zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ፩

"…ሲጀመር ያን አረመኔያዊ አሰቃቂ ድርጊት ማንም ይፈጽመው ማን የተወገዘ ይሁን፣ ድርጊቱን እንዳየ ሰው፣ መረጃው እንዳለው ሰው የድርጊቱን ፈጻሚዎች የሚያውቅ ሰው ካለ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ለሕግ ይቅረቡ እንኳን አልልም። እንደተያዙ ይሰቀሉ፣ ይገደሉ። ይህ አቋሜ ይመዝገብልኝ።

"…ወደ ጥያቄዬ ስገባ… ሰውየውን ዛሬ መግለጥ የማልፈልገው የጉርሻ ፔጅ ባለቤት ልክ እንደ ባሕርዳሩ የጎንደር ስኳዶች በሕጻን ፌቨን ጉዳይ እንደሠሩት ቲያትር ዛሬም ከሁሉ ፈጥኖ በመምጣት ሟቹ፣ የታረደው ልጅ ይሄ ነው ብሏል። አዩ ዘሀበሻም እንደዚያው የታረደው ልጅ ይሄ በፎቶው ላይ የሚታየው ታዳጊ ወጣት ነው ብሏል። አንድ የኦነግ ፔጅም እንዲሁ የዚህን ልጅ ፎቶ ነው ይዘው የወጡት።

• ልጁ ግን የተገደለው በብልጽግና ሚልሻ ነው። ለምን በብልጽግና ሚሊሻ የተገደለን የኦሮሞ ወጣት "በስመ አብ ብለህ እረደው" የሚል አጃቢ ቃል በመጠቀም በግፍ በአሰቃቂ ሁኔታ ያረዱትን ዜጋ ሞት በዚህ ልጅ ፎቶ መሸፈን ተፈለገ።

• በፎቶው ላይ የሚታየው ልጅ የታረደው ሰው እንዳልሆነ ከራሳቸው ከኦሮሞዎቹ ሚዲያ ያገኘሁትን ማስረጃ ቀጥሎ አቀርባለሁ።

• ጉርሻና አዩ ዘሀበሻ መረጃውን ከየት አገኛችሁት? ብልፅግና የገደለውን ምስኪን የኦሮሞ ወጣት በግፍ ከታረደ፣ ማንነቱ ካልታወቀ ዜጋ ጋር ለማገናኘት ለምን መረጣችሁ…?

• እመለሳለሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የአስተያየት መስጫ ሰንዱቄን ጠርቅሜ አንዲት አነስተኛ ቀጭን የግል ጉዳዬን ለመፈጸም ወጣ ብዬ ስለነበር ነው የጠፋሁት። በእኔ ቤት ልማድ ደግሞ እኔ የእሳት ሰይፌን ይዤ በማልቆምበት የአስተያየት መስጫ ሰሌዳ ላይ፣ ሰፈሩን የሚረብሽ ዋልጌ መጥቶ ትርምስምስ ሊያደርግ ስለሚችል ሰንዱቁን ዘግቼ፣ ቆልፌ፣ ጥርቅም አድርጌ ነው የምሄደው። አሁን ተመልሼ መጥቻለሁ እናንተም ሓሳብ አስተያየታችሁን መለገስ ትችላላችሁ።

"…ከዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ በተሰጠው የአቋም መግለጫ ላይ ሓሳባችሁን ማካፈል ትችላላችሁ።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ወደ ጉዳዬ በመሄድ ላይ ሳለሁ፣ ሌላኛው የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ የጦር አለቆች ደውለውልኝ አውርተውኝ ነበር። ልክ እንደ 7ለ70 ው ብርጌድ እኛም የአቋም መግለጫ አውጥተናልና ሳትጨምር፣ ሳትቀንስ ለሕዝብ አሳውቅልን ብለው ጠይቀውኛል። እኔም መግለጫቻችሁን በጽሑፍ እና በቪድዮ ካቀረባችሁልኝ ምን ገዶኝ ብዬ መልሼላቸዋለሁ። የጽሑፉም፣ የቪድዮውም ደርሶኛል እሱን ደግሞ በነገው ዕለት እለቅላችኋለሁ።

• አሁን ወደ ዛሬው ሓሳብ አስተያየት መስጫ ሳጥናችሁ ከፈታ እንሂድ። 1…2…3… ጀምሩ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…አሁን ደግሞ በቀጠሮ ወደ አሳደርነው በቪድዮ ወደ ተዘጋጀውና ከዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ ወደተሰጠው የአቋም መግለጫ እንገባለን።

