zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

359908

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰበር ዜና…💪💪

"…በመጨረሻም፣ ስለቴ ሰመረ፣ ጩኸቴም ተሰማ። ጎንደርን አንድ የሚያደርግ የምሥራች ከወደ ጎንደር ተሰማ።🙏🙏🙏

"…የጎንደር ዕዙ መሪ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ በእስክንድር ነጋ ከሚመራው አዲሱ የአፋሕድ ድርጅት በይፋ ተለየ። ለመረጃ ቲቪቪው ለጋዜጠኛ ሞገሴ ሽፈራውም መግለጫ ሰጥቷል። በቀጣይ ሁለቱ የጎንደር ፋኖዎች የአርበኛ ሀብቴ ወልዴና የአርበኛ ባዬ ቀናው የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት ይመጣሉ። ውህደትም ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

"…እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ደረጀ ሀብተወልድ፣ እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ በለጠ ካሣ፣ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እነ አበበ በለው እና እነ ዋን አዋራዎች ወደፊት ሊያመጡት የሚቋምጡለት ፋሕፍዴንም ውኃ በላው። እነ ጌታ አስራደ ጨረቃ ላይ ቀሩ። ሌባ ሁላ። ጎንደር አንድ ከሆነ የዐማራ ትግል መቋጫውን ያገኛል።

"…የሸዋው የእነ መከታው ማሞ፣ የእነ አበበ ጢሞ ፋኖ፣ የወሎው የኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባው ፋኖ ብቻ ነው አሁን ከእስክንድር ነጋው ድርጅት ጋር ተጣብቆ የቀረው። ብራቮ ጎንደር። ብራቮ ዐማራ። 💪💪💪

• አንድነት ኃይል ነው።
• በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እኔየምለው…

"…በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድን ሥርዓት በክላሽ መጣል አይቻልም" በማለት እሱ ብቻ አውርቶ፣ አስጨብጭቦ በሚወርድበት ሸንጎው ሲደሰኩር የነበረውን የአቢይ አሕመድን ዲስኩር ደጋግመው ሲያሰሙን የነበሩት እና አደንቁሬ የኢትዮጵያ ጎምቱ ሚዲያዎች የባሽር አላሳድ መንግሥት በአንድ ሳምንት ትጥቅ አከርካሪው ተመትቶ መገርሰሱን አልሰሙም እንዴ?

"…ምነ አቢይ አሕመድ ሲጨንቀው፣ ሲጠበው ወደ እነ ኢዩ ጩፋ፣ ወደ እነ እስራኤል ዳንሳ፣ ወደ እነ ዮናታን አክሊሉ፣ ወደ እነ ይዲዲያ ነው ኤዲዲያ ሀገር ወደ ደቡብ ሄዶ ሀገር ሰላም እንደሆነች ለማስመሰል ራሱን በራሱ የሚያረካበትን የደቡብ የዐርባ ምንጭ ጉዞው ላይ ብቻ አተኮሩ? አንድ መስመር ዜና ማንን ገደለ? 😂

"…የበሸር አላሳድ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን ቀይረው፣ መሳሪያቸውን ጥለው ወደ ኢራቅ ሲሰደዱ ቪድዮውን አላዩትም፣ ወይም አልደረሳቸውም? ቤተ መንግሥቱ ሲወረር፣ ማንኪያና ሹካ ሳይቀር ሲዘረፍ አላዩምን?

"…ለማንኛውም እነርሱ ካላሳዩአችሁ እኔ ዘመዴ ሶሪያን በተመለከተ ዛሬ ማታ ተአምር ነው የማሳያችሁ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንቅልፍ አጥታ ወያኔንና ሻአቢያን ስታሰለጥን የነበረችው ሶሪያም ኢትዮጵያ ሳትፈርስ ልክ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና እና ፍልስጤም ዓይናችን እያየ፣ ጆሮአችን እየሰማ እሷም ፈረሰች። አቤት የፈጣሪ ሥራ።

"…የኢትዮጵያም አምባገነን የብልፅግናው አቢይ አሕመድም ጉዳይ እንዲሁ ነው። አርባ ምንጭ በመደበቅ፣ ኦነግ ሸኔን ጠብቀኝ ብሎ ወደ ሸገር በመሰብሰብ፣ ሕፃናትና የአእምሮ ህሙማንን ጭምር ለጦርነት በማፈስ አገዛዙን ማጽናት አይቻልም። የሆነ ቀን የሆነ ቦታ መከላከያው አከርካሪው ሲሠበር ወይም መከላከያው ነቅቶ ከሕዝብ ጋር ሲቆም ሁሉም ነገር ያበቃለታል።

• እነ ፋና፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ ተንፒሱ እንጂ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…8

"…የሶሪያ መከላከያ ሠራዊት የሆነ ቦታ፣ የሆነ ነገሩ ላይ አከርካሪው ሲመታ ይኸው ፍርስርሱ ወጥቶ ተቃዋሚ የተባሉት ታጣቂዎች የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ሊገቡ በአራት እና በአምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። አዲስ አበባም ለመግባት የብልፅግናው አራጅ ሠራዊት የሆነ ሥፍራ ላይ፣ ወይ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወይ ወሎ ሸዋም ላይ ድንገት የሆነ ቀን አከርካሪው ከተመታ ያልቅለታል የሚሉም አሉ። በተለይ ፋኖ የብልጽግናን ዙፋን አስጠባቂ ብአዴኖች ላይ ጨክኖ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ የሌለ ዳይፐር አስወድዷል። በኢትዮጵያ።

"…ኧረ ዝም ብዬ እኮ ነው በተቀበል መርሀ ግብራችን የምቀባጥረው። እኔምለው ይሄ ትግራይ ድርሽ የማይለው። ወደ ዐማራ ክልል ዞሮ እንኳ የማይሸናው፣ በኦሮሚያ ምቾት የማይሰማው፣ ለጊዜው ወደ ምስኪኖቹ አርባ ምንጮች ሄዶ ሀገር ሰላም ናት ብሎ አጀንዳ ለመስጠት የሚላላጠው… 😂 የፖቶ ቦለጢቃ ኖ… ወፍ የለም።

• እኔምለው ይሄ የህንድ አክተር ስሙ ማነው…?

• እየገጠማችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

"…እናንዬ… ይሄ የእባብ የዘንዶ ነገር ዓለም አቀፋዊ ነው ማለት ነው? መቼም ዴየደብ ሆኜ እኮ ቶሎ አልገባህ እያለኝ ተሸገርኩ። አሁን እኮ ነው እየገባኝ የሚመጣው።

"…መቼም የዛሬው የተቀበል መርሀ ግብራችን እንደ እኔ የተመቸው የለም። ያን የጥንተ ጠላታችን የዘንዶውን ራስ መቀጥቀጫ ነው የሆነለኝ። ምድረ ጠንቋይ የጠንቋይ ልጅ ሁላ በቅድስቲቷ ሀገር መንበር ላይ ፊጥ ብሎ የንፁሐንን ደም እያፈሰሰ፣ የደም ግብርም እየጠጣ በዚህ መልኩ አይቀጥላትም።

ኃይልየ ሥላሴ
ወፀወንየ ሥላሴ
በስመ ሥላሴ
እቀጠቅጥ ከይሴ

• እየገጠማችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

"…አዲሲቱ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ብሬዘዳንት አርቲስት ማስተር ቺት ማስተዋል ወንደሰን ለአዲስ አበባ ወጣቶች የሕይወት ተመክሮ ልምዳቸውን እያካፈሉ ነው። አሪፍ ነው አላለም ጋዜጠኛው።

• እናንተ ቺት ግን ምንዲኖ…?

• እየገጠማችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…2

"…እሃሃ… ኢንዴዢያ ነው እንዴ…? 😂

"…አልገብቶኝም ነበር… ከፋስተሯ ጋር ሳያት፣ የመልካም ወጣት ፍሬ መሆኗን ሳይ ነው የባነንኩት። እንዲያ ከሆነ እንኳ ዘመኑ ነው። ጊዜው ነው። ወቅቱ ነው።

"…ወዳጄ አሁን ራብ፣ ጥም፣ ሽግር የሌለው እዚህ አካባቢ ነው። ሥልጣን፣ ገንዘብ፣ ሥራም ያለው በእነ "ጌታቸው" ልጆች ቤት ነው።

• እየገጠማችሁ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…ተጀምሯል…!

"…በሉ ግጠሙ፣ ቅኔውን አፍስሱት…

• ግጥም ስጡት…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሕፃን ፌቨን የፍርድ ውሳኔ…!

"…ለዛሬ ህዳር 27 ተቀጥሮ የነበረው የሕፃን ፌቨን ጉዳይ ዛሬም የዐማራ ክልል ፍርድ ቤት የቀረበልትን የይግባኝ አዳምጦና መርምሬ ውሳኔ ሰጥቻለሁ ማለቱ ተሰምቷል። ይግባኝ ባዩ የተፈረደብኝ የ25 ዓመት ፍርድ አግባብ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ጸያፍ ወንጀልም አልፈጸምኩም። በወቅቱ የልጅቷ እናት በቤት ነበረች። ጉዳዩ እኔ የማላውቀው ልደርስበትም ያልቻልኩት ውስብስብ ሴራ ነው፣ የሟች ሕጻንን አስከሬን ቀድማ ያየችው የሟች አክስት ለምስክርነት እንዳትቀርብ እንኳ አድራሻዋን አጥፍተዋታል። በሕፃኗ በአፍ ላይ የተገኘው አፈር የቀቧት እምነት ነው። የራሰችውም በጸበል ነው።

"…ፍርድ ቤቱም ይግባኙን አድምጦ ከ25 ዓመት ፍርድ ወደ 21 ዓመት ቅጣቱ ዝቅ እንዲደረግ ወስነናል ብሏል። ፍርድ ቤቱ አክሎ "ሕፃኗ ተደፍራለች ማለት አይቻልም" ብለው የሁለቱም ሆስፒታል ዶክተሮች መስክረዋል ካለ በኋላ…ነገር ግን የመደፈር ሙከራ የለም ማለት አይደለም። በወቅቱ ተከሳሽ በቤት ውስጥ ስለነበር የመድፈር ሙከራውን ከእሱ ውጭ ሌላ ሰው ሊያደርግ አይችልም ብለን ፍርዱ እንዲጠና አድርገናል። በዚህም ምክንያት ግራቀኙን ዓይተን ብሎ ከፍርዱ 4 ዓመት ብቻ ቀንሰው በዛሬው ዕለት 21 ዓመት እንደፈረዱበት ተሰምቷል።

"…ሴራው ያለው አሜን ክሊኒክ ውስጥ ነው። ጉዳዩን ያወሳሰቡት አሜን ሆስፒታሎች ናቸው። የሕፃኗን ማህፀን ያለመሳሪያ ብቻ ሳይሆን የመመርመር ፈቃድ ሳይኖራቸው በእጃቸው ነካክተው፣ ሪፈር ብለው ለፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የላኩት ፈለገ ህይወትም የሕፃኗ ማህፀን ከመቅላት እና ከመስፋት ውጭ ክብረንፅህነዋ ምንም እንዳልተነካ በግልፅ ጽፈው የነበር ቢሆንም የጎንደር ስኳድ ረጅም እጅ በጎጃሜው ልጅ ላይ ከብዶበታል።

• የተከሳሽ ሚስት ፌደራል ሄጄ ይግባኝ እጠይቃለሁ ማለቷንም ሰምቻለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ትግሬውን ስሙት…!

