zenatoday | Unsorted

Telegram-канал zenatoday - ዜና Today News

142

If you want up-to-date, fast, reliable domestic and international news, subscribe it. It is our struggle to make it a time when we hear the news of peace..። ወቅታዊ ፣ፈጣን ፣አስተማማኝ የሃገር ዉስጥ እና የዉጭ ሃገር ዜናዎችን ከፈለጉ ሱብስክራይበ ያድርጉ። https://www.youtube.com/channel/UCy

Subscribe to a channel

ዜና Today News

ገለልተኛ እንዲኾኑ የሚጠበቁ ተቋማትን ለአፈና መጠቀም የአምባገነናዊነት ማሳያ ነው!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ  ከመኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ እናት ፓርቲና ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ)

አገራችን ኢትዮጵያ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች የማይከበሩባት፣ ፍትሕ ርትዕ እና መልካም አስተዳደር የተጓደሉባት መኾኗ የአደባባይ ሀቅ ነው። ብዙ ጫናዎችን ተጋፍጠው ለሕዝብ ድምፅ በመኾን የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና አመራሮችን ማስፈራራት፣ ማፈን፣ መሰወር፣ ማሰርና አለፍ ሲልም መግደል የተለመዱ ሥርዓታዊ ባህል ከኾኑ ውለው አድረዋል። በዘመነ ብልጽግናም ይኼው ክፉ አባዜ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በቅርቡ ሾልኮ እንደወጣ በተገለጸ መረጃ መሠረት ምርጫ እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ ብልጽግና መራሹ መንግሥት ከተለያዩ ገለልተኛ ኾነው ከሕዝብ ጋር ብቻ መወገን ከሚገባቸው ተቋማት የተውጣጣ ቡድን መቋቋሙንና የዚኽ ቡድን ዋና ዓላማም ብልጽግናን ይገዳደራሉ ተብለው የሚታሰቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማፍረስ፣ አባላትና አመራሮችን ማፈን ብሎም እስከ መግደል የሚደርስ እርምጃ መውሰድ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ነገሩ ከመረጃ የዘለለ አይኾንም ተብሎ በታሰበ ማግስት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባው  ከነጉድለቶቹ ከሚንገዳገደው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 9 (የሕገ መንግሥት የበላይነት)፣ 14 (የሕይወት፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት)፣ 18 (ኢሰብዓዊ አያያዝ ስለመከልከሉ)፣ 25 (የእኩልነት መብት) ጋር ፍጹም የሚቃረን ከዚያም አለፍ ሲል አፈናንና ማሰቃየትን “ሕጋዊ” ሽፋን ለመስጠት ያለመ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ አጽድቋል፡፡ አዋጁ ምርመራ ወይም በቁጥጥር ሥር የሚደረግ ማስተላለፍን እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው ከነፍስ ግድያ ወንጀል በስተቀር በምርመራ ሂደት ውስጥ ለሚፈጽመው ማንኛውም የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ እንደማይኾን በግልጽ ይደነግጋል።

በሌላ በኩል ግንቦት 2017 ዓ.ም ከብልጽግና ዋና ጽ/ቤት ሾልኮ እንደወጣ የተነገረለትና “የጠላት አዲሱ የትግል ስልትና የመመከቻ አቅጣጫዎች” በሚል መነሻ “በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና አባላት ከወቅታዊ ጉዳይ አንፃር ለሚሰሩት ሥራ እንዲያግዝ የተዘጋጀ” የሚል ሰነድ እንዲኹ በመረጃ መልክ ደርሶን ተመልከተነዋል፡፡ በሰነዱ ገጽ 7 ላይ በዋናነት አራቱን በትብብር የምንሠራ ፓርቲዎች በስም ጠቅሶ “አፍራሽ” በሚል ይከስና “በጠላትነት” ፈርጆ ይታያል። 

አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ የኾኑት ከሥርዓቱ እግር ስር ቀለብ የሚሰፈርላቸው አክቲቪስቶችና እነ ሆዳቸው አምላካቸውም በድንግዝግዙ መሐል የሕዘብን ድምጽ የሚያሰሙ ፓርቲዎችንና አመራሮችን በስም ጭምር እየጠቀሱ “እንዴት ዝም ይባላሉ” ይሉ ነጠላ ዜማን ማንጎራጎር ጀመረዋል፡፡ በቀደሙት ሃያ ሰባት ዓመታት ለአፈና ያሰቡትን ግለሰብ በመንግሥት በሚታተሙ ጋዜጣዎችና በቴሌቪዢን ዘጋቢ ፊልም (ዶኩመንተሪ) ቀድመው ይሠሩበት የነበረው ስልት ግልባጭ ማለት ነው፡፡  

በአጠቃላይ እንደሥርዓት ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ማኅበራዊ አንቂዎችንና ሌሎችንም ዜጎች እያፈሱ በማሠር፣ በማሰቃየት ብሎም የተለየዩ ዘዴዎችን በማበጀት የፖለቲካ ስልጣን ማጽናት ለጊዜው ሊመስል ይችል ካልኾነ በቀር ለውድቀት የመንደርደሪያው ጅማሮ እንደኾነ ከትናንታችን መማር ተገቢ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ስለኾነም፦

1. መንግሥት ገለልተኛ እንዲሆኑ የሚጠበቁ ተቋማትን  ለስልጣን ማጽኛና ለአፈና መጠቀሙን በአስቸኳይ እንዲያቆም፤

2. በሕጋዊነት ስም ዜጎችን ለማሰቃየት የወጣው አዋጅ አፈጻጸሙ እንዲታገድ ብሎም እንዲሻር፤

3. የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ባለሀብቶች ላይ ያነጣጠሩ ፍረጃዎችና ጥቃቶች ሌላ የማንወጣው የመተላለቅ መዘዝ ከማምጣታቸው በፊት በአስቸኳይ እንዲቆሙና ከለላም እንዲሰጣቸው፤

4. የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰላማዊ ታጋዮች ጎን በመቆም ጭቆናና ኢፍትሓዊነትን አምርሮ እንዲታገል፤

5. ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመንግሥት የበዛ ጭቆና ምክንያት በአገራችን ሰላማዊ ትግል ለአንዴና ለመጨረሻ ከማክተሙና ወታደራዊ አገዛዝ ከመስፈኑ በፊት ጥረቱን እንዲያጠናክር እናሳስባለን።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

