bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

-

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses' Students! www.bdu.edu.et Contact @bdu_tana_bot

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

12ኛው የEAI አለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ኮንፈረንስ (ICAST 2024) ተካሄደ

*****

ጥቅም
ት 24/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) 12ኛው አለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገቶች (ICAST 2024) ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ በዋሸራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽነሩን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከጥቅምት 22-24/2017ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ላይ ትኩረቱን በማድረግ አካሂዷል፡፡ 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 12ኛውን ዓለማቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አውደጥናት በንግግር የከፈቱት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እሰይ ከበደ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም በየዓመቱ ትኩረቱን የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን መሰረት ያደረገ ዓለማቀፍ አውደጥናቶችን እንደሚያካሂድ ገልፀው፤ በአውደጥናቱ ላይ የሚቀርቡ የምርምር ፁሁፎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆነው  ስፕሪንገር (Springer) ጆርናል ላይ በመውጣት በመላው ዓለም ላሉ ህዝቦች ፣ ሳይንቲስቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት በመድረስ የዩነቨርሲቲውን የምርምር ስራዎች ጎልተው እንዲዎጡ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ የምርምር ስራዎች ከህትመት ባለፈ ቴክኖሎጅን በማሻገር ዩኒቨርሲቲው የራሱን አስተዋፆ እያደረገ መሆኑን ገልፀው በተመሳሳይ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ምርምሮች በአራት የምህንድስና መርሐ ግብሮች በዓለም አቀፍ የሕንፃ እና ቴክኖሎጂ አክሬዲቴሽን ቦርድ ዕውቅና በማግኘት ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የላቀ ውጤት ማስመዝገቡ የበለጠ ለመስራት ጉልበት እንደሚሆናቸው ፕሮፌሰር እሰይ ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ በበኩላቸው ተቋሙ ባለፉት አስራ አንድ ተከታታይ ዓመታት በተደረጉ አውደጥናቶች የተለያዩ ችግር ፈቺ ምርምሮች፣ ለማህበረሰቡ እና ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚጠቅሙ  አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ መቅረባቸውን ተከትሎ  ለተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎች አዳዲስ የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

በአውደጥናቱ ላይ ፐሮፌሰር ደስታ መብራቱ እና ፐሮፌሰር ማሞ ሙጨ ከደቡብ አፍሪካ በዙም ገብተው ለአፍሪካ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ልማት ስልታዊ ለውጦች እና እንደገና ማሰብ እንዲሁም  እንደገና መንደፍ ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ለዘላቂ ልማት ለሁሉም የሰው ልጅ ለአንድ የዓለም ማህበረሰብ  በሚል ርዕስ ቁልፍ መልክት ለአውደጥናቱ ተሳታፊዎች አስተላልፈዋል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Hosts Prestigious Conference on Science and Technology

Bahir Dar University, Ethiopia (November 1, 2024) –The 12th International Conference on Advances in Science and Technology (ICAST 2024) commenced today at the Washera Hall of the Bahir Dar University Institute of Technology campus. This annual event serves as a significant platform for scientists, engineers, and industry professionals to engage in meaningful discussions aimed at leveraging science and technology to tackle pressing societal challenges.
The conference was inaugurated by Professor Essey Kebede, Vice President of Academic Affairs at Bahir Dar University. In his opening remarks, Professor Essey underscored the critical need for collaboration among various stakeholders within the scientific community to effectively address current global issues. He emphasized that such partnerships are essential for fostering innovation and advancing knowledge.
Dr. Mitiku Damte, Acting Scientific Director of the Institute of Technology, also welcomed participants, expressing appreciation for their commitment to finding innovative solutions to pressing problems. His speech highlighted the importance of ICAST 2024 in promoting scientific advancement and technological innovation.
Over the next two days, attendees will participate in a series of technical sessions, keynote addresses, and panel discussions covering a wide array of topics, including: Artificial Intelligence and Machine Learning Renewable Energy and Sustainable Development, Biotechnology and Biomedical Engineering, Information and Communication Technologies, and Materials Science and Nanotechnology
ICAST 2024 aims to inspire critical thinking and stimulate interdisciplinary collaboration, fostering new partnerships among professionals in the field. By showcasing the latest research findings and industry trends, this conference seeks to drive innovation and contribute to a more sustainable future.
This gathering not only highlights advancements in science and technology but also reinforces Bahir Dar University's dedication to addressing global challenges through research and innovation.

