zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…አሁን ወደ መጨረሻው አካቢቢ ስንደርስ ትግሉ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ትግል መሆኑ ቀርቶ የሃይማኖት መልክ እየያዘ ይመጣል። በሃይማኖት ጦርነቱ ላይ ግን የብሔር፣ የነገድ፣ የዘር ፖለቲካ ቤንዚን፣ ናፍጣና ነዳጅ ሲጨመርበት ደግሞ እሳቱ ከአርታኢሌ በላይ የከፋ ይሆናል። አደገኛው ነገር እየመጣ ያለው ከአሁን በኋላ ነው። መለከቶታዊ ጣልቃገብነት ኖሮ የሆነ ተአምር ካልተፈጠረ በቀር መጪው ጊዜ ወደዚህ ድብልቅልቅና ውጥንቅጥ መቀየሩ አይቀሬ ነገር ነው። እየታየ ያለውም ሁኔታ ይኸው ነው። ከምር እጅግ አደገኛና አስፈሪ ጊዜ ነው እየመጣ ያለው። ይሄን አስፈሪ ጊዜ በጥበብና በድል ከተሻገርነው መጪው ጊዜ የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ዘመን ይሆናል። አልያ ግን አሁን እየታየ ባለው፣ በተለይ በምዕራባውያኑ በጀት እና የገንዘብ ፈሰስ የሚታገዘው የብልፅግና ወንጌል ፓርቲና በዓረቦቹ የሚመደገፈው የወሃቢይ እስላሞች ከመጠን ያለፈ የሥልጣን፣ ሀገረ መንግሥትን የመጠቅለል፣ የመቆጣጠር ፍላጎት ጣሪያ መንካትን አካሄድ ስንመለከት ከባድ ነው።

"…አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት መልኩን ቀይሯል። ከፍትሕና ዲሞክራሲ፣ ከሰላምና ደኅንነት፣ ከማንነት እና ድንበር ማስከበር ብላ ብላ ቦለጢቅስ አልፎ ዘልሎ፣ ተሻግሮ ሌላ መልክና ቅርጽ ይዞ መጥቷል። ብዙዎች ደፍረው መናገር፣ መጻፍ አቅቷቸው ነው እንጂ እውነታው ከዚህ የተሻገረ፣ የዘለለ አደገኛ ቅርጽ ነው እየያዘ የመጣው። አዎ ጉዳዩ የሃይማኖት የበላይነት ማምጣት ዘመቻ፣ ጦርነትም ሆኗል። የሃይማኖት ፍትጊያ ሆኗል። አንደኛው ሃይማኖት ገና ጉዳዩ የሃይማኖት መሆኑ አልገባውም። ሌሎቹ ግን ገብቷቸው ወጥረው ጊዜአቸውን እየተጠቀሙበት ነው። ከሆነ ሆነ እናሸንፋለን፣ ካልሆነም ደግሞ ድራሻቸውን አጥፍተን፣ በቁጥር አመንምነን፣ ታሪካቸውን በርዘን፣ ቅርሶቻቸወወን አውድመን፣ ሊቃውንቶቻቸውን ጨፍጭፈን፣ አሸማቀን፣ ማይኖሪቲ ውስጥ መድበን፣ እንዳይነሱ አድርገን ቀብረን፣ ወደ ሀገረ መንግሥት መሪነት እንዳይመጡ፣ እንደ ኩርዶች ሀገር አልባ ተቅበዝባዥ አድርገን እናስቀራቸዋለን በማለት 24/7 ዓመቱን ሙሉ ያለ እረፍት እንቅልፍ ሳይተኙ እየደከሙ፣ እየተጉ ነው።

"…የምጽፈውም፣ የምናገረውም ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነቡት፣ ሲሰሙኝም ይዘገንናል። ምነው ባላለው፣ መኘባልተናገረውም ይላል አንባቢ። ነገር ግን ልቡም የሚነግረው የእኔን ጽሑፍ ነው። መሬት ላይ በዓይኑ የሚያየው፣ በጆሮውም የሚሰማው ግን እኔ የምጽፈውን፣ የምናገረውን እውነታና ጥሬ ሃቅ ነው። ቆይቶ፣ ቆይቶ ነው ያ ዘመድኩን የተናገረው፣ ያለው፣ ያወራው ነገር እውነት ነው የሚለው። ዛሬ ላይ ግን ጥቂት ነው ሰሚው። በተለይ እኔ የምናገረው፣ የምጽፈው ነገር ዓላማቸውን፣ ዕቅዳቸውን የሚያፈርስባቸው ቀድመው አካሄዴ እንደገባኝ የሚያውቁት መሰሪ ጠላቶች በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ተጠልፈው በሚከፍቱት ዘመቻ የሚታለሉ ገልቱ፣ የዋሕ የማይባሉ ዥልጥ ዥል ሰገጤ የእኔው ወገን ተብዬዎቹ ከጠላት በባሰ መልኩ ዘመቻ ይከፍቱብኛል። እውነቱን እያወቁ የጠላት አፍ ሆነው በምላሳቸው ሲለበልቡኝ ውለው ያድራሉ። እኔ ግን መጻፌን አላቋርጥም። መናገሬንም አልተውም።