• ወገን ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቀን 10/3/2017 ዓ.ም

"…ከዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ…

"…የነገ ጠዋት ርእሰ አንቀጻችን ነው። ሙሉውን ጠዋት ይጠብቁ። ነገ ጠዋት ከእግዚአብሔር ሰላምታ 1ሺ ሰው ከመሰገነ በኋላ ይቀርብላችኋል።
 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ቁምነገር ጠይቄ በቁምነገር ምላሽ የሰጡኝ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ሊመሰገኑም ይገባል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ በኢንቦክስ በውስጥ መስመር ማውራት የምትችሉትን ነገር በአደባባይ፣ ስንት ቁምነገር በሚወራበት ፔጅ ላይ ከርእሱ ጋር የማይገናኝ ሓሳብ አንሥታችሁ ስትጨቃጨቁ ሁላ አያለሁ። ይሄ ቢስተካከል ጥሩ ነው። ፔጁ የቀልድ፣ የነቆራም ቀን አለው አይደል? የግል ጉዳያችሁን በውስጥ መስመር አውሩ።

"…ስለመርካቶ እያወራን ነው። አትቀልዱ። የተደገሰው ድግስ ቀላል አይደለም። በቀልድ፣ በዋዛ፣ ፈዛዛም፣ በቧልትም አትለፉት። ፔጁን ለሚያነቡ ሰዎች ግሩም ሓሳብ ለማዋጣት አቅምና ጊዜ ያጠራችሁ ሰዎች ቢቻል ዝም ብትሉ መልካም ነው።

"…እውነት ነው መርካቶ ሃይማኖት ታይቶ፣ አንገትህ ላይ መስቀልና ክር ካለ የ100 ብሩን ዕቃ 500 ብር እንደሚያስገዙ ከተነገረ ቆየ። "ለሁሉ ሽጥ፣ ከራስህ ወገን ግዛ" ብለው በተለይ እስላሞቹ፣ አሁን ደግሞ ፕሮዎቹ ኢኮኖሚውንም፣ አስመጪና ላኪነቱንም ጭምር በመቆጣጠር በተለይ ኦርቶዶክሱን ክፍል ሸማች ብቻ አድርገው እንደቆረቆዙት ይነገራል። እሱ እንዳለ ሆኖ ግን መርካቶ ኦሮሞ የለም ብሎ ነገሩን በሚዲያ ማጮህ ቀጥሎ ምንድን ቢያስቡ፣ ወይም ቢያቅዱ ነው።

"…ንግድ ክህሎት እና የፀጋ ስጦታ እንጂ የሚያስፈልገው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌና ዐማራ መሆን በራሱ ምን ይፈይድልሃል? በዘመነ ወያኔ ከግብር ነፃ የተደረጉ በዘራቸው ትግሬ የነበሩ ነጋዴዎች እርግጥ ነው ተጠቃሚ ነበሩ። ሥርዓቱ ሲወድቅ ግን አብረው ነው የወደቁት። ኦሮሞም ለወያኔ የተደረገው ይደረግልኝ እያለ ነው። የእኔ ምክር ሥርዓቱ ሲወድቅ ትወድቃለህና ይልቅ በፀጋህ ጠንክረህ ሥራ።

• ዛፍ ቆራጭ
• ጣሪያ ቀዳጅ
• አራሽ
• ቀዳሽ
• ተኳሽ
• ደጓሽ ወዘተ ሁሉም በፀጋው ቢኖር እላለሁ። ድግሱ ግን ሌላ ይመስላል።

• ከሳትኩ ልታረም…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ስለ መርካቶ እናውራ አስቲ…

"…ትናንት በአዲስ አበባ መርካቶ የመርካቶ ነጋዴዎች ሱቃቸውን ዘግተው ነበር ሲባል ሰምቼ ነበር። ግርግርም ሁላ ተፈጥሮ ነበር ነው የተባለው። ነጋዴዎቹ ሱቃቸውን ለምንድነው የዘጉት…? ምንሆነው ነው? ምን በደል ተፈጽሞባቸው ነው? ትናንት ሱቅ የዘጉት ዛሬስ ከፍተዋል ወይስ ዛሬም ሱቃቸውን እንደዘጉ ነው?

"…እስቲ ስለ መርካቶ የምታውቁትን ሁሉ ስጋታችሁን ጭምር አስረዱን። ጥፋቱ የማንነው? የአገዛዙ ወይስ የነጋዴው? ጎበዝ ለመርካቶ ምን ታቅዶላት ይሆን…? …ከቦታው፣ ከሁኔታው ለራቅን ለእንደ እኔ ዓይነቱ እስቲ ገለጻ ስጡን።

• አመሰግናለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤” ምሳ 23፥17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።” መዝ 3፥5

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:15 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ እጅግ ሞቅ ደመቅ ያለ ነው። ተሰብስባችሁ ጠብቁኝ። ከበድ፣ ከበድ ያሉ መረጃዎችም የሚለቀቁበት ዕለት ነው ዛሬ።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/tOwBnDIMQgA
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"… ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።ሰቆ ኤር 3፥ 22-23።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችጀሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…8

