bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

-

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses' Students! www.bdu.edu.et Contact @bdu_tana_bot

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

የጥሪ ማስታወቂያ
በ2015 ዓ/ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ“Remedial” ፕሮግራም ለመከታተል ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም #አዲስ_ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

(የካቲት 20/2015) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ሳይንስ ኮሌጅና በግሽ ዓባይ ግቢ አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን የተማሪዎች ቅበላ ግብረ-ሃይል ከተማሪዎች ዲን፣ ከስምሪትና ትራንስፖርት ክፍል እና ከተማሪዎች ህብረት የተውጣጣ ቡድን እየተቀበለ ነው፡፡

አዲስ ከሚገቡ ተማሪዎች መካከልም ከማቻከል ወረዳ፣ ሸለል ቀበሌ የመጣ፣ ተማሪ መኮነን አዲስ ከመናኸሪያ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በአውቶብስ እንደመጡ እና አቀባበሉ ጥሩ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሌላዋ ከደብረዘይት ቢሾፍቱ ከተማ የመጣችው ተማሪ ገሊላዊት እንደሻው ስትሆን በር ላይ አስተባባሪዎች ሻንጣቸውን ተቀብሎ እንዳስገቧቸውና በታም ደስ የሚል አቀባበል ዩኒቨርሲቲው እንዳደረገላቸው፣ ምግቡም እንደተመቻት እና ዶርማችንንም አዘገጃጅተን ጨርሰናል። አሁን የቀረን ግቢውን ማየት ነው በአጠቃላይ አቀባበሉ በጣም እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡ ከሰሜን ወሎ ዞን የመጣው ተማሪ ድስታው ተመስገን አቀባበሉን ከጠበቅኩት በላይ ነው ያገኘሁት በጣም ተመቶኛል ይላል፡፡

ልጆቻቸውን ሊያደርሱ ከአዲስ አበባ የመጡት አቶ አምለክ የበረከት አምላክ አባት እንዲሁም ከጎንደር የመጡት እና የተማሪ ፍቅሩ ደሳለኝ እናት የሆኑት ወይዘሮ ሀና ጌጡ እጅግ መልካም አቀባበል ነው ዩኒቨርሲቲው ያደረገልን አሰራራቸው ጥሩ ነው፤ ይበል የሚያሰኝ ነው ሲኔር ተማሪዎችንም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

የባሕር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ የተማሪ አቀባበል አስተባባሪ የአራተኛ አመት ተማሪ የሆነችው መክሊት ሙሏለም ተማሪዎችን ከጠዋት ጀምሮ እየተቀበሉ እንዳሉና ተማሪዎችን በሚቀበሉበት ጊዜ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ያለው ድባባ ደስ እንደሚል ገልጻለች

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#peda
የማይቀርበት!!
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት ውስጥ የዩኒቨርስቲው ግማሽ አካል የሆነው ፔዳ (College of Education and Behavioral Sciences) 50ኛ ዓመት የትምህርት ሚኒስቴርና የ UNESCO ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ይከበራል።
UNESCO የባሕርዳር መምህራን ትምህርት ኮሌጅን በመመስረት ያበረከተው አስዋጽኦ ይወሳል። ስለቀጣይ ስራዎች ይመከራል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ኦዲትርየም
ከ2:00ሰዓት ጀምሮ
የካቲት 13/2015ዓ/ም
#bdu60th_anniversary
A 50-years pursuit of knowledge and Wisdom !!

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ሆነ

(የካቲት 6/2015ዓ/ም ፣ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ )ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም ከ50% በላይ በማምጣት ቀጥታ ወደ ዪኒቨርሲቲ በሚገቡ ተማሪዎች ከተመረጡ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንደኛ ተመራጭ በመሆን በኢትዮጵያ በተማሪዎች በመመረጥ ቀዳሚ ተመራጭነቱን በማረጋገጥ ራዕዩን በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግ በቃ።

በ2022 በአፍሪካ ቀዳሚ የምርምር ዩኒቨርስቲዎች አንዱና በኢትዮጵያ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ የመሆን ራዕዩን ይዞ እየተጋ የሚገኘው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ተመራጭ ዩኒቨርስቲ በመሆን ራዕዩን አሳክቷል።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2014ዓ/ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ሁለተኛ ተመራጭ የነበረ ሲሆን በ2015ዓ/ም የመጀመሪያው ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ በመሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲነቱን ማረጋገጥ ችሏል።

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ በሚል መሪ ቃል ላለፉት 60ዓመታትን በትምህርት ጥራት ትኩረት በማድረግ ሲሰራ የኖረ ሲሆን የ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓላችን በምናከብርበት በዚህ ወቅት አንደኛ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ በመሆናችን ደስታና ኩራታችንን ድርብ ድል በመሆኑ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራንና አስ/ሰራተኞች፣ ተማሪዎቻትን፣ የቀድሞ ምሩቃንና አጋሮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።

ዩኒቨርሲቲያችን በ15 የአካዳሚክ ፕሮግራሞች፣ በ9 ግቢዎች፣ በውጭ ሃገራት የከፈትናቸው ሱዳንና የሶማሌ ሐርጌሳን ጨምሮ በበርካታ የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ማዕከሎቻችን በድምሩ ከ434 በላይ የስልጠና ዘርፎች አሕጉራዊ ራዕይ በመሰነቅ በመትጋት ላይ እንገኛለን።