"…አስመሳዮች ነነ። ሲበዛ አፈ ጣዲቆች ነነ። ሰው መሳይ በሸንጎዎች ነነ። የቤት ቀጋ የውጭ አልጋዎች ነነ። ጠዋት ታቦት ማታ ጣኦት አምላኪዎች ነነ። ለታቦትም ለጠንቋይም እኩል ሰጋጆች ነነ። ሲበዛ አስመሳዮች፣ ሸርዳጆች፣ ገልቱ፣ ዳተኛ፣ ንህዝላሎች ነነ። ስለነገ የማናስብ ከርሳሞች እንበዛለነ። ለዚህ ነው የሃይማኖተኞች ሃገር በምትባል፣ አርብ ሮብን፣ አጿማትን ቆጥሮ፣ ጠብቆ ከሥጋና ከቅቤ ይጾማል፣ አልፎ አልፎም ሰንበትን ጠብቆ ያስቀድሳል፣ አርብ ጁምዓ ሄዶ ሶላት ይሰግዳል፣ አዳራሽ ሞልቶ ሃሌ ሉያ እያለ ይጨፍራል የሃይማኖተኞች አገር ነው በሚባለው ኢትዮጵያ ይኖራል። ቁልቢ፣ ግሸን ደብረ ከርቤ፣ አክሱም ጽዮን በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ ተግተልትሎ ይሄዳል፣ ሲያዩት ወንጌልም፣ ቁራንም የገባው አማኝ፣ ሃይማኖተኛ ይመስላል።።በአደባባይ ዝሙትን ሲያወግዝ ሲያዩት ያስቀናል። ነገር ግን ይኸው ሕዝብ በ ኤች አይ ቪ ኤድስ ከዓለም ሦስተኛ፣ ከአፍሪካ አንደኛ ነው ይባልልሃል። ጨለማን ተገን አድርጎ፣ ከአካባቢው ርቆ ሲያመነዝር ይውል ያድርና ሃይማኖተኛ መስሎ በአደባባይ ይገማሸራል። አስመሳዮች ነነ። አይደለህም? አይደለሽም? እኔ ግን ነኝ።

"…ይሄ አስመሳይ፣ እስስትነታችን፣ ቅሽምናችንን፣ ስንፍናችንን በምክንያት፣ ፍርሃት ሽንታም ቅዘናም፣ ቦቅባቃ፣ በጭባጫነታችንንም በመንፈሳዊነት፣ በእግዚአብሔር ሰውነት በመደበቅ፣ በመሸፈናችን ምክንያት የበለጠ ጉዳት፣ የበለጠ ውድመትና ጥፋት ሊደርስብን ችሏል። ጠላት ሆነው እያወደሙህ ያሉት በሙሉ አንተን እያወደሙህ ያሉት፣ ሃይማኖት፣ ይሉኝታ፣ ሼም፣ ሰው ምን ይለኛል፣ ነገ ምን ይፈጠራል? ግብረ ገብ ወዘተን ጠቅልለው አቃጥለው ቀብረው፣ ፈጣጣ፣ ይሉኝታ ቢስ፣ ሼምለስ ሆነው በመገለጥ ነው። አዎ በዚህ መልክ ነው እነሱ ባለ በሌለ ኃይላቸው እየተንቀሳቀሱ ያሉት። አንተስ ነው ጥያቄው? አንተ ገና ከርስህን ለመሙላት የሆድ፣ ማደሪያ ለማግኘት የቤት ጥያቄ ላይ ነህ። ይሄን ለማሟላት ስትል የእነሱ ባሪያ፣ የእነሱ ገረድ ሆነህ መከራህን ትበላለህ። የቁስ ሰቀቀን ላይ ነህ። ገና ማቴሪያል ስብሰባ ላይ ነህ። ሰቀቀናም። መሬትህን ቀምተው፣ ቤትህን አፍርሰው በተስፋ ሞልተው አዳራሽ እንደ ካርቶን አጭቀው ሲያስቀምጡህ ገና ለገና ነገ የሆነ ነገር ያደርጉልኛል በማለት አፈር ላይ፣ ሲሚንቶ ላይ ተንከባልለህ ትልመጠመጣለህ። ግን አፈር ከደቼ ከመብላት አትድንም።

"…ደግሜ እላለሁ። አሁን ጉዳዩ የሃይማኖት መልክ ይዟል። ቅርፁም በደንብ እየታየ፣ እየፈጠጠ መጥቷል። በዚያ ላይ ዲቃላ ማንነት፣ የአናሳነት ስሜት፣ የበታቸኝነት ስሜት የሚያሰቃያቸው፣ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎና ከሸዋ ዐማራ ውስጥ በቅሎ ሲገኝ ጉዳዩን የበለጠ ያጦዘዋል። ለተያዘው ትግልም ትልቁ እንቅፋቶችም አንደኞቹ እነዚህ አካላት መኖር ነው። መኖር ሲባል በገዢው ፓርቲም ገረድ፣ በተቃውሞ ጎራውም ውስጥ ሚዲያውንና ገንዘቡን በበላይነት መቆጣጠራቸው ነው አደገኛ ሁናቴ እየፈጠረ ያለው። የወሃቢ እስላም እና የብልፅግናው ወንጌል የፈጠሩት ጥምረት ለኦርቶዶክሳዊው ዜጋ የመኖር ኅልውናውን የጥያቄ ምልክት አደጋ ውስጥ ከትቶታል። በሙሉ ጉልበት ነው የሚሠሩት። በምድር ላይ በጦርነት፣ በራብ፣ በበሽታ እያዳከሙ፣ እየፈጁት ነው። ለጦርነቱ ቦንብና ጥይት ለብልፅግና ወንጌሉ ምዕራባውያኑ፣ ለወሃቢስቶቹ ዓረቦቹ በገፍ እያቀረቡላቸው ነው። ይሄ በትግራይ ጦርነት፣ አሁንም በዐማራ ክልሉ ጦርነት እየታየ ያለ ነው። የእነ ዐሜሪካ የዓለም ባንክ ብድር፣ የእነ እንግሊዝና ጣልያን በእርዳታ ስም የሚፈሰው ዶላርና ፓውንድ፣ የቱርክ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ፣ የኢራን ድሮን፣ ቦንብ ምስክር ነው።

