የመስኮተ ጥበብ መሰናዶ ግብዣ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ህብረት ቀንን የተመለከተ ዝግጅት በመስኮተ ጥበብ የቴሌቪዥን መርሀግብር ተሰናድቷል፣ እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ።
https://youtu.be/zC4Uu7KT3HY
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህፀን ካንሰር ሰብ-ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን አስመረቀ *****የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ / gynecology oncology subspecialty / ከፍተኛ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች በዛሬው ዕለት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ የፍሪቦርግ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ ፕሮፌሰሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተሰጠውን ስልጠና አጠናቀው በዛሬው እለት ለምረቃ የበቁት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማሕፀን እና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር እያያ ምስጋን እና ዶ/ር ዳውድ ሙሐመድ ከሰኔ 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ /gynecology oncology subspecialty/ በመሆን የምርቃት ሰርቲፊኬታቸውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እጅ ተቀብለዋል፡፡በስልጠናው አስተዋፆ ለነበራቸው ጀርመን ሐገር ለሚገኜው ሆፕ ፕሮጀክት እና ለኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ ለሆኑት ለፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ለዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የእውቅና ሰርፊኬት ከዶ/ር ፍሬው ተገኘ እጅ ወስደዋል፡፡በመጨረሻም የሁለቱ ተቋማት ተወካይ የሆኑት ፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ እንደሀገር የተያዙ ተመሳሳይ የስልጠና ቦታዎች መካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጊዜው እና በሰዓቱ ሙያው በሚጠይቀው ልክ ስልጠናውን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም በመሆኑ ምስጋና አቅርበው የሰልጣኞች ተነሳሽነት እና የዩኒቨርሲቲውን ማኔጅመንት ለስልጠናው የነበራቸውን ቁርጠኝነት አመስግነው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት ለሚሰራቸው ማንኛውንም የጤናነክ ፕሮጀክቶች ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
/channel/bahir_dar_university
Call for applications for workshop participants
Working in solidarity with Ethiopian Research Universities: Writing and mentoring program for Early Career Researchers and PhD students
With the support of the British Academy, Bahir Dar University and Hawassa University in collaboration with the University of East London are implementing a two-year capacity-building program for 40 early career researchers and postgraduate students. The program aims to enhance the academic publishing capacity of research universities in Ethiopia through training workshops to improve scholarly writing skills and by creating a mentorship infrastructure. The context is the twofold global concern about low numbers of articles published in high-impact international peer-reviewed journals by academics living in the global south and poor representation of female academic authors from and living in the global south.
The program will support networking and collaborative opportunities for researchers within Ethiopian Universities and the University of East London. In addition to strengthening publication practices, it will empower women in academia, ensuring 50% of participants are women. Interested early career researchers and PhD students are cordially invited to apply to this program.
To apply, you must send all of the following documents to babdhu2023@gmail.com:
●Evidence of graduation from a Social Science PhD program
●Evidence of Master’s degree for those in the 2nd year or above of their PhD program
●Evidence of current employment in a research University in Ethiopia
●CV - 2 pages maximum, highlighting any writing activity
●A statement of no more than 250 words explaining:
o Why you wish to attend these workshops;
o Your ability to attend six one-day workshops over the 24-month duration of the program;
oPlease also confirm that you are willing to submit drafts of your writing for peer review
and develop it into an article that can be submitted to an academic journal.
Deadline: 15th June 2023 Applicant informed of outcome: End of June 2023
We particularly encourage applications from female scholars. Support workshops for women can be obtained by emailing: babdhu2023@gmail.com joining the following Zoom meeting links.
