የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሕጻናትና አቅመ ዳካማ አረጋዊያን ጋር የገና በዓልን አሳልፈዋል
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዝግባ ሕጻናትና አረጋዊያን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት በመረዳት ላይ ለሚገኙ ወገኖች የምሳ ግብዣ በማድረግ በዓልን አሳልፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ተገኝተው ድርጅቱን በመጎብኘት ለዚህ መልካም ተግባር ትኩረት ለሰጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች አድናቆታቸውን ችረዋል።
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
#Announcement
Second Round of GAT Training
To Interested PG Applicants
The Science College and Faculty of Humanities at Bahir Dar University are pleased to announce the second round of GAT training scheduled for Tir 1-4, 2017 E.C.
The training will focus on the following key areas:
Verbal Reasoning: Tests reading comprehension, vocabulary, and the ability to understand and analyze written material.
Quantitative Reasoning: Measures mathematical skills, including arithmetic, algebra, geometry, and data analysis.
Analytical Writing: Assesses critical thinking and the ability to articulate complex ideas clearly (in versions of the GAT that include a writing component).
Training Schedule:
Tir 1-2, 2017 E.C.: Online Training
Portal for Online Training:https://lms.bdu.edu.et
Tir 3-4, 2017 E.C.: Face-to-Face Training
Venue for Face-to-Face Training: Science College Smart Rooms, Peda Campus
Coordinators:
Prof. Tsegaye Kassa: 0920761042
Dr. Ayenew Guadu: 0967610008
Trainers: Experts from the Departments of Mathematics and English Language and Literature
We encourage all interested postgraduate applicants to take advantage of this valuable opportunity to prepare for the NGAT.
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና (CPD) ዕውቅና ሰጪ ተቋም ሆኖ ፈቃድ አጊኝቷል።
ኮሌጁ ለሌሎች ማዕከላት ዕውቅና የመስጠት ፈቃድ (CPD Accreditor) ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን አሳውቋል።
ይህም ኮሌጁ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችለው ሲሆን፤ ፈቃዱ ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና Continuing Professional Development (CPD) የሚሰጡ ከ250 ተቋማት እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
ደማቅ የስነጽሁፍ ምሽት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲ ፋኩሊቲ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ት/ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪዎች የስነፅሑፍ ኮርስን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የጥበብ ምሽት አዘጋጅተዋል፡፡
ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ክፍት የነበረው ይህ መድረክ የተለያዩ የኪነጥበብ ዘውጎች ያላቸው ስራዎች በተማሪዎች ቀርበውበታል፡፡
በመክፈቻው መርሃ ግብር የሲኒማና ቴአትር ጥበባት መምህር አቶ ግርማው አሸብር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የስነጽሁፍ ምሽቱ የተዘጋጀው ለተማሪዎቹ ኮርስ ማሟያነት ሲሆን እግረ መንገዱንም ለግቢው ማህበረሰብ በአዝናኝነትና በአስተማሪነታቸው የተመረጡ ስራዎች ለመድረኩ በተማሪዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው በቀጣይም የስነጽሁፍ ምሽቶች ውስን በሆነ ጊዜ ለግቢው ማህበረሰብ ቢቀርቡ ሊኖራቸው የሚችለውን ፋይዳ አስገንዝበዋል፡፡
የኮርሱ መምህር የሆኑት አቶ ግርማው አክለውም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሰጡ ኮርሶች በተግባር መደገፍ ያለባቸው መሆኑን በመናገር የ2ኛ ዓመት የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ተማሪዎችም የስነጽሁፍ መግቢያ ኮርሳቸውን ምክንያት በማድረግ በክፍል ውስጥ የተማሩትን በመድረክ ለማሳየት እና ስነጽሁፍ በመድረክ እንዴት ይህንመከወን እንዳለበት ለመለማመድ ሲባል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አሳውቀዋል።
በመርሃ-ግብሩ በትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች የተዘጋጁ ግጥሞች፣ መነባንብ፣ ቅኔ እና ሀገራዊ መልዕክት ያላቸው የሙዚቃ ስራዎች ቀርበው ታዳሚዎቹን ሲያዝናኑ አምሽተዋል፡፡ በዕለቱ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተጋባዥ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በመድረኩ ታድመዋል።
በመድረኩ በታዳሚነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር ለማ ካሳዬ የቀድሞ የባህል ማዕከል የተማሪነት ዘመን ተሳትፏቸውን በማስታወስ ትዝታቸውን አካፍለዋል፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ወደዚህ መድረክ በኪነጥበብ ክዋኔ መጋበዛቸውን በማስታወስ ቀድሞ በተማሪነታቸው ጊዜ ሲጫወቷቸው ከነበሩ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊያን ዜማዎች ውስጥ የኤፍሬም ታምሩን ዜማዎች ለታዳሚው አንጎራጉረዋል፡፡ ዶ/ር ለማ አክለውም በቀጣይ ይህን አይነት ቋሚ የስነ-ጽሁፍ መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል፡፡