"…ዛሬ ዛሬ በኦሮሚያ ለዚህ የሞት ሽረት ፍልሚያ የኦሮሞ ወሃቢያ እና ጴንጤ፣ ከዋቄፈና ጋር ሆኖ፣ አባ ገዳው በግዝት፣ ፓስተሩና ሼኩ በስብከት ወጣቱን በአደባባይ ግልጽ የሆነ ወታደራዊ ምልመላ እያደረጉ ወደ ዐማራ ክልል እያዘመቱ ነው። በደማችን፣ በ150 ዓመት የኦሮሞ ተጋድሎ እጃችን የገባውን ሥልጣን ዐማራ እና ኦርቶዶክስ ሊወስዱብን፣ ሊነጥቁብን ነው በማለት ነው ስብከቱ፣ ቅስቀሳቅ፣ ምልመላው እየተከሃደ ያለው። ዘማቾች ነግዳጅም ይሁን በፈቃደኝነት ወደ ዐማራ ክልል የሚሄዱት በዚህ መልኩ ነው። ድል ቢያደርጉ እሰየው…👇① ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ። መዝ 150፥ 6

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሦስት መረጃዎች…

መረጃ፥ ①

"…የዐማራ ክልል ጎጃምን በማስተዳደር ላይ የሚገኘውና በአርበኛ ዘመነ ካሤ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ለጥቂት ቀናት በጎጃም ክፍለ ሀገር ውስጥ ከአምቡላንስ በቀር የመከላከያም፣ የፎሊስም፣ የሕዝብና የድርጅቶችና የግለሰቦችም የሆነ ማንኛውም ዓይነት መሂና እንዳይንቀሳቀስ አግዶት የቆየውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የፋኖ ድርጅቱ ዕቅዱን ስላሳካ ከዛሬ ጀምሮየመሂና እንቅስቃሴ በክፍለ ሀገሩ እንዲንቀሳቀስ መፍቀዱን አሳውቋል። በዚህም መሠረት የዐማራ ፋኖ በጎጃምን ትእዛዝ አክብሮ እስከዛሬ ድረስ ጎጃም ሳይገባ፣ ወደ ጎንደርም መሄድ ሳይችል መንገድ ላይ ቆሞ የከረመው መሂና ሁሉ መንቀሳቀስ ተፈቅዶለታል። ፋኖ ካዘዘ አዘዘ ነው።


መረጃ፥ ②

"…በዐማራ ክልል ሸዋን በማስተዳደር ላይ የሚገኘውና በአርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የሚመራው የዐማራ ፋኖ የሸዋ ዕዝ ደግሞ ከነገ ጀምሮ ለተለየ ወታደራዊ ተልዕኮ ሲባል ሸዋን አቋርጠው የሚያልፉ መሂኖችም ሆነ በሸዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መሆኖች ከአምቡላንስ በቀር ትውር እንዳይሉ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም መሠረት ከነገ ጀምሮ መከላከያም፣ ፎሊስም፣ ሀገር አቋራጭ ኦቶቢስም፣ ሚኒባስም፣ ቢሽኪሊሊትም እንዳይንቀሳቀስ አዟል። ትእዛዝ ይከበርም ብሏል። አዘዘ፣ አዘዘ ነው። ሀለቀ።😂

መረጃ፥ ③

"…የፊታችን ረቡዕ የዐማራ ፋኖን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በስደተኛው ብዓዴን ተዘጋጅቷል። በሰላማዊ ሰልፉም ላይ እስከአሁን ሊወገዙ ባነር ላይ ፎቶአቸው ተለጥፎ የተዘጋጀው አርበኛ ዘመነ ካሤ፣ ምሬ ወዳጆ፣ ባዬ ቀናው፣ ሀብቴ ወልዴ፣ ኢንጂነር ደሳለኝ፣ ሳሙኤል ባለድል እና እኔ አሸበርቲ ዘመድኩን ነቀለ መሆናችን ተረጋግጧል። የእኔ ግን አስቂኝ ነው። ዝርዝሩን ነገ ከነ መፈክራቸው እመለስበታለሁ።

• እኔን በተመለከተ በዐማራ ጉዳይ ከሆነ ስቀሉኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አላችሁ አይደል…?

• ንቅል… ፍርጥ ነው። 💪

~ በሉ ገባ በሉማ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ጊዜ አይጣል። የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለም። እንደሠራ አይገድል፣ አግኝቶ ከማጣት፣ ከብሮ ከመዋረድ፣ አብቦ ከመጠውለግ ይሰውረነ። ጌታሆይ መጨረሻዬን አሳምርልኝ፣ ደግሞም የማታ እንጀራ ይስጣችሁ የሚባለውን አባባል እንደዋዛ፣ እንደ ቀላልም እንዳታዩት።

"…የእግዚአብሔር ስሙም ቅዱስ ነው። ለሚፈሩትም ምህረቱ ለልጅ ልጅ ነው። ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው ሓሳብ የሚኮሩትን ትዕቢተኞችን በታተናቸው። ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው። የተዋረዱትን ከፍ ከፍ አደረጋቸው። የተራቡትን በቸርነቱ አጠገባቸው። ባለፀጋዎችን ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው እንዳለች እመቤታችን በጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ጸሎቷ።

• ዓለሙኒ ኃላፊ ንብረቱኒ ኃላፊ እስመ ኵሉ ኃላፊ ውእቱ እንዲል የመልክአ ሥዕል ደራሲ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” ማቴ 8፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…11