30th of May, 2023; time: 02:00 PM Nairobi time
https://us04web.zoom.us/j/73875620933?pwd=N1CuGu6vjOfDwanuvwet3MJvmGuRo2.1
Meeting ID: 738 7562 0933 Passcode: 5pGhVJ
1st of June, 2023; time: 04:00 PM Nairobi
https://us04web.zoom.us/j/71486735439?pwd=CcpbpTPmtKNqbMgobBadSt6RaX7IdC.1
Meeting ID: 714 8673 5439 Passcode: xRNjh6
ለዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) ላይ ስልጠና ተሰጠ
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) የተሰኘ የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ከመጋቢት 23-24/2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሁሉም ግቢ ለሚገኙ አካል ጉደተኛ ተመራቂዎች በፔዳ ግቢ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ለአካል ጉዳተኛ ተመራቂዎች ስልጠናውን ያዘጋጁት የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ የስራ ክፍልና ከፍታ ፕሮጀክት የተሰኘ ድርጅት በጋራ ሲሆኑ የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር ቀረብህ አስረስ የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያውቁና ከሌሎች በተሻለ መልኩ ስራ ለማፈላለግ ብሎም ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በቀላሉ ተግባብተው ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ ታልሞ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ቀረብህ በማስከተል ተማሪዎች ከፅንሰ ሃሳቡ ትምህርት ጋር ይህ ስልጠና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ መሰጠቱ ከትምህርቱ ዓለም ወደ ስራው ሲቀላቀሉ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በቀላሉ እንዲተገብሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በዘንዘልማ ግቢ ለሚሰለጥኑት ተመራቂዎች የስልጠናውን ጠቀሜታ ያስገነዘቡት የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ ተገቢውን እውቀት እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አውስተው ተመርቀው ከወጡ በኋላም ወደ ስራው ዓለም በቀላሉ ለመቀላቀል ግንዛቤ ያገኙ ዘንድ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ወርቁ አክለውም ስልጠናው ከሌሎች ስልጠናዎች ለየት ያለና ተመራቂዎች በቀላሉ ስራ ለማፈላለግ የሚያግዝ ስልጠና በመሆኑ ለዘንዘለልማ ግቢ ተማሪዎች ቅድሚያ ቢሰጥም የመማር ማስተማሩን መርሃ ግብር በማይነካ መልኩ ለሁሉም ተመራቂዎች ስልጠናው ተደራሽ እንደሚሆን አስገንዝበው ተማሪዎች በነቃ ተሳትፎ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል፡፡
/channel/bahir_dar_university
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና የዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ኤግዚቪሽን ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከባሕር ዳር ከተማ ከካቶሊክ ት/ቤት፣ከSOS ትምህርት ቤት፤STEM ትምህርት ቤቶች የመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከባሕር ዳር ዩኒቨርቲ ግቢዎች መካከል ሰላም ካንፓስ፣ የቴክኖሎጂ ተቋም (ፖሊ) እና ፔዳ ግቢን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍል የሳይኮሎጂ መምህር አቶ ታምሩ ደለለኝ ስለ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጠቅለል ያለ መረጃ ከአመሰራረቱ ጀምሮ አሁን እስካበት ደረጃ ያለውን የ60 ዓመት ጉዞ ታሪክ እና ያሳለፋቸውን ሁነቶች እንዲሁም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ትላልቅ ደረጃ ስለደረሱ፣ በአመራር ላይ ስላሉ ግለሰቦች፣ ስለ ትምህርት አሰጣጥ ጥራቱ ለተማሪዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመቀጠልም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሙዚየም ባለሙያ ወ/ሮ ኤልዳና ደሳለኝ የዚህ ጉብኝት ዓላማ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ60ኛ ዓመት ጉዞው ውስጥ ምን እንዳደረገ እና የት እንደደረሰ ለማስተዋወቅ በተጨማሪም እኒህ የሚጎበኙ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ምንነት