"…ዛሬ ባሕርዳር ውስጥ በተከሰከሰችው ሂሊኮፕተር ውስጥ የነበሩት እነማን ይሆኑ? ጠይቅልን ተብዬ ነው።

• እየኮመታችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…6

ሀብታሙ አፍራሳ አንሥቶታል…

"…አዝማሪ አበበ በለው ጎንደሬ ስለሆነ የዐማራን ትግል የሚከፋፍሉትን፣ ጎጃምን በዘመነ ካሤ ምክንያት እንደ ሕዝብ የሚጠሉትን፣ ፋኖ ዳዊት ደግሞ፣ መስቀል አንጠልጥሎ ለምን ይዋጋል ብሎ በግልጽ ፀረ ኦርቶዶክስነቱን ላስመሰከረው ለፓስተር ምስጋናው ጣና ቴቪ በግልጽ ማስታወቂያ ሠርቷል።

"…የአበበ በለውን ማስታወቂያ መሥራት ተከትሎ አበበ በለውን ጆሮውን ጠምዝዞ ቁጭ ብድግ አድርጎ የሚያሽቆጠቁጠው ሀብታሙ አያሌውም ማስታወቂያውን ሠርቶት ነበር። ስኳድና ሀብታሙ አይንእና ናጫ ቢሆኑም አሁን ግን አለቃቸው ዶር አምሳሉ አስናቀ የባልደራስም፣ የግምባሩም ገንዘብ እያለቀ ስለሆነ ሰብሰብ ብላችሁ ወደ አንድ ምጡ ብሎ የበረሀው መሪያቸው እስክንድር ነጋም በማዘዙ ምክንያት ነው የግድ ወደ አንድ ለመምጣት የሚታትሩት።

"…ሀብትሽ የዓየሩን ፀባይ ካየ በኋላ ግን የአራዳ ልጅ ስለሆነ የእነ ምስጋናውን ማስታወቂያ ከፔጁ ላይ አንሥቶታል። አሁን ከእኔ ልጥፍ በኋላ ዶር አምሳሉ ተቆጥቶት መልሶ ካልለጠፈው በቀር ለጊዜው አንሥቶታል።

• እየነቆራችሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

"…አንባቢ ተመልካች አድማጮቻችን በቀድሚያ ይሄን አጅግ አስተማሪ የሆነ ቪድዮ ደጋግማችሁ ተመልከቱት። ከዚያ ቪድዮውን ዓይታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከቪድዮው ያገኛችሁትን ቁምነገር በገባችሁ መጠን ግጥም ግጠሙበት። 😂

• ከቪድዮው ምን ተማራችሁ? አትፍሩ በግጥም ግለጹት። ቤት ይምታ እንጂ ሽግር የለውም። ግጥምን ማንም ከእናቱ ሆድ ተምሮ አልወጣም። ሞክሩት። ኤት አባቱንስና።

• ተቀበል…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 2

"…ባሕርዳር ላይ ሂሊፕተሯ ነዳጅ ጨርሳ ወደቀች…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት "የተቀበል" መርሀ ግብራችን አሁን በይፋ ተጀምሯል። ትናንት እና ከትናንት ወዲያ ሌሊት እስከንጋት ድረስ በትዊተር ስፔስ ስሜ ተደጋግሞ ስለተጠራ የተጠራሁበት ቤት በአካል ገብቼ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱን ግሪሳ፣ የጎንደር ዐማራ ካንሰር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን የስኳድ መንጋ፣ ፀረ ዐማራ እና በኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ እህት በወሮ የሺ የሚመራውን የዋን ዐማራ ገዳይ ቡድን፣ እነደእነ አቶ ወዳጄ የመሳሰሉትን ጥርብ ፍልጥ የደርግ ጨፍጫፊ ወታደር፣ የግንቦት 7፣ ኋላ ኢዜማ፣ አሁን ደግሞ የእስክንድር ደጋፊ የሆነ ሰካራም የኒውዮር ገልቱ የሆነ የራሱን ትውልድ ቀርጥፎ በልቶ የአሁኑን ትውልድ ሊበላ ያሰፈሰፈ፣ የመጪው ትውልድ የዕድሉ ደንቃራ የሆነ ፀረ ዐማራ እከክ ልክ ሳስገባ፣ ሥርዓት ሳስይዝ አምሽቼ ሊነጋ ሲል ተኝቼ አርፍጄ ነው የተነሣሁት።

"… የስፔሱን ባለቤት በብዕር ስሟ ዳማከሴን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። አምርራ ትጠላኝ የነበረች እህት ብትሆንም የቤቷ አለቃ ሁላ አድርጋ ሥልጣን እስከመስጠት ስለደረሰች ዝቅ ብዬ እጅ ነሥቼ አመሰግናታለሁ። ከሀብታሙ በቀለ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከጄ ብሩ፣ እና ከሌሎች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚከብዱ ስላልሆነም አመሰግናለሁ። እስክንድር ስር የተኮለኮለውን የስኳድ እና የግንቦቴ መንጋ ግን አልፋታቸውም። ለጌዜው የእነዚህ ገተቶች አለቃና መድኃኒታቸው ነኝ። አለቀ። ምንም አባህ አታመጣም።