• የምስክርነት ሰዓት ነው።

"…በእስልምና ቀልድ የለም አባቴ። 😂

"…በዘራችሁ አይድረስ። እየኮመታችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…9 😂😂😂

• ታሪክን የኋሊት ክፍለ ጊዜ።

"…አምላኬ ሆይ 🙏 እንደነዚህ እንደሚታዩት ወንድምና አባቶች ስላላደረግኸኝ እጅግ አድርጌ አመሰግንህሃለሁ።🙏🙏🙏

"…ከብሮ ከመዋረድ፣ ከፍብሎ ዝቅ ከማለት፣ ታይቶ ከመጥፋት፣ አግኝቶ ከማጣት ሰውረን። ሸሽገን። አሜን🙏

"…አቡነ ጴጥሮስ ግን አንጀቴን ነው የሚበሉኝ። ከምር ወይ እንደ ኦርቶዶክስ አክት አላደረጉ፣ ወይ እንደ ጴንጤ አክት አላደረጉ፣ ወይ አልበለፀጉ፣ እንዲሁ ወንጌሉን ትተው "ዶፍቶር አቢይ፣ ዶፍቶር አቢይ ብለው እንደጮሁ አዋርዶ፣ አንገት አስደፍቶ ከቦሌ ሮጲላን ጣቢያ ወደ ኒውዮርክ ሸኛቸው። አቢይን ያመነ፣ ጉም የዘገነ አንድ ነው የሚባለው እውነት መሆኑን ነው ያረጋገጥኩባቸው።

• ሲያዛዝኑ…😁

• እየኮመታችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…7

• የጦሎት ሰዓት ነው።

"…በዘመነ መንግሥቱ የዐማራንና የኦሮሞን ወጣቶች በራሱ ፊርማ በትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓት አግአዚ በተባለው ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች እንዲጨፈጨፉ ያደረገው ሶዬ በሕግ የሚጠይቀው ሥርዓት ስለሌለ አሁን ጭራሽ ፓስተር ሆኖ "እሳት በቁርጭምጭሚቴ፣ በኩላሊቴ" ይልልኛል። ኩላሊት አባቱ ይፍረስና ልል ብዬ ከአፌ መለስኩት።

• ቆይቶ አንድ በእንግሊዝኛ፣ አንድ በኦሮሚኛ ጦሎት ይዤላችሁ እመለሳለሁ።

"…ይሄና ይሄን የመሳሰሉ ነፍሰ ገዳይ አረመኔዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ "ጌታቸው" እንዳይጠራቸው አጥብቀን እንጸልይ።

• አሜን ነው…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል …6

• ወገን የማስመረጫ ክፍለ ጊዜ

• የሽልማቱ አጠቃላይ ይዘት ይህ ነው።

"…ኔዘርላንድ ውስጥ Emigrants with higher education background (ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ካላቸው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኔዘርላንድ ከገቡ ሰዎች ውስጥ) ዘርፈ ብዙ በሆኑ የውድድር መመዘኛዎች ተወዳድሬ ከምርጥ 4ቱ ውስጥ ገብቻለሁ። ምርጥ 4 ውስጥ እንድገባ ያበቁኝ ነገሮች በዋነኝነት:-

- በተለያዩ የማኅበረሰብ ሥራዎች ተሳትፎዬ
- ደች ቋንቋ በAdvanced level በአጭር ጊዜ በመጨረሴ
- የ2ኛ ማስተርስ ትምህርቴን በጥሩ ውጤት በማጠናቀቄ እና በቀጣይ grant አግኝቼ ምርምር ላይ እየሠራሁ በመሆኔ
- በጋዜጦች እና በኢንተርኔት መገናኛዎች ላይ በመውጣት ለሌሎች inspiration መሆን በመቻሌ እና
- ከቋንቋ አስተማሪዬ ጋር ሆኜ የጻፍኩት የልጆች መጽሐፍ ናቸው።

"…ከምርጥ አራቱ 1ኛ የወጣውን ለመለየት የኦንላይን ምርጫ ተጀምሯል። በመጨረሻ ሚንስትሮችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተጋበዙ ሰዎች በተገኙበት አንደኛ የሚወጣው ተወዳዳሪ ይታወቃል። ስለዚህ ከታች ባለው ሊንክ እየገባችሁ እንድትመርጡኝ እጠይቃለሁ በማለት ጥሪውን አቅርቧል።

~ ዳይ 1…2…3… ወደ ምርጫ… 👇 ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ምረጡት።

• ቆይቼ በነቆራ እመለሳለሁ።

https://www.uaf.nl/en/uaf-award/tadele/

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…4

• ሙን ኡኖ ኖ?

• እና የልቅሜ ኪዳኑ ልጅ ሆነህ የት እንድታርፍ ፈለግህ…? ጉድ እኮ ነው።

"…ጎንደር የጎንደር ዐማራን አንድ እንዳይሆን የሚበጠብጡትን የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎችን አልፋታቸውም። ብቻዬን የጎንደርን ጠላቶች፣ የጭቃ ውስጥ እሾሆች ለቅሜ፣ ለቅሜ እያንጨረጨርኩ እነቃቅላቸዋለሁ። ብቻዬን አልኳችሁ።

"…ጎንደሬነት የጎንደር ዐማራን ትግል ለመጥለፍ እንደ መደበቂያነት ማገልገሉ ይበቃል። ጎንደሬ ነኝ የሚል በአብዛኛው ተጎንደር ዐማራ ነኝ የሚለውን አሳዳጅ ነው። ዲቃላው የጎንደር ዐማራ ነኝ ማለት ይፀንነዋል። ወልቃይቴ ነኝ የሚለውም እንደዚያ። ዋጠው።

"…እኔ የማውቀው የጎንደር ዐማራን ነው። አለቀ። ዐማራነትን ተጸይፎ ጎንደሬ ነኝ፣ ወልቃይቴ ነኝ እያሉ ማጭበርበር አይቻልም። ምረጥ።

"…እናስ የአደይ ልቅሜ ኪዳኑ ልጅ አቤ እስክስ ዘመድ ከዘመዱ እንጂ የት ልታርፍ ኖሯል? ትግሬ ጋር ማረፍስ እንዲህ ይበሰጫል እንዴ? …ጉድ እኮ ነው።

