መልካም…
"…እስከ ፊታችን ማክሰኞ ድረስ የማይኖረንንና የሳምንቱ መጨረሻ የሆነውን የዕለተ አርብ "ርእሰ አንቀጻችንን" እንደ ኦንድሜ ስዩሜ ተሾሜ በምርቃና የሚተነትነውን የጦቢያ ቦለጢቃ "ሁ ማይነስ ሁ" በሚለው ሕግ መሠረት እኔ ዘመዴስ በ "ቀኝ ትከሻዬ ሸከከኝ" የቦለጢቃ ትንተና ሕግ መሠረት ቦለጢቃውን ብተነትነው ምን ይላችኋል? እንዲየው ቁምነገር ባታገኙበት እንኳ በዚህ ጭፍግግ ዘመን ትንሽ ፈገግ ማለትስ ቀላል ነው እንዴ?
• እኔ ዘመዴ የምሥራቅ አፍሪቃን ጂኦቦለጢቅሱን እንደ ስዩሜ፣ ተሾሜ በምርቃና ባልተነትነውም ጠላዬን እየጠጣሁ "በቀኝ ትከሻዬ ሸከከኝ" የቦለጢቃ ትንተና አግባብ በማይም ዕውቀቴ ደግሞም ከዕውቀቴም አንጣር ልተነትነው ነኝ።
"…መቼም ዘንድሮ ተው ይቅርብህ የሚል ክፉ መካሪ የለም። ሁሉም ለጥቅ፣ ግፋበት፣ ተንትን ነው የሚለኝ ግን ላስፈቅዳችሁ ብዬ ነኝ። ትን እስኪላችሁ ልተነትን ነኝ።
• እህሳ ምን ትላላችሁ…? 😂
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!
"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።
የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ
👉YouTube
https://www.youtube.com/live/-mPx6OuuEeM?feature=shared
👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v5ylos8--ethiobeteseb.html
👉በፌስቡ / Facebook
https://www.facebook.com/share/1Nx6YYWdeC/ facebook.com/ethiobeteseb
👉 በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb
👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb
👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v5pa5f5--ethiobeteseb.html
"…ሻሎም ! ሰላም !
👆②✍✍✍ …ሊነቁ አልቻሉም። የዋህነታቸው ብቻ ሳይሆን መሃይም መሆናቸው ጎድቷቸው ትግሉንም ጎድተውታል።
"…ልብ በሉ የእነ መከታው ዋና ሰው የድርድሩ፣ የሽምግልናው ወቅት እነ አቤ ጢሞና፣ እነ መከታው የመደቡት ሰው ፓስተር ዮናስ ይባላል። ፓስተር። መዝግቡልኝ። የሸዋን ቦለጢቃ፣ እነ መከታውን የሚመራው ፓስተር ነው። ይሄንን ሁሉም ያውቃሉ። እነ ፓስተር ምስጋናው ደግሞ ከጎንደር እኩል ሸዋ ላይ ነው ዓይናቸውን የጣሉት። ብልጽግና ፓርቲም በሙሉ የፓስተሮች ስብስብ ነው። የሸዋ ፋኖዎች ሲጣሉ እንኳ የሚታረቁት ኦርቶዶክሳውያኑ በቤተ ክርስቲያን በካህን ፊት ወንጌል ስመው ሲሆን እስላሞቹ በመስጊዳቸው በሼሆች ፊት ቁርዓን ስመው ነው። አበበ ጢሞ፣ መከታው የጻድቃኔዋ እመቤት እያሉ ሲምሉ ደሙ የሚፈላው ፓስተር ዮናስን ነው አለቃ አድርገው የሾሙት። ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ ሰው ነው እነ መከታውን የሚዘውረው።
"…የሸዋው ስምምነት አልቆ እነ ጋሽ አሰግድ 5ሰው፣ እነ መከታው 5 ሰው እንዲመድቡ ተደረገ። የመደቧቸው ሰዎች በቶሎ ተገናኝተው እንዲመክሩና በቶሎ የሸዋ አንድነት እንዲታወጅ ነበር ስምምነቱ። ይሄን ጉዳይ እንዲመሩ በእነ አቶ አሰግድ በኩል ዶክተር አብደላ፣ በእነ መከታው በኩል ፓስተር ዮናስ ተመደቡ። አምባሳደር ብርሃነ መስቀል፣ ልጅ ተድላ መላኩ፣ እነ ኤልያስ ክፍሌና እነ ሳራ ዘልዑልም ምስክር ናቸው። እነ አቶ አሰግድ ሽማግሌዎቻቸውን አሳወቁ። የተወሰደ ንብረት አለ እሱን የሚያስመልሱ፣ እና አንድነቱን የሚያመቻቹ። የእነ መከታው ፓስተር ዮናስ ግን ነገሩን አጓተተው። በስንት ጭቅጨቃም አምስት ሰዎች ስምዝርዝር ሰጠኝ። በእነ ልጅ ተድላ አማካኝነት የሁለቱንም ወገን ሽማግሌዎች ሥራ እንዲጀምሩ እና በአጭር ቀን ውስጥ ውጤቱን እንዲያሳውቁን መመሪያ ሰጠን።
"…መሸ ነጋ ብዙም ቀን ሆነው። የእነ አሰግድ ሽማግሌዎች ጭቅጨቃ ጀመሩ። ከቀረ ንገሩን፣ ከተዋችሁት ንገሩን። የምን ቀልድ ነው የተያዘው ብለው ተቆጡ። እውነት አላቸው። ፓስተር ዮናስን ልመና ጀመርኩ። ውትወታ ያዝኩ። ኧረ ፓስተር በናትህ አፍጥነው እለው ጀመር። ልጅ ተድላም፣ ኤልያስ ክፍሌም። አንዲት በአሜሪካ የሚኖሩ ወዳጄም ባሉበት ወተወትኩ። በመጨረሻም ፓስተሩ እነወዲህ አለኝ። "ዘመዴ እንዲያውም ሽምግልና አያስፈልግም። ከመጡ ይምጡና በእኛ ስር ይሁኑ። ካልመጡ ግን እነሱን ለመደምሰስ የግማሽ ቀን ሥራ ናት። እዚህ ግባ የሚባል ኃይል የላቸውም። የምንሰጣቸው መሣሪያም የለም። ከእነሱ የወሰድነው መሣሪያም ልጁ ከእኛ ከድቶ ጋሼ ጋር ይዞት ገብቷል። እናም ይኸው ነው አለኝ። መረጃ ይዤ ነው የማወራችሁ። ከዚያም እኔም አልኩት። ስማ ፓስተር ዮኒ። ጉዳዩ እና ሴራው የት እንዳለ ቁልጭ ብሎ ይታያል። አንተና እስክንድር ነጋ፣ ዐቢይ አሕመድም ዐማራን አታሸንፉም። የሆነ ቀን ችግሩ መፈታቱ አይቀርም። ያኔ አንተም ታፍራለህ። አንተ አሁን የናቅካቸው ወንድሞችህ ይከብራሉ። አንተም፣ አለቃህ መከታውና አቤ ጢሞም፣ መምህር ምንተስኖትም ታፍራላችሁ። ትዋረዳላችሁ። ፀጋችሁም፣ መፈራታችሁ፣ መወደዳችሁም ይገፈፋል። ታያለህ መዝግብልኝ ብዬ አስረግጬ በመንገር ተለያየን። እኔም በይፋ የሽምግልናውን ውጤት ለሚጠብቀው ሕዝብ እንዲህ አብራርቼ ሳልጽፍ፣ ሳልናገርም እስከዛሬ ቆየሁ።
"…ቆይቶ ፓስተር ዮኒ ደወለልኝ። ደወለልኝና ሊያናግረኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ። እኔም ብቻዬን እንዳልሆን ብዬ ልጅ ተድላን ይሁን ኤልያስን አላውቅም ብቻ አንዱን ሰው አስገባሁ። ፓስተሩም አለኝ። ዘመዴ እኔን ለምን የሽምግልናው መቋጫ አድርገው እንደመረጡኝ አላውቅም። በእርቁ መርሀ ግብር ላይ የተገኘሁት ሁለት ወይ ሦስት ቀን ቢሆን ነው። እነ መከታው፣ እነ አበበ ምን አስበው እንዳስገቡኝ አላውቅም። ስምምነቱም በምን ጉዳይ እንደተቋጨ ዐላውቅም። እናም እኔን ከዚህ ነገር ዐውጣኝ አለኝ። እኔም መልሼ ነገርኩት በቃ ሁሉ ነገር ተበላሽቷል። ሁላችሁንም ሥራችሁ ያውጣችሁ። እናንተ ግን እስክንድር ነጋ ያዋጣችሁ እንደሆነ ወደፊት የምታዩት ይሆናል። እኔ አሁን ምንም ውስጥ አልገባም ብዬ ከፓስተሩ ጋር የነበረንን ግኑኝነት አቋርጬ ወጣሁ። ዳግምም አልተመለስኩም። የፓስተሩ የትውልድ ሀገር ሸዋ ይሁን ጎንደር ግን አላውቅም። የሸዋ ጉዳይ ሽባ የሆነው። እነ መከታው የሸዋ ልጆችን በቢለዋ ተልትለው የመግደል፣ የማስወገድ ድፍረትን ያገኙት፣ አሰግድን አዋክበው፣ በቤቱ ተገኝተው፣ አዋርደው አሳልፈው የሰጡት ጉዳዩ የሃይማኖትም ጭምር ስላለበት ነው። ዛሬ የሸዋ መኳንንት ነቅተው ለእነ መከታው የሚረዱት ዶላር ሲጠርባቸው አንዴ ሚኪ ጠሽ ቴሌግራም ላይ ገብተው ስለ ማርያም አምስትም፣ አስርም ጣል አድርጉልን ወደሚል ተራ ልመና የወረዱት በገዛ እጃቸው ነው። የሌለ ስለታበዩም ጭምር ነው።
"…አሁን ተሸዋ ፋኖ በእነ ኢንጅነር ደሳለኝ የሚመራው ከሚገባው በላይ እየተደራጀ ነው። በእነ መከታውና ፓስተር ዮናስ ስር የነበሩት ፋኖዎች እነ ዘኪን ጨምሮ ሌሎችም ከዚያ ወጥተው እየገቡ ነው። በዚያ የቀረው ኤርሚያስ የሚባል ቀማቴ ከማስቸገሩ በቀር አሁን የእነ መከታው ቡድን በዜሮ ቀርቷል። እነ መከታው ከእስክንድር ነጋ ጋር ተያይዘው የፖለቲካ ሞት ሞተዋል። እኔ ለማዕተቤ እመሰክራለሁ መከታው ማሞ አንደበቱ ቁጥብ፣ ሲናገር ረጋ ብሎ፣ የአባት ዐማሮች ወዝና ለዛ ያለው፣ ምንም ክፋት ይኖርበታል ብዬ ሰውነቴን የማይሸክከኝ ቅን ሰው ነው የሚመስለኝ። ለተጠየቀው ጥያቄ ሁሉ ረጋ ብሎ ነጥብ በነጥብ የሚያስረዳ፣ ከዚህ ጠባዩ የተነሣ በሠራዊቱም ዘንድ የሚወደድ ከምር ግሩም ሰው እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። አቤ ጢሞም አጥፍቶ ተንበርከክ ስለው እንኳ፣ ምንአባክ፣ የትአባክ ሳይል የተንበረከከ፣ የጻድቃኔዋ ማርያምን ስም ጠርቶ ሁለተኛ አልስትም ያለኝ፣ በመከታው ማሞ ዋስትና ከተንበረከከበት የተነሣ ሰው ነው። ይሄንን እነ አምባሳደር ብርሃነ መስቀልንም ሆነ ልጅ ተድላን ጠይቁ። ነገር ግን እነዚህን የሸዋ ዐማሮች እስክንድር ነጋ የተባለ የደቡብ ጎንደር ስኳድ መሃላቸው ገብቶ እግር ከወርች አሳስሮ ሽባ አድርጎ አስቀራቸው።
"…ከጎንደር ሰሎሞን አጠናው ቢመጣም ቢቀርም አይጠቅምም፣ አይጎዳም። እንደሰማችሁት ነው። ይሄ የስልክ ቅጂ ሳይወጣ ነው እኔ ስለ ሰሎሞን አጠናው የነገርኳችሁ። "የፋይናንስ ችግሩ ቢፈታልን ይሄንን የጎንደር አንድነት ብትንትኑን ነው የምናወጣው" የሚለው ሰሎሞን እውነቱን ነው። እስክንድር ነጋ ከድሮ ጀምሮ አጓጊ፣ ሳቢ፣ አማላይ የትግል ፕሮጀክቶችን እየቀረጸ፣ በሚዲያ በኩል ስሙን እየገነባ፣ የአቢይ አሕመድን ሚና ሲጫወት የከረመ መሰሪ ክፉ ሰው ነው። አዲስ አበባን በተራ አስከባሪ ኮሚቴዎች አስከብራለሁ ብሎ ለኦህዴድ ኦነግ አሳልፎ የሸጠ ሰው ነው። ባላደራው፣ ባልደራሱ፣ ሰናይ ቲቪ፣ ኢትኢጵ፣ ግምባሩ፣ ሠራዊቱ፣ አሁን ደግሞ ድርጅቱ እያለ አጓጊ ፕሮጀክቶችን እያቀረበ በተለይ ዐማራው የሚያዋጣው ገንዘብ ለእሱ ብቻ እንዲደርስ በማድረግ፣ ድኩማን የደሀ ልጆችን በማማለል የዐማራን ትግል ሲጎትት፣ ሲሸቅጥ የኖረ ግለሰብ ነው። በእስክንድር ነጋ ስር ያሉ በሙሉ ነጋዴዎች ናቸው። ሰሎሞን አጠናው የሻይ ነጋዴ ጎንደር፣ መከታው ማሞ የበርበሬ ነጋዴ ሸዋ። እንዲህ ያሉትን በፍቅረ ነዋይ የታሠሩ ግለሰቦችን በገንዘብ ኃይል አንቆ ይዞ ነው ትግሉን አፈር ከደቼ ያበላው። ምንም እንኳ መጀመሪያ ላይ ብትጠሉኝም መጨረሻ ላይ ግን ይኸው የእግዚአብሔር ቀን ሲደርስ ሁሉ ፍርጥርጡ ወጣ። ገንዘቡን ብትልክልኝ እኮ ፍርስርሱን ነው የማወጣው አላለም?👇②✍✍✍
መልካም…
"…ለእኔ ትልቅ ድል ነው። ለጎንደር ዐማራም ትልቅ ድል ነው። ለመላው የዐማራ ፋኖ ትግልም ትልቅ ድል ነው። ጎዶኞቼ ዝርዝሩን እሁድ ነው በመረጃ ቴቪ በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በሚለው የቀጥታ ስርጭት ዝግጅቴ በሰፊው የምመለስበት። ለዛሬው ግን ለአሁኑ እንደ ማቆያ የሚሆን "አንጀት አርስ" የሆነ ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችኋለሁ። እንዴት ያለ ሰናፍጭ የበዛበት፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ርእሰ አንቀጽ መሰላችሁ ያዘጋጀሁላችሁ። አሜን ነው…?😂
"…እስቲ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ነካ አድርጉትና… ትንሹ… ኖ ዶላር…😂 ዝግጁ ነነ ዘመዴ በሉኝማ…🙏🙏🙏
መልካም…
"…እኔ የእኔን ሓሳብ በርእሰ አንቀጼ ላይ ገልጫለሁ። አስፍሬአለሁም። በቀረው ደግሞ እናንተ ተወያዩበት። እናንተስ ምንድነው የሚታያችሁ? የሚሰማችሁስ…?