"…ወደዛሬው መርሀ ግብራችን ስንመለስ…

• ግጥም
• ነቆራ
• መረጃ
• ጥቆማ
• ጥያቄና መልስ ያላቸው ውይይቶች ይኖሩናል። የሚያስቁ፣ ፈገግ የሚያሰኙ አጫጭር ቪድዮዎችን፣ ጥቅሶችን፣ ሥዕሎችንም በውስጥ መስመር ላኩ። እኔ ለመቶ ሺ አድማጭ ተመልካቾቼ በመለጠፍ ዘና ፈታ ስንል እናመሻለን።

• አሁን ለአዝማሪው የመነሻ ግጥም ስጡት።

• 1…2…3✍✍✍ ጀምሩ

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዝም አላልኩም… ነገር ግን እጠይቃለሁ።

"…እነ ቶሎሳ ኢብሳ በሌላ መልኩ ቀደም ብለው የገለጹት። አረመኔያዊው ድርጊት የተፈጸመበት ቦታና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ዐማሮች ያለመሆናቸውን የገለጹበትን መልእክት ሰማሁ፣ አየሁ።

"…ቀጥሎ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሚዲያዎችን አክቲቪስቶችን እና እስላማዊ ጂሃዲስቱን የኦኤም ኤንን ዘገባዎች አየሁ። ተመለከትኩ።

"…በመቀጠል የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሚዲያ ደጋፊ ሆነው የተከሰቱትን ደሩ ዘሀረሩ እና ሰሞኑን የወረመች አንዲት አውሮጳ የምትኖር የአዲስ አበባ ትግሬ በድርጊቱ አዝነው ዐማራን ከኦሮሞ ለማቀሳሰር የሰሩትን ቪድዮም ተመለከትኩ። አቤት መዝቀጥ።

"…ቀጥሎ አረመኔያዊውን ድርጊት በሚመለከት የእያንዳንዱን የኦሮሞ አክቲቪስት እርስ በእርስ የሚጋጭ መልእክቶችን ተመለከትኩ። መረጃዎችንም አስቀርቼ አድፍጬ ተቀመጥኩ።

"…በመጨረሻ ግን ኦሮሞዎቹ እንኳ ይስተካከል ያሉትን ጉዳይ ጉርሻ የተባለ አውርቶ አደር የብልፅግና አጀንዳ አራጋቢ የዐረብ ሀገር ወሬያም እና አዩ ዘሀበሻ በግድ ለዚህ ነገር ምላሽ እንድሰጥ፣ ጥያቄም እንድጠይቅ አስገደዱኝ።

• አረመኔያዊውን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ለማጥራት እኔ ዘመዴ ጥያቄ በመጠየቅ ብጀምርስ?

• መጠየቅ ልጀምር…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ይህ ከዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ነው።

"…መግለጫው መጀመሪያ በጽሑፍ የደረሰኝ ሲሆን፣ እኔም ቪድዮ ይታከልበት፣ ማብራሪያም እፈልጋለሁ ባልኩት መሠረት የብርጌዱ አመራሮች ደውለው አግኝተውኝ ማብራሪያም ሰጥተውኛል።

"…7 ለ70 ብርጌድ የተለየው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከሚመራው አዲሱ የአፋሕድ እንጂ ከዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እንዳልሆነ በቃል በሰጡኝ ማብራሪያ ላይ ገልጸውልኛል።

"…የብርጌዱ አመራሮች ተራ በተራ በሰጡኝ ቃል ላይ ይህንን መግለጫ የሰጡበትን ዋና ምክንያቶች 6 ነጥቦችን በማንሣት በዋናነት ግን "ችግራችንን በውይይትም ሆነ በንግግር መፍታት ከማንችልበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን ምክንያት ነው ብለዋል።

"…አመራሮቹ በአጽንኦት አጥብቀው የነገሩኝ ነገር ቢኖር የሚዲያና የጋዜጠኞች ገለልተኛ የመሆን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ ያነሱት ጉዳይ ነው። እኛ የምንሰጣቸውን መግለጫዎች ለራስ ፖለቲካ ጥቅም ማስፈጸሚያነት ማዋል ተገቢ አለመሆኑንም አበክረው አሳስበዋል።

"…የአራቱም ግዛት የፋኖ አድንደነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አንድነት ይመጣ ዘንድ የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የተናገሩት አመራሮቹ ይህ የሰጠነው መግለጫ ግን ከእስክንድር ድርጅት መውጣትና መለየታቸውን ብቻ በተመለከተ እንጂ አርበኛ መከታው ከሚመራው ከጠቅላይ ግዛቱ የፋኖ አደረጃጀት ስለመውጣታቸው እንዳልሆነ ደጋግመው አደራ ዘመዴ በማለት አሳስበውኛል። እኔም ይሄንኑ አደራቸውን ሳልቀንስ፣ ሳልጨምር እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ። ለመግለጫው እኔን የመምረጣቸውም ምስጢሩ የእኔን ባለማዕተብ መሆን በመተማመን መሆኑን ልብ ይሏል።