• እየኮመታችሁ። 100 ሰው ከኮመተ በኋላ በአዲስ ልጥፍ ብቅ እላለሁ።

• አልገባኝም እኔ…😂 አቤ እስክስ ሙን ኡኖ ኖ?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…2

• ጥያቄ ነው።

"…እንዲህ አድርጎ አደይ እናቱን የሚያከብር፣ ጎንበስ ብሎ የአደይ ማዕረይ እናቱን እግር ስሞ የሚመረቅ፣ በአደይ ማዕረይ የሚመረቅ፣ ድንቅ እንቅ የዐማራ ፋኖ ታጋይ፣ አታጋይ፣ እንደ አጋጣሚ፣ እንደ ዕድል ሆኖ ጠጉር፣ ጎፈር የለውም እንጂ የደንቢያ የድሮ የዳልጋ አንበሳ የመሰለ ሶዬ ማነው…?

~ በዚያውም የዐደይ ማዕረይ ስማቸውንም ሞክሩ… ፍጠኑ ሽልማት አለው።

• ይገምቱ… ይሸለሙ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… ተጀመረ

"…መልካም የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን በጉጉት እየተጠበቀ ነው። በሉ ግጥም፣ ቅኔ፣ ነቆራ፣ ፉገራ፣ ፉከራም መጻፍ ጀምሩ። ሁሉም በያለበት በጉጉት እየጠበቀው ነው የተቀበል መርሀ ግብራችንን።

• ጥያቄ ይኖረናል
• ፍትፈታም በሽ ነው
• ነቆራም በየዓይነቱ ነው

"…✍✍✍ ጀምሩ… ግጠሙ። ደፍራችሁ ግጠሙ። እኔ መግጠም አልችልም አትበሉ። ቤት ይምታ እንጂ ሽግር የለውም። ግጠሙ አልኳችሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጥያቄ ነው።

"…እስኬው ዘመነን ሲቦጭቀው ምን ይላል…? ዘመነ እዚያ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ተናግሯል። በዚህ የተነሣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የዘመነ ደጋፊዎች ራሱ እየወረዱበት ነው።" ምናምን ይላል። መልካም ሐሜቱ እንዳለ ሆኖ ዘመነ የቀረበው በሞገሴ ሚዲያ በመረጃ ቴቪ በእኔ በነጭ ነጯ መርሀ ግብር ላይ ነበር። እናም እስኬው ጫካ፣ ዋሻ ውስጥም ሆኖ ነጭ ነጯን ይከታተላል ማለት ነው እንዴ?

"… 😂 ጉድ እኮ ነው። እንግዲያው እንደዚህ ከሆነማ በመጪው እሁድ ከባድ ሚዛን ሆኜ ሁላ ነው የምመጣው ማለት ነው። በተለይ የእስክንድር ነጋን ባለቤት ሰርኬን ስለተዋጣው የባልደራስ ገንዘብ የት እንዳደረሰችው ለሕዝብ እንድታስረዳልን በይፋ ጥሪ አቀርብለታለሁ ማለት ነው። ችግር የለውም አይደል?

"…አዛኜን ዘመነ ካሤ ማለት ከምር ነፍጠኛ ዐማራ ነው ማለት ነው። ይሄን አስሬ በምን ምክንያት እየታሰረ፣ በምን ምክንያት እንደሚፈታ ያልተነገረንንና በእስር የጀገነን ባለ ፌስታል ታላቁ የተባለን አጥፊ ሰው እኮ ጨጓራውን ላጠው። ከምር ዘመነ ድብን ያለ ዐማራ ነው። የዐማራም ብሔርተኛም ነው። አበዱበት እኮ። ሳስበው ሳስበው ግን ዘመነ ካሤ ሳይነግሥ አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ። የሚነግሥ ይመስለኛል። 😂😂

"…ሌላው እስኬው ለሰሌ አጣናው "እጃችን ታስሯል" የሚለው ነገርም አልገባኝም። ምን ማለቱ ነው?

• ወጥር ዘመዴ…!😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እሺ ቁቤውስ…?

"…ጂርቱ…? ጂርቱ…? ጂርቱ…?
😂  😂  😂

"…ዕቃ ሊገዛህ የሚመጣው ሰው በኦሮሚኛ ሳይሆን በአማርኛ ካወራህ እንዳትሸጥለት" ፓስተር በቀለ ገርባ ኦፌኮ።

"…ዐማራ ያገባችሁ የኦሮሞ ወንዶች በአስቸኳይ ሚስቶቻችሁን ፍቱና እኛ ሸመረን ኦሮሞዎችን አግቡ። መገርቱ ናት ጫልቱ ከኦፌኮ።

"…የነፍጠኛ ቋንቋ፣ ለልመናና ለንግድ ይመቻል ማለት ነው። ጅርቱ ጆሌ ጎጃም፣ ጆሌ ጎንዶር፣ ጆሌ ወሎ፣ ጆሌ አካሱማ አክሱም፣ ሞቱማ መተማ። ጅርቱ…😂

"…አልፀፀትም አላለም። ያውም በአማርኛ። ጉድ እኮ ነው። ቁቤውስ? ማን ይጻፍበት? ማን ያውራው? ማን ያስፋፋው? ኧረ ጡር ነው። ኧረ ግፍ ነው። እንደዚያ መከራ ተበልቶበት፣ ስንትና ስንት ቄሮና ቀሬ ወድቆበት እንዲህ በቀላሉ ጣል ማድረግ ነውር ነው።

"…የኦሮሞና የትግሬ ቦለጢቀኛ ሚስቱ ዐማራ ናት። መጽሐፍ የሚጽፈው በአማርኛ ኖ። መድረክ ላይ አማርኛንና አማራን ሲያብጠለጥል ይውላል እቤቱ ሲገባ በዐማራይቱ ሚስቱ ሲብጠለጠል ያድራል። አይ ዐማራና አማርኛ።