Читать полностью…

ዜና Today News

❗️የኢራን ጠቅላይ መሪ አማካሪ አሊ ሻምካኒ በህይወት እንዳሉ አረጋገጡ

እስራኤል ባሳለፍነው አርብ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ባካሄደችው ጥቃት ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሪፖርቶች ጠቁመዋል።

ባለሥልጣኑ ሆስፒታል ገብተው አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የዜና ማሠራጫው ገልጿል።

ለአያቶላ አሊ ኻሜኔይ መትረፋቸውን እና ህይወታቸውን መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ተብሏል።

Читать полностью…

ዜና Today News

🚨 እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ምርምር ማዕከል ላይ ሌሊት ጥቃት መፈፀሟን ገለፀች

🇮🇱🪖 የእስራኤል ጦር ስላደረሠው ጉዳት ያስታወቀው፦

▪️60 ተዋጊ ጄቶች በኢራን ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ቦታዎችን ኢላማ በማድረግ የሌሊት ድብደባ አካሂደዋል።
▪️የሚሳኤል ክፍሎችን ለማምረት የሚያገለግሉ ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማት ተመተዋል።
▪️ከኢራን የመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ግኑኝነት ያላቸው በርካታ ኢላማዎች ተደብድበዋል።
▪️በቴህራን የሚገኘው የመከላከያ ፈጠራና ምርምር ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮጀክት አካል ኢላማ ተደርጓል። sputnik

Читать полностью…

ዜና Today News

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ" በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር ውሳኔ ላይ እንደሚደርሱ ተናግረዋል።

ትራምፕ የሁለት ሳምንት ጊዜ የሰጡት ከኢራን ጋር ባለው " ትልቅ የመደራደር ዕድል" ምክንያት ሲሆን ይህ እርምጃ ውጥረቱን ይቀንሰዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሏል።ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ላይ ለመወሰን ሁለት ሳምንት ጊዜ ሲሰጡ ዩኬ እና የአውሮፓ ኅብረት ከኢራን ጋር ሊነጋገሩ ነው።

ኢራን በእስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 71 ሰዎች ቆስለዋል። ጥቃቱን ተከትሎ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እንዳሉት ይህ ጥቃት የሚያሳየው የኢራን ጠቅላይ መሪ "ከእንግዲህ ወዲያ እንዲኖር እንደማይፈቀድለት ነው" ብለዋል።

ኢራን በኢንተርኔት ላይ እገዳ ጥላለች፤ ይህም በአገሪቱ ታሪክ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና ዩኬ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ባደረጉት ስብሰባ ኢራን “የኒውክሌር መሣርያ እንዳይኖራት” ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አውሮፓ ኅብረት እና የኢራን ባለሥልጣናት ጋር ዛሬ ከሰኣት በጄኔቫ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል።

Читать полностью…

ዜና Today News

ሰበር መረጃ‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለከፍተኛ ረዳቶቻቸው ኢራንን የማጥቃት ዕቅዶችን ማፅደቃቸውን ዎል ስትሪት ካወጣው ዘገባ ላይ ተመልክተናል።
በሌላ ዜና ኢራን በቅርቡ ከዩኤስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ፍላጎት እንዳላት አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ለኒውዮርክ ታይምስ የገለፁ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚወያዩ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን ለማጥቃት መወሰናቸውን ተከትሎ
ኢራን የኑክሌያር ማበልፀግ ፕሮግራሟን ልታቆም እንደምትችል ዘገባው ጠቅሷል።
የኢራንን ከመሬት በታች 80 ሜትር ውስጥ የቀበረችውን በፎርዶው ግዛት የሚገኘውን የዩራኒም ማበልፀጊያ እና ማጣሪያ centrifuge በጥልቀት ሊመታ የሚችለው ቦንብ በአሜሪካ እጅ ብቻ የሚገኝ ሲሆን B-2 bunker bomb ይሰኛል። እስከ 60 ሜትር ድረስ ወደ መሬት በመግባት ጥቃት ማድረስ ይችላል።
ምስሉ ከላይ ተያይዟል።

Читать полностью…

ዜና Today News

የድል መረጃ
ምሽት 2:00 እስከ 6:00 ሰዓት

የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና የታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ወንድማማቾች ብርጌድ ጎንደር ከተማ አቅራቢያ ጉንብሪት ቀበሌ ክልል እየሱስ የተባለ ልዩ ቦታ የነበረ የጠላት ሀይል ተደመሰሰ።

ድንገተኛ አፈና ውስጥ የገባው ጠላት አብዛኛው የተደመሰሰ ሲሆን ውስኑ ተበትኖ ራሱን ለማትረፍ ወደ ጎንደር ከተማ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሸሽቷል ከፊሉም ተማርኳል።

ያገኘነው መረጃ የሸሹት ለአገዛዙ በድጋሜ አያገለግሉም ወደ መረጡት አቅጣጫ ይሰወራሉ።

ይህ ድል የተመዘገበው በጎርጎራ የጠላት ሄሊኮፍተር መንደዷን ተከትሎ በውስጥ አርበኞቻችን ድጋፍ ከተጠቀሰው ቦታ ሰፍሮ የነበረውን ጠላት ጥሩ ቅጣት መቅጣት ተችሏል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዲችን
አፋብኃ ጎንደር ቀጠና

Читать полностью…

ዜና Today News

🔥በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) በጎጃም ቀጠና ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛክ/ጦር ስናን አባጅሜ ብርጌድ መብረቁ ሻምበል(3) የአባላት የግንባታ ት/ት ተሰጠ‼️

  ግንቦት ,28/09/2017 ዓ.ም

መግቢያ:-ስናን አባጅሜ ብርጌድ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጎጃም ቀጠና ካሉት 67 ብርጌዶች ዉስጥ አንዱ ሲሆን ዛሬ ላይ  የአገዛዙን ሰራዊት ከባድ የሰባዊናየቁሳዊ ኪሳራ እንዲደርስበት ካደረጉት ዉስጥ ቀዳሚ ነዉ!!ብርጌዱ ረ/ገበያ ከተማ የመሸገዉን ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ አገዛዙንናአገልጋዮቹን ካለምንም ዘብ ባዶ ያሰቀረ ብዙ አዋጊናተዋጊ የተፈጠሩበት ስመጥር ብርጌድ ነዉ!!የአብይ አህመድ ሰራዊት የጮቄን ሰንሰላታማ ቦታ ለመያዝ ሶስት-አራቴ ባደረገዉ ሙከራ አናብስቶቹ ባደረጉት ታላቅ ተጋድሎ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የአሸናፊነት ካባ የተከናነበ ድንቅ ታምረኛ ብርጌድ!