• ሙሉ ቪድዮው ይኸው። ሙሉ መግለጫውንም አብሬ እለጥፋለሁ።

• ይኸው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው። ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፤ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም። ሶፎ 3፥ 3-5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እውነቱን ተጋፈጡት…

"…ብዙ ሰዎች ይሄን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ቃለ መጠይቅ ሊንክ እየላኩ ዘመዴ እስኪ አዳምጠው ይሉኛል። ዓይቼው ምላሽ ሳልሰጥ ዝም እላለሁ። ተደጋገመ፣ አሁንም ዝም። አሜሪካ የሚገኝ አንድ አብሮአደጌ እና በዚህ በጀርመን የሚኖሩ አንድ ወዳጄም ይሄንኑ ሊንክ ላኩልኝ። ለእነርሱ ግን መለስኩላቸው። ከዚያ በችርቻሮ ከምመልስ ለምን በጅምላ አልመልስም ብዬ መጣሁ።

"…ለማንኛውም ይሄ የኮሎኔሉና የጋዜጠኛ በለጠ ካሣ ቃለመጠይቅ የቆየ ነው። አሁን እኮ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ናዝሬት አዳማ ደርሶ ከመጣ በኋላ ሰውነቱ ውልቅ ብሎ ከስቷል። ጋዜጠኛ በለጠ ካሣም ከኢትዮጵያ ተሰድዶ ኡጋንዳ ከገባ ዓመት አለፈው። እናም የቆየ ቃለመጠይቅ እያመጡ ይሄ ሕዝብ አንድ ጊዜ ሾርት ሚሞሪያም ተብሏል ተብሎ በሕዝብ የማወቅ መብት ላይ መቀለድ፣ ማላገጥ፣ ማሾፍ ትክክል አይደለም። ነውር ነው።

"…በወልቃይት ጉዳይ እኮ ምን እንደሰሙ ባላውቅም እነ አያሌው መንበር፣ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም፣ ሙሉዓለም፣ ሙላት አድኖ፣ ጋሻው መርሻ፣ ሲሳይ ሙሉ፣ እነ ጥላሁን ጽጌ ወዘተ፣ ሁሉም ዝም ጭጭ ብለዋል። 😂 ትዊተር ስፔስ ላይ ይንጫጩ የነበሩት ጫጫቴያሞች ሁሉም ኩምሽሽ ካሉ ቆዩ። ስለወያኔ ኃጢአት እንኳ መጻፍ ያቆሙ ሞልተዋል። ስለወልቃይት ጉዳይ የአሸቦ ዕቃው ሲሳይ አልታሰብም እንኳ ጮጋ ብሏል።

"…ይልቅ ጎንደሬ ነኝ፣ የጎንደር ዐማራ ነኝ ሲል የከረመው ግሪሳ በሙሉ ሰሞኑን ወልቃይት ነህ ዐማራ? ወልቃይቴ ነህ ትግሬ? ተብሎ ሳይጠየቅ እኔ ወልቃይቴ ነኝ የሚሉ በዝተዋል? ምን ቢሰሙ ነው በአንድ ጊዜ ከዐማራነት፣ ከጎንደሬነትም ዘጭ ብለው "ወልቃይቴ" ነኝ ማለት የጀመሩት ብሎ መጠየቅ ይበጃል። በወልቃይት መከላከያና የደመቀ የተከዜ ዘብ ጦር እንጂ ፋኖ እንኳ የለም።

• ምን ለማለት ፈልጌ ነው? ቃለመጠይቁ የቆየ ነው። አከተመ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሦስት ነገር…

፩፦ አገዛዙ የሚለው ነጋዴው ሱቁን የዘጋው በደረሰኝ ሽጥ ስንለው በደረሰኝ አልሸጥም ብሏል። ስለዚህ በግድ በኃይልም ቢሆን በደረሰኝ እንዲሸጥ ይደረጋል ነው የሚለው የሚሉ አሉ። ከዚህ በተጨማሪም እሳት አደጋ በመርካቶ እሳት ሲነሣ ማጥፋት ስለተቸገርኩ መርኬ ይፍረስና መልሶ ይልማ የሚል ምክረ ሓሳብ ማቅረቡንም ነው የሰማሁት።

፪ኛ፦ ነጋዴው ሱቄን የዘጋሁት ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ኃይሎች በየጊዜው እየመጡ ንብረታችንን ጭነው ያለከልካይ ስለሚወስዱብን፣ በየቀኑ መዋጮ እያሉ ስላሰለቹን፣ ስላዛጉን ነው የዘጋነው ነው የሚሉት የሚሉም አሉ?