የሂውማኒቲ ፋካሊቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት ዶ/ር ተመስገን በየነ የመርሃ ግሩን መዘጋጀት በማድነቅ መማር ማስተማር ሂደቱ በተግባር መደገፉ ለተማሪዎች ጥሩ እድል የሚሰጥ መሆኑን በማስታወስ የተለያዩ የጥበብ ዘውጎች በአንድ መድረክ ሲቀርቡ ውብ በመሆናቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ተመስገን አክለውም ይህ አይነት የጥበብ መድረኮች በሲኒማና ቴአትር፣ አዲስ በተከፈተው የሙዚቃ ጥበብ መርሃ ግብር ፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ባህል ማዕከል በትብብር በመደበኛ መርሃ ግብር እየተዘጋጀ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የሐዘን መግለጫ
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ አለበል በአጋጠማቸው ድንገተኛ ሕልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ በሙሉ ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን!
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ታሕሳስ 23/2017 ዓ/ም
Condolence Statement
Bahir Dar University expresses its deepest sorrow and extends its sincerest condolences on the sudden passing of Ato Tewodros Alebel, a valued lecturer and esteemed researcher in the Department of Amharic Language and Literature.
We recognize and deeply appreciate Ato Tewodros's significant contributions to the department and the university as a whole. His dedication to teaching, research, and academic excellence will be deeply missed.
Our thoughts are with his family, friends, colleagues, and the entire Bahir Dar University community during this difficult time.
‹‹ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙሃን››
የመጽሀፍ ምረቃ
በዩኒቨርስቲያችን የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ት/ክፍል ባልደረባና ለረጅም አመታት በጋዜጠኝነት ስራ ያገለገሉት ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ ‹‹ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙሃን›› በሚል ርዕስ አዲስ መፅሀፍ በቅርቡ አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡
በመሆኑም መፅሀፉ አርብ ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዊዝደም ህንፃ፣ ከቀኑ 8:00 ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ ምሁራን፣ የተቋሙ አመራሮችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኘበት ደማቅ ስነ-ስርዓት በዩኒቨርቲያችን ስለሚመረቅ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት በመገኘት የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት
Happy New Year 2025!
As we welcome this new year, Bahir Dar University extends its gratitude to all its partners for your unwavering collaboration and support.
Together, we have achieved remarkable milestones, and we look forward to a brighter year ahead filled with growth, opportunities, and shared success.
May 2025 bring all celebrating happiness, success, and prosperity!
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
Bahir Dar University Hosts Stakeholders Consultative Workshop on Lake Tana Water Hyacinth and Water Quality Monitoring
(December 27, 2024) Bahir Dar University, Ethiopia – Bahir Dar University (BDU) successfully hosted a Scientific Project Stakeholders Consultative Workshop on Remote Sensing for Community-driven Applications: from WA+ to Co-learning (RS-4C), focusing on Lake Tana Water Hyacinth and Water Quality Monitoring.
The workshop brought together key stakeholders, including researchers, government officials, and community representatives, to collaboratively address the urgent environmental challenges facing the vital lake.
The workshop commenced with welcoming remarks from Dr. Muluken Zegeye, Deputy Scientific Director for Research and Community Service at BDU, who emphasized the crucial need for collaborative efforts to protect and sustainably manage Lake Tana.
Dr. Claire Mikhailovsky, RS-4C Project Leader, IHE Delft Institute for Water Education , the Netherlands, in a recorded video presentation, introduced the RS-4C project, highlighting its focus on bridging the gap between the growing availability of remote sensing data and its effective utilization by communities. The project emphasizes a community-centric approach, prioritizing co-identification of issues, co-development of tools, integration of local knowledge, and fostering local ownership.