አገዛዙ ከደ/ማርቆስ ረ/ገበያ ሬሽን ቅብብል በየወሩ  በሚያደርግበት ሰዓትም በገባ በወጣ ቁጥር ከፍተኛ የሰባዊናየቁሳዊ ኪሳራ በጀግኖች የስናን አባጅሜ ልጆች ደርሶበታል!!አገዛዙ ስናን መቋቋም አቅቶታል!!በምናደርገዉ ተጋድሎ እንኳንስ በጎጃምናበክልሉ ያሉ ታጋይናደጋፊዎቻችን፤በሌሎች አካባቢ ያሉ የትግሉን ደጋፊዎቻችንም አኩርተናል፤ተደንቀናልም!!መስዋት እኛም ሕዝባችንም እየከፈልን ነዉ ይህን ታምራዊ ስራ የሰራ ነዉ!!የምንከፍለዉ መስዋት ነገ ከነገ ወዲያ በታሪክ አምድ ዉስጥ በትልቁ ይፃፋል!!አቅም አለን አቅም መኖሩን ያየነዉ ወገን ገለን ሳይሆን ተወልድን ባደግንበት ቀዬ ዘሎ ገብቶ ሊገለን የመጣን ጥላት በመመከታችን ነዉ!!

ስናን አባጅሜ ለጠላት የቆንጥር እሾህ ነዉ!!የቆንጥር እሾህ ባለበት አካባቢ ማንም እንደፈለገ ማለፍ አይችልም ፥እኛ ስናኖች ባለንበት ቦታም ጠላት እንደፈለገ መዉጣት መግባት አይችልም!!እኔም፣እናንተም፣ሕዝባችንም ባደረግነዉናበምናደርገዉ ተጋድሎ ስማችን በአማራ ሕዝብ ትግል ዉስጥ ደምቆ  እንዲፃፍ አድርገናል!!የእኛ እናቶች ማህፀን ምንኛ የተባረከ ነዉ!!

     ✅የአማራን ሕዝብ ሕልዉና ለማስቀጠል በአፍራሽ/አማራን ጠል በሆኑ ሐይሎች የተሸረበብንን ኢ-ምክንያታዊ  ፖለቲካ ከሕዝባችን ጫካ ላይ ለማስወገድ ሁሉም አማራ በአንድነት መታገልና ሕልዉናችንን ማስቀጠል መቻል አለበት!!የአማራ ሕዝብ  የደረሰበትን ከባድ ፈተና ለመቋቋምና ጠላቶቹን ለመመከት ለትግሉ ቁርጠኛ መሆን ከምንም በላይ አስፈላጊ ነዉ!!

  ✅ፋኖ የወል ስማችን ነዉ!! ታሪካዊ ቃሉም የአማራ ሕዝብ ዉርስናቅርስ ነዉ!!ዉርስና ቅርስ የሆነዉ ድርጅታችንን መጠበቅና መንከባከብ የትዉልዱ ግዴታ ነዉ!!የእዕለት ተግባራችንም ጭምር!!ፋኖነት መርህ አለዉ!!ካለመርህ የሚንቀሳቀስ ድርጅት አይደለም፤ መርህ አልባ አድርገዉ የሚመለከቱት በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያጡት ታርጋ ሰጭዎች ተለጣፊ የአብይ አሕመድ ጋሻ ጃግሬዎች ናቸዉ!! ድርጅታችን ግብ አለዉ!!ርዕዮተ አለም አለዉ። ዓላማም አለዉ። ሕዝባችን በፍትህ፣በእኩልነትናበዲሞክራሲ ሁለንተናዉ እስኪከበር ድረስ እንታገላለን፣እናደራጃለን፣የጀመርነዉን ትግል ታግለን እናታግላለን!!በመድሎ፣በኢ-ፍትሃዊ አሰራርና በሌሎች አሉታዊ ተፅዕኖ በሕዝባችን ላይ የሚደርሰዉን የግፍ ፅዋ ለመመከትናለመቀልበስ ቅርፅ እስከሚይዝ ድረስ በፅናት እንታገላለን!!

    ✅ማንኛዉም አባል ካምፕ ተጠርንፎ ምን ምን ተግባራትን መከወን አለበት በሚሉ ጉዳዮችም ሰፋ ያለ ዉይይት አድርገናል!!

  1/የትግሉን አላማ  መረዳት (ከቤታችን ወጥተን ጫካ     የተቀመጥንበት ምክንያት ምን እንደሆነ መገንዘብ)
2/የትግሉን አሁናዊ ሁኔታ መገንዘብና ለሌሎች ማህበረሰቦች ግንዛቤ መስጠት
3/በስነምግባር የታነፀ መሆን (እርስ በእርስ መከባበር፣ መቻቻል፣ መረዳዳት፣መግባባት፣መደማመጥናታማኝ)
4/በወረደዉ መመሪያ፣ደንብና ሕግ መገዛትና ማክበር
5/የሕዝባችን መብት ማክበርና ማስከበር፤እሴቶቻችንን ማስቀጠል
6/የድርጅታችንን ሐብት ንብረት መጠበቅናመንከባከብ
7/ከአሉባልታናበሬ ወለድ ወሬ ራስን መቆጠብ
8/ሚስጥር ጠባቂ መሆንናፅናት መኖር
9/ንፅህናችንን መጠበቅ
10/ከመጥፎ ነገር ራስን ማራቅ(ስርቆት፣ስካር፣ስድብ፣ጥይት ተኩስናሌሎች መጥፎ ተግባር ማስወገድ)....በሚል ሰፋ ያለ ዉይይት በማድረግ የነበርንን ዉይይት በሰላም አጠናቀናል።


##ክብር በጀግንነት ለተሰዉት ሰማዕታት !!
##ድል ለአማራ ፋኖ!!
##ድል ለአማራ ሕዝብ!!