፫ኛ፦ ሌሎች ሦስተኛ ሓሳብ የሚሰጡት ደግሞ "ወያኔ ኦሮሞን ከመርካቶ ነቅላ አባርራለች፣ በመርካቶ የኦሮሞ ነጋዴ የለም። በመርካቶ ጉራጌ፣ ትግሬና ዐማሮች ናቸው የሚነግዱት። እናም ይሄን ለማመጣጠን ትግሬዎቹ ጉራጌንና ኦሮሞን አፈናቅለው ንግዱን እንደተቆጣጠሩት አሁንም በዘመነ ኦሮሞ መርካቶን ከጉራጌ፣ ከትግሬና ከዐማራ አጽድተን፣ ወይም አመጣጥነን ኦሮሞን በመጨመር መርካቶን የሁላችንም እንድትሆን እናደርጋታለን ነው የሚሉት የሚሉም አሉ። ስለዚህ የትኛው ነው ትክክል?

"…የእኔ ሓሳብ አቢይ አሕመድ በሦስተኛው የኮሪደር ልማት ልክ ከዚህ በፊት ፒያሳንና ካዛንቺስን እንዳጸዳው አሁንም በእሳትም፣ በግርግርም ይሞክረውና፣ የነጋዴውን ኅብረት፣ አንድነት፣ ሙቀት ከለካ በኋላ በግሬደር ያርሰዋል። የሰው ወኔ እንደተሰለበ ስላወቀ፣ በሁለት ሳምንት ውስጥ መርካቶን ለቅቀህ ውጣ ይለዋል። ከዚህ በፊት አትክልት ተራን እንዳደረገው ማለት ነው። እንደዚያ የሚያደርግ ይመስለኛል።

• የዚህ ነገር መጨረሻው ምን ይሆን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የአወሮጳው ምች…

"…በኢትዮጵያ ተልባ፣ ቅባት ያለበት ምግብ በልተህ፣ አፍህን ሳትታጠብ ወጥተህ ፀሐይ ቢያገኝህ ምች ድብን አድርጎ ይመታሃል። ከዚያ ነው ዳማከሴ እና ፌጦ ጤና አዳምም ወደመተሻሸት፣ ጨምቀህ ወደመቀባባት የምትሄደው። የአውሮጳው ምች ግን ይለያል። ብርድ፣ ቅዝቃዜ ምች ሆኖ ሲያጠናግር ያየሁት እዚህ ነው። ትናንት ረፋድ ላይ በሳሎን ቤቴ ሶፋ ላይ ጋደም ብዬ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከ7 ለ70 ብርጌድ የተላከልኝን ከእዙ የመለየት መግለጫ አነብባለሁ። ከወትሮው የተለየ የሚቆረጣጥም ብርድ ተሰማኝ፣ ልብስ ደራረብኩ፣ ለቤቱ ሙቀት የሚሰጠውን ሃይሱንግ ይሉታል ከፈትኩ፣ ወባ እንደያዘው ሰው ያንዘፈዝፈኝ፣ ይቆረጣጥመኝ ጀመር። ላብ በላብ። ኤሌክትሪክ እንደያዘው ሰው ነው የሚያንዘረዝረኝ። ቆይቼ ነው በመጋረጃ የተሸፈነውን የተከፈተ መስኮት ዓይቼ የምቹን ምንጭ ያወቅኩት። ጭራሽ ወደ ጉንፋንነት ሁላ ሊቀየር? ጉድ እኮ ነው።

"…የትም ሳልወጣ፣ ቤቴ ተቀምጬ ጉሮሮዬን ከረከረኝ፣ ምኔ ሞኝ ነው ዳይ ወደ ፍልሚያው። እነ ነጭ ሽንኩርት፣ እነ ዝንጅብል፣ እነ ማር ከያሉበት ተጠርተው እንዲመጡ አደረግሁ። አፍልቼ በላይ በላዩ ለቀቅኩበት፣ ዘመዴ ዳይ ተሸፋፍነህ ተኛ ብዬ መክሬው ተሸፋፍኜ ለጥ። ላቡ እንደ ስቲም ባዝ አጥለቀለቀኝ፣ ሳሉም በፈላው የዝንጅብልና የነጭ ሽንኩርት ሠራዊት ተመከተ። እንደ ጎጃም እስክስታ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ ድረስ እንደ ጎንደሬዋ እንዬ እንቅጥቅጥ ያደርገኝ፣ እንደ ባለ ዛር ይወዘውዘኝ የነበረውም ቆመ። ቀጥ ነው ያለው። በዚህ ላይ ዕለተ ሰኞ የእረፍት ቀኔ መሆኑም በጀኝ እርፍ ብዬ ዋልኩ። አደርኩም። ዛሬ እንደተደበደበ ሰው ሰውነቴ ከመጓጎሉ፣ ድምጼ ጎረምሳ እንደዋጠ ሰው ከመጎርነኑ በቀር ሰላሜን አገኝቻለሁ። የአውሮጳ ምች አደገኛ ነው። እኔ በዚህ ዕድሜዬም መድኃኒት አልጠቀምም። እነ ነጭ ሽንኩርት፣ እነ ዝንጅብል፣ እነ ፌጦ፣ እነ ማር፣ ጤናአዳምና ዳማከሴን ያቆይልኝ። ውኃ አፍልቼ ትንሽ ጨው ጠብ አድርጌበት ታጥኜው ተሸፋፍኜ እተኛለሁ። ሲነጋ ዳይ ጤና ይስጥልኝ ነው።

