gospel_of_god | Unsorted

Telegram-канал gospel_of_god - የእግዚአብሔር ወንጌል

2967

Subscribe to a channel

የእግዚአብሔር ወንጌል

"...You must find its significance in the ultimate portrait of God's work of redemption and rescue. If you don't, you are settling for something far less significant, and you have completely missed your greatest need."

__Voddie Baucham (Rescue)
(Thank you God for Brother Voddie’s life and ministry!!)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

And can it be that i should gain
An int'rest in the Savior’s blood?
Died He for me, who caused His pain?
For me, who Him to death pursued?
Amazing love! How can it be
That Thou, my God, should die for me?

Amazing love! how can it be
That Thou, my God, should die for me!

He left His Father’s throne above,
So free, so infinite His grace;
Emptied Himself to show His love,
And bled for Adam’s helpless race.
‘Tis mercy all, immense and free;
For O my God, it found out me.

Long my imprisoned spirit lay
Fast bound in sin and nature’s night;
Thine eye diffused a quickn’ing ray,
I woke, the dungeon flamed with light.
My chains fell off, my heart was free;
I rose, went forth and followed Thee.

No condemnation now I dread;
Jesus, and all in Him is mine!
Alive in Him, my living Head,
And clothed in righteousness divine;
Bold I approach th’ eternal throne
And claim the crown through Christ, my own.

Hymns of Grace (Hymn180)
Written by: Charles Wesley

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ መሆን ታላቅ በረከት ነው። እርሱ ቸር፣ መልካም፣ ባለሞገስ ብቻ ሳይሆን የአጽናፈ ዓለም ሁሉ አምላክ ነው። ባህሪው ፍጹም፣ ፍቅሩ ዘላለማዊ፣ ኃይሉ ወደር የሌለው፣ ጥበቡ የማይመረመር፣ ቸርነቱ የማይነጻጸር ነው። ...
ለዘላለም ንጉሥ ባሪያ መሆን እንዴት ያለ ደስታና መታደል ነው! በክብሩ ብርሃን ፊት ሐሴት እያደረግን በአክብሮትና በፍቅር ከልባችን ለዘላለም ውዳሴን እናቀርባለን። ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነው ስሙ በግንባራችን ይጻፋል። ከኃጢአታቸው በደሙ ቤዝዎትን ካገኙ ቅዱሳን ሁሉ ጋር ለእርሱ እንድንሆን ስለመረጠን መገረማችንን አናቆምም።
ከነገሥታት ንጉሥ ጋር ከመሆን የበለጠ ክብር የለም!!

__John MacArthur (Slave)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ሃይማኖታዊ ህይወትህ ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ አድርጎ ከሌሎች የተሻልክ መሆንህን ከጠቆመህ አጋንንት እየተጫወቱብህ እንደሆነ ማወቅ አለብህ።

__ሲ ኤስ ሉዊስ(Amanuel Assegid እንደተረጎመው)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ቅዱሳት መጻሕፍት እኛን እንደ እግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ እንደ ሰማይ ዜጎችና እንደ ዓለም ብርሃናት አድርገው ይገልፁናል።
አዎን! የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከክርስቶስ ጋር ወራሾች፣ የአካሉ ብልቶች፣ በመንጋው ያለን በጎች፣ የአገልግሎቱ አምባሳደሮች እና በጠረጴዛው ዙሪያ ያለን ወዳጆች ነን። እንደ አትሌቶች እንድንወዳደር፣ እንደ ወታደሮች እንድንዋጋ፣ በወይኑ ግንድ እንዳሉ ቅርንጫፎች እንድንኖርና ለቃሉ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት እንድንሆን ተጠርተናል። እነዚህ ሁሉ መግለጫዎች ክርሰቲያን መሆን ማለት ምን እንደሆነ እያንዳንዳቸው በራሳቸው መንገድ ያስረዱናል።

