zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ሌላ ሰበር የግልግል ዜና…!

~ እልህ ምላጭ ሲያስውጥ እንዲህ ነው።

• በመጨረሻም እዚያ እዚህ ሲረግጥ የከረመው የጎንደር ስኳድ ፋፍዴኑ ወደ አንድ አቁማዳ ተሸክፏል። አሁን ለዐማራ ግልግል ነው።

"…ትልቅ ነገርም ነው። የእስክንድር ተልእኮና ማንነትም የበለጠ ግልጥ ሆኗል። የድርጅት ኢንኪዩቤተሩ እስኬው ዛሬ ደግሞ በጎንደር አዲስ ድርጅት ቀፍቅፎ አዋልዷል። ሸዋን ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ብሎ እነ መከታውንና አቤ ጢሞን ከእነ አሰግድ ገንጥሎ ጥሎ ጠቅልሎም ይዞ የነበረው እስኬ አሁን ደግሞ ጎንደር ፋኖን የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ብሎ እንደሸዋ ሽባ ሊያደርገው ሌላ ሁለተኛ ድርጅት ፈጥሮ አስፈጥሮም ከቻሳ ብሎ መጥቷል።

"…እነ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም፣ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ እነ እነ አበበ በለው ሰሞኑን እንቅልፍ ያጡበትን ጉዳይ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ለማንኛውም ጉዳዩ እየጠራ መጥቷል።

"…ለጎንደር ይሄኛውም አያዋጣውም። ለጎንደር ማሸነፊያው ለዐማራም ድል ማድረጊያው አንድነት ብቻ ነው። መላኩ አለበልና አገኘሁ ተሻገርም አረጋ ከበደና ተመስገን ጥሩነህም አያሸንፉም። ለማንኛውም እንዲህ ሲጠራ በጣም ጥሩ ነው። ያሳቀኝ ነገር የማከብረው ደረጄ በላይ ሞቼም ቆሜም ከፋፍዴን ጋር አልሠራም ሲለኝ ቆይቶ ጭራሽ የጌታ አስራደ አለቃ ሆኖ ከች ሲል ገረመኝ። ግን ቢሆንም እንዲህ ሲጠራ ጥሩ ነው።

• ፩ ዐማራ…✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አዛኜን 99.9% ተሳክቶ የቀረው ጥቂት ነው።

"…ሠራዊቱ በእስክንድር ነጋ መመራት፣ በጎንደር ስኳድ መሾር፣ መሽከርከር አይፈልግም። ኮሎኔሉም እንደዚያው። ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ ለመሆን ወሳኙ ነገር በፖለቲካው ቅማንት በትግሬ ዲቃሎቹ የጎንደር እስኳድ ከሚዘወረው ድርጅቱ ከሚባለው ኮተት መለየት ነው። ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው እሱ። በአንድ ቤት አንድ አባወራ።

• ፩ ዐማራ…✊

• ይኸው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ለዛሬ ስላልተሳካው የኮሎኔሉ መግለጫ ጥቂት ልበላችሁ

"…የዛሬውን ርእሰ አንቀጼን በግማሽ ልብ ነበር እየጻፍኩ የነበረው። ምክንያቴ ደግሞ በቅርበት የምከታተለው የወሎ ቤተ ዐማራ ልጆችን ትንሣኤና አንድነት የሚያበሥር የምሥራች ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ከቤተ ዐማራ ልጆች በኮሎኔል ፈንታሁን አማካኝነት ይበሠር ፣ ይታወጅ ነበርና ነው። አንዱን ልቤን ሁለት ቦታ ልኬ በመቸገሬ ምክንያት ርእሰ አንቀጹን ተረጋግቶ ለመጻፍ አልተመቸኝም ነበር። የሆነው ሆኖ የወሎ ዐማራ ዕዝ መሪ የነበሩትና በእስክንድር ነጋ ሕዝባዊ ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጣን የነበራቸው ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀቤ ለዛሬ 8:00 ሰዓት ከእስክንድር ነጋ ድርጅት መውጣታት መለየታቸውን በማወጅ ሊሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለጊዜው አቁመውታል። እኔም ወደ ቀልቤ ተመልሻለሁ።

"…በጎንደር የጎንደር ዐማራ የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞች በእነ አባት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ብርቱ ጥረት የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ መሪ በሆነው እና በአዲሱ የእስክንድር ነጋ ቄጤማ ድርጅት ውስጥ ምክትል የድርጅቱ መሪ የነበረው አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ድርጅቱን ለቅቆ ከወንድሞቹ እነ አርበኛ ባዬ ቀናው ከዐማራ ፋኖ በጎንደር ጋር የፈጠረው ዕርቅ በዓለሙ ሁሉ ከተሰማ በኋላ በመላው ዐማራውያን ዘንድ የተፈጠረው የደስታ ስሜት ይደግማል ተብሎ የተጠበቀው የዛሬው የቤተ ዐማራው የኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር። እሱ ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል።

"…ለጊዜው ኮሎኔሉን መግለጫውን እንዳያወጡ ጎትጉቶ ያስቀረው ይሄ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሰው ሲሆን ስሙም ብዙ ነው ተብሏል። አንደዜ መስፍን፣ አንደዜ ተስፋዬ፣ ሌላ ጊዜ ተስፋሁን ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህ ሰው ነው ኮሎኔሉን "ጫና በመፍጠር እንዳስቆመ የተነገረው።

"…ሰውየው ቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ሠራተኛ ሳይሆን ኃላፊ የነበረ፣ ተጣልተው እስር ቤት እስኪገባ ድረስ የጌታቸው አሠፋ ቀኝ እጅ የነበረ፣ አቶ ልደቱ አያሌውን ራሱ የማያውቀውን የመጬ የሌለ አስቂኝ ድራማ በመሥራት ከሕዝብ ሁሉ ልብ ያወጣ፣ በብአዴን አማካኝነት በዐማራ ኮታ ደኅንት መሥሪያ ቤቱን የተቀላቀለ። ከእነ ጌታቸው አሰፋ ጋር በተጣላ ጊዜ ወኅኒ ቤት ሲወረወር በዚያው በወህኒ ቤት ከኮሎኔል ፈንታሁን ጋር እና ከእስክንድር ነጋ ጋር መተዋወቁን፣ ኬኒያ ድረስ በመጓዝ ግንቦት ሰባት ሰዎችን እና የሻአቢያን መንግሥት ሰዎች ያገናኘ እና አብረው እንዲሠሩ ያደረገ ከባድ ሰው ነው ይባላል።

"…የፋኖ ትግል አይቀሬ መሆኑን በተረዳ ጊዜም በባልደራስ አብረው ከነበሩት ከእስክንድር ነጋ ጋር መጀመሪያ ወደ ጎጃም መሄዱም ተነግሯል። ዘመነ ካሤ እስር ላይ ስለነበር እስክንድርም በግማሽ ጎኑ ጎጃሜ፣ በግማሽ ጎኑ ደቡብ ጎንደሬ ስለሆነ በጎጃም መሠረት ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል። በወቅቱ የዘመነ መታሰር ብቻ ሳይሆን የጎጃም ፋኖዎች በየጎጥ በየመንደራቸው የተደራጁ ስለነበር በጎጃሜው አቶ ተመስገን ጥሩነህ መሥሪያ ቤት እርዳታ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ ሀብታሙ አያሌው ወዘተ እንደ ልባቸው ሊፈነጩ ችለዋል።

"…ሰውየውም ከእስክንድር ጋር ጎጃም የገባው እሱም በግማሽ ጎን ጎጃሜ፣ በግማሽ ጎኑ ወሎዬ ነኝ ይል ስለነበር እንደሆነም ተነግሯል። ይህ ሰው የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን መዋቅር በመጠቀም ጎጃምን እንኩትኩቱን ሲያወጣ ከከረመ በኋላ የእነ ዘመነን መፈታት፣ የተበታተነውን የጎጃም ፋኖ ወደ አንድ መምጣት ተከትሎ ሊከተላቸው የሚችለውን አደጋ በመፍራት ከእስክንድር ነጋ ጋር ሲያበጣብጠው የከረመውን ጎጃምን ለቅቆ እሱ ወደ ደቡብ ወሎ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ ጋር፣ እስክንድር ደግሞ ወደ ሸዋ ከደንበጫ ተነሥተው የሦስት ወሩን የእግር ጉዞ እነሱ በተአምራት ደመና ጠቅሰው፣ በደመና ተጭነው፣ ስምሪት ካሰማራቸው ኃይል አዲስ ስምሪት ወስደው አብረው ሸዋና ወሎ ላይ ተከስተዋል። ሰውየው በወሎ ኮሎኔሉን፣ እስክንድር በሸዋ መከታውን ጠርንፈው እንዲይዙም ተደርገዋል።

"…አራቱን የዐማራ ግዛት ወደ አንድ የፋኖ አደረጃጀት ለማምጣት የነበረው ጥረት እንዳይሳካ ያደረገው ይሄ ሰው አንደኛው ነው። የአመቻች ኮሚቴው በፋኖ ማርሸት ሰብሳቢነት፣ በዚህ ሰውዬ ምክትል ሰብሳቢነት፣ በጎንደሩ ፋኖ በኢያሱ ጸሐፊነት ነበር ሲመራ የነበረው። ኋላ ላይ ፋኖ ማርሸትም በሠራው ስህተት ከሰብሳቢነቱ ሲሰናበት፣ እሱ ምክትል ሰብሳቢ ስለነበር የሰብሳቢነቱን ስፍራ በመውሰድ፣ የስብሰባውን አካሄድ በመገምገም፣ እነ ጋሽ አሰግድ እስክንድርን መቃወማቸው ሲያበሳጨው የቆየው ሰውዬ ሁሉንም ከመስመር ስልኩ አስወግዶ "እስክንድር ነጋ ተመርጧል" በማለት ለዓድዋው ተወላጅ ለትግሬው ስታሊን ሰበር ዜናውን በመላክ የውንብድና ሥራም የሠራ ሰው ነው።

"…እኔ ዘመዴ ዘመዳችሁ የጎንደር ስኳድ፣ የዓድዋ ትግሬው ሚዲያ ዋና ሰው፣ የባልደራስ፣ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱ ካምፕ፣ እነ ግምቦቴዎች፣ ኦነጌና ብልፄ፣ ዶር ዳኛቸው አሰፋ፣ ሲሳይ አጌና፣ እነ መሳይ መኮንን፣ ኢትዮ ፎረም፣ ኤርሚያስ ዋቅጅራ፣ በለጠ ካሣ፣ እነ አበበ በለው ጭምር ተደራጅተው የረገጡትን ጮቤ በሰበር ዜና ገብቼ "ስቀዳው የነበረውን ኦዲዮ ለቅቄ፣ ቀዝቃዛ በረዶ ውኃ ቸለስኩባቸው" አፈሩ። ዋሾ፣ ቀጣፊ መሆናቸውም ተጋለጠ። እኔም የስድብ ውርጂብኝ ወረደብኝ፣ በተለይ የጎንደር ስኳድ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹ በሙሉ ጓ አሉብኝ። ዘመቱብኝ። እኔ ዘመዴ የዳዊት ጠጠር ደግሞ ለጎሊያድ ልደነግጥ? ኬሬዳሽ ብዬ ቀጠልኩ። ይኸው ተራ በተራ አጋድሜ፣ አጋድሜ አሰጣኋቸው።

"…ባይገርምላችሁ ከዚህ ዝግጅቴ በኋላ ሁል ጊዜ ከእስራኤል የሚደውልልኝ ዐማራ ደውሎልኝ ነበር። እኔም እንደወትሮው ለሰላምታና ለዐማራ አንድነት የዘወትር ቁጭቱን ይነግረኛል ብዬ ነበር እንደወትሮው ስልኩን ያነሣሁለት። እመቤታችንን መቼም ጠርቶ አይጠግብም። የዚያን ቀን ግን ከፍ ያለ እልህ፣ ቁጣ፣ ንዴት ጨምሮ ነበር የደወለልኝ። የተፈጠረውን ሁሉ ካስረዳሁት በኋላ ቆይ አንደዜ ልደውልና አውራቸው ይለኛል። እነማንን እለዋለሁ። ኮሎኔል ፈንታሁንንና መስፍንን ይለኛል። ምን ገዶኝ እለዋለሁ። ከዚያ ደውሎ ያገናኘኛል። ሁለቱንም አወራኋቸው። ያነዜ ነው ኮሎኔል ፈንታሁንን "ጮክ ብዬ በዚህ ሰው ፊት የተናገርኩት፣ ስማ አልኩት መስፍንና ሰውዬው ፊት፣ መጨረሻ ላይ የጎንደሩ ስኳድ ብቻህን ቀርጥፎ ይበላሃል፣ አንተ የጄነራል አሳምነው ጽጌ ወንድም፣ የሥራም ባልደረባ መሆንህን አትዘንጋ፣ ያልኩት ያነዜ ነበር።