አውቀው ለወደፊቱ ተመራጭ እንዲያደርጉት፣ ስለዩኒቨርሲቲ ያላቸው ንቃተ ህሌናም ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወ/ሮ ኤልዳና ወደ ፊት በባህር ዳር ከተማ ስር ያሉ ሌሎች የመንግስት ተማሪዎችም በዚህ ጉብኝት እንደሚሳተፉ እና ፕሮግራሙም እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም እንደሚቆይም ገልጸዋል፡፡ ከትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች ስለጉብኝቱ ከሰጡት ሀሳብ መካከል ከSTEM ማበልጸጊያ ማዕከል የመጣው ተማሪ ዮናታን አባይነህ ጉብኝቱ ጥሩ እንደሆነ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት ተመልክቶ ታሪኮችን ሰምተናል፡፡ የሰማነው ታሪክ ደስ የሚል ነበር፤ እኛም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ገብተን እንዲህ ያለ ታሪክ እንደሚኖረን ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ተማሪ ዮናታን አክሎም የተለያዩ ነገሮችንም አይተናል ይህን እድል ያላገኙት ሌሎች ተማሪዎችም እንዲጎበኙ ዩኒቨርሲቲው ቢያመቻችላቸው ሲል ሀሳቡን ገልጿል፡፡
ከSOS ትምህርት ቤት የመጣችው ተማሪ አና ያረጋል ጉብኝቱ አስደሳች እንደሆነና ሌሎች ተማሪዎችም እድሉ ቢመቻችላቸው እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደፊት የመማር እድሉ ቢገጥመኝ ደስተኛ ነኝ ብላለች፡፡ ሌላዋ ተማሪ ከካቶሊክ ትምህርት ቤት የመጣችው ናርዶስ ኃይሌ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመቱን አስቦ እኛን በመጥራቱ ደስተኛ ነን፡፡ ምክንያቱም የብዙዎቻችን ህይወት እዚህ ዩኒቨርሲቲ ላይ በመመስረቱና ብዙ ነገሮችን ማየት በመቻላችን ደስተኛ ነን ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን አይተን አናውቅም እናም ይህን እድል በማግኘታችን እናመሰግናለን፤ ትምህርት ቤቱ ወደ ፊትም እንዲህ አይነት ጉብኝቶችን ቢያዘጋጅ ጥሩ ነው ለተማሪዎች መነሳሳትን ይፈጥራል ብላለች፡፡
/channel/bahir_dar_university
የጥሪ ማስታወቂያ
በ2015 ዓ/ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ“Remedial” ፕሮግራም ለመከታተል ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
/channel/bahir_dar_university
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም #አዲስ_ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
(የካቲት 20/2015) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ሳይንስ ኮሌጅና በግሽ ዓባይ ግቢ አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን የተማሪዎች ቅበላ ግብረ-ሃይል ከተማሪዎች ዲን፣ ከስምሪትና ትራንስፖርት ክፍል እና ከተማሪዎች ህብረት የተውጣጣ ቡድን እየተቀበለ ነው፡፡
አዲስ ከሚገቡ ተማሪዎች መካከልም ከማቻከል ወረዳ፣ ሸለል ቀበሌ የመጣ፣ ተማሪ መኮነን አዲስ ከመናኸሪያ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በአውቶብስ እንደመጡ እና አቀባበሉ ጥሩ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሌላዋ ከደብረዘይት ቢሾፍቱ ከተማ የመጣችው ተማሪ ገሊላዊት እንደሻው ስትሆን በር ላይ አስተባባሪዎች ሻንጣቸውን ተቀብሎ እንዳስገቧቸውና በታም ደስ የሚል አቀባበል ዩኒቨርሲቲው እንዳደረገላቸው፣ ምግቡም እንደተመቻት እና ዶርማችንንም አዘገጃጅተን ጨርሰናል። አሁን የቀረን ግቢውን ማየት ነው በአጠቃላይ አቀባበሉ በጣም እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡ ከሰሜን ወሎ ዞን የመጣው ተማሪ ድስታው ተመስገን አቀባበሉን ከጠበቅኩት በላይ ነው ያገኘሁት በጣም ተመቶኛል ይላል፡፡
ልጆቻቸውን ሊያደርሱ ከአዲስ አበባ የመጡት አቶ አምለክ የበረከት አምላክ አባት እንዲሁም ከጎንደር የመጡት እና የተማሪ ፍቅሩ ደሳለኝ እናት የሆኑት ወይዘሮ ሀና ጌጡ እጅግ መልካም አቀባበል ነው ዩኒቨርሲቲው ያደረገልን አሰራራቸው ጥሩ ነው፤ ይበል የሚያሰኝ ነው ሲኔር ተማሪዎችንም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
የባሕር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ የተማሪ አቀባበል አስተባባሪ የአራተኛ አመት ተማሪ የሆነችው መክሊት ሙሏለም ተማሪዎችን ከጠዋት ጀምሮ እየተቀበሉ እንዳሉና ተማሪዎችን በሚቀበሉበት ጊዜ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ያለው ድባባ ደስ እንደሚል ገልጻለች
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#peda
የማይቀርበት!!