__John MacArthur (Slave)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እውነተኛ ክርስትና ኢየሱስን 'በራስ' ሕይወት ውስጥ መጨመር አይደለም። ክርስትና በሁለንተና ለእርሱ ማደር፣ ለፈቃዱ መገዛት እና ከምንም በላይ እርሱን ማስደሰት ነው። ይህም [የቱንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል] ለራስ ሞቶ ጌታን መከተል ይጠይቃል።
በሌላ አነጋገር ክርስቲያን መሆን ማለት የክርስቶስ ባሪያ መሆን ነው።

  __John MacArthur (📖-Slave)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ቅዱሳት መጻሕፍት መንግስተ ሰማያት የማያልፍ ደስታ፣ የማይነጥፍ ክብር፣ ፍጹም ሐሴት፣ መሉ ፌሽታና ዘላለማዊ ተድላ መሆኑን ደጋግመው በግልጽ ያሳዩናል።
በዚያ ምንም ነገር አሰልቺ ወይም ደባሪ ሊሆን አይችልም። ፍጹም ሕልውና ይሆናል። ከሰማይ ሰራዊት ጋር ዘላለማዊ ህብረት ይኖረናል። ሀዘን፣ ጭንቀት፣ እንባ፣ ፍርሃት፣ ወይም ህመም የሌለበት ይሆናል።

__John MacArthur(1939-2025)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እግዚአብሔርን ማምለክ፣ ከእርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ ደግሞም ማንነቱ ይበልጥ ማወቅ ከፈለግን አእምሯችንን ከቃሉ ጋር ማስማማት አለብን። ከመለኮታዊ መገለጥ ውጭ እግዚአብሔርን ለማወቅ የምናደርገው ሙከራ ሁልጊዜ ከሽፏል።

—Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ለቅዱሳት መጻሕፍት መገዛት ለእግዚአብሔር መገዛት ነው። በቅዱሳት መጽሐፍት ላይ ማመጽ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነው።

    __Kevin DeYong

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ቤተክርስቲያን በሚፈራርሱ ባሕሎች መቃብር ላይ ትቆማለች። ኩሩው የግሪክ ግዛት የት አለ? [ሀያል የነበረው] የሮማ ግዛት የት አለ? የሶቪየት አገዛዝ የት አለ?  ፖል ፖት (Pol Pot) የት አለ? እነዚያ [በዘመኑ አስፈሪ የነበሩ] ሰዎች የት አሉ?  እነሱ ጠፍተዋል።
ክርስቶስስ የት አለ? በዙፋኑ ላይ! አየህ?  ነግሧል!! አዎን ቅዱሳን ሆይ ዝንባሌያችሁን ከፍ አድርጉ፤ አምላካችሁ ንጉሥ ነው። እርሱ እውነተኛ ፍቅር፣ የተሰቀለው በአብ ቀኝ ነግሧል። ቅዱሳን ዓይኖቻችንን ከአሁኑ ስርዓትና ከፖለቲካዊ ሃያልነት አውጥተን በዙፋኑ የምናተኩርበት ጊዜ ነው። የሁሉ በላይ ነግሧል። ከዙፋኑ ግርማ ስር የሁልጊዜ ጉዳዮች [ከፍ ከፍ ብለው የሚታዩ] ሁሉ ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ እናስታውስ።

—Alistair Begg

#መልካም_ሰንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እግዚአብሔር ካለን፣ ችግር በሕይወታችን ምን ያህል ጊዜ እንኳ ብቆይ ምንም ማለት አይደለም። እርሱ እግዚአብሔር ዘላለማችን ነው፤ ደግሞም ለዘላለማችን በቂ ነው።

     —Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

“ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል?
በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።“ መዝ 119፡9

በንጽሕና መኖር የማይፈልግ የለም፡፡ ተረትተን እንሸነፍ እንደሆነ እንጂ ሆነ ብሎ የማይወደውን ሕይወት መኖር የሚፈልግ ብዙ አይመስለኝም፤ በቀመር ክፋትን የሚለማመድ ቢኖርም ቅሉ፡፡

መንገዴን እንዴት አነጻለሁ? እንዴት ነው በታማኝነት መኖር የምችለው? እንዴት ነው ሞራሊ ብቁ ሕይወት መምራት የምችለው? እንዴት ነው ነቃፋ የሌለበት ሕይወት መኖር የምችለው? እንዴት ነው ጸጸት አልባ ሕይወት መምራት የምችለው?....... እያልን ጥያቄዎችን ብንደረድር፤ መልሱ አንድ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወይም በእግዚአብሔር ቃል መሠረት በመኖር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት፣ በማሳላሰልና ዕለት ተዕለት በመታዘዝ ነው፡፡ ምርጫዎቻችንን፤ ውሳኔዎቻችንን በቃሉ መሠረት በማድረግ፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ይርዳን!

