zewjeti | Unsorted

Telegram-канал zewjeti - ሀላል ትዳር❤️

7103

...................ፍቅርን.......................... በትዳር ውስጥ ..................ፈልጉ።......................... ትዳር የእውነተኛ ፍቅር መገኛ 💝ተዘወጅ በነቢዬ ሱና ሀላል ትዳርን ላይ ላለዎት የትኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Abuyabot

Subscribe to a channel

ሀላል ትዳር❤️

ኸሚስ ምሽት 5
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ሰዎቹ ይላሉ፤
በኸሚስ ምሽቱ
'ቡናሽ ጣዕም አለዉ'

ቄጤማዉ ጉዝጓዙ፤
እጣኑ አድሩስሽም
ለአፍንጫ ቀለብ ነዉ

እኔ ሚስኪን ኑዕማን
አንቺን የቀመስኩት
እንደምን ልሁነዉ?

ቴሌግራም ● telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

(4)

ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ አበቃህ ወይኔ ባሌ!" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።

ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።

ከዚያም በድል አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ።
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"
" እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።

የሰው ልጅ ጎዶሎ ነው የተሟላ አይደለም፣ ፍፁምነት ለአላህ ብቻ ነው።
ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት ... በሀሳብም በአካልም እንዲሞላሉ ተደርገው ነው ጀሊሉ የፈጠራቸው። አንዱ የጎደለው ሌላው አለው። አንዱ የማይችለዉን ሌላው ይችለዋል ፣ ለአንዱ የማይታየው ለሌላው ይታየዋል።

ለመናናቅ፣ ለመገፋፋትና ለመለካካት ሳይሆን ዱንያን አብረን እንድንኖር፣ ፈተናዎቿንም አብረን እያሸነፍን ወደ ጀነት እንድንጓዝ ነው አላህ ወደዚህች ምድር ያመጣን።

አራተኛው ህግ
አንዱ የሌላኛዉን ሀሳብ ጆሮ ሰጥቶ ያድምጥ፣ አይናናቅ፣ አያጣጥል።

👌 telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

http://telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ኸሚስ ምሽት 3
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አንቺዬ...
ከቤትሽ ብመጣ
ምሽቱ አሸብርቋል
ቄጤማዉ ጉዝጓዙ
በጭሳጭስ ደምቋል

ከረከቦትሽ ስር
በሂጃብ ተዉበሽ
ዚክሩ ሶለዋቱ
በሃይባ ተከበሽ

ኸሚሱ አጅቦኛል
ዉበትሽ ማርኮኛል
ይዣለሁ ማብሰልሰል

ሰዉን መላዕክቱን
እንዲህ ያማለልሽዉ
ወሎዬ ነሽ መሰል

አጀብ አጀብ
👁 በቴሌግራም ፦ telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

የወሎዬ ዉበት
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ቡና ልጠጣ ከተቀመጥኩበት በረንዳ ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች በክርክር ተጠምደዋል። የክርክራቸዉ መነሻ ሁለት ሴቶች በመንገድ ሲያልፉ ተመልክተዋል። ጸጉራ ላይ ሻሽ ጣል ያደረገቸዉ ሴት ዉበቷ የሁሉንም ወንድ ልብ ፈትኗል። አብራት ያለችዉ ሴት ግን ጸጉሯን አንጨባራ፤ በሱሪ ተወጥራ፤ በመነጽር ለመጉላት ብትሞክርም አዲሱ የንግድ ባንክ ህንጻ ስር እንደሚገኝ ሳር ቤት ኩስስ ብላ ታየቻቸዉ።