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት ውስጥ የዩኒቨርስቲው ግማሽ አካል የሆነው ፔዳ (College of Education and Behavioral Sciences) 50ኛ ዓመት የትምህርት ሚኒስቴርና የ UNESCO ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ይከበራል።
UNESCO የባሕርዳር መምህራን ትምህርት ኮሌጅን በመመስረት ያበረከተው አስዋጽኦ ይወሳል። ስለቀጣይ ስራዎች ይመከራል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ኦዲትርየም
ከ2:00ሰዓት ጀምሮ
የካቲት 13/2015ዓ/ም
#bdu60th_anniversary
A 50-years pursuit of knowledge and Wisdom !!
/channel/bahir_dar_university
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ሆነ
(የካቲት 6/2015ዓ/ም ፣ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ )ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም ከ50% በላይ በማምጣት ቀጥታ ወደ ዪኒቨርሲቲ በሚገቡ ተማሪዎች ከተመረጡ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንደኛ ተመራጭ በመሆን በኢትዮጵያ በተማሪዎች በመመረጥ ቀዳሚ ተመራጭነቱን በማረጋገጥ ራዕዩን በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግ በቃ።
በ2022 በአፍሪካ ቀዳሚ የምርምር ዩኒቨርስቲዎች አንዱና በኢትዮጵያ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ የመሆን ራዕዩን ይዞ እየተጋ የሚገኘው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ተመራጭ ዩኒቨርስቲ በመሆን ራዕዩን አሳክቷል።
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2014ዓ/ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ሁለተኛ ተመራጭ የነበረ ሲሆን በ2015ዓ/ም የመጀመሪያው ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ በመሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲነቱን ማረጋገጥ ችሏል።
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ በሚል መሪ ቃል ላለፉት 60ዓመታትን በትምህርት ጥራት ትኩረት በማድረግ ሲሰራ የኖረ ሲሆን የ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓላችን በምናከብርበት በዚህ ወቅት አንደኛ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ በመሆናችን ደስታና ኩራታችንን ድርብ ድል በመሆኑ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራንና አስ/ሰራተኞች፣ ተማሪዎቻትን፣ የቀድሞ ምሩቃንና አጋሮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።
ዩኒቨርሲቲያችን በ15 የአካዳሚክ ፕሮግራሞች፣ በ9 ግቢዎች፣ በውጭ ሃገራት የከፈትናቸው ሱዳንና የሶማሌ ሐርጌሳን ጨምሮ በበርካታ የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ማዕከሎቻችን በድምሩ ከ434 በላይ የስልጠና ዘርፎች አሕጉራዊ ራዕይ በመሰነቅ በመትጋት ላይ እንገኛለን።
ውድ የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን በኢትዮጵያ ተመራጭነታችንን በአዲስ ገቢ ተማሪዎች እውን ያደረግን በመሆናችን ከፍ ያለ ኩራት ይሰማናል። ለወደፊትም በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ልክ እንደመማር ማስተማሩ ሁሉ ተመራጭነታችንን በልዩነት አስጠብቀን ለመቀጠል ከአጋሮቻችን ጋር ያለንን ትስስር አጠናክረን እንቀጥላለን።
ውድ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር እና የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም የትምህርት ጥራት በማረጋገጥ እና ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ተመራጭነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ይሰራል።
ውድ የ2015ዓ/ም አዲስ ወደዩኒቨርሲቲዎቻችን የምትገቡ ተማሪዎቻችን ምርጫችሁ አድርጋችሁ ስለመረጣችሁን እያመሰገንን በእንግዳ ተቀባይ የውቢቷ ባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች በደማቅ አቀባበል ልንቀበላችሁ ፣ ባሕርዳርን እንደቤቴ በሚል በሚታወቀው መርሃግብራችን ለእያንዳንዳችሁ አንድ ቤተሰብ አዘጋጅተን ልንቀበላችሁ ዝግጅታችንን እያጠናቀቅን ነው።