__Yonatan Simon

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

በኃጢአት የወደቀ ሰው ልበ ስውር ነው። ሰይጣን ልቡን የሚቆጣጠረው ነው። (የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። 2ቆሮ 4V4) በጉልበት፣ በዘዴ፣ በትምህርት በመሄድ መላቀቅ አይቻልም። የመገለጥ ብርሃን እስካላገኘ ድረስ በውርቅ ብታሽቆጠቁጠው፣ በድንቅ ነገሮች ብትከበው፣ [ሁሉም ቦታ] ብትወስደው፣ የዓለምን [ድንቃ ድንቅ] ነገሮች ብታስረክበው ምንም ነው፤ በጨለማ የተያዘ ሰው የታሰረ ነው።
ነገርግን "በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፡” ያለ እግዚአብሔር ነውና። (2ቆሮ 4V6)
እግዚአብሔር ራሱ በሰው ልብ ይበራል!!

     __ሰለሞን አበበ ገብረመድህን

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ለክርስቶሱ ያልተኖረች ነፍሴ ረብ የለሽ ናት።
ለእግዚአብሔር መንግሥት ያልፈሰሰ ጉልበቴ የባከነ ነው።
ለእግዚአብሔር ክብር ያልተኖረ ዕድሜዬ ከንቱ ነው።
ወንጌለ መለኮትን የማይሰብክ እስትንፋሴ ቃና ቢስ ጩኸት ነው።
ለኢየሱስ ጌታነት ያልታመነ ኑሮ ሊኖር ያልተገባው ነው።
እጅግ አስፈላጊው ደግሞም አንገብጋቢው ጉዳይ በምንኖራት አንዲት ሕይወት በፍርድ ቀን የማናፍርበት ምልልስ ይኖረን ዘንድ ወደ ፍጽምና በእምነት ኃይል መጓዝ ነው። ዝለት፣ ሞኝነት እና ክፋት ሲከብበን በኑዛዜ መንገድ ኅብረትን በማደስ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኘው ጎዳና መገስገስ ነው። በዚህች እንደ ዕንፋሎት በምትተንን ሕይወት ልናደርገው የምንችል ዘላለማዊ ፋይዳ ያለው ነገር ይህ ብቻ ነው።

__Tesfatsion Alemayehu

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እግዚአብሔር በሁሉም ነፃ ምርጫዎቻችን፣ ውሳኔዎቻችን እና በሁሉም ኃላፊነት በምንወስዳቸው ነገሮች ውስጥ በመግቦቱ እየሰራ ነው።

__Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

በእርሱ [በክርስቶስ] መባረክ፣ እንደ ባለጠግነቱ መጠን በዋጋ ሊተመን በማይችል ስጦታ መበልጸግ ከፍቅር የመነጨ የደግነት [ውጤት] ነው። በምላሹ ለምስጋና ራስን መፍቀድ ከሁሉም የበለጠ ጣፋጭ ነው።

   __Charles Spurgeon

#መልካም_ሠንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

"ኃጢአት ጨካኝና ጨቋኝ የባሪያ ጌታ ነው፤ ክርስቶስ አፍቃሪና መሐሪ ነው። የኃጢአት ቀንበር ከባድና አስጸያፊ ነው፤ የክርስቶስ ቀንበር "ልዝብ፣" እና ሸክሙም ቀላል ነው።”(ማቴ.11V30) ኃጢአት ባሪያዎቹን በጨለማና በሞት አጥምዶ ይይዛቸዋል፤ ክርስቶስ በእርሱ ላሉት ሁሉ በብርሃኑ ሕያዋን አደረጋቸው። (ቆላ 2V13 ) ኃጢአት ወደ ጥፋትና ስህተት ይመራል፤ ክርስቶስ “መንገድና እውነት ሕይወትም ነው።”( ዮሐ 14V6 ) የኃጢአት ባርነት ጥላቻ፣ ስብራት፣ ፍርሃትና ውርደት የተሞላ ስሆን የክርስቶስ ባርነት በልካምነት፣ በክብር፣ በሐሴት፣ በእውነትና በቅንነት የተሞላ ነው።

