bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

-

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses' Students! www.bdu.edu.et Contact @bdu_tana_bot

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ በመደመኛው መርሃ ግብር የግል ትምህርት (Self Sponsor) መስጠት ጀመረ።
ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርስቲ ለመሆን መጠነ ሰፊ ቅደመ ዝግጅቶችን እያደረገ ሲሆን በተከታታይ ትምህርትና የማታ ኢ-መደበኛ መርሃ ግብሮች ትምህርት ፈላጊዎትች ከፍለው እንደሚማሩት ሁሉ በመደበኛው መርሃ ግብር በግላቸው የትምህርት ክፍያ እየፈጸሙ የሚማሩበትን አሰራር ይፋ አድርጓል።
ቀጣዩን ማስታወቂያ እነሆ✍️✍️✍️

#ማስታወቂያ

ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ:

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በመደበኛ መርሃ ግብር በግላቸው ከፍለው የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉና በግላችው ከፍለው መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ የሚፈልጉትን የትምህርት ፕሮግራም (Department) በመምረጥ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

#የመግቢያ_መስፈርት:-
✍️በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
✍️የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤

#ለማመልከት_የሚያስፈልጉ፣

✍️ የ12ኛ ክፍል ካርድ ወይም የአቅም ማሻሻያ ውጤት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ
✍️የማመልከቻ ክፍያ፤ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር

#የማመልከቻ_ቦታ፤
✍️በየአካዳሚክ ክፍል ባሉ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

#ማሳሰቢያ፡-
✍️ተማሪዎች የሚማሩብተ የትምህርት መስክ በመረጡት ይሆናል፡፡
✍️በቂ የአመልካች ቁጥር ያልተመዘገበበት የትምህርት መስክ አይከፈትም፡፡
✍️በርካታ አመልካቾች ያሉባቸው ፕሮግራሞች በውድድር የሚለዩ ይሆናል፡፡
✍️በአቅም ማሻሻያ ውጤት ለሚገቡ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት(Official Transcript) ከምዝገባ በፊት ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡

የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
(ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም)

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ELIC/BDU holds its annual program opening event

English Language Improvement Center/ELIC held the annual program opening event at Peda Campus of Bahir Dar university. In the event that hosted more than a couple of hundred students, a few teachers and graduate students, professor Abiy Yigzaw made a inspiring speech that aims to motivate students to join ELIC and be proficient in the language in short time. The professor who presented research supported and efficient language learning strategies emphasized the importance of cooperative learning. The event was introduced by Dr. Abebe Admasu, ELIC Head and officially inaugurated by Dr. Waltenigus Mekonnen, Dean of Faculty of Humanities.
In the event, Roza Tilahun presented Film based language activity as a way to inspire the new entrants and a presentation about the historical background and the major annual club activities of the center was presented by Dr. Fisseha Derso.
An brief but quite inspiring speech was also made by a former ELIC member and a student at Poly, School of Computing, Hasset Abrham. She explained the benefits she reaped as a participating student in the language improvement center at Peda.
The event was come to halt by Dr. Manendante Mulugeta, Director for External Relations and Partnership, BDU. While officially closing the event Dr. Manendante told the participants that participating in ELIC helpful. He told them how much his debate club students changed in their language and argumentation abilities in his tenure as debate coach a few years back. The director reiterated that students shouldn't bother about their background. He even insisted students with different level of language
(low to advanced) will surely benefit from their time in the center.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንስሳት ህክምና ያሰለጠናቸውን ዶክተሮችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ

የእንስሳት ህክምና ትምህርት ክፍል በትምህርት ቤትነት ማደጉም ተነግሯል።

(ጥቅምት 30/2017 ዓ/ም ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርና የአካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ትምህርት ክፍል በእንስሳት ህክምና ሙያ የትምህርት መስክ ዶክትሬት ያስተማራቸውን 21 ተማሪዎች በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