Dr. Minyichil Gitaw, Deputy Scientific Director for Administrative Affairs at BDU and Project Co-PI, presented findings on the significant impact of water hyacinth infestation on Lake Tana's water quality.
Dr. Goraw Goshu, Director of the Blue Nile Water Institute and Project PI, shared the progress of the RS-4C project, emphasizing key findings on the watershed export of nutrients and its detrimental effects on the lake's ecosystem.
Dr. Ayalew Wondie, General Director of the Lake Tana and Other Water Bodies Protection Agency in Amhara Region, discussed the multifaceted challenges and potential opportunities for effective water hyacinth management in Lake Tana. Dr. Assefa Tessema from Wollo University provided valuable comparative insights by presenting on water management challenges in the Lake Hayq-Ardibo Catchment.
A lively panel discussion followed, moderated by Prof. Yihenew G/Selassie, where experts debated effective water hyacinth management strategies, explored the potential of remote sensing technology for environmental monitoring, and discussed opportunities for collaborative action among stakeholders.
The workshop, organized by in collaboration with the Bahir Dar Institute of Technology and the Blue Nile Water Institute, served as a vital platform for fostering dialogue and collaboration among diverse stakeholders in addressing the pressing environmental challenges facing Lake Tana. By bringing together researchers, government agencies, and community representatives, the workshop aimed to pave the way for innovative and sustainable solutions to protect this vital resource for generations to come.
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
BDU Researcher Wins Prestigious Young Statistician Showcase Award
We are delighted to announce that Getahun Mulugeta Awoke, an Assistant Professor and PhD candidate at Bahir Dar University, has been awarded the prestigious Young Statistician Showcase Award at the 32nd International Biometric Conference (IBC) in Atlanta, USA.
Getahun's research focuses on developing innovative statistical models to predict renal graft survival in Ethiopian transplant recipients. His award-winning paper, "Developing Prognostic Models to Predict Renal Graft Survival: Comparison of Statistical and Machine Learning Models," explores the use of advanced machine learning techniques to improve patient outcomes.
This significant achievement highlights the exceptional research conducted by our faculty and the growing impact of our university on the global scientific community.
Congratulations, Getahun!
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
Collaborative Food Safety Initiative Launched in Amhara Region!
Bahir Dar University, the Ethiopian Food and Drug Authority (EFDA), and the RAISE-FS project collaborated to establish a regional food safety technical working group platform. At a one-day meeting, stakeholders emphasized the urgent need to address food safety challenges in the Amhara region. Prof. Netsanet Fantahun representing RCE office of BDU underscored the importance of coordinated action to tackle concerns from duplication and sometimes fragmented efforts to policy challenges.