..."ክርስቶስ ኃጢአትንና ሰይጣንን በመስቀል ላይ ድል ነሥቷል። በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሙሉ ቅጣት ተቀብሏል። የእርሱ ሞት ከኃጢአት፣ ከኩነኔ እና ከፍርሃት ነፃ አውጥቶናል።"

..."ከኃጢአት አርነት ወጥተናል። ማለትም ለመታዘዝ፣ በጽድቅ ለመኖር እና ቅድስናን ለመከተል ነፃ ወጥተናል። [አሁን] የክርስቶስ ባሪያዎች ነን።
በጣም አስደማሚውና አስደናቂው ነገር ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ መሆን እውነተኛ ነፃነት ነው።"

__John MacArthur (📖 Slave)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

የክርስቲያን ሕይወት እውነተኛ ፈተና ሁሉንም የማይመቹ ሁኔታዎችን ከሕይወታችን ማስወገድ ላይ ሳይሆን፥ በሁሉም ሁኔታዎች መኻከል ሉዓላዊውን፣ ጥበበኛውን፣ ጥሩውን እና ኃያል አምላክን ማመን ላይ ነው።

    __John MacArthur

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

"ቅዱስ እግዚአብሔርን መውደድ ከሥነ ምግባራዊ ኃይላችን (ተፈጥሯችን) በላይ ነው። በኃጢአተኛ ተፈጥሮአችን ልንወደው የምንችለው ብቸኛው አምላክ እርኩስ እና በገዛ እጃችን የሰራነው ጣዖት ነው።
በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተወለድን በቀር፣ እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን ካላፈሰሰ በቀር፣ በጸጋው ልባችንን ሊለውጥ ካላጎነበሰ በቀር፣ እርሱን [ቅዱስ እግዚአብሔርን] መውደድ አንችልም።
ቅዱሱን እግዚአብሔርን ለመውደድ የደነደነውን ልባችንን ለመለወጥ እና ሟች ነፍሳችንን ለማንቃት ፀጋ ያስፈልጋል።"

  __R.C. Sproul (Holiness of God)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

No Gospel, No Salvation!

__John MacArthur

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

⨳ለእኛ ክርስቲያኖች በጣም ወድ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በሰማይ ነው ያሉት። በዚያ፡
-አብ አለ (ማቴ. 6V9)።
- ኢየሱስም በአብ ቀኝ ተቀምጦ (ዕብ. 9V24)
-ብዙ ወንድሞችና እህቶች አሉን (ዕብ.12V23)።
- ስማችን በዚያ እዚያ ተመዝግቧል
(ሉቃስ 10V20)
- ርስታችን እዚያ ነው(1ጴጥ.1V4)።
-ዜግነታችንም የሰማይ ነው። (ፊልጵ. 3V20 )
- ዋጋችን በሰማይ ነው (ማቴ.5V12)።
በሌላ አነጋገር ለዘላለም ልንወደው የሚገባን፣ ወድ ዋጋ የሚንሰጠው እና የዘላለም ወጋ ያላቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ነው።

__John MacArthur(1939-2025)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

What the Cross Means to God (Selected Scriptures)
https://youtube.com/watch?v=wFjFegGNiFA&si=BG3Gfwj2Qgnq-vgP

WHAT THE CROSS MEANS TO GOD

# The most important aspect of the cross is not about you. Christ died for us, yes primarily Christ died for God (Romans 11v33-36, 1peter 4V11)
~ In the work that Christ did, God was glorified.
John 17 “he came into the World to glorify the Father”
John 12V27&28,
~Jesus came into the world to do the Father’s will. He came into the world to seek the Father’s glory.
⨳When we think about the cross:-
1- The death of Christ was a sacrifice to God (Hebrews 9V12, 14, 26, 28)...