የምረቃ መርሐግብሩን በንግግር የከፈቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር መንገሻ አየነ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ት/ክፍል ከትምህርት ክፍልነት ወደ ትምህርት ቤትነት ያደገ መሆኑን አብስረው ያለንበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሳይንቲስቶች እንደሚሉት "በራስ መነሻ ወደ ራስ መድረሻ" የራስን ድልድይና ሀዲድ በመገንባት ሙያዊ አበርክቶቱን በቀጥታ ከመቀጠር ባለፈ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ራሳችሁን ሙሉ ተዋናይ ሁናችሁ መሳተፍ የሚገባችሁ ጊዜ ላይ ናችሁ ብለዋል።

ፕሬዚደንቱ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት "መጻዒ ዘመናችሁ በብዙ ድሎችና ተግዳሮቶች ላይ የሚቆም መሆኑን በመረዳት ዝግጁ ልትሆኑ ይገባል" በማለት መክረዋል።
ዶ/ር መንገሻ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በስራ ፈጠራና ቅጥር ብቁ ምሩቃንን እያፈራ መቀጠሉን በማስገንዘብ ለምሩቃኑ መልካም ዕድል ተመኝተዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ አያሌው ለተመራቂዎቹ የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን በመልዕክታቸውም ለአገራችን የእንስሳት ህክምና ዘርፉ አዲስ ተስፋዎች በመሆናችሁ ለአገራችሁን ለወገናችሁ ጠቃሚ በመሆን የተጣለባችሁን ሙያው ሃላፊነት ለመወጣት በቀጣይነት ባገኛችሁት እውቀት አገልጋዮች መሆን እንደሚገባቸው መክረዋል። የክብር እንግዳው በስራ መመሪያቸው አክለው እንደተናገሩት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ ሰፊ ድጋፍ መስጠቱን በማስታወስ በቀጣይም ከተቋሙ ባገኛችሁት እውቀት ለአገር አለኝታ ዜጎች መሆን እንደሚገባቸው በአንክሮ ለተመራቂዎቹ በመናገር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ የ "ብሩክ ኢትዮጵያ" በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ክሊኒክ እና የእንስሳት ደህንነት በዕለቱለሚያደርገው የአጋርነት ሰናይ ስራው እውቅና ተሰጥቶታል።

በእለቱ በእንስሳት ህክምና (Veterinary Medicine) በዶክተርነት ከተመረቁ ተማሪዎች ውስጥ ዶ/ር ዘላለም በላይነህ 3.97 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ ከተመራቂዎች አንደኛ በመሆን የወርቅና መዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ከሴቶች ዶ/ር ሶስና አሸናፊ አንደኛ በመውጣት የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

እንዲሁም ሰሎሞን ሽብሩ 3.89 በማምጣት ሁለተኛ ፣ ዶ/ር ሀቢብ ሀብታሙ 3.87 በማግኘት ሶስተኛ በመሆን እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በመጨረሻም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈረም ለረጅም አመታት ሲሰራ የቆየውን ብሩክ ኢትዮጵያ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጧቸዋል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ መምህራን፣ ተመራቂ ተማሪዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል፡፡
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ህክምና ዶክተሮችን አሰልጥኖ ሲያስመርቅ ይህ የመጀመሪያው ነው።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University School of Law students Yonas Muche, Roza Yimer, and Yeabsira Belete are representing Bahir Dar University and Ethiopia in the All Africa Moot Court Competition on International Humanitarian Law (IHL).

After a tough competition, the team has advanced to the semifinals. The competition, organized by the ICRC, is taking place in Nairobi, Kenya.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

🌟 Congratulations to Bahir Dar University Students for Achieving 2nd Place in the Global Social Logistics Student Challenge! 🌟

We are thrilled to announce that our talented students from the Department of Logistics and Supply Chain Management, College of Business and Economics, have secured 2nd place in the 2024 Social Logistics Student Challenge, organized by the Global Business School Network (GBSN), which was established by the World Bank in 2003 to enhance access to quality, locally relevant management education for the developing world.

This prestigious challenge immerses learners in a dynamic, digital environment, fostering teamwork, collaboration, and innovative thinking to solve societal problems through logistics principles and technology.

This success reflects the dedication of our students and the exceptional guidance of our staff and mentors who have played a crucial role in their journey. We also extend our heartfelt appreciation to our valued partner, the Khune Foundation, whose ongoing support has been instrumental in strengthening our Department of Logistics and Supply Chain Management and to our students' achievements in this competition.