• 1…2…3…ጀምሩ ✍✍✍
👆② ✍✍✍ "…አሁን በዐማራ ክልል የቱርክና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ የሳዑዲ ቦንብና ጥይት ብዙዎችን እየቀጠፈ ነው። እየገደለም ነው። እያወደመም ነው። ኢትዮጵያ የበለጠ እርድታ እንድታገኝ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በግልጽ የዐረብ ሊግ አባል ካልሆንን በማለት ከኦሮሚያው መጅሊስ ጋር ጉዳዩን እያፋጠኑት ይገኛሉ። ዐረቦቹ ኢትዮጵያ ላይ ጆፌ ጥለዋል። የዐማራ ውኃው ዳር መገኘት ደግሞ ትልቁ ስጋታቸው ነው። ስለዚህ ለዚህ በፕሮቴስታንት ከቨር ለተጠቀለለው ለእስላሙ አቢይ አሕመድ አገዛዝ ያለ የሌለ ርዳታቸውን እየሰጡ ዐማራውን እያስጨፈጨፉት ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሠሩት፣ የደከሙት ሀገራት በሙሉ ፈርሰዋል። ሊቢያ፣ የመን፣ ሱዳን፣ ፍልስጤም፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ሶማሊያ በሙሉ ፈርሰዋል። የሚቀሩትም ይፈርሳሉ። ግብጽና ሳዑዲ አረቢያም ግማሽ መሬታቸውን ያጣሉ። በቅርቡ ያጣሉ። ልክ ፍልስጤማውያን መሬታቸውን እንዳጡት፣ ሶሪያም የዛሬ ሳምንት መሬቷን እንዳጣች ሌሎቹም ያጣሉ። በቀጣይ ኢራን ትወድማለች። ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሠሩት የመካከለኛ ምሥራቅ እና የዓረብ ሀገራት በሙሉ ከነስም አጠራራቸው ይፈራርሳሉ። ሀገሬን ያስራቡ፣ ያስጠሙ በሙሉ በሀገሬ ላይ ያደረሱት በሙሉ በእጥፍ ይደርስባቸዋል። ቱርክም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የሀበሻን ምድር ነክታለችና ዳግም ትፈርሳለች። መጀመሪያ የኦቶሞን ቱርክ የፈረሰው፣ የጣሊያን ገናናነት ያከተመው፣ የእነ እንግሊዝም ዘመን ያበቃው ተወደደም ተጠላም፣ አመናችሁም አላመናችሁም ዳግሚት ኢየሩሳሌም፣ ሀገረ እግዚአብሔር በሆነች ኢትዮጵያ ላይ በሠሩት ሴራ እና ሸር ነው። እመኑኝ ኢትዮጵያ ላይ የመከሩ በሙሉ ይወድቃሉ። መዝግቡልኝ። ሚጢጢዋ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትም ምንአልባትም በእኛው ዘመን ሳንሞት ትናዳለች፣ ሀገራትን በገንዘቧ አፍርሳ በደም ገንዘብ የተገነባች ናትና ትወድማለች። ትፈርሳለች። ኢትዮጵያ ዓይናቸው እያየ ትነሣለች። ይሄን ስጽፍ ዓረባዊ አፍቃሬ ዓረብ የወሃቢያ እስላም ሊበሳጭ ይችላል። ግን ምንም አያመጣም። ብስጭቱ ዓይናችን እያየ የፈራረሱትን ዓረባውያኑን ሀገራት እነ ሊቢያን፣ ሶማሊያን፣ ሱዳንን፣ ሶሪያን፣ ፍልስጤምን፣ የመንን፣ ኢራቅን አይታደግም።
"…አቢይ አህመድ አራጁ አሁን የሚተማመነው በእነዚህ ዓረብ ሀገራት እና በአረቦቹ ፈንድ ያዘጋጀውን ሕጋዊው የመከላከያ፣ የኦሮሚያ ፖሊስንና ሚሊሻን፣ ሕገወጡን የኦነግ ሸኔን ቡድንን ነው። አሁን ላይ በተለይ ይሄ አራጅ አገዛዝ በዐማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ ይቅር የማይለው እጅግ ክፉ ጠባሳ ነው ትቶ እያለፈ የሚገኘው። ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፣ በድሮን ከሚጨፈጭፈው ሕዝብ፣ ከሚያወድመው መሠረተ ልማት፣ በገዳ ሥርዓት ሚሰልበው የዐማራ ወንድ፣ ከሚደፍራቸው ሴቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ከሚያርዳቸው የሃይማኖት አባቶች በተጨማሪ የቁም እንስሳትን እግር እየቆረጠ በከብቶች ላይ የሚፈጽመውን፣ በእንስሳት ላይ ሳይቀር የሚፈጽመውን በደል ብታዩ ትደነግጣላችሁ። አልፎ ተርፎ አሁን ደግሞ የደረሰና የተሰበሰበ እህል በድሮን፣ በከባድ መሣሪያ ጭምር ከዓረብ ኤምሬትስ እና ከቱርክ በሚያገኘው መሣሪያ እያነደደው ይገኛል። ይሄን ቂም ለመወጣት ዐማራው በምን ዓይነት የበቀል ስሜት ውስጥ እንደሚሆን መገመት ነው። ገምቱ ብቻ። አሁን አሁን በአዲስ አበባ ከተማ የተበተነው አራጅ ሸኔ በካፌዎች ውስጥ የአማርኛ ዘፈን የሚከፈቱ አስተናጋጆችን መደብደብ ጀምረዋል። በተለይ ደግሞ ዐማራ ክልል ሠራዊቱ መሸነፉን ካረጋገጠ መሀል ሀገር ከፍተኛ ውድመት እንደሚያደርስ ከወዲሁ መገመት ይቻላል።
"…አንዳንድ የአገዛዙ ደጋፊዎች ስለ አገዛዙ ሲነገር፣ ሲወራም አገዛዙ እጅግ ግዙፍ እንደሆነ፣ ሠራዊቱም ጠንካራና በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ሁላ የተደራጀ እንደሆነ በኩራት ነው የሚያወሩት። የሠራዊት ብዛት ከውድቀት እንደማያድን አይታያቸውም። በጽናት የታገለ ትሪልዮን ዶላር በጀት መድቦ 20 ዓመት በአፍጋኒስታን የተዋጋው ታሊባን ግዙፉን የኔቶና የአሜሪካንን ጦር እንዳሸነፈም አያውቁም። ቢያውቁም ልባቸው በጮማ የተደፈነ ስለሆነ፣ ደናቁርት ማይሞችም ስለሆኑ አይገባቸውም። ነገር ግን የሠራዊትም የጦር መሣሪያ ብዛትም ግፍ እየሠራህ አይታደግህም። የሩቁን ደርግ፣ የሩቁን የወያኔን ትእቢተኛ፣ ጉረኛ አገዛዝ ድንፋታ ትተን፣ የዛሬ ሳምንቱን የሶሪያ ውድቀት፣ የአልአሳድን መገርሰስ እንዴት እንደሆነ እንይ፣ እንረዳ። እንመልከተውም። አዎ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ቀን፣ የሆነች ሰዓትና ደቂቃ፣ ሰከንድም ላይ የሠራዊቱ አከርካሪ ሲመታ ከመበተን በቀር ሌላ ምንም ዕጣ ፈንታ አይኖርህም። ከዚያ በኋላ የሚከሰተውን የበቀል ጥፋት እንዴት ከወዲሁ እናርቀው በሚለው ላይ ነው ከወዲሁ መነጋገር። እንጂ ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም የተባለው ጥንት ነው። ጥንት በነቢየ እግዚአብሔር በልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት አንደበት።
"…ይህን በማስመልከት ትናንት አሌክስ አብርሃም የተባለው ደራሲና ጦማሪ የት ሄዱ? በማለት ስለ ሦሪያ ሠራዊት የጠየቀው ጥያቄ ለዚህ ርእሰ አንቀጽ ተስማሚ ሆኖ ስላገኘሁት ላካፍላችሁ ወደድኩ። አሌክስ ይጠይቃል። የት ሄዱ? ሶሪያ ከሳምንት በፊት 260 ሺ እስከአፍንጫው የታጠቀ በራሽያ የሰለጠነ ጦር፣ 25 ሺ ለዓመታት በልዩ ሁኔታ የሰለጠነ ስፔሻል የኮማንዶ ጦር፣ 4,800 የዘመኑ ታንኮች፣ ድሮንን ጨምሮ ዘመናዊ የውጊያ ጀቶች የታጠቀ አየር ኃይል፣ በልዩ ሁኔታ የሰለጠነ ደማስቆ አጠገብና ሜዴትራንያን የሰፈረ ባህር ኃይል፣ ይሄ ሁሉ በኃያሏ ሩሲያና በኢራን ጦር ሙሉ የቴክኖሎጂና የባለሙያወች ድጋፍ፣ እንዲሁም አስፈሪ የጦር ኃይል አጀብ በተጠንቀቅ ቁሞ ነበር። በሳምንት ውስጥ "አከርካሪያቸው ተሰብሮ እንደትቢያ ተበተኑ" የተባሉት አማፅያን በነጠላ ጫማ፣ በኤርገንዶ ምናምን ሸክ ሸክ እያሉ እንደአውሎ ንፋስ ገለባብጠውት ቤተመንግሥቱን ተቆጣጠሩ። መሪውም ወደ ሩሲያ ፈረጠጡ። የት ሄደ ያ ሁሉ ለዓመታት የተገነባ ሠራዊት? "ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም" የሚለው መጽሐፉ እንዲህ ያለውን ነገር ነው። አይገርማችሁም ጦርነት? አለሁ ማለት ከንቱ። በማለት ይጠይቃል።
"…አዎ የሆነ ቀን፣ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ሰዓት ላይ፣ የሆነች ደቂቃና የሆነች ሰከንድ ላይ ይሄም እቡይ፣ የታበየ፣ አረመኔ የሆነ አገዛዝ መሰበሩ አይቀርም። የምፈራው ከዚያ በኋላ ስላለው ነገር ነው። ከአሁኑ በዐማራና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች በአገዛዙ ካድሬዎችና ባለሥልጣናት ላይ የከፋ የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። በዐማራ ክልል የብአዴን ብልጽግና ላይ፣ በኦሮሚያ የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎች ላይ የከፋ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ሥርዓቱ በንፁሐን ላይ ለሚፈጽመው ዘግናኝ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የሥርዓቱ ተባባሪዎች ናችሁ በማለት የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይሄ ደግሞ ውጤቱን ከወዲሁ መገመት ነው። ዛሬ በለጠፍኩላችሁ ቪድዮ ላይ የምትመለከቱትም ይሄንኑ ነው። ከ5 ዐማራ አራቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አባሉን በዚህ ሥርዓት ያጣ ነው። ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ ጥቁር የሚለብሰው ሕዝብ ዕለት በዕለት እየጨመረ ነው። ከአዲስ አበባ ቤቱ ፈርሶበት፣ ኪራይ እንኳ ተከልክሎ የተሰደደው፣ ሀገር አልባ የተደረገው፣ አሁን ነፍጥ አንሥቶ ቀን ነው እየጠበቀ የሚገኘው። የከፋ ቀን ነው እየመጣ ያለው። አቢይ አሕመድ ከሚስቱ ጋር ወደ ዱባይ ቪላው ሊሸሽ፣ ሊያመልጥም ይችል ይሆናል። ቀሪው ካድሬ ግን በሶሪያ እየሆነ እንዳለው ዓይነት የበቀል…👇②✍✍✍
መልካም…
"…ርእሰ አንቀጹ የተቃኘው በምታዩት ቪድዮ ቅኝት ነው። ገና አንድ ዓመት ተኩል ይቀረኛል የሚለውም ደፋር ገና መች ጨፈጨፍኳችሁና የሚል ይመስላል። ቀጥሎ የምታዩት ቪድዮ የአገዛዙ ወታደር ሆነው ጎጃም ዘምተው ተማርከው በእንክብካቤ ላይ የነበሩ የራሱን ወታደሮች እና ወታደሮቹን ይንከባከቡ የነበሩ ዐማሮችን በድሮን ረፍርፎ ነው የምታዩት። በመቀጠል የምታዩት አገዛዙ ከጥይት የተረፈውን የዐማራ ገበሬ የደረሰ እና የተከመረ እህል ሲያቃጥል ነው። መዝግቡት።