2- The death of Christ was not only a sacrifice to God, it was a submission to God (Hebrews 10V5 -10, John 10V17 Romans 5V19)
⨳The submission of Christ to the will of God provided righteousness for us....
# Think about it this way :
Jesus lived for God
He loved for God
He worked for God
He believed for God's hono
He worshipped for God's honor
He preached for God’s honor
He healed for God's honor
Every word he spoke was for God's honor
Every thought he had was for God’s honor
Every deed he did was for God’s honor
⨳He submitted to him in all things and it culminated in death.
# The death of Jesus Christ was a sacrifice for God and a submission to God. ...

3- The death of Christ was a substitution to God (Hebrews 9V28, 2cor 5V14, 21 1peter 2V24)
~He was innocent, but he did in the place of the guilty. He was punished by God. He died as God’s chosen substitute.
~God had determined that the penalty for sin is death, Christ endured that penalty for his people willingly.
~Jesus Christ satisfied the justice of God by absorbing all punishment in three hours of darkness on Friday afternoon in Jerusalem.

4- Christ's death was a satisfaction to God. Satisfied divine justice.
~Justice had to be satisfied, and it is satisfied in the death of Christ = propitiation
Propitiation (Romans 3V25, 1john 2V2, John 4V10
# Propitiation = satisfaction
~God’s holiness required wrath. Jesus satisfied the wrath of God, satisfied justice...
# All of that leads to another wonderful reality.
~His death was a salvation for God
⨳Why is the lord gathering redeemed people? Why is he saving sinners?
-They come to heaven and glorify him forever.
We're bought with a price therefore glorify God. …

ከ John MacArthur ስብከቶች  ውስጥ መጀመሪያ ከሰመኋቸውና ይበልጥ እንድሰመው ደግሞም ጽሑፎቹን እንዳነበው ምክንያት የሆነው ስብከቱ ይህ ነበር። "What the cross means to God" በዚህም ስብከት የክርስቶስ መስቀል ቀዳሚ ግብ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ያገኙት በረከት ሰይሆን የእግዚአብሔር ክብር እንደሆነ ያብራራሉ። መስቀልን ከእኛ ከአማኞች አንጻር ሳይሆን ከእግዚአብሔር አንጻር፣ መስቀል ለእግዚአብሔር ምን እንደሆነ ስነ መለኮታዊ ገለጻ ይሰጣሉ። በዚህ ስብከት የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በማንሳት በተደራጀና ግልጽ በሆነ መልኩ የወንጌልን እውነት ይሰብካሉ።
እኔ ለራሴ ያስቀረውትን በጥቅቱ ከላይ አስቀምጬላችኋለሁ። ሙሉ ስብከት ብትሰሙ በብዙ ታተርፋላችሁ።
መጋቢ John MacArthur ላለፉት 50+ አመታት በ Grace Community Church በመጋቢነት፣ በGrace to you በኩል በማሕበራዊ ሚድያ፣ በ150+ መጽሐፎች እና ጽሑፎች፣ የተለያዩ ተቋማዊ አገልግሎቶችን በትጋትና በታማኝነት በማይዋዥቀው አቋማቸው የእግዚአብሔርን ወንጌል ፈጽመው በመስበክ አያሌ ትሩፋቶችን በመተው ወደ ሙሉ ደስታ ገብተዋል።
Thank you, God for the life and faithful ministry of John MacArthur!