"…ቆይቶ ተአምር ተፈጠረ። የስልክ ውይይያችን እየጋለ መጣ። በቃ እስክንድርን አንደዜ መርጠነዋል። ዘመነን በሰኔ 15ቱ ጎንደሬዎቹ ይጠሉታል። ብአዴንም ነው ይሉታል። የተማሩ ፕሮፌሰሮች ስለተቀላቀሉን እስክንድር መምራት ካልቻለ በ15 ቀንም ሆነ በወር በሁለት ወር እንቀይረዋለን። ብላ ብላ ይለኛል። ዘመነ ካሤ በዚህ ምክንያት ነው ምርጫ ሳይኖር በምርጫ እንደጣላችሁት አድርጋችሁ የዋሻችሁት እለዋለሁ። በቃ ዘመዴ ተወወን፣ አንተን 98% ፐርሰን ዐማራ በሥራህ ያምንሃል፣ ይከተልሃልም። እርዳን፣ ሕዝቡን አረጋጋልን ይለኛል። እኔም አልኩት "አንተ ልክ አይደለህም። መዋሸት ከአንተ አይጠበቅም። በሰኔ 15 ጉዳይ ከሆነ፣ ሀብቴም፣ ኮሎኔል ታደሰም፣ ሙላት አድኖም፣ ዘመነም፣ እነ ማስረሻ ሰጤም ተጠርጥረው ታስረዋል። እስክንድርም ይጠረጠራል፣ አንተ ደግሞ ቀጥተኛ ተሳትፎ አለህ ተብለህ ነው የታሠርከው። ስለዚህ ልክ አይደለም። እንዲያ ከሆነ እኔ ሙሉ ድጋፌን ከዛሬ ጀምሮ ለዘመነ ካሤ እሰጣለሁ አልኩት። ስልኩ በላዬ ላይ ተዘጋ።👇①✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…እንዲህ ዓይነት ትግል ነው የገጠመን…?

"…የቀረ፣ የተረሳ፣ የድሮ፣ ኦልዲስ፣ ዘመኑ ያለፈበት፣ ስድብ ካለና የረሱት ነገር ካለ ጨምሩላቸው።

"…አዲስ እና ብራንድ የሆነ፣ ሰሞኑን ለገበያ የቀረበም ስድብ ካለ ለጌታ ሰው ለጠቅላያችን እና ለማርሻል ፊልዳችን ጠቁሙልን።

• ገለቶማ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በኢትዮ ቤተሰብ ሚድያ የሚቀርበው ሳምንታዊው መርሀ ግብራችን እስኪጀመር ድረስ ርእሰ አንቀጹን በተመለከተ ደግሞ እስቲ እናንተን አስተያየት ልስማ።

• ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ …ሁላ ስለሚችል ላለመጣላት ብሎ ነው ለዛሬ ምንም የተለየ አዲስ ነገር ባይኖርም እስክንድርን ቃለ መጠይቅ አቀርብላችኋለሁ በማለት ቀጠሮ የሰጠው። እንጠብቀዋለን። እኔ እጠብቀዋለሁ። እንደ አቤ የሚያዝናናኝ ሰው በዚህ በስደት ሀገር በዚህ ጭለማ ክረምት አላገኘሁም። ሲቀር አይደለም ሲያረፍድ ሁላ መቀሴን ይዤ ነው የምጠብቀው። የእኔ እናት።

"…የትናንቱ የእስክንድር ነጋ "የዜሮ ድምር ቦለጢቃ" ትርክት የተኮረጀ ነው። አስቀድሞ ወያኔ፣ ከዚያ ኦነግ፣ ከዚያ የእስክንድር ምክትል የኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጂራ፣ የወነጌው ተብታባ ሞገስ፣ የአብን፣ የኢዜማ እና የወዘተዎችን ንግግር ነው ይዞ ከች ያለው። ሁሉም ከዚህ ከእስክንድር በፊት ስለ ዜሮ ድምር ፖለቲካ ያሉትን ዩቲዩብ ገብታችሁ ጎልጉላችሁ ተመልከቱት። ይሄ የሚያሳየው እስክንደር በጥባጭ አፍራሽ እንጂ አይደለም ፖሊሲ የራሱ የሆነ አዲስ አባባል እንኳን ይዞ መምጣት አለመቻሉን ነው ያሳየን። ከዚህ በፊት አቶ ልደቱ አያሌው ከኢሕአዴግ ጋር ሲከራከር "ዜሮ ድምር ፖለቲካ" የሚለውን በተደጋጋሚ ይናገረው እንደነበር አስታውሳለሁ። አንቼም ዜሮ ዜሮ። አከተመ።

"…ደፍረን መነጋገር አለብን። እነ እስክንድር ጃል ሰኚን ሆነው እንኳ እንዳይከሰቱ ቀልባቸውን መግፈፍ አለብን። ሰለሞን አጠናውን የመሰለ ፀረ ዐማራ ብሪቱ ይዞ ከፈለገ ይግባ እንጂ ምስኪን የሸዋ ዐማሮችን ለኦሮሙማው ፊዳ አድርጎ እንዳያቀርብ መከላከል፣ መሞገት፣ አለብን። እስክንድር በጥባጭ፣ አፍራሽ ነው። እስክንድር ጀምሮት ተቋም የሆነ አንድም ነገር የለም። እስክንድር በወያኔ ጊዜ ብልጽግና ከመምጣቱ በፊት 6 ጋዜጦችን ማለትም ኢትዮጲስ፣ ሐበሻ፣ ምኒልክ፣ አስኳል፣ ሳተናው እና ወንጭፍ የተባሉ ጋዜጦች መሥርቶ አንዱንም ከዳር ሳያደርስ በለብለብ ዜና ሳንቲም እየቃረመ ያፈረሰ ግለሰብ ነው። አስቡት ምኒልክ፣ አስኳልና ሳተናው በተመሳሳይ ጊዜ ይታተሙ ነበር። ሚስቱና እሱ በባለቤትነት የመሯቸው እነዚያ ተቋማት አንዳቸውም የሉም። እንዲሁም ከአብይ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላም 2 ሚዲያ መሥርቶ ነው ያፈረሰው። ኢትዮጰስ እና ሰናይ ቴሌቪዥኝ የተባሉ ማለት ነው ነው። ሰናይ ቴቪን አክሲዮን ሁላ ሽጦ በልቶበታል ነው የሚባለው። አሁንም በእጅ አዙር የሚቆጣጠራቸው፣ የሚረዳቸው ምኒልክ ቲቪ፣ 360፣ አበበ አዲስ ድምጽ፣ ጣና ቴቪም የእስክንድር ሀብቶች ናቸው። ዶላር ጠፋ እንጂ ከዚህም በላይ ይጨመር ነበር።

"…ይሄ ብቻ አይደለም ከብልጽግና በፊት መኢአድን እና ቅንጅትን አፍርሷል ተብሎ የሚታማው እስክንድር ብልፅግና ከተመሰረተ በኋላ እንኳ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶችን መስርቶ አራቱን በማፍረስ ስኬታማ የሆነ ሰው ነው ሰውዬው። ባላደራው፣ ባልደራስ፣ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር፣ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት እና አሁን ደግሞ የዐማራ ሕዝባዊ ድርጅት የተባሉ ድርጅቶችን መሥርቶ ነው ያፈረሰው። ይሄ ድርጅት ሲመሰርት ሲያፈርስ የከረመ ሰውዬ ነው እንግዲህ ትናንት ሀብታሙ አፍራሳ ጋር ቀርቦ ስለድርጅት መፍረስ ደረቱን ነፍቶ እየተንተባተበ ሲያወራ ያመሸው። እስኬው በሀብቴ ማምለጥ፣ በጎንደር አንድነት፣ በኮሌኔሉ ማፈግፈግ ሆን ብሎ ዐማራውን ሊያበሳጭ እና ፕሮቮክ በማድረገ ራሱን በራሱ ለማርካት የመፈለግ ሁናቴ ነው እንጂ ከቁምነገርም የሚቆጠር አይደለም። 

"…ካለፈው መስከረም ጀምሮ አበበ በለው በምሽት ፕሮግራሙ እኔን ሳያነሣ እንዳያድር ማስደረጌ ለእኔ ይሄ አንደኛው ስኬቴ ነው። ሌላ ሴራ፣ ሌላ ሸር፣ ሌላ ተንኮል ምድር ላይ ባሉት ፋኖዎች ላይ እንዳይጎነጉን እኔ ራሴ አጀንዳ ሆኜ እየቀረብኩለት ከእኔ ጋር ሲላፋ መሬት ላይ ያሉት እረፍት እያገኙ ነው። አበበ በየቀኑ ዘመድኩንን ከዛሬ ጀምሮ አላነሣም ይል ይምል ይገዘትና መልሶ የጠረረበት ዶላር በእኔ የተነሣ መሆኑ ትዝ ሲለው ሳያስበው ዘመድኩን በማለት ያላዝናል። እስክንድር እና አምሳሉ በሰጡት የምኒሊክ የአየር ሰዓት ላይ በቀደም ዕለት "ዘመድኩን ከመረጃ ቴሌቪዥን አየር ላይ ይውረድ እንጂ የቲክቶክ እና የቴሌግራሙ ባይቆምም ምንም አያመጣም ሲል ነበር። የቴሌግራሙን በእሱ ጉዳይ አልመለስበትም ካለ 24 ሰዓት ሳይሞላው ተመልሶ ይዞት መጥቶ ሲያለቃቅስብኝ አምሽቷል። እነርሱ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሕዝቡ አቢይን ተቃወመ ብለው ቦለጢቃ ሲሠሩ ቢውሉም። ዘመነ ካሴ፣ ባዬ፣ ምሬና ደሳለኝ የታል ሕዝባቸው ሰልፍ የወጣው? ብለው ሲንጫጩ ውለው እኔ በአንዲት ቪድዮ ድባቅ መትቼ አፈር ከደቼ አበላኋቸው። ለዚህ ነው አበበ ያበደው። የሽማግሌው መረሸን ሳያንገበግበው የመከታው ዕዝ መተቸት ነርቩን በጠሰው።

"…ሌላው እነ አበበ በለው፣ እነ ሀብታሙ አያሌውና እነ ፓስተር ምስጋናው፣ እነ አቶ አምሳሉ አስናቀ፣ ጋሽ እስክድር ነጋ፣ እነ ሙሉነህ ዩሐንስ እና የጎንደር ኅብረቶ በሲስተም የሸዋውን ዳያስጶራ ገንዘቡን ሊያልቡት ነበር አሰፍስፈው የነበረው። እኔ ዘመዴ ደግሞ ገጀራ ሆኜ የሸዋን ዳያስጶራ ከነመከታው ወደ እነ ደሳለኝ፣ ወደ ከሰም ክፍለጦር ፊታቸውን እንዲያዞሩ አደረግሁ። እዚያው እነ መከታው ጋር ሆነው የሚጠባበቁም አሉና ለእነሱም በመከታው በኩል ሳይሆን በግል እንዲረዷቸው ምክር ለገስኩ። አይ እኔ ዘመዴ አሁን ነፍሴ ይማራል ብላችሁ ነው። ይሄኔ በሰፊው የለመዱት እነ መከታው ገረጡ፣ ሚኪ ጠሽ ቤት ገብተው በማርያም አምስት አስር ጣል ጣል አድርጉልን ብለው ውርደት ላይ ወደቁ። በሳምንት 30 ሺ ዶላር ተቆጥሮ ከሸዋ ዳያስጶራ ይላክላቸው የነበሩት እነ አቤ ጢሞ ጨለሉ፣ በባዶ ሜዳ አክሮባት መሥራት ጀመሩ። እነ ፋኒት ባርች በF ወርድ በቲክቶክ ላይ መሳደብ ጀመሩ። ሁሌ ጮማ ራሳ ቀበሌ መሽጎ መቶ ሚልዮን ብር መሰብሰብ ቀረ። ሠርተህ ብላ ተባለ። አበዱ።