ውድ የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን በኢትዮጵያ ተመራጭነታችንን በአዲስ ገቢ ተማሪዎች እውን ያደረግን በመሆናችን ከፍ ያለ ኩራት ይሰማናል። ለወደፊትም በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ልክ እንደመማር ማስተማሩ ሁሉ ተመራጭነታችንን በልዩነት አስጠብቀን ለመቀጠል ከአጋሮቻችን ጋር ያለንን ትስስር አጠናክረን እንቀጥላለን።

ውድ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር እና የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም የትምህርት ጥራት በማረጋገጥ እና ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ተመራጭነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ይሰራል።

ውድ የ2015ዓ/ም አዲስ ወደዩኒቨርሲቲዎቻችን የምትገቡ ተማሪዎቻችን ምርጫችሁ አድርጋችሁ ስለመረጣችሁን እያመሰገንን በእንግዳ ተቀባይ የውቢቷ ባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች በደማቅ አቀባበል ልንቀበላችሁ ፣ ባሕርዳርን እንደቤቴ በሚል በሚታወቀው መርሃግብራችን ለእያንዳንዳችሁ አንድ ቤተሰብ አዘጋጅተን ልንቀበላችሁ ዝግጅታችንን እያጠናቀቅን ነው።

ባሕር ዳርን እንደቤቴ ማለት ለአንድ አዲስ ተማሪያችን አንድ የቃል ኪዳን ቤተሰብ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ፈቃደኛ ቤተሰብ በቆይታችሁ ተንከባካቢና ደጋፊ ቤተሰብ ልክ እንደቤታችሁ እንድትኖሩ ለማድረግ እየሰራን መሆኑን ስንገልጽላችሁ በታላቅ ደስታና ኩራት ነው።

የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎት ውቢቷን የአባይና ጣና ሙሽራዋ ከተማችሁን ወደው በአንደኝነት የመላው ኢትዮጵያዊያን ልጆች ከተማችሁን ስለመረጡ እንኳን ደስ አላችሁ።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ዩኒቨርሲቲው ከ(HUMAN BIRDGE) ጋር በመተባበር ለመርዓዊ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ
*************
(የካቲት 4/2015 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስዊድን ሀገር ከሚገኘው ሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና ማሽኖች፤ አልጋዎች እና ልዩልዩ መገልገያ ቁሳቁሶችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኘው መርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው  ተገኘ  ተወካይና  የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እንደገለጹት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራዎች ባሻገር በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ የምርምር ስራዎችን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በአቅራቢያው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት፤ በአካባቢ ጥበቃና ግብርና ላይ እንዲሁም በትምህርትና ጤና ተቋማት ላይ የተለያዩ ድጋፎችን  እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በስዊድን ሀገር ከሚገኘው ሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና ማሽኖች፤ አልጋዎች እና የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኘው መርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊትም ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለተለያዩ ሆስፒታሎች ድጋፍ ማድረጉን ዶ/ር እሰይ ከበደ አውስተዋል፡፡
የሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) ግብረ ሰናይ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አዳሙ አንለይ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንደገለጹት ድርጅታቸው ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አልጋዎች፤ አልትራሳውንድ፤ የዐይን ቀዶ ጥገና መስሪያ ማይክሮ ስኮፕ፤ የደም ማቆያ ፍሪጅ፤ቁጥራቸው በርከት ያሉ ዊልቸር፤ ክራንቾችና እና ሌሎችም የተለያዩ መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የተደረገው ድጋፍም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት ዶ/ር አዳሙ ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ያለው የጤና ፖሊሲ በፊት ከነበረው ለመከላከል ቅድሚያ መስጠት ባሻገር ማከምም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የመርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ዘሪሁን ሆስፒታሉ በህክምና መሳሪያ እጥረት የነበረበትን ችግር ተረድተው ድጋፍ ላደረጉላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና HUMAN BIRDGE ግብረ ሰናይ ድርጅት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር ጋሹ ክንዱ በክልሉ የጤና ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ ቢሆንም በመንግስት በጀት ብቻ ያለውን የህብረተሰብ ፍላጎት ማሟላት ስለማይቻል የግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ስለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድጋፍ መርሀ ግብሩ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አቶ ብርሀኑ ገድፍና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች፤ የአማራ ክልል የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎችና የጤና ቢሮ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
በተደረገው ድጋፍም ከፍተኛ አስተዋፆ ላደረጉ አካላት የእውቅናና ምስጋና ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#TGSH

መልካም ዜና!!!
ከየካቲት 1-4፣2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
=========

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ትብብሩ ሆስፒታሉ ውስጥ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጡ የሚሳተፉትን ሐኪሞች ልምድ በማዳበር ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በቀጣይም ዘለቄታ ባለው መልኩ ሀኪሞችን ወደ እስራኤል ሀገር በመላክ የድህረ-ስፔሻሊቲ ስልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ሲሆን ለሆስፒታሉ ብሎም ለአገልግሎት ተጠቃሚ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዎጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል።

ስለሆነም በአሁኑ ዙር የድህረስፔሻሊቲ ስልጠና በጋራ ማስጀመሪያ ጭምር ሲሆን አንድ ሰልጣኝ ሐኪም ወደ እስራኤል አብሮ የሚሄድ ይሆናል።

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!
ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@bahir_dar_university

Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አር.ቲ.ፒኤ (rtPA) (alteplase) መድኃኒትን በመጠቀም የስትሮክ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው።
================================================================================
(ጥር 16፣ 2015 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የደም መርጋት ወደ አንጎል ደም የሚወስደውን የደም ቅዳ ቧንቧ ሲዘጋ ወይም ሲያጠብ በሚከሰት ስትሮክ (Ischemic stroke) የተጠቁ ህሙማንን ከዓለም የስትሮክ ድርጅት በተደረገለት rtPA (alteplase) መድኃኒት በመጠቀም እንዲሁም በአሜሪካን ሀገር በቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ የስትሮክ ድህረ_ስፔሻሊስት ሀኪም ዶክተር መሃሪ ገብረዮሐንስ ጋር በመተባበር የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በደም ማጠር ምክኒያት የሚከሰትን አጣዳፊ ስትሮክ ('Acute Ischemic Stroke') በ 'rtPA' (alteplase) የህመም ምልክቱ በጀመረ በ4.5 ሰዓት ውስጥ ከተሰጠ ውጤታማ በመሆኑ ታካሚዎች የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ዶክተር ሙሉጌታ ቢያድጌ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የነርቭ ሐኪም አሳስበዋል።

መድሀኒቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በሆስፒታሉ የስትሮክ ህመም እንክብካቤ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ለውጥ እንዳመጣ ዶ/ር ሙሉጌታ አክለው ተናግረዋል።

ፈጥኖ ወደ ሆስፒታል መምጣት በርካታ ጠቀሜታ አለው!!!

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
Bahir Dar University Alumna’s account of her former BiT
The current software engineer of the big Microsoft Company, Eden Melaku was a student at Bahir Dar University in 2013. Among female graduates, she was awarded a gold medal with 3.97 average high score and a gold medal with a high score from the computer faculty and a certificate of recognition for doing the best graduation project of the year by the faculty. Her stay at Bahir Dar University testified that she has contributed to her identity today. In addition, she helped the institution she studied and the students in different ways. She's all in the way.
Bahir Dar Institute of Technology would like to express its gratitude for all the support given to Eden.

Eden’s Account
"My name is Eden Melaku Mulugeta. I graduated from the software engineering department in february 2021. I am a software engineer at Microsoft.
I joined BDU in 2015 as a freshman student in Yibab campus, after a year, the Computing faculty moved some students to peda and I was part of that. I completed my second year study in peda campus and moved to poly campus for my 3rd and remaining years of study. I had adventures and memorable times at Bahir Dar University.
During my 5 year study in BIT I had the privilege to learn the basics of programming and software engineering from amazing teachers who went above and beyond to help me build a foundation that I can thrive on. My department has an excellent curriculum designed to prepare us with skill and mindset for the corporate and entrepreneurial world. I thank all my teachers for helping me achieve my goal. I would like to give special gratitude to teachers who made me fall in love with software engineering. My first year object oriented design teacher Mr. Asegahegn, my object oriented programming and advanced programming teacher Mr. Desta Berihu.
I got the opportunity to stay the summer and work on a project under the help of an advisor after completing my second year that gave me extra time to work on real world problems outside of regular classes. I would like to thank the computing faculty and Dr. Gebeyehu for organizing this.
I would like to thank the ICT4D research center for helping me during my final year project with materials, office space and technical advice. BIT has an excellent staff from teachers to administration, I am so happy to study in an institute determined to create high-skilled, valuable engineers.
I would like to help BIT with mentoring graduating students to prepare them for technical interviews, which can help them get a job in big tech companies; I can give technical training and workshops. I will also participate in the poly alumni network on a variety of projects it is working on.
Thank you,
Eden"