For full coverage of the news:
#HappeningNow
BDU Training on Education Quality , Quality Assurance system , outcome -Based Education & Program Accreditation.
@Wisdom Hall
December 6&7/2024
ማስታወቂያ
ነጻ የትምህርት እድል ማስታወቂያ
ለ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት (500 እና ከዛ በላይ ከ600) ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ሙሉ ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት በመደበኛ መርሃ ግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉና መማር የሚፈልጉ አመልካቾች
የማመልከቻ ጊዜ፡- ከህዳር 23 እስከ ታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለማመልከት የሚያስፈልጉ፣
የ12ኛ ክፍል ካርድ ውጤት የማይመለስ ኮፒ
የማመልከቻ ክፍያ፤ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር
የማመልከቻ ቦታ፤
በየአካዳሚክ ክፍል ባሉ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች፡፡
ማሳሰቢያ፡-
የትምህርት ፕሮግራም ምደባ ከሌሎች የመደበኛ ተማሪዎች ጋር በውድድር የሚመደቡ ይሆናል፡፡
የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
ለተመራማሪዎች የ Grant Proposal Writing ስልጠና ተሰጠ
********
ለብሉ ናይል ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች የፕሮፖዛል ጽሁፍ ዝግጅት (Grant Proposal Writing) ስልጠና ተሰጠት፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት በብሉ ናይል ኢንስቲትዩት (Blue Nile Water Institute) ስር ለሚገኙ ተመራማሪዎች (Grant Proposal Writing) ጽሁፍ ዝግጅት ስልጠና በጥበብ ሕንፃ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አዳራሽ ከህዳር 20-22/2017 ዓ.ም ድረስ ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲው የመምህራንን አቅም ለመገንባት በርካታ አጫጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን በስፋት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም ስልጠናው ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ባላቸው የዩኒቨርሲቲው ምሁራን እንደሚሰጥና ፋይዳውም የጎላ መሆኑን በመጠቆም ሰልጣኝኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ያገኘናቸው የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ጎራው ጎሹ የስልጠናውን አስፈላጊነት ሲገልፁ በኢንስቲትዩቱ ስር በርካታ ወጣት ተመራማሪዎች ስላሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን ማግኘት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበው የስልጠና ክፍሉ ጥያቄውን ተቀብሎ ማዘጋጀቱንና ለስልጠናው መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ የገና በዓልን ከተማሪዎች ጋር አሳለፉ
ፕሬዚዳንቱ በሁሉም ግቢዎች ተዘዋውረው የበዓል ቀን የተማሪዎች የምሳ ግብዣ ላይ ተገኝተው ከተማሪዎች ጋር የምሳ ሰዓት አሳልፈዋል።
ዶ/ር መንገሻ በዩኒቨርስቲው ግቢዎች ማለትም በፔዳ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በሰላምና በፖሊ ግቢዎች በሁሉም የምግብ አዳራሾች ተገኝተው የተማሪዎችን የበዓል መዋያ ልዩ ዝግጅት በመመልከት ለተማሪዎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከፕሬዚዳንቱ ጋር የዩኒቨርሲቲዉ የስራ ኃላፊዎች፦ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር እንዲሁም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተገኝተዋል።
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
"የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ጥናት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት” በሚል መሪ-ቃል አውደ ጥናት በፔዳ ግቢ ተካሂዷል፡፡