"…የሸዋው ዳያስጶራ ገገሜክስ ሲልባቸው አሁን እነ አበበ በለው፣ ያን የጎንደር ኅብረት አዋራውን አራግፈው ብር ሊግጡት መሰባሰባቸውን ሰማሁ። ከኮሚቴው መካከልም የእኔ ሰዎች እንዲካተቱ አደረግሁ። አሁን በቀጣይ እስራኤል ሀገር የሚገኘውን የጎንደር ዲያስፖራና በአሜሪካ፣ በአውሮጳ፣ በካናዳና በደቡብ አፍሪካ የተበተነውን ጎንደሬ በሰፊው ኪሱን ሊያራቁቱት ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን ደረስኩበት። ዘፋኞች፣ አክቲቪስቶች ሁላ ናቸው የተዘጋጁት። በትናንት’ ምሽት ዲስኩሩም አቤ እስክስ ደጋግሞ ሚሊየን ዶላር ከጎንደር ዲያስፖራ እንሰበስባለን ሲል ያደመጣችሁት ለዚያ ነው። በቅርቡም በየከተማው እየዞሩ በአዳራሽ እንደሚሰበስቡ ተናግሯል። የሸዋ ዲያስፖራ ላይ አፍጦ የነበረው የስኳድ ዓይን ተነቅሎ አሁን ጎንደሬ ላይ ተተክሏል።

"…የሸዋ ዲያስፖራ ደግሞ እሱንና ሀብታሙን ጭምር በደደብነታቸው ምን ያህል እንደሚጸየፉአቸው አይባንኑም። መቼም ድንቁርናቸው ለጉድ ነው። ሳይማሩ ራሳቸውን “ጋዜጠኛ” ብለው የሚጠሩ ጉዶች እነሱን አየሁ። ከዚህ ቀደም ፓስተር ምስጋናውም ተንግሮ ነበር። ተስፋ አድርገው የተነሡት የሸዋን ዲያስፖራ ነበር። የሸዋ ዲያስፖራ ደግሞ እነሱን መስማት፣ ማየትም አይፈልግ እንኳን ዶላሩን ሊሰጥ። እነ አበበም ገብቷቸዋል። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ጎንደር፣ ጎንደር ብለው መውጣት ብቻ ነው። የሚገርመው የጎንደር ዲያስፖራዎችም በተለይ ለእኔ የሚደውሉት ትልልቆቹ አበበን እንዴት እንደሚጠሉት አትጠይቁኝ። በተለይ ሃኪሞቹ በግልጽ ነው ይሄ “ደንቆሮ አዝማሪ” ብለው ክፉ ቃል የሚናገሩት። ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው። እንዴት እንደሚያፍሩበት፣ እንዴት አዋረደን እንደሚሉት አልነጋርችሁም። አሁን ከአበበ ጀምሮ ፕሮፌሽናል ማጅራት መቺዎችና…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ወደ ተናፋቂው እና በጉጉት ወደምትጠብቁት ተወዳጁ ርእሰ አንቀጻችን ልመጣ ነኝ። አላችሁ አይደል…?

"…ታስታውሱ እንደሆን በለፈው የሕዝባዊ ድርጅቱን ሰዎች ፎቶ ስለጥፍ በድፍረት የሀብቴ ወልዴንና የደረጀ በላይን ፎቶ ሸፍኜ ነበር ያወጣሁት። ደረጄ ለጊዜው ባይሳካም የሀብቴ ግን ተሳክቶልኝ ጎንደር ወደ አንድነት ለመምጣት መንገድ ጀምሯል። በጣም ነው ደስ ያለኝ። የደረጄ የማይሳካው ደረጄ በአበበ በለው የሰፈር ልጅነት የሚመራ በመሆኑ ነው።

"…ዛሬ ደግሞ የወሎውን አርበኛ የጦር መሀንዲሱን የኮሎኔል ፈንታሁንን ፎቶ ሸፍኜ መጥቻለሁ። ምክንያቱም የስኳድን ሴራ፣ የእስክንድርን አመራር ቅሽምና በግልፅና በድፍረት መቃወሙን በጆሮዬ ስለሰማሁ ማለት ነው። እናም የምሥራች ይኖር ይሆናል ብዬ ቀኝ ትከሻዬን እየሸከከኝ ስለመጣም ለጊዜው ከድርጅቱ አውጥቼዋለሁ።

"…የቀረውን ደግሞ በደንብ አድርጌ ላስነጥሰው ነኝ። የትናንቱንም ሰልፍ የሸዋውን ለእነ መከታው ተዘጋጅቶ የነበረውን ብሮባጋንዳ አፈር ከደቼ ላበላው ነኝ።

• እኔ ፊልድ ማረሻው ዘመዴ ላስነጥሳቸው ወይ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በአጭሩ የዛሬው ሰልፍ…😂

"…የዛሬውን ሰልፍ በተመለከት በሲአይኤ ማንዋል መሠረት ዲዛይኑ የተሠራው "ጎንደር እነ ባዬ፣ ወሎን እነ ምሬ ወዳጆ፣ ባሕርዳርን እነ ዘመነ ካሴ ነፃ አላወጡም። ነገር ግን ሸዋን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አርበኛ መከታው ማሞ አካባቢያቸውን ነፃ አውጥተው እንዲያውም አገዛዙን ተቃውመው ሁላ ሰልፍ ወጥተዋል የሚል መልእክት ነው በአጭሩ ማስተላለፍ የፈለጉት። በዚያውም ወደ ደሴ ኮምቦልቻ የሚወስደውን መንገድ ደብረ ብርሃን ላይ ዘግተው ሥርዓቱ ሽባ መሆኑን ያሳዩትን እነ ኢንጂነር ደሳለኝንም ማንኳሰሻ መሆኑ ነው።

"…ሀብታሙ አፍራሳም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ይዞት መጥቶ ከኤርሚያስ ለገሰ፣ ከሞገስ ዘውዱ፣ ከአብን እና ከኢዜማ ወዘተ በቀጥታ የተኮረጀውን "የዜሮ ድምር ፖለቲካን" ፍልስፍናን ቃል በቃል እስኬው ሲተርከው አምሽቷል። አንድ ታላቁ የተባለ የቦለጢቃ መሪ "አዲስ ፍልስፍና ይዞ ካልመጣ እንዴት ነው ቦለጢቀኛ ሊባል የሚችለው የሚሉም አሉ። ደግሞስ አበበ በለው ዛሬ እስኬውን ይዤ እቀርባለሁ ካለ በኋላ ሀብታሙ እንዴት ቀማው?

"…ሰልፉ አጠቃላይ በዐማራ ክልል ከሽፏል። የፖለቲካው ቅማንት፣ የትግሬ ዲቃሎቹ በሙሉ የከሸፈውን ሰልፍ መዘገብ ትተው "ጀግናው መከታው፣ እስኬ ብረቱ ሲሉ መዋላቸው ሲያስቀኝ ውሏል። በለጠ ካሣ ከኡጋንዳ፣ እነ ሚኪ ጠሽ ከጀርመን፣ እነ ሀብታሙ አፍራሳ፣ እነ ስኳድ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ወዘተ መከታው፣ መከታው መከታው ማሞ፣ ጀግናችን፣ ጀግናችን ሲሉ፣ ሌላውን ሲሰድቡ ውለዋል። 

"…ወዳጄ እኔ ነቄ ነኝ። መች አላውስህና። ወፍ፣ ወፍ የለም ስልህ። ተኛ።

ማስታወሻ፦ ይልቅ ወሬ ልንገራችሁ። ከዛሬው ሰልፍ በኋላ አጠቃላይ የብልጽግናው ጀነራሎች እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በአቫንቲ ሆቴል ውስጥ መሽገው እየመከሩ፣ እየዘከሩ ነው። ለሽንት ሁላ ንቅንቅ የለም። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የወሃቢ እስላም እኮ አይቀልድ…😂

"…ሰላም ሲለፈለግን በቃ ኑ። ሁላቹም ኑ አላለም። 😂

"…ከቤት ስኳር ቅሞ እናቱን ፈርቶ ጎረቤት ጓዳ የተደበቀ ሕፃን የሚጠራ እኮ ነው የሚመስለው። አይ ኦሮሞ አለ አቢይ…!

"…ቆይ የፋኖ ጠብ ከአባ ገዳ ጋር ነው እንዴ? አባ ገዳ ተብዬው ራሱ መርቆ ዐማራን ያጸዳለት ዘንድ ጫካ እንዳስገባው፣ አሁንም ሲጨንቀው ከጫካ ጠርቶ ካምፕ እንዳስገባው እንደራሱ እንደ ሸኔ ነው እንዴ ፋኖን የሚቆጥረው?

"…ዐማራ መድረሻ አጣሁ። የኦሮሞ ታጣቂ በኦሮሚያ ፈጀኝ፣ ገደለኝ፣ አረደኝ ሲል ባላየ ባልሰማ ካፊር ነው ይበለው ሲል ከርሞ ዛሬ ምን ታይቶት ነው ባካቹ፣ ባካቹ እያለ የሚወበራው?

"…የደጋ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ይቀጣል፣ 10 ዓመት ይታሠራል ሲል የከረመው፣ በደብረ ዘይት አህያ የገረፈ፣ የመታ በእስራት ይቀጣል ብሎ ለአጋዘንና ለአህያ መብት ሲታገል የቆየው አባ ገዳ ዛሬ ምን ዓይቶ ነው ፋኖ ከጫካ ኢምጣ፣ ኢታረቀን የሚለው?

"…ቀበሌ ሙሉ ዐማራ ሲታረድ፣ በግሬደር ሲቀበር፣ ኩላሊትና ጉበቱ ሲበላ፣ ከኖረበት ቄዬ ሲፈናቀል፣ ሀብት ንብረቱ ሲቃጠል። ካህኑ በመቅደስ፣ ምዕመናን በተገኙበት ሲታረዱ በልቡ ጮቤ ሲረግጥ የከረመው አባ ገዳ የሞት ባራኪ፣ ፀረ ሰው፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራ ገዳይ ቡድን ምን ሆኖ ነው ዛሬ በአጣዬ፣ በከሚሴ ዋይዋይ ሲል የዋለው?

~ ዐማራ ከአባ ገዳ ጋር ጠብ ከሌለው አባ ገዳ ምን አስለፈለፈው?

• አባ ገዳ ግን ሙንኡኖ ነው…? 

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በአጣዬ የአባገዳ ጥሪ…?

"…አጣዬ ሰባት ጊዜ ስትቃጠል፣ ስትወድም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ለሽ ብሎ ተኝቶ የነበረው የኦሮሞ አባገዳ በዛሬው ሰልፍ ላይ " መንግሥቲ አልነካቾውም፣ ኢምጡ ቢሏል። ጫካ ያላችሁ ኑ እናስታርቃቹ በማለት ለዐማራ ፋኖ ጥሪ አቅርቧል።

• ጃልሰኚ ደኅና ነው ግን…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አይ ዐማራ… ቅኔ የሆነ ሕዝብ እኮ ነው።

"…ህብለ ሠረሰሩን ነው የሰበሩት።

~ የብልፅግና አክቲቪስቶች ሙንኡኖው ነው ዝም ጭጭ ያሉት።

• ዐማራ አሸንፏል። አራት ነጥብ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ሰልፍማ ድሮ ቀረ። ወንዱ ሁሉ ሰይፍ አንሥቶ ፈነነ እኮ። በሴፍቲኔት እያስፈራራህ በግድ አሸማቀህ አደባባይ አሰወጥተህ፣ ፎቶ ተነሥተህ ብትበተን ምን ይጠቅምሃል? ምንስ ሊረባህ አጎቴ።

"…ሰልፍ ማለትስ ይሄ ነበር። ሰው እንዴት ራሱን በራሱ ለማርካት መከራውን ይበላል? ድሮ ድሮ ሰው ምን ይለኛል ይባል ነበር። አሁን ግን ቀረ ሳይሆን ጠፋ በለው። ይሉኝታን፣ ሼምን ቀርጥፈው በሏት።

"…ለማንኛውም ዐማራ ቅኔ የሆነ ሕዝብ ነው። ሰልፋማ ድሮ ቀረ። ምድር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ድሮ ቀረ። ሰይፍ ያነሣን ሕዝብ በሰልፍ እንዴት ትመልሰዋለህ? የማይሆነውን?