ባሕር ዳርን እንደቤቴ ማለት ለአንድ አዲስ ተማሪያችን አንድ የቃል ኪዳን ቤተሰብ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ፈቃደኛ ቤተሰብ በቆይታችሁ ተንከባካቢና ደጋፊ ቤተሰብ ልክ እንደቤታችሁ እንድትኖሩ ለማድረግ እየሰራን መሆኑን ስንገልጽላችሁ በታላቅ ደስታና ኩራት ነው።
የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎት ውቢቷን የአባይና ጣና ሙሽራዋ ከተማችሁን ወደው በአንደኝነት የመላው ኢትዮጵያዊያን ልጆች ከተማችሁን ስለመረጡ እንኳን ደስ አላችሁ።
ዩኒቨርሲቲው ከ(HUMAN BIRDGE) ጋር በመተባበር ለመርዓዊ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ
*************
(የካቲት 4/2015 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስዊድን ሀገር ከሚገኘው ሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና ማሽኖች፤ አልጋዎች እና ልዩልዩ መገልገያ ቁሳቁሶችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኘው መርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ተወካይና የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እንደገለጹት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራዎች ባሻገር በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ የምርምር ስራዎችን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በአቅራቢያው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት፤ በአካባቢ ጥበቃና ግብርና ላይ እንዲሁም በትምህርትና ጤና ተቋማት ላይ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በስዊድን ሀገር ከሚገኘው ሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና ማሽኖች፤ አልጋዎች እና የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኘው መርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊትም ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለተለያዩ ሆስፒታሎች ድጋፍ ማድረጉን ዶ/ር እሰይ ከበደ አውስተዋል፡፡
የሂውማን ብሪጅ (HUMAN BIRDGE) ግብረ ሰናይ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አዳሙ አንለይ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንደገለጹት ድርጅታቸው ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አልጋዎች፤ አልትራሳውንድ፤ የዐይን ቀዶ ጥገና መስሪያ ማይክሮ ስኮፕ፤ የደም ማቆያ ፍሪጅ፤ቁጥራቸው በርከት ያሉ ዊልቸር፤ ክራንቾችና እና ሌሎችም የተለያዩ መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የተደረገው ድጋፍም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት ዶ/ር አዳሙ ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ያለው የጤና ፖሊሲ በፊት ከነበረው ለመከላከል ቅድሚያ መስጠት ባሻገር ማከምም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የመርዓዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ዘሪሁን ሆስፒታሉ በህክምና መሳሪያ እጥረት የነበረበትን ችግር ተረድተው ድጋፍ ላደረጉላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና HUMAN BIRDGE ግብረ ሰናይ ድርጅት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር ጋሹ ክንዱ በክልሉ የጤና ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ ቢሆንም በመንግስት በጀት ብቻ ያለውን የህብረተሰብ ፍላጎት ማሟላት ስለማይቻል የግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ስለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድጋፍ መርሀ ግብሩ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አቶ ብርሀኑ ገድፍና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች፤ የአማራ ክልል የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎችና የጤና ቢሮ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
በተደረገው ድጋፍም ከፍተኛ አስተዋፆ ላደረጉ አካላት የእውቅናና ምስጋና ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile
/channel/bahir_dar_university
#TGSH
መልካም ዜና!!!