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ10 ዓመቱን ስትራቴጅክ ዕቅድ ለማስፈፀም የሚያስችል መተግበሪያ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለውይይት አቀረበ
---------------------------------------------
--------------------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ10 ዓመቱን ስትራቴጅክ ዕቅድ ለማስፈፀም የሚያስችል መተግበሪያ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡ ኮሌጁ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ የ10 ዓመቱን ስትራቴጅክ ፕላን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ሰነዶች በተለያዩ ምሁራን የቀረበ ሲሆን በመማር ማስተማር ዘርፍ ዶ/ር አምሃ አድማሴ፣ በምርጥ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ዶ/ር እያያ ምስጋን፣ በመሪነት ዘርፍ ዶ/ር አበበ አሳየ እና በልህቀት ማዕከል ማቋቋሚያ አደረጃጀት እና አስተዳደር ዘርፍ አቶ ካሳውማር አንጋው ሰነዶችን አቀረበዋል::
ውይይቱን የመሩት የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕ/ር የሺጌታ ገላው ስትራቴጅክ ዕቅዱን ለመተግበር ስምንት ማስፈፀሚያ ሰነዶች የተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁመው እነዚህን ማስፈፀሚያ ሰነዶች ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ንቁ እና ጥሩ ተሳትፎ የሚያደርግ ሠራተኛ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የሠራተኛውን ሞራልና ተነሳሽነት በመጨመር፤ ሠራተኛው በሥራው ውጤታማ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር፤ ጥሩ የሚሰራን በማበረታትና በመሸለም፣ ተቋማዊ እድገት ለማምጣት መሰረት ይሆናል ብለዋል፡፡ ይህንን ወጥ በሆነ መንገድ ባይሆንም በኮሌጁ ሲተገበር መቆየቱን የተናገሩት ፕሮፌሰሩ አሁን ግን ስርዓት ባለው እና በመመሪያ ይመራ ዘንድ ሰነዶች ተዘጋጅተው ለውይይት መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የህክምና ተቋሙ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር እና በምርምርና ማህበረሰብ ዘርፍ ልቆ እንዲወጣ ከፍተኛ አስተዋፆ እያደረገ መሆኑን አውስተዋል፡፡ ይህንን ለማስቀጠል በመማር ማስተማር ዘርፍ ምርጥ መምህር እና ተመራማሪ በመሆን እግር ፈቺ ምርምሮችን ለሚያካሂዱ እንዲሁም በተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በልዩነት የሚሳተፉ መምህራንን መሸለምና ማበረታታት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ይህም የዩኒቨርሲቲውን ራዕይና ተልዕኮ ከማሳካት አንፃር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የገለፁት ፕሮፌሰር የሺጌታ አገራዊ ፋይዳውም ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ፕ/ር የሺጌታ ለተሳታፊዎቹ እንደገለፁት ሌላው ሀሳቡ አዲስ የሆነና ተቋሙን እንደ ተቋም ሊመሩ የሚችሉ ብቁ መሪዎች የመምረጥ እና ትልቅ አስተዋፆኦ ያላቸውን መሸለም የሚያስችል ስርአት እንደሚያስፈልግ እና ይህን የሚመለከት ሰነድም የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተቋሙን፣ ማህበረሰቡንና አገሪቷ የምትፈልገውን ተልዕኮ ለማሳካት ተከታታይ የሆነ መሪ የማፍራት እንዲሁም ያለውንም የማብቃት እና አዳዲሶችን ወደ ተቋሙ እንዲቀላቀሉ መደገፍ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ የመሪዎች ማብቂያ ሰነድ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ተቋሙ በመማር ማስተማር፣ በህክምና አገልግሎት፣ በምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንዲሆን እንፈልጋለን ያሉት ፕሮፌሰሩ ይህን ርዕይ ለማሳካት ደግሞ በተመረጡ ስምንት ዘርፎች የልቀት ማዕከል ለመሆን የሚያስችሉ ፍኖተ ካርታዎች ተዘጋጅተው በመገምገም ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ እነዚህም የ10 ዓመቱን ስትራቴጅክ ዕቅድ ለመተግበርና የምንፈልገውን ውጤት በማምጣት ግባችን ላይ ለመድረስ ይረዳሉ ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ፡፡ ሰነዶቹ አልቀው ወደ ተግባር ሲገቡም ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሳይሆን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ለጤና ሚንስቴር ግብዓት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
ሰነዱ ከዚህ በፊት የተወሰኑት በውጪ አጋር አካላት፣ በዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ባለሙያዎች የተገመገመ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመው አሁንም በኮሌጁ የሴኔት አባላት፣ በሆስፒታሉ የስራ አመራሮች እና በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገምግሞ ሀሳቦች ተካተውበታል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ኮሌጃችንን የሚያስተዳድረው ቦርድ አጠቃላይ ሰነዶችን ገምግሞ በማፅደቅ ወደ ስራ ያስገባቸዋል ብለን እናምናለን ሲሉ ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላው እምነታቸውን ገልፀዋል፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ማስታወቂያ
ለአዲስ #የማታ ትምህርት አመልካቾች

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 29-07-2013ዓ.ም
#BiT
#ማስታወቂያ

በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት-ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም የ4ኛ አመት ሁናችሁ የ Holostic ፈተና ያላለፋችሁ/የወደቃችሁ/ ተማሪዎች በሙሉ ፈተናው የሚሰጠው በ13-08-2013 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በ01-08-2013 ዓ.ም በየፋካልቲያችሁ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
#Urgent and top concern Announcement
________
For All BiT BDU Community

SHARE SHARE

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
#Urgent and top concern Announcement
________
For All BiT BDU Community

SHARE SHARE

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ ሃገር አቀፍ ወርክሾፕ አካሄደ
-------------------------
መጋቢት 20 እና 21/2013 ዓ.ም. በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ የተዘጋጀው ወርክሾፕ በኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ እና jhpiego በተባለ ግብረሰናይ ድርጂት ትብብር Benchmarking Visit to Human Nutrition Department of Bahir Dar University በሚል ስያሜ የተካሄደ ሲሆን ከ9 የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዘርፉ የአካደሚክ አመራሮችና ተወካዮች፣ የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የ jhpiego ተወካዮች እና የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና አመራሮች የተሳተፉበት ነበር፡፡
የወርክሾፕ ዝግጂቱን እና መድረኩን በማስተባበር በፋኩልቲው የአፕላድ ሂውማን ኒውትሪሽን ቼር ሃላፊ ዶ/ር መስፍን ወጋየሁ የመሩ ሲሆን የፋኩሊቲው ዲን ዶ/ር መታደል ካሳሁን ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈው ወርክሾፑን ከፍተዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር መታደል ስለ ኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ አጠቃላይ ገጽታ፣ በመተግበር ላይ ያሉ ስትራቴጂዎችና ያጋጠሙ መሰናክሎችን በተመለከተ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
የ jhpiego ተወካዩ አቶ ከፍያለው ሙለታ በበኩላቸው Feed the Future Ethiopia Growth through Nutrition Activity ተብሎ ስለሚጠራው ፕሮጀክት አላማ አብራርተው jhpiego ይህንን ፕሮጀክት በመደገፍና Strengthening Multi-sector Nutrition Workforce በሚል መርህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በስልጠና፣ በካሪኩለም ዴቨሎፕመንት፣ የትምህርት መሳሪያዎችን በማቅረብ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ ያገባኛል ብሎ የሚንቀሳቀስ ግብረሰናይ ድርጂት መሆኑን ጠቁመው የወርክሾፑ አላማም በዚህ አግባብ እንደሚታይና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሂውማን ኒውትሪሽን አኳያ ያለው የትምህርት ስርዓት፣ ሰኪል ላብ፣ ጂምር ስማርት ክላስ ሩሞች እና ዶኩመንቴሽኖች ለሌሎች ተቋማት እንደ ቤንች ማርክ ያገለግላሉ ተብሎ ታምኖበት የተዘጋጀ ወርክሾፕ መሆኑን አውስተዋል፡፡
በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ እና የአካደሚክ ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደምስ አልማው የተገኙ ሲሆን ለአዘጋጅ ፋኩልቲው እና ለድጋፍ አድራጊው ድርጂት ምስጋና አቅርበው ያማረ ቆይታና መልካም የወርክሾፕ ፕሮግራም አንዲሆን ያላቸውን ምኞት ለተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
ወርክሾፑ በሁለት ተከታታይ ቀናት በተያዘለት መርሃግብር መሰረት የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የኒውትሪሽን ላቦራቶሪዎችንና የቢዝነስ ኢንኩቤሽንና የቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