በአውደ ጥናቱ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ፤ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፤ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እስከዳር ግሩም፤ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲ ፋኩሊቲ አባላት እና ተማሪዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሂውማኒቲ ፋኩሊቲ ዲን ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን እንደገለጹት ጉባኤው ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት” በሚል መሪ-ቃል የመወያያ አጀንዳ የሆነበት ምክንያት የሀገር በቀል እውቀት ለሀገራዊ እድገት የሚያበረክቱትን ወሳኝ ሚና አጉልቶ ለማሳየትና የተቋማት የትኩረት ነጥብ ለማድረግ በመፈለግና ቅንጅታዊ አሰራርን ለመመስረት በማለም ነው ብለዋል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከሀገራዊ የእድገት ስትራቴጅዎች ጋር በማዋሃድ ማህበረሰቦች ዘላቂ ልምዶቻቸውን ሳይንሳዊ ከሆነው አስተሳሰብ ጋር በማዋሃድ መጠቀም እንዲችሉ ለማበረታታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶች ያሉንን ሃብቶች ከመሰነድና እውቀቱን ለትውልድ ከማሻገር በተጨማሪ ለምርምርና ለፈጠራ ማእከል በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆን አንገብጋቢ የሆኑ አለማቀፋዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ሀገር በቀል እውቀቶች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል ዶ/ር ዋልታንጉስ፡፡
ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን አክለውም ሀገር በቀል እውቀቶች በአገሬው ተወላጅ ማህበረሰቦችና በተፈጥሮ መካከል ያለውን የተወሳሰበ ግንኙነት የሚያንጸባርቁ ሲሆን በሰዎች እንቅስቃሴ፤ በጤናና በስነ-ምህዳር መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅም ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር በቀል እውቀትን ወደ ዘላቂ የልማት ማእቀፎች በማቀናጀት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ የሀገር በቀል አመለካከቶችን በስርዓተ ትምህርትና በምርምር አጀንዳዎች ውስጥ በማካተት ዩኒቨርሲቲዎች ከባህላዊ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የአካባቢ ተግዳሮቶችን የሚፈታ ትምህርት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
ሀገር በቀል እውቀት ሰፊ ቢሆንም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማእከል አደርጋቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘርፎች መካከል ትምህርትና ህክምና በመሆናቸው በነዚህ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን ብለዋል ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እስከዳር ግሩም በበኩላቸው ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ድርሳኗ የከተበቻቸው ዘመናትን ያስቆጠሩ ባህላዊ የእውቀት ማዕከላትና ተቋማት ያሏት ታሪካዊ ሃገር መሆኗን ገልጸው ተቋማቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የእውቀት፤ የፍልስፍና እና የጥበብ እንዲሁም የምርምር ጥናት ማእከል ሆነው በርካታ ሊቃውንትን አፍርተዋል ብለዋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት የገነባቻቸው አገር በቀል የእውቀት ማእከላትና ተቋማት በየዘርፎቹ የሚኖራቸው ሚና የጎላና ከፍተኛ ቢሆንም በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ አበው ሀብቶቻችን በወጉ ሳንጠቀምባቸው ለውስብስብ ችግሮች እየተዳረግን እንገኛለን ብለዋል ወ/ሮ እስከዳር ግሩም፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ የሀገር በቀል እውቀት ምንጭ ማእከላት ያላቸውን ሙሉ አቅም ለሀገራዊ ልማት በማዋል ረገድ አስተዋጾ አላቸው፡፡ ስለሆነም ሃገር በቀል እውቀቶችን ከልማት አጀንዳዎች ጋር በማዋሃድ ለባህል ደጋፊና ለአካባቢ ተስማሚ ለሆነ ዘላቂ እድገት አስተዋጾ ማድረግ እንዲያስችሉ አድርጎ ማስተሳሰር እና ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በዶ/ር ማረው ዓለሙ፤ የድጓ ማስመስከር ትምህርት ስነ ትምህርታዊ ፋይዳ በቅድስት ቤተልሔም የሚል ገላጭ ጥናት እና በዶ/ር ተመስገን በየነ፤ የባህል ህክምና ዕውቀት ሥርዓትና ተግባር አውዳዊ ትንተና በደቡብ ጎንደር ዞን በሚሉ ርእሶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ከታዳሚው ሰፋ ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው በጽሁፍ አቅራቢዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የዶ/ር ጀማል መሐመድ ተፅፎ ለንባብ የበቃው "ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙሃን" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ተመረቀ