ከየካቲት 1-4፣2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::
አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
=========
1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)
2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)
3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)
4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና
5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::
ትብብሩ ሆስፒታሉ ውስጥ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጡ የሚሳተፉትን ሐኪሞች ልምድ በማዳበር ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል።
በቀጣይም ዘለቄታ ባለው መልኩ ሀኪሞችን ወደ እስራኤል ሀገር በመላክ የድህረ-ስፔሻሊቲ ስልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ሲሆን ለሆስፒታሉ ብሎም ለአገልግሎት ተጠቃሚ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዎጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል።
ስለሆነም በአሁኑ ዙር የድህረስፔሻሊቲ ስልጠና በጋራ ማስጀመሪያ ጭምር ሲሆን አንድ ሰልጣኝ ሐኪም ወደ እስራኤል አብሮ የሚሄድ ይሆናል።
የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!
ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
@bahir_dar_university
Share
#አስደሳች_ዜና
==========
ከሀምሌ 19- 23/2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::
አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------
1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)
2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)
3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)
4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና
5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::
ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::
የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!
መረጃው የተገኘው ከጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
/channel/bahir_dar_university
✍️Register now for an IELTS test to be administered at Bahir Dar University on July 29, 2023. ✍️ Test type: Academic and General Training
✍️Contact us @ +251 908181110 or ieltsatbdu2022@gmail.com ✍️Venue: Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University, Jan Moscove Library
https://ieltsregistration.britishcouncil.org/ors/find-test "Your goal of having a life abroad becomes achievable with IELTS!"
/channel/bahir_dar_university
ኑ!ኑ!ኑ!
Reunion Weekend: Are you a former graduate of #Peda, #Poly or #BDU?
Have you missed your dormmates and campus friends; your former instructors and services providers; the lounge and cafe; classrooms, library, laboratory and workshops? TV rooms and cultural center (Auditorium); the palm and canopy streets and gardens; sport courts and intramural tournaments? Bahir Dar city, views of Abay and Tana?
Then, come and refresh your campus memories on the special occasion of Poly-Peda-BDU students' reunion weekend in the closing days of BDU'S 60th anniversary.
Date June 10 & 11, 2023 ( Sene 3& 4, 2015 E.C)
/channel/bahir_dar_university
#TGSH
ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ሕክምና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!!!
===============================================
(መጋቢት 18፣2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።
የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመልስ ያለመ ሲሆን እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
SHARE SHARE
127ኛውን #የአድዋ_ድል ብሔራዊ ቀን ዋዜማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተከበረ
(የካቲት 22/2015 ዓ/ም ፣ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በማስመልከት የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣የጥንታዊ ኢትዮጱያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የአማራ ክልል የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ዳኝነት አያሌዉ፣ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በዊዝደም ህንፃ ጥበብ አዳራሽ በኪነ ጥበብ ስራዎችና በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