"…ቀጥሎ የምታዩት በሶሪያ እየሆነ ያለ ነው። አላሳድ ወደ ሩሲያ ሲኮበልል፣ ሕዝቡም፣ ታጣቂዎችም የአላሳድ ፓርቲ ሰዎችን፣ ሚሊሻ፣ ወታደር፣ ተማረከ አልተማረከ በእልህ ሲረሽን ነው። ሕዝብ ሲያለቅስ የነበሩ አሁን ደም እንባ እያለቀሱ ነው። በቀሉ ሆስፒታል ቆስለው የተኙ የአላሳድ ወታደሮችን ከተኙበት አልጋ ላይ ጭምር ነው ገብተው የሚበቀሉት።
"…የቻለ የአላሳድ ወታደር የጦር መሳሪያውን እያንጠባጠበ ሀገር ለቅቆ ተሰድዷል። የቀረው ግን እንጃለቱ። እሺ የብአዴን ካድሬ፣ የብልጽግና አሽከሮች ከዚህ ምን ትምህርት ትወስዳላችሁ? ብሎ መጠየቅ ጉንጭ ማልፋት ነው። ቢሆንም ግን ርእሰ አንቀጹ ይለጠፋል።
• ቪድዮዎቹን እያያችሁ ጠብቁኝ።
"…እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው። 2ኛ ሳሙ 8፥6
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
በላሌዴንጣ… አዲጭ… 🖐
• ወደ መንደሬ በሩጫ እየሄድኩ ነው… 🏃♂➡️
• ወደ መንደሬ የመግቢያ ካርዱ ይኸው
👉🏿 zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b
👆③ ✍✍✍ "…የወሎ የዐማራ ወንዝ ወደ አንድ ከመጣ በኋላ ከእስክንድር ነጋ ጋር ወደ ሸዋ፣ ከዚያም ወደ ወሎ የተሻገረው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋነኛ ሰው የወሎውን ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባውን በመጠጋት፣ እሱንም በመጠርነፍ አንድ ሆኖ እንደ ተለያየን፣ እንደ ቦርከና የበጋ ወንዝ ጥርት ያለውን የወሎ ቤተ ዐምሓራ የትግል ወንዝ በክለው አቆሽሸውታል። በኮሎኔሉ እንዝህላልነት እነ እስክንድር በደካማ ጎኑ ገብተው የወሎ ቤተ ዐምሓራ የትግል ወንዝ እንዲበከል አድርገዋል። ዛሬ ከፋኖ ዮሴፍ ጆሲ ጋር ደውሎልኝ ለረጅም ሰዓት ባደረግነው የስልክ ውይይት ወሎም እንደ ጎንደር ወደ አንድነት በቅርቡ ይመጣል የሚል የምሥራችን አብሥሮኝ ደስ ሲለኝ ነው ያረፈድኩት። በቀደም ዕለት ከዋን አማራዎች ጋር ግንኙነት ይኖርህ እንደሁ ብዬ የወቀስኩት ጆሴ "ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት በፍጹም የለኝም ዘመዴ ብሎኛል።" ከብርጋዴል አሳምነው ጽጌ ጋር በመሆን የዐማራ ልዩ ኃይልን ከመሠረቱት አንዱ እንደሆነ የሚናገረው ጆሲ ከእስክንድር ጋር መቼም ሆኜ አላውቅም፣ እነ ድርሳን፣ እነ ሙሀባው፣ እነ ምሬ አንድ እንዲሆኑ ነው የምሠራው። እኔ ወታደር ነው የማሠለጥነው። የሚሠለጥነው ወታደር ደግሞ የሚዋጋው ለዐማራው ነው። ወሎ በቅርቡ አንድ ሲሆን የሚፈጠረውን ታየዋለህ ዘመዴም ብሎኛል ጆሲ። ዋናው ወንዙን የሚበክለው ቱቦ ከተደፋፈነ ዕዳው ገብስ ነው።
"…የዐማራ የትግል ወንዝ ከጠራ ለመላው ዐማራ ጤና በሽ ነው የሚሆነው። ለማ መገርሳ አስመራ ሂዶ ከኦነግ ጋር ተስማማሁ ብሎ ሲመለስ፤ የሰጠው ማብራሪያም መግለጫ አልነበረም። የጠየቀውም አልነበረም። የኦነግ የአዲስ አበባ አስተባባሪ የሆነው አብይ አህመድም ሲጠየቅ "ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ያለው የአፍ ወለምታ ነው።" በማለት እየሳቀ የተናገረው፣ ከወራት በኋላ ግን ስምምነታቸው ዐማራን በኦሮሚያ ምድር በእሳትም በጥይትም በመጨረስ ሱናሚ መዕበል ሆነው እንደነበር ሁሉም የሚያውቀው ነው። የኦሮሚያው አራጅ ማዕበል ያፈሰሰው ደም ሳይደርቅ ከአምስትና ስድስት ዓመት በኋላ አቢይ አመድና ሽመልስ አብዲሳ ሌላ ስምምነት ተፈራርመው የጫካውን አራጅ ማዕበል ወደ አዲስ አበባ እያጎረፈ እያየንና አየተመለከትን ነው። በወለጋ ዐማራ ላይ የተፈጸመውን ታሪክ በአዲስ አበባ ሕዝብም ላይ ሊደገም ከጫፍ ደርሷል ሳይሆን፤ በይፋም ተጀምሯል። መገናኛ አደባባይ ላይ ስምምነቱን በተግባር አሳይተውናል። የአዲስ አበባ ሕዝብም "ኦነግ እንዴት ትጥቅ ሳይፈታ ገባ? እንዴት በከተማ እየተኮሱ፣ እየገደሉ አለፉ? ወዘተ እያለ ሕግና ሥርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ እንደሚኖር ዜጋ በማስመሰል መመጻደቁን ትቶ ስለ ምልክቱ ኦሮሙማውን አመስግኖ ራስን ከማዕበሉ የመከላከል ዝግጅቱን ከወዲሁ ቢጀምር ይሻለዋል። ቢያንስ የዐማራ ክልሉ የዐማራ ፋኖ ወንዝ ጥርት እያለ በመምጣቱ አዲስ አበቤም ለዐማራው ትግል ድጋፉን በተለያየ መልኩ በመስጠት የዐማራን ወንዝ ገባር ምንጮች ማጎልበት ይጠበቅበታል።
"…አሁን የሸዋው የትግል ወንዝ ነው የሚቀረው። እንደ ጎንደሩ የትግል ወንዝ በብዙ የተጎዳ፣ ብዙ ግም ቱቦዎች ቆሻሻቸውን ተረባርበው የለቀቁበት ነው የሸዋው የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝ። የጎንደሩ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ፣ ግንቦቴው፣ ባልደራሱና ግንባሩ፣ ዋን አዋራው በሙሉ ያለ የሌለ ኃይሉን አስተባብሮ እጅ እግሩን ያሰረው ነው የሸዋ ዐማራው የትግል ወንዝ። አሰግድ የተባለን መሪ አዋክበው ለገዳዩ ኦሮሙማ አሳልፈው የሰጡ፣ ሸዋን ለሁለት ከፍለው ያጫጩ፣ በአንድ ቤት ሌላ ደባል አባወራ አምጥተው በቤታቸው አለቃ፣ ናዛዥ፣ አዛዥ፣ ፈላጭ ቆራጭ አድርገው የሾሙ። እንደ ንጉሥ መሆን ሲገባቸው እንደ ገረድ፣ እንደ አሽከር ራሳቸውን የቆጠሩ፣ ሸዋን ያመነመኑ፣ ያኮሰመኑ ገተቶች የተፈጠሩበት ነበር የሻው የትግል ወንዝ። የሸዋ የትግል ወንዝ ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ አፄ ዳዊት ከተማ፣ ወደ ምኒልክ መናገሻ እንዳይፈስ ደንቃራ የሆነ ቆሻሻ የተከመረበት ነበር የሸዋውም የዐማራ ፋኖ ወንዝ። አሁን ግን ምንም አማራጭ ስለጠፋ፣ የገንዘብ ምንጩም ስለደረቀ፣ አስመስሎ መኖርም ስላልተቻለ፣ የግድ አንድ ከመሆን በቀር ሌላ አማራጭ የለውም። ቢሆንም የሸዋው አንድነት ጥንቃቄ ይፈልጋል። እነ ኢንጅነር ደሳለኝ በጣም ብልህ፣ አርቆ በማሰብ፣ አስሬ ለክቶ አንዴ በመቁረጥ ላይ እንዲያተኩሩ እመርጣለሁ። በተለይ በብዙ ተፈትነው የወደቁ፣ ሃይማኖት ያላቸው የማይመስሉትን የእነ መከታውን ቡድን በብዙ ጥንቃቄ ዓሣን መብላት በብልሃት እንዲሉ አበው በጥንቃቄ እንዲይዙት እመክራለሁ። በቀደመው ጊዜ ስላየኋቸው ቀኝ ትከሻዬን ነው የሚሸክኩኝ። ለማንኛውም ወዳጄ ከጥንቃቄ ጋር እንደ ጎንደር ሁን። አንድ ሁንና ወንዝህን ከብክለትም ከበካዮችም በጊዜ ታደግ። አከተመ።
"…ተወዳጆች ሆይ…! ርእሰ አንቀጹን ካነበባችሁ በኋላ ሳምንታዊው የቲክቶክ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በዐማራ የትግል ወንዝ ጥራት ዙሪያ እየተወያየን እናመሻለን። አስተያየት ለመስጠት ተዘጋጁ።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 1/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርእሰ አንቀጽ"
"…በዐማራው ሕዝብ እና በኦሮሙማው አገዛዝ መካከል የተጀመረው ዓመት ከመንፈቅ የሆነው ጦርነት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ተላላኪ፣ አሽከር፣ ገሌውንና ገረዱን ብአዴንን ተማምኖ በሳምንት ውስጥ ቀበቶውን አስፈትቼ፣ ሱሪውን አስወልቀዋለሁ ብሎ ዝቶ እየፎከረ ልምጭ፣ አለንጋ ይዞ እያስፈራራው የሚቀጣው ሕፃን ልጅ ይመስል እተቆጣ የዘመተበትን ታላቁን ዐማራ እንኳን በሳምንት ውስጥ ቀበቶውን ሊያስወልቀው፣ ሱሪውንም ሊያስፈታው ይቅርና ራሱ ቀበቶውንና ሱሪውን እያወለቀ እጅ መስጠትን ሥራው አድርጎ የማያልቅ የኦሮሞና የደቡብ ልጆችን እየገበረ ጦርነቱ ቀጥሏል። አርጩሜ፣ ልምጭ፣ አለንጋ ይዞ በማስፈራራት አንበረክከዋለሁ ብሎ የነበረውን ዐማራ አሁን በጦር ጀት፣ በሂሊኮፕተር፣ በድሮን፣ በታንክ፣ በሞርታር እና በጀነራል መድፍ ጭምር የታገዘ ውጊያም እያደረገ ዐማራን ንቅነቅ መድረግ ሳይቻለው ቀርቷል። በሳምንት እፈጽመዋለሁ ብሎ ዝቶ የገባው ሶዬ ይኸው ዓመት ከመንፈቅ ፈጅቶበትም መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር አጥቶ ተጨንቋል። መሬት ላይ ያለው ትንቅንቅም ከምንጊዜውም በላይ ከፍ ብሏል። ከብዷልም።
"…ሲጀመር እንደ ደራሽ ጎርፍ አሰሱም፣ ገሰሱም፣ ባንዳውም፣ ብአዴኑም፣ ፀረ ዐማራውም፣ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላውም ስኳድ፣ የአገው ሸንጎውም፣ ግራ ቀኝ የተጋባውም፣ ቅንጅቱም፣ ግንቦቴውም፣ ባልዲራሱም ሁሉ ግርር ብሎ የገባበት የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝም አሁን ከቆይታ ብዛት ደራሽ ጎርፉ እያለፈ ጥርት ወዳለ ወንዝ እየተቀየረ መጥቷል። ጥንቡ፣ ቆሻሻው፣ ላስቲክ ፕላስቲኩ፣ ግንዱ፣ የደፈረሰ ጭቃው፣ አፈሩ፣ ቅጠላ ቅጠሉ ሁሉ አሁን ወንዙ ሲረጋጋ ጥግ ጥጉን እየያዘ የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝ እንደ ሰማይ የጠራ ኩልል ያለ የወንዝ ውኃ ሆኖ ለመጠጣትም ቢሆን የማያሰጋ ወደመሆን እየተሸጋገረ መጥቷል። አሁን የደፈረሰው እየጠራ ነው። አላሻግር ብሎ የነበረው አደገኛው የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝ አሁን ሁሉን አሻጋሪ እየሆነ መጥቷል። ለተመልካች፣ ለታዛቢ ሁላ የዐማራ ትግል ኩልል፣ ከሩቅ ጭምር ጥርት ብሎ መታየት ጀምሯል።