Bahir Dar University is immensely proud of its students, staff, and partners as we celebrate this international recognition.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የማኀበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ ማቅረቡን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
= = = = = = = =
ባሕርዳር: ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች፣ የአካዳሚ እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች አዳዲስ ግኝቶቻቸውን የሚያቀርቡበት 12ኛው ዓለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የምርምር ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እሰይ ከበደ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለመፍታት ሳይንሳዊ ምርምሮች አስፈላጊ መኾናቸውን በአጽንኦት ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የምርምር ሥራዎችን ወስዶ ወደ ገበያ በማቅረብ ረገድ ያለውን ክፍተት ለማስተካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥረት እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
ፕሮፌሰር እሰይ ዩኒቨርሲቲው በተከታታይ በሠራቸው ችግር ፈቺ ምርምሮች በአራት የምህንድስና መርሐ ግብሮች በዓለም አቀፍ የሕንፃ እና ቴክኖሎጂ አክሬዲቴሽን ቦርድ ዕውቅና በማግኘት ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም መኾን ችሏል ብለዋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር እና ሽግግር ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሙሉቀን ዘገዬ በጉባኤው ላይ 175 የምርምር ሐሳቦች ቀርበው አዲስ ሐሳብ የያዙ፣ ችግር ፈቺ የኾኑ፣ ዓለም አቀፍ የምርምር መሥፈርቶችን ያሟሉ 59 የምርምር ሥራዎች ለጉባኤው ቀርበዋልም ነው ያሉት።
በጉባኤው ከሀገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ተመራማሪዎች እርስ በእርስ በመወያየት እና በተለይ ነባሮቹ ለወጣት ተመራማሪዎች ዕውቀታቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
በባለፉት ዓመታት በተደረጉ ምርምሮች ችግር ፈቺ፣ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚጠቅሙ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ መቅረባቸውን ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ የቴክኖሎጂ ሐሳቦች መፍለቃቸውንም እንዲሁ።
በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሲቪል እና ውኃ ምህንድስና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አክሎግ (ዶ.ር ) ውኃ፣ ኀይል እና የምግብ ዋስትና ያላቸውን ተያያዥነት በተመለከተ ባቀረቡት ጽሑፍ "በሀገራችን ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ኀብረተሰቡ የተቸገረበት ጊዜ ነው" ብለዋል።
በገጠር እና በከተማ የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትም የማኀበረሰቡ ችግር በመኾኑ ንጹህ ውኃ ለሁሉም መቅረብ የሚችልበትን ዘዴ አሳይቻለሁ ነው ያሉት።
በቂ የኤሌክትሪክ ኀይል አለመኖርም የኀብረተሰቡን ኑሮ አክብዶታል ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ዳኛቸው እነዚህ ችግሮች ተሳስረው የሚፈቱበትን የምርምር ሐሳቦች ማቅረባቸውንም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቤል ፈለቀ ከአቅም ግንባታ አንጻር የምርምር ጉባኤው ለክልሉ የሚያበረክተው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት በዲጂታላይዜሽን እና ኦቶሜሽን ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ሠርተናል ያሉት ኮሚሽነር አቤል በቀጣይም ኮሚሽኑ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና አቅም ከማጎልበት አኳያ ዓለም አቀፍ ልምድ ካካበቱ ምሁራን ጋር ትስስር የምንፈጥርበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ማኀበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከጉባኤው ግብዓት ይገኝበታልም ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት ከ180 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ከ440 በሚልቁ የትምህርት መርሐ ግብሮች ተማሪዎችን ተቀብሎ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ እያስተማረ ይገኛል።

👉የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዛገባ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

You are kindly Invited!
Please, explore the detailed schedule from the conference website: https://icast-conf.eai-conferences.org/2024/

Today @1:30PM ከ7:30 ጀምሮ በዋሸራ አዳራሽ ፖሊ በአካል እንጠብቅዎታለን። በአካል መገኘት ካልቻሉ ባሉበት ሆነው በቨርቹዋል ይሳተፉ።