• ቄሮ… ጂርቱ 😁

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ከምስጋናው በመቀጠል ወደ ተለመደው፣ ተናፋቂውና ተወዳጁ በብዙዎች ዘንድ በስጋት፣ በጉጉጉትም ወደሚጠበቀውና በዕለተ ማክሰኞ ተጀምሮ ዕለተ ዓርብ ላይ ወደሚጠናቀቀው ርእሰ አንቀጻችን እናመራለን።

"…የዛሬው ርእሰ አንቀጻችንም እንደወትሮው መረር፣ ኮምጠጥ፣ ጎምዘዝ ያለ ነው። እንደ ኮሶ፣ እንደ መተሬ፣ እንደ እንቆቆ ያለ ሬት ሬት የሚል ርእሰ አንቀጽ ነው። ሰናፍጭ የበዛበት፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ የተጀለበት ብዙዎችንም ንፍጥ በንፍጥ፣ ለሃጫቸውንም የሚያዝረከርክ ርእሰ አንቀጽ ነው። በል በል ሲለኝ። ምንአባቱ ይመጣል፣ ሞት አይቀር ባይሆን ለታሪክ ይቀመጥ ጻፈው፣ ጻፈው ዘመዴ ሲለኝ እንደምጽፈው ያለ ርእሰ አንቀጽ ነው የጻፍኩት።

"…እስከዚያው ድረስ ለመንደርደሪያ ቪድዮዎቹን እያያችሁ ጠብቁኝ። ጠብቁኝ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን ተገዳችሁ ሰልፍ ለመውጣት በዝግጅት ላይ ያላችሁ ወደ ቄራ ለእርድ የምትነዱ የደለበ አእምሮ ባለቤት አጋሰስ ዐማራ መሳይ ጎጋ አሞሮችም ቪድዮዎቹን እየተመለከታችሁ ጠብቁኝ።

"…ከዚያ ከርእሰ አንቀጹ ንባብ በኋላ የእናንተን ወርቃማ አስተያየቶች ከተመለከትኩ፣ ካየሁና ካነበብኩ በኋላ ወደ አጫጭር የነገን ሰልፍ በተመለከተ መረጃ ወደመስጠት እሸጋገራለሁ።

• ዐማራን ብቻ አጥፍተው የሚተዉን መስሎን ነበር ያለው ደቡቤ አሁን መበላት ጀምሯል። በተለይ ደቡብ ያለህ ኦርቶዶክስ በኦሮሙማው ወሃቢና ፅንፈኛ ጴንጤ በደቡብ ፅንፈኛ ጴንጤዎች ትእዛዝ፣ በገፍ ለመታሰር፣ ለመታረድ፣ ለመሰደድ ተዘጋጅ። ጻፈው ተዘጋጅ ብዬሃለሁ ተዘጋጅ። በዐማራ ብቻ የሚቆሙ የመሰለህ ጠብቅ። እንደ ዐማራ በጅምላ ይጨፈጭፉሃል፣ በራብም ያረግፉሃል። ከሥራ ትባረራለህ፣ ለማኝም ትሆናለህ። እንደ ዐማራ በጊዜ ያልተዘጋጀ ሁሉ ያለ ምሕረት ይበላል። ነገርኩህ።

• እህሳ…! ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከለሠልፉ ከተዘጋጁ መፈክሮች በጥቂቱ…

1. መንግሥት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን! 
2.በደምበጫ በገርጨጭ፣ በላሊበላና በሌሎች አካባቢዎች ንፁሃንን የጨፈጨፉ ፅንፈኛ ኃይሎች ለሕግ ይቅረቡልን! 
3.ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን! 
4.መንግሥት ሕግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ገዳዮች ለሕግ ያቅርብልን! 
5.መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን! 
6.በደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ ፅንፈኛው ኃይል በንፁሀን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግድያ በፅኑ እናወግዛለን! 
7.ንፁሀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው! 
8.የልማት ማዕከል የነበረው ክልላችንን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ የሚሠራው ሥራ የባንዳነትና የፅንፈኝነት ጥግ ነው! 
9.ንፁሀንን በግፍ መጨፍጨፍ የአረመኔነት ጥግ ስለሆነ ሊወገዝ ይገባዋል! 
10.ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም እና ልማት ነው! 
11.ፅንፈኛ እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል! 
12.ሰላም የጋራ ሀብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል! 
13.መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል! 
14.ፅንፈኛው ኃይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል! 
15. መከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች እና የክልላችን የፀጥታ ኃይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን!

"…የቀረ ካለ ጨምሩላቸው። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። መዝ 106፥1

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:15 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬውም መርሀ ግብራችን እንደወትሮው ሁሉ ልዩ ነው። ያበጠ ይፈነዳል። ነጭ ነጯን እውነት ስናጣጥም እናመሻለን። ተከታተሉን።

•ዩቲዩብ👉 https://youtu.be/1LFMNmPmQSE
•ትዊተር👉 https://twitter.com/MerejaTV
•Mereja TV: https://mereja.tv
•በራምብል👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” ማቴ 8፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…12

• በጸሎት እንዝጋው…!