ታህሳስ 25/2017 ዓ. ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የጋዜጠኝነትና ስነተግባቦት መምህርና ተመራማሪ በሆኑት ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ የተደረሰ ጋዜጠኝነትን የሚመለከቱና ሌሎች ከ22 በላይ መጣጥፎች በመድብልነት የተዘጋጁበትና የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መጣጥፎችንና ወጎችን ያካተተ ‹‹ ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙኃን›› በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በመጽሐፉ ምረቃ ላይ የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ንግግራቸው መጽሐፉ ከደራሲው ልምድ፣ ትምህርት ዝግጅት የሚቀዳ ወደ ፊት የመጭው ዘመንን በተለይ ጋዜጠኛን አርሞና አስተካክሎ ወደፊት የሚመራ እንደሚሆን እምነት እንዳላቸው ተናግረው ለመማር ማስተማርና ለምርምር መነሻ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ ብለዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ አክለውም ደራሲው በኢትዮጵያ የመገኛ ብዙኃንና ጋዜጠኞች ላይ እርማት የሚያስፈልግበት ነገር እንዳለ የሚያሳይ ርዕሰ ጉዳይ ይዘው መምጣታቸውንም ተናግረዋል። ዶ/ር መንገሻ አክለውም በመጭው ዘመን ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በበጋጠኝነትና በጋዜጠኞች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ፕሮጀክቶችን ከወዲሁ ለመጀመር መንገድ ይሆነናል ብየ አስባለሁ፡፡ ትምህርት ክፍሉ በቀጣይ ዘመን ትውልድ አወንታዊ ተፅዕኖ እንዲኖርዎት በተለይ የጋዜጠኛ ሚና ምን መሆን አለበት? ወደዚህ ሙያ የሚመጡ ተማሪዎችን እንዴት እናስገባ? ምን አይነት እገዛ እናድርግ? ምሁራን በዚህ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ከተቋም ወይ ከሌላ ከፕሮጀክት ምን እናድርግ ? በሚሉ ሃሳቦች ላይ የሚሳካልኝ ከሆነ ለመስራት ቃል እገባለሁ በማለት ለደራሲው የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጋዜጠኝነትና ስነተግባቦት ት/ክፍል መምህርና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ገብሩ ከመጽሀፉ ለቅምሻ ቅንጭብጭብ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡
ዶክተር ሰለሞን ተሾመ ከፎክሎር ት/ክፍል ስለ መጽሐፉ ከባህል አንጻር ያዩትን ምልከታ አካፍለዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ አጠቃላይ የማህበረሰቡን ማንነት፣ ባህል፣ እውቀት በአንድ ግለሰብ እይታ የታየውን የተገነዘበውን የተማረውን ልምድ ያደረገውን ሀሳብ በሰላ ብዕሩ ልዩ በሆነ የስነጽሑፍ ችሎታው አቅርቦልናል፤ እንዲሁም ማንም ሊደፍራቸው የማይችሉ ሀሳቦች በመጽሐፉ ተነስተዋል በማለት ከባህል አንጻር ከዩኒቨርሲቲያችን ግቢ ውስጥ ካለ የደንገል ተክል ጥቅም ጀምሮ እስከ የአፋር ዳጉ፣ የህንድ አለባበስ፣ የሳውዲ ጉዞ አለባበስ፤ ስለ መውሊድ በአል አከባበር፣ በሰቆጣ በኩል የራሳችንን ማንነት፣ ባህል፣ ችግሮች፣ ኋላቀርነትና በጣም የመጠቁ ነገሮች እንዲሁም የፖለቲካ ባህላችንን አሳይቶናል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፉ እንደ መጣጥፍ ለአንድ ጋዜጠኛ ወይም የተግባቦት ተማሪ እንዴት እንደሚጽፍ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ስለ ድርሰቱ አይነት፣ የድርሰቱ የሽፋን ገፅ ስዕል ትርጓሜ፣ የትረካውን አይነት፣ መቼቱን እንዲሁም በድርሰቱ ውስጥ ስላሉት መጣጥፎች ከስነጽሑፍ አንጻር ሰፋ ያለ ገለጻ ያደረጉት የስነጽሑፍ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አንተነህ አወቀ ሲሆኑ የጋዜጠኝነት መምህር የሆኑት አቶ ሐሰን ዑስማን ደግሞ በድርሰቱ ውስጥ ከጋዜጠኝነት አንጻር ወደ ሙያው የሚገቡትንም ሆነ በዘርፉ ተሰማርተው ለሚገኙት ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ ብለዋል፡፡
አቶ ሐሰን አክለውም ለዛሬ ተማሪዎች ለነገ ጋዜጠኞች ናሙና ይሆናሉ በሚል በመጽሐፍ ዝግጅቱ ስር ከተካተቱት መጣጥፎች በርካታ ነገሮችን መቅሰም እንደሚቻል፣ ጋዜጠኝነት ምንነት፣ ስራው ምን እንደሆነ፣ ምን መሆን እንዳለበት፣ የሚሰራበት ቋንቋ ምን እንደሆነ፣ የቋንቋ አጠቃቀምና የሀሳብ አደረጃጀት ጠንቅቆ ማወቅ እንዳለበት ከድርሰቱ አንጻር ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ከታዳሚዎች ለተነሱት አስተያየቶች የደራሲው ምላሽ የተሰማ ሲሆን የመጽሐፉ ደራሲ ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ መጽሐፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ስላስመረቀላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የተሰጡ ሃሳቦች ለቀጣይ ስራቸው ማዳበሪያነት እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። በመጨረሻም ደራሲው በምረቃው ላይ ለተገኙት የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ ለተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ለተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የሐገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ :-
በፕሮግራሙ ላይ እንድትገኙ በክብር ተጋብዘዋል!!
በፔዳ ኦዲትርየም አዳራሽ ነገ ከ8:00 ጀምሮ
በሰዓቱ ቀድመው ስለሚገኙልን እናመሠግናለን !