“አድዋ! የኢትዮጱያ ሕብረ ብሔራዊነት ቋሚ መዘክር፤የአፍሪካውያን ነፃነት ቀንድል” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የ127ኛው የድል በዓል ዋዜማ ላይ ለተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ የአድዋ ጦርነት በየካቲት 23 ቀን 1896 ዓ.ም በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ውጊያው በኢትዮጵያ አሸናፊነት የተጠናቀቀ እና የጣሊያኖች የቅኝ ግዛት መስፋፋት እቅድ ሳይሳካ የቀረበት ታላቅ ድል ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ አክለውም የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማህተም፤የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል እና የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ፤ የአንድነታችን አርማ በመሆኑ ሁሌም ስንዘክረው እንኖራለን ብለዋል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባሕርዳር ከተማ ከንቲቫና የዩኒቨርስቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳሕሉ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉ የዚያን ዘመን አድዋ እያከበርን የዛሬ የኛን አድዋ ድል ለማድረግ የምንሰራበት ነው ብለዋል። በመካከላችን መከባበርና መደማመጥ፣ የታሪክን ጠቃሚ ክፍል መገንዘብና ለጋራ እሴት መስራት ትልቅ ቁምነገር ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ተናግረዋል።
በታላቅ ድምቀት በተከበረው በዚሁ የዋዜማ ዝግጅት ላይ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና በተጋባዥ እንግዶች ግጥሞች፣ መነባንቦች እና በዓሉን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው ታዳሚውን በደስታ አስፈንድቀዋል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመረማሪ የሆኑት ዶ/ር ገረመዉ እስከዚያ በዓሉን አስመልክተው ለተሳታፊዎች በአቀረቡት ፅሁፍ በጦርነቱ ወቅት 7000 አካባቢ የጠላት ወታደሮች ሲገደሉ፤ 470 ጣሊያን እና 958 ጥቁር ወታደሮች በጠቅላላዉ 1428 የጠላት ወታደሮች ቆስለዋል፤ 3000 ደግሞ የጦር ምርኮኞች ሆነዋል፤ 11000 ጠመንጃ እና 56 መድፎች በሙሉ ተማርከዋል፤ በኢትዮጵያዊያን በኩልም ደግሞ 4000-6000 ተዋጊ ሲሞት 8000 ደግሞ መቁሰላቸውን የተለያዩ ዋቢዎችን በመጥቀስ የገለፁ ሲሆን ጀግኖች አባቶቻችን አድዋ ላይ በከፈሉት መስወዕትነት ኢትዮጵያ አገራችን ነጻነቷን አስከብራ የአፍሪካ ብቸኛ ነጻ ሀገር ሆና ለመቆየት በቅታለች ብለዋል፡፡ አክለውም የአድዋ ድል ለአፍሪካ እና በጠቅላላዉ ለጥቁር ሕዝቦች መመኪያና ኩራት ሆኖ ይኖራል ብለዋል፡፡
/channel/bahir_dar_university
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
********
(የካቲት17/2015 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም በመደበኛው መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከባሕር ዳር ከተማና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች፤የጸጥታ አካላት፤የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የሰላም ምክር ቤት ኮሚቴ አባላት ጋር የተማሪዎችን አቀባበል በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እንደገለጹት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በዚህ አመት 5,187 ተማሪዎች መርጠውታል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ይህ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አንጻር ሲዎዳደር በጣም ትልቅ ቁጥር ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ እንድንመረጥ ያደረጉንም በጣም ብዙ ምክኒያቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ የመማር ማስተማር ስራዎች አቅምና ብቃት፤ የመልካም አስተዳደር ስራዎች፤ ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት ከተማ እና ማኅበረሰብ ሰላማዊ መሆን ከምርጫው ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ ከበደ አክለውም ባሕር ዳር እንደቤቴ መርሀ ግብርም ለአንድ አዲስ ተማሪ አንድ የቃል ኪዳን ቤተሰብ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ልክ እንደ ቤተሰብ ሆኖ በቆይታቸው ተንከባክቦና ደግፎ እንደቤታቸው እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም በበኩላቸው ተማሪዎች አንድን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከተማሪዎች ባሻገር የቤተሰብ ይሁንታም ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ ቤተሰብ ስለ ዩኒቨርሲቲው መገኛ አካባቢ ያለው መረጃ እና የሚሰማው ስሜት በራሱ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ባሕር ዳር ውበቷና ድምቀቷ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተፈጥሮ ለሚዋደዱ ሰዎች እንደ ጣና ያለ መዝናኛ ያላት፡፡ መንፈሳዊ ነገር ለሚያሻቸው ደግሞ ገዳማቷ አይጠገቡም ብለዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላትም በትኩረት በተማሪዎች ቅበላ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አቶ አራጋው ብዙዓለም ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ሀብታሙ መለሰ እንደተናገሩት ተማሪዎች ደህንነትና ሰላምን ጠብቆ ቅበላውን ለማካሄድ የዩኒቨርሲቲው የጸጥታ አካላት ከሌሎች በከተማው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ዶ/ር በላይ ተፈራ ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊው ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች የሚገቡባቸውን ግቢዎች የማሳወቅና የዶርም እና የአልጋ ድልድል እና ተያያዥ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋርም ተማሪዎችን በቅንጅት ለመቀበል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ጥበበ ሰሎሞን በበኩሉ ተማሪዎች የሚገቡባቸው የዘንዘልማና የግሽ ዓባይ ግቢዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ተማሪዎችን ለመቀበል ህብረቱ ከተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት ጋር በመሆን እየሰራ ሲሆን አዲስ ተማሪዎችም ስለዩኒቨርሲቲው ህግና ደንብ እንዲሁም ስለግቢዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዝግጅት ተደርጓል ብሏል፡፡
/channel/bahir_dar_university
የጥሪ ማስታወቂያ
ለአዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
SHARE SHARE SHARE
በ2015 ዓ/ም አዲስ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ለየካምፓሶች Group ተከፍቷል
Join በማለት የምትፈልጉትን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ!
1.ፔዳ Main campus👇
@pedabdu
@pedabdu
2.ይባብ ካምፓስ👇👇
@yibabbdu
@yibabbdu
3.ዘንዘልማ Agri ካምፓስ👇
@zenzelmabdu
@zenzelmabdu
4. ሰባታሚት health ካምፓስ👇
@tibebebdu
5.ፓሊ technology ካምፓስ👇
@bitbdu
6.ሰላም textile ካምፓስ👇
@textilebdu
ለተማሪዎች ስለምትገኙበት ካምፓስ መረጃ ለመስጠት Admin መሆን የምትፈልጉ @bdustudentbot
ላይ አናግሩን!
For all BDU campuses
👉Channel
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
👉 group
@bdu_students
@bdu_students
Share for your friends!
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የ2ኛነት ደረጃ እገኘ
==========================
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #በዓለም እና #በአፍሪካ እንዲሁም #በኢትዮጵያ_የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ምደባ መሰረት ከኢትዩጵያ 2ኛ ከአፍሪካ 66ኛ እንዲሁም ከዓለም 2285ኛ ደረጃ ያገኘ መሁኑን WWW.webmetrics.info በጥር 2023 ዓ.ም (January 2023) እትሙ ባወጣው ዘገባው ያመለክታል:: ከአለም ከእፍሪካና በኢትዮጵያ ያገኘውን ደረጃ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንክ ይመልከቱ::
WWW.webmetrics.info
World ranking
“””””””””””””
1. AAU -------- 1282
2. BDU--------- 2285
3. Mekelle----- 2687
4. UoG -------- 2915
5. Haramaya-- 3043
6. Hawassa ----3245
7. Arbz Minch--3850
8. Jimma----- - 5425
9. ASTU --------9924
10. AASTU----- 10898
https://World ranking www.webometrics.info/en/ranking_africa
/channel/bahir_dar_university
#STEM #BDU
"ሁሉም የስቲም ተማሪዎቻችን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡበትን ውጤት አስመዘገቡ"
ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ስቲም ማዕከል
(ጥር 19/2015 ዓ/ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ BDU)የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዘገቡ።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ 43 የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ ከ375 እስከ 621 ውጤት ያመጡ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ከ50% በላይ አስመዝግበዋል። ከነዚህም ውስጥ 27ቱ ሴቶች ሲሆኑ 16ቱ ወንዶች ናቸው።
አንድ ተማሪ ብቻ 375 ያስመዘገበ ሲሆን ተማሪዎች ሌሎቹ በሙሉ ከ460 በላይ ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ነጥብ አስመዝግበዋል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል ከባሕርዳር ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ሲዛወሩ በሂሳብ፣ በኬሚስትሪ፣ በስነህይወት፣ በፊዚክስና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከ85 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸውንና ልዩ የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን መልምሎ መግቢያ ፈተና በመስጠት ወደዩኒቨርስቲው ስቲም ማዕከል በማስገባት በማስተማር ላይ ይገኛል።
በዚህ ሂደት በዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን የተከታተሉና የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ 43 ተማሪዎች ውስጥ ሁሉም ፈተናውን ከ50% እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል። በዩኒቨርሲቲያችንም ከፍተኛው ውጤት 621 ሆኖ ተመዝግቧል።
ወላጆችና፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራንና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የስቲም ማዕከል ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!
/channel/bahir_dar_university