"…ለፓስተሪት ማራማዊት ነው ትግሬው ልፋዓተይ ተስፋ ነጭ ነጯን የሚነግራት። ወያኔ ትግሬ ለነገዬ ብላ ብዙ ወቅት ጠብቀው የሚፈነዱ ፈንጂዎችን በመላው ኢትዮጵያ ቀብራለች ብዬ ቅድም በርእሰ አንቀጼ ላይ የጠቀስኩላችሁ ይሄንን ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንደበትን ከፈቶ፣ ፊትን ፀፍቶ ሃቅ ሲያናግር እንዲህ ነው።

"…የዐማራ ፋኖ ለምን አንድ አይሆንም? የሚሉ ብዙ ምስኪን ሰሞነኛ ፖለቲከኞች ያጋጥሙኛል። ዐማራ እኮ በከባዱ የተዋለበት ምስኪን በፈጣሪ ጥበቃና ቸርነት ያለ ነገድ ነው። ውስጡ ተሰግስገው በየት በኩል አንድ ይሁን? ጎንደርን በፖለቲካው ቅማንት በትግሬው ዲቃላ ስኳድ፣ ጎጃምንም እንዲሁ በፖለቲካው አገው ሸንጎ፣ ወሎንና ሸዋንም በፀረ ዐማራ የትግሬና የኦሮሞ ዲቃሎች ሰንጎ ይዞት እንዴት ይፈናፈን?

"…ተመልከቱ የትግሬዎቹ እህትማማች ባል የሆኑት ደቡብ ጎንደሬዎቹ እስክንድር ነጋና ፋርማሲስቱ አምሳሉ አስናቀ፣ እንግሊዝኛ ሳይችሉ ፕሮፌሰር የተባሉት የጎንደሮቹ ጌታ አስራደ እና ሲሳይ፣ ቅማንቴው ፓስተር ምስጋናው፣ ደመቀ ዘውዱ፣ ርስተይ ተስፋይ፣ እነ ሙላት አድሓኖ ወዘተ እንዴት ፀረ ዐማራ ሆነው ዐማራውን እንደሚታገሉት ታውቃላችሁ አይደል? የትግሬዋ ልጅ አበበ በለው እንዴት የዐማራ ፋኖን ትግል እንደሚያቦካው፣ ሸዋንና ወሎን በእስክንድር በኩል ኮሎኔሉን እና መከታውን ይዘው እንዴት እንዳፈዘዙት ምስክር ናችሁ።

"…አልፎ ተርፎ ነው እንግዲ ኦሮሞ የዋህ ነው፣ ዥል ነው፣ ምስኪን ነው፣ ሞኝ ነው ብለው የተቆረጠ የጡት ሃውልት ሠርተው ከዐማራ ጋር ያናከሱት የትግሬ ቦለጢቀኞች አሁን ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ትግሬ አሰማርተው ዐማራውን በኦሮሞ ስም የሚፈጁት። የህወሓት ደጋፊዎች ወቦ እያሉ ሲጨፍሩ ካየህ አትደንግጥ።

• ስደቡኝ አሏችሁ ደግሞ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ✍✍✍ …ብትልም ዘገባው የዓረቦቹ ቦንብ ክርስቲያን ዐማሮችን፣ ትግሬዎችንና የዐማራ እስላሞችን እየፈጀ መሆኑን ዘግቧል። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ጭምር የሚጠሉትን ዳዊትና መስቀል ዐማሮቹ ይዘው እንደሚዋጉ ነው የዘገበው። ተወደደም ተጠላም አሁን በኢትዮጵያ ሞቶ ተሟሙቶም ነገዱን ከእልቂት የሚያተርፈው ዐማራው ብቻ ነው። ያውም ገና 98%ቱ ዐማራ ትግሉን በይፋ ሳይቀላቀል፣ ከአሽከር ብአዴን ጋር ጭምር እየተፋለመ ማለት ነው። 20 % ዓመራ መታገል ሲጀምር ነገር ሁሉ ያበቃል። በ2% ዐማራ ይሄን ግዙፍ የዓረብ ቅልብ አፈር ከደቼ ማብላት ከተቻለ ቁጥሩ ከፍ ሲል አስባችሁታል?

• አንተ ይሄን መልእክት የምታነብ ዐማራ የትኛው ላይ ነው የቆምከው? ረኸጥ ነህ ረመጥ ዐማራ፣ ዐማራ ነህ ወይስ ዐማራ መሳይ ጆፌ ዐሞራ፣ ባለ ዐእምሮው ዐማራ ነህ ወይስ ማይም፣ እርጥብ፣ ሰገጤ፣ መቶ ኪሎ ፋራው ዐማራ? ንገረኝ የትኛው ዐማራ ነህ? አራዳ ለመምሰል የምትጋጋጥ ለፍዳዳ እንጭጩ ሰገጤ ነህ ወይስ የወገንህ ሞት ስደር ጭፍጨፋ የሚቆጭህ፣ የሚያንገበግብህ ዐማራ? የትኛው ዐማራ ነህ? ጴንጤ አድርገውህ ማንነትህን የሰለቡህ፣ ፈሪ፣ ቅዘናም፣ ቅንቅናም፣ አስመሳይ፣ ሽባ ያደረጉህ ፀረ ዐማራ አድርገው የጋቱህ ጀዝባ፣ ነሆለል ዐማራ ነህ ወይስ ባለ ዳዊቱ፣ ባለ መስቀሉ፣ በለ ቁራኑ ዐማራ? ንገረኝ አንተ ማነህ? ሴት ጭን ስር ስትሸና፣ ስትሟሟ ይምታድረው ጋለሞታው ዐማራ ነህ? ለገዳይህ ካድሬ ሆነህ ለአራጅህ የተገረድክ ዐማራ ነህ? ሆድህ የበለጠብህ ባንዳ ዐማራ ነህ? ንገረኝ አንተ ማነህ?  በየቲክቶኩ ተዘፍዝፈህ እኔን መስደቡን ትተህ እስቲ ራስህን ጠይቅ፣ ጠይቅ ራስህን? ጠላቶችህ በዚህ ልክ እንቅልፍ አጥተው ሊያጠፉህ ሌት ተቀን ይኳትናሉ አንተ ትጃጃልልኛለህ። ዥልጥ ጅል።

• ማርያምን ዐማራ ግን አሳምኖ ድብን አድርጎ ያሸንፋል…!!

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሕዳር 27/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②…✍✍✍ …የሚረሽን ሸኔ፣ አባቶርቤም ብለው መሠረቱ። የወለጋውና የጉጂው፣ የሸዋውም ሸኔ በዚህ ተለያዩ።

"…ታስታውሱ እንደሆን የለውጡ ሰሞን አቢይ አሕመድ ከለማ መገርሳ ጋር ወለጋ ድረስ ሄዶ ከእነ ጃልመሮ ጋር በቃ የታረቅን እንምሰልና በጋራ ዐማራን እናደባየው። ዛሬ ይሄ ዕድል ካመለጠን መቼም አናገኘውም። አየር ኃይሉ ይልማ መርዳሳ ነው። መከላከያው ብራኑ ጁላ ነው። ፌደራል ፎሊስ ደመላሽ ነው። ሁሉም ቦታ እኛው ነን የሚል ይዘት ያለው መልእክት አስተላልፍ እንደነበር ሲነገር ይሰማል። አቢይ አክሎም በወቅቱ መከላከያ ሚንስቴሩ ዶር አብርሃም በላይ ነው፣ ጄነራል አበባው ታደሰም ትግሬ ነው። አገኘሁ ተሻገር ቅማንቴ ሰካራም ዘሩን የከዳ የትግሬ ዲቃላ ነው፣ ግርማ የሺጥላም፣  ከዳንኤል ክብረትም፣ እነ ሰማ ጥሩነህ፣ ኢንጂነር ሃብታሙ፣ ብናልፍ፣ መላኩ አለበል፣ ይልቃል እኔ ነኝ የማዛቸው፣ ተመስገን ጥሩነህ የእኔ ሻንጣ ተሸካሚ ገረድ ነው እና ተስማምተን አብረን እንሥራ ብሏቸው ነበር የሚሉም አሉ። ነገር ግን አልተቻለም። አልተስማሙም።

"…የእነ ጃዋር ቡድን ከወለጋው ሸኔ ጋር ገጠመ። ለዚህ ነው የወለጋው ሸኔ ደጋፊ በሙሉ ለማ መገርሳን የሚደግፈው። በተለይ ፅንፈኛው የኦሮሞ ወሃቢይ እስላምና አክራሪው የወለጋ ጴንጤ አሁንም ከጃልመሮ እና ለለማ መገርሳ ድጋፉን የሚያሳየው ለዚህ ነው። ስለዚህ የምዕራብ ሸዋው ሥርወ መንግሥት የራሱን ሸኔ መሥርቶ ምዕራብ ሸዋን በሙሉ፣ ሰላሌን፣ ደራን፣ አልፎም ሰሜን ሸዋ አጣዬን እንዲያወድም ኃላፊነት ሰጥቶ የሚያዝ የሚያንቀሳቅሰውን ቡድን ፈጠረ። ያ ቡድን ነው ዐማራን በአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት፣ ደብረ ዘይትና ዱከም፣ ዝቋላ ተራራ ላይ ሳይቀር መነኮሳትን ጭምር ሲያርድ የከረመው። ከምዕራብ ሸዋ ኦርቶዶክስን እና ዐማራን ቀርጥፎ የበላው፣ ሽባ ያደረገውን ቡድን ፈጥረው ጫካ ያስቀመጡት ቡድን ነው አሁን ወደ ሰላም መጣሁ ብሎ ለአገዛዙ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለመዋል ደፋ ቀና እያለ ድራማ ሲሠራ የምናየው።

"…የምዕራብ ሸዋን፣ የሰላሌ፣ የደራንና የአጣዬን ዐማራና ኦርቶዶክስ ጨፍጭፎ አሁን ወደ አገዛዙ ተጠቃልሎ የገባው ቡድን በወንጀል፣ በዘር ማጥፋት የሚጠየቅ ቡድን እንጂ የአበባ ምንጣፍ ተነጥፎለት እንዲህ ሽር ጉድ የሚባልለት አይደለም። ተመልከት ጃል ሹርቤ እና ጃል ሰኚ ማለት እኮ ሁለቱም የትውልድ ቦታቸው ምዕራብ ሸዋ አምቦ ዙሪያ ነው። የኢንጂነር ታከለ ኡማን አባት አግተዋል ተብሎ ከመንግሥት ካዝና ለአቶ ኡማ በንቲ ማስለቀቂያ 10 ሚልዮን ብር ፈሰስ ሲደርገለት፣ የሙገር ሲሚንቶን ለመቆጣጠር፣ የደርባን ሲሚንቶ ለመቆጣጠር ሲነባል ማኔጅመንቱን በጠራራ ፀሐይ የረሸነው ይሄ ቡድን እኮ ነው። የኦሮሞ ኦርቶዶክሶችን አጥፍቶ የምዕራብ ሸዋን ሕዝብ በግድ ጴንጤ ያደረገ እኮ ነው ይሄ ቡድን፣ የሸዋ ኦሮሞ አልጨክን ሲል ከአሩሲ፣ ከባሌና ከሀረርጌ ፅንፈኛ የኦሮሞ ወሀቢይ እስላም ተዋጊ ሸኔዎችን በማምጣት የሸዋ ኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያንና ዐማሮችን ሲቀላ የከረመ ቡድን እኮ ነው። ከ2012 ዓም ጀምሮ እነ ሽመልስ አብዲሳ ከጀርባ ሆነው በሥልጠና፣ በመረጃ እና በፋይናንስ ሲደገፉት የነበሩት እና የምዕራብ ሸዋው የቱለማ ኦሮሞዎች ሥርወ መንግሥት ፕላን ቢ የነበረ እኮ ነው፣ ከራሱ ከመንግሥት መዋቅር የነበሩ ሰዎች በበላይነት እንዲመሯቸው ተቀላቅለዋቸው የነበረው ቡድን እኮ ነው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራንፕ ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ አስቀድሞ ፖለቲካ ሊሠራ በማቀድ ፈጣጣ የእንጭቅ ልጅ ድራማ ለመሥራት የሚንደፋፈደፈው።