• ሰልፍማ ድሮ ቀረ አባቴ። የሚሰማው ሲያጣ ይሄ የምታየው ነጎድጓድ ወጣት ሰልፉን ጨርሶ ሰይፉን አነሣብህ እኮ። መፍትሄው ሰይፍ ብቻ ነው አለህ እኮ። ዓለም የጉልበተኞች ናት ስትለው እስቲ ጉልቤ ሆኜ ልሞክረው ብሎ ገጠመህ እኮ። ሚልኢላልኢሄ?

• ሰልፍ ድሮ ቀረ አልኩህ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…አንደዜ የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም። አንዴዜ ከልብ የወጣም አይመለስም። አንደዜ ሞቶ የተቀበረ ከትንሣኤ ዘጉባኤ ወዲህ አይነሣም፣ አይመለስም። ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ መመለሻም የለው። ነገሩ እንደዚያ ነው።

"…በጨዋ ደምብ አስቀድሞ እንደሠለጠነ ማኅበረሰብ ዘመኑን ዋጅቶ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወንድ ሴት ሳይል ግልብጥ ብሎ ነቅሎ ወጥቶ አደባባዩን ሞልቶ፣ መፈክር ጽፎ፣ ባነር ለጥፎ ኧረ በሕግ አምላክ አትግደሉኝ፣ አታሰቃዩኝ፣ እንደ ዜጋ ልቆጠር፣ መማር፣ ማስተማር፣ መነገድ፣ መሸጥ፣ መለወጥ፣ እንደልብ፣ በፈቀድኩበት፣ በሀገሬ መዟዟር፣ ማረስ፣ ማምረት አልከልከል። በጅምላ አልታፈስ፣ አልገረፍ፣ አልገፈፍ፣ አልታረድ፣ አልሰቀል፣ ሀብት ንብሬት፣ ከብቶቼን አልቀማ፣ እርሻዬ፣ ሰብሌ፣ ጎተራዬ አይዘረፍ፣ አይቃጠል፣ አይውደምብኝ። እንደ ቅጠል አታርግፉኝ፣ በማንነቴ ብቻ የዘር ጭፍጨፋ አትፈጽሙብኝ። ቤቴን አታፍርሱ፣ ትዳሬን፣ ቤተሰቤን አትበትኑት ብሎ በተደጋጋሚ ሰልፍ ወጣ።

"…በሰልፉም አሾፉበት፣ አላገጡበት። ለመፈናቀሉ ምክንያት፣ ለሞቱ፣ ለጭፍጨፋውም መልስ ተሰጠው። የምትፈናቀለው ዛፍ ስለቆረጥክ ነው። ሰፋሪ ነህ፣ ወራሪ ነህ አሉት። የምትገደለው፣ የምትጨፈጨፍም ዝኒ ከማሁ አሉት። ለሞትህ፣ ለተጨፈጨፍክበት ለአስከሬንህ ችግኝ እተክልልሃለሁ፣ አስከሬንህንም ፀሐይ እንዳይመታው መቃብርህ ላይ ጥላ ይሆንህ ዘንድ ዛፍ እንተክልልሃለን አሉት። በዋናው ሰው በአቢይ አሕመድ፣ በሕዝብ እንደራሴዎች ተላገጠበት። ደንቆሮው፣ መሃይሙ ፓርላማም እጁ እስኪላጥ አጨበጨበለት። ደመቀ መኮንን፣ አገኘሁ ተሻገር ሁሉም የዐማራ ወኪል ነነ የሚሉት በሞሉበት የበሻሻው አራዳ አላገጠበት።

"…የጎጃም ዐማሮቹ ኦርቶዶክሳውያኑ እዶር ደሳለኝ ጫኔ እና እነ ክርስቲያን ታደለ ቢያንስ እንኳ በኦሮሚያ ለተጨፈጨፉት ምስኪን ዐማሮች ምክር ቤቱ ለአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት ያድርግ ሲሉ ቢማጸኑም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፓስተር ታገሰ ጫፎ "ደግሞ ለዐማራ የምን ጸሎት ነው? ሥነ ሥርዓት" ብሎ ዘጋው። እንዲህ ነበር ዐማራው የተቀለደበት። የተሾፈበት። መሬቱ ዐማራም፣ ታጋሹ ዐማራም በታላቅ ትእግስት ጥያቄውን በጨዋ ደንብ ለታሪክም፣ ለትውልድም እያስመዘገበ፣ እየሞተ፣ እየተጨፈጨፈም ሕጋዊና ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ።

"…ዐማራው አዲስ አበባ ለመግባት ሰላሌ ላይ በኦሮሞ ጋጠወጦች ሚልዮን ብር ከፍለህ ግባ ተባለ። ዐማራ ስለሆነ ብቻ እንደ ቆሻሻ ተቆጥሮ በየማጎሪያ ካምፑ ተከተተ። ተጋዘ። በዚያም በሰበሰ፣ ቀመለ፣ ተላ። ሸተተም። በደሉ በዛ፣ ግፉም ሰማይ ጥግ ደረሰ። ምሑራኑ ተለቅመው ታሰሩ፣ ተገደሉም። ገበሬው ማዳበሪያ ተከለከለ። ያለው በደልና ግፍ አላንስ ብሎ ህወሓትና ብልጽግና ቤቱ፣ ቀዬው ድረስ መጥተው በመድፍ ተደባደቡ። ንብረቱንም አወደሙ። በማይካድራ፣ በጭና ዐማራው እንደ በግ ታረደ። ተጨፈጨ። በመላው ኢትዮጵያ ዐማራነት የሞት፣ የመሰደድ፣ የመፈናቀል፣ የመጨፍጨፍ ምልክት ሆነ። ለዐማራው የሚያዝንለት፣ ጠበቃ የሚሆንለትም ጠፋ። የሚከራከርለትም ሰው ታጣ። ሁሉም ናቀው። አቅመ ቢስ፣ ፈሪ፣ ሽንታም፣ ቅዘናም፣ ቦቅቧቃ ቢሆን ነው እንጂ እንዲህ ቀበሌ ሙሉ እየተጨፈጨፈ፣ በግሬደርም እየተቀበረ እንዴት አይቆጣም? እንዴትስ ራሱን ለመከላከል አይነሣም ብለው የሚያሾፉበት ነገዶች ተፈጠሩ።

"…ዐማራነት በኦሮሞ ነፃ አውጪና በትግሬ ነፃ አውጪዎች ዘንድ ማሾፊያ፣ መቀለጃ፣ መሳቂያ፣ መሳለቂያም ሆነ። ምንም አያመጣም። እንደ ባሪያ፣ እንደአሽከር ተረግጦ፣ ተወግሮ ከመገዛት በቀር ምንም አባቱ አያመጣም ተብሎ ተደመደመ። ዐማራው መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆመ። ግራ ተጋባ። ቤተ መቅደሱ ከነ ካህኑ፣ ከነዲያቆኑ ነደደበት። ምእመናን በመሰዊያው በታቦቱ ፊት በኦሮሞ ፅንፈኛ የወሃቢይ እስላሞች እንደበግ ታረዱ፣ ተጨፈጨፉ። ለዐማሮች የሚጮህላቸው፣ ድምጽ የሚሆንላቸውም ጠፋ። ራሱ ዐማራ ነኝ የሚለው ዳያስጶራ የግንቦት ሰባትና የፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ምርኮኛ፣ አሽከርና ገረድ ስለሆነ ደፍሮ እኔ ዐማራ ነኝ ለማለት አንደበቱ ተያያዘ። ልሳኑም ተዘጋ። ሌሎች ነገዶች ሳይቀር ዐማራ ማለት ፈሪ ነው እንዴ? እስከዛሬ ሲነገረን የነበረው ያሁሉ ጀግንነት ውሸት ነበር እንዴ? ብለው በዐማራው ነገድ ላይ በግልፅ ማፈር፣ ማላገጥ፣ ማንቋሸሽ፣ በዘመኑ ቋንቋ ሙድ ሁላ መያዝ ጀመሩ። በዐማራው ላይ ቀለዱበት አይገልጸውም።

"…ነፍሰጡር፣ ድርስ የዘጠኝ ወር የዐማራ ሴት በቁሟ አርዶ መብላት። የዐማራን ኩላሊት፣ ልብና ጨጓራ በሚጥሚጣ መብላት ነውር እንዳይደለ በቪድዮ አሳዩን። በኦሮሚያ ምድር ዐማራ አይወለድም ብሎ እርጉዝ መግደል፣ በወላጆች ፊት አባትን፣ ወንዶችን መድፈር፣ መግደል፣ ማረድ። የዐማራ ሰው ገድሎ ሕፃናት አንገቱን በገመድ አስረው እያሾፉ፣ እየቀለዱ፣ እየተፉበት፣ እንዲሳለቁበት፣ ቪድዮም ቀርጸው በሀረር ከተማ የመስፍንን አስከሬን በመጎተት ለዓለሙ ሁሉ በተኑት። ዐማራ ተሰቃየ። መድረሻም አጣ።

"…ዐማራው በሁሉም ቦታ ውክልና አጣ። ለትግሬ ህወሓት፣ ለኦሮሞ ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ ለሌላውም ሌላው ውክልና ወስዶ መብቱን ይጠብቅለት ያስጠብቅለት ነበር። ዐማራው ግን ባልወከለው፣ ባልመረጠው በህወሓት ተሠርቶ፣ ለኦህዴድ ብልፅግና በውርስ፣ በአደራ በተላለፈው በበድኑ ብአዴን ይረገጥ፣ ጭራሽ በገዛ ክልሉ ውስጥ ይረሸን፣ ይገደልም ጀመር። እስቲ ሌላ ወኪል ልፈልግ ብሎ አብን የሚባል ፓርቲ ቢመለከትም አብንም በጎንደር ስኳድ፣ በፖለቲካው ቅማንት በትግሬ ዲቃሎችና በአገው ሸንጎ ተጠልፎ መልሶ መከራ ሆነበት። ዐማራ ጨነቀው፣ ጠበበው።

"…ኖ ሞር ብሎ በቃ በማለት መፈክር ይዞ ሰልፍ ቢወጣ ይሄን ያዩ ትግሬዋ ሄርሜላና ኤርትራዊ ወዳጇ ከግንቦት 7 ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ጋር በማበር፣ በመነጋገር መፈክሩን ቀምተውት ለብልጽግና ተገረዱበት። መፈክሩን ብልፅግና ወሰደው። ግንቦት ሰባት የዐማራን ብሩን ብቻ ሳይሆን የተቀውሞ መፈክሩን ኖ ሞርንም በትግሬዎቹ አስቀማው። ዐማራው ድምጽ አጣ። በገዢዎች ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚዎቹ በኩል ሁላ ክብርን፣ ሞገስን ተነፈገ። ከእኔ ከዘመዴ በቀር በአደባባይ በድፍረት አንድም ድምጽ የሚሆነው ሰው አጣ። ዐማሮች ተናቀ፣ ተዋረዱ፣ በገዛ ልጆቻቸው ሳይቀር ተሸማቀቁ። መድረሻ አጡ።

"…ዳያስጶራው ተቃዋሚ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ የዳያስጶራ ዐማራውን አጃጅሎ እንደ ፈረንጅ ላም ገንዘቡን ብቻ፣ ዶላር ፓውንዱን፣ ዩሮውን ብቻ ይገፍፈው፣ ያልበው ነበር። ዐማራው በዐማራነቱ እየታረደ፣ እየተጨፈጨፈ ዐማራ ታረደ፣ ተገደለም አትበሉ፣ ዐማራ ሞቶ ሳለ ዜጎች ሞቱ ይባል። ዐማራ ዘረኛ መሆን የለበትም፣ በዘሩ መጠራት የለበትም ብለው የግንቦት ሰባት ማዴቦዎች፣ ብራኑ ነጋዎች ሰቅዘው ያዙት። እነ አጌና፣ እነ አፍራሳ፣ እነ ዋቅጅራም የዐማራ ድምፅ ነን ብለው ከፊት ተሰለፉ። ዐማራው ተደበቀ።