"…የሰማነውን፣ ያየነውን በእዝነ ልቦናችን ያኑርልን። የሳምንት ሰው ይበለን። የዛሬው የተቀበል መርሀ ግብራች በዚህ ይዛዘምሎ። ነጋቲ ቡላ… ደኅና እደሩልኝ።

🖐🖐🖐

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…10

"…በዐማራ ስም፣ በዐማራ ኮታ ጀነራል በሆኑት የፖለቲካው ቅማንት የርግሬ ዲቃላው ስኳድና የአገው ሸንጎ ጀነራሎች ምትክ የሚሾሙት አዲሶቹ የኦሮጲያ መከላከያ ኃይ ዠነራሎች እኒህ ናቸው።

"…መጣም፣ መጣም፣ መጣም ያምራለች አይደል…? በኦሮሚያ የተዘረፈው የባንክ ብር፣ የታረደው እና የተዘረፈው ዐማራና ኦርቶዶክስ እንዴት ውብቢት ኦሮሚያ እንዳስመሰላቸው ግን አያችሁ? የጠጉራቸው ቅቤ ግማቱ እንኳ እንዴት አባቱ እንደሚያብለጨልጭ እዩልኝማ።

• የመጀላከያ ልብስ ተጸዳዱበት አይደል…?

• አበባው ታደሰ ግን ኤት ጠፋ…? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…8

• የስልክ ውይይት ክፍለ ጊዜ ነው።

"…የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ወዶገብ ገሌዎች፣ የሀብታሙ አፍራሳ፣ የፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም፣ የእስክስ አበበ በለው የዶላር ዕዞቹ፣ የጎንደር ዐማራ አሰዳቢ ከፋፋዮቹ አይተ ሰሎሞን አጠናው እና የ33 ሚልዮን ብር ዘራፊው የፋሕፍዴኑ ፍሮፌሶር ኢያሱ የሚያደርጉት የስልክ ውይይት ነው። በጥሞና ተከታተሉት።

• ደረጀ በላይ እና ሀብቴ በመጣላታቸው ጮቤ ይረግጣሉ።

• ጸዳሉን ተዉትና ተሼን ያዙት። ተሼ የባላገር ቅን ነው። 😂

በመጨረሻም…ሰሌ ፍሮፌሶርን ይጠይቃል…

• እኔና ደጀኔ ቸግሮናል… አንድ አራት ፈልጉልን።

• አራት ሜልዮን…?

• ኧረ ኧረ ሚልዮኑ ቀርቶ መቶሺውም በተገኘ።

~ ሰሌ በቃ በሄደበት ያገኘውን ሁሉ "እኔና ደጀኔ ቸግሮናል" ማለት ነው በቃ ሥራው።

• እነ አበበ በለው፣ እነ እስክንድር ደረጄንና ሰሌን የሚጫወቱባቸው በስስ ልባቸው፣ በደካማ ጎናቸው ነው ማለት ነው።

• ስልኩን የሚቀዳው ግን ማነው?
• ዋን ዐማራዎች፣ ስኳድና ሀብታሙ አያሌው በገዛላቸው ስልክ ባይጠቀሙስ…?

• እየኮመታችሁ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…7

• "ዘመድኩን ነቀለ" ነኝ…😂 መነቃቀሉን ልቀጥል ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል… 5

• የምርጫ ሰዓት ነው።

"…ያነዜ "ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማኅበርን" በመሰረትኩ ጊዜ ይሄን የምታዩትን ሥዕል የሳለኝ ልጅ ተሰድዶ እዚህ አውሮጳ ጎረቤት ሀገር መጥቶ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል።

"…ስደተኛው ወንድም በዚሁ በስደት ሀገር ወጥሮ ተምሮም ጥሩ ዕድል አግኝቷል። አሁን ደግሞ ከብዙ ተወዳዳሪዎች መሃል ተመርጦ አራተ ተወዳዳሪዎች የቀሩበት ምድብ ውስጥ ገብቷል። እናም አንደኛ ከወጣ ጥቂት ዩሮም ይሸለማል። ይሄም ብቻ ሳይሆን በታላላቅ የሀገር መሪዎች፣ የዓለምአቀፍ ሚዲያዎችና ዓለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ባሉበት መድረክ ላይ ስለ ሀገሩ የመናገር ዕድልም ያገኛል። እናም ፈቃደኛ ከሆናችሁ የልጁን የሚመረጥበትን የመወዳደሪያ ሊንክ ልለጥፍላችሁ ወይ።

"…ውድድሩ የሚያበቃው ነገ ዕሁድ ነው። ምን ትላላችሁ…?

• ልለጥፈው…? ከዚያ ወደ ጮማ ጮማ ወጋችን እንመለሳለን።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…4

• የተቀበል…3 ጥያቄ መልሱን እነሆ እንካችሁ።

"…እንዲህ አደይ እናቱ እግር ስር ድፍት ብሎ የሚመረቀው የዐማራ ትግልን ካልዘወርኩ፣ ካልመራሁ፣ አድራጊ ፈጣሪው ካልሆንኩ ብሎ የጎንደር ዐማራን ፍዳ የሚያበላው ሶዬ… ተወዛዋዥ፣ እስክስ፣ የአዲስ ድምፅ ሚዲያ ፈጣሪ፣ ዳይሬክተር፣ ሊቀመንበር፣ ዋና ፀሐፊ፣ የቦርድ አመራር፣ ገንዘብ ያዥ፣ ኦዲተር፣ ኮሜዲያን፣ የቴሌቭዥን አስተዋዋቂ፣ የዋ ዐማራ ማኅበር ባለቤት አይተ አበበ በለው ናቸው። (ኡፍ ማዕረጋቸውን መጥራት ያደክማል)

"…አርበኛ ደረጀ በላይ የአበበ በለው የሰፈሩ ልጅ ነው። አርበኛ ደረጀ በላይን በደካማ ጎኑ ገብቶ ለእስክንድር ነጋ ባሪያ፣ አሽከር ገረድ እያደረገው ያለው አበበ በለው ነው። የደንቢያ ልጅ ነን በማለት ያን የመሰለ የጎንደር አርበኛ የሀብታሙ አያሌው አፍራሳ እና የፓስተር ምስጋናው አንዷለም መጫወቻ፣ መሳቂያ መሳለቂያም አደረገው።