"…የሸዋ ቱለማ የእነ ሽመልስ አብዲሳው የምዕራብ ሸዋ ቡድን አሁን የቀረው ሆሮጉድሩ ወለጋ ላይ ጥቂት ሴል አላቸው። ከእነዚህም መካከል አሙሩ ወረዳ አካባቢ ፈቀደ የሚባል አመራር፣ ምሥራቅ ወለጋ ላይ ጊዳአያና አካባቢ የሚንቀሳቀስ ደግሞ  ፍቃዱ የሚባል አመራር አላቸው። አሁን ለምዕራብ ሸዋው ሥርወ መንግሥት የቦለጢቃ ድራማ ሲባል በሚዲያ ላይ ሲተራመሱ የምናያቸው የእነ ጃል ሰኚ ቡድን ብዙም ኃይል የሌላቸው ናቸው። ይህ አሁን ወደ አገዛዙ መንደር በይፋ የተቀላቀለው ቡድን ቀደም ሲል እንደተጻፈው በእነ ሽመልስ አብዲሳ በሥልጠና በፋይናንስ እና በመረጃ የሚደገፈው ሲሆን ዐማራንና ኦርቶዶክስን ብቻ ሳይሆን በመከላከያ ውስጥ "ለምን ሕዝባችን ይጨፈጨፋል? ብሎ የሚጠይቅ እና መንግሥትን የሚሟገት የመከላከያ መኮነንም ይሁን ተራ ወታደር በመንግሥት መረጃ ሰጭነት በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ግንባር እንዲዘምት ተደርጎ በእነዚህ ኃይሎች እንዲገደል ይደረጋል። ከእነዚህ ሸኔዎች ጋር ለጦርነት ለውጊያ የሚላኩት ከእነ ሽመልስ ጋር ግንኙነት ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች ሲሆኑ፣ በፈጠራ ጦርነቱ ዐማራው እና ኦርቶዶክሱ ሲጨፈጨፍ ጭፍጨፋውን እያዩ ከላይ እርምጃ እንድንወስድ አልታዘዝንም በማለት ሠራዊቱ በካምፕ እንዲቀመጥ በማድረግ እነ ጃል ሰኚ ሚሽናቸውን ከጨረሱ በኋላና ሥፍራውን ለቀው ከሄዱ በኋላ መከላከያ ወደ ቦታው ተልኮ ሬሳ እየቆጠረ እንዲቀብር ሲያደርጉ የኖሩባቸው ናቸው አሁን በመጨረሻ በክብር የአበባ ምንጣፍ አንጥፈው የተቀበሏቸው። ግብረ ሰዶማዊነቱ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

"…እኒህ ከላይ የተገለጹት የምዕራብ ሸዋ ሥርወ መንግሥቱ ፕላን ቢ ኃይሎች ማለትም በሁለቱ ጃሎች የሚመራው እና በእነ ሽመልስ ( ኦህዴድ ) የሚደገፈው ኃይል በጎሳ ደረጃ ሁለቱም የቱለማ ኦሮሞ ጎሳዎች ናቸው። በኦሮሞ ከአስራ አንድ ቤት የሚባል አለ፣ ከአስራ አንደኛው ቤት ከሸዋ ነው፣ ሸዋ ውስጥ ቱለማ አንደኛው ነው። እኒህ አሁን ለአገዛዙ የገቡ የጃል ሰኚ ታጣቂዎችም አብዛኛው እንቅስቃሴአቸው ሸዋ ውስጥ ነበር። በትግሬ የሚደገፈው እና መሠረቱን ወለጋ ያደረገው በጃልመሮ የሚመራው ሸኔ ከስድስት እና ከሰባት ወራት በፊት ነው አጠቃላይ ግምገማ አድርጎ እነዚህን የቱለማ ኦሮሞ የምዕራብ ሸዋውን ኢምፓየር ቡድኖች ከሠራዊቱ በይፋ ያገዳቸው። ከአገዛዙ ጋር ታንዛኒያ ሄደው የተደራደሩትም ጃል መሮ እና ጃል ገመቹ አቦየ ናቸው። የኦነግ ሸኔ ዋናኛዎቹ አመራሮችም እነሱ ናቸው። እነዚህ እነ ጃልመሮ ለድርድር ታንዛኒያ ከመሄዳቸው በፊት ነው ከሥልጣን የታገዱት። መጨረሻ ላይ ግን ከስድስት ወር በፊት አጠቃላይ ቀጠናው ላይ እነሱ የሚመሩበት ወይም የሚንቀሳቀሱበት ቀጠና ማዕከላዊ ኮሚቴአቸው ተሰብስቦ ሌላ አመራር እነ ጃል መሮ መደቡ። ከዛ በጥቅምም ትስስር የነበራቸው ከ100 እስከ 150 የሚደርሱ ታጣቂዎች በጃል ሹርቤ እና በጃል ሰኚ እየተመሩ ከእነ ጃል መሮ አፈንግጠው ከአገዛዙ ጋር ንግግር ጀመሩ።

"…እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳም በተለይ በቱለማ ጎሳ የሆኑ የታጣቂ መሪዎችንና አባላቱን እንዲሁም የቱለማን የጎሳ ማኅበረሰብ "እኛ ቱለማዎች ሥልጣኑንም፣ ፖለቲካውንም፣ ኢኮኖሚውንም ተቆጣጥረን ባለንበት በዚህ ሰዓት ለምን እርስበርስ እንዋጋለን? ወለጋ የራሱን ክልል ለማድረግ ነው የሚዋጋው፣ የወለጋን ጉዳይ የወለጋ ተወላጅ ፖለቲከኛውም፣ ሃይማኖተኛውም፣ እነ ጃልመሮም እየሠሩበት ነው። እኛ ሸዋዎች ለሚሽን ልጆች የፖለቲካ መጠቀሚያ ለምን እንሆናለን በማለት ነው ጉዳዩን ሳይገባቸው በጀሌነት ዝም ብለው እውነት መስሏቸው የተቀላቀሉትን ሰብከው ያሳመኑአቸው። "ይህ ደግሞ ኦሮሞን ለመከፋፈል ነው" እያሉ በሠሩት ፕሮፖጋንዳ እና ፖለቲካ ተሳክቶላቸው እኒህ ታጣቂዎች ገሌ አድርገው ያገቧቸው። እነዚህ በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቁ፣ በእነ ሽመልስ መመሪያ ሰጪነት እነ ሽመልስ ያይናቸው ቀለም ያላማራቸው፣ አፈንጋጭ ነው ተብሎ የተጠረጠረን አመራር፣…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በጎጃም በቀጥታ የጦርነት ፍልሚያ ሳይ አርፍጄ ነው የመጣሁት። ከነ 200 ጥይቱ የሚማረከውን የምርኮኛው ብራኑ ጁላን መንጋ ሳይ ስሰማ ቆይቼ ነው የመጣሁት። ዐማራ እንደሚያሸንፍ በዓይኔ በብረቱ ዓይቼ ነው የመጣሁት። የብር ሸለቆ ሠልጣኝ ደንግጦ ገደል ሲገባ፣ ሲበታተን ዓይቼ ነው የመጣሁት። የብአዴን አባላት መግቢያ መውጫ አጥተው ምድር ስትጠባቸው ዓይቼ ነው የመጣሁት። ማርያምን ቀርጬዋለሁ። የመድኃኔዓለም ያለህ።

"…ዶናልድ ትራንፕ ከመንገሡ በፊት ይኸው ከታጣቂዎች ጋር ዕርቅ አውርጃለሁ፣ ትግሬዋንም ወያኔን ሁሉን ፈቅጄላት ለሁለት ተከፍላ እሷን ለማስታረቅ እየደከምኩ ነው በማለት እያፋጃቸው ያለው አቢይ አሕመድ የምዕራብ ሸዋውን አራጅ፣ ገዳይ፣ ነፍሰ በላ አረመኔ የጃል ሰኚ ቡድን ጭራሽ የመከላከያ ልብስ አልብሶ ለሀገሪቱ ያለውን ንቀት ሲያሳይም አይቼ ነው የመጣሁት።

"…እናም ወዳጆቼ የዛሬውን የሳምንቱን መጨረሻ ከትናንት የቀጠለ ርእሰ አንቀጻችንን ልለጥፈው ነኝ…? እናንት የተለጠፈውን አንብባችሁ የራሳችሁን ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁን? አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ በሉኝ እስቲ። 😂

• አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጪው ጊዜ…

"…ህወሓትን ከመቀሌ ጠርተህ ብትለምን ብታስለምን፣ ደጅ ብትጠና ብትለማመጥ፣ በሴራ ቦለጢቃ ሁለት ቦታ ከፍለህ ብታነታርክ፣ ኦነግ ሸኔን ከሰንቀሌ አምጥተህ በሀገር ምድሩ በከተማ በገጠሩ ብታፈስ መጪው ጊዜ ከባድ ነው የሚሆንብህ። ከቱርክና ከኤምሬትስ ድሮንና ቦንብ ሸምተህ እንደ ክረምት ዶፍ በዐማራ ምድር ላይ ብታዘንብ፣ መጪው ጊዜ ለአንተ እና ለአንተ ሰዎች ወዳጆችም ከባድ ነው።

"…አይደለም ፀጉሩን ተቆንድዶ ንፁሀንን ሲገድል፣ ሲዘርፍ የኖረው ሸኔን ይዘህ ልታሸንፍ ይቅርና የልዕለ ኃያሏ ሀገር አሜሪካ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ድረስልኝ እያለች ነው። ባለ ዳዊቶቹ ያሸንፋሉ። ሰይጣንና ሠራዊቱ በቅዱስ ሚካኤል ሰይፍ ድል ይነሣል።

"…አሄሄ በቃ ተይዘሃል፣ ተይዘሃል፣ የትኛውም ድራማ አያስጥልህም። ኦሮሚያ ሰላም ሊሆን ነው፣ አራጁን ካምፕ አስገቤቻለሁ፣ ትግሬም መሳሪያ እያስረከበ ካምፕ ሊገባ ለመቶኛ ጊዜ ተስማምቷል። ማን ቀረ…?😂 ዓመፀኛው ፋኖ፣ ፅንፈኛው ፋኖ፣ አይደል…? …ሞኝህን ብላ 💪። አባቴ ከወደ አሜሪካ የተደገሰልህን ብታውቅ የሳሳው ፀጉርህ ተመልጦ ያድር ነበር። FANo Go GO GO አለ ዘመዴ

"…ታዲያ ይሄን ስለጻፍኩ ፀረ ዐማራ ፋኖው፣ ፀረ መስቀል፣ ፀረ ዳዊቱ የፓስተር ምስጋናው አንዷለም መንጋ ቢጮህብኝ ልደነግጥ ነው? ቲሽ።

• ማኔቴቄልፋሬስ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ✍✍✍ …ዳንኤል ክብረት ስለነበር እሱን ነው ያማከሩት። ጴንጤዎቹ የምዕራብ ሸዋ ሥርወ መንግሥት ባለቤቶች የኦርቶዶክስን የውስጥ ምስጢር ታውቃለህና መላ አምጣ ብለው አሉት። ዳንኤል ክብረትም ልክ ጎንደሬዎቹ በበብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አማካኝነት በአንደዜ ግሪሳ ጳጳሳትን እንደሾሙት፣ ትግሬም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ቀጥሎም በብፁዕ አቡነ ማትያስ እንደተወከለው አሁን ደግሞ ኦሮሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ የራሱ ፓትርያርክ ካላስቀመጠ ዋጋ የለውም በማለት መከራቸው። ለዚሁም ልክ እንደ ጎንደሬዎቹ በሕገወጥ መልኩ ነፍ ጳጳሳት ይሾሙ። ፀብ እንኳ ከመጣ እርቅ ሲባል የወደቀው ወድቆ የቀሩት በዕርቅ ሰበብ ይገባሉ ብሎ መከራቸው። ለዚሁም ተብሎ የምዕራብ ሸዋ ተወላጅ ጳጳሳትና ዲያቆናት፣ ካህናትም ጭምር ሓላፊነት ወስደው መንቀሳቀስ ጀመሩ።