BDU in partnership with EENSAT project is offering GIS training to Natural Resource Managers
---------------------------------------------
-----------------------------
Geospatial Data & Technology Center (GDTC) of Bahir Dar University in collaboration with Ethiopian Educational Network to Support Agricultural Transformation (EENSAT) project offers five days long hands-on GIS training for Natural Resource Managers working at Woreda (District) level.
The training which is underway for five days (March 29-April 02, 2021) is offered by qualified GIS & Remote Sensing professionals from GDTC, BDU. The training aims to provide the knowledge and skills needed for the collection, interpretation, and management of spatial information, using geographic information systems and remote sensing technology. It also aims to support the planning and decision-making processes in natural resources management.
The topics covered in the training are: Basic concepts in GIS and Remote Sensing and its relation to Natural Resource Management (NRM), Watershed Delineation, GIS & Remote sensing based Watershed Management & Planning, Collection & analysis of spatial data for NRM, Geoprocessing for NRM, and Extracting Land Use/Land Cover data from Google Earth.
EENSAT is an innovative capacity development project working to strengthen the use of geo-data for agriculture and water to enhance food security and socio-economic development in Ethiopia in line with the Growth and Transformation Plan (GTP) priorities at the participating Higher Education institutions (BDU, AAU & MU) and Technical Vocational Education and Training (TVET) institutes. To get further information about EENSAT, please visit the following website: https://www.eensat.org/

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

127ኛውን #የአድዋ_ድል ብሔራዊ ቀን ዋዜማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

(የካቲት 22/2015 ዓ/ም ፣ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በማስመልከት የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣የጥንታዊ ኢትዮጱያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የአማራ ክልል የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ዳኝነት አያሌዉ፣ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በዊዝደም ህንፃ ጥበብ አዳራሽ በኪነ ጥበብ ስራዎችና በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

“አድዋ! የኢትዮጱያ ሕብረ ብሔራዊነት ቋሚ መዘክር፤የአፍሪካውያን ነፃነት ቀንድል” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የ127ኛው የድል በዓል ዋዜማ ላይ ለተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ የአድዋ ጦርነት በየካቲት 23 ቀን 1896 ዓ.ም በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ውጊያው በኢትዮጵያ አሸናፊነት የተጠናቀቀ እና የጣሊያኖች የቅኝ ግዛት መስፋፋት እቅድ ሳይሳካ የቀረበት ታላቅ ድል ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር እሰይ አክለውም የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማህተም፤የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል እና የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ፤ የአንድነታችን አርማ በመሆኑ ሁሌም ስንዘክረው እንኖራለን ብለዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባሕርዳር ከተማ ከንቲቫና የዩኒቨርስቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳሕሉ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉ የዚያን ዘመን አድዋ እያከበርን የዛሬ የኛን አድዋ ድል ለማድረግ የምንሰራበት ነው ብለዋል። በመካከላችን መከባበርና መደማመጥ፣ የታሪክን ጠቃሚ ክፍል መገንዘብና ለጋራ እሴት መስራት ትልቅ ቁምነገር ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ተናግረዋል።

በታላቅ ድምቀት በተከበረው በዚሁ የዋዜማ ዝግጅት ላይ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና በተጋባዥ እንግዶች ግጥሞች፣ መነባንቦች እና በዓሉን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው ታዳሚውን በደስታ አስፈንድቀዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመረማሪ የሆኑት ዶ/ር ገረመዉ እስከዚያ በዓሉን አስመልክተው ለተሳታፊዎች በአቀረቡት ፅሁፍ በጦርነቱ ወቅት 7000 አካባቢ የጠላት ወታደሮች ሲገደሉ፤ 470 ጣሊያን እና 958 ጥቁር ወታደሮች በጠቅላላዉ 1428 የጠላት ወታደሮች ቆስለዋል፤ 3000 ደግሞ የጦር ምርኮኞች ሆነዋል፤ 11000 ጠመንጃ እና 56 መድፎች በሙሉ ተማርከዋል፤ በኢትዮጵያዊያን በኩልም ደግሞ 4000-6000 ተዋጊ ሲሞት 8000 ደግሞ መቁሰላቸውን የተለያዩ ዋቢዎችን በመጥቀስ የገለፁ ሲሆን ጀግኖች አባቶቻችን አድዋ ላይ በከፈሉት መስወዕትነት ኢትዮጵያ አገራችን ነጻነቷን አስከብራ የአፍሪካ ብቸኛ ነጻ ሀገር ሆና ለመቆየት በቅታለች ብለዋል፡፡ አክለውም የአድዋ ድል ለአፍሪካ እና በጠቅላላዉ ለጥቁር ሕዝቦች መመኪያና ኩራት ሆኖ ይኖራል ብለዋል፡፡