ሁለቱም ወሎዬ ሆነዉ እንዴት በዉበት ይቺኛዋ በለጠች በማለት ሁሉም የየራሱን ሀሳብ ይሰነዝራል።

እንደኔ ራቅ ብለዉ ዉይይታቸዉን የሚያደምጡ አባት "በወሬያችሁ ገባሁ መሰል ብለዉ..." ንግግራቸዉን ቀጠሉ። ሁሉም ወደሳቸዉ ዙሪዉ ምን እንደሚሉ ለማዳመጥ ትኩረት ሰጧቸዉ። "... ወሎ የዉበት ምንጭ፤ የቆንጆ መፍለቂያ ሀገር ናት። አርጎባዉ፤ ኦሮሞዉ፤ ሶዶማዉ ተደማምሮ ወሎዬ ነዉ። ታዲያ ሴቶቻችን በሄዱበት ሀገር ሁሉ የወንድን ልብ ከፍተዉ እንዲገቡ ዉበትንና ገራገርነትን አብዝቶ አድሏቸዋል። ሴቶች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ ወሎዬዋ ከሁሉም ደምቃና አሸብርቃ ትታያለች። ምክንያቱም ወሎዬ ናታ..." አሉ። እኔን ጨምሮ በበዙሪያችን ያሉ ሰዎች በሽማግሌዉ ሰዉ ንግግር ተስበናል። ማሳረጊያቸዉ ምን ይሆን ብለን ጓጉተናል። "... እና ልጆቼ የወሎ ሴቶች ከሁሉም ይበልጥ ተዉበዉ የመታየታቸዉ ሚስጥር 'ሂጃባቸዉ' ነዉ።..." አሉ። ሁላችንም ተደነቅን። ያላስተዋልነዉ ነገር ነበር።

ዙሪያ ገባዉን ቃኝተዉ እየሰማናቸዉ እንደሆነ ሲያዉቁ ንግግራቸዉን ቀጠሉ "... ሂጃብ ዉበት ነዉ። ጸጉሯ ላይ ሻሿን ጣል ስታደርግ ፀሃዩ ላይ ጨለማን ጥሎበት አለምን በዉበት እንደምታስገርመዉ ጨረቃ ደምቃ ትታያለች። ሃያማኖቷ ደግሞ ክብሯን ይጨምርላታል፤ ቁጥብ ያደርጋታል። እና ልጆቼ የሴቶቻችን ዉበት ሚስጥር ሂጃባቸዉ ነዉ። ይሄን ደግሞ አሁን አብረዉ ካለፉት ሴቶች አረጋግጣችኃል።" ብለዉ ንግግራቸዉን ቋጩ።

Telegram.me/Nuiman_9

Photo - ከዚሁ መንደር

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ጀቢኝ
ኸሚስ ምሽት 2
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሂጃብ ተዉበሽ
ቡናዉን አፍልተሽ
ምሽቱን አድመቀሽ