"…ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ዘራቸው የደራ ዐማራ ቢሆንም ዕድገታቸው ምዕራብ ሸዋ፣ ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ ምዕራብ ሸዋ፣ አስተባባሪው ዲን ኃይለሚካኤል ምዕራብ ሸዋ፣ እነ ቢስሚላ ዋህድ ሁላ እነ ይቴ ጭሷ፣ ይታገሱ ከምዕራብ ሸዋ ተመረጡ። አቡነ ማትያስን አስወግደው ነበር አቡነ ሳዊሮስን በማፐትረክ ሥርወ መንግሥቱን ለማጽናት የፈለጉት። ይሄን ሕገወጥ አካሄድ የተቃወሙ የትየለሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካህናትም ምእመናን ታረዱ። በሻሸመኔም ተጨፈጨፉ፣ ተገደሉ፣ ቆሰሉ። በወቅቱ ምንም እንኳ አፍቃሬ አቢይ ቢሆኑም እንቅፋት ሆነው ነበር የተባሉት ጎንደሬው አሜሪካዊው አባት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም ከኢትዮጵያ ትውልድ ሀገራቸው በውርደት፣ አንገት በማስደፋት ተባረሩ። ቅስማቸውን ነው እነ ዳንኤል ክብረት የሰበሩት። አሁን ላይ የሃይማኖቱ ጉዳይ ለጊዜው ባይሳካም የአቡነ ማትያስ ዕረፍት እየተጠበቀ እንጂ ፕትርክናው ለኦሮሞ መስጠቱ የሚቀር አይመስልም። ምክንያቱም እስልምናው በኦሮሞ ተይዟል። ፕሮቴስታንቱም በኦሮሞ ተይዟል። የቀረው ኦርቶዶክስ ነው እሱም የብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን የሥጋ ዕረፍት ነው በጉጉት የሚጠብቀው። ከእኔ ጋር ናችሁ አይደል? ነገ እንቀጥላለን።

"…በነገው ዕለት ኦነግ ሸኔ ማነው? እንዴት ነው ወዴት ነው? የሚለውን እና ሸኔ እንዴትና ለምን እንደተፈጠረ? ከምዕራብ ሸዋው ሥርወ መንግሥት ጋር አያይዘን በጥልቅ እመጣበታለሁ። ማርያምን እኔ እኮ ማይም መሆኔ ነው የጎዳኝ እንጂ አቤት ትንተናዬ… ትን እኮ ነው የሚያስብለው አይደል?

• ሌባ ሁላ…ጨበርበርቱ…ሃቱ…

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሕዳር 26/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…መለስ (ለገሰ) ዜናዊ ዓድዋ፣ ስብሐት ነጋ ዓድዋ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ዓድዋ፣ ዓባይ ፀሐዬ ዓድዋ፣ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ዓድዋ፣ ክንድያ ገብረሕይወት ዓድዋ፣ ስታሊን ገ/ሥላሴ ዓድዋ፣ ዳዊት ከበደም እንደ አቅሚቲ ዓድዋ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዓድዋ፣ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ዓድዋ… ጨምሩበት… ይሄ ሁሉ በዘመነ ሕወሓት ኢትዮጵያን ለ27 ዓመት እንደ ብረት ቀጥቅጦ፣ እንደ ሰም አቅልጦ የገዛው የዓድዋው የአቦይ ስብሐት ነጋ ሥርወ መንግሥት ነበር። በዘመነ ወያኔም ሆነ አሁን እንኳ በዘመነ ብልጽግና ትግራይን ይዞ የሙጢኝ ብሎ እየተንገታገተ የሚገኘው ኃይል የዓድዋው የአቦይ ስብሐት ሥርወ መንግሥት ትራፊ የነበረው ነው። ከወሎዬዎቹ ከራያ ልጆች ከእነ ጌታቸው ረዳ፣ ጻድቃንና መሰሎቹም ጋር ግብግብ የገጠመው ቡድን ይሄው የዓድዋው ኃይል ነው። ሃይማኖቱን፣ ወታደራዊ ክንፉን፣ ኢኮኖሚውን፣ መዝናኛውን፣ ሚዲያውን ሁሉ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሎ አሁን ላለችበት ቀውስ መሠረት የጣለው ይሄው የዓድዋው ሥርወ መንግሥት ቡድን ነበር። በቀደም ጌታቸው ረዳ "የትግራይን ወርቅ እየዘረፉ ነው" ብሎ የወረፈውም ይሄንን የዓድዋ የአቦይ ስብሐት ስርወ መንግሥትን ነው።

"…ዐማራም አካባቢ ይኸው የዓድዋ ሥርወ መንግሥት ዓይነት መሳሳብ ይታያል። ከዘመነ ስሁል ሚካኤል ዓድዋ በጎንደር ዘመን ጀምሮ፣ ከሕወሓት መምጣት በኋላ በተለይ የጎንደር ስኳድ እና አሁን ደግሞ የጎጃም የአገው ሸንጎ በዚህ መልኩ ይጠቀሳሉ። ዐማራውን አቀጭጨው ነው አፈር ከደቼ ሲያበሉት የኖሩት፣ የሚኖሩትም። ከአክሱም መናገሻው አሳዳው አሁን ከጎንደር ርስቱ ሊነቅሉት ነው እየታተሩ የሚገኘው። የጎንደርም ሆነ የጎጃም ዐማራ ከሥርዓቱ የተጠቀመው፣ ያተረፈው አንዳች ነገርም የለም። አናሳ፣ የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች እና አናሳ የፖለቲካ አገው የትግሬ ዲቃሎች ናቸው በዐማራው አናት ላይ ተጭነው ዐማራውን በእሾህ መካከል የበቀለ ጽጌሬዳ ሆኖ እንዲኖር ያደረጉት። በተለይ የጎንደሩ ስኳድ በጣም ይለያል። ሲበዛ ስግብግብ፣ ይሉኝታ ቢስ፣ ሆዳም፣ ነፍሰበላ ጨካኝ ነው። ለጎንደር ዐማራ ደንታ የሌለው፣ የጎንደር ዐማራን አሳዳጅ፣ ገዳይ ጭምር ነው። ይሄን ልምድ የወሰደው ደግሞ ከዓድዋው የስብሐት ነጋው ሥርወ መንግሥት ነው። በትግራይ አብዛኛዎቹ ሌሎች ወረዳዎች በፖለቲካውም፣ በኢኮኖሚውም፣ በሃይማኖት መሪነቱም ሆነ በወታደራዊ አመራሩ ውስጥ ቦታ የላቸውም። ሰብዓ እንደርታ፣ ተንቤን፣ ኢሮብ፣ ወዘተ ምንም ቦታ የላቸውም። የጎንደሩም ስኳድ ይሄንኑ ነው ኮፒ ያደረገው።

"…ለምሳሌ እንመልከት በአሜሪካ ተሰድዶ የነበረው ስደተኛው ሲኖዶስ ተብሎ ይታወቅ የነበረው እና በጎንደር ተወላጁ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስተዳደር ስር ይመራ የነበረው የስደተኛ መነኮሳት ስብስብ የነበረው ቡድን ይፎካከር የነበረው ከዓድዋው ተወላጅና በሟቹ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ይመራ ከነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስብስብ ጋር ነበር። አቡነ መርቆሬዎስ የሾሟቸው ጳጳሳት በሙሉ ከሁለቱ ማለትም አንድ ከጎጃም፣ አንድ ከወሎ በቀር በሙሉ ጎንደሬዎች ነበሩ። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። አቡነ መቃርዮስ ወሎና የኔቫዳው አቡነ ቴዎፍሎስ ጎጃሜ ከመሆናቸው በቀር በሙለየ እነ አቡነ ባርናባስ፣ ማርቆስ፣ ጴጥሮስ ወዘተረፈ በሙሉ ጎንደሬዎች ነበሩ። ፉክክሩ ከዓድዋው ሥርወ መንግሥት ጋር ስለሆነ ወሎና ሸዋን አባ ከና የሚል አልነበረም። ሁለቱ የበዪ ተመልካች ሆነው ከዳር ተቀምጥው ማየት ከጀመሩ ዘመናት ተቆጥረዋል። ሽኩቻው በሃይማኖቱም ሆነ በፖለቲካው በጎንደር ስኳድ እና በዓድዋው የአቦይ ስብሐት ሥርወ መንግሥት መካከል ነው። የጎጃሙ የአገው ሸንጎ ደግሞ ከሁለቱ የተረፈን ፍርፋሪ እንዲለቃቅም ተፈቅዶለት ውርውር ከማለቱ በቀር በተለይ ወሎና ሸዋ በኢትዮጵያ ቦለጢቃ የተረሱ፣ የተገፉ ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም። ሸዋ የሆነ ወቅት እንደምንም ብሎ በፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ በኩል ብቅ ቢል የዓድዋው የአቦይ ስብሐት ሥርወ መንግሥት እና የጎንደሩ ስኳድ ተረባርበው ነው ጨፍልቀው፣ ደፍጥጠው ያጠፏቸው። ፕሮፌሰር አሥራትን የደገፈው የጎጃምና የሸዋ ገበሬ የበቀል ዱላ ነው ያረፈበት። ውሸት የሚለኝ ካለ ይምጣ።

"…ይሄ ነገር በገዢው ፓርቲ ውስጥ ብቻ አይደለም የሚታየው። በተቃዋሚው ፓርቲ ውስጥም ያየን እንደሆነ የዓድዋና የጎንደር ስኳድ ፉክክር ቀላል አይደለም። ከትግራይ ለትጥቅ ትግል ኤርትራ ድረስ ሄዶ ኋላ ኮብልሎ መጣ የተባለው ሰው የዓድዋ ሰው ነበር። ስኳድን ያየን እንደሆነም እንደዚያው ነው። በምሳሌ እንመልከት ብዓዴን የድሮውን ትተን የአሁኑን ያየን እንደሆነ ለብልጽግና ተገርደው የምናገኛቸው ሁለቱን ነው። የጎንደሩን ስኳድ እና የጎጃሙን አገው ሸንጎ። አገኘሁ ተሻገር፣ መላኩ አለበል፣ ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ወዘተ ጎንደር ስኳድ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አረጋ ከበደ፣ ብናልፍ አንዷለም ጎጃም አገው ሸንጎ፣ ሸዋ እና ወሎ ዘብጥያ፣ ወይም ስደት ነው የሚፈቀድለት። ጎንደሬ ሆኖ ዐማራ፣ ጎጃሜ ሆኖ ዐማራ ከሆነ ዘብጥያ ነው ማረፊያው። ከወሎ ዮሐንስ ቧ ያለው፣ ከጎጃም ክርስቲያን ታደለን መመልከት ይቻላል። ይሄ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለ ነው። ለዐማራ ተቃዋሚ ፓርቲ ተብሎም በተቋቋመው ፓርቲ ውስጥም እንኳ ጎንደርና ጎጃም ሁለቱ ናቸው የሚፎካከሩት። ወሎና ሸዋ አጃቢ፣ አዳማቂ፣ አጨብጫቢ እንዲሆኑ ብቻ ነው የሚፈቀደው። ለምሳሌ እንመልከት አሁን አብንን የጠቀለሉት የጎንደር ስኳዶች ናቸው። ወሎን አጃቢ አድርገው፣ ጎጃሞቹን ከጨዋታ ውጪ አድርገው ጠቅልለው የያዙት እነርሱ ናቸው። ተቃዋሚ ሆነው ብልጽግናን ለማገልገል ቅሽሽ የማይላቸው ጉደኞች ናቸው የጎንደር ስኳዶች። የጎንደር ዐማሮችን አላልኩም። የጎንደር ስኳዶችን ነው ያልኩት። መዝግብ።

"…ስኳዶች የብልጽግናው አገዛዝ በተቃውሞ የሚወድቅ ከሆነ ብለውም ከወዲሁ በተቃውሞው ጎራ ቦታ ቦታቸውን ይዘው እየዳከሩ ነው የሚገኙት። ሲበዛ ዓይን አውጣ ፈጣጦች ናቸው። ይሉኝታ ብሎ ነገር አያውቁም። ራሱ የጎንደር ዐማራው ላይ የሚያሳዩት ጭካኔ ከወያኔ ትግሬ ከኦሮሞው ኦነግ እጅጉን የከፋ ነው። የጎንደር ዐማራውን አርበኛ ውባንተ አባተን ቀርጥፈው ሲበሉት ቅሽሽ አላላቸውም። ገድለውት እኮ ነው  እነሳሚ ቅማንቴው ቲክቶክ ላይ ወጥተው ሲጨፍሩ የታዩት። ይሄን ስታዩ ሰዎቹ ጎንደሬ ሳይሆኑ የኦነግ ኃይል ሁላ ሊመስሏችሁ ይችላሉ። ሲበዛ ጨካኞች ናቸው። እስክንድር ነጋን ከደቡብ ጎንደር ዘሩን ቆጥረው በዐማራ ፋኖ ላይ በመሾም እስክንድርን እንደ አድራሽ ፈረስ በመጠቀም ሊጋልቡት ይላላጣሉ። እስክንድር በአንድ ወገን ጎንደር፣ በአንድ ወገን ጎጃም ስለሆነ፣ የተወለደው፣ ያደገውና የኖረው አዲስ አበባ፣ አሁን ደግሞ ለትግል ብሎ የሄደው ሸዋ ስለሆነ ስኳዶች ካልኩሌት አድርገው ነው ስክንድር ላይ የሙጢኝ ብለው የተቀመጡት። ሸዋ ለቤተ መንግሥቱ ቅርብ ስለሆነ ቀድሞን ከገባ ጥሩ አይደለም ብለው ነው ማይሙን መከታውን የወርቅ ሰዓት በሴት ጭን ጠቅልለው በስጦታ መልክ ሰጥተው አደንዝዘው ሸዋን የበታተኑት። እስኬው ሸዋ ሄዶ የተቀመጠው በጎንደር ስኳድ ሴራ ነው። በዚህም የሸዋን ሕዝብ እንይዝበታለን በማለት ነበር ሒሳቡ የተሠራው። እነ ሀብቴ ወልዴን፣ ደረጄ በላይን፣ ኮሎኔል ታደሰን፣ ሰሎሞን አጠናውን፣ ኢያሱና ጌታአስራደን ይዘው አልተሳካም እንጂ ከጎጃም ኮሎኔል ጌታሁንንና መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን በመያዝ ነበር የዓድዋው ዓይነት ኢምፓየር መመስረት የፈለጉት።👇① ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይ አዲስ አበቤ…!