የስናን አባጅሜ ብርጌድ የሕ/ግንኙነት ኃላፊ

[አዲስ አትዉልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ]

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

28/09/2017 ዓ.ም

Читать полностью…

ዜና Today News

በራያ ቆቦ ግንባር አንድ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮሎኔል ሲቆቅል በርካታ ወታደሮች ደግሞ መገደላቸው ተሰማ!

በአፋብኃ የቤተ-አማራ ቀጠና ልዩ ዘመቻ አሃድ ኮማንዶዎቹ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ አንድ ኮሎኔል በማቁሰል እና በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል ሲል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አበበ ፈንታው አስታወቀ።

ምሽግ ለቆ መሃል የገባውን የጠላት ሃይል እንደተለመደው ስንቅና ንብረት እንዳይደርሰው እንዲሁም ተጨማሪ ሃይል እንዳያገኝ ብሎም ወንዝ በመሄድ ውሃ እንዳይቀዳ ጭምር በማድረግ መፈናፈኛ በማሳጣት ከቦ የመምታቱ ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

የቤተ-አማራዎቹ የልዩ ዘመቻ አናብስቶች ዛሬ ግንቦት 26/2017 ዓ.ም ንጋት 1:00 ጀምሮ እስከ ቀን 8:00 በዋለ ከባድ ተጋድሎ ከቆቦ ከተማ ተነስቶ በርካታ እግረኛ ሃይል እና በብረት ለበስና ዙ23 ታጅቦ በሶስት አቅጣጫ ስንቅና ንብረት ሲያጓጉዝ የነበረን የጠላት ሃይል በግድብ በመቀረጫው እና በጠበለት አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ኮሎኔል በማቁሰልና በርካታ ሃይሉን በመረምረም ሙትና ቁስለኛውን እንዲታቀፍ አድርገውታል::

በዚህ ተጋድሎ በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ የተመታበት የጠላት ሃይል ከቆቦ ከተማ አቅራቢያ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተጠመደ መድፍ ከ20 በላይ ቅምቡላ ንፁሃንን ኢላማ አድርጎ በማስወንጨፍ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አድርሷል::

Читать полностью…

ዜና Today News

🔥#ኮማንደር_አሕመድ_ሰይድና ጓዶቹ #ተደመሰሱ‼️

የአድማ ብተና ሻለቃ መሪው #ኮማንደር_አሕመድ_ሰይድ እና የ303ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች ከምሽት 1:00-4:00 በተደረገ ውጊያ ተደምሥሠዋል❗️

የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ የዋለው የአቢይ ዙፋን ጠባቂ ጥምር ጦር ምሽት 1:00-ምሽት 4:00 ድረሥ ከውባንተ ልጆች ጋር ገጥሞ አምሽቷል። የውባንተ ልጆችን ክንድ መቋቋም ያቃተው መከላከያና አድማ ብተና አለኝ ያለውን ሞርተር በግምት ሢያዘንበው አምሽቷል።

የአፋብኃ በጎንደር ቀጠና የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የአቢይን 303ኛ ኮር ሞራለ ቢሥ ወታደሮች እና አማራ በታኞችን በነፍጣቸው አናፍጠዋቸዋል። ኮማንደር አሕመድ ሰይድ እንደተመታ ከወታደር ሥነምግባር በማይጠበቅ መልኩ የአቢይ ወታደሮች ሥም እየጠሩ ሢያለቅሱ አምሽተዋል። መሪዎቻቸውንም ቴሌ ላይ ቀብረዋቸዋል። አገዛዙ አንድም ቁሥለኛ ይዞ መውጣት አልቻለም። ምክንያቱም 340° ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ንሥር ዕይታን በደምብ ተላብሧልና።

ወገን የሚኮራባቸው ጠላት የሚፈራቸው ዕንቁ ታጋዮች አሉ። የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ልጆች። ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በወታደራዊ ሥነምግባር በእጅጉ የተገነቡና ጥንቅቅ ያሉ የነጻነት ተፋላሚ ናቸው።

ድላችን በነፍጣችን❗️
ዝንተዓለም አምሐራ Forever Amhara
፩ኛ ኮር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/4dhDXbYdBOU

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/FPW8789YD0o

Читать полностью…

ዜና Today News

ኢትዮጵያ After WAR❗️❗️❗️❗️❗️❗️

ከአንደኛው እና ሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ያስከተለው ውጤት ከፍተኛ ከሆነ ሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በተጨማሪ በጦርንቱ የተሸነፉ ሃገራት በቅኝ ግዛት የያዟቸው ሃገራትና የራሳቸውን ግዛት ጭምር በመበታተን በርካታ ትንንሽ ሃገራት ተፈጥረዋል።ጦርነቱን እየዘገየች የምትቀላቀለው አሜሪካ ሃያል ሃገር ሁና እንድትቀጥልና የሚላላኳትን በርካታ ትንንሽ ሃገራትን ፈጥራለች።

ኢትዮጵያ ከፊታችን ሃይለኛ ጦርነት ከፊቷ ይጠብቃታል ።ከጦርነቱ በኋላ ምን ይፈጠራል የሚለው ለመገመት ይከብዳል።

"ትልቁ አሸናፊነት ጦርነትን ማስቀርት ነው"በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የጃፓኑ የባህር ሃይል አዛዥ የነበረው ማምያቶ


በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ ጦርነቱን ሳትቀላቀል በፊት ጃፓን የቻይናን በርካታ ግዛቶች እነ ማንቹሪያን ጨምሮ ደቡብ ምስራቅ ቻይናን በጥቅላላ በወርራ ይዛ ነበር።በዚህ ወቅት በጃፓን ዙሪያ ያሉ ድሴቶችን የጦር ሃይል ያሰፈርችው አሜሪ ምክንያት ጃፓን ቻይናን በተለያየ አቅጣጫ ለመውረር አልመቻት አለ።ይህኔ ነበር ያጃፓን መንግስት በደሴቶቹ ዙሪያ ያሉ ደሴቶችን ለመያዝ በአሜሪካ ላይ ጦርነት እናውጅ አለ።