"…ከዚህ የተነሣ ዓይኔ እንባ እያቀረረ ርእሰ አንቀጻችንን አሳምሬ፣ አሰካክቼ መጻፍ አልሆንልህ አለኝ። ቢሆንም ግን ቤታችን ጭር ብሎ እንዳይውል አንዳንድ ነገሮችን በማንሣት አጫጭር መረጃዎችንም ወደ እናንተ በማድረስ በመረጃዎቹም ላይ እየተወያየን ለማምሸት እንሞክራለን።

• የዛሬው ቲክቶክም ይለፈኝ። ግን እንወያያለን። ከ20 ደቂቃ በኋላ በጥያቄ እመለሳለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አመሰግናለሁ ምስጌ…🙏🙏🙏

"…በትናንትናው ምሽት የመረጃ ቴቪ ሳምንታዊው የነጭ ነጯን ከዘመዴ መርሀ ግብር ላይ… በትግል ሜዳ ያላችሁ ታጋዮች ዘመኑ አደገኛ ነውና በቲክቶክ ላይ አትግቡ፣ ለእናንተም ለታጋይ ጓደኞቻችሁም ጦስ ትሆናላችሁ፣ በራስ ስህተት ለምን በአጭር ትቀጫላችሁ ብዬ ምስጌንና ሌላ አንድ አርቲስት ወንድሙንም ምክር ለግሼ ነበር። እናም ሁለቱም ወንድሞች ከጎጃም ምድር ሆነው ምክሬን ተቀብለው ሁለተኛ ላይቭ አንገባም ብለውኛል።

• ምክሬን ስለሰማችሁ አመሰግናችኋለሁ። 🙏🙏🙏

• ድል ለእናንተ…!
• የሞትን ባሕር ያሻግራችሁ…!

"…በመጨረሻም መርካቶ ጓ ብሏል አሉ። ሲደግመው ነው መጻፍ፣ ሸዋ አንድ ብርጌድ ተገንጥሎ ወጥቷል፣ መግለጫውንም ልከውልኛል፣ በስልክም ደውለው አውርተውኛል፣ በነገው መደበኛ መርሀ ግብራችን እንቀጥላለን።

• የካዛንቺስ፣ የአራት ኪሎ ልጅ ተነሥ፣ ጥፋ ሲባል ብድግ ያለው ደንታ ስለሌለው ነው። የመርካቶን ልጅ መነካካት እንደ ካሳንችስ ልጆች ቀላል አይደለም። የሕይወትን ትርጉም፣ የቤተሰብ ሓላፊነትን፣ በላቡ፣ በወዙ፣ እንቅልፉን አጥቶ ሠርቶ የሚበላን መርኬ መነካካት ምላሹ ከባድ ነው። ለማንኛውም በመርካቶ ደም መፍሰስ ከጀመረ የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል። ግን ደግሞ ነገም ይደግሙታል ወይ ነው ጥያቄው?

• ምስጌ ግን በድጋሚ አመሰግናለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አላችሁ አይደል…?

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የመርሀ ግብር ሰዓት ለውጥ…

"…በእኔ በዘመዳችሁ በኩል ተዘጋጅቶ በመረጃ የሳታላይት ተለቭዥን የቀጥታ ስርጭት ሚቀርብላችሁ ተናፋቂውና ተጠባቂው " ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘው ሳምንታዊው የዕለተ እሑድ መርሀ ግብራችን ከዛሬ ህዳር 8/2017 ዓም ጀምሮ የሰዓት ለውጥ በማድረግ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የሚቀርብ ይሆናል።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ወልቃይት ነበር ያረፈድኩት። በወልቃይት ባለ አምባሻውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቀል የተከለከለው ለምንድነው? የጎንደር ጃኖ በመልበስ ጎንደሬ መሆን ይቻላል እንዴ? እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በስተመጨረሻ ሰንደቋን መንው ደበቋት፣ ሸሿት፣ ከስብሰባ ማዕከላትና ከአደባባዮች ላይ ምነው አራቋት?