"…የዐማራ ፋኖ ትግል አሁን ተገማች እየሆነ መጥቷል። ማንም ሰው በጠራው የዐማራ ፋኖ ትግል የወንዝ ውኃ ውስጥ ስላለውው ቆሻሻና መልካም ነገር ከዳር ቆሞ ያለመነጽር ማየት እና መመልከትም ይችላል። ዕውር በደባሳ፣ በማሽተት ሁላ ማወቅ ይችላል። ስለወንዝ ውኃ ጥራት የማያውቁ ሁላ መናገር፣ መገመት ይችላሉ። የዐማራ የትግል ወንዝ ሃቅ ያለው ስለሆነ ዓለሙ ሁሉ በፈለገው መልኩ ተዟዙሮ ቢያየው ለመረዳት አይቸገርበትም። በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ ውስጥ ስላለው የዐማራ ፋኖ ወንዝ ሁኔታ ለመናገር፣ ሁሉም ሰው ወዳጅ ጣላት ሳይቀር መመስከርም ይችላል። በወንዙ ውስጥ ስላሉ አዞዎች፣ ጉማሬና ዓሣዎች፣ እንቁራሪቶችም፣ ትላትልም፣ የከበሩ ድንጋዮችም፣ ወርቅ እንቁዎችም፣ አሸዋና አፈር ጭምር አደገኛው ጎርፉ ስላለፈ አሁን ሁሉ ማየት ይቻለዋል። ትግሉን ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ አሁን አስቸጋሪ፣ አጠራጣሪ ሁኔታ የለም። ምንም የሚደረደር ምክንያትም የለም። ቢያንስ ያልጠራው፣ በስሱም ቢሆን እስከአሁን የደፈረሰው የወንዙ ክፍል በየት አቅጣጫና ክልል ውስጥ እንደሆነ ማንም ይቻላል። የትግሉን የወንዝ ሂደት የሚከታተል ማንኛውም ሰው መገመትም ሆነ በድፍረት መናገርም ይችላል። የጎንደር ወንዝ፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ የትኛው የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝ ነው እስከ አሁን ያልጠራው? እስከአሁን የቆሸሸው? ጭቃ፣ አፈር፣ ጥንብና ግንዲላም የሚገማሸርበት ብሎ ማየት ይቻላል። የትኛው ወንዝ ነው እስከአሁን ለዐማራቅ ጤና የነሳው? ጭንቀት፣ ስጋት የሆነው? ለመጠጥም፣ ለመታጠብም፣ ለመሸጋረም አስቸጋሪ የሚሆነው የቱ ነው ብሎ ማንም ሰው ማየትና መለየት ይችላል።
"…አሁን ሁሉ ነገር ቁልጭ ብሎ ወጥቷል። ፍጥጥ ያለ ነው። ይሄን መደበቅ አይቻልም። የወንዙ አደፍራሾችም በስም ጭምር ተለይተው ታውቀዋል። ሰፈር፣ ቀበሌ፣ ወረዳቸውም ሁሉ ታውቋል። የዐማራ የጠራ የትግል ወንዝ ውኃ ውስጥ ሽንት ቤት መጸዳጃቸውን በቱቦ የአገናኝተው ወንዙን የሚበክሉ ግለሰቦች በስም፣ በአድራሻም ታውቀዋል። ተለይተውም ተይዘዋል። እነዚህ ግማታም፣ ጥንባታም፣ ክርፋታም፣ ሸታታ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ወደ ዐማራ ትግል የጠራ ወንዝ ውስጥ የሚለቁትን ቆሻሻ ቱቦ ከወዲሁ በቶሎ ለመድፈን ዐማራ የሆነ ሁሉ መረባረብ መጀመሩም እጅግ ተአምር የሚባልም ነው። ዐማሮች ለወንዛቸው ትኩረት ሰጥተው በድፍረት መንቀሳቀስ መጀመራቸው በሚገርም ሁኔታ የትግሉን ወንዝ ከግማት፣ ከክርፋት፣ ከጥንባት እየገላገሉት መጥቷል። ደራሽ ጎርፉ ሲሰክን የዐማራ የትግል ወንዝ ቀርበውም፣ ከርቀትም ሲያዩት መንፈስን የሚያረካ፣ ቢቀርቡት እና ቢሻገሩት የማይገፋ፣ የማይጥል፣ ቢታጠቡበት የሚያነጻ፣ የሚያጠራ፣ የሚያሳምር፣ ቢጠጡት የሚያረካ የሚያለመልም፣ እረፍት እና ጤናም የሚሰጥ እየሆነ መጥቷል። ከአሁን በበለጠ መልኩ በቴሌቭዥን፣ በዩቱዩብ፣ በቴሌግራም፣ በቲክቶክና በፌስቡክ፣ በራምብልና በትዊተር የሚለቀቅን ግም፣ ጥንብ ቆሻሻ መድፈን ከተቻለ የዐማራ ፋኖ ትግል በቅርቡ ውጤቱን የምናየው ይሆናል።
"…የዐማራ ፋኖ የጠራው የወንዝ ውኃ የመሰለ ትግል አሁን ትግሉን ጠልፎ በመስኖ ወደ ተለያዩ እርሻዎች በመውሰድ አትክልቶችን፣ እርሻዎችን ማስፋፋትም ይቻላል። በወንዙ ውኃ የሚበቅለው እህልም ሆነ አትክልት ለሰው ልጅ ጤና ነው የሚሆነው። ከሽንት ቤት በሚለቀቅ በሠገራና በሽንት በጨቀየ ወንዝ የሚመረት ምርት ስላልሆነ አትክልቱም፣ ሰብሉም ለጤና ተስማሚ ነው የሚሆነው። እንደዚያ ነው። ጀርም የለው፣ ቫይረስ የለው፣ ወላ ሃንቲ ነገር የለውም። የዐማራ ፋኖን የጠራ ወንዝ ለማደፍረስ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። የዐማራ ወንዝ ጠባቂ ገበሬዎች እንቅልፍ አጥተው ለዐማራ ህልውናው የሆነውን የትግል ወንዝ በንቃት እየጠበቁት ነው እንጂ ጠላትስ፣ ምቀኛስ ከሩቅ ጭምር ሳይመጣ በውስጥ ያለው ጠላት አይተኛም ነበር። እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ላይ ግን የዐማራ ወንዝ ጥራት ጠባቂዎች እንደ በረዶ ነጭ፣ እንደ ሰማይ ኩልል ብሎ የጠራ ወንዛቸውን ከውስጥም ከውጭም በሚመጣ ጠላት እንዳይበከል እያደረጉ ያለው ተጋድሎ እጅግ ይበል የሚያሰኝ ነው።
"…የጎንደር ከጎንደር ይነሣ የነበረው የዐማራ የትግል ወንዝ ከሁሉ በከፋ መልኩ የተበከለ ሆኖ ጎንደሬ ብቻ ሳይሆን መላው ዐማራ ጤናው ታውኮ ነበር። እግዚአብሔር ይመስገንና ሰሞኑን ግን ይሄ እስከዛሬ ለዘመናት ተበክሎ ለጎንደርም ለዐማራም ጤና ጠንቅ የነበረው የዐማራ የትግል ወንዝ እየጠራ መጥቷል። አራት አምስት ስድት ሰባት ስምንትና ዘጠኝ አስር ትንንንሽ ቦታ ድብልቅልቁ ወጥቶ የነበረው የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ አሁን እየጠራ መጥቷል። ምስጋና ለጎንደር ዐማራ አባት አርበኞች ይግባቸውና በብልሃት፣ በጥበብ፣ በዘዴ፣ በሃይማኖት፣ በጸሎት ተግተው የመከሩበት፣ የደከሙበትም ወንዙን የማከም ተግባር ውጤታማ በመሆኑ፣ የጎንደር ዐማራን በሙሉ ሰብስበው፣ ወደ ወንዙ የገባውን ቆሻሻ መነሻ ምንጩን ለይተው፣ የቆሻሻውን ቱቦ ሁሉ ደፋፍነው አሁን የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ ጥርት፣ ኩልል ብሎ እንዲፈስ አድርገዋል። ለጎንደር አባት አርበኞች በእውነት ክብር ይገባቸዋል። ከዚህ በፊት ወደ ጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ ተቀላቅለው ገብተው የማኅበረሰቡን ጤና ሲያውኩ የቆዩ ቫይረሶች፣ አልቅትና አልጌዎችም በጎንደር ዐማራ ፋኖ ተጋድሎ ሰሞኑን ብቻ ሻንቆ፣ ሻንቆ የሆኑቱ ፈንገሶች…👇① ✍✍✍
“…ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።” ማቴ 23፥4
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
ለትኩስ እና ወቅታዊ የዐማራ ፋኖ መረጃ የቻናል ጥቆማ…!
"…የዛሬው የጎንደር ዐማራ ፋኖ አንድነት የተበሰረበትን ይህን የጋዜጠኛ ሞገሴ ሽፈራው የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ተከታተሉት።
ቴሌግራም
/channel/MogesieShiferaww
ዩቲዩብ
haddismedia1?si=yOfu4ldD4DCUOFYT" rel="nofollow">https://youtube.com/@haddismedia1?si=yOfu4ldD4DCUOFYT
• ተከታተሉት…
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ምሽት 1:30 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• የዛሬውም ደግሞ ልዩ ብቻ አይደለም። ድንቅም እንጂ። የጎንደር ፋኖ መግለጫንም በቀጥታ ተከታተሉን።
• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/bn4TVVNYJy8
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሻሎም…! ሰላም…!
“…እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8፥44
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…አላችሁ አይደል…?
• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።
"…አለን አለን ዘመዴ እያላችሁ በዚያውም እግረመንገዳችሁንም በዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ላይ የራሳችሁን አስተያየት እየሰጣችሁ ጠብቁኝ። እኔም ከቀሲስ ሳሙኤል ጋር የማቀርበውን የዕለተ ሐሙሱን የኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ መርሀ ግብሬን እንደጨረስኩ በቀጥታ ወደ ቴሌግራም መንደሬ ስመለስ አየዋለሁ። እኮመኩመዋለሁ።
• ሻሎም…! ሰላም…!
👆③✍✍✍ "…እኔ ከሠራሁት እስከዛሬም ከፈጸምኩት ተጋድሎ ከእነ በጋሻው ተሃድሶ፣ የእነ ሽመልስ ኦሮማራ ብትንትኑን ከማውጣት ቀጥሎ በከፍተኛ ኩራት ደረቴን ነፍቼ የምመሰክረው ነገር ቢኖር "የዳያስጶራ ዶላር ወደ እስክንድር ቋት መፍሰሱን እንዲያቆም ያደረግኩበት ተጋድሎ ነው" አዎ በዚህ አድርጌ እንዴት እንደምኮራ አትጠይቁኝ። ነገሮች ሳይጠሩ ዶላር የሚባል ነገር ወደ መሬት እንዳይወርድ፣ በእስክንድር ስም ልመና እንዲቆም፣ በእነ ሀብታሙ አያሌው፣ በኢትዮ 360 በኩል ምንም ነገር ሳንቲም ዱዲ ጢና እንዳይዋጣ፣ ለአበበ በለውም አምስት ሳንቲም እንዳይሰጠው፣ ለአዲስ ድምፅ፣ ለዋ የአበበ በለው ካዝና መሙያ መዋጮ እንዳይዋጣ ማድረጌ ነው የዐማራን ትግል ሾተላዩን የነቀለለት። ፋኖ እንደ አትክልት ነው። ዶላሩ እንደ ወንዝ ነው። እነ እስክንድር፣ ሀብታሙና አበበ በለው፣ ፓስተር ምስጋናው ፋርማሲስት አምሳሉ ደግሞ ግድብ ናቸው። ወንዝ ዶላር ፋኖ አትክልት ጋር እንዳይደርስ ገድበው የፋኖ ትግል እንዲደርቅ፣ እንዲጠወልግም ለማድረግ የሞከሩ የሰይጣን መልእክተኞች፣ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች። አዎ እነሱ ነበሩ ግድብ ሆነው ያስቸገሩት። ፋኖ ግን ወንዝ ዶላር ስለተገደበ መጽደቅ፣ መለምለም፣ ፍሬ ማፍራቱን አላቆመም። ወንዙ ቢገደብ ባንጠለጠለው መስቀል፣ በሚደግመው ዳዊት፣ በሚቀራው ቁርዓን ወደ ፈጣሪው በመጸለይ በፈጣሪ ቸርነት በፈጣሪ ዝናብ ለመለመ። ጸደቀ፣ አበበ፣ አፋራ። እኔ ያደረግኩት ለወንዙ ገንዘብ ዶላር የሚያዋጡትን ምንጮች ነው ያደረቅኩት። ዶላር ወንዝን ወንዝ ያሰኙት ትናንሽ የዶላር ምንጮች ናቸው። ከእነ እትዬ ስርጉት፣ ከእነ ጋሽ አበራ፣ ከእነ ወጣት ቻሌ፣ ከእነ ወሪት ትእግስት በ50፣ በመቶ የሚመነጭ ዶላር፣ እሱነው ገባር ሆኖ ለግድብ የበቃ ወንዝ ዶላር የሆነው። እሱን ነው እኔ ዘመዴ እየተሰደብኩ፣ እየተረገምኩ አናቱ ላይ ቆሜ ያደረቅኩት። አሁን ዶላር ስለሌለ የዶላር ዕዝ ይፈርሳል። ገንዘብ ብሎ የገባ ትግሉን ትቶ እንደ ጃል ሰኚ ወደ ላከው አገዛዝ በውርደት ይገባል። ይኸው ነው። ነጋዴው ሰሎሞን ያለውም እሱን ነው። ብሩ ቢለቀቅልን የጎንደርን አንድነት አፈራርሰዋለሁ።