ማምያቶ ግን ጦርነትን ከጅምሩ አስፈላጊ አይደለም ፣ጭራሽ እንደ አሜሪካ ያሉ ሃገራትን መንካታ ዋጋ ያስከፍላል ይቅር ሲል ሞገተ።የጃፓን መንግስት ግን አሻፈረኝ አለ ።ጦርነቱ የማይቀር ከሆነ በአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ይከፈት አለ ማምያቶ።

እንዳለውም በድንገት የጃፓን አውሮፕላኖች በአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ የቦምብ ናዳ አወርዱ ፣ሙሉ በሙሉ አመድ ሆነ ፣ከ3000 በላይ የአሜርካ የባህር ሃይል ሰራተኞች ተገደሉ፣ሙሉ መርከቦች ጋዮ።አሜሪካ በጃፓን ላይ ጦርነት አወጀች፣መጨረሻው አላማርም ፣በጃፓን ከተሞች ሄሮሽማን እና ናጋሳኪ ላይ የአቶሚቦምብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ አውላ ከ100ሺ በላይ ጃፓናዊያን አለቁ።የጃፓን መንግስት እጅ ሰጠ።ማምያቶም በአውሮፕላን ጦሩን ሊያበርታታ በሚሄድበት ጊዜ የአሜሪካ ጀቶች ከበው አውሮፕላኑን መተው ገደሉት።

ጦርነትን ማስቅርት ትልቁ አሸናፊነት ነው ።አሁንም የአማራን ጥቅም እንዲሁም የሌሎችን ብሄርች ጥቅም የሚያስከበር ስምምነት ያለጦርነት የሚፈታ ከሆነ ከአሁንም ንግግር ይጀምረ እንላለንን ፣በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ሁሉም ተፋላሚወች አንዱ አንዱን ለማሸነፍ እንጅ እንነጋገር የሚለውን አስበውት አያውቁም፣አሜሪካ ብቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጥሪ ታደርግ ነበር።በመጨርሽ ነው የጦርነቱ ጥቅም ምንድነው ብለው ያሰቡት.በርካቶቹ አሸናፊወች ሳይቀር በጦርነቱ ደስታ አላገኙም ።ምንም ጥቅም የሌለው ብለውታል።ነገር ግን ጨፍጫፊና ገዳይ war mongering ጠቅላይ ሚኒስተር ይዘህ ጦርነት ላስቀር ብትል በአንድ እጅ ማጨብጨብ ይሆናል።ጦረነቱ ተጀምሯል።ሃይለኛው ጦርነት ግን ከፊት ይጠብቀናል።

ከፊታችን የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ የሚወስኑ ሶስት ሃይላት አሉ።ኤርትራ ፣ህውሃትና ፣ፋኖ

ጦርነቱ እንዴት እንደሚሄድ ባይታወቅም የተለያዩ ግምቶችን ማስቀመጥ ይቻላል

1/ ኤርትራ ህውሃትና ፣ፋኖ በጋራ ይህን ጨፍጫፊ ስርአት በጋራ አስወግዶ የኤርትራን ከስጋት ነጻ የሆነ መንግስት መመስርትን የወደብ ጉዳይንም የሁለቱን ሃገራት ጥቅም ያስከበር ውይይት በማድርግ ሰላም በቀጠናው ማስፈንንና ዘላቂ ሰላም እና እድገት ማምጣት ፣የትግራይን ህዝብ ምን በልቸ እኖራራለሁ።የአሳ እራት እየሆነ ፣በስደት የትግራይ ህዝብ ይጠፋል የሚለውን የትግራይ ህዝብ እጠፈንታ ታሳቢ ያደርገ ውይይት ማድርግ ፣የሳር ራስ ፋራፍሬወችን እየበላ በጫካ ከዝንጀሮ ጋር የሚኖርውን የኦሮሞ ህዝብ አርሶ በማብላት የአማራና የትግራይ ገበሬ ለራሱም ፣ለኦሮሞ ህዝብም ሁነኛ መፍትሄ ይሰጣል፤የባሌ 1000 ኪሎ ሜትር ሜዳማ ቦታ የወለጋ ጫካ የወርሰው ለም መሬት ይህን የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ፣እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ ድህነት ጥያቄ ይመልሳል።

2/በጦርነቱ መሸናነፍ ከሌለ 3 /4 ሃገራት ሊፈጠሩ ይችላሉ።ከገዛሁ አብርን እንቀጥላለን ፣ይህ ካልሆነ የራሳችንን ቤት እንገነባለን የሚሉት እነሽመልስ አብዲሳ የራሳቸውን ቤት ይሰራሉ።በአልጀርስ ስምምነት ወቅት የኢትዮጵያን የወደብ ባለቤትነት አስፈላጊነት ያነሳው የሜሪካው ዲፕሎማት ህርማን ኮህን እና በዚህ የተስማው ኢስያስ ፣ነገር ግን ያልበላህን አትከክ ያለው መለስ ዜናዊ ፣በአሁኑ ሰአት ደግሞ የትግራይ ሀገርነት ፌርማ እያሰባሰበ ያለው ህውሃት ፣ሊጣጣሙ የማይችሉት ትግራይና ኤርትራ ምናልበት ትግራይ ትግሪኝ በሚሏት ጨዋታ በጋራ ሁነው ሃገር ሊመሰርቱ ይችላሉ።ይህ ካልሆነ ህውሃት በድህነት የሚማቅቅ እና ሽብርተኛ ሆኖ የሚቀጥል የራሱን ሃገር መሰረትሁ ሊል ይችላል።የራሱን ሲኖደስ ያቋቋመው ህዝቡ ራሱንን ወደ መቻል እየተቃርበ መሆኑን ልብ ይሏል።ሌሎች ክልሎች የራሳቸውን ካሉ ፣ኢትዮጵያ እንደ ይጎዝላቪያ ሆነች ማለት አይደለ።አማራስ??ፋኖ አብሮ ለመስራት አስቦ ከሆነ ምን አስቧል?

3/በዚህ አሸናፊ ተሸናፊ በሌለበት ጦርነት ከቀጠለ ፣በኢኮኖሚ የደቀቀ ፣ተሰዳጅ ህዝብ ይዞ 20/30 አመታት መተራመስ

4/ብልጽግና ቢያሸንፍስ ?