ስትይ አወል ጀባ
እንደዉ ሆዴ ባባ

ከቡናዉ  በኃላ አንቺን ብጀቢኝ
ለጀሊሉ ሱጁድ አሁን ባረኩኝ

በይነል ፈኺዘይን ኒዕማዉን ይዘሽ
ሀላሌ አድርጌሽ ጀቢኝ እባክሽ

@Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ታላቁ የበድር ጦርነት
***,*
(1)
ከበድር ጦርነት በፊት የነበሩ ሁኔታዎች
ቅፍለቱ ከሻም ወደ መካ መመላሻው ሲቃረብ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ንብረቱን ለመማረክና ከሃዲያኑ መካ ላይ ከሙስሊሞች የዘረፉትን ንብረት ለባለንብረቶቹ ማካካሻ ለመስጠት ወሰኑ፡፡ ስለሆነም በስባስ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) የተባለ ባልደረባቸውን ስለ ቅፍለቱ መረጃ ይዞላቸው እንዲመጣ ላኩት፡፡ በስበስ የቅፍለቱን መመለስ አጣርቶ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲነግራቸው ባልደረቦቻቸው ቅፍለቱን ለመማረክ እንዲከተሏቸው፡- “እነሆ የቁረይሾች ቅፍለት ደርሷል፡፡ በርሡ ውስጥ ሃብታችሁ አልለ፡፡ ስለሆነም ውጡ ምናልባት አላህ ምርኮ እንድታገኙ ያደርጋችሁ ይሆናል” በማለት አዘዟቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በወርሃ ረመዳን አሥራ ሁለተኛ ቀን ሁለተኛው ዓመተ ሂጅራ መዲናን ለቅቀው ወጡ፡፡
ይሁን እንጂ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዲናን ሲለቅቁ ጦርነት ሊያደርጉ አስበው አልነበረም የወጡት፡፡ ምንም እንኳን በእያንዳንዱ ቅኝት ወቅት የጦር ቁርቁሶች ቢኖሩም ሙሉ ጦርነቶች ነበሩ ለማለት አይቻልም፡፡ በዚህ የአቡ ሱፍያን ቅፍለት ውስጥ የነበሩት ሠላሳ አራት ሰዎች ሲሆኑ ከእርሳቸው (ከነቢዩ ሰ.ዐ.ወ) ጋር አብረው የወጡት ደግሞ ሦስት መቶ ባልደረቦቻቸው እንደመሆናቸው ዘጠኝ ለአንድ በሆነ ልዩነት ይበላለጡ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ስለሆነም እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡
እንደሚታወቀው የመካ ከሃዲያንና የመዲና ሙስሊሞች በጦርነት ሁኔታ ላይ እንደሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ ያ ማለት የአንዱ ደምና ገንዘብ ለሌላው የተፈቀደ (ሐላል) ነው ማለት ነው፡፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ በድር ሲያቀኑ መዲና ላይ ሶላት እንዲያሰግዱ ዐብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱምን (ረ.ዐ) ወከሉ፡፡ ኋላ ላይ ግን ‘አር ረውሃ’ ከተባለ ሥፍራ ሲደርሱ አቡሉባባህ (ረ.ዐ) ወደ መዲና እንዲመለስና ጊዜያዊ አስተዳዳሪ እንዲሆን ላኩት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ቅፍለቱ ወሬ አጣርተው እንዲያመጡላቸው ሁለት ሰዎችን ላኩ፡፡ ሰዎቹም ከተንቀሳቀሱ በኋላ ያዩትን መረጃ ይዘውላቸው ተመለሱ፡፡
የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሠራዊት በተመለከተ ሶሒሕ የሚባሉ ሠነዶች ሳይቀሩ በቁጥሩ ላይ የተለያየ አቋም ይዘዋል፡፡ ቡኻሪ በበድር ዘመቻ የተሳተፉትን ሙስሊሞች “ሦስት መቶ ምናምን ይሆናሉ” በማለት ጽፈዋል፡፡ ‘ምናምን’ የሚለው አገላለጽ ከሦስት አስከ አሥር ሰዎችን ያጠቃልላል፡፡ ሙስሊም በበኩላቸው ዘማቾቹን ሦስት መቶ ዘጠኝ ናቸው በማለት ትክክለኛ ያሉትን ቁጥር አስቀምጠዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሦስት መቶ አርባ ሰሐቦችን (ረ.ዐ) ስም በመዘርዘር በድር ላይ መሣተፋቸውን ጽፈዋል፡፡
የሆነ ሆኖ ወደ በድር ያቀናው ሠራዊት አጠቃላይ መዲና ውስጥ የነበረውን ሙስሊም እንደማይወክል ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም የሠራዊቱ ዓላማ በአቡ ሱፍያን የሚመራውን የመካውያንን የንግድ ቅፍለት ለመማረክ እንደመሆኑ በርካታ ሰዎች መዲና ውስጥ ቀርተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ይህ ሠራዊት መጨረሻ ላይ አንድ ሺህ ከሚሆነው የከሃዲያን ጦር ጋር ይጋጠማል ብለው ፈጽሞ አልገመቱም፡፡

ይቀጥላል ....

/channel/zewjeti

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

አግብተሽ ተፈተሽ ፤ እንዲህ ካማረብሽ
እኔም ላንዴ ላግባሽ...
ባ'ልጋ ጨዋታ ነዉ የሚጠራዉ ፊትሽ!
(ኑዕማን ኢድሪስ)

🅙🅞🅘🅝 🅜🅔
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

በሐራም የኖረ ረከሰ
በሀላል ያደረ ነገሰ፡፡
ሁሌም ሀላል ለእይታም ማራኪ፤ ለመስማትም መሳጭ፤ ለማደርም ጣፋጭ ነዉ!!

ኑዕማን ኢድሪስ
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

በአላህ ፍቃድ በቅርቡ አዲስ ልብ ወለድ ጽሁፍ የማቀርብላችሁ ይሆናል!!

እስከዚያ ቻናሌን Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ!!!