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

የእግዚአብሔር መግቦት ሁልጊዜ በሁኔታዎች ግልጽ አይደለም። ነገር ግን ኋላችችንን ስንመለከት የእርሱን ጽኑ እጅ እንመለከታለን። እርሱን እመኑት። እርሱ ፍጹም አይዘገይም፣ በጭራሽ አይሳሳትም ደግሞም አይቀርም።

__Dustin Benge

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

አይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ
ወደየት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ

የሕይወቴ ሰላም ሁሌ የሚፈልቅበት
ከጭንቀት ሁሉ ልቤ የሚያርፍበት
ሀዘን ከእኔ ርቆ ደስታን የማገኘው
አይኖቼን አንስቼ መስቀልህን ሰይ ነው
አይኔን የጣልኩበት ከመስቀልህ ሌላ
ዘለቄታ የለውም ጠፍ ነው በኋላ
አለሙም ምኞቱም ሁሉም ያልፋልና
እርዳኝ የኔ ጌታ ባንተ እንድጸና

ሰላም  እረፍት መታደስ የማገኝበት
ስብራቴ የሚጠግንበት
አይኖቼን ወደ አንተ አነሳለሁ
መስቀልህን አያለሁ ...

__Zema for Christ

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ቃል ሥጋ የሆነው ለእግዚአብሔር ክብር ኃጢአትን ለመደምሰስ ነበር።

    __Stephen Nichols

#መልካም_የልደቱ_መታሰቢያ!!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እኔን የጠፋሁትን ፍለጋ መጥተህ ነፍሴን ከኃጢያት ባርነት ፤ ከዘለአለም ሞት እሳት አድነኃታል  ።  እኔኑ ፍለጋ መጥተህ እዳዬን ከፍለህ ተቤዥተኸኛል!  ክብር ለስምህ ይሁንንን!🤲   
Have a good Lord's day !🖤

__Esther Esek

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

የእምነት ሕይወት የሚፈልገው የራሱ ነገር አለው። የሚናፍቀው ነገር አለው። ባገኘሁት፣ በነካውት፣ በተገለጠና በያዝኩት ብሎ የሚመኘው ነገር አለው። [ይህም] ሰማያዊው ነገር ነው።

__ሰለሞን አበበ ገብረመድህን

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

ኢየሱስ የኖረውም የሞተውም ለታሰሩት ነፃ መውጣትን፣ ለዕውሮች ማየትን፣ ለተሰበሩት መፈወስን፣ ለኃጢአተኞች  መዳንን ልሰጥ ነው።

      —Alistair Begg

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

"ስለ ሥጋ ማሰብ" አእምሯችን ግራ በሚያጋባ ሐሳቦች ይሞላል፤ ፍርሃት፣ ሀሳብ፣ ጭንቀት፣ ምኞት ደግሞ ወደ ሁከት፣ ጨለማና ግራ መጋባት ውሰጥ ይጥሉናል። “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና” (ሮሜ 8V6)። ነገር ግን አሳባችን በኢየሱስ ላይ ስናደርግ ልባችን የተቀደሰ፣ የተረጋጋ ይሆናል። አእምሯችንና ልባችን በእግዚአብሔር ሰላም ይጠበቃል። “ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።” (ሮሜ 8V6)

       —Alistair Begg

#መልካም_ሰንበት!

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…

የእግዚአብሔር ወንጌል

እያንዳንዱ የትላንት ጊዜ፣ የአሁኑ ጊዜ እና የወደፊት ጊዜ የምንለው የጊዜ ሰሌዳ የራሱ የሆነ ምስጢር አለው። እያንዳንዱ የጊዜ ሰሌዳ የራሱ በቂ ጭንቀት አለው። ደግሞ እያንዳንዱ የጊዜ ቀመር፥ በሕይወት ውስጥ መነሳት ወዳለበት የመጀመሪያም የመጨረሻም ወደሆነ ጥያቄ ይመራናል። እና ለዚህ ጥያቄ አንድ መልስ ብቻ አለ! ዘለዓለማዊው እርሱ!
ጊዜን ሁሉ ጠቅልሎ የሚውጠውን ኋይል የሚልቅ ኋይል አለ! ዘለዓለማዊው እርሱ! የነበረውና ያለው፣ የሚመጣውም መጀመሪያውና መጨረሻ የሆነ! እርሱ ለትላንትናችን ይቅርታ ይሰጠናል፣ እርሱ ለሚመጣው ድፍረት ይሰጠናል። እርሱ
በዘላለም መገኝቱ ውስጥ ዕረፍትን ይሰጠናል።

__ማንደፍሮ ማሩ (የሕላዌ እንቆቅልሽ)

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God

Читать полностью…
Subscribe to a channel