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
ለወጣት ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የስራ መጀመሪያ ድጋፍ ተደረገ
ወጣት ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለአመታት ሲሰጥ የነበረው የፕሮጀክት ስልጠና የማጠቃለያ መረሃ-ግብር ተካሄዷል፡፡
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ኢምባሲ ጋር በመተባበር ባገኜው የገንዘብ ድጋፍ ከዘጠኝ በላይ ለሆኑ ወጣት ሴት ስራ ፈጣሪዎች በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ስልጠናውን ወስደው ላጠናቀቁ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የመስሪያ ቁሳቁስ፣ የመስሪያ ቦታ እና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ መርሀ ግብር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማሕበረሰብ ተሳትፎ ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ እንደገለጹት የስልጠናው ዋና አላማ የስራ ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሴት ወጣቶችን በማወዳደር ሐሳባቸውን ዕውን እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ከአሜሪካን ኢምባሲ ጋር በመተባበር በተገኜው ገንዘብ የሙያ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ስራ ፈጣሪዎች በሚያገኙት ስልጠና ራሳቸውን ለውጠው ለህብረተሰቡ በእውቀት ላይ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማሕበረሰብ ተሳትፎ ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በምርምር የሚገኙ ዕውቀቶችን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማቀናጀት ወደገበያ እንዲወጡ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ፕሮፌሰር እንየው ተናግረዋል፡፡ በዘጠኝ የሙያ መስኮች ስልጠናውን የወሰዱ እና የመስሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለተደረገላቸው ሰልጣኞች በዘላቂነት የክትትል እና የድጋፍ ስራዎች በአማካሪዎቻቸው አማካኝነት መሰራት እንዳለባቸው ተናግረውዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ስራቸው ባሻገር ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል እንዲፈጥሩ ስልጠናዎችን በመስጠት ዘላቂ ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽዎ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉም በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ተሾም ይዘንጋው በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ አጋርነት ለተቋማዊ ለውጥ እና አቅም ማጎልበት ምርምር እና ልማት ተባባሪ ምክትል ፕሬዝዳንት በበይነ መረብ ገብተው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ወጣት ሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ስራ ሐሳቦች ሰፊና ጥልቅ አንድምታ ያላቸው እና አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡ ስልጠናውን የወሰዱ የቢዝነስ ስራዎች በደብረማርቆስ ባሕር ዳር ኮሪደር የሚገኙ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች የሚፈለገውን ድጋፍ ካገኙ በተግባር ማሳየት ከሚችሉት የቢዝነስ ሐሳቦች መካከል በጣም ጥቂቶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከመንግስት እና ከልማት አጋሮች የሚደረግ ትንሽ ድጋፍ በጣም ብዙ ውጤቶችን እንደሚያመጣ በቁልፍ መልዕክታቸው ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ተሾም አክለውም የክልሉ መንግስት የፌዴራል ኤጄንሲዎች እና የልማት አጋሮች ለስራ ፈጣሪ ወጣቶች የፈጠራና የንግድ ስራዎች የተሳኩ እንዲሆኑ እና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለመለወጥ የሚደረገውን ጥረት በገንዘብ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ አሰጣጥን በማቀላጠፍ የመስሪያ ቦታ በማመቻቸት የስራ ፈጣሪ ወጣቶችን እንዲበረታቱ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ታቅፈው ስልጣናውን ከወሰዱት ሴት የስራ ፈጣሪ ወጣቶች መካከል በልብስ ስፌትና ዲዛይን፣ መሽሩም በማምረት፣ የቤት ለቤት የህክምና አገልግሎት፣ የተመጣጠነ የእናቶች እና ህፃናት ምግብ ዝግጅት፣ የወተት ተዋጾ ልማት፣ በህፃናት ማቆያ እና በፍየል ርባታ እና ማድለብ ስራዎች ሰልጥነው ለስራው የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ እና የመስሪያ ቦታ እንዲሁም የእውቅና ሰርተፊኬት ከፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ተበርክቶላቸዋል፡፡
በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው የፕሮጀክቱ ዋና ዋና አላማዎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመስራት አቅም መገንባት፤ በኮሪደሩ ያሉ ስራ አጥ የሆኑ ሴት ወጣቶች የራሳቸው የቢዝነስ ሀሳብ አቅርበው በስልጠናና በገንዘብ እንዲደገፉ በማድረግ የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ማድረግ እና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራትን መሰረት ያደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
New Year Greetings and Gratitude from Our International Student!
Dear Bahir Dar University, Ethiopia,
As we sojourn to usher in the New Year in one week’s time, it is with sincerest pleasure that I cease this rare opportunity on behalf of International Students Fraternity to wish the entire BDU Staff, Students, fellow International Students, Workforce and its International Partners a Happy New Year, 2025 in advance. The year 2024 has been a struggle for all of us and we fortunately overcame its challenges together, a victory we all attribute to God’s maximum protection, love, provision of wisdom and sustenance. We are so grateful to Him.