"…ዐማራው በፈሪ የዐማራ ጳጳሳት፣ ሃይማኖት በሌላቸው ካህናት፣ ፀረ ዐማራ በሆኑ ሼሆች፣ ኡስታዞችና ፓስተሮች ሁሉ ነው የተካደው። ለብልፅግና ለአራጁ ለአቢይ አሕመድ ድጋፍ ቀሚሳቸውን ገልበው፣ ብብታቸውና ብሽሽታቸው በላብ እስኪጨቀይ፣ ልሳናቸው እስኪዘጋ፣ ድምጻቸው እስኪሰልል፣ ጉሮሮአቸው ላንቃቸው እስኪሰነጠፍ፣ በጠራራ ፀሐይ፣ በክረምቱ የአውሮጳና የዐሜሪካ በረዶ የደገፉት ጳጳሳት ተብዬዎቹ ዐማራ መሳይ አማሮችም ደብዛቸው ጠፋ። ፈሪ፣ የሃይማኖት መልክ ያላቸው፣ ግን ሃይማኖትም የሌላቸው ጳጳሳት ከዱት። ገንዘቡን እንጂ እሱን የማይፈልጉት ሰባክያን፣ ለትግሬ ሞት ዋይ ዋይ ያሉ እንደ ሄኖክ ሃይሌ ያሉት…👇①✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መራር እውነት

"…በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ወረራ ወቅት ወራሪው የኦሮሞ ሠራዊት በኢትዮጵያ የነበሩትን ነገዶች በሙሉ ያጠፋው ከጦርነት ባሻገር ዋነኛው በራብ ነው ይላሉ የታሪክ ሰዎች። ኦሮሞ የከብት ጭራ በመከተል፣ በእንስሳት ማርባት ነበር ሕይወቱን የሚገፋው። ወተት ይጠጣል፣ ከርቢው አርዶ ይበላል። አለቀ።

"…በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩትን የሀዲያ፣ የዐማራ፣ የጋፋት ወዘተ ነገዶችን ክረምት አርሰው፣ መስከረም አርመው፣ ጥቅምትን ተንከባክበው፣ ህዳር አጭደው፣ ታህሳስ በጎተራ ይከቱ ና ጥር ላይ የምድር ፍሬን፣ የደከሙበትን የላባቸውን ውጤት ለመብላት ሲዘጋጁ ኦሮሞ ሆዬ ቀን ጠብቆ ወረራ በመፈጸም፣ የበሰለውን በልቶ፣ ሌለውን አቃጥሎ፣ አውድሞ፣ ወንዱን ሰልቦ፣ ሴቷን ማርኮ፣ በጉንም፣ ፍየሉንም፣ ከብቱንም ዘርፎ ይሄዳል። ከወረራ ያመለጠው በራብና በጠኔ ይረግፋል። ኦሮሞ ወተት እየጠጣ ገበሬውን ነገድ ድራሽ አባቱን ነው ያጠፋው። ኦሮሞ የከብትና የግመል ወተት በመጠጣት በሕይወት መቆየት ይችላል።

"…በዘመኑ ዐማራ ዘሩን እንዳይተካ ጄኖሳይድ ነበር የፈጸሙበት። ይሄን ሲያደርጉ ጋላ ተብለው ይጠሩ ስለነበር ኋላ ላይ ጀርመናዊ መነኩሴ ክሩፍ ኦሮሞ የሚል የጄኖሳይዳል ስማቸውን የቀየረላቸው። ይሄ የ16ኛው ክፍለ ዘመን የጋላ ወረራ ታሪክ ነው። አሁንስ…? አሁን ትግሬን አደቀቁት። ዐማራን በራብ፣ በጥም፣ በአረብ ቦንብ እየፈጁት ነው።

"…አባቴ አንተ ለምን ፍግም አትልም የኦሮሞው ፓርቲም ሆነ የኦሮሞዎቹ አለቃ አቢይ አሕመድ ደንታ አለው እንዴ? አንድ ላይ ቆመህ ጠላት እንዳትመክት እንኳ እስክንድር ነጋ የተባለ ቅጥረኛ ውስጥህ ገብቶ ያምስሃል፣ ያተራምስሃል። አሜሪካ መግለጫ ሰጠች አልሰጠች ለዘር አጥፊው ደንታው አይደለም።

• ለማሸነፍ አንድ ሁን፣ ዓምደ ጽዮንን አምጠህ ውለድ። ይኸው ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ✍✍✍ "…የደወለው የእስራኤሉ ወንድም ስለሆነ እኔ አልሞቀኝ አልበረደኝ። ቆይቶ ግን ይሄው እስራኤላዊ ደዋይ ወዳጄ በጣም ተቆጥቶ መደወል ጀመረ። የኮሎኔሉ ስልክ ዝግ ሆነ። ቆይ ብሎ እየተቆጣ ወደ መስፍን ደወለ። መስፍን ስልኩን አነሣ። የእስራኤሉ ሰውዬ ቆጣ ባለ ድምጽ ዐውሩት እንጂ። ለምን ስልክ ትዘጋላችሁ። ከተሳሳታችሁ ታረሙ አለ። ኮሎኔሉንም አስገባው አለው። መስፍን ተብዬውም ዘመነ አይሆንም። ዘመነ አይመራንም አለኝ። እኔም መልሼ መች ይምራህ አልኩህ። ምርጫ ተደርጎ ሠራዊቱም፣ ሕዝቡም ዘመነ ይምራን ካለ አንተ ምን ቤት ነህ? ምን ያበሳጭሃል አልኩት። አይሆንም አይሆንም ከእስክንድር በቀር ሌላ ሰው አይሆንም። እስክንድር አቅም አለው። ከውጪዎቹም ጋር ይገናኛል ብሎ ገገመ። እሱንም ጉባኤው ይወስናል እንጂ አንተ እኮ አይደለህም ብዬ አቋም ያዝኩ። በዚያው ተለያየን።

"…ከውይይቱ ይልቅ እኔን ቀልቤን የሳበው የእስራኤሉ የስልክ ወዳጄ ነበር። ሲቆጣቸው፣ በአንድ ስልክ ጥሪ ሲያገኛቸው። ከዘመዴ ጋር አውሮ ብሎ ሲያዛቸው። የእነሱ ታዛዥነት፣ እሺ ባይነት ገርሞኝ ጠይቄ የማላውቀውን ታሪክ ጠየቅኩት። እኔምልህ ይሄን ሁሉ የምታደርገው በምን ኃይልና ሥልጣን ነው? ዘርህስ ከወዴት የሚመዘዝ ነው አልኩት። እሱም ከጎጃም እንደሆነ ነገረኝ። የእስራኤል የደኅንነት መሥሪያ ቤት አባልም እንደሆነ ነገረኝ። እናም ይሄን ወሎ ተቀምጦ ኮሎኔሉን የሚያሾረው የጌታቸው አሰፋን ሰው ባሰብኩት ጊዜ ነገሩ ሁሉ ተገለጠልኝ። እስኬውን ሲአይኤ እንዳልጠረነፈው ማን ሊያስረዳኝ ይችላል? ሰሞኑን የሰሙትን ሰምተው ነው ለካስ እነ አኪላ ኮሎኔል ፈንታሁንን ይሞልጩ የነበረው። አሁን እኮ ነው የሚበራልኝ።

"…የኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤን የጦር አዛዦችም አሁን ደውለውልኝ ጥቂቶቹን ሰምቼአቸዋለሁ። በሙሉ ጦሩ ከወንድሞቻችን ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ እንሆናለን። እስክንድር ነጋም አይመራንም። ኮሎኔልም ከእኛና ከእነርሱ አንዱን ይምረጥ ብለው ነግረውኛል። አከተመ።

[እንደ መውጫ ለፈገግታ]

"…ሰሞኑን የጎንደሩ እስኳድ ስለ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ አንድ ሪፖርት ያቀርባል። ኮሎኔል ፈንታሁንን በልጅ አስረነዋል። ከሸዋ ከመከታው ጋር የተላከች ልጅ ኮሎኔሉ ጋር ሄዳ እንድታረግዝለት አድርገናል። አሁን ሰሞኑን ወልዳለች። ለዚህም 10 ሺ ዶላር አስተላልፈናል ይላሉ። እኔም ወደ ኮሎኔሉ እንደወረደ መልእክቱን ላክሁኝ። "ኧረ ዘመዴ እንደው ልከውልኝ ዘር በተካሁ። እንኳን 10 ሺ ዶላር! 10 ዶላርም አልላኩልኝም" ማለትን ሰማሁ። እነ ሀብትሽ፣ እነ አምሳሉ በመሃል 10 ሺ ዶላር እምጷ ቀሊጦ አደረጉ ማለትም አይደል ብዬ ፈገግ አልኩ።

"…ዛሬ ለጊዜው የኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው ከእስክንድር ድርጅት መለየቱን ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ አልተሳክቶም። ዛሬ አይሳካ እንጂ ነገ ግን መሳካቱ ግድ ነው። ትናንት ለኮሎኔሉ በቃል የነገርኩትም ይሄንኑ ነው። ዐማራ ከአንድነት በቀር ሌላ መዳኛ፣ ምርጫም የለውም።

• አለቀ፣ አበቃ፣ አከተመ፣ ሃላስ… ፩ ዐማራ✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰበር ዜና…

• ጋዜጣዊ መግለጫው ለጊዜው ተሰርዟል…

"…በምሥሉ ላይ በምታዩት ሰው ጫና ምክንያት ለዛሬ 8:00 ሰዓት በኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ ከእስክንድር ድርጅት በይፋ መውጣትና መለየት ዙሪያ ይሰጣል ተብሎ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። ሠራዊቱ አጉረምርሟል። ደቡብ ወሎ ጭንቅ በጭንቅ ሆኗል።

"…ስኳድ ያለ የሌለ ኃይሉን አሟጥጦ ርብርብ ይዟል። እስክንድር ነጋ ኮሎኔሉን የዛሬን ቅበረኝ፣ አታዋርደኝ ብሎ ልመና ይዟል ነው የሚባለው። ሰሞኑን በነበረ ስብሰባ ላይ ኮሎኔሉ እስክንድርን "አንተ ድርጅት መምራት አትችልም። አቅመ ቢስ ነህ፣ በቃ ገለል በል ከዐማራ ትግል" እንዳሉት የደረሰኝ መረጃ ያሳያል።

"…ኮሎኔሉን ለጊዜው ያስቆማቸው ይህ ሰው ማነው? የዛሬውን ርእሰ አንቀጼን ወደ አዘግይቼ ቅድሚያ እሱን እለጥፍላችኋለሁ። ትንቅንቁ ቀጥሏል። የጎንደር ስኳድ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቷል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴሩ አቶ መላኩ አለበል ሰማይ ምድር እየረገጠ ነውም ተብሏል።

• ተመልሼ እመጣለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ወደፊት አንድ ፩ ዐማራ

"…40ም ዓመት ይፍጅ 4 ዓመት፣ አልያም 4 ሳምንት ብቻ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ዐማራው ዐማራ ሆኖ ተነሥቷል። እንዲህ እንዲሆን ነበር ምኞቴ፣ ስዕለቴም። አሁን ያሰብኩት እየተሳካ ነው። ህልም ምኞቴም እየተፈጸመ ነው። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዐማራ እንደ እስራኤል ለአንድ ዜጋው ደኅንነት የገባበት ገብቶ ተግቶ ይሠራል። ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ። ለአሁን ግን ስለዚህ መረጃ ልስጣችሁማ።

• የሥልጠና ማዕከሉ
ፀደይ ወታደራዊ ፋኖ ማሰልጠኛ

• አሰልጠኝ ክፍለ ጦሩ
ዓድዋ ክፍለጦር

• የሥልጠናው ተቆጣጣሪና አሰልጣኝ
ኮማንዶ ሳሚ ባለ ድል

• አሰልጣኞች
የዐማራ ፋኖ በጎንደር
የዐማራ ፋኖ በጎጃም፣

• ሰልጣኞች
የጎንደር ቀጠና ሰልጣኞች
…የጎጃም ቀጠና ሰልጣኞችና
…ከፊል የወሎ ቀጠና ሰልጣኞች ናቸው።

• ደስደስ እያለኝ ኖ አለ አዝማሪው።

• ጎንደር
• ጎጃም
• ወሎ
• ሸዋ አንድ ፩ ዐማራ ወጥር ዐማራ ✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…4 ኪሎ በሚገኘውና የዕድሳት ጊዜው በመጠናቀቅ ላይ ያለው በጥንታዊውና በታሪካዊው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጠኛ ክፍል ከዋናው የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በር እስከ መቅደሱ ድረስ መሬት ላይ በምታዩት መልኩ ቅዱስ መስቀሉ በትልቁ ተቀርጾ በመሬት ላይ ተለጥፋል። ምን አስበው ነው ግን…?