"…ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርገው መንፈስ፣ ዐማራን እንዲያሸንፍ የሚያደርገው መንፈስም መነሻው ከጎንደር ነው የሚል ጽኑ ዕምነት ነው ያለኝ። ኢትዮጵያን ለማፍረስም ድጅኖው፣ ፈንጂው፣ የሚቀበረው ጎንደር ላይ ነው። ኢትዮጵያን ያፈረሱ ሰይጣናት መርጠው ለጋብቻ ሴት የሚያመጡት ከጎንደር ነው።
• ለመንግሥቱ ኃይለማርያም - ውብአንቺ ቢሻውን (የጎጃም ዐማራ ናት የሚሉ አሉ)
• ለመለስ ዜናዊ - አዜብ መስፍን (ወልቃይት የጎንደር ዐማራ ናት)
• ለአብይ አህመድ - ዝናሽ ታያቸውን (ጎንደር ዐማራ)። የለገሰው የጎንደር እና የጎጃም ምድር ነው። ጎንደር እርስ በራስ ማባያ፣ ማነቂያ እና መሰልቀጫ የነበሩት የጎንደር ሴቶች ናቸው። ተመልከት ኦሮሙማውም ሥልጣኑን ለማፅናት፣ ዐማርን ለማዳከም ብሎም ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ከደርግና ከህወሓት በተማረው መሰረት የአፄ ቴዎድሮስ ሀገር ጎንደርን ማድከም ዋነኛው ስትራተጂው አድርጎ ነው የተነሣው። እስክንድር ብትሉት ደቡብ ጎንደር ነው። ሰሜኑና ደቡቡን ከሁለቱም ከሃዲ፣ ከሃዲው ተመርጦ ነው የዐማራ ትግል ማነቆ ውስጥ እንዲገባ፣ እንዲቀረቀር የተደረገው። ተመልከት ሚዲያው በጎንደር የትግሬ ዲቃሎች የተሞላ ነው። የልቅሜ ኪዳኑ ልጅ አበበ በለውን ተመልከት፣ የጣና ቲቪን ርምስምሶች የፓስተር ምስጋናውን ጅሎች ቁጠር፣ እነ በረደድ፣ እነ ዶር ደረጄ፣ እነ መሳፍንት ባዘዘው፣ እነ ሰሌ ባለ ሃውልቷን ተመልከት፣ እነ ሚኪ ጠሽ፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ መማር አለባቸው ወዘተ በሙሉ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎንደር ስብስብ ከየት እንደተሰባሰበ ተመልከት። በዘመነ ካሤ ሰበብ ፀረ ጎጃም ሁላ በሚዲያ በኩል እንዴት እንዳሰፈሰፈ ተመልከት። ሁላቸውም ግን ቋንጃቸው ነው የተሰበረው።
"…አገዛዙም ሆነ አገዛዙን የቀጠረው የዓረቡና የምዕራቡ ዓለም በሙሉ ጎንደርን በሚስት፣ በሆድ አስረው ሲጠብቁ ጎጄ ሳተነው የበላይ ዘለቀ ልጆች ከሰማይ ይሁን ከምድር ሳይጠበቁ ዱብ አሉ እንደ በረዶ፣ በልጅነቱ በረሃ ለምዶ እያለ እየፈኮረ። የጻድቁ ላሊበላ፣ የንጉሥ ሚካኤል የቤተ ዐምሓራ የወሎ ልጆችም ከተፍ አሉ። ከሸዋም የእምዬ ምኒልክ ልጆች ብቅ ብቅ አሉ፣ ወሎም ሸዋም የሚላስ ሚቀመስ አልሆን አለ። አሁን ትልቁ ሳንካ የነበረው የጎንደር ነገር መልክ መልክ እየያዛ ሲመጣ ኦሮሙማው ደንብሮ ሸኔን አዲስ አበባ አስገባው። ከዚያ ከዚህ ተራወጠ። አበደ በሉት። ትናንት ምሽት አበበ በለውን፣ ሰሞኑን ሀብታሙ አያሌውን ያየ የእብደቱ መጠን ምን ያህል ጣሪያ እንደነካ ይረዳዋል። ይገባዋልም። የጎንደር እና የወሎ ነገር ሙሉ ለሙሉ ሲጠራ ብሎም የሸዋ ነገር መልክ ሲይዝ ደግሞ ገና ገና ጉድ እንሰማለን። አሁን መደረግ ያለበት አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው። የጎንደር ፋኖ ከእስክንድርን ነጋ የባርነት ቀንበር፣ ከአሽከርነቱ ወጥቶ አንድነቱን ማፅናት። ከተቻለ ደረጄ በላይን በካህን በጳጳስ አስመክሮ ከወንድሞቹ ጋር እንዲሰለፍ፣ የአባቶቹን ቃል እንዲሰማ ማድረግ። እነ አርበኛ ሰሎሞን አጠናውን ግን ጆሮ አለመስጠት። አለቀ።
እንደ መዝጊያ…
"…በዚህ አጀንዳ ተጠምደን ዋናውን የቀንዱን ቦለጢቃም መዘንጋት የለብንም። ስለ ሶሪያ እየሰማን፣ እያየን ስለ ኢትዮጵያም መዘንጋት የለብንም። አሁን ፋኖ እየጠነከረ ሲመጣ አብረው የሚመጡ ነገሮችንም በትኩረት ማየትና መከታተል ይገባል። የዐማራ አንድነት፣ የፋኖ ምት ሲበረታበት…
• ህወሓት ወረራ ትጀምራለች። ተኝተው የከረሙ ትግሬዎች በሙሉ ድንገት ብትት ብለው ተነሥተው ግርር ብለው በመምጣት የሻገተውን የፕሪቶሪያ ስምምነት አዋራ አራግፈው ፕሪቶሪያ፣ ፕሪቶሪያ የሚሉ አጀንዳዎችን ማጮህ ይጀምራሉ።
• ሀ ገደሉ የበሻሻው አራዳ አረመኔው አቢይ ወይ ከኤርትራ ጋር አልያም ከሌላ ጎረቤትጋ ጦርነት ልገባነው፣ ወደብ ላገኝ ነው በማለት በበቀቀኖቹ በኩል አጀንዳውን ያራግቡታል።
"…ነገ ጠዋት ይቀጥላል…
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርእሰ አንቀጽ"
"…አሁን እኔ ስለ ሰለሞን አጠና እና ስለ እስክንድር ነጋ፣ ስለ እነ ጌታአስራደ እና ስለ ፋሕፍዴን፣ ስለ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም እና ስለ ጣና ቴቪ፣ ስለ ሀብታሙ አያሌው አፍራሳው ኢትዮ 360 እና ስለ የፖለቲካው ቅማንት የልቅሜ ኪዳኑ ልጅ ስለ ፀረ ዐማራው ስግብግብ ዳንኪረኛ የዐማራ ትግል ገዳይ ስለ ማይሙ አበበ በለው እስክስ፣ ስለ ግምባሩ፣ ድርጅቱና ስለ ፋርማሲስት ዶፍቶር አምሳሉ፣ ስለ መሃይምናኑ አበበ ጢሞና መከታው ማሞ፣ ስለ ኮሎኔል ሙሀባው እና ስለ ኮሎኔል ታደሰ፣ ስለ ድርሳን ብርሃኔና ስለ አርበኛ የራስ ደረጄ በላይ፣ ስለ ጎንደር ስኳድ፣ ስለ ጎጃሙ አገው ሸንጎ የምጽፍበት፣ የማወራበት ሰዓትም፣ ወቅትም አይደለም። ከበቂ ጊዜ በላይ ወስጄ አውርቻለሁ አሁን ሥራቸው ያውጣቸው።
"…ትናንት አንድ የድምፅ የሰሎሞን አጠናው እና የእስክንድር ነጋ የስልክ መረጃ ወጣ ተብሎ ባልሣሣት ከ700 ሰዎች በላይ ናቸው "አልሰማህ እንደሆን? ዘመዴ አልደረሰህ እንደሆን በማለት የዐማራ ቦለጢቃ፣ የዐማራ ፋኖን ትግል ቀልባሽ ኮንትሮባንዲስት ነጋዴዎቹን የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የሻይ ቀቃዩን የአርበኛ ሰሎሞን አጠናውን የክፉ ሴራቸው ውጤት የሆነን የድርጅቱን ሰዎች አረመኔአዊነትም የሚያሳይ፣ የሚያጋልጥም፣ በተለይ የእስክንድር ነጋን ጭንብሉን በኃይለኛው የገላለጠውን የስልክ ቅጂ ሲልኩልኝ ያመሹት። እንደ ጉድ ነበር ሲዥጎደጎድልኝ ያመሸው። እኔም ለአንዳቸውም ምላሽ ሳልሰጥ ነው አምሽቼ የነጋልኝ። በተለይ ለእኔ በወር 10 ዶላር በፔይ ፓልና በዶነር ቦክስ እየደገፉ የነበሩና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "እስክንድርን ነካህብን፣ ተቸህብን፣ ስኳድን አስቀየምክብን፣ እኛንም አስቀየምከን" ስለዚህ ቻዎ ከዚህ በኋላ ዱዲ ጢና አምስት ሳንቲም አንሰጥህም በማለት ከድጋፉ የተለዩኝ እና በ10 ዶላር ድጋፍ እንደ ባርያ የገዙኝ፣ እንደ አሽከርም እንደ ገረድም የቀጠሩኝ ይመስላቸው የነበሩ ምስኪኖች "ይቅርታ ዘመዴ" ሲሉኝ ነበር ያመሹት። የሚገርሙ እኮ ናቸው። በዚህ ጉዳይ የነገውን ርእሰ አንቀጼን ሙሉ በሙሉ "እኔ ዘመዴን ማዕከል ያደረገ ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅና እውነታውን በተመለከተ ለታሪክ የምታስቀምጡት ጦማር አዘጋጅላችኋለሁ። የነገ ሰው ይበለን። ለዛሬ ወደ ዛሬው ርእሰ አንቀጼ ጦማር ልግባ።
"…መልካም እሺ ወደ ዛሬው ርእሰ አንቀጻችን ስንመለስ በስልክ ቅጂው ላይ ዛሬ ብዙም አልሄድበትም። እሁድ በቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ነክሼ አደማዋለሁ። ለዚህ ነው እኔ አስቀድሜ የጎንደር ጉዳይ፣ የስኳዱ ጉዳይ እጅግ አደገኛ ነው። ማንም ሊነካው አይደፍርም፣ የጎንደርን እስኳድ አማኑኤል ካልረዳህ በስተቀር፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የቅዱሳን ምልጃ፣ የመላእክት ተራዳኢነት ካላገዘህ በስተቀር አይደለም በግለሰብ ደረጃ ልትጋፈጠው በቡድን፣ በመንግሥት ደረጃ የምትጋፈጠው አይደለም። እናም የመጣው ይምጣ ብዬ ገዳማውያን አባቶቼን ጸሎት አስይዤ፣ በል አሁን እንደ ሰሞሶም ኃይል፣ እንደ ሰሎሞን ጥበብ ተሰጥቶኃል፣ እንደ ዳዊት ጠጠር ብዕርና አንደበትህን ይዘህ ጎልያድ ስኳድ ላይ ዝመት ከተባልኩ በኋላ ነው ብቻዬን የገባሁባቸው። አይታችኋል እስክንድር ነጋን የተቸሁ ቀን የተንጫጫብኝን ሕዝብ፣ አይታችኋል ኢትዮ 360ን፣ እነ ሀብታሙ አያሌውን የተቸሁ ቀን የተነሣብኝን ሕዝብ፣ እነ ባህርዳር ዊክሊክ እንኳን ነበሩ እኮ ዛሬ ከኔ ብሰው ሊገኙ በወቅቱ ጓ ያሉብኝ። ምድር ነበር የተደበላለቀው። ኤልያስ ክፍሌ ሆኖ ነው እንጂ እንደ እስኳድ አነሣስ እኮ መደበቂያ ነበር የሚያሳጡት። ስኳድ የሀሰት አባት ስለሆነ በጎንደር ፋኖዎች ማኅተም መረጃ ቲቪን ከሩዋንዳው የዘር ቀስቃሽ ሚዲያ ጋር አጃምለው መግለጫ በፓስተር ምስጋናው በኩል በማውጣት ነበር ክፋታቸውን የገለጹት። ርብርባቸው አደገኛ ነበር። ነገር ግን የጎንደርም፣ የዐማራም፣ የኢትዮጵያም ትንሣኤ ስለተቃረበ በአባቶች ጸሎት ድባቅ ሊመቱ ሴራቸውም ሊከሽፍ፣ እነርሱም እንደ ጉም ሊበታተኑ ችለዋል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…አዎ እኔ ዘመዴ ተጠላሁበት፣ ሰው አጣሁበት፣ ተቅማጥ የሚያመጣ ስድብ ተሰደብኩበት፣ ተዋረድኩበት፣ የዛቻ መዓት ተዥጎዶጎደብኝ እንጂ እነሱማ ከመድቀቅ፣ ከመውደቅ፣ ከዐማራ ትግል በውርደት መውጣታቸው አይቀርላቸው እንደነበር አስቀድሜ ዐውቃለሁ። እስክንድር ነጋ እና ፋሕፍዴኖች ከጎንደር ትግል ላይ እጃቸውን ካነሡ አይደለም ጎንደር፣ አይደለም ዐማራ፣ አይደለም ኢትዮጵያ ምሥራቅ አፍሪካ ይፈወሳል። ዋናው ጎንደር ነው። ጎንደርና ሸዋ። ሁለቱ ከተፈወሱ ትንሣኤው ቅርብ ነው። አገዛዙም፣ ምዕራባውያንም፣ አረቦቹም እየሠሩ ያሉት ሁለቱ ላይ ነው። ጎንደርና ሸዋ ላይ። ጎጃም በጣጥሶ፣ ወሎ 95% ከመቶ ወደ አንድነት መጥቷል። ጎንደር ጥቂት ነው የቀረው። የምወደው፣ የማከብረው፣ አርበኛ የራስ ደረጄ በላይ ከተመለሰ፣ ወንድሞቹን ከተቀላቀለ የጎንደር ሴራ ያበቃለታል። ሻይ ቀቃዩ፣ በፍቅረ ንዋይ ያበደው አርበኛ ሰሎሞን አጠናው ድሮም ነጋዴ ነበር ለጎንደር የሚፈይደው ወላሃንቲ ነገር የለም። እንዲያውም ሰሎሞን አጠናው እና አበበ ጢሞ በናሁሰናይ ግድያ ጉዳይ ወደፊት ጥያቄ አቀርብላቸዋለሁ። ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ። አዎ የናሁሰናይ ግድያ ገና ሌላ የሚያመጣው ብዙ መዘዝ አለ። ሰሎሞን አጠናውም፣ አበበ ጢሞም ደግሞ ከእስክንድር ነጋ ሥር መሆናቸውን መዝግቡልኝ። መዝግባችሁ ያዙልኝ። ዛሬ አልሄድበትም።
"…እመኑኝ ከጎንደር ደረጄን መመለስ፣ ከወንድሞቹ ጋር አንድ ማድረግ ከተቻለ፣ ደግሞም ይቻላል ባይ ነኝ። ሰሎሞን አጠናውና ጌታ አስራደ ምንም ማለት አይደሉም። ከጎንደር ትግል ኢትዮ 360 እነ ሀብታሙ አፍራሳ ከወጡ። ስኳዶቹ የደቡብ ጎንደር የዐማራ ነቀርሶቹ እነ በለጠ ካሣ፣ እነ አያሌው መንበር፣ የሰሜን ጎንደሮቹ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ እነ እስክስ አበበ በለው፣ እነ ፓስተር ምስጌ ከወጡ የጎንደር ዐማራ አንድነት ዕውን ከሆነ በቃ ሁሉ ነገር የቤት ሥራው እንደተጠናቀቀ ቁጠሩት። ዋነኞቹ የዐማራ ትግል መርገምቶች እነዚህ አካላት ናቸው። በደቡብ ጎንደሬነት የመሸጉት እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ ፋርማሲስት አምሳሉ፣ እነ አያሌው መንበር የዐማራን ትግል ማቡካት ከተከለከሉ፣ ከታገዱ ጎንደር ይፈዋሳል። እመኑኝ የዐማራ ትንሣኤ በቅርቡ ይሆናል። እነዚህ ናቸው ጎንደርን አንቀው የያዙት።
"…በሸዋም በኩል ደግሞ ደፍሬ እነግራችኋለሁ የእነ መከታው ማሞ፣ የእነ አበበ ጢሞ የእስክንድር ነጋ አሽከሮች አበበም ወደ ጥበቃነቱ፣ መከታውም ወደ በርበሬ ንግዱ እንዲመለሱ አድርጎ ሸዋን የሸዋ ልጆች እንዲመሩት ከተደረገ የሸዋም ጉዳይ በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል። የጎንደሩ ስኳድ እስክንድርን ወደ ሸዋ አምጥቶ ሸዋ አስቀምጦ የሸዋን ትግል እጅ እግሩን ያሰረው እንዲሁ በአጋጣሚ አይምሰላችሁ። ቀመር ተሠርቶ ነው። ሒሳብ ተሠርቶ። ሸዋ ለአዲስ አበባ ቅርብ ስለሆነ ከጎንደር ተነሥተን እስክንመጣ ቤተ መንግሥቱ ይያዝብናል በሚል ቀሽም የትግሬ ዲቃሎች፣ ዐማራ መሳይ አሞሮች ሴራ ተቀነባብሮ የተቀመረ ቀመር ነው። እነዚህ መሰሪዎች ከጎንደር ያሳሳቱት በእምነት ስም ገብተው ጋሽ መሳፍንትን ነበር። ዶላር እና መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ሄዶ ነው እስክንድር የሸወዳቸው። የጎንደሩ በጎንደር ገዳማውያን አባቶች ጸሎት፣ በእነ ጋሽ መሳፍንት ጸሎት ፍርስርሱ ወጥቷል። የሸዋውም በዚያው መልክ የገባ ቢሆንም በሸዋ ሽማግሌ ስለጠፋ፣ የሃይማኖት አባት ድርቅም ስለተከሰተ እንደጎንደሩ መከታውና አቤ ጢሞ…👇① ✍✍✍
“…ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1ኛ ቆሮ 5፥13
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
👆③ ✍✍✍ …ጭፍጨፋ ዕጣ ነው የሚገጥመው ብዬ አስባለሁ። ይሄን የሚያስቆም መለኮታዊ ጣልቃገብነት እንዲኖር አብዝቶ ካልተጸለየ በቀር የሚሰማ፣ የሚታየው ነገር እጅግ የከፋ ነው።
"…አሁን ላይ ዛሬም ሶሪያ ድብልቅልቋ ወጥቷል። የበቀል ግድያ በየቦታው ተጀምሯል። በአላሳድ አገዛዝ ውስጥ ሚኒሻ ነበርክ፣ አድማ ብተና ነበርክ፣ ሰልለሃል፣ በካድሬነት አገልግለሃል እየተባለ በየሰፈሩ ሰው እየተጎተተ በሃላል እየተገደለ ነው። በበቀል የነደዱት ከዚህ በፊት ቆስለው ሆስፒታል የተኙ ጓዶቻቸውን የረሸኑ የወደቀው ሥርዓት አገልጋይ ቆስለው በየሆስፒታሉ የተኙትን ሳይቀር በየሆስፒታሉ እየገቡ የቆሰሉ የአድማ ብተና፣ መከላከያና ሚኒሻ የነበሩትን አልጋቸው ላይ እንደተኙ እየረሸኗቸው ነው። ሬሳዎች ሳይቀር በመኪና በሞተር ከተማ ለከተማ የሚጎተቱ እየታዩ ነው። ሁሉንም ቪዲዮዎች ብለጥፍላችሁ ትደነግጣላችሁ። በኢትዮጵያስ በተለይ ወልድያ ከሆስፒታል አውጥተው የረሸኑትን ያን ፋኖ የሚያስታውስ፣ እስከአሁንም የሚንገበገቡ ነገ ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ መገመት ነው። በዘመነ ሥልጣንህ የጦርነት ሕግ ሳታከብር ቀርተህ የምትመካበት ሥርዓት ጥሎህ ኮብሎ ሲሄድ የሚጠብቅህ ሰይፍ የያዘ፣ በበቀል የነደደ ማኅበረሰብ ነው። እመኑኝ ነገም ከአገዛዙ ጋር ቂጥ ለቂጥ ገጥመው የሕዝቡን ስቃይ ያራዘሙ የዐማራ ካድሬና ባለሥልጣናትም ሆኑ የኦሮሞዎቹ አስጨፍጫፊ ጨፍጫፊ፣ አራጅ አሳራጁ ወንጀለኞች በሙሉ የሚጠብቃቸው ዕጣ ፋንታ ይሄው የሶሪያ ዓይነት ዕጣ ፈንታ ነው።
"…አዲሱ የሶሪያ ገዢ አልጁላኒ ለሁሉም ጠላቶቻችን ይቅርታ አድርገናል። የበቀል ግድያ አይኖርም ቢልም፣ ሕዝቡ ግን የደረሰበትን ያውቃልና ጥፋ ከዚህ እያለው ነው። ሕግ የት ያውቃሉና፣ በሕግ መቼ አስተዳደሩንና፣ በሕግ መቼ ዳኙንና፣ ከቀዬአችን፣ ከመንደራችን፣ ከርስታችን ሲያፈናቅሉን፣ ሀገር አልባ አድርገው ሀገር ለሀገር በስደት እንድንንከራተት ሲያደርጉን የኖሩት የምን ፍትሕ ነው የሚያስፈልጋቸው እያለ ነው ሕዝቡ። የደቦ ፍርድ የሚከሰተው በአንድ ሀገር ፍትሕ አፈር ከደቼ ስትበላ ነው። አሁን በየቤቱ እየዞሩ ካድሬዎቹን እየለቃቀሙ እዚያው ነው እየረሸኗቸው ያሉት። ይሄ የሶሪያ ዕጣ ፈንታ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ በሃገሬም እንዳይከሰት ስጋት አለኝ። በዐማራ ሞት ላይ የተሳለቁ፣ ያሾፉ፣ የዘበቱ በሙሉ የሚጠብቃቸው የውሻ ሞት ነው። ነገ አርበኛ ዘመነ ካሤ፣ ሀብቴ ወልዴና ባዬ ቀናው፣ ምሬና ኢንጂነር ደሳለኝ እንኳ እንደ አል ጁላኒ በቀል የለም ቢሉ እንኳ አሁን መድረሻ አጥቶ እሱ እየተራበ በራቡ ላይ እያሾፈ የሚጨፍረው፣ እሱ እየተገደለ በአስከሬኑ ላይ ቆሞ የሚደንሰውን አቃጣሪ ካድሬ ሕዝቡ የሚምረው አይመስልም። ይቅር ለእግዚአብሔር ከኢትዮጵያ ከጠፋ ቆየ። ታቦት ተሸክሞ፣ መስቀል ይዞ፣ ቄስና ሼክ አግተልትሎ ሄዶ እየፎገሩ ጀግኖችን ካስቀረጠፉ በኋላ ቀርቷል። አሿፊው፣ በስላቅ የሚናገረው፣ በሕዝብ በንፁሐን ደም የሚቀልደው አሁን የትየለሌ ነው። እናም ሕዝብ በሆዱ የያዘውን ይዟልና አይሰማውም። ደም በደም፣ ዘሩ የጠፋበት ሁሉ እንደ ሶሪያ እያወጣ በየመንገዱ ይደፋዋል። አቢይ አሕመድ ግን እኛን ትተህ ወዴት የሚሉ ጥቂት ደፋሮች ካልቀደሙትና ለሕግ ካላቀረቡት በቀር ለጊዜውም ቢሆን ወደ አለቆቹ ሀገር ወደ አንዱ ሀገር ሊያመልጥ ይችላል። ይብላኝ ለቀሪው ካድሬ።
"…ከራብ፣ ከማጣት፣ ከመቸገር ጋር ይሄ በስቃይ የሚኖር ሕዝብ ላይ በምቾት፣ በድሎት፣ እያላገጡ የሚኖሩ የሥርዓቱ አገልጋዮች የሚጠብቃቸው ቀላል ነገር አይመስለኝም። ጳጳስም፣ ሼክም፣ ፓስተርም የማያስቆመው ጥፋት ነው የሚፈጸመው። የሚበጀው ጥፋቱን ለመቀነስ ከወዲሁ ይሄን አረመኔ ሥርዓት መላ ማበጀት ነው። ተናግሬአለሁ። መዝግቡልኝ። አሁን የተናቀው፣ የተጣሰው፣ መቀለጃ የሂነው ፍትሕ፣ ሕግ፣ ሞራል የሚባለው ነገር የማይሠራበት ዘመን እየመጣ ነው። በሕግ አምላክ ስትባል በሕግ ያሾፍክ የብልፅግና አገልጋይ አሁን የሕግ ያለህ ብትል የማትሰማበት ዘመን እየመጣ ነው። በሃይማኖትና በሃይማኖት አባቶች ስታሾፍ የከረምክ ካድሬ አሁን የሃይማኖት አባት ያለህ ብትል የማትሰማበት ዘመን እየመጣ ነው። እነ በላይነህ ክንዴ ትናንት የዐማራ ተወላጅ ጳጳሳትን ይዘው "ኧረ ምን ተሻለን? እናንተን ይዘን እርቅ እንድንሞክር መንግሥት ልኮናል" በማለት ጳጳሳቱን ቢለምኑም። ረፍዷል። አሁን የሚሰማን የለም። እናንተ ሞክሩ እንዳላቸው ስሰማማ ነገ በጣም ነው ያስፈራኝ። ዕርቅና ሽምግልና መቀለጃ አይደለም። እንደ ትግሬ ሚልዮን አስፈጅቶ አቢይ እግር ላይ የሚወድቅ ዐማራ ያለ አይመስለኝም