የኦሮሞን ጥቅም አስከበርሁ በሚል አግበስባሽነት ትቂት ወሮ በላ ቡድኖች በሚያካብቱት ሃብት ፣አማራን ትግራይን እና ኤርትራን እርስ በእርስ እያዋጉ ሌሎች ብሄሮችንም እያቆራቆሱ ፣አሁንም የተጎሳቆለ ህዝብ ፣በጦርነት የሚኖር ህዝብ ፣ሰላም የሌለው ህዝብ ይዞ መቀጠል።

5 ኛውና መሆን የአለበት የአማራ ጠንክሮ መውጣት

ይህ ለአማራም ለትግራይም ለሌሎች ህዝቦችም ወሳኝና ተስፋ የሚሰጥ ፍትሃዊ ስርአት ይገነባል።አማራ በሚሊየን የሚቆጠር ሃይል ሞብላይዛድርጎ ወደ ሸዋ ካስጠጋ እና በህዝብ ማኧበል መሸነፍ ከቻለ ፣ለቀጠናው ሰላም አስማማኝ ነው።ከሽዋ ከተነሳ ውጊያው ግፋ ቢል 4 ቀን አለዛ በሁለት ቀን ሙሉ በሙሉ መቆታጠር ይችላል።ለዚህ ደግሞ ምንም አይነት የድንበርም ሆነ ሌላ ተቃርኖ የሌላቸው አማራና ኤርትራ በጋራ ለመስራት የበለጠ መተማመን የሚችሉ ስለሆነ ፣በጋራ መስራቱን በፍጹም እመነት መግባባት እና አብሮ መስራት ያስፈልጋል።አማራ/ፋኖ ሌሎች ሃገራትንም አብሮ ለምስራት መግባባት አለበት ።

ይህ በሆነበት ሰአት ግን ፋኖ ምን እየሰራ ነው ያለው?በሰፈር ፣በጎጥ ፣በወንዝ ፣በዞን እየተቧደነ መጠዛጠዝ ???

ይታሰብበት ለማለት እንወዳለን።

Читать полностью…

ዜና Today News

🔥ለሚመለከተው ሁሉ‼️
ጉዳዩ ፦ህጋዊ  የድጋፍ መስመር ስለማሳወቅ

   ከላይ በጉዳዩ ለመግለፅ እንደተሞከረው  አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ፮ኛ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ በህዝባችን ሙሉ ድጋፍ እና ያላሰለሰ እገዛ ይህን አማራ ጠል  ኦህዴድ መራሽ ጨፍጫፊ ስርዓት እየተፋለመ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ጀብዶችን እየሰራ ጠላትንም አንገት እያስደፋ ይገኛል።ትግላችን ከዚህ የደረሰውና ወደፊትም ሊቀጥል የሚችለው በህዝባችን ትክሻላይ መሆኑ ደግሞ የአደባባይ ሃቅ ነው።

ስለሆነም ብርጌዱ ለአደረጋችሁልን ሁሉ ድጋፍ ከልብ ምስጋናውን እየገለፀ ለቀጣይም በተለመደው እና በተጠናከረ መልኩ ድጋፋችሁ እንዲቀጥል እያልን ድጋፍ በምታደርጉበት ጌዜም ብርጌዳችን በአዲስ መልክ ሪፎርም ሰርቶ የሎጅስቲክ አመራር ካደረጋቸው ሦስት አመራሮች ማለትም :-
1. ትልቅስው መብት 
2. ኢ/ር መንግስቱ ዘላለም 
3. ላቀ አበበ ውጪ በየትኛውም መንገድ በብርጌዳችን ስም ድጋፍ ሊጠይቅ የሚችልን  ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን እንዳታስተናግዱ በጥብቅ እናሳስባለን።
ስርዓቱ ያሰማራቸው ጥቁር ጣሊያኖች በስማችን በዝርፊያ እንዳሰማራቸው ደርሰንበታል። ጥቂቶችንም ከጠላት መካክል እያወጣን አስፈላጊውን ርምጃ እየወሰድን እንገኛለን። ለወደፊትም ማንኛውም ዘራፊ አካል ወደ እናንተ መጥቶ ወይም በተለያየ መንገድ ቢጠይቅ ሙሉ መረጃውን ለኛ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን ።

የብርጌዱን የሎጅስቲክ ኮሚቴዎች በትክክል በማረጋገጥ እና አስፈላጊውን የደህንነት አካሄድ ተጠቅማችሁ ድጋፋችሁ ለትክክለኛው የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ እንዲደርስ እና ለትክክለኛው ዓላማ እንዲውል የየግላችሁን የአርበኝነት ተጋድሎ እንድትፈፅሙ ጥሪ እናስተላልፋለን።
              
© ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ

18/09/2017 ዓ.ም

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtube.com/shorts/SnO5FttxETA?si=tnAy3GYjZQrIdfdI

Читать полностью…

ዜና Today News

https://www.youtube.com/watch?v=kvDBx0TIUZ4

Читать полностью…

ዜና Today News

ጦርነቱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ይሁን ?

🇮🇷" ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል (የሆርሙዝ መዘጋት) " - ኢራን

🇺🇸" አራን ሰርጡን ብትዘጋ መጥፊያዋ ይሆናል " - አሜሪካ


ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።

የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሚገኝ የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የጦርነቱ ሂደት ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ሲሆን ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የተጠየቁት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም " ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል " ብለው መልሰዋል።

የአያቶላህ አሊካሚኒ ከፍተኛ አማካሪም ሃገራቸው በአሜሪካ በተጠቃች በኋላ ኢራን ሰርጡን መዝጋት እንዳለባት እና የአሜሪካን መርከብ ማጥቃት እንዳለባት ሲገልፁ ነበር።

የምክር ቤቱ ውሳኔ የአለምን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ የነዳጅን ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችል ሲሆን የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ምክትል ፕረዚዳንት ጄዲ ቫይንስ ፤ የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገልየዋል።

ቫይንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል።

በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ ? በሚል ተጠይቀው "ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤  የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል " ብለዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች በሚል የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ "እሱ ለኢራን መጥፊያዋ ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል።

ሆርሙዝ ቢረበሽ ምን ይጠራል ?

- ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ ኩዌት ኢራቅ ፣ ኳታር አብዛኛውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋር ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩት በሆርሙዝ ሰርጥ ነው።

- ነዳጅ ላኪዎች የሚጠቀሙበት ሰርጥ ስለሆነ የነዳጅ እጥረት ይከሰታል በመሆኑም ዋጋው ይወደዳል።

- ብዙ ሀገራት በዚህ ሰርጥ በሚመጣው ነዳጅ ነው ኢኮኖሚያቸው የሚንቀሳቀሰው በመሆኑም ሰርጡ ቢረበሽ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ይፈጠራል።

- የተለያዩ ሸቀጦችም፣ የኢንዱስትሪ እቃዎች፣ ምርቶች በመርከብ በዚህ ሰርጥ ያልፋሉ ይህ ሰርጥ ቢረበሽ የሎጂስቲክስ ስራዎች ችግር ይገጥማቸዋል የዓለም የንግድ ስርዓት ላይም ትልቅ ችግር ይፈጠራል። ዋጋም ይወደዳል።

መረጃው ከተለያዩ የውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰበ ነው።

Читать полностью…

ዜና Today News

ከሁለቱም ወገን ጋብ ብሎ ያደረው ውጊያ ጀምሯል!

የኢራን ሚሳይሎች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ። ጦሩ "ከኢራን የተተኮሱ ሚሳይሎችን ለይቻለሁ፣ ነገር ግን የመከላከያ ሥርዓቶቼ እየመጡ ያሉትን ሚሳይሎች ለመከታተልና ለመጥለፍ እየሰሩ ነው" ሲል  አሁን ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።

የእስራኤል ሕዝብ ወደ መጠለያ እንዲገባ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

Читать полностью…

ዜና Today News

ትግራይ‼️

በዛሬው ዕለት በመላው ትግራይ ክልል ቢሮዎች ዝግ ሆነው በዋናነት "ተፈናቃዮች ይመለሱ" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/Hq42Dquhv7o

Читать полностью…

ዜና Today News

የድል ዜና
አፋብኃ በጎጃም ቀጠና 5ኛ ክ/ጦር
⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️
በቀን 9/10/2017ዓ.ም  ከማንኩሳ ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች በአብደጎማ ፣ በማናና በዛባ ቀጠናዎች ለዘረፋ ፣ እና በሰከላ ለነበረው ውጊያ ኃይል ለመቀነስ ቢገባም የምድር ድሮኗ የቢተው ሻለቃ ተሰባስቦ ለዘረፋ ፣ የመጣውን የአብይ ቱልቱላ ኃይል ድል አርጋ መልሳመልሳዋለች
   በተለይም በማና ቀጠና የገባው ዘራፊና ጨፍጫፊው የጁላ ሰራዊት በውጊያ ሰዓት በተመቱበት አባላት በመናድ በአካባቢው ማሕበረሰብ ላይ ዘረፋ ፈጽሟል ። በዚህም በአካባቢው ካለው ቤት ለቤት በመግባትለምግብና ብለው ያስቀመጡትን እህል የጫነውን እህል ጭኖ ዘርፎ ከወሰደ በኋላ ያልቻለውን ደግሞ አውጥቶ ሜዳ ላይ በትኖት ሩጧል ። ይህ የሚያሳየው ቅልብ ሆዳሙ ሰራዊት ሕብረተሰቡን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያደርሰው ጫና ምን ያህል ለአማራ ያላቸውን ጭካኔ እንደሚያሳይ ሕዝቡን በጦርነት ፣ በረሃብ ማዳከም ለገበያ የሚጓጓዝበትን መንገድ በመዝጋት ከቤተሰብ ተጠያይቆ እንዳይሞት እያደረጉት ይገኛል ።
      ይህንን ተረድቶ ለሕዝብ የወጣው ፋኖ በተለያየ አቅጣጫ የመጣውን ወራሪ  በአጠቃላይ 7 ሙት ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ በማድረግ መልሰዋቸዋል ሲል የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ፍስሃ አደራው ተናግሯል ።

➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚
ድል ለአማራ ፋኖ

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/7Bt9rhRGCYg

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/Ae0ZmUdLboQ

Читать полностью…

ዜና Today News

🔥ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ጎንደር  ቀጠና #ዳግማዊ_ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር ምስረታን አስመልክቶ የተሠጠ መግለጫ‼️

የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ እስከ ወዲያኛው ለመቀልበስ የፋኖ ትግል በሁለንተናዊ የትግል ስትራቴጂ በስርዓቱ ላይ የበላይነቱን አስጠብቆ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ስለሆነም በአማራ ህዝብ ተሳትፎና ድጋፍ በሰው ሃይል፣ በትጥቅና ስንቅ እንዲሁም በአደረጃጀት እየጠነከረ መጥቷል።

ሆኖም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ግዙፉ ኮር  እነሆ ዛሬ ማለትም ግንቦት 26 ቀን 2017ዓ.ም 
          
ከበለሳ እስከ ደንቢያ ሳንኪሳ፣ ከፎገራ እስከ ወገራ፣ ከዞዝ አምባ እስከ አይንባ፣ ከእብናት እስከ ዳባት እንዲሁም ከፎገራ እስከ ጃናሞራ ቀጠናን የሚሸፍን ስያሜው “
#ዳግማዊ_ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር የተባለ ኮርን መስርተናል።

መስራች ክ/ጦሮችም የሚከተሉት ናቸው።
   1- መብረቅ ክፍለ ጦር
   2- ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር
   3- ንስር በለሳ ቅ/እጅጉ ክፍለ ጦር
   4- ጥቁር አንበሳ       ""
   5-ዞዝ አምባ ንጉሱ    ""
   6- ታድሎ ብርሃን        ""
   7- ፋናየ ውቤ ክፍለ ጦር ናቸው።
     
የዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር የስራ አስፈፃሚ አባላት የሚከተሉት ናቸው:-