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
********

(የካቲት17/2015 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም በመደበኛው መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከባሕር ዳር ከተማና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች፤የጸጥታ አካላት፤የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የሰላም ምክር ቤት ኮሚቴ አባላት ጋር የተማሪዎችን አቀባበል በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች  ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ   እንደገለጹት  ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በዚህ አመት  5,187 ተማሪዎች መርጠውታል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ይህ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አንጻር ሲዎዳደር በጣም ትልቅ  ቁጥር ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ እንድንመረጥ ያደረጉንም በጣም ብዙ ምክኒያቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ የመማር ማስተማር ስራዎች አቅምና ብቃት፤ የመልካም አስተዳደር ስራዎች፤ ዩኒቨርሲቲው  የሚገኝበት  ከተማ እና ማኅበረሰብ ሰላማዊ መሆን ከምርጫው ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ ከበደ አክለውም  ባሕር ዳር እንደቤቴ መርሀ ግብርም ለአንድ አዲስ ተማሪ አንድ  የቃል ኪዳን  ቤተሰብ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ልክ እንደ ቤተሰብ ሆኖ በቆይታቸው ተንከባክቦና ደግፎ  እንደቤታቸው  እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም በበኩላቸው ተማሪዎች አንድን  ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከተማሪዎች ባሻገር የቤተሰብ ይሁንታም  ትልቁን  ቦታ ይይዛል፡፡ ቤተሰብ ስለ ዩኒቨርሲቲው መገኛ አካባቢ ያለው መረጃ እና የሚሰማው ስሜት በራሱ ትልቅ ድርሻ  ይኖረዋል፡፡  ባሕር ዳር ውበቷና ድምቀቷ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተፈጥሮ ለሚዋደዱ ሰዎች እንደ ጣና ያለ መዝናኛ  ያላት፡፡ መንፈሳዊ ነገር ለሚያሻቸው ደግሞ ገዳማቷ አይጠገቡም ብለዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላትም በትኩረት በተማሪዎች ቅበላ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አቶ አራጋው ብዙዓለም ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ሀብታሙ መለሰ እንደተናገሩት ተማሪዎች ደህንነትና ሰላምን ጠብቆ ቅበላውን ለማካሄድ የዩኒቨርሲቲው የጸጥታ አካላት ከሌሎች በከተማው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ዶ/ር በላይ ተፈራ ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊው ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች የሚገቡባቸውን ግቢዎች የማሳወቅና የዶርም እና የአልጋ ድልድል እና ተያያዥ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋርም ተማሪዎችን በቅንጅት ለመቀበል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ጥበበ ሰሎሞን በበኩሉ ተማሪዎች የሚገቡባቸው የዘንዘልማና የግሽ ዓባይ ግቢዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ተማሪዎችን ለመቀበል ህብረቱ ከተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት ጋር በመሆን እየሰራ ሲሆን አዲስ ተማሪዎችም ስለዩኒቨርሲቲው ህግና ደንብ እንዲሁም ስለግቢዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዝግጅት ተደርጓል ብሏል፡፡

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የጥሪ ማስታወቂያ
ለአዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

SHARE SHARE SHARE

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በ2015 ዓ/ም አዲስ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

ለየካምፓሶች Group  ተከፍቷል
Join በማለት የምትፈልጉትን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ!

1.ፔዳ Main campus👇
@pedabdu
@pedabdu

2.ይባብ ካምፓስ👇👇
@yibabbdu
@yibabbdu

3.ዘንዘልማ Agri ካምፓስ👇
@zenzelmabdu
@zenzelmabdu

4. ሰባታሚት health ካምፓስ👇
@tibebebdu

5.ፓሊ technology ካምፓስ👇
@bitbdu

6.ሰላም textile ካምፓስ👇
   @textilebdu

ለተማሪዎች ስለምትገኙበት ካምፓስ መረጃ ለመስጠት Admin መሆን የምትፈልጉ @bdustudentbot
  ላይ አናግሩን!

For all BDU campuses
👉Channel
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
👉 group
@bdu_students
@bdu_students

Share for your friends!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የ2ኛነት ደረጃ እገኘ
==========================

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #በዓለም እና #በአፍሪካ እንዲሁም #በኢትዮጵያ_የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ምደባ መሰረት ከኢትዩጵያ 2ኛ ከአፍሪካ 66ኛ እንዲሁም ከዓለም 2285ኛ ደረጃ ያገኘ መሁኑን WWW.webmetrics.info በጥር 2023 ዓ.ም (January 2023) እትሙ ባወጣው ዘገባው ያመለክታል:: ከአለም ከእፍሪካና በኢትዮጵያ ያገኘውን ደረጃ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንክ ይመልከቱ::

WWW.webmetrics.info

World ranking
“””””””””””””
1. AAU -------- 1282
2. BDU--------- 2285
3. Mekelle----- 2687
4. UoG -------- 2915
5. Haramaya-- 3043
6. Hawassa ----3245
7. Arbz Minch--3850
8. Jimma----- - 5425
9. ASTU --------9924
10. AASTU----- 10898
https://World ranking www.webometrics.info/en/ranking_africa