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 2/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ሆነ ቀን፣ የሆነ ቦታ፣ የሆነ ሰዓት ላይ፣ የሆነች ደቂቃና የሆነች ሰከንድ ላይ ይሄ እየተገዘገዘ ያለ የኦሮሙማው የአቢይ አሕመድ ጅሃዲስት የሆነ ዓረባዊ ጠባይ ያለው፣ በዓረብ መሣሪያ የገዛ ሕዝቡን የሚጨፈጭፍ አረመኔ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ መከላከያ ተብዬ ፀረ ሕዝብ ጦር አከርካሪው መሰበሩ፣ ህብለ ሰረሰሩም መበጠሱ አይቀርም። የሆነ ቀን ቀጥ አድርጎ ያቆመው ወገብ ዛላው ይቆረጣል። ፍርክርኩም ይወጣል። ወይ ተኝተን ስንነሣ፣ ወይ ረፋድ እኩለ ቀን ላይ፣ አልያም አመሻሽ ላይ፣ ወይ በድቅድቅ ጨለማ ብቻ በሆነ ሰዓት፣ በሆነ ቀን አከርካሪው ይሰበራል። ሠራዊቱም ይበተናል። ነቢይ አይደለሁም ነገር ግን ቀኝ ትከሻዬን በሸከከኝ ጊዜ የምጽፈው ነውና ይሄን ጦማሬን እንደ ትንቢት ባትቆጥሩትም ለማንኛውም ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ መዝግባችሁ አስቀምጡልኝ።
"…የሠራዊት ብዛት፣ የመሣሪያ ብዛት፣ የቦንብና የሚሳኤል ጋጋታ አንደዜ ቆርጦ ተቃውሞ የጀመረን ሕዝብ ከድል መለስ ሊያቆመው የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል የለም። ባለጊዜዎች በጊዜ በዘመናቸው ለጊዜው ግደል ሲሉት የሚገድል፣ እረድ ሲሉት የሚያርድ፣ በቦንብ የሚያደባይ፣ በእሳት የሚለበልብ፣ ሀገር ምድሩን በኬሚካል ጋዝ ጭምር የሚፈጅ ታዛዥ፣ ገረድ ሠራዊት ስላላቸው ሁሉን ነገር በጉልበት የሚቆጣጠሩት ይመስላቸዋል። ለዚህ ነው ነገን ሳያስቡ ሲደነፉ፣ ሲዝቱ፣ ሲወበሩ የሚታዩት። 1ሺ ዓመት እንደማይኖር እያወቀ 1ሺ ዓመት ብትዋጉ አታሸንፉንም፣ እኛን አንድም ምድራዊ ኃይል አያሸንፈንም ወዘተ ይሉት ድንፋታ የሚያሰመቱ። ነገ ሌላ ቀን፣ ሌላ ገዢ የሚመጣ የማይመስላቸው ለዚህ ነው። ሰው መሆናቸውን ይዘነጉታል። የሚታመሙ፣ የሚሰበሩ፣ የሚሸነፉ፣ የሚያረጁ፣ የሚያለቅሱ፣ የሚወድቁ፣ የሚቀየሩም አይመስላቸውም። ጊዜያዊ ስሜት ያጠቃቸዋል። አምባገነን ሆነህ በላዩ ላይ ማይምነት ሲጨመርበት ደግሞ እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው። ችግሩን የከፋ የሚያደርገው ማይም ሆነህ ስትወድቅ አንተ አለመውደቅህ ነው። ብቻህን አትወድቅም። ጦስህ ለሁሉ ነው የሚተርፈው። ሀገር ምድሩን ይዘህ ነው የምትወድቀው።
"…በአቢይ አሕመድ መከላከያ ጦር ላይ ድፍን አምስት ሚልዮን ትግሬ ቂም እንደቋጠረ ነው። አቅም አጥቶ፣ ጉልበት ርቆት፣ አጋጣሚውን አላገኝ ብሎ ነው እንጂ እንደ ትግሬ በብልፅግናው ላይ ቂም የቋጠረ በዚያች ሀገር ያለ አይመስለኝም። የትግሬ ቂም በኦሮሙማው መከላከያ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ በጦርነቱ ወቅት ተሳትፎ አድርገዋል ባላቸው ኃይሎች ላይ ሁሉ ነው ቂም ቋጥሮ አድፍጦ ቀን የሚጠብቀው። በሻአቢያ ላይ፣ በተለይ ደግሞ በዐማራ ላይ፣ ከዚያም በጦርነቱ መሪ በኦሮሞ ብልፅግና ላይ እና በጦርነቱ ላይ ሰፊ ተሳትፎ ነበራቸው ባላቸው እንደ ደቡብ ክልል ባለ ኃይል ላይ ሁሉ የተቋጠረው ቂም ቀላል አይደለም። ይሄን ቂሙን የሚወጣውም ዕድል አግኝቶ አጋጣሚውን እስከሚያገኝ ድረስ ብቻ ነው። ትግሬ በዚህም ጊዜ ቢሆን ስህተቱ የህወሓት እንደሆነ ልቦናው ቢያምንም እምነቱን ግን ህወሓትን በመበቀል ለዚህ የዳረግኸኝ፣ እዚህ አረንቋ ውስጥ የከተትኸኝ አንተ ነህ በማለት ህወሓትን ከመገሰጽ ፈንታ ጣቱን የሚቀስረው ሌላ ሌላ ቦታ ላይ ነው።
"…ከትግሬ በላይ ግን በትግሬ ነፃ አውጪው የትግሬ ልጆች ዘመንም ጭምር ትልቁን መከራ በዚያች ምድር ላይ በመቀበል ይሄን ያልተቋረጠ ለዘመናት መከራ ያመጣበትን አገዛዝ እና ሥርዓት ለመቀልበስ በመዋደቅ ላይ ያለው፣ የሚገኘውም ታላቁ፣ ሆደ ሰፊው፣ ጀግናው ዐማራ ሕዝብ ነው። ዐማራው ያለፉትን መቶ ዓመታት ከዘመነ ጣሊያን ወረራ ጊዜ ጀምሮ ፍዳ መከራውን እየበላ ያለ ነገድ ነው። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ኤሊቶቹ በሙሉ ተለቅመው ተጨፈጨፉ። በመንግሥቱ ነዋይ ግርግር ዘመንም የዐማራ ኤሊቶች በግፍ ተጨፈጨፉ፣ የ1966 ቱ የኦሮሞ መሩ የደርጉ ሥርዓትም ዐማራውን ያለምህረት ጨፈጨፈው፣ አሰደደው፣ ወደ ዘብጥያ አጋዘው። የ1983ቱም ህወሓት መሩ ሥርዓት ዐማራ የተባለ ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ማርያም ጠላት፣ እንደ አብዶ ቤተ ክርስቲያን ወይ መስጊድ እንደገባ ውሻ እንዲሳደድ፣ ሁሉም ባገኘበት ቦታ ሁሉ ድንጋይ አንሥቶ የሚቀጠቅጠው፣ የሚወግረው ሆነ፣ እንደ እባብ ነው አናት አናቱን ቀጥቅጠው የጨፈጨፉት። የወላይታው የፓስተር ኃይለማርያም ዘመነ መንግሥት ራሱ በአቅሚቲ የዐማራን ሕዝብ በአደባባይ በአግአዚ ጦር ያስጨፈጨፈ ነው። የአቢይ አህመድ የቡቸሩን መምጣት ተከትሎ ግን በሁሉም ዘመነ መንግሥታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መንግሥታዊ ዐዋጅ በሚመስል መልኩ ዐማራው በግሬደር እስኪቀበር ድረስ ተጨፈጨፈ።
"…እናም የሆነ ቀን፣ የሆነ ሰዓት እንደ ሶሪያው አላሳድ ሠራዊት የኢትዮጵያም ጨፍጫፊ፣ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት ቅስሙም፣ ጅስሙም ተሰብሮ መበተኑ አይቀርም። ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር ይሄ አረመኔ አራጅ ሠራዊት ይሠበራል። ይበተናል። ያነዜ ነው እኔን የሚያስፈራኝ፣ የምሰጋውም ክስተት ይፈጠራል ብዬ የማስበው። መለኮታዊ ጣልቃገብነት ካልተፈጠረ በቀር ዓለም ዓይቶት የማያውቀው ጥፋትና እልቂት ይፈጠራል ብዬ ነው የምሰጋው። በቀል፣ በቀል፣ በቀል፣ በቀል በበቀል ምድሪቷ የምትዘፈቅ ነው የሚመሰለኝ። አዎ ከወዲሁ ለዚህ ጊዜ ተዘጋጅተን ካልመከርንበት፣ ይሄ ግማታም፣ ጥንባታም፣ ሸታታ ሥርዓት መገርሰሱ እንደማይቀር ዐውቀን ተረድተንም ከሥርዓቱ መውደቅ በኋላ እንደ ሕዝብ ከመጠፋፋታችን በፊት ከወዲሁ ምክክር ካልተደረገ እጅግ ሰቅጣጭ ነገር ነው የሚከሰተው። ከወዲሁም ዘገዛዙ ራሱ ምልክቱን እያሳየ ነው። በኦሮሚያ ሰው ሲያሳርድብት የነበረውን የሰው ቄራ ሠራተኞቹን በታላቅ ክብር ተቀብሎ መሃል ሃገር ለሌላ ጭፍጨፋና ዕልቂት እያዘጋጀ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይሄን ዓለም ሁሉ እያየ፣ እየተመለከተም ነው። ሩዋንዳ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲፈጸም እነ ፈረንሳይ በዚያ ነበሩ። ዛሬም አቢይ አሕመድ ከተመረጠ ወዲህ ፈረንሳይና ጣልያን እንደ ውኃ ቀጂ ሴት ነው የተመላለሰው። ጣልያን የገንዘብ እርዳታ ሁላ ነው ስታደርግለት የሚታየው። እናም በመንግሥታቱ ዕውቅና በቀጣይ ዕልቂት እንደሚኖር መጠርጠርና መስጋት ሟርተኛ አያሰኝም።
"…ከጃንሆይ መንግሥት ወደ ደርጉ ስንመጣ እንደ ሕዝብ ያልተባላነው በወቅቱ የሃይማኖት ወዝና መልካችን ስላልተቀየረም ነበር። የጃንሆይ ዘመን ግብረገብ ትምህርት የተማሩ ታላላቆች ሀገር ስለነበረች ኢትዮጵያዊ እንደዚያ በቀይ ሽብር እና በነጭ ሽብር እየተጨፋጨፈ፣ ጉዳዩን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ግጭት ጋር በማያያዝ ያዝን፣ ይተክዝ ነበር እንጂ እንደ ብሔር፣ እንደ ሃይማኖት ቆጥሮ የሚከስ አልነበረም። ፓትርያርኳ የተገደለባት ኦርቶዶክስ፣ ሼዃ የተገደሉባት እስልምና፣ ፓስተሯ የተገደለባት ፕሮቴስታንት ደርግ የተባለ የወታደሮች ፓርቲ ገደለብን እንጂ እንደ አሁን ከብሄርና ከሃይማኖት ጋር ለማያያዝ አልተሞከረም ነበር። አሁን ግን ይለያል። ገዢው የብልፅግና ወንጌል ፓርቲ ኦርቶዶክስን እንደ ሃይማኖት፣ የዐማራን እስልምና፣ ሰሜናዊውን ነገድ ትግሬና ዐማራን ጠላት አድርጎ፣ እንደነ ብርሃኑ ነጋ አቃጣሪ ገሌ ፓርቲዎች ሳይቀር ሥልጣኑ ከሰሜን ወደ ደቡብ ሽፍት ማድረግ አለበት በማለት በይፋ ነው በተጻፈም፣ ባልተጻፈም ግልጽ ፖሊሲ ጭምር መንግሥት መር የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው። ስጋቴ አሁን ራሱን እየተከላከለ የሚገኘው የዐማራው ነገድ ከአሁኑ ምልክት እያሳየ ስለሆነ በመጪው ጊዜ ለቁጥጥር የማይመች ዕልቂት እንዳይፈጠር እሰጋለሁ።👇① ✍✍✍
መልካም…
"…የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ ጽፌ ከጨረስኩ በኋላ ልለጥፈው አልለጥፈው ብዬ ተወዛገብኩ። በዐማራ ክልል የአቢይ አሕመድ የብልጽግና ሠራዊት የሚፈጽመው በቪድዮ የተደገፈም መረጃ ነው። ሶሪያም ሄጄ በዚያ እየተፈጸመ ስላለ ዘግናኝ የበቀል ቪድዮ እያየሁ ለሀገሬም ሰጋሁ። እናም ልለጥፈው አልለጥፈው ብዬ ተወዛገብኩ።
"…በተለይ የሆነ ቀን መውደቁ የማይቀረው ይሄ የበሰበሰ፣ የከረፋ አገዛዝ በወደቀ ማግስት የአገዛዙ አገልጋዮችን የሚታደጋቸው እንደሌለ ሳስብ ይጨንቀኛል። በሶሪያ እየሆነ ያለው እንደዚያ ነው።
"…ርእሰ አንቀጹ አስተማሪ ነው። ግን ደግሞ ይረብሻል። በተለይ የአቢይ አሕመድ የጦር አዛዦች ዐማራው ላይ የሚፈጽሙት ጭፍጨፋ ናላም፣ አናትም ያዞራል። ይሄን ጭፍጨፋ እያዩ ሥርዓቱን የሚያገለግሉት የአገዛዙ ካድሬዎችና የፓርቲ አባላት፣ ባለሥልጣናትስ ምንድነው የሚጠብቃቸው ብዬም ስጠይቅ ይዘገንነኛል። በሶሪያ እየሆነ ያለው ቪድዮ ዘግናኝ ነው።
"…ለአንድ እብድ ተብሎ ሀገር መፍረስ፣ በአፍጢሟ መደፋት አለባት ወይ? ብዬም እጠይቅና ምላሽ አጣለሁ። ከምር መጪው ጊዜ ይሰቀጥጣል።
• አሁን ርእሰ አንቀጹን ልለጥፍ አልለጥፍ በሚለው ተወዛግቤ ቁጭ ብያለሁ። ምን ትመክሩኛላችሁ…?
በላሌዴንጣ… አዲጭ… 🖐
• ወደ መንደሬ በሩጫ እየሄድኩ ነው… 🏃♂➡️
• አሁን ደርሻለሁ… ገባ ገባ በሉና ተከታተሉኝ።
~ አላችሁ አይደል…?