Bahir Dar University, Ethiopia
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Get ready, Bahirdar!

Join us this Thursday, October 31Morning (8:30 AM - 12:00 PM) at Washera Hall, BIT inside the university of Bahirdar for an insightful conversation on Urban Agriculture Sustainability.

Keynote speaker Gulilat Menbere, an entrepreneur and lecturer, will be sharing his expertise on sustainable urban farming practices.

Make sure you join us! Save your seat here

#venture360 #venturemeda #sustainability #bahirdar

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Partners with Children’s Surgery International for Pediatric Surgical Breakthrough

Bahir Dar, Ethiopia – Bahir Dar University (BDU) and Children’s Surgery International (CSI) have successfully concluded a transformative surgical week in Ethiopia, marking a significant milestone in pediatric healthcare.

The collaborative effort resulted in life-changing surgeries for 48 children, encompassing 31 ENT (Ear, Nose, and Throat) procedures and 17 urology cases. This achievement is particularly noteworthy as it includes two ENT surgeries independently performed by BDU’s own Dr. Melesse. This accomplishment represents a pivotal step towards establishing sustainable pediatric surgical care within Ethiopia.

A highlight of this partnership was the formal launch of the Pediatric Otolaryngology and Facial Plastic Surgery Fellowship at BDU. This groundbreaking initiative positions BDU as a pioneer in Ethiopia and one of only two institutions in sub-Saharan Africa offering such specialized training. By nurturing the next generation of pediatric surgeons, BDU and CSI are jointly working to expand access to quality healthcare for children across the country.

As the surgical team prepares to depart, volunteers will conduct final patient rounds tomorrow morning. This collaboration exemplifies the power of international partnerships in addressing critical healthcare needs and advancing medical education in Ethiopia.

Bahir Dar University is a leading academic institution in Ethiopia, committed to excellence in teaching, research, and community service. Through partnerships with organizations like Children’s Surgery International, BDU strives to make a lasting impact on the health and well-being of the Ethiopian people.

Children’s Surgery International is a global non-profit organization dedicated to providing life-saving surgeries to children in underserved communities worldwide. CSI works with local partners to build sustainable surgical programs and train healthcare professionals, ensuring long-term impact.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የጥራት አውደ ጥናት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞችን ያሳተፈ አውደ ጥናት በዩኒቨርሲቲው ጥበብ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር አንዳርጋቸው ሞገስ የጥራት ጉዳይ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመምህሩ፤ የተማሪውና የሰራተኛው የሁሉም የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ በበኩላቸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመማር ማስተማርና በምርምር ልህቀት እንዲሁም ተጽዕኖ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ለማበርከት በሙያ ያከናውናቸው ጥራት ተኮር ስራዎች እና እስከ አሁንም የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡በየደረጃው ያሉ አካላት ጥራት የኔ ጉዳይ ነው ብለው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ በኩል ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ለዚህም መምህራንና ሰራተኞችን መደገፍና ተማሪዎቻችን በእውቀት ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ከሚለዋወጠው አለም ጋር አብሮ የሚሄድ ማንንት እንዲላበሱ የሚያሥችሉ አስፈላጊ ክህሎቶችና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማረጋገጥ የሁላችንም ተግባር ሊሆን ይገባል በማለት መድረኩን ከንግግር ከፍተዋል።