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#STEM #BDU
"ሁሉም የስቲም ተማሪዎቻችን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡበትን ውጤት አስመዘገቡ"
ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ስቲም ማዕከል

(ጥር 19/2015 ዓ/ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ BDU)የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዘገቡ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ 43 የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ከ375 እስከ 621 ውጤት ያመጡ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ከ50% በላይ አስመዝግበዋል። ከነዚህም ውስጥ 27ቱ ሴቶች ሲሆኑ 16ቱ ወንዶች ናቸው።

አንድ ተማሪ ብቻ 375 ያስመዘገበ ሲሆን ተማሪዎች ሌሎቹ በሙሉ ከ460 በላይ ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ነጥብ አስመዝግበዋል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ከባሕርዳር ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ሲዛወሩ በሂሳብ፣ በኬሚስትሪ፣ በስነህይወት፣ በፊዚክስና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከ85 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸውንና ልዩ የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን መልምሎ መግቢያ ፈተና በመስጠት ወደዩኒቨርስቲው ስቲም ማዕከል በማስገባት በማስተማር ላይ ይገኛል።

በዚህ ሂደት በዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን የተከታተሉና የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ 43 ተማሪዎች ውስጥ ሁሉም ፈተናውን ከ50% እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል። በዩኒቨርሲቲያችንም ከፍተኛው ውጤት 621 ሆኖ ተመዝግቧል።

ወላጆችና፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራንና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የስቲም ማዕከል ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
መልካም የጥምቀት በዓል!
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በ2013 ዓ.ም አዲስ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎችን የሚመለከት አስፈላጊ መረጃን ያካፍሉ
====================

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2013 ዓ.ም አዲስ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምርጫ አስመልክቶ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ማስታወቂያው አዲስ የዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎችን የሚጠቅም በመሆኑ እባክዎ አንብበው ለተማሪዎቹ መረጃው እንዲደርስ የበኩልዎትን ያድርጉ፡፡

እባክዎ ሼር ያድርጉት!
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

ማስታወቂያውን ለማግኘት ቀያዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡ https://www.facebook.com/SHE.Ethio/

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች የሙሉ ቀን መደበኛ ስራቸውን በተማሪዎች ዶርሚታሪ አከናወኑ::
----------------------------------
የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ፣ የአካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደምስ አልማው እና የማኔጂንግ ዳይሬክተሩን ዶ/ር ቢምረው ታምራትን ጨምሮ የፋኩልቲ ዲኖችና ዳይሬክተሮች ሚያዝያ 01/2013 ዓ.ም. ጊዚያዊ ቢሮአቸውን በተማሪዎች ዶርሚታሪ አድርገው መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ ውለዋል፡፡
በእለቱ አመራሮቹ ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቡድን የተማሪዎችን ዶርሚታሪዎች ከጎበኙ በኋላ እያንዳንዳቸው ወደ ተለያዩ የተማሪ ዶርሞች አምርተው የቢሮ ስራቸውን አካሂደዋል፡፡ በጊዜያዊ ቢሮአቸው ባለጉዳዮችን ማስተናገድ ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን ሲከውኑ የዋሉ ሲሆን ከተማሪዎቹ ጋርም በተለያዩ ችግሮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ከቀኑ 6 ሰዓት ሲሆን ደግሞ ማዘር ካፌ ተብሎ በሚጠራው የመመገቢያ አዳራሽ በመገኘት የተማሪዎችን የምሳ ማዕድ ተጋርተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ እንደገለጹት ፕሮግራሙ እንደተቋም ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የሎጂስቲክ አቅርቦቶች ላይ ያሉብንን ውስንነቶች እና ሌሎችም ችግሮች በቅርበት ሆነን እንድንለይ ከማስቻል ባሻገር ከተማሪዎች ጋር ያለንን ቤተሰባዊ ቅርርብ ያጎለበትንበት ሆኖ አግኝተነዋል በማለት ተናግረዋል፡፡ ከተማሪዎች ጥያቄዎችና በቦታው ተገኝተው ከተመለከቷቸው ችግሮች መካከልም አንዳንዶቹን ባጭር ጊዜና በውስጥ አቅም፤ ጊዜና ተጨማሪ አቅም የሚጠይቁትን ደግሞ ደረጃ በደረጃ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ለመፍታት እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡
አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች በበኩላቸው ጊዜያዊ ቢሮአቸውን ዶርሚታሪ አድርገው ለሰሩ አመራሮች ያላቸውን ክብር እና አድናቆት ገልጸው አመራሮቹ በምልከታቸው ወቅትና ከተማሪዎች ጋር በነበራችው ውይይት የተገነዘቧቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት አንጸባርቀዋል።

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#Tibebe_Gion #TGSH
አስደሳች ዜና
=======
ከሚያዝያ 11-15/2013 ዓ.ም #ከእስራኤል ሐገር በሚመጡ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በመሳሪያ የተጋዘ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል::

የሚሰጡ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚከተሉት ናቸው::
1.የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (laparascopic cholecystectomy)
2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (esophageal cancer and achalasia surgery)
3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዝ ቀዶ ህክምናዎች ህክምናዎች (gastric cancer and other benign gastric pathology surgery)
5. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምናዎች (hepatopancreatico biliary surgery) እና
6. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዝ ቀዶ ህክምናዎች (colorectal and intrabdominal mass surgery)
የታካሚዎች ልየታ ከሚያዝያ 3-7/2013 ዓ.ም #በጥበበ_ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ተመላላሽ ክፍል ይካሄዳል።

ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናሳዉቃለን::
ጥበበ ግዮን ስፔሻ ሻልዝድ ሆስፒታል
#BDU
#CMHS
#TGSH

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BiT
Total Quality Management Office of Bahir Dar Institute of Technology Bahir Dar University has organized and provided training on Laboratory Management and Kaizen
-----------------------------------------------------
The Laboratory Management and Kaizen training which includes theoretical and practical sessions has been conducted for 3 days from 2nd to 5th of April, 2021.
The trainers were Mr. Fetene Teshome from Bahir Dar Institute of Technology (BiT) and Mr. Alene Endaylalu from the Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology (EiTEX).
Dr. Demis Almaw, Academic Deputy Scientific Director of BiT-BDU, in his closing remark pointed out that this training was organized after observation of laboratories by the management team. According to him, the team understood and decided on the necessity of training regarding laboratory management and Kaizen. Dr. Demis also added that the institute is highly dedicated to enhancing the level of laboratories not only for the reason that laboratory works are with superior priorities for the fields of technology and engineering but also for their essentiality as a part of ABET accreditation process in which selected programs of BiT-BDU are striving for.
Dr. Mekonnen, Director of Total Quality Management Office of BiT-BDU, in his turn, justified that the training is initiated after 53 out of 79 laboratories of BiT-BDU are visited by the management team and the organizing duty of this problem-driven training is given to the office. He also remarked that the training is not a one-time duty; rather the office will follow up its practical implementation continuously cooperating with different academic sections and units.
According to Dr. Mekonnen, the same training will be conducted starting from April 06, 2021, for the remaining group of trainees.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ምን መሰልጠን ይፈልጋሉ? 👇

👉 የኮምፒውተር ሃርድዌርና ሶፍትዌር ጥገና
👉ETABS, SAP, AUTOCAD, CIVIL 3D, PEACHTREE, SPSS, STATA
👉 Phyton, Java, c++
👉 WATER CAD, GIS, PHOTOSHOP

✔ስልጠናው የሚሰጠው በተመችዎት ሰዓት
✔ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፊኬት ይሰጠዎታል
✔ 80% በተግባር የተደገፈ
👍 በእኛ በኩል ተመዝግበው በግሩፕ ሲሰለጥኑ #ቅናሽ ይደረግሎታል::
✔ በተመጣጣኝ ክፍያ ብቁ በሆኑ መምህራን ጥሩ እውቀት ይዘው የሚወጡበት
ለመመዝገብ @bdu_tana_bot ላይ ያናግሩን
ስልጠናው ከጥቂት ቀን በኋላ ስለሚጀምር ይፍጠኑ!

ቦታ: ቅ.ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፊት ለፊት ባህር ዳር

ለመመዝገብ ስም:ስልክ ቁጥርና መሰልጠን የሚፈልጉትን @bdu_tana_bot ላይ ላኩልን!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

BiT
#Invitation
******
BiT MakerSpace has organized two Hackathon (innovation competition) events for students. We are looking for young makers, hackers, and thinkers like you !!
1. Health Hackathon
This year's health hackathon focuses on an innovative solution that will help the health sector, the selected students will get a chance to training, visit local hospitals and three winners projects will be funded for prototyping. The students will have the chance to use the state of the art tools like 3D printers, CNC, and Laser cutters. (Open to 4th and 5th year BiT students)
For more information and registration use the link below. Application deadline before April 15th, come and innovate with us.
https://docs.google.com/forms/d/e/
1FAIpQLSdwuDjbsreT032Q9GMYgumrWx-oaoQmkdCZ67yYb-MNYxQDiA/viewform?usp=sf_link
2. Agri-hackathon
This year's Agri-hackathon focuses on an innovative solution that the irrigation sector, the selected students will get a chance to training, visit local irrigation farms and four winners projects will be funded for prototyping. The students will have the chance to use the state of the art tools like 3D printers, CNC, and Laser cutters.
(Open to all BDU students)
For more information and registration use the link below. Application deadline before April 15th, come and innovate with us. https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScd11YY3yqmXQiAtY-hoZURHQGNLGIhZIUjUrLwvtMbUAv0Ug/viewform?usp=sf_link

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ
*****************************************
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ የመጀመሪያ አመት ማጠቃለያ ፈተና ላይ ይገኛል:: በዩኒቨርስቲው በዚህ አመት አዲስ ከሚጀምሩ ትምህርት ክፍሎች መካከል የሲኒማ እና ቴአትር ጥበባት ዲፓርትመንት (Cinema and Theatre Arts Department) ይገኝበታል:: በዚህ ትምህርት ክፍል ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ጋዜጠኝነት እና ሰነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል በመሄድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
መጋቢት 27/7/2013 ዓ.ም ጥዋት 3:00 ፔዳ ግቢ ኦዲትሪየም አዳራሽ የመግቢያ የሙከራ ፈተና ስለሚሰጥ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በመገኘት መግቢያ ፈተናውን እንድትወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
በአካል በመሄድ መመዝገብ ለማትችሉ ከዚህ በታች በሚገኘዉ ሊንክ በኦንላይን (online) መመዝገብ ትችላላትሁ::
ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑDescription:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScyFtTJXoFmR15Wa6TGwoAhakMj1AxGpy7iqMENTFAzT9Uv7Q/viewform?usp=pp_url

Читать полностью…
Subscribe to a channel