Virtual meeting details:
Topic: ICAST 2024 Plenary Session
Time: Nov 1, 2024 01:00 PM Nairobi

Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/88906953941?pwd=nEILOC8bn6UvMlT2ho0kkeGJDYLfY2.1

Meeting ID: 889 0695 3941
Passcode: 787148

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Institutional Memory
Blue Nile Club/ "ጥቁር አባይ ክበብ"/

Recently, I was able to find a metal plate dropped around Peda's water tower with a script "Blue Nile Club/ጥቁር አባይ ክበብ". Interviewing veteran staff and consulting documents of 1970s witnessed the names of various sport teams of Bahir Dar Academy of Pedagogy from 1970-1973 E.C. In those years, the club had won 5 trophies competing at provincial and "awraja" levels in basketball, athletics and football. In 1974 E.C, its name changed to Bahir Dar Teachers College (BDTC) sport club.The footballers picture attached was taken in 1972 E.C. It comprises of TTI, diploma and degree program students of the Academy. The player standing at far left from the camera is Demissie Zergaw (PhD) who was the gold medalist student of class of 1974 E.C and later became staff of BDTC & AAU.

Club BDTC had played friendly games for 32 consecutive years against Gondar College of Health and Medical Sciences.

Former instructors of Physical Education Department like Negaliku Afework and Wondimu Tadesse (AAU Staff and MP) had played a great part in organizing and strengthening the club in its formative years.

BDU has to revamp its former contributions in supporting at least the city's and region's sport sector development and strengthening its links with other academic institutions.
(Credit: Tamiru Delelegn)

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

EITEX Admissions Open!

Looking to pursue a career in the exciting world of textiles and fashion? 

EITEX is now accepting applications for the 2024/25 academic year!

Apply now and join a center of excellence in Africa!

Students who have passed the Grade 12 National Examination and have been placed at different Universities are invited to apply through the following link.

Link: [https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746](https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746)

"Wisdom at the Source of the Blue Nile!"

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቅዳሜ ሐምሌ 15/2015ዓ/ም እየደረሰ ነው...!
ባለፈው ዓመት ደማቅ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካሂደናል። ዘንድሮም በቀማቅ ልዩ ልዩ ሁነቶች ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየሠራን ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ስታዲየም 🏟️ ታሪካዊና ደማቅ ሁነቶችን በማካሄድ ላይ ነው። ከተማችን ውቢቷ ባሕር ዳር አስመራቂ እንግዶችን ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ነው

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Warmly Invited !!
Physical Science and Engineering (PSE) Seminar Series

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#አስደሳች_ዜና
==========
ከሀምሌ 19- 23/2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

መረጃው የተገኘው ከጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Centers of Excellence

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

December 2/2024
Vacancy announcement
******
Bahir Dar University would like to hire qualified and competent professionals in its vacant positions. Please see the details of the vacancy and the requirements required from the documents attached herewith.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 23/03/2017 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ(በድጋሜ የወጣ)
--------------------------------------
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለSchool of Earth Science አካዳሚክ ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም በወጣው ማስታወቂያ በቂ አመልካች ባለመኖሩ ለተጨማሪ ቀናት ማራዘም አስፈልጓል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ለSchool of Earth Science አካዳሚክ ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ህዳር 23 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Alumni Stories: Academy of Presidents!

BDU have had 6 Presidents since PTI (BiT-BDU) and Peda (BDTC) merged together 25 years ago. 3 of its 6 presidents, Tsehaye Jemberu (PhD), Ambassador Yeshimebrat Mersha (PhD) and Mengesha Ayene (PhD) received their bachelor degrees from Peda (BDTC).

The first two got their degrees with Pedagogical Sciences in 1975 E.C and 1984 E.C respectively whereas the later graduated in 1994 E.C. with B.Ed. in Physics.

Ambassador Dr.Yeshimebrat was actually the first female university president in the country's history.