"…የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች ከጎንደር ዐማራ ፋኖ ትግል ካልራቁ ሽግሩ ይቀጥላል። አይቆምም። የደሀ አእምሮ ይዞ ብርብር እያለ የሚታገል እንደ ሰሎሞን አጠና ዓይነቱን ሻይ ቤት ከፍታችሁ ከትግሉ ገለል ካላደረጋችሁ እነአቤ ይጫወቱባል። እስክንድር የአራዳው ልጅ ከጎንደር ፋራ ካገኘ እንቅርቅቦሽ ነው የሚጫወትበት። ተናግሬአለሁ። ጎንደር ቴዲን ሁን።

• እስክንድር ነጋ (ደጎጎ) በሚስቱ ትግሬ ነው።
• አምሳሉ አስናቀ(ደጎ) በሚስቱ ትግሬ ነው።
• አበበ በለው (ሰጎ) በእናቱ ትግሬ ነው።
• ፓስተር ምስጋናው(ሰጎ) መኔ ነው።
• ሀብታሙ አፍራሳ (ኦወ) ሃዲግ ነው።
• እነሙላት አድሓኖ፣ እነበረደድ፣ እነእሸቱ ገጠሬው፣ እነሰሎሞን ባለ ሃውልቱ…„😂

• የራስ አርበኛ ደረጀ በላይ ከአበበ በለው ጋር መገገም ግን ደሬን በጎንደር ዐማራነቱ ላይ ጥያቄ እንዳነሣ እያስገደደኝ ነው።

• እየኮመታችሁ…✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…፩

"…ወደ ዐማራ ክልል በመሄድ የዐማራ ፋኖን ይገጥም ዘንድ በፈረንሳይኛ ልዩ የሽምቅ ውጊያ የሰለጠነው የሐረርጌው ቆቱ ሚሊሻ ከዘመቻው በፊት የምረቃው ዕለት በበርጫ ጓ ብሎ በምርቃና "ሚስቶቹን" ይሰናበት ዘንድ ቅልጥ ያለ ፓርቲ በዚህ መልኩ እነደተዘጋጀለት ሪፖርተራችን ቄሮ ኢብሮ ኢብሮሼ ከሥፍራው የላከልን ቪድዮ ያመለክታል።

• ነፍስ ይማር…! ፋኖ ግን ግድህ ፈላ…😂

"…እየገጠማችሁ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።” መዝ 113፥3።”

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ኧረ መግለጫው ዘገየ…!

"…እስክስ አበበ በለው አቤ ሰሞኑን ምነው ምነ ጠፋብን? የሰፈሩ ልጅ ደሬ አላምንለት ብሎ አስቸግሮት ይሆን? ኧረ ብቅ በል አቤ።

"…እነ ደሬስ ቢሆን እስከአሁን እንደተጓዙ ነው ወይ? ስንት ቀን ነው የሚጓዙት? ያውም አለቃችን እስክንድር ነጋ ነው። እኛ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዶላር እዝ ታማኞች ነን ብሎ አንዲት ገጽ ግንቦት 20 መስመር መግለጫ ለማውጣት እንዲህ መታሸት ከምር ፌር አይደለም።

"…ሀብትሽ አፍራሳም፣ ኤርሚ ዋቅጅራም፣ እየጠቧቸው መዘግየታቸው ልክ አይመስለኝም። ፍጠኑ። እስኬም እኮ ጨነቀው፣ ጠበበው። ሁለትም ባይሆኑ ደሬ ብቻውንም ቢሆን መግለጫ ቢሰጥ ጥሩ ነው። እስኬው ተስፋ ከቆረጠ ትግሉን ውኃ ነው የሚበላው። እናም ደሬ ከጓደኞቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ መግለጫ ቢሰጥ ጥሩ ነበር።

"…ዶላር ግን ኢንጂሩ። ሰው እንዴት አብሮ አደግ ዘመዱን አግቶ 600 ሺ ብር አስተፍቶ ይቀበላል? ከዚያስ የፋኖ መሪ ነኝ ብሎስ እንዴት ደፍሮ ይናገራል? ያውም ለለቅሶ የሄደን አብሮአደጉን አግቶ 600 ሺ ብር ከባድ ነው። ይሄም ወንጀል ከዚያው ከባለማተቡ ሀገር በጎንደር ምድር ላይ ተደረገ ቢባልስ ማን ያምናል? ከምር እንዲህ ሲባል ያሳዝናል፣ አንገትም ያስደፋል።

"ለማንኛውም አቤን ንገሩልኝ። ዘመዴ መቀስ ይዞ እየጠበቀህ ነውና ዛሬ እንዳትቀርበትም በሉልኝ። አደራ፣ አደራ ንገሩልኝ።

• ጆሌ ዶላሪ ጂርቱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

• ያራድዬ ልጅ… ይሞታል እንዴ…? ይብላኝ ለበቀቀን ካድሬው እንጂ እሱማ ውርደት ጌጡ እኮ ነው። አይሞቀው አይበርደው። እህእ…

"…ለማንኛውም ይሄን የዛሬውን 6 ፍሬ ሰው ብቻ የተባሳጨበትንና ጓ 😡 ብው ያለበትን ርእሰ አንቀጽ በተራችሁ ደግሞ እናንተ የፈለጋችሁትን ተንፍሱበት።

"…እንደኔ እንደዘመዴ "በቀኝ ትከሻዬን ሸከከኝ" እንደ ስዩሜ ተሾሜ በበርጫ ያለ ትንተና ሳይሆን በዕውቀት የሆነ ትንተና ተንትኑልን እስኪ። ምሽቴን የእናንተን ትን የሚያስብል ትንተና በማንበብ አሳልፋለሁ።

• 1…2…3…ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…
Subscribe to a channel