🙏 ኑዕማን ኢድሪስ

@Nuiman_official
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ቢራቢሮዋ ኢትዮጵያ
(ኑዕማን ኢድሪስ)
.
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በአንድ ወቅት ያደረገዉን ዳዕዋ ዛሬ እያዳመጥኩ ነበር። በጣም ደስም ይላል። ስለዚች አሳዛኝና ሚስኪን የሆነች ሀገር ደስ የሚል ምሳሌ ነበር ያስቀመጠዉ።

አንድ ታዋቂን ጠቢብ በሰዎች መወደድና መከበር ያብከነከነዉ ወጣት ጠቢቡን በሰዎች ፊት ለማዋረድና ዝቅ ተደርገዉ እንዲታዩ ያደረገዉ ፈታኝ ጥያቄ የሚገርም መልስ እንዲያገኝ አድርገዉታል።

ወጣቱ ወደ ጠቢቡ በእጁ ቢራቢሮ ይዞ ይሄዳል። ሰዎች በተሰበሰቡበት ፊት ጠቢቡን አንድ ጥያቄ ይጠይቃቸዋል። 'በእጄ የያዝኳት ቢራቢሮ በህይወት አለች ወይስ ሞታለች?' አላቸዉ። ጠቢቡም የልጁን ሁኔታ ተመልከተዉ የተረዱት ነገር ስላለ ለመልሱ ዘገዩ። ምክንያቱም በህይወት አለች ቢላቸዉ በእጁ ጨፍልቆ ይገላታል። ሞታለች ቢሉት ደግሞ ይለቃትና እንድትበር ያደርገታል። በዚህም ፈተናዉ መዉደቅ እንደሌለባቸዉ ተረዱ።

'ይበሉ እንጂ የጠየቅኮዎትን ጥያቄ ይመልሱ' ብሎ በድቃሜ ጠየቀ።

'ልጄ ሆይ የቢራቢሮዋ የመኖር ህልዉና በእጅህ ነዉ ያለዉ' ብለዉ መለሱለት።

😳 ኢትዮጵያ በቢራቢሮዋ ትመሰላለች። ህዝቦቿ እርስ በእርሳቸዉ በብሄር፤ በዘር፤ በሀይማኖትና በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እርስ በእርሳችን የምንባላ ከሆነ የኢትዮጵያ መኖር ህልዉና ጥያቄ ዉስጥ ይገባል። ምክንያቱም የመኖር ህልዉናዋ እኛዉ ነን።

በአለፉት ዘመናቶች በመቻቻል ፈሊጥ አንዱ በሌላዉ ላይ የበላይና ጨቋኝ ጊዜ ነበር። አልፏልም። አሁን ግን ሁላችንም እንከባበር። ለሀገራችን የእድገት ህልዉና እኛዉ ነንና ልዩነታችንን አቻችለን በፍቅርና በሰላም እንኑር!!

@Nuiman_official
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ይ ህ ን ያ ው ቁ ኖ ሯ ል ?
በተቀደሰው ከዕባ ላይ መብረር የማይቻለው ለምንድን ነው?መካ ምድር ላይ
የአየር ማረፊያ የሌለውስ ለምንድን ነው?
ብዙዎች ኢስላምን እንዲቀበሉ መነሻ የሆነ አስደማሚ መረጃ ነው! የተቀደሰው
ከዕባ የያዘው ልዩ ስፍራ በጂኦግራፊ ቋንቋ ትክክለኛው የመሬት እንብርት ነው።

ማዘንበል፣መዛባት ወይም መጣመም የማይስተዋልበት ፍፁማዊ ( ፐርፌክት)
ነጥብ ነው።ከዕባው ያረፈበት ልዩ ስፍራ የምድራችን የስበት ( ግራቪቲ)
ማዕከልም ነው።ስለሆነም ማንኛውንም ማግኔታዊ ኃይል ወይም አካል ወደ ራሱ
ይስባል።

በዚህ ምክኒያት የመጀመሪያው የፀሀይ ጨረር የሚያርፈው በዚህ ልዩ
ስፍራ ላይ ነው።ከዕባው የያዘው ልዩ ስፍራ የምድራችን የስበት ማዕከልና
የዩኒቨርሱ( ከውኑ) የጨረር ኃይሎች መገናኛ ስለሆነ ፣በከዕባው ሰማይ ላይ
ማንኛውንም በረራ ለማድረግ አያስችልም።አዕዋፍም ሆኑ አውሮፕላን በላዩ
መብረር አይችሉም።ወፎቹ በጎኑ እየበረሩ ይዞሩታል እንጂ በላዩ አይበሩም ።