"…ዘመዴ አዲስ አበባ ተኩስ አለ። ከመገናኛ በአራት ኪሎ መስመር ሹርቤዎቹ ተኩስ እየተኮሱ እየወጡም፣ እየገቡም ነው። ዘመዴ ከእንጦጦ ወደ ሽሮሜዳ በሎንችን ሆነው እየተኮሱ አለፉ። ዘመዴ፣ ዘመዴ ወፎችህን ልከህ አጣራልን፣ ምን እየተካሄደ ነው ይልልኛል አዲስ አበቤ። 😂

እኔ~ በዓይነህ ዓይተሃል? በጆሮህ ሰምተሃል?

እነሱ~ ገሚሶቹ አዎ እያየናቸው እኮ ነው። ገሚሱ ቤተሰብ ደውሎ ነግሮኝ ነው።

እኔ~ ቪድዮ ቀርጻችኋል…?

እነሱ~ ኧረ አልቀረጽንም። ደንግጠን ተደበቅን፣ ሸሸን፣ አመለጥን።😂

እኔ~ እና እኔ ምን ላድርግ…?

እነሱ~ አጣራልን ዘመዴ። ወፎችህን ልከህ አጣራልን።

"…መድኃኔዓለም ያሳያችሁ። በ120 ሺ ብር የተገዛ የሞባይል ስልክ ይዞ እሱ ቆሞ ያልቀረጸውን መረጃ እኔ ጀርመን ራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ ቀርጬ እንዳሳይለት ይፈልጋል። አይ አዲስ አበባ። አዲስ አበቤ ነቃ በል። የአራዳ ልጅም አልነበርክ እንዴ?

"…መደንገጥ፣ መበርገግ፣ መፍራት፣ መቅዘን፣ መንቦቅቦቅ አያዋጣም። በተጠንቀቅ መጠበቅ ነው። ተደብቀህ በስልክህ ቅዳ። ወፎቼ አንው ራስህ ሁን። ወፍ ወፍ ስል ከምር አንተ እኮ አታፍርም የምር አድርገህ በሰማይ የሚበር ወፍና ርግብ እያየህ የዘመዴ ወፍ ትል ይሆናል። ራስህ ነህ ወፉ። ገባህ።

"…ተኩስ ስትሰማ ላይህ ላይ አትሽና፣ እንኳን ለሹሩቤ ለሴት፣ ለሕፃናት አራጅ አዲስ አበባ ለጣልያን አልተንበረከከም። ሽንታምነት የአዲስ አበቤ መገለጫ አይደለም። አትንቦቅቦቅ። አትፍራ። የምን የዋንጫ ጨዋታው ሳይጀመር መቅዘን ነው።

"…ቢረፍድም ከመቅረት ይሻላልና እንደ ዘአማራ ፋኖ አሁንም በቀበሌህ፣ በሰፈርህ ተደራጅ፣ ተደራጅና ራስህንም፣ ቤተሰብህንም ከጥፋት ታደግ። እደግመዋለሁ አትንቦቅቦቅ።

• ስልክህን ዘግተህ አትሩጥ፣ ደበቅ ብለህ ቅረጽ። ቅረጽና ላክ። ይኸው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። ሮሜ 13፥ 11-12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…7

"…ከዘንዶ ጨዋታ ሳንወጣ ለአዲሱ መከላከያ ሠራዊታችን እስቲ ግጠሙላት…🙏

• በነገራችን ታች ጠፋ ብላችሁ የቀወጣችሁት መብራት ግን መጣ ቀረ…? …በየሰፈሩ ያለው ጫኝና አውራጅ እኮ በቀን ብርሃንማ እያፈጠጠ ዕቃ አያስወርድ አያስጭን። እንዲህ መብራት አጥፍቶ ቦታ ቦታ ካላስያዙ ሽግር ኖ። በተለይ ካራና ገርጂ፣ ስለት ካለባችሁ እንደ ጠመንዣ ያዥና እንደ ጦር ኃይሎች በቀላሉ ዕቃ ማራገፍ፣ መረካከብም የማይታሰብ ነው።

• እየገጠማችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…6

"…1200 ዐማሮችን ከሰፈሩ አባርሮ ሜዳ ላይ የበተነው ይሄን የኢዩ ጩፋ ደቀ መዝሙር የትግሬ ነፃ አውጪ ድርጅት ሰዎች እንደነፍሳቸው ሲወዱት ሳይ በእውነት ኢገርመኝ ነበር። ከምር እንደኔ ዓይነት ነገራት ቶሎ የማይገቡት ደደብ በዚህ ምድር ይኖር ይሆን?

• እየገጠማችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

"…የቀደመው እባብ የዘንዶው አፉ በየት በኩል ነው። አልታይ ብሎኝ ተቸግሬ ነው። ወዳጄ ዘመኑ የአውሬው ነው ስልህ አላምን ብለኸኝ እኮ ነው። አደራ ግን የዘንዶውን አፍና ጅራት በየት በኩል እንደሆነ ፈልጋችሁ ንገሩኝ።

• እየገጠማችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…1

• የሃይሚ ግጥም ነው…

ተቀበል አዝማሪ…

ርኩሰት እንዲህ ነው ሲቀርብ ከነርቃኑ፣
ኳስ በሜዳ ይዞ ጀምሯል ካሁኑ፣
አብዮቱ ደርቷል ብሎ ሴታዊነት፣
ይብላኝ ለወንዶቹ ቁጭ ላሉት ከቤት።

• እንዲያነው…👏👏👏

~ ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።” ኢሳ 50፥4

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ደናቁርት ሆይ ደግማችሁ ስሙት።

"…ብዙ የትግራይ ልጆች የኦላ ታጋዮች ናቸው። ወለጋ ላይ ተወልደው ያደጉ፣ የክፍለጦር፣ የብርጌድ፣ የሬጅመንት መሪዎች ወለጋ ተወልደው በዚያ ያደጉ ትግሬዎች ናቸው። እኔ እንኳ ወለጋ ብሔድ የምቀላቀለው ኦህዴድን ሳይሆን ኦላን ነው የሚለው።

"…ትግሬ በኦሮሞ ስም ወንጀል ይፈጽማል። ትግሬ በኦሮሚያ ውስጥ የዘር ጭፍጨፋ ይፈጽማል። የሚገደለው፣ የሚሞተው ዐማራ ስለሆነ ግን ኦሮሞው ጨርቁን ጥሎ ይጨፍራል። በኦሮሞ ስም በኦሮሚያ በዐማራ ላይ ለሚካሄድ የትግሬ ልጆች የዘር ማጥፋት ወንጀል ኦሮሞው በዓለም ላይ በአራጅነት ይከሰሳል።

"…በወልቃይት፣ በራያ፣ በመተከል፣ በከሚሴ፣ በአጣዬ፣ በደራ፣ በደቡብ፣ በሀረርጌ፣ በአሩሲና በባሌ፣ በሸዋ በፅንፋኛ የዓረብ ተላላኪ የኦሮሞ ወሃቢይ እስላም ጋር ዐማራን እየጨፈጨፈ ያለው የትግሬ ነፃ አውጪ ዲቃላ ነው።

"…ቅማንትን አዲግራትና መቀሌ፣ ለአገው ሸንጎ መቀሌ ቢሮ ከፍቶ ዐማራን እረፍት የነሳው የትግሬ ነፃ አውጪው ነው። የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር የትግሬ ኮንዶም ነው።

"…ደግሞ ይህቺን ጻፍክ ብላችሁ ተናደዱብኝ አሏችሁ…!😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…13 ሺ ሰው አንብቦት 9 ፍሬ ሰዎች ብቻ ጓ ገጭ ብው 😡  ብለው የበሰጩበትን የዛሬ የዕለተ አርብ የሳምንቱ መጨረሻ የሆነውን ርእሰ አንቀጽ ላይ አሁን ደግሞ አስተያየት የመስጠት ተራው የእናንተ ነው።

• 1…2…3 ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …ገበሬ፣ የሃይማኖት አባት፣ ወጣት ሽማግሌ እያሳደዱ ሲገድሉ፣ ሲያርዱ፣ ሲጨፈጭፉ፣ ሀብት ንብረት ሲዘርፉ፣ ሲያወድሙ የኖሩ ወንጀለኞች ናቸው እንዲህ ባለ የክብር አቀባበል የተደረገላቸው። የሚገርመው ግን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በትግሬዋ ሕወሓት የሚደገፈውና በትግሬ ተዋጊዎች የተሞላው የጃል መሮ ቡድን ከእነ ሽመልስ አብዲሳ ጋር ተነጋግረው ወደ አገዛዙ የገቡት እነ ጃል ሰኚ ለቅቀው በሄዱት ቀጠና አዲስ አመራር መርጠው፣ ከምፑንም ተረክበው በአዲስ መልክ ውጊያ ጀምረዋል። የትግሬ ነፃ አውጪዋን የዋዛ አድርገዋት?