Astoundingly, in 2015 E.C. while BDU was celebrating its Diamond Jubilee, about 25% (10) of Ethiopian public universities presidents were graduates of Peda (9) and Poly (1). The universities lead then by BDU alumni include the likes of Gondar, Arbaminch, Adama, Ambo, Kotebe, Debre-Markos, Debre-Tabor, Wollo, Assosa and Worabe.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 28/02/2017 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
--------------------------------------
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለህግ ት/ቤት አካዳሚክ ም/ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ለህግ ት/ቤት አካዳሚክ ም/ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ጥቅምት 28 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

12ኛው የEAI አለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ኮንፈረንስ (ICAST 2024) ተካሄደ

*****

ጥቅም
ት 24/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) 12ኛው አለም አቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገቶች (ICAST 2024) ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ በዋሸራ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽነሩን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከጥቅምት 22-24/2017ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ላይ ትኩረቱን በማድረግ አካሂዷል፡፡ 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 12ኛውን ዓለማቀፍ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አውደጥናት በንግግር የከፈቱት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እሰይ ከበደ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም በየዓመቱ ትኩረቱን የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን መሰረት ያደረገ ዓለማቀፍ አውደጥናቶችን እንደሚያካሂድ ገልፀው፤ በአውደጥናቱ ላይ የሚቀርቡ የምርምር ፁሁፎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆነው  ስፕሪንገር (Springer) ጆርናል ላይ በመውጣት በመላው ዓለም ላሉ ህዝቦች ፣ ሳይንቲስቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት በመድረስ የዩነቨርሲቲውን የምርምር ስራዎች ጎልተው እንዲዎጡ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ የምርምር ስራዎች ከህትመት ባለፈ ቴክኖሎጅን በማሻገር ዩኒቨርሲቲው የራሱን አስተዋፆ እያደረገ መሆኑን ገልፀው በተመሳሳይ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ምርምሮች በአራት የምህንድስና መርሐ ግብሮች በዓለም አቀፍ የሕንፃ እና ቴክኖሎጂ አክሬዲቴሽን ቦርድ ዕውቅና በማግኘት ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የላቀ ውጤት ማስመዝገቡ የበለጠ ለመስራት ጉልበት እንደሚሆናቸው ፕሮፌሰር እሰይ ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ በበኩላቸው ተቋሙ ባለፉት አስራ አንድ ተከታታይ ዓመታት በተደረጉ አውደጥናቶች የተለያዩ ችግር ፈቺ ምርምሮች፣ ለማህበረሰቡ እና ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚጠቅሙ  አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ወደ ገበያ መቅረባቸውን ተከትሎ  ለተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎች አዳዲስ የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

በአውደጥናቱ ላይ ፐሮፌሰር ደስታ መብራቱ እና ፐሮፌሰር ማሞ ሙጨ ከደቡብ አፍሪካ በዙም ገብተው ለአፍሪካ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ልማት ስልታዊ ለውጦች እና እንደገና ማሰብ እንዲሁም  እንደገና መንደፍ ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ለዘላቂ ልማት ለሁሉም የሰው ልጅ ለአንድ የዓለም ማህበረሰብ  በሚል ርዕስ ቁልፍ መልክት ለአውደጥናቱ ተሳታፊዎች አስተላልፈዋል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Hosts Prestigious Conference on Science and Technology

Bahir Dar University, Ethiopia (November 1, 2024) –The 12th International Conference on Advances in Science and Technology (ICAST 2024) commenced today at the Washera Hall of the Bahir Dar University Institute of Technology campus. This annual event serves as a significant platform for scientists, engineers, and industry professionals to engage in meaningful discussions aimed at leveraging science and technology to tackle pressing societal challenges.
The conference was inaugurated by Professor Essey Kebede, Vice President of Academic Affairs at Bahir Dar University. In his opening remarks, Professor Essey underscored the critical need for collaboration among various stakeholders within the scientific community to effectively address current global issues. He emphasized that such partnerships are essential for fostering innovation and advancing knowledge.
Dr. Mitiku Damte, Acting Scientific Director of the Institute of Technology, also welcomed participants, expressing appreciation for their commitment to finding innovative solutions to pressing problems. His speech highlighted the importance of ICAST 2024 in promoting scientific advancement and technological innovation.
Over the next two days, attendees will participate in a series of technical sessions, keynote addresses, and panel discussions covering a wide array of topics, including: Artificial Intelligence and Machine Learning Renewable Energy and Sustainable Development, Biotechnology and Biomedical Engineering, Information and Communication Technologies, and Materials Science and Nanotechnology
ICAST 2024 aims to inspire critical thinking and stimulate interdisciplinary collaboration, fostering new partnerships among professionals in the field. By showcasing the latest research findings and industry trends, this conference seeks to drive innovation and contribute to a more sustainable future.
This gathering not only highlights advancements in science and technology but also reinforces Bahir Dar University's dedication to addressing global challenges through research and innovation.