መልካም…
"…በመቀጠል ደግሞ ይሄን 13 ሺ ሰው አንብቦት 10 ፍሬ ሰዎች ጓ 😡 ብው ያሉበትን የዛሬውን በወንዞች ጥራት እና በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ላይ ያተኮረ በናይል ቤዝ ኤንሼቲቭ አባል ሀገራት ስፖንሰር የተደረገ የሚመስል ርእሰ አንቀጽ ላይ እናንተ ደግሞ አስተያየታችሁን ወደመስጠት ታመራላችሁ።
"…እኔ ዘመዴ ደግሞ የዛሬው የዕለተ ማክሰኞ ሳምንታዊው ተወዳጅና ተናፋቂ የቲክቶክ መርሀ ግብሬ እስኪደርስ ድረስ አርበኛ ሀብቴ ወልዴን ያጣው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቡድን ከተከዜ ማዶ እናቱ ከወሮ ለቅሜ ኪዳኑ በሚወለደው በእስክስ አበበ በለው ምልጃ የሀገሩ፣ የወንዙ ሰው ነው ተብሎ የሚታመነውን አርበኛ ደረጀ በላይን የድርጅቱ ምክትል መሪ በማድረግ ጎንደርን ዳግም ወደ ብጥብጥ ለመክተት የፖለቲካው ቅማንት ፀረ ዐማራ የትግሬ ዲቃሎች በሸዋ በእነ አቤ ጢሞና መከታው ማሞ እየታገዙ ከውጭ በእነ አቤ እስክስ እና በፓስተር ምስጋናው እየተደገፉ፣ የሚያደርጉትን ስብሰባ እየተሳተፍኩ በጎን ደግሞ የእናንተን ወርቅ፣ ወርቅ የመሳሰሉ አስተያየቶች ወደ መኮምኮም አመራለሁ።
• 1…2…3…✍✍✍ ጀምሩ…
👆② ✍✍✍ …ወደ ዋናው የዐማራ በካይ የገማ ቱቦ ምንጭ ወደ ሆነው ወደ ዐማራው ካንሰር ወደ ብአዴን ብልፅግና ገንዳ መሰስ ብለው ተመልሰው ገብተዋል። ከእነ ቫይረስ ሻንቆ በተጨማሪም የጎንደር ወንዝን ያግማሙትና ቤሮአቸው መነሻ ምንጫቸው ከመቀሌና ከአዲግራት የነበሩት የቅማንት ታጣቂ ተብዬ አልጌ፣ ተውሳክ ቫይረሶች እና ጀርሞችም እጃቸውን በጊዜ ለአገዛዙ ሰጥተው ወጥተዋል። በዚህ ምክንያት አሁን የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ እየጠራ መጥቷል። የጎንደር ውኃ ፕሮጀክትም በተያዘለት ዕቅድ መሠረት ወደ ጤናማ ውኃነት እየተቀየረ ነው።
"…የጎንደርን የዐማራ የትግል ወንዝ የበለጠ ጤናማና ንፁህ፣ አንድ ወጥም ለማድረግ በተደረገው ርብርብ መሰረት ሰሞኑን በአባት አርበኞች ተጋድሎ የተደረገው የልማት ሥራም መላውን ዐማራ ያስደሰተ ነበር። በሁለቱ የጎንደር ልጆች በጀግኖቹ በባዬ ቀናው እና በሀብቴ ወልዴ አንድ መሆን አይደለም የጎንደር ዐማራ የጉደር ዐማራ እንዴት እንደተደሰት ማየት ይቻላል። ደግሞም በምንያለ ተጋድሎ የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ ቆሻሻው ሁሉ እንዴት እየደተወገደ ወደ ጥራት እየመጣ እንደሆነ እናንተ ሁላችሁም ምስክር ናችሁ። ዳርና ዳር ቆመው በቸልተኝነት፣ በዳተኝነት፣ በጠላት ሴራም ለወንዛቸው ትኩረት ባለመስጠታቸው ምክንያት የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ እንዴት ተበክሎ እንደነበር ማንኛውም ሰው የሚመሰክረው ነው። በወንዙ ውስጥ ያሉ ነፍሳትም ሆኑ ከወንዙ የሚጠቀሙ ዐማሮች ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገው ሲማቅቁ እንደነበርም የታወቀ የተረዳ ነው። የጎንደሮች አንድ ያለመሆን ወንዙ በቆሻ እንዲበከል ትልቅ አስተዋጽኦም ነበረው። ሺዎችን ለህማምና ለሞት ዳርጎ እንደነበርም የሚታወቅ ነው። አሁን ግን ቢያንስ ሁለቱ ታላላቅ ግዙፍ የጎንደር የወንዙ ጠባቂ ኃይሎች ወደ አንድ በመምጣታቸው የወንዙም ቆሻሻ በራሱ ጊዜ ስለቀነሰ፣ እየቀነሰ ስለመጣ፣ ከዳር ያለ ተመልካች እንኳ በሚታዘብ መልኩ የቆሸሸውን፣ የተበከለውን የወንዙን ክፍል ዓይቶ መፍረድ፣ ለማስተካከልም መንቀሳቀስ እንደሚቻል መመስከር በድፈርትም መናገር ይችላል። አሁን ወንዙን ለማከም እጅግ በጣም ቀላል ነው።
"…ከጎንደር የሚፈሰው ወንዝ ጤናማ መሆን ለጎንደር ብቻ አይደለም የሚጠቅመው። ለመላው ዐማራ ሁሉ ነው ጤና የሚሰጠው። ለወሎው፣ ለጎጃሙ፣ ለጎንደሩ፣ ለሸዋው፣ ለወለጋው፣ ለመላው ኢትዮጵያ ሁሉ ነው ጤና የሚሰጠው። ጠላትም በአንደኛ ደረጃ በሚባል መልኩ በከፍተኛ በጀት በመንቀሳቀስ በቅድሚያ ማቆሸሽ፣ መበከል የፈለገው ወንዝም የጎንደሩን የዐማራ የትግል ወንዝን ነው። ወያኔ ከትግራይ፣ ሱዳን እና ኤርትራም ከጎረቤት ሀገር፣ የወልቃይቱ ስኳድ፣ ከውስጥ ፋሕፍዴን የተባለ ሽንት ቤት፣ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬው ዲቃላ ስኳድ ፀረ ዐማራው ብአዴን በጋራ ሆነው ከውስጥ የጎንደር ዐማራ የጠራው የትግል ወንዝ ላይ ይለቅቁ የነበረው ዝቃጭ እና ሰገራ ሽንት በቀላሉ የሚታይ አልነበረም። በብዙ ትሪልዮን ብር በጀት የማይስተካከል፣ የማይጠራም ነበር የሚመስለው። ስኳዱ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ሆኖ የሚያራው አር፣ በተቃዋሚ ፓርቲም ውስጥ ሆኖ የሚሸናው ሽንት፣ በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ቱቦዎች በኩል የሚደፋው ቆሻሻ፣ በአበበ በለው አዲስ ድምጽ እና በእነ ሀብታሙ አያሌው 360፣ በእነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ጣና ቲቪ በኩል ያቀረሽ፣ በእነ እስክንድር ነጋ በኩል ያስታውክ የነበረው ትውከት በእውነቱ የጎንደር ዐማራን የትግል ወንዝ እስከ አሁን አግማምቶት ቆይቷል። አሁን ግን ክብር ለጎንደር ዐማራ የበላይ ጠባቂ አባቶች ይሁንና ይኸው ይሄ ሁሉ ግሳንግስ በእነሱ ተጋድሎ፣ በአምላካቸው እርዳታ ተቃልሎ ወንዙ ጥርት እያለ መጥቷል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…የጎንደር ዐማራ የትግል ወንዝ ለማጥራት በተወሰደው እርምጃ የተከፉ፣ የሚንጫጩ ቡድኖችን እያየን ነው። ካካቸውን ወደ ወንዙ በቱቦ መልቀቅ የለመዱ ከርሳም ፀረ ዐማራ ትግል በካዮችም እየተንጫጩ ነው። ግን ምንም አያመጡም። የጎንደር ዐማራ አንድ መሆን የእንጀራ ገመዳቸውን የሚበጥስባቸው አካላት ተለይተው ታውቀዋል። የጎንደር ዐማራ ሲጣላ የዘገቡ፣ ሰበር ዜና ብለው ዓለሙን ሁሉ ያንጫጩ ዐማራ መሳይ ፀረ ዐማራ አሞሮቹ ለቅሶ ተቀምጠዋል። ነጠላ ዘቅዝቀው እያለቀሱ ነው። ሽንትቤት ቆፍረው ካካቸውን እንደ ድመት ቀብረው ኋላ ገንዘብ ከፍለው ካካቸውን እንደማስመጠጥ በቱቦ ወደ ወንዙ ካካቸውን መልቀቅ የለመዱ ጥንባታሞች ላያቸው ላይ መቅዘን ጀምረዋል። ውባንተ ይገደል ሲሉ የነበሩ መልአከ ሞቶች አሁን ጎንደር ወደ አንድነት ሲመጣ ልሳናቸው ተዘግቷል። የአባት አርበኞችን መልእክት፣ ቀጥሎም በቀደም እሁድ ዕለት የሀብቴና የባዬ ሠራዊትን እርቅ በተመለከተ ትንፍሽ አሏሏትም። በለጠ ካሣ ከኡጋንዳ፣ ኢትዮ 360፣ አዲስ ድምፅ ወዘተ ዝም ጭጭ ነው ያሉት። ትንፍሽ አላሉም። ጭራሽ እነ አርበኛ ራስ ደረጀን ከጎንደር ግንድ ገንጥለው ለማሳየት ነው ሲሯሯጡ የታዩት። እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ደረጀ ሀብተ ወልድ፣ እነ ፓስተር ምስጋናው ሁሉ ጌታ አስራደ፣ ጌታ አስራደ ብለው የጮሁት ያለነገር አይደለም። ነገር ግን ጅብ ከሄደ ሆነባቸው። አለቀ። አበቃ።
"…የጎጃሙ የዐማራ የትግል ወንዝም እንደምታዩት ነው። ቀድሞ ነው የጠራው። በሰኔ 15 ቱ የዐማራ ክልል ግድያ ተሳታፊ የነበሩት ስኳዶች፣ አሳምነው ጽጌን ያስገደሉ ስኳዶች፣ ዘንዘልማ ላይ ብለው የደነፉ ስኳዶች፣ አርበኛ ዘመነ ካሤ ወደ ፊት ከመጣ ይበቀለናል ብለው ከመንቦቅቦቃቸው የተነሣ ከሚያጯጩሁይ ጩኸት በቀር ሌላው አሸወይና ነው። ጎጃሜውን መማርን ከተደበቀበት አውጥተው ወደ አሜሪካ እናሻግርህሃለን በማለት ካግባቡት በኋላ ከምሥራቅ ሸዋ ወደ ደቡብ ጎንደር ወስደው አረመኔያዊ ድርጊት የፈጠሩበት የአብን የደቡብና የሰሜን ጎንደር ስኳዶች አሁን ጎጃሜው ዘመነ ካሤ ወደ ፊት ከመጣ ለፍርድ ያቀርበናል በማለት ሌት ተቀን ለሃጫቸውን እያዝረበሩቡ የሚታዩትም ለዚህ ነው። እስክንድር ነጋ አቢይ አሕመድን ከሰኔ 15ቱ ድራማ ጀርባ የለበትም ያለው ቪድዮም አለኝ። ሰኔ 15 ባህርዳር ላይ ግርግር ፈጥሮ በሰላም አዲስ አበባ የተመለሰው ቅጥረኛም ሠራዊቱን በቲክቶክና በቴሌቭዥን አሰማርቶ የሚንበጫበጨውም ለዚህ ነው። ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲል ዓሣ አጥማጅ።
"…እስክንድር ነጋ አሁን በሕዝብ ገንዘብ የተቋቋሙና የዐማራ ፋኖ የትግል ወንዝ ላይ ካካቸውን፣ ግማት ትውከታቸውን የሚለቁ ሦስት የቱቦ ሚዲያዎችን አቋቁሟል። ከወሮ ልቅሜ ኪዳኑ ልጅ አበበ በለው እስክስ ከአዝማሪው አዲስ ድምጽ ቤት፣ ከአፍራሳ የልጅ ልጅ ከሀብታሙ 360 ቤት፣ ከፖለቲካው ቅማንት ከትግሬው ዲቃላ ከፓስተር ምስጋናው ጣና ቲቪ ቤት፣ በፋርማሲስቱ ስኳድ በአምሳሉ እጅ የነበረው ገንዘብ በሙሉ ተመድቦ የዐማራን የትግል ወንዝ ለማቆሸሽ የሚባዝኑ ሆኗል። ነገር ግን እነዚህን ቱቦዎች በገንዘብ እየደገፈ ያለልክ እየወጠቁ፣ እየበሉ፣ ካካቸውን የሚዘፈልሉት ቱቦዎች ገንዘቡን ይለግሳቸው የነበረው ዐማራ ልገሣውን ቀጥ ስላደረገው ካካቸውም ደርቋል፣ ቱቦአቸውም እየተደፈነ ነው። ያለ ሀሳብ እስክስ እያሉ እየጨፈሩ እየበሉ በዐማራ የትግል ወንዝ ላይ መጸዳዳት አይቻልም። እዚያው ፖፖህ ላይ ተጸዳዳ አባቴ። ወፍ የለም። 👇② ✍✍✍
መክካም…
"…ርእሰ አንቀጻችን ተዘጋጅቷል። ማቀራረብ ብቻ ነው የሚቀረው። የዛሬው ርእሰ አንቀጻችን በቆሻሻ፣ በግማት፣ በሰገራና በሽንት፣ በትውከትም፣ በቅርሻትም ተበክሎ የነበረው የዐማራ የትግል ወንዝ እየጠራ ስለመምጣቱ ነው ቀኝ ትከሻዬን ስለሸከከኝ በደስታ ደስ ብሎኝ የጻፍኩት። ወደ ዐማራ የትግል ወንዝ ቆሻሻቸውን የሚለቁ ቆሻሾችን ቱቦ ለመድፈን የሚረዳ ቆንጆ አዳፍኔ የሆነ ርእሰ አንቀጽ ነው የጻፍኩት።
"…እስቲ ገምቱ ርእሰ አንቀጹን እስክለጥፈው ወደ ዐማራ የትግል ወንዝ ካካቸውን፣ ሽንትና ትውከታቸውን፣ ዝቃጫቸውን በመክተት ጤናማውን ትግል ሊያጠነቡ፣ ሊያግማሙ፣ ሊያሸቱ ቱቦአቸውን ከወንዙ ያገናኙትን ኃይሎች በስም ጥቀሱ እስቲ። የእነዚ ኃይሎች ቱቦ ከተደፈነ የዐማራ ፋኖ ወንዝ ጤናማ ይሆናል፣ ለመጠጥ ቢሉ ለመስኖ፣ ለጤናም ተስማሚ ይሆናል። አይደለም እንዴ?
• ቆሻ ቱቡአቸውን ከወንዙ ጋር ያያዙ ቆሻሾችን በስም እየጠቀሳችሁ ትጠብቁኝ ዘንድ እኔ ፊልድ ማረሻው ዘመዴ በቴሌግራም መንደር ወታደራዊ ትእዛዝ መሠረት አዝዣለሁ።
• የዐማራ ፋኖን የትግል ወንዝ ከበካዮች በጋራ እንከላከል።💪💪✊
• እየጻፋችሁ ቆዩኝ።
“…የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች…።” ማቴ 27፥64 “…በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” 1ኛ ጴጥ 5፥8
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
የመርሀ ግብር ማስታወቂያ…
• በዛሬ ምሽቱ "…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" በተሰኘው ሳምንታዊው የመረጃ ተለቭዥን የቀጥታ ስርጭት ላይ
• የአርበኛ ሀብቴ ወልዴን መግለጫ ትሰማላችሁ
• የሶሪያን ትኩሳት ከኢትዮጵያ ጋር እያነፃፀርን እናወጋለን።
• ስለ ብልጽግና ሸኔና ስለ ኦነግ ሸኔም እንወያያለን።
• የዐማራ ፋኖ በብአዴን ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመር ብአዴኖች ወደ ባሕርዳር እና ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ ስለመሆኑም እናወጋለን። የትም አታመልጥም በሉልኝ። የማን ቤት ፈርሶ የማን ይቀራል፣ የማን ወገን ሞቶ የማን ይቀራል?
• ዛሬ ነጭ ነጯን ነው የምናወራው። ዛሬ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ፣ የአገው ሸንጎና እነ አበበ በለው፣ እነ ሀብታሙ አያሌው አፍራሳ ከንቱ ሓሳብ ይቀበራል። እንደ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም አይነቱም ሾተላይ ከእነ ፋፍህዴኖቹ ጌታ አስራደ ሓሳብ ጋር ድባቅ ይመታሉ።
• አይ ዘመዴ መራታው…😂 እንዲህ ነኝ እኔ። ዐማራ በዐማራነቱ ብቻ ያሸንፋል። አለቀ። ኮተታም፣ ከፋፋይ፣ ሌባ፣ ሾተላይ ሁላ ጥግህን ትይዛለህ።
• ምሽት 1:00 ጀምሮ ጠብቁኝ።