"…ሲጠቃለል አሁን ወደ አገዛዙ የገቡት የምዕራብ ሸዋ ሥርወ መንግሥት ልጆች በእነ ጃልመሮ አገላለፅ ያን ያህል ምንም ዓይነት ተፅዕኖ የሌላቸው፣ እንዲያውም አብዛኛዎቹ የመንግሥት ካድሬ የነበሩ ናቸው ተብለው ተገምግመው ከድርጅቱ በይፋ ቀደም ብለው የተባረሩ ናቸው። የኦነግ ሸኔ በይፋ እንደሚታወቀው ሦስት ክንፍ ነው ያለው። ዋነኛው ኦነግ ሸኔን የሚመራው  መቀመጫውን ወለጋ ያደረገው በጃል መሮ የሚመራው ቡድን ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከዚህ ከምዕራብ ሸዋው አሁን ከገባው ቡድን ጋር የሆነ ሴል አለው የሚባለውና በሁሩጉዱሩ የሚገኘው በጃል ፍቃዴ የሚመራው ቡድን ነው። ይሄ ትናንት በይፋ ሽመልስ አብዲሳ አቅፎ፣ አዳነች አበቤ ስማው፣ ብራኑ ጁላ መርቆ የተቀበላቸው የጃል ሰኚ ቡድን በእነ ጃል መሮ የብልጽግና ካድሬ፣ ዘራፊና ወንበዴ ተብሎ ከድርጅቱ የተባረረ አፈንጋጭ ቡድን ነው። የፍርድ፣ የፍትሕ ቀን ሲመጣ ይሄ አሁን በአደባባይ የተገለጸው፣ በፎቶ፣ በቪድዮ የታየው የጃል ሰኚ ቡድን  በምዕራብ ሸዋ፣ በሰላሌ፣ በደራ፣ በአጣዬና በዙሪያዋ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ላይ የዘር ማጥፋት ሲፈጽም የኖረ ይዘገይ ይሆናል እንጂ የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ሲመጣ ከብልፅግና ጋር የእጁን የሚያገኝ ቡድን ነው።

"…ተመልከቱ ወደ መንግሥት ገቡ የተባሉት በሙሉ የሚለብሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ዩኒፎርም ነው። ከየት አመጡት? አቢይ አሕመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ዱርዬዎቹ ማፍያዎች በኢትዮጵያ ሀብት ወንበዴ አስታጥቀው ወንጀል ሲፈጽሙ ለመቆየታቸው አንደኛው ማሳያ ይሄ ጭምር ነው። ዘረፋ፣ እገታ ሲፈጽም የኖረ ወንበዴን በዚህ መጠን አክብሮ መቀበል ራስን ከማጋለጥ ያለፈ ሌላ የረባ ነገር አይኖረውም። በቀጣይ ሊሆን የሚችለው ብዙ ነገር ነው። ይሄ ገባ ለተባለው ጦር አገዛዙ ፍላጎቱን ማቅረብ አለበት። ቤት መሥጠት፣ ሥራ ማስጀመር አለበት። ለዚህ ደግሞ በሙሉ ዐማራው ከሥራ ይባረራል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ 50 ሺ ሠራተኛ ሊቀንስ ነው ተብሎም እየተወራ ነው። ይሄን ማረድ የተለማመደ ኃይል በከተማ ማስፈሩ ሌላ ወንጀል እንዲበራከት ያደርጋል። በትግራይ ይሄ ሁሉ ወንጀል የበዛው ከጦርነቱ በኋላ ተመልሰው ያለ ሥራና ያለ ትምህርት የተቀመጡ ወጣቶች መብዛት ነው። ገሚሱ ይሰደዳል፣ ገሚሱ ይሞታል፣ ገሚሱ በወንጀል ላይ ተሠማርቶ ይቀመጣል። ሸኔ ግን ለጊዜው እየተንከባከቡት ነው። ወደ ካምፕ የገባውን ፀጉሩን ላጭተው ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ወሎ ይልኩታል፣ የቀረውን ጉራጌን ያጸዱበታል፣ ወደ ደቡብም ያሠማሩታል። ዋና ዋናውን ደግሞ በመርዝም፣ በጥይትም ያጸዱታል። ሸኔንም ሆነ ህወሓት፣ ብልፅግና ኦነግም ያንን ሁሉ ዐማራ አርደው፣ አፈናቅለው፣ አሳብደው፣ ዘብጥያ አውርደው፣ አሰድድው፣ ጨፍጭፈው በድርድር፣ በእርቅ ስም መሸወድ፣ ማምለጥ አይችሉም። አረመኔ፣ ጨካኝ፣ ሰቅጣጭ ርኅራሄ የሌለባቸው ሼምለስ የሆኑት እነዚህ ኃይላት የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ከላይ በፈጣሪ፣ ከታች በዜጎች ፊት ፍርዳቸውን ሳይቀበሉ ለኢትዮጵያ ስርየት የላትም። አይኖራትምም።

• ወዳጄ ከሽኔ ጋ ድርድር 🤝 ከራስ ጋር ንግግር ማለት ነው። አታየውም ጃል ሰኚ የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ለብሶ መግለጫ እንዲሰጥ ሲያደርጉት። ዐማራ ከዚህ በኋላ በክልልህ ሊወጋህ የሚመጣው መከላከያ ፀጉርን የተላጨ ሸኔ መሆኑን ዐውቀህ ግጠመው፣ አትራራለት፣ አትንከባከበው፣ ለመማረክ አትጣደፍ፣ ግባለት። በወለጋ፣ በኦሮሚያ የፈሰሰውን የዐማራ ወገንህን ደም ተበቀል። ዳዊትህን ድገም፣ መስቀልህን አንጠልጥል፣ ቁራንህን ቅራ፣ ዱአህን አድርግ፣ ከዚያ ቤትህ ድረስ የመጣውን አራጅ ጠላት ተበቀለው። ብአዴንንም ከጠላት እኩል ፈርጀው፣ ተዋጋው፣ አስደንግጠው። ጦርነቱን በተቻለ መጠን ከክልሉ አውጡት።

"…በመጨረሻም በኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሚሽን አስደንጋጭ ሪፖርት ርእሰ አንቀጻችንን እንቋጨዋለን። ኦሮሚያ ክልል ህፃናትን ለጦር ስልጠና እያፈሰ መሆኑን ደረስኩበት‼️ ነው የሚለው ኢሰመኮ።

"…በሻሸመኔ ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የገለጹ ሕፃናት" ወታደራዊ ስልጠና ትገባላችሁ" በሚል ወደ ማቆያ አዳራሾች እንዲገቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል። በሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በማቆያ አዳራሽ ከነበሩና ኢሰመኮ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አንድ ሕፃን ደግሞ ዕድሜው 11 ዓመት መሆኑን ገልጿል።ከት/ቤት ሲወጡ ከነዩኒፎርማቸው  ሀሌሉ ወረዳ ወደ ሚገኘው ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት የ15 ዓመት ሕፃናት ወደ አዳራሽ ከገቡ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ገልጸው የገቡበትን ሁኔታም አስረድተዋል።

"…ሕፃናቱ “ከትምህርት ቤት ስንመለስ መከላከያ ለሚገቡ 25,000 ብር ይሰጣል ብሎ አንድ ግለሰብ በባጃጅ አሳፈረን፤ ከዚያ 010 ቀበሌ (ሀሌሉ ወረዳ) ወደ ሚገኘው አዳራሽ ገባን፤ ነገር ግን ከገባን በኋላ መውጣት አልቻልንም ”  ሲሉ ነው የገለጹት። በጅማ ከተማ ኢሰመኮ ያነጋገረው የ14 ዓመት ሕፃን ስለተያዘበት ሁኔታ ሲያስረዳ፦“ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለሁ መንገድ ላይ ቆመው የነበሩ ሚሊሻዎች ባትሪ አብርተውብኝ አስቆሙኝ፤ መታወቂያ ሲጠይቁኝ ዕድሜዬ ገና 14 ዓመት ነው፤ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ መታወቂያ የለኝም ብዬ ስመልስ፣ ቀበሌ ሄደህ ጉዳይህ ይጣራል በማለት ወደ ቀበሌ ወስደው ብዛታቸው ከ20 በላይ ከሚሆኑ ወጣቶች መካከል ቀላቅለውኝ ሄዱ። ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት መያዜንም ወጣቶቹ ናቸው የነገሩኝ። በማግስቱ በድብቅ ለቤተሰቦቼ ደውዬ ካሳወቅኩ በኋላ ለመውጣት ችያለሁ” ብሏል።

"…ይሄ የሚያሳየው ኦሮሞ ሀገር መምራት እንደማይችል ነው። ሥርዓት፣ ሕግ፣ ፍትሕ፣ ሰብአዊነት የሚባለው ነገር ሁሉ ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ ያደረገው ይሄው የኦሮሙማው አገዛዝ ነው። ለራሱ ለኦሮሞው የማይራራ፣ አረመኔ ጨካኝ ቡድን ነው ያለው። እነዚህ ሁሉ ወደ ዐማራ ክልል እንዲጸዱ የሚላኩ ናቸው። የተያዘው የሕዝብ ቅነሣ ነው። እስከ አሁን በከተማ ሲዘንጥ፣ ለምንም ደንታ ሳይኖረው ሲማግጥ፣ ሲያሾፍ፣ በፕራንክ ሲዝናና የከረመው አዲስ አበቤ ደግሞ ቀን ይመጣለታል። ጨለማ ቀን። ተደራጅ ሲባል፣ ተዘጋጅ ሲባል ሲያሾፍ የከረመው ሁሉ ደጁን መከራ ያንኳኳለታል። የኅዘን ድንኳን ከሁሉ ደጃፍ ይተከላል። የማይጨነቅ ኢትዮጵያዊ አይገኝም። ግብጽ በሱማሊያና በአሰብ ጦሯን አስፍራለች፣ ኤርትራ ወደ ትግሬ እየተጠጋች ነው። አረቦቹ በአቢይ አህመድ ትከሻ ላይ ታዝለው ከተማዋን አፍርሰው ደብረ ዘይትን ሳይቀር ሸምተው እየቦረቁ ነው። ትናንት ኒውዮርክ ታይምስ በዚህ ጉዳይ የወቀሳት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ "እጄ የለበትም"…👇③ ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…በትናንትናው ርእሰ አንቀጻችን ላይ የትግሬውን ህወሓት የዓድዋው የስብሐት ነጋን ሥርወ መንግሥት፣ በዐማራ ስም አደራጅተው በጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ ሥርወ ኘንግሥት፣ በጎጃም የፖለቲካው አገው ትግሬ ፈጠሩ ኩሻንኩሽ የአገው ሸንጎው ሥርወ መንግሥትን እና በኦሮሚያም የትግሬ ፈጠሩ ኦህዴድ አሁን በኦሮሞ ብልጽግና የሚመራው የምዕራብ ሸዋው የቱለማ ኦሮሞ ሥርወ መንግሥትን ማየት ጀምረን ነው ሳንቋጨው ለዛሬ በይደር ያቆየነው። አጭር ነው እነሆ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

"…ኦነግ ሸኔ ማለት ማን እንደሆነ ከዚህ ቀደም የሀረርጌው ቆቱ መራታው አፈንዲ ሙተቂ ነግሮናል። አፈንዲ የመሥራቾቹን ስም፣ ለሸኔ ሁሉንም ድጋፍ ያደረጉት ለማ መገርሳና አቢይ አሕመድን ጭምር ነው ጠቅሶ የጻፈው። ለማ መገርሳ ለኦነግ ሸኔ ከምሥረታው አንስቶ ኤርትራም ድረስ በመሄድ ከቡድኑ መሪዎች ከእነ ጃል ዳውድ ኢብሳ ጋር ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተደበቀ ስምምነት በመፈራረም የኦነግን ተዋጊዎችን በትግራይ በኩል በአቦይ ስብሀት ነጋ አቀባበል አድርጎ ከነየጦር መሣሪያቸው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወለጋ በማምጣት ለውጊያ የሚሆን ገዢ መሬት የሰጣቸውም ጭምር እሱ ነው ይባላል።

"…የወለጋው ሸኔ በትግርኛ ተናጋሪዎች የሚመራ ሲሆን፣ ቀጥታ ግኑኝነቱም ከወያኔ መሪዎች ጋር እንደሆነ ነው የሚነገረው። ወያኔ ሥልጣን ባጣ በማለት አስቀድማ አስባ ጊዜ ጠብቀው በየአከባቢው የሚፈነዱና ሀገሪቱን ለማተራመስ ይረዷት ዘንድ ቀደም ብላ በፕላን ቢ ከቀበረቻቸውና ካስቀመጠቻቸው ፈንጂዎች መካከል፣ በጎንደር የፖለቲካውን ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ፀረ ዐማራ አናሳ ዲቃላውን እስኳድን ፈጥራ፣ የጦር መሣሪያ በማቅረብ በጭካኔ የጎንደር ዐማራን ሕፃናት፣ ነፍሰጡሮች፣ ገበሬዎች፣ ወንድና ሴቶችን በሰቅጣጭ ሁኔታ በማገት፣ በመስለብ፣ በማረድ ስታስደነግጥ ኖራለች። የቅማንት ታጣቂዎችን ቢሮ መቀሌና አዲግራት በመክፈት ስትረዳ ኖራለች። ከዚህም በላይ ይሄው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ቡድን በጎንደር የመንግሥት ቢሮክራሲውን በሙሉ፣ ኢኮኖሚውን፣ የጸጥታ ኃይሉን፣ የፍትሕ ተቋማትን፣ የሃይማኖት ተቋማትን እንዲቆጣጠር በማድረግ የጎንደር ዐማራን ጎንደር በተወለዱ ፀረ ጎንደሬዎች እንዲመራ እንዲሰቃይ አድርጋለች። በመቀሌ ሴት ደፍሮ የሞት ፍርድ የሚፈረድበት ወንጀለኛ በጎንደር አርባ ሴት ደፍሮ አርዶም የሚጠብቀው የፌደራል ሹመት ነው። የጎንደር ዐማራ ከቀበሌ እስከ ክልል በፖለቲካው ቅማንት በትግሬ ዲቃሎች የተሞላ ነው። ዐማራውን እንዴት እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት የጎንደር ዐማሮች ደፍረው መናገር በመጀመራቸው ደስተኛ ነኝ።