የተቀደሰው ከዕባ የመሬት ብርሀን መሆኑም ይታወቃል።ከከዕባው የሚመነጨው
ብርሀን የመሬትን ከባቢ ክልል በማለፍና ወደ ጠፈር( ሰማይ) በመዝለቅ በዚያው
ዓለም በሚገኘውና በይተል መዕሙር በሚባለው ማዕከል ላይ ያርፋል።ሁለቱ
ቅዱስ ማዕከላት ( ከዕባና በይተልመዕሙር)በ አንድ ቀጥተኛ የሆነ የቁም
( ቨርቲካል) መስመር ላይ ( ትይዩ) ናቸው።
( ኢዒቁከ/Tahar Tahar)
© Awwal Hamza Hamza
ወቅታዊ መረጃወች ለማገኘት የtelegram አድራሻችንን Link በመጫን ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFACld9qu1NhysxDHw

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

💝የጥንዶችን ሕይወት የተሻለ የሚያደርገዉ
የቁስ የገንዘብና የዱንያ መጣቀሚያዎች
መብዛት ሳይሆን እዝነትና ፍቅር በመካከላቸዉ መብዛቱ ነው።

“ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን
ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣
በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ
ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።” 
ሱራ አር-ሩም :2
#Islam

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

🕛 ረመዳንን ምክንያት በማረግ የተዘጋጀ

ከየትኛውም አገር ሁነው ለቤተሰብ፤ ለዘመድና ለወዳጅ ለኢፍጣር የሚጠገሙበትን እቃዎች በተለይ ደግሞ ለምግብነት የሚያገለግሉ እህል ነክ ነገሮችን የትኛውም ቦታ እናደርሳለን።

ለበለጠ መረጃ
📲 0910558792 ይደዉሉ ወይም ደግሞ በቴሌግራም @PrinceMizz2 & @nuimanveiw አብዱሠላም (ሚዕዛር) ብለዉ ያናግሩን።

በፈለጉት አማራጭ ማዘዝ ይችላሉ!!!
🅁🄴🄼🄴🄳🄰🄽 🄺🄴🅁🄸🄼

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ስኬት ማለት ሁሉንም ስራ በብቃት ማከናወን ማለት አይደለም ግን በሙሉ አቅማችን ለመስራት መጣርና እያሻሻሉ መሄድ ነው። ስለዚህ የስኬት ጉዞህን ቀንህን በማሸነፍ ጀምር ወዳጄ።

🙏መልካም ቀን🙏
@Nuiman_official
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

'መዉሊዱ'
ኸሚስ ምሽት 4
(ኑዕማን ኢድሪስ)


ለመዉሊዱ ደስታ ከቤት ስትወጪ
ባለሽ ነገር ሁሉ ፈኪበት አጊጪ

ግን...
በአረንጓዴዉ ሻልሽ
እንዳያይሽ ባልሽ

ምክንያቱም ዉዴ
የጨረቃን ዉበት፤ እጅጉን በልጠሻል
ከጧት ፀሐይ በላይ ይበልጥ ፈክተሻል

ቁንጅናሽን አይቶ መለየት ይሳሳል
እቅፉ ዉስጥ አ'ርጎሽ የልቡን ያደርሳል
ተያማ በኃላ... መዉሊዱ ይረሳል 😂
--
🙄 መዉሊድ ቢድዓ ነዉዴ 😜

👌 በቴሌግራም - telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

'ዳዒም ተፈቀርኩ'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

የኔ ነቢ፤ የኔ ራህመት
አደረሰኝ አመት ካ'መት

የኔ ረሱል፤ ሸፈዓዬ
ድርብ ሆነ ያ ደስታዬ

የኔ ሀቢቢ፤ ያ ሙስጠፋ
ሽርኩ ሁሉ ባንቱ ጠፋ

ባንቱ'ኮ ነዉ ሰዉ የሆንኩት
የኔን ጌታ አላህዬን ያመለኩት

ባንቱ'ኮ ነዉ ፤ ሴቱ ወንዱ
ለጀሊሉ ዳኢም መስገዱ

ያ ኻሊቅ...
የኔ አምላክ አላህ፤
ምንኛ ወዶኛል

የኑህን የሙሳን የሉጥን የኢሳን፤
የነሱን ጊዜ አልፎ ኡመቶ እንድሆን ከኃላሁ ፈጥሮኛል

ምንኛ እድለኛ ፤ ጀሊሉ አድርጎኛል
በወዱ ነቢ ልብ እኔን አስናፍቆኛል

ሀቢቢ...
እኛን ናፍቀሁ አንቱ፤ አፈር እንደጫርኩ
ይሄዉ በኔ ልብም፤ ዳኢም ተፈቀርኩ !