Bahir Dar University, Ethiopia
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Get ready, Bahirdar!

Join us this Thursday, October 31Morning (8:30 AM - 12:00 PM) at Washera Hall, BIT inside the university of Bahirdar for an insightful conversation on Urban Agriculture Sustainability.

Keynote speaker Gulilat Menbere, an entrepreneur and lecturer, will be sharing his expertise on sustainable urban farming practices.

Make sure you join us! Save your seat here

#venture360 #venturemeda #sustainability #bahirdar

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University Partners with Children’s Surgery International for Pediatric Surgical Breakthrough

Bahir Dar, Ethiopia – Bahir Dar University (BDU) and Children’s Surgery International (CSI) have successfully concluded a transformative surgical week in Ethiopia, marking a significant milestone in pediatric healthcare.

The collaborative effort resulted in life-changing surgeries for 48 children, encompassing 31 ENT (Ear, Nose, and Throat) procedures and 17 urology cases. This achievement is particularly noteworthy as it includes two ENT surgeries independently performed by BDU’s own Dr. Melesse. This accomplishment represents a pivotal step towards establishing sustainable pediatric surgical care within Ethiopia.

A highlight of this partnership was the formal launch of the Pediatric Otolaryngology and Facial Plastic Surgery Fellowship at BDU. This groundbreaking initiative positions BDU as a pioneer in Ethiopia and one of only two institutions in sub-Saharan Africa offering such specialized training. By nurturing the next generation of pediatric surgeons, BDU and CSI are jointly working to expand access to quality healthcare for children across the country.

As the surgical team prepares to depart, volunteers will conduct final patient rounds tomorrow morning. This collaboration exemplifies the power of international partnerships in addressing critical healthcare needs and advancing medical education in Ethiopia.

Bahir Dar University is a leading academic institution in Ethiopia, committed to excellence in teaching, research, and community service. Through partnerships with organizations like Children’s Surgery International, BDU strives to make a lasting impact on the health and well-being of the Ethiopian people.

Children’s Surgery International is a global non-profit organization dedicated to providing life-saving surgeries to children in underserved communities worldwide. CSI works with local partners to build sustainable surgical programs and train healthcare professionals, ensuring long-term impact.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የጥራት አውደ ጥናት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞችን ያሳተፈ አውደ ጥናት በዩኒቨርሲቲው ጥበብ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር አንዳርጋቸው ሞገስ የጥራት ጉዳይ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመምህሩ፤ የተማሪውና የሰራተኛው የሁሉም የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ በበኩላቸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመማር ማስተማርና በምርምር ልህቀት እንዲሁም ተጽዕኖ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ለማበርከት በሙያ ያከናውናቸው ጥራት ተኮር ስራዎች እና እስከ አሁንም የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡በየደረጃው ያሉ አካላት ጥራት የኔ ጉዳይ ነው ብለው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ በኩል ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ለዚህም መምህራንና ሰራተኞችን መደገፍና ተማሪዎቻችን በእውቀት ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ከሚለዋወጠው አለም ጋር አብሮ የሚሄድ ማንንት እንዲላበሱ የሚያሥችሉ አስፈላጊ ክህሎቶችና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማረጋገጥ የሁላችንም ተግባር ሊሆን ይገባል በማለት መድረኩን ከንግግር ከፍተዋል።