1. አርበኛ የሻምበል ሙሉሰው..የኮር  ዋና ሰብሳቢ
2. አርበኛ መኮነን አስፋው......... ምክ/ሰብሳቢ
3. አርበኛ አንተነህ ብርሃኔ ....... ወታደራዊ አዛዥ
4. አርበኛ ጌታቸው አያልቅበት.... ምክ/ወ/አዛዥ
5. አርበኛ አየልኝ ውዴ...............ዘመቻ መምሪያ
6. አርበኛ ሱራፌል ኢልያስ...ምክ/ዘመቻ መምሪያ
7. አርበኛ ሰሎሞን ደሴ...............ፅ/ቤት ኃላፊ
8. አርበኛ ኤርሚያስ ንጉሴ....ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ
9. አርበኛ አብነት ሞላ ........ ህ/ግንኙነት ኃላፊ
10. አርበኛ ናትናኤል ሙሉዓለም. አስተዳደር ኃላፊ
11. አርበኛ ሲራክ ጥሩነህ.........አደረጃጀት ኃላፊ
12. አርበኛ ደምወዝ ጀግናው.....ሕዝብ አስተዳደር ኃላፊ
13. አርበኛ አምባቸው ወንዴ... ህግና ስነ-ምግባር ኃላፊ
14. አርበኛ ገዛኸኝ ያለው ......ሎጀስቲክስ ኃላፊ
15. አርበኛ ደምወዝ ጀምበር ...ምክ/ሎጀስቲክስ ኃላፊ
16. አርበኛ አለሜ ባየ..  ት/ት እና ስልጠና ኃላፊ
17. አርበኛ ባብል ብርቁ.... ፋይናንስ አስተዳደር 
18. አርበኛ አበበ ደስታው ....ግዥ ክፍል  ተጠሪ
19. አርበኛ አማኑኤል ምትኩ..የሰው ኃ/ አስተዳደር 
20. *                  ....   መረጃና ደህንነት መሆናቸውን እየገለፅን ለተመረጡት የስራ አስፈፃሚ አባላት በሙሉ መልካም የስራ ጊዜን እየተመኘን በተመደባችሁበት የስራ መደብ ከሙሉ መተማመን ጋር አደራ እንላለን።
      
      ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!!
           ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ/ም
            ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/09/2017 ዓ.ም

Читать полностью…

ዜና Today News

አማራነት

አማራነት ብዙ የተለያዩ ኅብረተሰቦች የተዋኅዱበት አካል ክፍል መሆን ነው። አማራነት ከጎሠኝኛት በላይና ውጭ የሆነ አጠቃላይ ማንነት ነው።

አማራነት የዚች ውጥንቅጥ መሬት ባለቤትነት ነው፣ አማራነት የደጋው ብርድና የቆላው ሙቀት የሚገናኙበት፣ የደጋው ዝናብም ከቆላው ወንዝ ጋር የተዛመደበት ኃይል ነው።

አማራነት ለሙሴ፣ ለክርስቶስና ለመሐመድ የሚጨሰው ዕጣን በእርገት መጥቶ የሚደባለቅበት እምነት ነው።

አማራነት በቄጤማ ጉዝጓዝ ላይ የሚታየው መተሳሰብና መፈቃቀር ነው።

አማራነት የአስተዋይነት፣የሚዛናዊነት የጨዋነት ባሕርይ ነው።

አማራነት ረዢምና ተጽፎ ያላለቀ ታሪክ ነው፤ ብዙ ሰዎችም የተሰዉለት ስሜት ነው።

አማራነት ስቃይና መከራ ነው፤ አማራነት ኩራትና
ክብርም ነው።

አማራነት ጭቆናና ጥቃት ነው። አሻፈረኝና እምቢ ባይነትም ነው።

የአማራ ዓላማ ያለችውንና የኖረችውን አማረነት እንደገና ለመፍጠር አይደለም። የአማራ ዓላማ ለአማራውያን በሙሉ የሚስማማ እድገታቸውንም የሚያፋጥንና፣ኅብረታቸውን የሚያጠነክር ሥርዓትን መፍጠር ነው። የአማራነት ችግር አማራ አይደለችም፣ችግሩ የሥርዓት ችግር ነው። የቤቴ
መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ እንዳለው ቂል እንዳንሆን።

አማራነት መካድ የራስን ማንነት መካድ ብቻ አይደለም። አባቶችንና እናቶችን፣ቅድም አያቶችን ከነቅርሳቸው መካድ ነው። በእንደዚህ ዓይነቱ ክህደት ላይ የተመሰረተ ማንነት የት ይደርሳል?ከበሽታ በቀርስ ትርፉ
ምን ይሆናል? ክህደት ራሱን የቻለ በሽታ ሲሆን ማስካድ ደግሞ የባሰ ነው። ክዶ ማስካድ ታምሜያለሁኝ፣ ታመሙ እንደማለት ነው። አስታማሚ እንኳን እንዳይገኝ የማድረጉ ጥረት የበሽታውን ምለዓትና ጽናት ያመለክታል።

ሆኖም የአማራ ታሪክ ሊያስተምረን እንደሚችለው አማራ እንደ ላስቲክ ነው። ሲስቡት ይሳባል፣ሲለቁት ይሰበሰባል። ማለት-ይሳብና ይሳሳል እንጂ አይበጠስም።

ዲቭ ዳዊት ነኝ ከአዲስ አበባ ለውድ ጀግኖች ለአማራ ፍኖ  ክብር እንዲሆንልኝ ነው።

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/mmNrTP1YQDo

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/KkODzNc7n24

Читать полностью…

ዜና Today News

🇪🇹 ትግራይ ክልል ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ በማቅረብ ቀዳሚ እንደሆነ ተገለፀ

💵 ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ውስጥ ከወርቅ 2.57 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡

🏦 በአጠቃላይ 29.396 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቧል።

እንደ የማዕድን ሚኒስቴር ገለጻ ከክልሎች ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን፦

🔸 ትግራይ፤ 12 ሺህ 210 ኪሎ ግራም

🔸 ኦሮሚያ፤ 6 ሺህ 910 ኪሎ ግራም

🔸 ጋምቤላ፤ 4 ሺህ 590 ኪሎ ግራም

🔸 ቤንሻንጉል፤ ጉሙዝ 3 ሺህ 689 ኪሎ ግራም

📌 በሌሎች ማዕድናት አመርቂ የሆነ ውጤት እየተመዘበ እንደሚገኝም የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዮስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtube.com/shorts/th9rGyAajZY?si=Y_UUloCI--snfqWR

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtu.be/LezB06ASxME

Читать полностью…

ዜና Today News

https://youtube.com/shorts/MqSDo7EbmYw?feature=share

Читать полностью…
Subscribe to a channel