⭐️ በቴሌግራም - telegram.me/Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ኸሚስ ምሽት 3

ዛሬ 3 ሰአት

Follow me @Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

አልሐምዱሊላህ

@Nuiman_9

Join

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ወሎየዋ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አላህዬ አላህዋ
ማርካኛለች ወሎየዋ

ስጠኝና አሳርፈኝ
ሸህዋዉ ነዉ በኢባዳ ያሰነፈኝ 😜

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ኸሚስ ምሽት
- ተቀበይ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሶለዋት ደምቆ
በዚክር አሸብርቆ

ቡናዉን አፍልተሽ
ነዱን አጫጭሰሽ
ስትይ አወል ጀባ

ቀና ብዬ ባይሽ
እስከ'ነ ሂጃብሽ
ከፊቴ ቁመሻል

ምርቃቱ ጠፋኝ
ጀሊሉ በቁድራዉ
ልቤን ጀብቶሻል

@Nuiman_9

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

እርስዎ የአማኑኤል የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ኖት እንበል… ሆስፒታሉ አንድ ሠው ብቻ የመቀበል አቅም ቢኖረው… ከሚከተሉት ሠዎች ውስጥ የትኛው የሆስፒታሉን አገልግሎት ቅድሚያ እንዲያገኝ ይፈቅዳሉ???
:
1⃣ በግፍያ መሐል ታክሲ ውስጥ ለመግባት ጫማውን የሚያወልቅ ሰው😂😂😂
:
2⃣ ሌሊት የተኛበትን የጊዜ ርዝመት ለመለካት ሜትር አቅፎ የሚተኛ ሠው😂😂😂😂
:
3⃣ ለህመምተኛው የእንቅልፍ ኪኒን ለመስጠት ህመምተኛውን ከእንቅልፉ የምትቀሰቅስ ነርስ😂😂😂
:
4⃣ ጉርድ ፎቶ ለመነሳት ጫማውን የሚያስጠርግ
ሠው😁😁😁😁
:
5⃣ የሾላ ፍሬው መብሠሉን ዛፍ ላይ ወጥቶ ካረጋገጠ
በኋላ፤ መሬት ወርዶ ፍሬውን ለማውረድ ድንጋይ
የሚወረውር😂😂😂

:
:
ሥንት ቁጥር አፋጣኝ ህክምና ያስፈልገዋል???

መልሱን በ @nuimanveiw
ፏ ያለ ኸሚስ ምሽት 😍😍

@Nuiman_official
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

✳️
____________________
#የዙልሒጃን_10_ቀኖች_መፆም_የፈለገ_እነሆ___________________________

የዙል ሒጃ ፆም እሁድ ይጀምራል👈 🕋

1⃣✏️ እሁድ
11/ 7/ 2021

2️⃣✏️ሰኞ
12/ 7/ 2021

3️⃣✏️ማክሰኞ
13/ 7/ 2021

4️⃣✏️እሮብ
14/ 7/ 2021

5️⃣✏️ሀሙስ
15/ 7/ 2021

6️⃣✏️ጁመዓ
16/ 7/ 2021

7️⃣✏️ቅዳሜ
17/ 7/ 2021

8️⃣✏️እሁድ
18/ 7/ 2021

9️⃣✏️ሰኞ አረፋ ላይ ለመቆም ያልበቃ ሰኞ ይፆመዋል19/ 7/ 2021
የአረፋ ፆም የሚመጣውን ያለፈውን የአመት የሚመጣውን የአመት ወንጀላችን የማበስ ፈድል አለው ا አላህ ይወፍቀን የተቀበል ሚነ ወሚንኩም ያረብ!


🔟 ማክሰኞ የውሙል አረፋ ኢዱል አድሀሙባረክ . 20/ 7/ 2021

✏️~•° መልዕክቱ እናንተ ጋር እንድቀር አትፍቀዱ
ሌሎችን አሰወታውሱበት !!

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ሚስት ሆኜም ቢሆን ፤ አግቢኝ ግድ የለሽም
ብርዱ እስኪያልፍ ድረስ፤ ከላይ ልሁን ብዬ አላስቸግርሽም🤣🤣
(ኑዕማን ኢድሪስ)
.
@Nuiman_official
@Nuiman_official

ቻናሌን 🅙🅞🅘🅝 ያድርጉ!!

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ዘምዘም ባንክ ተበድረህ ብሩን በጊዜ አልመልስ ስትላቸው በMessage "ያ አኺ አሏህን ፈርተህ ሀቃችንን መልስ!"😂

@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

@Nuiman_official
@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

የሀይማኖት ስብጥር በፓርቲዎች!
**
ነፃነት እና እኩልነት ፖርቲን በተመለከተ ዛሬ በምርጫ ክርክር ላይ የቀረበው ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ የተለያዩ ...(ረብሻ ፈጣሪ ጎጠኛ ሚዲያዎች)... ባለፉት ቀናት በፎቶሾፕ ጭምር በውሸት ሲነዙት የነበረው ጥያቄ በመሆኑ ብዙም አልገረመኝም
ለማንኛውም ይቺን ግርድፍ መረጃ ተመከቷት

የኃይማኖት ስብጥር በፖለቲካ ፓርቲዎች
👉ብልፅግና ፓርቲ
1. ጴንጤ- 45%
2. ኦርቶዶክስ-34%
3. ሙስሊም-21%

👉ኢዜማ ፓርቲ
1. ጴንጤ- 15%
2. ኦርቶዶክስ-82%
3. ሙስሊም-3%

👉ኦፌኮ ፓርቲ
1. ጴንጤ- 35%
2. ኦርቶዶክስ-40%
3. ሙስሊም-20%
4. ዋቄፈታ-5%

👉ነእፓ
1. ጴንጤ- 5%
2. ኦርቶዶክስ-20%
3. ሙስሊም-75%

👉ባልደራስ
1. ጴንጤ- 5%
2. ኦርቶዶክስ-94%
3. ሙስሊም-1%

👉አብን
1. ጴንጤ- 10%
2. ኦርቶዶክስ-80%
3. ሙስሊም-10%

👉እናት ፓርቲ
1. ጴንጤ- 0%
2. ኦርቶዶክስ-100%
3. ሙስሊም-0%
(አብዱረሂም አህመድ)

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ወንድሜ ዒሳ ታደለ ተወዳጆቹን 99 የአላህ ስሞች እጅግ ተወዳጅ በሆነው የካሎግራፊ ጥበብ ውድከት በተሰኘ ስታይል ተጠቅሞ አይነግቡ በሆነ መንገድ እንደሚያዘጋጅ ሁላችንም እናውቃለን። እንዲያውም ከተወሰኑ አመታት በፊት ጀምሮ ረመዳን መጣ ሲባል ዒሳ ምን ሰርቶ ይሆን ብለን እንድንጠብቅ ሁሉ አላህ በስጠው አቅም አስገድዶናል።
ዘንድሮ የረመዳንን መምጣት ተከትሎ የቤቶቻችን ግድግዳ የምናስውብባቸው በወጣን በገባን ቁጥር ቀና ብለን ስናያቸው የአላህን ፀጋ እንድናስብ የሚያደርጉ በእንጨት ላይ የተቀረፁ የአላህን ስሞች አዘጋጅቶ ለሰባተኛ ጊዜ ኤግዝቢሽን አዘጋጅቶ ይመጡ ይጎብኙ ከወደዱት ደግሞ የድርሻዎን ይውሰዱ ብሎናል። ኤግዚቢሽኑ በዛሬው እለት ሚኒስተሮች ባሉበት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቶዋል ኤግዝብሽኑ እስከ ሚያዝያ 17 ይቆያል በጊዬን ሆቴል ይምጡና ይጐብኙ
የድርሻዎን ይውስዱ።

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ አልተፈቀደምና እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው ፡፡ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ስለማናውቅ ለመፍረድ መቸኮል የለብንም።


@Nuiman_official

Читать полностью…

ሀላል ትዳር❤️

ቃል በገባነው መሰረት መልሱን ለመለሰው ተሳታፊ የ 100 ብር ካርድ ተልኮለታል
Al-nur እንኳን ደስ ያለህ

Читать полностью…
Subscribe to a channel