"…ኢሉሚናቲዎች እና ሰይጣኒዝም አምላኪዎች ነበሩ እስከዛሬ ድረስ በአምልኮ ምኩራባቸው እንዲህ ባለ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስን እና ክቡር ቅዱስ መስቀሉን አማኞቻቸውን አስረግጠው የሚገቡት። እናስ የእኛዎቹ አባቶች ምን አስበው ነው በዚህ መልኩ ፍጥጥ ብለው የመጡት…?

"…እንጠይቃለን…! በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጠን ዘንድ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ተከታይ ከፍ ባለ ድምጽ እጠይቃለሁ።

"…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል" ማቴ 24፥ 15

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…!

"…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል።

የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ

👉YouTube
https://www.youtube.com/live/9i67s9DzoWE?feature=shared

👉በረንብል /Rumble
https://rumble.com/v60vkdz--ethiobeteseb.html

👉በፌስቡክ / Facebook

facebook.com/ethiobeteseb

👉 በቲውተር / Twitter
https://twitter.com/EBeteseb

👉 ቴሌግራም / Telegram
/channel/ethiobeteseb

"…ሻሎም !  ሰላም !

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …ለምኖ አዳሪዎቹ በሙሉ ቀን ጨልሞባቸዋል። ሁሉም ሌቦችም፣ ለማኞችም ናቸው።

"…የጎንደር ኅብረት የሚባለው እነ ዩሐንስ ሙሉነህ በ2016 ዓም ከሁሉም ዐማራ ብዙ ሺህ ዶላር ሰብስበው የጠፉ ናቸው። እነ መሳፍንት ባዘዘው የአብንን የተዋጣ ወደ 200ሺህ ዶላር ዘርፎ የጠፋ ሰው ነው። አያሌው መንበር ለአስራት ቲቪ የተዋጣን ከ300ሺ ዶላር በላይ ያወደመ እና ተቋሙንም ያፈረሰ ሰገጤ ነው። አያሌው በብአዴን አባቱ ቤት የለመደውን አሜሪካ ቁጭ ብሎ "የልብስ ባጀት፣ የሻይ የአበል እያለ ሶፋና ወንበር፣ ውድ ካሜራ ገዝቶበት ብሩን የጨረሰ እና ተቋሙን ያፈረሰ ሰው ነው። ሙሉቀን ተስፋው አብኔት ለሚባል ቲቪ ወደ 200ሺህ ዶላር ስብስቦ የጠፋ እና ተቋሙን ያፈረሰ ነው። አበበ በለው ሳይጠየቅ ለአብን እሰበስባለው ብሎ ሲያምታታ ሲሰበስብ የነበረ ሰው ነው። ከባልደራስ እስከ ሕዝባዊ ሠራዊቱም ገንዘብ ሰብሳቢ ቀማቴ ነው። አብን አሁን በአብይ በልጽጓል፣ አበበ’ም በዶላሩ በልጽጓል። አበበ ለዋሽንግተን ዐማራ ማኅበርም እሰበስባለሁ እያለ ቤት እና ቴስላ የገዛ ሰው ነው። ዕድሜ ልኩን አዲስ ድምጽ እያለ ሲለምን የኖረ ለማኝ ነው።

"…አምሳሉ አስናቀ፣ አበበ በለው፣ ሙሉጌታ አያሌው፣ ኤርሚያስ እሹሹ፣ ሰርካለም ፋሲል፣ ሀብታሙ አያሌው ለባላደራ፣ ባልደራስ፣ ሰናይ ቴሌቪዥን፣ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ እያሉ ዶላር ሲሰበስቡ እና ሲዘርፉ የኖሩ ዘራፊዎች ናቸው። ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ ደረጀ ተሾመ፣ ሳሙኤል አበበ፣ ለዐማራ ፋኖ በጎንደር ለነ አርበኛ ባየ የተሰበሰበን ዶላር ዘርፈው ጣና ቴሌቪዥን ምናምን ከፍተንበታል ያሉ ዘራፊዎች ናቸው። እስክንድር፣ ሀብታሙ፣ አበበ ሳይለምኑ በእራሳቸው ሥራ ሠርተው ኑረው አያውቁም። በአሜሪካ ሬስቶራንት ገብተው የበሉበትንና የጠጡበትን መክፈል የማይችሉ ሰዎች ለሕዝብ ገንዘብ ለመሰብሰብ አይታመኑም። ትናንት ባሎቻቸው መሬት ላይ የሚዋጉ የፋኖ ሚስቶች ደውለው አለቀሱ፣ አንዷ እናት ናት ምናምን ሲል የነበርው ሰርካለምን እኮ ነው። ከዚህ በፊት ራሱ የተናገረውን ነው የምነግራችሁ። እናም ወሎ ላስታ ሰው ተርቦ እንደ ቅጠል እየረገፈ ለጥጋበኛ በዐማራ ችግር ልመናን መተዳደሪያቸው ላደረጉ ሱፍ ለባሽ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ የጎንደር ስኳድ የኢንተርኔት ላይ ለማኞች የምትቀልቡበት ምክንያት አይታየኝም። እናንተ ምንአገባህ ብትሉኝም እናንተ ተይዛችሁ፣ በሱዳን መተት ውለውባችሁ ነው ብዬ ስለምጠረጥር መናገሬን አላቋርጥም። 😂 ማርያምን አልፋታቸውም። ፋኖ የወከለው ርዳታ አሰባሳቢ እስኪመጣ እነዚህን ቀማኛ ገፍፎ አዳሪዎች መቀጥቀጤን አላቆምም። አበደን።

"… ትግሬዋ የእስክንድር ሚስት የምትኖረው በዐማራ ስም ባሏ እየለመነ በሚያመጣው ብር ነው። የዲሲ ግበረ ኃይሎችና አምሳሉ አስናቀ ናቸው ከፋዮቹ። ሰርካለም እንደለመደችው የሰው አንጀት ለመብላት አሁንም ሰዎች ጋር እየደወለች የባሌን የእስክንድርን ፎቶ ልላክላችሁ? እንዴት እንደተጎሳቆለ ብታዩት ታዝናላችሁ ምናምን እያለች እንደነበር የተደወለላቸው ነግረውኛል።  የሰሞኑ የሰሎሞን አጠናውና የኢያሱ የስልክ ቅጅ ግን ቀልቧን ገፏታል። ባሏም ወጥቶ ስለጎንደር’ም ሆነ ስለድርጅቱ የነገረን በስልክ ቅጂ የሰማነውን ነው ደግሞ የዘበዘበን። የስልክ ቅጅው ትክክል የመሆኑ ማረጋገጫው እስክንድር በስልክ ቅጅው የሰማነውን ዕቅዳቸውን መልሶ የነገረን። አልፋታቸውም ስልህ አባቴ።

"…መሬት ላይ ትልቅ ሥራ እየተሠራ ነው። በቅርቡ የምሥራች ትሠማላችሁ። የአየር ላይ አጋንንቱን እኔ የደብተራው ልጅ ዘመዴ ብቻዬን አምላኬን አጋዥ አድርጌ እብድ እብድ እየተጫወትኩ እሬቻውን አበላዋለሁ። ወሎ ቤተ ዐማራ አንድ ከሆነ በኋላ ጎጃም ላይ አንዴ እዞርበታለሁ። በጎጃም አንዴ በስሱ የማጥራት ሥራ እሠራለሁ። አሰልፌ እዠልጣቸዋለሁ። ያበጠ መፈንዳት አለበት። ደግነቱ ጎጃም ምክር ይሰማል። ያዳምጣል። ራሱን ይገመግማል። እንደ ጎንደር ስኳድ እንደ ፖለቲካው ቅማንት እንደ ትግሬ ዲቃላው እልኸኛ አይደለም። የጎጃም ሴረኛ አገው ሸንጎና የብአዴን ሴል አፈረሰዋለሁ። በመረጃና በማስረጃ ነው የምንደው። ሱፐር ሶኒክ ሚሳኤል ነው የማስወነጭፈው። ግንቦቴን፣ ግንባሩንና ስኳድን የሚያስደስት፣ ጮቤ የሚያስረግጥም አይደለም። ይኸው ጎጃም ላይ መጣ ብላ ብላ ብለው ትንሽ ለሃጫቸውን እያዝረበረቡ የጣልኩላቸው የአጀንዳ አጥንት ላይ እንዲራኮቱ እነሆ ለእነ ቡቺ እና ውሮም ወርውሬላቸዋለሁ። ጎጃም የማጣሪያ ሽያጭ መፈጸም አለበት። አለቀ። የእኔ ሥራ አጀንዳ መሸጥ ነው። ይሄን አንብበው በውስጥ ቢደውሉልኝ እንኳ አልሰማቸውም። ደብቀው የያዙትንና እስከ ዛሬም የሚያስታምሙትን ደስ ባለኝ ቀን፣ ቀኝ ትከሻዬን በሸከከኝ ዕለት አፈነዳዋለሁ። የወለጋ ፋኖን ምስረታም በተመለከተ የምለው ይኖረኛል። እነ አኪላና እነ እስክንድር፣ የኡጋንዳ እስኳድ የሚመራው ፋኖ በወለጋ አይኖርም። ሴራዋን አከሽፋታለሁ። አለቀ።

"…ምሽት በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ እስክንገናኝ ድረስ ቸር ቆዩኝ። እስከዚያው ይሄን እያነበባችሁ ጠብቁኝ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…✊
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…✊

••• ከ30 ደቂቃ በኋላ እመለሳለሁ። የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው እያነበባችሁ፣ አስተያየታችሁንም ጽፋችሁ አዘጋጅታችሁ ቆዩኝ። መልካም ንባብ።

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 10/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…እኔ ከተናገርኩት፣ እኔ ካወራሁት፣ ይሸክከኛል ብዬ ከጻፍኩላችሁ ሺ ምንተ ሺ ጦማሮች መሃል ምን ያልተፈጸመ አለ? እብድ ነው፣ ዘብዛቢ ነው፣ ተሳዳቢ ነው፣ ጯሂ ነው፣ ዘርጣጭ ነው እያላችሁ እየናቃችሁኝ፣ ዲግሪ የለውም ዲፕሎማ እንጂ እያላችሁኝ፣ ዶፍቶር፣ ፍሮፌሶር አይደለም ጎጋ መሃይም ነው እያላችሁኝ፣ በእንግሊዝ አፍ አያወራም፣ አይጥፍም እያላችሁ እየናቃችሁኝ እንጂ በእኔ በማይሙ ዘመዴ ተጽፎ ያልተፈጸመ ምን አለ? ይቆያ ይዘገይ ወይ ወዲያው ይፈጸም ይሆናል እንጂ ምን አለ አልኳችሁ እኮ? አዛኜን የኢትዮጵያን ጉዳይ እኮ ካለሁበት ሆኜ እንደ ተከታታይ ፊልም ነው ቁጭ ብዬ ሳይ ስመለከት የምውል የማድረው። ለሥልጣን፣ ለገንዘብ፣ ለእውቅና ግን አይደለም የምቸከችከው። የዳዊትን ጠጠር ሆኜ ጎልያዶችን ልገነድስ፣ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን ልመነጥር፣ ሾተላዮችን ልነቅል ግን መቀባቴን አልክድም። እኔ ከኢዩ ጩፋ፣ ከዳንሳና ከዮናታን በምን አንሼ ነው? አሜን ነው?