"…ወያኔ ለጎንደር ቅማንትን ለጎጃም ደግሞ ከሃይማኖት ቅባትን፣ በፖለቲካው አገው ሸንጎን ጠፍጥፋ ፈጥራ ነው የሰጠችው። ጎጃም የፖለቲካውን ሥልጣን፣ የፍትሕ መንበሩን በሙሉ በአገው ሸንጎ እንዲያዝና ራሱ የጎጃም አገው ከዐማራው እኩል አፈር ከደቼ እንዲበላ ነው ያስደረገችው። የአገው ሸንጎም ቢሮው የሚገኘው በመቀሌ ከተማ ነበር። መሪዎቹም ትግርኛ ተናጋሪዎቹ እነ አቦይ ሀደራ ናቸው። ጎጃም ውስጥ ለሚፈጠር የፖለቲካ ችግር መመሪያ የሚመጣው ከመቀሌ ነበር። ወያኔ አናሳ ስለሆነች መኖር የምትችለው ግዙፉን ሕዝብ በማተራመስ ስለሆነ ለጎንደር ቅማንትን፣ ለጎጃም አገው ሸንጎንና ቅባትን አቅፋ፣ ደግፋ፣ ኮትኩታ፣ አሳድጋ ለዐማራም ለኢትዮጵያም ጠንቅ እንዲሆን አደረገችው። አሁን ዐማራ ክልል ገብተው ከኦሮሙማው ትእዛዝ ተቀብለው ዐማራውን የሚወጉት ጀነራሎችና ኮሎኔሎች በሙሉ ወይ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው የጎንደር ስኳድ ነው፣ አልያም የፖለቲካው አገው ሸንጎ የትግሬ ዲቃላው የጎጃም ወይ የዋግ ኽምራ አገው ሸንጎ የትግሬ ዲቃላ ነው። አበባው ታደሰን ተመልከተው አባቱ ትግሬ እሱ የአገው ዐማራ ነው። እንደ ደራው ጄነራል ከኦሮሞ የተዳቀሉም ፀረ ዐማሮች አሉ። የዐማራው ዕዳ ብዛቱ እኮ አስደናቂ ነው።

"…በዚሁ መንገድ ነው በወሎም ለዐማራው ኦሮሞን፣ ለሸዋም ኦሮሞን አስነሣችበት። ወያኔ አስቀድማ ነው ፕላን ቢን ያዘጋጀችው። ለምሳሌ የዐማራን ለም መሬቶች ከወልቃይት እና ከራያ ስትወስድ በኋላ ዐማራ ጉልበት አግኝቶ መሬቶችን ልውሰድ ካለ ከእኔ ከትግሬ ጋር ብቻ እንዳይጋጭ ለምን ከሁሉም ጋር አላጋጨውም በማለት ጎጃምን ቆርሳ መተከልን ለጉምዞች በመስጠት አዲስ ክልል ፈጠረች። ሸዋን ቆራርጣ ብቻ አላበቃችም ደራን ለኦሮሞ ሰጥታ በኦሮሚያ አካለለች፣ በሰሜን ሸዋ የኦሮሞ ልዩ ዞን በማለት በዐማራ በጀት እንዲተዳደሩ፣ የኦነግ ሸኔ ምሽግ ሆነው እንዲቀመጡ አደረገች። በምሥራቅ ሸዋ ብዙ መሬቶች ለኦሮሞ እንዲካለል አደረገች፣ ከወሎ ቆርሳ ለአፋር ሰጠች፣ አዲስ አበባን ከዐማራ አርቃ ባህርዳር ወሸቀች፣ ከርስቱም ነቀለችው። አሁን ዐማራው አቅም አግኝቶ ወልቃይትና ራያን ሲያስመልስ ለኦሮሞ "መስሎሃል ዐማራ አቅም ሲያገኝ በወልቃይትና በራያ አይቆምም፣ መተከልን ወደ ጎጃም፣ ደራን ወደ ሸዋ ላስመልስ ይላል በማለት ዐማራን አስቀድማ ራሷ ቀምታ በጉልበት ያከፋፈለችበትን ርስቱን ሼም አስይዛ እንዳይጠይቅ፣ ሌሎችም ዐማራን ርስት አስመላሽ እያሉ እንዲያንጓጥጡት አድርጋለች። አቤት ሴራዋ…

"…ይሄም ብቻ አይደለም ወያኔ ህወሓት በኦሮሚያም ፕላን ቢ ቀደም ብላ ነው የሠራችው። በ1977 ዓም በትግራይና በወሎ በነበረው ድርቅ ምክንያት ከትግሬ ተነሥተው በሠፈራ ወለጋ የሠፈሩ ትግሬዎችን ለፕላን ቢ መርሀ ግብሯ በሚገባ ነው የተጠቀመችባቸው። እነዚያን ተሰፋሪ ትግሬ ልጆች በትግሬ አስተሳሰብ ቀርጻ አሳድጋ፣ ኋላ ላይ አማፂ አድርጋ፣ መሣሪያ በገፍ አቅርባ፣ ከኦሮሞ ፅንፈኞች ጋር ግንባር ፈጥረው አንድ ላይ ጠላታችን የሚሉትን ዐማራን በጋራ በኦሮሚያ ምድር ሲበቀሉት፣ ሲጨፈጭፉት ኖረዋል። ሰሞኑን ፓስተሪት ማርያማዊት ዩቲዩብ ላይ ቀርቦ ቃለመጠይቅ ሲሰጥ ያየሁት በመቀሌ የሚኖር አንዱ ወያኔ ትግሬም በግልጽ ያመነው ይሄንኑ ነው። "በጃል መሮ የኦነግ ሸኔ ጦር ውስጥ እኔ ራሴ የማውቃቸው፣ ጓደኞቼ የሆኑ የትግራይ ልጆች በብዛት አሉ" በማለት በድፍረት ሲናገር ቪድዮውም አለኝ። ጃልመሮ በትግርኛ የሰጠውንም ኢንተርቪው የሆነ ግዜ የሰማሁ ይመስለኛል። ይሄ ሁሉ መላላጥ ዐማራ የተባለ ነገድን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት፣ እንደ ኮርድ ሀገር አልባ ለማድረግ የሚደረግ ትግል ነው።

"…ኦቦ ለማ መገርሳ ምንም እንኳ ኦሮሙማን ቢተርክም፣ ለኦነግ ሸኔም መመሰርት የራሱን አስተዋጽኦ ቢያደርግም፣ በመጨረሻ ሃይማኖቱን ቀይሮ ጴንጤ ቢሆንም ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመን ሳይሆን ሊቀ ዲያቆን የነበረ መሆኑ፣ ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋር በነቀምት ገብርኤል አብሮ ሲቀድስ መኖሩ፣ ከእስልምና ወደ ጴንጤነት የተቀየረውን አቢይ አሕመድንም ሆነ ህወሓቶቹ፣ የምዕራብ ሸዋው የኦሮሞ ብልፅግና ሥርወ መንግሥት መሥራቾችን ምቾት አልሰጠም። በተለይ ደግሞ ዳንኤል ክብረት በድርጅቱ በኩል ለማ መገርሳን ሲሸልመው ለፀረ ኦርቶዶክሶቹ መንጋዎች ጎረባብጧቸዋል። ለማ መገርሳ ኤርትራ ድረስ ሔዶ ያመጣውን የኦነግ ኃይል ለወለጋ ዐማራ ማጽጃ ወለጋ ወስዶ ሲያሰፍር፣ እነ አቢይ አሕመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ ደግሞ የወለጋው ከትግሬዋ ወያኔም ጋር ሆኖ ሊበላን ይችላል በማለት የራሳቸውን ከሸዋ ዐማራና ኦርቶዶክስን፣ ለወያኔ ስስ ልብ ያላቸውን፣ ለዐማራና ለኦርቶዶክስም የሚቆሮቆሩ የቀድሞ ኦህዴድ፣ ኋላ ኦዴፓ፣ በመጨረሻም የኦሮሞ ብልጽግናን ካድሬና ባለሥልጣናት እስከ ቡራዩ ድረስ እየመጣ…👇①ከታች ይቀጥላል✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል፤ ታጋሽም ከትዕቢተኛ ይሻላል።” መክ 7፥8

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ተራው የእናንተ ነው። እኔ እስከ አሁን 17 ሺ ሰው አንብቦት 21 ፍሬ ሰዎች 😡 ብው ብለው የተናደዱበትን የዕለቱን ርእሰ አንቀጽ ጽፌአለሁ። እናንተ ደግሞ በጎደለው ሞልታችሁ፣ የጠመመውንም አቅንታችሁ በመቀጠል ሓሳባችሁን መስጠት ትችላላችሁ።

"…ሌሎች እንደ ስኳድ ሳሚ ቃኜ ቲዩብ የመሳሰላችሁት ደግሞ ርእሰ አንቀጹን አንብባችሁ በኋላ በቲክቶክ ሥራ ፈትታችሁ ዘመዴ እንዲህ ብሎ የጻፈው ዘመነ ቀጥሮት፣ ወርቁ ከፍሎት ነው እያላችሁ ስታላዝኑ ታመሹ ዘንድ ይሄን አኞ አጥንት የሆነ አጀንዳ ሰጥቼአችኋላሁ። ስታለቃቅሱ አምሹ።

"…ትዊተር ስፔስ እነ ጥሌም ትግሉን ትታችሁ ስለ ወስከንባ፣ ስለ ድብኝት፣ ስለ አክንባሎ እያወራችሁ ነውና ታረሙ። አቶ ክንፉ ወዳጄነህም ወደትግሉ ተመለስ።

"…ድርጅቱ ዶር አምሳሉን መርጦ ቢሰጣችሁም ከወንዴ፣ ከወዳጄነህና ከፓስተር ምስጋናው በቀር ሌሎቻችሁ በጉዳዩ ላይ ሓሳብ እንኳ አልሰጣችሁም። ይሄ ልክ አይደለም። የማስረሻ ሰጤን መልእክት እንኳ አልተወያያችሁበትም። የሸዋ ሮቢቱንም የትናንት ኦፕሬሽን ቀብራችሁታል። ዘመድኩንን ትታችሁ ሥራ ብትሠሩ መልካም ነው ብዬ እመክራለሁ እስኳድን። 😂😂