• ለማንኛውም የሰዓት ለውጡን እንዳትረሱት። ምሽት 1:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ይጀምራል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…9

"…የሁለት ቀን እንቅልፍ አለብኝ። ነገ ምሽት ደግሞ የመረጃ ቴሌቭዥን የነጭ ነጯን የቴሌቭዥን መርሀ ግብር አለብኝ። እናም በጊዜ ልተኛ።

• ደኅና እደሩልኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማስታወቂያ…

"…የፊታችን ማክሰኞ በእኔ በዘመዴ የቲክቶክ ቤት በወልቃይት ጉዳይ ነጭ ነጯን እናወራለን። የማይካድራን ጭፍጨፋም በሃላል እንወያይበታለን። ተከዜ ወንዝ ወስጥ ተገድለው የተጣሉት ትግሬዎች ናቸው ዐማሮች የሚለውንም እየጠየቅን በግልፅ እንወያያለን። ወልቃይት ለዐማራው እንደ ዐማራ፣ ለጎንደር ዐማራ በተለየ ሁኔታ አሁን ላይ ምን ዓይነት ጥቅም እየሰጠ ነው? እውን የጎንደር ዐማራ በወልቃይት ላይ የማዘዝ፣ የመኖር፣ የመጠቀም መብት አለውን? እንደ አያሌው መንበርና ምስጋናው አንዱአለም ቀይ መስመር ብሎ ነገር የለም። ቢያምህም፣ ቢጠዘጥዝህም። የግድ ጨከን ብለህ ትወያያለህ። የግድህን አልኩህ። የግድህን ትወያያለህ።

"…ሌላው ትዊተር ስፔስ ነው። የስፔሱን ጥቅም ያየሁት በዚህ ባለፉት ሁለት ቀናት ነው። እናም እዚያ ሰፈር ቀደም ብዬ ቤት ቦታ ገዝቻለሁ። 10 ሺ ቤተሰብም አፍርቻለሁ። አሁን ምን አቀድኩ መሰላችሁ በትዊተር መንደር ብዙ የደርግ ርዝራዦች በዝተው አይቻለሁ። እናም እነዚህን የትውልድ ህልም ሾተላዮችን ቆንጆ፣ ቆንጆ ጠጡኝ፣ ጠጡኝ የሚል ነጭ ነጯን የሆነ የሚያሽር ፈዋሽ የሆነ የኮሶ መድኃኒት እየጋትኩ ብፈውሳቸው ብዬ አሰብኩ። እነ ሲሳይ ሙላውን፣ እነ ደርጉ አቶ ወዳጄን እና እስክንድራውያንና ስኳድን የማገኘው እዚያ መንደር ነውና ልክ እንደ ቲክቶካችን ስፔሱንም መስመር ባስይዘው ምን ትመክሩኛላችሁ?

• እየኮመታችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…5

"…በመጨረሻም እስከዛሬ ድረስ በጭልጋ ወረዳ የገጠር ቀበሌው የደንቢያ የጎንደር ዐማራ ነኝ ሲል የከረመውና የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው አዝማሪ ደፋሩ ፀረ ዐማራ አበበ በለው ጭንብሉ ተገለጠ።

"…አሁን አቤ በግልጽ እስኳድ እንደሆነ እና የፖለቲካው ቅማንት የፀረ ዐማራው የፓስተር ምስጋናው አንዷለም የጣና ቴቪ ሼር እንዳለው በግልፅ እየገለጸ ነው። ጣና ቴቪ በተለይም በጎጃም እና በወሎ ፋኖ ላይ ለሚሠራው የመከፋፈል ሴራ አዝማሪ አበበ በለው ሓላፊነቱን ይወስዳል። ጣና ቲቪ የጎጃም ፋኖን ለመከፋፈል የሕዝባዊ ድርጅቱ ጎጃም ዕዝ እያለ ለሚሠራው ዘገባም አዝማሪ አበበ በለው ሓላፊነት ይወስዳል።

"…እኔ የነከስኩት ሰው መጨረሻው አያምርም። መጀመሪያ ላይ ሄጵ የሚልብኝ ቢበዛም መጨረሻ ላይ ማሸነፌ አይቀርም።

• ነቆራ እየነቆራችሁ…😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…3

"…የተቀበል ኤዲቶሪያል ቦርድ ይሄ የዮኒልታዛር 500 የፔንስዮን የፈውስ አገልግሎት በተቀበል ገጣምያን ለአዝማሪው ግጥም ተሰጥቶት ይገጠምበት ዘንድ ወደ እናንተ ተላልፏል።

• ግጠሙበት፣ ግጠሙለት…

• ከ100 ኮመንት በኋላ በአዲስ ተቀበል እከሰታለሁ። እየገጠማችሁ።

"…ግጥም መግጠም ካልቻላችሁ በጨዋ ደንብ ነቆራም፣ ትችትም፣ ምክርም ይቻላል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 1

ካባ ለበሰ አሉ ብርሃኑ ጁላ
ዲሽቃ ታጥቆ ገብቶ ተማርኮ በዱላ

"…ተቀበል… አንተው…

እየገጠማችሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ነው። አንድ አምላክ አንዲት መንግሥት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይወዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈጽማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሠለጥናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ።

"…አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨንቃሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለሟል ያደርጋሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ።

"…እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን፤ አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ። ቅዳሴ ማርያም

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel