• ቢመርም ደፈር ብላችሁ ተወያዩበት።
"…ሴትይዋ ላለፉት 15 ዓመታት ባንግላዴሽን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ሸክላ አድቅቀው የገዙ ናቸው ይሏቸዋል። ኑሮ ከበደ፣ የግለሰቧ ፈላጭ ቆራጭነት ቅጥአጣ፣ የፓሪቲ ሰዎች ብቻ የሌማት ቱሩፋቱም፣ የኮሪደር ልማቱም ተጠቃሚ ሆኑ። ሌላው የባንግላዲሽ ዜጎች በጠሚዋ ፈላጭ ቆራጭነትና በፓርቲያቸው አገዛዝ ተሰላቹ። መረራቸውም።
"…ከሳምንት በፊት በቁጥ ቁጥ ባንጋሊዎች ተቃውሞ ጀመሩ። ጠሚዋም ለማስደንገጥ በሪፐብሊካን ጋርዳቸው አንድ 200 ያህል ተቃዋሚዎችን ገደሉ። ደም ሲፈስ ደም ይፈላልና ሕዝቡም በአቋሙ ጸንቶ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ወጣ። በመጨረሻም ጠቅላይዋ እያየለ የመጣውን የሕዝብ ተቃውሞ ሰግተው እግሬ አውጪኝ ብለው ወደ ዱባይ ማነው ወደ ሕንድ ፈረጠጡ።
"…አሁን እነዚያ ተቃዋሚዎች በተራቸው ጠቅላይዋ ይኖሩበት ወደ ነበረው ቤተ መንግሥት በኃይል ሰብረው በመግባት በጠቅላይዋ መኖሪያ ቤት እንዳሻቸው እየፈነጩበት መሆኑም ተነግሯል። ሪፐብሊካን ጋርዱ፣ መኴው፣ የኦሮሚያ ፎሊስ ጭምር ማነው የባንግላዲሽ ፎሊስ ማለቴ ነው ይቅርታ ከዳር ቆመው ከመመልከት በቀር ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም።
"…ለአንዲት ጥጋበኛ አምባገነን ሴትዮ ምቾት ብለን ሕዝባችን ላይ ለምን እንተኩሳለን? ሀገር ቀጣይ ናት፣ ፓርቲም፣ መሪም ይሄዳል ይመጣል ያሉት ወታደሮች ለበዓሉ ድምቀት 200 ያህል ሰው ከገደሉ በኋላ ከዚህ በላይስ ይበቃናል። “ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።” ዕብ 9፥22 እንዲል መጽሐፍ እነርሱም የ200 ባንጋሊዎች ደም በከንቱ ካፈሰሱ በኋላ ሀገሪቷ ከጋንግሪኗ መገላገሏን እና ሕዝቡም እምነቱን ጥሎብን ሕዝባዊ መንግሥት እንዲመጣ አብረን እንሥራ ብሏል።
• እኔ አረፍት ላይ ነኝ። ወደ ኋላ አንድ የፋኖ ዜና እለቅባችሁና ድጋሚ ወደ እረፍቴ እመለሳለሁ። እስከዚያው…በረከተ ባንግላዲሽ ይደርብን አሜን።