"…በተረፈ የዛሬውን በይደር የቀረውንና በማይም ዕውቀቴ በገባኝ መጠን የጻፍኩላችሁን ርእሰ አንቀጼን እንዴት አገኛችሁት? እስቲ ቀረ፣ ዘነጋኸው፣ ተዘለለ የምትሉት ካለ፣ የሚስተካከልም ካለ ሓሳባችሁን ስጡኝ።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ "…ዐማራ ባንክን በመላኩ ፈንታና በቲሙ በኩል፣ ሃይማኖቱን በጳጳሳቱ በኩል፣ ዐብንን፣ ብአዴንን በሙሉ ወርሰው ሲያበቁ አሁን ደግሞ የተቃውሞ ፖለቲካውን ለመጠቅለል እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ። ዘመነ ከሤን የጠሉት መስለው በመታየት ነገር ግን ጥላቻቸው በሙሉ የሚዘረገፈው ሙሉ ጎጃምን እንደ ሕዝብ ነው የሚጠሉት። ዘመነ የጦስ ዶሮ ነው። ተመልከቱ ስኳድ በሙሉ ሚዲያውን እንዴት ነው የተቆጣጠረው? ኡጋንዳ ተሰድዶ ሆቴል፣ ከረምቡላ ቤት፣ እርሻ ላይ ከተሠማራው ውጪ ሚዲያውን፣ ዩቲዩቡን የተቆጣጠረው ማነው? ይሄው የጎንደር ስኳድ አይደለምን? የጎንደር ዐማራው እነ አባት አርበኛ ሻለቃ መሳፍንት በእስክንድር ነጋ ተጭበርብረናል ብለው መግለጫ ሲያወጡ መግለጫውን አፍኖ የያዘው ማነው? ይሄው የጎንደር ዐማራ ፀር የሆነው፣ ሥልጣን በዚህም በዚያም ካጣን ወልቃይትን ይዘን እንገነጠላለን ብሎ የሚቃዠው ህልመኛ የስኳድ ቡድን አይደለምን? ከባላደራው፣ ባልደራስ፣ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ ጀምሮ አሁን እስካለው እስከ ድርጅቱ ድረስ ከዳያስጶራ የሚሰበሰበውን ዶላር እስክንድር ነጋን እንደ ማባያ አድርጎ ገንዘቡን ዘርፎ የሚይዘው፣ የሚቆጣጠረው ይሄው የጎንደር ስኳድ አይደለምን? ዶር አምሳሉ አስናቀ በተቃውሞው የዐማራ ፋኖ ስም፣ ወንድሙ የደቡብ ጎንደር የብአዴን ገዢ፣ አስተዳዳሪ፣ የእስክንድር ነጋና የዶር አምሳሉ ሚስቶች ትግሬዎች፣ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል እስክንድር ከዶር አምሳሉ ውጪ ገንዘቤን የሚመራ ሰው ሌላ አልመርጥም የሚለው መስተፋቅር ተደርጎበት ከመሰለህ አባቴ አንተ በኃይለኛው በከባዱ ተሳስተሃል። ሆን ተብሎ ነው።

"…የበለጠ ካሣ ሚዲያ፣ ጣና ሚዲያ፣ አሁን ደግሞ ሚኒሊክ የሳታላይት ሚዲያን እስክንድር በገንዘቡ ነው ነው የገዛው። ከሕዝብ በተዋጣ ገንዘብ። እነ ሀብታሙ አያሌው ቅጥረኛ ናቸው። አበበ በለውን ተመልከቱት። የዚሁ የስኳድ አካል ነው። እናቱ የተከዜ ማዶ ሰው ናት። ጎንደር ላይ የተዋለው ውሎ፣ የተጣባው ኮሶ እና አልቅት በቀላሉ የማይለቅ ቢሆንም እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል ግን አነካክቼ እየሰባበርኩት ስለሆነ አሁን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ የጎንደር ዐማራ የጎንደር ስኳድ ሴራ በሚገባ ገብቶት በመንቃት ላይ ነው የሚገኘው። ለጎንደር ዐማሮች ትልቅ ሸክም ነው ያቀለልኩላቸው። ትልቅ ሾተል ነው የነቀልኩላቸው። አሁን ከጎንደር ዐማራ ላይ የተነቀለው ሾተል ያለበት አካባቢ የሚገኘው ቁስል ቢጠዘጥዘው ነው እንጂ መፈወሱ አይቀሬ ነው። ይኸው 300 ሾተላይ የትግሬ ዲቃላ ከእነ ሀብቴ ግሩፕ ወጥቶ ወደ ብአዴን ብልፅግና ሰተት ብሎ የገባው እኮ መረፊያ ሜዳ ስላጣ ነው። በጎንደር ስኳድ በእስክንድርና በአምሳሉ በገፍ ይሰበሰብ የነበረው የዳያስጶራ ዶላር ስለጠረረ፣ ስላረጠ፣ ስከተቋረጠ፣ ስለደረቀበት ነው። 300 ውን ተከትሎ ሰሞኑን በጎንደር የጎንደር ዐማራን ሲያግት፣ ሲዘርፍ፣ ሲገድል የነበረው የቅማንት ታጣቂም ለመንግሥት እጁን ሰጠ የተባለው የጎንደር ዐማራ የእነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም አዚም ስለተራገፈለት ነው። እነ በረደድ፣ እነ ዶክተር ደረጄ፣ እነ ሚኪ ጠሽ ትኩስ ድንች፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ አያሌው መንበርን የመሳሰሉ ስኳድ ሁሉ ድራሽ አባታቸው የጠፋው የጎንደር ዐማራ ስለነቃ፣ ስለባነነ ነው። ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። እኔ አጀንዳ እሰጠዋለሁ እሱ እኔ ላይ ሲያፈጥ በምድር ያለው ዐማራ በሰላም ይደራጃል። እኔ እነሱን ይዤ እጋተታለሁ አለቀ።

"…ይሄን የትግሬና የዐማራ ሥርወ መንግሥት ያየው፣ የተመለከተው፣ ከሥር ከሥር ብሎም ሲቀጽል የኖረው የኦሮሞው አዲሱ ገዢም እኔም ለምን ይቅርብኝ ብሎ ያንኑ መንገድ በሰፊው ተከተለው። በአቢይ እና ለማ ቲም የተመሠረተው የኦሮሙማው አገዛዝም ገና ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ነበር የኢትዮጵያን የፖለቲካ የስህበት ማዕከል በሸዋ ኦሮሞ ላይ ያውም የምዕራብ ሸዋ ኦሮሞ ላይ አድርጎ መንቀሳቀስ የጀመረው። ቀደም ሲል የኦሮሞን ፖለቲካ የተቆጣጠረውንና በእነ አቶ ጁነዲን ሳዶ የሚመራውን የአርሲ የኦሮሞውን የኦሮሞ አክራሪ የወሀቢያ እስላም ሥርወ መንግሥት ቡድን ድራሽ አባቱን አጥፍቶ ነው የምዕራብ ሸዋው የጴንጤ ኦሮሞ ቡድን ሥልጣኑን የተቆጣጠረው። ኩርፊያ እንዳይኖር የወለጋ ጴንጤዎችን እና የጅማ እስላሞችን ጥቂት ፍርፋሪ ወርውሮ ነው ሥልጣኑን በእጁ ያስገባው። ለዚህም አጋዥ ይሆኑት ዘንድ ከወሎ ገዱ አንዳርጋቸውን፣ ከጎንደር የተገደሉትን የደቡብ ጎንደር የብአዴን ባለሥልጣናት በሙሉ ይዞ ነበር የመጣው። የምዕራብ ሸዋው ጋንግሥተር የጁነዲን ሳዶን የአሩሲ እስላም ኦሮሞ ሥርወ መንግሥት ለመናድ የተጠቀመው መሰረቷ ኦርቶዶክስ ሆኖ የምዕራብ ሸዋዋን አዳነች አቤቤን ነበር ናዝሬት በመሾም የሳዶን ኔትወርክ ብጥስጥሱን ያወጣው። አዳነች የአሩሲ ሰው እንጂ የምዕራብ ሸዋ ሰው መሆኗን የማያውቅ ሰው የትየለሌ ነው።

"…አቢይ አህመድ ለሸገሯ መዓዛ ብሩ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ወሎዬ እናቱን ወይዘሮ ትዝታን የምዕራብ ሸዋ ሰው፣ የአዲስ ዓለም ማርያም ሰው አድርጎ በማቅረብ ነበር ቃሉን የሰጠው። እናም እሱም ራሱ ዐቢይ አሕመድ አሊ ራሱን የሚቆጥረው እንደ ምዕራብ ሸዋ ሰው ነው ማለት ነው። ስለዚህ ምዕራብ ሸዋዎች ልክ እንደ ዓድዋው ሥርወ መንግሥት የኦሮሞን አስኳሉን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ክንፍ ተቆጣጠሩ። ሰፋ ሲያደርጉት ደግሞ ሙሉ ሸዋን በስሱ፣ ወለጋንና ሌሎችን በአጃቢነት ያካትታሉ። ጦሩ የሰማዩም ምዕራብ ሸዋ ነው። የምድሩም ሸዋ ሻሸመኔ ነው። ወርቁ በታከለ ኡማ ነበር የተያዘው፣ ታከለ ኡማ ምዕራብ ሸዋ ነው። ኦሮሚያን ገዢ አድርገው ያስቀመጡት የጊንጪው ሽመልስ አብዲሳ ነው። ዘርዝሯቸው፣ ፌደራል ፖሊስ በምዕራብ ሸዋው ደመላሽ ስር ነው። አንድም የቀራቸው የለም። ጀዋር መሀመድ ራሱ እስላም ስለሆነ በጴንጤ በሚመራው በምዕራብ ሸዋው ሥርወ መንግሥት ሥር አልተካተተም እንጂ እሱም ቁጥሩ በእናቱ ኦርቶዶክስ ሸዋ በአባቱ አሩሲ ነው። እነ ሀጫሉ፣ አሁን ያሉት አዝማሪዎች፣ ቲክቶከሮች ሳይቀሩ በብዛት ምዕራብ ሸዋ ናቸው። ኦፌኮ መራራ ጉዲና ሳይቀር ሸዋ ነው። ምዕራብ ሸዋ። በቀለ ገርባ ኦሮሞም፣ የጴንጤ ፓስተርም ቢሆን ነገር ግን ወለጋ ስለሆነ በካልቾ ተጠልዞ ተባርሯል። መራራ ጉዲና እንደ አቦይ ስብሃት እንደልቡ የሆኑት በመልካቸው ቆንጆ፣ በእውቀታቸው ምጡቅ ከመሰሉህም ተሳስተሃል። ምዕራብ ሸዋነት፣ ጊንጪ፣ አምቦ፣ ጉደር፣ አድአ በርጋ፣ ሜታ ሮቢ…ነው ጨዋታው አባቴ። ሸዋን ማዕከል አድርገው ነው የአሁኑ ኦሮሙማ ኢኮኖሚውን፣ ሥልጣኑን፣ ባንክና ታንኩን ይዞ ወጥሮ እየገዛህ ያለው። የሲሚንቶ ንግድ በሽመልስ አብዲሳ ቤተሰብ ሥር እንዲወድቅ የተደረገው በስህተት ይመስልሃል እንዴ? ወይስ በአጋጣሚ? ሃኣ…?

"…የምዕራብ ሸዋው ቡድን ከምዕራብ ሸዋ የወጣውን እነ ጄነራል ብርሃኑ በቀለን ዐማራ ላይ አዝምቶ እየጨፈጨፈም ቢሆን ሁለት ነገር ይጎድለው ነበር። እንደ መራራው ኦፌኮ ዓይነት በሰላማዊ መልኩ የሚንቀሳቀስ የራሱ የሆነ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳይሆን ፕላን B የታጠቀ የተቃዋሚ ፓርቲና የራሱ የሆነ የሃይማኖት መሪ። እሱ ይጎድለው ነበር። ደርግም የራሱ ፓትርያርክ ነበረው። የንጉሡ ናቸው የተባሉትን አንቆ ገድሎ። ወያኔም የራሷ የሃይማኖት መሪ ፈጥራ ነበር። ደርግ የሾመው ነው ያለችውን በካልቾ ጠልዛ አባራ። ኦሮሙመው የምዕራብ ሸዋ ኢምፓየር የቀረው እሱ ነበር። እናም እሱን ለማምጣት አማካሪ ያስፈልገው ነበርና ከወሎዬዎቹ አሁን ከተሰደዱት ከእነ ገዱ አንዳርጋቸውን እና ከታሰሩት ከእነ ዮሐንስ ቧ ያለው መካከል በሕይወት የቀረው…👇② ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…እኔ ወዳጃችሁ ዘመድኩን ነቀለ… ከአጎት ሀገር ጀርመን ሆኜ ለተለያዩ አካላትም አጀንዳ ይሆን ዘንድ ለዛሬ ደግሞ ስለ ዓድዋው፣ ጎንደሩና ምዕራብ ሸዋው ሥርወ መንግሥት የሚያወሳ ልክ እንደ ኮሶ፣ መተሬ ያለች ፈዋሽም የሆነች ርእሰ አንቀጽ ነው ያዘጋጀሁላችሁ።

• ለማንበብ ዝግጁ…?

Читать полностью…
Subscribe to a channel