"…ከወር በፊት እነ ኤልያስ አኪላ፣ እነ ዘርዓያዕቆብ ዋን ዐማራዎች በዐማራ ክልል መንግሥትን የሚቃወም ድብልቅልቅ ያለ ሰልፍ ካልተወጣ ብለው ፎገሉ። እነ አኪላ ተናገሩ ማለት ብአዴን ተናገረ ማለት ነውና ይህቺን ቃል የት ቤት ተደግማ ልስማት ይሆን ብዬ ስጠብቅ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ከነ ሚስቱ ቴስላ ነጂው አዝማሪ አበበ በለው ተቀብሎ ሲያጯጩሃት ሰማሁ። መናበባቸው አልገረመኝም። ግን አሳቀኝ። ብዙዎች ሁለት ሆነው በድሮን በሚመቱበት በዚህ ዘመን የእነ አኪላና አበበ በለው ጭራሽ ሰልፍ መጥራት የትግሬ ዲቃሎች እንዴት አድርገው ዐማራውን ቢንቁት ነው ብዬ መገረሜ ግን አልቀረም። እሱም ከሸፈ።

"…ከዚያ ለትናንት የትግሬ ዲቃላው የኦሮሞ ገረዱ ብአዴን በአጣዳፊ ሁናቴ አስገዳጅ ሰልፍ በተመረጡ ከተሞች ጠራ። ሰልፉ የተጠራበት ዋነኛ ምክንያት ብልፅግና በዐማራ ክልል ያለውን ቅቡልነት፣ የሕዝብ ተቀባይነት ለማሳየት ቢመስልም ነገሩ ግን ሌላ ነው። ምስጢሩም ወዲህ ነው። በተለይ የጎንደሩ ዐማራ የበላይ ጠባቂዎች እነ አርበኛ ጋሽ መሳፍንት በይፋ እስክንድርን መቃወም፣ ከዚያም አልፎ ተርፎ የአርበኛ ሀብቴ ወልዴ በይፋ ከእስክንድር ድርጅት መውጣት። የአርበኛ ዘመነ ካሤ፣ የእነ አርበኛ ባዬ ቀናው፣ የእነ ምሬና የእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ለጎንደሮች ድጋፍ መስጠት ሾተላዩን ሁሉ አሯሯጠው። በእነ ፓስተር ምስጋናው የሚመራው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬው ዲቃሎች የጎንደር ስኳድ ተረበሸ። እነ አኪላ ተራወጡ። እነ አበበ እስክስ፣ እነ ሀብታሙ አፍራሳ አበዱ። ኤርሚያስ ዋቅጅራ ሳይቀር በጋሽ መሳፍንት ላይ ከሀዲ ብሎ እንዲጮህ ተገደደ፣ እነ ሳሚ ቀኜ ቲዩብ ፎገሉ። ከኡጋንዳ እስከ አማሪካ ልቅሶና ዋይታው በረታ። በብልጽግናም፣ በኦህዴድ ኦነግም ቤት ሽብር፣ ሁከት ሆነ። እኔ ደግሞ እሰይ ስለቴ ሰመረን እየዘመርኩ በእልልታ ቀለጥኩ። አበድኩ፣ ሀሴትና ደስታም እንደ ዓባይ ወንዝ ፈሰሰብኝ።

"…ሰልፉ የተጠራው ከዚህ በኋላ ነው። የእነ ሽመልስ ሸኔም ከጫካ ተጠራ፣ የጎንደር አንድ መሆን በሬክተር እስኬል ሲለካ 12 ነጥብ ምናም ስኬል ያስቆጠረ ንዝረት ነው በኢትዮጵያ ምድር አልፎ ኡጋንዳና አማሪካ ድረስ የተሰማ መሬት መንቀጥቀጥ የተፈጠረው። ይሄን ለማወቅ እንደ እኔ ያሉ በሥራው ላይ ያለን ንቁ የዘርፉ ባለሙያዎችን እንጂ በሚዲያ ላይ ውርውር የሚሉትን እንደ ሞጣ ንቅሴ፣ እንደ ብሪጅ እስቶን፣ እንደማኛው ወዘተ ያሉት ሊገባቸው አይችልም። ውዳሴ ከንቱ አይሁንብኝና ለእነሱ ይከብዳቸዋል። የሴት ጭን እንደመተንተን ቀላል አይደለም የኢትዮጵያ ቦለጢቃ። ረቂቅ ነው። ምስጢር ነው። ያን ምስጢር ከሚያውቁ ጥቂት ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱና ምንአልባትም ዋነኛው ሰው እኔ ነኝ ስል እየጎረርኩ እንዳይመስላችሁ ትልና ጓ ሄጵ ትልባቸዋለህ አባቴ።

"…የጎንደር አንድ መሆን በአንደዜ ወልቃይት የመሸገውን የወልቃይት ስሁላዊ የትግሬ ዲቃሎችን አንቀጠቀጠ፣ አሸበረ። ስብስቡ ደነገጠ። ገረጣም። የእውር ድንብሩን የወልቃይት የትግሬ ሚሊሻ ልኮ ከጎንደር ዐማራ ፋኖ ጋር ሰይፍ አማዘዘ፣ ነፍጥም አስነሣ። አታኮሰ። ብአዴን የላካቸውና በጎንደር ፋኖ ዕዝ፣ በእስክንድር ስር የነበሩት በሙሉ እጃቸውን ለብአዴን ሰጡ። ጃልሰኚንም ሆኑ። የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ፀረ ጎንደር ዐማራው ቅማንት ተብዬው የጎንደር ዐማራን ሲያግት፣ ሲሰልብ፣ ሲገድል፣ ሲዘርፍ፣ እንዲሰደድም ሲያደርግ የከረመው የቅማንት ታጣቂ ተብዬው ጋንግስተር አርበኛ ሀብቴና አርበኛ ባዬ መጣመራቸውን ሲያይ ሹልክ፣ ግትልትል ብሎ ወደ ብአዴን ብልፅግና ከነመሳሪያው ገባ። ተገላገልን። ገላገሉን። ይሄ ሁላ የጎንደር አንድነት ያመጣው ጣጣ ነው።

"…ከዚያ ነው የትናንትናዋ ሰልፍ በድንገቴ መሳይ ግርግር ከች ያለችው። አመጣጣም ከላይ እንዳልኩት ብልፅግና አልሞትኩም አለሁ ለማለት ፈልጎ ብቻ ሳይሆን የግርማ የሺጥላን ቤተሰቦች፣ እነ መከታው ማሞን የሸዋ ጠቅላይ ዕዝ ተብዬ ዘራፊ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ ወንበዴ፣ ቀማኛ ቡድን እና የቡዱኑን ነፍስ አባት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አቅማቸውን ለመገንባት፣ ስማቸውን ለማደስ፣ እና አልሞቱም አሉ ለማሰኘት ነበር የተቀመረው። ሰልፉ ለዚያ ነበር የተዘጋጀው። ለዚያ ነበር ከጠዋት ጀምሮ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬው ዲቃላ የጎንደር ስኳድ ቡድን "ፐፐፐ ፖለቲካንስ መከታው ይሥራት? የሸዋ ፋኖ ነፃ ባወጣው ቀጠና ሕዝቡ መንግሥትን ሲቃወም ዋለ፣ ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ አንደኛ፣ ተማሪዎች አገዛዙን ተቃወሙ፣ ወዘተ እያሉ ሲያቅራሩ ዋሉ። እኔም ቀኑን ሙሉ እንዲበጠረቁ ሳደርጋቸው ውዬ ምሽት ላይ ውኃ ደፋሁባቸው። ቀዝቃዛ በረዶ ውኃ ቸልሼባቸው ፋራ፣ እርጥብ ሰገጤውን ስኳድ እስክስ አበበ በለውን ሳንዘባዝበው አመሸሁ። እኔኮ አዛኜን ሲያመኝ እኮ ጤና የለኝም።

"…ጎጃም ሞጣ ላይ ብልጽግና ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ የጎጃም ዐማሮች በድፍረት ተቃውሞ፣ የተቃውሞ ድምጽም አሰምተዋል። ነገር ግን አንዳቸውም የኡጋንዳ ስኳድ ሚዲያዎችም ሆኑ የአሜሪካው ስኳድ ሚዲያዎች አልዘገቡትም። አንዳቸውም አልኳችሁ። ሸዋ ጠቅላይ ዕዝ መከራው ማሞ፣ መከራው ማሞ ሲባልልኝ አመሸላችሃ። ወዲያው ደግሞ ጋዜጠኛ ሆኖ ስንቱን ኢንተርቪው ሲያደርግ የከረመው አፍርስ እስክንድር ነጋ እንደተለመደው በሀብታሙ አያሌው አፍራሳ ሚዲያ ከች ብሎ ይዘበዝብ ጀመረላችሃ። እንደ አቢይ አሕመድ በፎቶ ቦለጢቃ አንጀት ሲበላ በሚለው ፍልስፍና እኔን ጨምሮ ፒፕሉን ሲያደነዝዝ የኖረው እስክንድር ነጋ። እንደ አቢይ አሕመድ የማይጠይቁትን ጋዜጠኞች መርጦ በራሱ አሻንጉሊቶች ፊት ሲያቀረሽ እንደሚውለው የጋዜጠኝነት ትምሮ ሳይኖራቸው በገገሜክስ ጋዜጠኛ ነነ ብለው በተደነሠሩት በእቶ ሀብትሽ 360 ቀርቦ "የዜሮ ቦለጢቃ ድምር" በማለት ሲዘበዝበን አመሸ። ጭራሽ አስታራቂ ሁላ ሆኖ ነው ከች ያለው።

“…ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ራሱ ጠያቂ፣ ራሱ አስተካካይ በሆነበት የትናንት ምሽቱ "የዜሮ ድምር ፖለቲካ” ዝብዘባው ሳይሳካለት ወረደ። የትላንቱን የእስክንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ አበበ በለው አስቀድሞ እሱ እንደሚሠራው ዐውጆ የነበረ ቢሆንም እነ አምሳሉ ደውለው በመጀመሪያ ለሀብታሙ ስጥና ከዚያ ፍርፋሪውን ለአበበ ትሰጣለህ። አቤ ፋራ ነው ያስፎግረናል በማለት እስክንድር ለአቤ እስክስ ሊሰጥ የነበረውን ቃለ መጠይቅ ሽሮ ለአፍራሳ ልጅ ቅድሚያ ሰጠ። አበበ ማታ በሽቆ ነው የቀረበው። ከዚያው ከሳታላይቱ ላይ ከወረደ የበለጠ ራሱን ሊያጠፋ…👇① ✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው። ዮሐ 8፥ 43

“…ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1ኛ ቆሮ 5፥13 “…እነሆ። ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ አድርጌሃለሁ አለኝ።” ኤር 1፥10

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ገዳይ ደጀኔ መቁሰሉ ተሰምቷል።

"…በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ድርጅት የሚመራው፣ እነ ኮሎኔል ታደሰ፣ እነ ኮሎኔል ፈንታሁን መሁባው፣ እነ ማስረሻ ሰጤ በሚመሩት በአዲሱ የዐማራ ድርጅት ውስጥ ያለውና በእነ ሻለቃ መከታው ማሞ እና በእነ አቤ ጢሞ የሚመራው የሸዋ ፋኖ ጠቅላይ ዕዝ የመኮይ ፋኖ መሪ የሆነው ፋኖ ደጀኔ ከተማ የተባለ ጨካኝ አረመኔ ነፍሰ ገዳይ በግፍ የገደላቸውን እኚህን ምስኪን አዛውንት አስታወሳችሁ አይደል…?