በአውደ ጥናቱም ሁለት ቁልፍ መልዕክቶች በፕሮፌሰር ታደሰ መለሰ እና ፕሮፌሰር አበባው ይርጋ የቀረቡ ሲሆን፤ በዶ/ር ዝይን ምህረት፤ ዶ/ር ቀረብህ አስረስ፤ አቶ ተረፈ በላይ እና ዶ/ር አንዳርጋቸው ሞገስ አጠቃላይ የጥራት አስተዳደርን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው በተሳታፊዎች እና በባለ ድርሻ አካላት ውይይት የተደረገ ሲሆን ጥራት ሁሉን አቀፍ ስለመሆኑ፣ በየደረጃሁ ሁሉንም ባለድርሻ አካል የሚያሳትፍ ስለመሆኑ ተነስቷል።

አውደ ጥናቱ በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ በግማሽ ቀን ተካሂዷል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች 84.7% የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል

ፈተና ከተሰጠባቸው 79 ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች ሁሉንም ማሳለፍ ችለዋል።

ሐምሌ 09/2015ዓ/ም(የውስጥ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን-BDU) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ79 ፕሮግራሞች 3229 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በማስፈተን 84.7 በመቶ የማለፊያ በቂ ውጤት አስመዘገቡ።

በመደበኛው መርሐ ግብር ብቻ ፈተናውን ከወሰዱ 2843 ተማሪዎች ውስጥ 89.5 በመቶ ከ>50% ያመጡ ሲሆን ፈተና ከተሰጠባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% ሁሉም ተማሪዎች፣ በ14 ፕሮግራሞች ደግሞ በእያንዳንዱ ፕሮግራሞች 1ተማሪ ብቻ ሲቀር ሁሉም አልፈዋል።

በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር 45 ተማሪዎች ተፈትነው 55.3% ፣ በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር 305 ተማሪዎች ተፈትነው 43.9 ፣ በክረምት መርሐ ግብር 34 ተማሪዎች ተፈትነው 85.3% ያሳለፈ ሲሆን በሁሉም መርሐ ግብሮች 84.7 የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ጥራት ላለው ትምህርትና ምርምር አበክሮ የሚሰራው የ60ዓመት ባለፀጋው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዚሁ አጋጣሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የመስኮተ ጥበብ መሰናዶ ግብዣ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ህብረት ቀንን የተመለከተ ዝግጅት በመስኮተ ጥበብ የቴሌቪዥን መርሀግብር ተሰናድቷል፣ እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ።

https://youtu.be/zC4Uu7KT3HY

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህፀን ካንሰር ሰብ-ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን አስመረቀ *****የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ / gynecology oncology subspecialty / ከፍተኛ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች በዛሬው ዕለት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ የፍሪቦርግ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ ፕሮፌሰሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተሰጠውን ስልጠና አጠናቀው በዛሬው እለት ለምረቃ የበቁት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማሕፀን እና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር እያያ ምስጋን እና ዶ/ር ዳውድ ሙሐመድ ከሰኔ 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ /gynecology oncology subspecialty/ በመሆን የምርቃት ሰርቲፊኬታቸውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እጅ ተቀብለዋል፡፡በስልጠናው አስተዋፆ ለነበራቸው ጀርመን ሐገር ለሚገኜው ሆፕ ፕሮጀክት እና ለኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ ለሆኑት ለፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ለዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የእውቅና ሰርፊኬት ከዶ/ር ፍሬው ተገኘ እጅ ወስደዋል፡፡በመጨረሻም የሁለቱ ተቋማት ተወካይ የሆኑት ፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ እንደሀገር የተያዙ ተመሳሳይ የስልጠና ቦታዎች መካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጊዜው እና በሰዓቱ ሙያው በሚጠይቀው ልክ ስልጠናውን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም በመሆኑ ምስጋና አቅርበው የሰልጣኞች ተነሳሽነት እና የዩኒቨርሲቲውን ማኔጅመንት ለስልጠናው የነበራቸውን ቁርጠኝነት አመስግነው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት ለሚሰራቸው ማንኛውንም የጤናነክ ፕሮጀክቶች ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Our 60th Anniversary Closing Event in Pictures

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ማስታወቂያ

ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for applications for workshop participants
Working in solidarity with Ethiopian Research Universities: Writing and mentoring program for Early Career Researchers and PhD students
With the support of the British Academy, Bahir Dar University and Hawassa University in collaboration with the University of East London are implementing a two-year capacity-building program for 40 early career researchers and postgraduate students. The program aims to enhance the academic publishing capacity of research universities in Ethiopia through training workshops to improve scholarly writing skills and by creating a mentorship infrastructure. The context is the twofold global concern about low numbers of articles published in high-impact international peer-reviewed journals by academics living in the global south and poor representation of female academic authors from and living in the global south.
The program will support networking and collaborative opportunities for researchers within Ethiopian Universities and the University of East London. In addition to strengthening publication practices, it will empower women in academia, ensuring 50% of participants are women. Interested early career researchers and PhD students are cordially invited to apply to this program.
To apply, you must send all of the following documents to babdhu2023@gmail.com:
●Evidence of graduation from a Social Science PhD program
●Evidence of Master’s degree for those in the 2nd year or above of their PhD program
●Evidence of current employment in a research University in Ethiopia
●CV - 2 pages maximum, highlighting any writing activity
●A statement of no more than 250 words explaining:
o Why you wish to attend these workshops;
o Your ability to attend six one-day workshops over the 24-month duration of the program;
oPlease also confirm that you are willing to submit drafts of your writing for peer review
and develop it into an article that can be submitted to an academic journal.

Deadline: 15th June 2023 Applicant informed of outcome: End of June 2023
We particularly encourage applications from female scholars. Support workshops for women can be obtained by emailing: babdhu2023@gmail.com joining the following Zoom meeting links.

30th of May, 2023; time: 02:00 PM Nairobi time
https://us04web.zoom.us/j/73875620933?pwd=N1CuGu6vjOfDwanuvwet3MJvmGuRo2.1
Meeting ID: 738 7562 0933 Passcode: 5pGhVJ
1st of June, 2023; time: 04:00 PM Nairobi
https://us04web.zoom.us/j/71486735439?pwd=CcpbpTPmtKNqbMgobBadSt6RaX7IdC.1
Meeting ID: 714 8673 5439 Passcode: xRNjh6

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Just 19 days to our Anniversary closing ceremoney

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) ላይ ስልጠና ተሰጠ
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) የተሰኘ የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ከመጋቢት 23-24/2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሁሉም ግቢ ለሚገኙ አካል ጉደተኛ ተመራቂዎች በፔዳ ግቢ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ለአካል ጉዳተኛ ተመራቂዎች ስልጠናውን ያዘጋጁት የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ የስራ ክፍልና   ከፍታ ፕሮጀክት የተሰኘ ድርጅት በጋራ ሲሆኑ የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር ቀረብህ አስረስ የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያውቁና ከሌሎች በተሻለ መልኩ ስራ ለማፈላለግ ብሎም ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በቀላሉ ተግባብተው ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ  ታልሞ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ቀረብህ በማስከተል ተማሪዎች ከፅንሰ ሃሳቡ ትምህርት ጋር ይህ ስልጠና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ መሰጠቱ ከትምህርቱ ዓለም ወደ ስራው ሲቀላቀሉ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በቀላሉ እንዲተገብሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በዘንዘልማ ግቢ ለሚሰለጥኑት ተመራቂዎች የስልጠናውን ጠቀሜታ ያስገነዘቡት የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ ተገቢውን እውቀት እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አውስተው ተመርቀው ከወጡ በኋላም ወደ ስራው ዓለም በቀላሉ ለመቀላቀል ግንዛቤ ያገኙ ዘንድ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ወርቁ አክለውም ስልጠናው ከሌሎች ስልጠናዎች ለየት ያለና ተመራቂዎች በቀላሉ ስራ ለማፈላለግ የሚያግዝ ስልጠና በመሆኑ ለዘንዘለልማ ግቢ ተማሪዎች ቅድሚያ ቢሰጥም የመማር ማስተማሩን መርሃ ግብር በማይነካ መልኩ ለሁሉም ተመራቂዎች ስልጠናው ተደራሽ እንደሚሆን አስገንዝበው ተማሪዎች በነቃ ተሳትፎ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል፡፡
/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

የባሕር ዳር
ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና የዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ኤግዚቪሽን ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከባሕር ዳር ከተማ ከካቶሊክ ት/ቤት፣ከSOS ትምህርት ቤት፤STEM ትምህርት ቤቶች የመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከባሕር ዳር ዩኒቨርቲ ግቢዎች መካከል ሰላም ካንፓስ፣ የቴክኖሎጂ ተቋም (ፖሊ) እና ፔዳ ግቢን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍል የሳይኮሎጂ መምህር አቶ ታምሩ ደለለኝ ስለ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጠቅለል ያለ መረጃ ከአመሰራረቱ ጀምሮ አሁን እስካበት ደረጃ ያለውን የ60 ዓመት ጉዞ ታሪክ እና ያሳለፋቸውን ሁነቶች እንዲሁም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ትላልቅ ደረጃ ስለደረሱ፣ በአመራር ላይ ስላሉ ግለሰቦች፣ ስለ ትምህርት አሰጣጥ ጥራቱ ለተማሪዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመቀጠልም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሙዚየም ባለሙያ ወ/ሮ ኤልዳና ደሳለኝ የዚህ ጉብኝት ዓላማ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ60ኛ ዓመት ጉዞው ውስጥ ምን እንዳደረገ እና የት እንደደረሰ ለማስተዋወቅ በተጨማሪም እኒህ የሚጎበኙ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ምንነት አውቀው ለወደፊቱ ተመራጭ እንዲያደርጉት፣ ስለዩኒቨርሲቲ ያላቸው ንቃተ ህሌናም ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወ/ሮ ኤልዳና ወደ ፊት በባህር ዳር ከተማ ስር ያሉ ሌሎች የመንግስት ተማሪዎችም በዚህ ጉብኝት እንደሚሳተፉ እና ፕሮግራሙም እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም እንደሚቆይም ገልጸዋል፡፡ ከትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች ስለጉብኝቱ ከሰጡት ሀሳብ መካከል ከSTEM ማበልጸጊያ ማዕከል የመጣው ተማሪ ዮናታን አባይነህ ጉብኝቱ ጥሩ እንደሆነ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት ተመልክቶ ታሪኮችን ሰምተናል፡፡ የሰማነው ታሪክ ደስ የሚል ነበር፤ እኛም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ገብተን እንዲህ ያለ ታሪክ እንደሚኖረን ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ተማሪ ዮናታን አክሎም የተለያዩ ነገሮችንም አይተናል ይህን እድል ያላገኙት ሌሎች ተማሪዎችም እንዲጎበኙ ዩኒቨርሲቲው ቢያመቻችላቸው ሲል ሀሳቡን ገልጿል፡፡
ከSOS ትምህርት ቤት የመጣችው ተማሪ አና ያረጋል ጉብኝቱ አስደሳች እንደሆነና ሌሎች ተማሪዎችም እድሉ ቢመቻችላቸው እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደፊት የመማር እድሉ ቢገጥመኝ ደስተኛ ነኝ ብላለች፡፡ ሌላዋ ተማሪ ከካቶሊክ ትምህርት ቤት የመጣችው ናርዶስ ኃይሌ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመቱን አስቦ እኛን በመጥራቱ ደስተኛ ነን፡፡ ምክንያቱም የብዙዎቻችን ህይወት እዚህ ዩኒቨርሲቲ ላይ በመመስረቱና ብዙ ነገሮችን ማየት በመቻላችን ደስተኛ ነን ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን አይተን አናውቅም እናም ይህን እድል በማግኘታችን እናመሰግናለን፤ ትምህርት ቤቱ ወደ ፊትም እንዲህ አይነት ጉብኝቶችን ቢያዘጋጅ ጥሩ ነው ለተማሪዎች መነሳሳትን ይፈጥራል ብላለች፡፡

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የማኀበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ ማቅረቡን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
= = = = = = = =
ባሕርዳር: ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች፣ የአካዳሚ እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች አዳዲስ ግኝቶቻቸውን የሚያቀርቡበት 12ኛው ዓለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የምርምር ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እሰይ ከበደ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለመፍታት ሳይንሳዊ ምርምሮች አስፈላጊ መኾናቸውን በአጽንኦት ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የምርምር ሥራዎችን ወስዶ ወደ ገበያ በማቅረብ ረገድ ያለውን ክፍተት ለማስተካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥረት እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
ፕሮፌሰር እሰይ ዩኒቨርሲቲው በተከታታይ በሠራቸው ችግር ፈቺ ምርምሮች በአራት የምህንድስና መርሐ ግብሮች በዓለም አቀፍ የሕንፃ እና ቴክኖሎጂ አክሬዲቴሽን ቦርድ ዕውቅና በማግኘት ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም መኾን ችሏል ብለዋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር እና ሽግግር ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሙሉቀን ዘገዬ በጉባኤው ላይ 175 የምርምር ሐሳቦች ቀርበው አዲስ ሐሳብ የያዙ፣ ችግር ፈቺ የኾኑ፣ ዓለም አቀፍ የምርምር መሥፈርቶችን ያሟሉ 59 የምርምር ሥራዎች ለጉባኤው ቀርበዋልም ነው ያሉት።
በጉባኤው ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ተመራማሪዎች እርስ በእርስ በመወያየት እና በተለይ ነባሮቹ ለወጣት ተመራማሪዎች ዕውቀታቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
በባለፉት ዓመታት በተደረጉ ምርምሮች ችግር ፈቺ፣ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚጠቅሙ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ መቅረባቸውን ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ የቴክኖሎጂ ሐሳቦች መፍለቃቸውንም እንዲሁ።
በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሲቪል እና ውኃ ምህንድስና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አክሎግ (ዶ.ር ) ውኃ፣ ኀይል እና የምግብ ዋስትና ያላቸውን ተያያዥነት በተመለከተ ባቀረቡት ጽሑፍ "በሀገራችን ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ኀብረተሰቡ የተቸገረበት ጊዜ ነው" ብለዋል።
በገጠር እና በከተማ የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትም የማኀበረሰቡ ችግር በመኾኑ ንጹህ ውኃ ለሁሉም መቅረብ የሚችልበትን ዘዴ አሳይቻለሁ ነው ያሉት።
በቂ የኤሌክትሪክ ኀይል አለመኖርም የኀብረተሰቡን ኑሮ አክብዶታል ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ዳኛቸው እነዚህ ችግሮች ተሳስረው የሚፈቱበትን የምርምር ሐሳቦች ማቅረባቸውንም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቤል ፈለቀ ከአቅም ግንባታ አንጻር የምርምር ጉባኤው ለክልሉ የሚያበረክተው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት በዲጂታላይዜሽን እና ኦቶሜሽን ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ሠርተናል ያሉት ኮሚሽነር አቤል በቀጣይም ኮሚሽኑ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና አቅም ከማጎልበት አኳያ ዓለም አቀፍ ልምድ ካካበቱ ምሁራን ጋር ትስስር የምንፈጥርበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ማኀበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከጉባኤው ግብዓት ይገኝበታልም ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት ከ180 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ከ440 በሚልቁ የትምህርት መርሐ ግብሮች ተማሪዎችን ተቀብሎ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ እያስተማረ ይገኛል።

👉የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዛገባ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

You are kindly Invited!
Please, explore the detailed schedule from the conference website: https://icast-conf.eai-conferences.org/2024/

Today @1:30PM ከ7:30 ጀምሮ በዋሸራ አዳራሽ ፖሊ በአካል እንጠብቅዎታለን። በአካል መገኘት ካልቻሉ ባሉበት ሆነው በቨርቹዋል ይሳተፉ።

Virtual meeting details:
Topic: ICAST 2024 Plenary Session
Time: Nov 1, 2024 01:00 PM Nairobi

Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/88906953941?pwd=nEILOC8bn6UvMlT2ho0kkeGJDYLfY2.1

Meeting ID: 889 0695 3941
Passcode: 787148

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Institutional Memory
Blue Nile Club/ "ጥቁር አባይ ክበብ"/

Recently, I was able to find a metal plate dropped around Peda's water tower with a script "Blue Nile Club/ጥቁር አባይ ክበብ". Interviewing veteran staff and consulting documents of 1970s witnessed the names of various sport teams of Bahir Dar Academy of Pedagogy from 1970-1973 E.C. In those years, the club had won 5 trophies competing at provincial and "awraja" levels in basketball, athletics and football. In 1974 E.C, its name changed to Bahir Dar Teachers College (BDTC) sport club.The footballers picture attached was taken in 1972 E.C. It comprises of TTI, diploma and degree program students of the Academy. The player standing at far left from the camera is Demissie Zergaw (PhD) who was the gold medalist student of class of 1974 E.C and later became staff of BDTC & AAU.

Club BDTC had played friendly games for 32 consecutive years against Gondar College of Health and Medical Sciences.

Former instructors of Physical Education Department like Negaliku Afework and Wondimu Tadesse (AAU Staff and MP) had played a great part in organizing and strengthening the club in its formative years.

BDU has to revamp its former contributions in supporting at least the city's and region's sport sector development and strengthening its links with other academic institutions.
(Credit: Tamiru Delelegn)

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

EITEX Admissions Open!

Looking to pursue a career in the exciting world of textiles and fashion? 

EITEX is now accepting applications for the 2024/25 academic year!

Apply now and join a center of excellence in Africa!

Students who have passed the Grade 12 National Examination and have been placed at different Universities are invited to apply through the following link.

Link: [https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746](https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746)

"Wisdom at the Source of the Blue Nile!"

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቅዳሜ ሐምሌ 15/2015ዓ/ም እየደረሰ ነው...!
ባለፈው ዓመት ደማቅ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካሂደናል። ዘንድሮም በቀማቅ ልዩ ልዩ ሁነቶች ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየሠራን ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ስታዲየም 🏟️ ታሪካዊና ደማቅ ሁነቶችን በማካሄድ ላይ ነው። ከተማችን ውቢቷ ባሕር ዳር አስመራቂ እንግዶችን ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ነው

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Warmly Invited !!
Physical Science and Engineering (PSE) Seminar Series

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#አስደሳች_ዜና
==========
ከሀምሌ 19- 23/2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

መረጃው የተገኘው ከጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Centers of Excellence

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

✍️Register now for an IELTS test to be administered at Bahir Dar University on July 29, 2023. ✍️ Test type: Academic and General Training
✍️Contact us @ +251 908181110 or ieltsatbdu2022@gmail.com ✍️Venue: Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University, Jan Moscove Library
https://ieltsregistration.britishcouncil.org/ors/find-test "Your goal of having a life abroad becomes achievable with IELTS!"


/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for applications for workshop participants

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ኑ!ኑ!ኑ!

Reunion Weekend: Are you a former graduate of #Peda, #Poly or #BDU?
Have you missed your dormmates and campus friends; your former instructors and services providers; the lounge and cafe; classrooms, library, laboratory and workshops? TV rooms and cultural center (Auditorium); the palm and canopy streets and gardens; sport courts and intramural tournaments? Bahir Dar city, views of Abay and Tana?

Then, come and refresh your campus memories on the special occasion of Poly-Peda-BDU students' reunion weekend in the closing days of BDU'S 60th anniversary.

Date June 10 & 11, 2023 ( Sene 3& 4, 2015 E.C)

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#TGSH
ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ሕክምና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!!!
===============================================

(መጋቢት 18፣2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመልስ ያለመ ሲሆን እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም  የሚሰጥ ይሆናል።

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
SHARE SHARE

Читать полностью…
Subscribe to a channel