በአውደ ጥናቱም ሁለት ቁልፍ መልዕክቶች በፕሮፌሰር ታደሰ መለሰ እና ፕሮፌሰር አበባው ይርጋ የቀረቡ ሲሆን፤ በዶ/ር ዝይን ምህረት፤ ዶ/ር ቀረብህ አስረስ፤ አቶ ተረፈ በላይ እና ዶ/ር አንዳርጋቸው ሞገስ አጠቃላይ የጥራት አስተዳደርን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው በተሳታፊዎች እና በባለ ድርሻ አካላት ውይይት የተደረገ ሲሆን ጥራት ሁሉን አቀፍ ስለመሆኑ፣ በየደረጃሁ ሁሉንም ባለድርሻ አካል የሚያሳትፍ ስለመሆኑ ተነስቷል።

አውደ ጥናቱ በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ በግማሽ ቀን ተካሂዷል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች 84.7% የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል

ፈተና ከተሰጠባቸው 79 ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች ሁሉንም ማሳለፍ ችለዋል።

ሐምሌ 09/2015ዓ/ም(የውስጥ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን-BDU) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ79 ፕሮግራሞች 3229 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በማስፈተን 84.7 በመቶ የማለፊያ በቂ ውጤት አስመዘገቡ።

በመደበኛው መርሐ ግብር ብቻ ፈተናውን ከወሰዱ 2843 ተማሪዎች ውስጥ 89.5 በመቶ ከ>50% ያመጡ ሲሆን ፈተና ከተሰጠባቸው ፕሮግራሞች ውስጥ 32 ፕሮግራሞች 100% ሁሉም ተማሪዎች፣ በ14 ፕሮግራሞች ደግሞ በእያንዳንዱ ፕሮግራሞች 1ተማሪ ብቻ ሲቀር ሁሉም አልፈዋል።

በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር 45 ተማሪዎች ተፈትነው 55.3% ፣ በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር 305 ተማሪዎች ተፈትነው 43.9 ፣ በክረምት መርሐ ግብር 34 ተማሪዎች ተፈትነው 85.3% ያሳለፈ ሲሆን በሁሉም መርሐ ግብሮች 84.7 የመውጫ ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ጥራት ላለው ትምህርትና ምርምር አበክሮ የሚሰራው የ60ዓመት ባለፀጋው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዚሁ አጋጣሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የመስኮተ ጥበብ መሰናዶ ግብዣ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ህብረት ቀንን የተመለከተ ዝግጅት በመስኮተ ጥበብ የቴሌቪዥን መርሀግብር ተሰናድቷል፣ እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ።

https://youtu.be/zC4Uu7KT3HY

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህፀን ካንሰር ሰብ-ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን አስመረቀ *****የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ / gynecology oncology subspecialty / ከፍተኛ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች በዛሬው ዕለት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ የፍሪቦርግ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ ፕሮፌሰሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተሰጠውን ስልጠና አጠናቀው በዛሬው እለት ለምረቃ የበቁት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማሕፀን እና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር እያያ ምስጋን እና ዶ/ር ዳውድ ሙሐመድ ከሰኔ 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ /gynecology oncology subspecialty/ በመሆን የምርቃት ሰርቲፊኬታቸውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እጅ ተቀብለዋል፡፡በስልጠናው አስተዋፆ ለነበራቸው ጀርመን ሐገር ለሚገኜው ሆፕ ፕሮጀክት እና ለኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ ለሆኑት ለፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ለዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የእውቅና ሰርፊኬት ከዶ/ር ፍሬው ተገኘ እጅ ወስደዋል፡፡በመጨረሻም የሁለቱ ተቋማት ተወካይ የሆኑት ፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ እንደሀገር የተያዙ ተመሳሳይ የስልጠና ቦታዎች መካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጊዜው እና በሰዓቱ ሙያው በሚጠይቀው ልክ ስልጠናውን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም በመሆኑ ምስጋና አቅርበው የሰልጣኞች ተነሳሽነት እና የዩኒቨርሲቲውን ማኔጅመንት ለስልጠናው የነበራቸውን ቁርጠኝነት አመስግነው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት ለሚሰራቸው ማንኛውንም የጤናነክ ፕሮጀክቶች ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

/channel/bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Our 60th Anniversary Closing Event in Pictures

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ማስታወቂያ

ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

@bahir_dar_university

Читать полностью…
Subscribe to a channel