"…ገዳዩን እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ መከታው ማሞ፣ ለፍርድ ባያቀርቡትም፣ ሚስቱን ወጥ ቀቃይ፣ እሱን ጀግና አድርገው ተንከባክበው ቢይዙትም ሰሞኑን ግን ይህ ነፍሰ ገዳይ በውጊያ ላይ ተመትቶ ቆስሎ ከግለሰብ ቤት መተኛቱን መረጃው ደርሶኛል።

"…በሸዋ ዐማሮችን የሚጨፈጭፍ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ስኳድ በጣም የትየለሌ ነው። እነ ፓስተር ምስጋናው፣ እነ አበበ በለው እስክንድርን ተከትለው ሸዋ ገብተው የሸዋን ሕዝብ ለምን እንደሚጨፈጭፉት የሸዋ ሕዝብ እስከአሁን አልተገለጠለትም።

• የእነ መከታው ማሞ ቡድን ነፍሰ ገዳይ ጨካኝ አረመኔ ነው። ዘመን ሲመጣ ለፍርድ የሚቀርብ ከኦሮሙማው የከፋ ጨካኝ ቡድን ነው።

• የአባታችንን ነፍስ ይማርልን 🙏🙏🙏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጨነቀለ’ት…

"…አዛኜን እንደኔ ምሽታችሁን በሳቅ አጠናቅቁ …😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😁😁😁😁😁😁😁😀😃😃😀😀😄😀😀😃😀😀😄😀😃😀😀😄😄😀😃😃😂😂😂😂😂😂😂😂

• ማርያምን ደንግጠዋል አይገልጸውም። የሚያነበው ሁላ እኮ ነው ጠፋው። ተነፈሰ፣ ተንተባተበ፣ ድንግርግር፣ ድንግዝግዝ ነው ያሉት።

• አዛኜን ዐማራ በዝረራ አሸንፏል። አከተመ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጎንደሩ ይለያል…😂

• ዘገባው የናቲ አንደግምም ወይ ነው።

"…እንኳንም አያሌው መንበር፣ ፓስተር ምስጋናው፣ ሰሎሞን አጠናው አላዩት። የጎንደሩ ልዩ ነው። አዳነች አበቤን ሳይቀር ነው ባነር አሠርተው የወጡት። አገኘሁ ተሻገር ግን ምን በድሏቸው ነው የዘነጉት?

"…የጎንደር ዐማራ ጫካ ነው። እየተዋጋም ነው። በጎንደር የደላው ስኳድ ነው። ቢሮክራሲው በሙሉ በፀረ ጎንደር ዐማራ የተሞላ ነው። የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ጎንደርን እንዲህ ሸብረቅ ሲያደረጋት አርፍዷል። ሰልፍ የተጠሩት 257 ሰዎችም የካድሬው ቤተሰቦች ናቸው ተብሏል።

• ዘገባው የናቲ አንደግምም ወይ? ነው።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሁመራው ሰልፍ ነው።

"…የሕዝቡን ብዛት፣ የመፈክሮቹንም ብዛት፣ የሰልፉን ርዝመት፣ የሰልፈኛውን ቁጣ ሳይ በቃ ፋኖ አለቀለት ብዬ በጣም፣ መጣም ደንግጬ ሰግቼ ሁላ ነበር።

"…ለማስታወስ ያህል ሁመራ የሚመራው በፖለቲካው ቅማንት በትግሬ ዲቃላው ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎንደሬው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነው። ደመቀ ዐማራን ከወልቃይት የሚያጸዳ ስሁላዊ ማሽን ነው። ደመቀ ብልፅግና የብልፅግና ወንጌል ገረድ ነው። ደመቀ በዐማራ ደም ሕይወቱ ተርፎ ዐማራን ከብልፅግና ጋር አብሮ የሚወጋ ባንዳ ነው ልል ብዬ አሰብኩና እነ ወዳጄ አያሌው መንበር፣ እነ ፓስተር ምስጋናው ይከፋቸዋል፣ አበበ በለው ያለቅስብኛል ብዬ ተውኩት።😂

"…በሁመራው ሰልፍ ላይ በዐማራ ክልል መውጣት፣ መውለብለቡ ቀርቶ የነበረው ባለ አንባሻው የትግሬ ነፃ አውጪው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ እና ወያኔ ሰፍታ ለብአዴን የሰጠችው የሽንት ጨርቅም አብሮ ከተቀበረበት ወጥቶ ተውለብልቧል።

"…ወያኔው ደመቀ ዘውዱ በወልቃይት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይውለበለብ፣ በስብሰባ አዳራሽም ውስጥ ሆነ በአደባባይ የአባቱ የወያኔ ባንዲራ እንጂ ሌላ ዝር እንዳይል ያስደረገ ሰው ነው።

• ሰልፉ ግን እጅግ ድንቅ ነበር። እንደ ትግሬዎቹ መስመር ገብተው በረድፍ፣ በመስመር መሰለፋቸው፣ በትግርኛ ሁላ ነበር አሉ መፈክሩ። አጆሃ ብልፄ። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ …የዐማራ አደንዛዥ ዘረመኔዎች ከዱት። ዝም ጭጭ አሉት። 

"…በስተመጨረሻ ለትእግስትም ገደብ አለው ብሎ ዐማራው ወሰነ። ወሰነና በጨዋ ደንብ ለፈፈ። ከነገ ጀምሮ ሰልፍ ሳይሆን ሰይፍ ነው የምናነሳው ብሎ ወሰነ። የጁንታው ጦርነት ለመሳሪያ መታጠቅ፣ የልዩ ኃይሉ መበተን በሰው ኃይል ለመሞላት ጠቀመው። እነ ብርሃኑ ነጋ እንዳይማር የፈረዱበት፣ እነ አቢይ አሕመድ እንዳይሠራ የፈረዱበት። እነ ዳንኤል ክብረት በስድብ መዓት ሊያሸማቅቁት የሞከሩት ዐማራው ዳዊት ቁርአኑንና ነፍጡን አነሣ። አንሥቶም ወደ ጫካ ተመመ። ተመመ በቃ። አንደዜ የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም። አንዴዜ ከልብ የወጣም አይመለስም። አንደዜ ሞቶ የተቀበረ ከትንሣኤ ዘጉባኤ ወዲህ አይነሣም፣ አይመለስም። ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ መመለሻም የለው። ነገሩ እንደዚያ ሆነ። አበቃ።

"…የዳዊቱ የጸሎት ውጤት ሱዳንን አፈራረሰለት። ገበሬውን ማዳበሪያ ከልክለው ለፋኖ አጋዥ አደረጉለት። እግዚአብሔር በኤርትራና በኦሮሙማው መሃል ሽብልቅ ከተተላቸው፣ ከሶማሊያ ጋር እሳትና ጭድ አደረገላቸው። ዐማራው ጊዜ አገኘ። ለመሰልጠን፣ ለመመካከር አመቺ ሁናቴ ተፈጠረለት። የብልፅግናው ወንጌል የሱስ ግራ ተጋባ። የዐማራው ኢየሱስ ደም አፍሳሹን የሱስ ሊበቀለው በዐማራ ፋኖ በኩል ተገለጠ። እውነተኛው ኢየሱስ ሐሳይ መሳዩን መጋፈጥ ጀመረ። በአንድ ሳምንት ሱሪውንም ቀበቶውንም እናስወልቀዋለን ብለው የዘመቱበት ዐማራ የራሳቸውን ፓንትና ካልሲ አስወልቆ በሳማ ለበለባቸው። የሆነው ይሄ ነው።

"…አሁን ሁሉም ነገር አልቋል። ሞተ በቃ። ሴፍቲ ኔት ተረጂዎችን፣ ከቤተ ክርስቲያን ተመላሽ ምስኪኖችን በግድ ሰብስበህ 50 የማይሞላ ሰው ይዘህ፣ አስገድደህ በተራህ ሰልፍ ብትወጣ ማን ሊሰማህ? ሰልፍማ ድሮ ቀረ። ሽንታም የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላና አገው ሸንጎ በጎጃምና በጎንደር፣ በወሎ የወሃቢይ እስላም የኦሮሙማው ገረድ ከወጣው በቀር ዐማራው፣ አገው ቅማንቱ ንቅንቅ አላለም። ዛሬ በሰልፉ ላይ የታዩት ጥቂት የቀበሌ ሠራተኞች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው። በግዳጅ፣ ፎርም ሞልተው፣ ቀሪ ተመዝግቦ ነው የወጡት። የወጡትም ተሸፋፍነው፣ ማስክ አጥልቀው። አድርገው ነው የወጡት።

"…እንደ ሸዋ ያለው ደግሞ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ቆሞ አቢይ አሕመድ ላይ ሰልፍ ወጥቶ አረፈው። ነገሩን ገለበጠው። ዛሬማ ዐማራነት ኩራት፣ የወንድነት፣ የአልሸነፍ፣ የአልበገር ባይነት ምልክት ሆኗል። ዛሬማ በቲክቶክ በለው በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ ዐማራ ነኝ ባዩ እንደ አሸን ፈልቷል። በዳኜ ዋለ ዘፈን የማይፎክር፣ የማያቅራራም የለም። ዛሬማ የዐማራ የውጭ አይደለም የውስጥ ጠላቶቹን በወረንጦ እየለቀመ መመንገል ጀምሯል። ዛሬማ የዐማራው ሰፌድ፣ የዐማራው ወንፊት ምርቱን ከግርዱ መለየት ጀምሯል። አበበ በለው እስክስ፣ ሀብታሙ አፍራሳ፣ ኤርሚያስ ዋቅጂራ የማያሾረው የማይነዳው ሆኗል። ዛሬማ አይደለም ከውጭ ከውስጥ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱን ጭምብል ገፍፏል። ግንቦት ሰባትን ዘርሯል። የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹን የጎንደር ስኳዶች እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለምን ሳይቀር በመንሹ አበራይቷል። ወጊድ፣ ክላልኝ ብሏል። ዛሬማ ዐማራው ቀና ብሏል። እስከ አፍንጫውም ታጥቋል። የደሴ የወሃቢይ እስላም ጩኸት ዐማራውን ከድል አያስቆመውም። በቅርቡ ተአምር እናያለን። ይሄን ስናገር የሚሰማኝን የደስታ ሲቃ መደበቅ አልተቻለኝም። ያላሳፈርከኝ ዐማራ። ክበርልኝ። 🙏🙏🙏

"…ዛሬ ታህሳስ 09 ቀን 2017 ዓ.ም በአርበኛ ዘመነ ካሴ ተጽፎ በተላለፈ መልእክት ርእሰ አንቀጹን እንቋጫለን። "…ሥርዓቱን ያሸነፍን መሆኑን ከብልግናው ቡድን በኩል ጥፍር ታክል ልቡ የሚጠራጠር ባተሌ ካድሬ ቢኖር የዛሬው ውሎ በሕዝብ የተመታ ታሪካዊ ማኅተም ሆኖ ይወሰድ። በአብዮቱም በኩል ካሸነፍን የሰነበትን መሆኑን ማመን ያልቻለ አንድ እንኳን ፋኖ ቢኖር የዛሬውን ቀን ድሉን ከሕዝብ ጋር ከፍ አድርጎ ያበሰረበት ዕለት አድርጎ ይጻፈው።

"…ሥርዓቱ ተሸንፏል። ለበሰበሰው ቡድኑ ሽታ አፍንጫችን ስንሸፍን ዓይናችንም በጋቢያችን ሸፍነነው ካልሆነ በስተቀር ሥርዓቱ ተሸንፏል። በትውልዱ የድል ዋንጫና በኛ መካከል የቀረውን ስንዝር እርቀት ለመጓዝ ግን ጉልበታችን ቄጤማ ሁኗል። ከራያ እስከ ጉበያ፣ ከመተማ እስከ ወንበርማ፣ ከምንጃር እስከ አቸፈር ያካለለ ብርቱ እግራችን ስንዝር ለመራመድ ስለምን አቃተው ካልን መልሱ ትግሉ በአንድ መዋቅር ማሰር ስላልቻልን ነው ይሆናል። የቀረን ነገር ቢኖር ሰኞ በአንድ ቁመን ማክሰኞ ዕለት የድሉን ዋንጫ ማንሣት ብቻ ነው። እዚህ ላይ እንበርታ ።

• ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም
• አዲስ ትውልድ !
• አዲስ አስተሳሰብ !
• አዲስ ተስፋ !
• አንድ ዐማራ !

"…የተጻፈውም ጽሕፈት፡— ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላል። የነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቈጠረው ፈጸመውም ማለት ነው። ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው። ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። ዳን 5፥ 26-28

• አዲዮስ ማኔ ቴቄል ፋሬስ…✊

• ድል ለዐማራ ፋኖ…✊
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…✊

••• ከ30 ደቂቃ በኋላ እመለሳለሁ። ሰንዱቁንም እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ።

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 9/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…የዕለቱን ርእሰ አንቀጽ ጽፌው ልለጥፍ ነኝ… የዕለቱ ርእሰ አንቀጽ ቀኑን ሙሉ ሆኖ ነገር ግን አጫጭር እንዲሆን እኔና ድርጅቱ ዘመዴ ወስነናል።

• ልለጥፍ ነኝ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel