Journalism is not just about speaking to those in power; it is about speaking truth to power ✊️
#Journalism
@EliasMeseret
"ጠንካራ ዲፕሎማሲ... " ብሎ ለኮመተ ክፍያ ተጀመረ እንዴ?
አንዳንዴ እኮ አንሰማም፣ የሰማችሁ አሳውቁን።
#የሚድያሰራዊት
Via Inbox
@EliasMeseret
"ጡጦ የምልበት አቅም የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት ወተት አሁን አነሳቸው፤ እንዴት ይድረሳቸው?. . . የተገኘው ምግብም አልሆናቸው አለ፤ አልስማማቸው አለ።"
ይህ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ዛሬ ላይ ያለው ሁኔታ ነው... መቸስ አይናችን እያየ ከሚረግፉ ህዝብ ያለውን አሰባስቦ ቢረዳስ?
በዚህ ዙርያ ለማስተባበር የምትችሉ እንነጋገር፣ ይህም ስም ካልተሰጠው እና ካልተከለከለ ማለት ነው።
Quote via BBC Amharic
@EliasMeseret
የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮንን አፍሪካ ውስጥ ያሉ ህፃናትን መቀንጨር የሚከላከል ድርጅት እንዳቋቋሙ ዛሬ ሰማን
ድርጅታቸው ለግዜው አፍሪካን ትቶ እሳቸው የወጡበት የአማራ ክልል ውስጥ እንዲህ በርሀብ እየተጎዱ ያሉ ህፃናት ላይ ትኩረት ቢያደርግ እላለሁ።
ይህ የ1977 ድርቅ ሳይሆን አሁን ላይ የኢትዮጵያ ህፃናት ምንም በማያውቁት እያለፉበት ያለ ስቃይ ነው፣ አንዳንዱ ህዝባችን ደግሞ "ጦርነት አቁሙ በሏቸው፣ ወይም ርሀቡ ይቀጥላል" እያለ በህፃናቱ መሳለቅ ይዟል።
እንደ ህዝብ መጨረሻችን ይህ መሆኑ ያሳዝናል።
Photo: Belay Manaye
@EliasMeseret
#MyOpinion በዚህ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ የዛሬ 11 ወር ገደማ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው ስምምነት ከዚህ በኋላ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው መረዳት ይቻላል።
በሌላ በኩል "የሶማሊላንዱ ስምምነት በስም ተጠቅሶ ተሰርዟል ካልተባለ ለስምምነት አንቀመጥም" ሲሉ የነበሩት የሶማልያ መሪዎች የፈለጉትን ሳያገኙ ቀርተዋል።
በዋናነት ግን ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የባህር በር የማግኘት አካሄዷን በሞቃዲሾ በኩል ለማድረግ መስማማቷ ሶማሌዎችን ዋናው የስምምነቱ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል። ሲቀጥል ስምምነቱ የግብፅ ጦር ከሶማልያ እንዲወጣ የሚል ነጥብ አልተካተተበትም።
ለዲፕሎማሲያችን ትልቅ፣ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ክስተት ሆኖ ማለፉ ግልፅ ነው... ግን ቢያንስ ጦርነት ማስቀረት መቻሉ ትልቁ ትርፍ ነው።
"ይሄ አካሄድ ግን ያስኬዳል?" ብለን በወቅቱ የጠየቅን የተለያየ ስም ሲሰጠን ነበር። የሆነው ይሁን... ከዚህ ክስተት መማር ከቻልን መልካም፣ ካልሆነ ግን የሀገርን ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን ታሪክ እና ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑ ግልፅ ነው።
@EliasMeseret
በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?
- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል
ሙሉ ዜናው ⤵️
/channel/meseretmedia/683
@EliasMeseret
አቶ ታዬ ደንደአ እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!
ፍርድ ቤት የፈታውን ግለሰብ እስር ቤት በር ላይ ጠብቆ ማፈን ከኢህዴግ ግዜ ጀምሮ ተደጋግሞ የሚፈፀም ድራማ ሆኗል፣ ይህ በግልፅ ለፍትህ ስርዐቱ ያለ ቸልተኝነት ማሳያ ነው።
ወደፊትም የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ፍትህ ጠባቂዎች ጉዳያቸው በፍጥነት ታይቶ እንደሚፈቱ ተስፋ አደርጋለሁ።
ጋዜጠኞቹን "ሶስት አመት አቆዩዋቸው" የሚል ትእዛዝ ከበላይ መጥቷል የሚል መረጃ አለ፣ እውን የፍትህ ሚኒስቴር ይህን ያውቀው ይሆን?
@EliasMeseret
#ጥቆማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተታለው ሚያንማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ በቻይና የወንጀለኞች/ጋንግ ቡድን ተይዘው እየተሰቃዩ ይገኛሉ
ውጭ ጉዳይ በቅርቡ ሲጠየቅ "የት እንዳሉ ለማወቅም አስቸጋሪ ሆኗል" ብሎ የሰጠውን ምላሽ አየሁ። አድራሻቸው ጠፍቶ ከሆነ እዚህ ይገኛሉ:
https://maps.app.goo.gl/CHHduoAGAVs4dx8J9
በነገራችን ላይ የስሪላንካ መንግስት ሙሉ በሙሉ ዜጎቹን ነፃ አስወጥቶ ወደ ሀገራቸው መልሷል፣ የእኛዎቹ ግን አሁን ድረስ በኤሌክትሪክ ሽቦ እየተገረፉ እና ካለ ክፍያ በቀን እስከ 16 ሰአት እንዲሰሩ እየተደረጉ ይገኛሉ።
@EliasMeseret
የዚህች ህፃን ልጅን ለቅሶ ተመልከቱ...!
ጎንደር አካባቢ ይቺን ልጇን ይዛ ወላጆቿን ለመጠየቅ የሄደች እናት ከቤተሰቦቿ ቤት ታግታ ተወስዳ 1 ሚልየን ብር ተጠይቆባታል። ህፃኗ እንዲህ ስታለቅስ ውላ ታድራለች፣ ቤተሰብ እንኳን 1 ሚልየን ብር ኖሮት ሊከፍል ብሩ ሲጠራ እንኳን ምን ያህል ገንዘብ እንደሆነም አያውቁም።
ድሀው ህዝብ እንዲህ እየተሰቃየ እየኖረ ነው።
በእውነት ይደክማል!
Via መሠረት ሚድያ/ነብዩ ሲራክ
@EliasMeseret
ሰዎች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት አካባቢ በሁለት እና ሶስት ቀናት አጣድፎ እና ቤት አፍርሶ ማባረር፣ ለሰራተኞች ለሁለት እና ሶስት ወራት ደሞዝ አለመክፈል፣ የአካል ጉዳተኞችን እና የ15 አመት ህፃናትን ጭምር አፍሶ ወስዶ ለመልቀቅ በብር መደራደር... ከሰሞኑ ግፎች በጥቂቱ።
የጥቁር ህዝብ የነፃነት ምሳሌ የሆነው ኢትዮጵያዊ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ህብረቱን አጥቶ በአንድነት ድምፁን ማሰማት አቅቶታል።
እሱ እንዳለ ሆኖ ይህን የሚያዙት እና ሚያስፈፅሙት አካላት ግን ቤተሰብ የላቸውም? ልጆች የሏቸውም? ሰብአዊነት አይሰማቸውም?
#FoodForThought
@EliasMeseret
እጅግ አሳዛኝ፣ አፀያፊ እና ሁላችንም ልናወግዘው የሚገባ ድርጊት ሰላሌ ላይ እንደተፈፀመ ታውቋል
የሰው ልጅ ላይ የዚህን ያህል ጭካኔ ለምን? ምን እየሆንን ነው? የነዚህ ግፎች መጨረሻ መቼ ይሆን?
ነፍስ ይማር!
@EliasMeseret
አዲስ አበባ ገና ፓሪስን አልመሰለችም፣ ወደፊት ግን ልትመስልም... ልትበልጥም ትችላለች!
ግን ኢቢሲ ህዝብ በሚሊዮኖች በሚራብበት፣ በሚገደልበት፣ በሚፈናቀልበት እና በሚሰደድበት ወቅት የቁንጅና ውድድር ይመስል ከተማ ለከተማ መልክ ሲያወዳድር የሚውል ሚድያ ሆኖ አረፈው?
ይህ ነው የኢቢሲ 'አዲሱ አቀራረብ' ተብሎ በስፋት ሲተዋወቅ የከረመው?
#ሙያውንአታርክሱት
@EliasMeseret
ከውጭ ጉዳይ እንዳጋራው የተላከልኝ ነው
የእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛና ዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የምትችሉ እና ዕድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መመዝገብ ትችላላችሁ
አይ ኢቢሲ Fact Check፣ አይ ማስተባበል!
ክስተቱን በአይን ያዩ የኤርፖርት ሰራተኞች፣ የሲቪል አሺዬሽን ባለሙያዎች፣ የአየር መንገድ ባልደረቦች እና አንዳንድ ተጓዦች ጭምር እውነት እንደነበር ትናንት አረጋግጠውልኝ ነበር።
ለማስተባበል የተሄደበት "ልምምድ ነበር" የሚለው ምላሽ ይባስ ብዙ ጫና ላይ ያለውን አንድ ለእናቱ የሆነውን አየር መንገዳችንን ሌላ ችግር ላይ መጣድ ነው።
ደሞ ልምምድ የሚደረገው በፕሮግራም በአየር ጦር ቤዝ እንጂ ኤርፖርት ገብተው ሊሳፈሩ check in ያረጉ ሰዎችን ወደ ቤታቸው መልሰህ ነው እንዴ?
ይህን ውሸት ሰምተን ሌላ ምን ቢነግሩን እንመን?
@EliasMeseret
አብዛኞቻችን ጋዜጠኞች የማህበረሰቡን ጉዳይ አጀንዳ ማድረግ አልቻልንም። We are failing our society!
ለብዙ ዜጎች የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ቅዳሜ እና እሁድ ኢቢኤስ ላይ የምናያት አይደለችም፣ ግን እሱን እስክትመስል አብረን መታደምን መርጠናል።
Praying for better days!
@EliasMeseret
Thank you, America!
የእነዛ በርሀብ የተጎዱ ምስኪን ህፃናት ምስል ከአእምሮ አይጠፋም።
/channel/meseretmedia/731
#መልካምዜና ሚያንማር ውስጥ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማውጣት እንቅስቃሴ ተጀምሯል
በቅርቡ ያጋራሁትን ይህን ከታች የሚታይ ካርታ መነሻ በማድረግ ምርመራ እንደተደረገ እና በቻይና ጋንግ ቡድን ታግተው የሚገኙትን 1,300 ገደማ ዜጎች ለማውጣት የውጭ ጉዳይ አንድ ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ ታውቋል።
ይሁንና እኔ ካጋራሁት ቦታ በተጨማሪ ሌሎች ስፍራዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። በእነሱ ዙርያ ምንም እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ አሳውቀውኛል ስለዚህ ለክትትል እንዲመች ቦታዎቹን ከታች አስቀምጣቸዋለሁ።
@EliasMeseret
1. "30 አመት ውጪ ሀገር ታክሲ እየሰራህ እዚህ መጮህ አይቻልም..."
2. "ዛሬ የአሜሪካንን ድሪም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ችለናል..."
... አለ አፍሪካን የሚወክል ሚድያ አዲስ አበባ ላይ ላቋቁም ነው ብሎ ከመንግስት በተሰጠው ሁለት ሰፋፊ ቦታ ከባድ ጆካ የተጫወተው ወንድማችን... አሜሪካን ሀገር Seattle ከተማ ላይ ደግሞ የገዛውን ጭውቴ እናውቃለን።
#የዛሬይቱኢትዮጵያ
በሰፊው እመለስበታለሁ...
@EliasMeseret
https://youtu.be/SazvQ0MBdUs?si=Nc5iVBj9H-NqKALN
Читать полностью…
አስታራቂ አይጥፋ!
Peace is what we need.
@EliasMeseret
ከሰሞኑ የሰማነው የተወሰኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) አባላት ሰላም መምረጥ ተስፋ ይሰጣል
አካሄዱ ላይ ግን ጥንቃቄ ካልተደረገበት ውጤቱ ከታሰበው በተቃራኒ እንዳይሆን ያሰጋል።
ዛሬ ጠዋት ስልኬን ስከፍት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልብስን የለበሱት ጃል ሰኚ ነጋሳ መግለጫ ሲሰጡ ተመለከትኩ። "በምን አግባብ?" የሚለው ትልቁ ጥያቄዬ ነበር፣ ምክንያቱም የሰራዊቱ አባል ያልሆነ ሰው ልብሱን ለብሶ ከተገኘ እንደ ከፍተኛ ወንጀል ስለሚቆጠር።
በርካቶች ይህን ሁኔታ አይተው "ቀድሞውም እኮ አንድ ነበሩ" እና "ቁስል እንኳን ሳይደርቅ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?" የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ እንደሆነ ታዘብኩ።
መንግስት ከጥቂት ሳምንታት እና ወራት በፊት በግድያ፣ በዝርፊያ፣ በእገታ እና በሽብር ሲከሰው ከነበረው አካል ጋር ስምምነት ሲፈፅም ረጋ ተብሎ እና በሰከነ ሁኔታ ካልተያዘ ጉዳት የደረሰባቸው እና በተለይ አሁን ድረስ ከታጣቂዎቹ ጋር በዱር በገደሉ ተፋጠው ላሉ የመንግስት ፀጥታ አካላት የሚያስተላልፈው መልዕክት ያሰጋል።
አለም አቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ከሁሉም በፊት የሚቀድመው የተሀድሶ ፕሮግራም ነው።
ሰላም ለሀገራችን።
@EliasMeseret
መንግስት 'ዋልታ' የተባለን ሚድያ ለማጠፍ መወሰኑ ይበል ያሰኛል፣ ጥቂት የሚባሉ መልካም ጋዜጠኞች ቢኖሩትም ከውልደቱ እስከ ሞቱ የፕሮፖጋንዳ እና ህዝብን የማጥቂያ መሳርያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል
ከአመት በፊት ፋና እና ዋልታ ሊዋሀዱ እንደሆነ አንድ መረጃ ባቀረብኩበት ወቅት የቀድሞው የዋልታ ስራ አስፈፃሚ መረጃው 'ሀሰት' እንደሆነ ተናግሮ ነበር።
ስራ አስፈፃሚው አክሎም "የቀረበው ሃሳብ ተራ አሉባልታ ከመሆኑም ባሻገር ከጀርባው ብዙ ሴራ ያዘለ ነው" ብሎት ነበር። ዛሬ ግን ራሳቸው በይፋ ተዋህደዋል እያሉን ነው።
ግዜ ደጉ...
@EliasMeseret
ከሰሞኑ ወጣቶች በብዛት ከየመንገዱ እየታፈሱ መጋዘን ውስጥ እየታጎሩ እንደሆነ መረጃ ስናቀርብ "ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ነገር ፈፅሞ የለው" ብለው ነግረውን ነበር
አሁን ላይ ግን ውሸቱን መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ "በፍቃደኝነት የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ካምፕ ገቡ" ብለው ዜና ይሰሩባቸው ይዘዋል።
ዩኒቨርስቲ፣ ሙያ ማሰልጠኛ፣ እርሻ ወይም ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ሊሆኑ የሚገባቸውን ወጣቶች ወደ #እሳት!
@EliasMeseret
ሌላ አሳዛኝ እና ሁላችንም ልናወግዘው የሚገባ የዘጠኝ ንፁሀን ሰዎች ግድያ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ትናንት ለሊት እንደተፈፀመ ታውቋል
ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም "ነፍስ ይማር" እያልን መኖር ነው። መቼ ይሆን የንፁሀን ግድያ የሚያበቃው?
ዛሬም ነፍስ ይማር!
@MeseretMedia
በመጪው የትረምፕ አስተዳደር ብዙ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከተው የኢሚግሬሽን ጉዳይ ዙርያ በአሜሪካ ሀገር የኢሚግሬሽን የህግ ባለሙያ ከሆነው ከአቶ ሙሉአለም ጌታቸው ጋር ያደረግኩት አጭር ቆይታ:
https://youtu.be/bW0VdKHE5yw?si=QbFZeO4N86mQ_NWH
ይህ የ40/60 ህንፃ ቦሌ አያት 2 ብሎክ 38 ይባላል
ዕጣ ከወጣበት ሁለት አመት ሊሞላው ሲሆን ባለ 13 ፎቁ "ህንፃ" በሚያሳፍር እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ተሰርቶ ቆሟል። እስካሁን ከ8ኛ በላይ ያለው የውስጥ ለውስጥ partition የሌለው፣ መወጣጫ ደረጃው ያላለቀ፣ የውስጥ ልስን የሌለው እና ጣራው ያልተመታ ነው። ህዝብ ግን የንግድ ባንክ ክፍያውን ቤት አገኝ ብሎ እየከፈለ ነው።
ህንፃው ውስጥ ሰው ገብቶ አስከፊ አደጋ ሳያደርስ በፍጥነት መፍትሄ ያስፈልገዋል።
@EliasMeseret
የ33 አመት እድሜ ያላት ሶማሊላንድ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ አድርጋ አዲስ ፕሬዝደንት መርጣለች
እኛ የ3 ሺህ አመት ስልጣኔ ያለንስ?
@EliasMeseret
ችግር መኖሩን አምኖ "ለማስተካከል እየሰራን ነው" የሚል ሳይሆን በዚህ መልኩ ፈጦ የሚታየውን እውነታ የሚክድ አካሄድ መኖሩ መጪው ግዜ ከባድ የመሆኑ አንድ ማሳያ ነው
ለመሆኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ትናንት የህዝብ አፈሳ መረጃ "ሀሰት ነው፣ ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን" ብሎ ምነው በዛው ቀረ? 🤔
@EliasMeseret
የእናንተው የሆነውን፣ ለእናንተው የተከፈተውን መሠረት ሚድያን ይከታተሉ። ወደፊት ወደ ሳተላይት ጣብያነት ተቀይሮ የምታዩት ይሆናል ⤵️
meseretmedianews?si=JwzjZsQgHfCDXQwl" rel="nofollow">https://youtube.com/@meseretmedianews?si=JwzjZsQgHfCDXQwl
መረጃን ከመሠረት!