BDU International Students are without doubt so grateful to the administration of this Mighty University for the invaluable services delivered, lives mentored and a nourishing environment enabled for them and the entire BDU community. We appeal to the administration to continuously render its services and make Bahir Dar University, Ethiopia a more promising and better place for its Staff, Students, Workforce, International Partners and Stakeholders in the year 2025 going forward.
May 2025 be more joyous, peaceful and fulfilling to the entire BDU Community!
Happiest New Year 2025!
Yours in Sincerity,
Martin Amet Liet
Former President,
South Sudan Students’ Union
Bahr Dar University, Ethiopia.
Happy New Year 2025!
As we welcome this new year, Bahir Dar University extends its gratitude to all its partners for your unwavering collaboration and support.
Together, we have achieved remarkable milestones, and we look forward to a brighter year ahead filled with growth, opportunities, and shared success.
May 2025 bring all celebrating happiness, success, and prosperity!
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የማኅበረሰብ ተሳትፎ ስልጠና
በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በመጤ ልማዶች ተጽእኖ ዙሪያ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሥልጠና
ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም
ቦታ :- ፔዳ ሴኔት አዳራሸ
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
የማኅበረሰብ ተሳትፎ ስልጠና
በቅርስ አያያዝ፣ በሙዚየም አደረጃጀትና በባህል ስነዳ ዙሪያ ለባለሙያዎች የተዘጋጀ ተግባር ተኮር ስልጠና፤
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂዩማኒቲስ ፋካሊቲ፣
በአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና
በአማራ ህዝብ ዝክረ-ታሪክ ማዕከል በትብብር የተዘጋጀ፤
ታህሳስ 2017 ዓ.ም ባሕር ዳር
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
Bahir Dar University Leads the Way in Regional Food Safety Collaboration
Bahir Dar University, Ethiopia – Bahir Dar University (BDU), in partnership with the Bahir Dar Branch of the Ethiopian Food and Drug Authority (EFDA) and the RAISE-FS project of SWR Ethiopia, has taken a significant step towards enhancing food safety in the Amhara region. A dedicated one-day meeting was held to establish a regional food safety technical working group platform.
The event, which brought together over 30 participants from regional bureaus and projects, was inaugurated by Prof. Netsanet Fantahun, from Research and Community Service at BDU.
Prof. Netsanet emphasized the critical importance of addressing food safety challenges in the region, particularly in light of the global concerns surrounding foodborne illnesses and mycotoxin contamination.
The meeting served as a platform for discussing the challenges associated with implementing EFDA policies and regulations, as well as the findings of recent mycotoxin studies conducted in the Amhara region. Participants recognized the need for a coordinated approach to tackle these issues, highlighting the potential for duplication of efforts and fragmentation of resources.
To address these challenges, the establishment of a sustainable regional food safety technical working group platform was proposed. The group will facilitate collaboration among key stakeholders, including government agencies, academic institutions, and industry partners. The Regional Health Bureau was selected to chair the group, with the Bureau of Agriculture serving as co-chair and the Bahir Dar EFDA branch as secretary.
This collaborative initiative signifies a promising step towards safeguarding public health in the Amhara region.
#SWAT+ and Python Workshop Kicks Off for Water Resource Management
Bahir Dar University, Ethiopia , (December 6, 2024) - The Geospatial Data & Technology Center (GDTC), in partnership with the SWAMP project, has initiated a four-day intensive workshop on "SWAT+ and Python for Water Resource Management." The event, which commenced on December 4th, 2024, is gathering 20 promising researchers and postgraduate students specializing in hydrological modeling and water resource management.
The SWAMP project, dedicated to fostering a global network of water professionals, is aligning with this workshop's practical approach. Participants are actively engaged in hands-on training sessions that seamlessly integrate the powerful SWAT+ model with Python programming. By tackling real-world case studies within the Lake Tana Sub-Basin, attendees are gaining invaluable experience in applying advanced hydrological modeling techniques.
This initiative is poised to cultivate a skilled workforce capable of addressing the intricate challenges of water resource management. By equipping participants with the necessary tools and knowledge, the workshop is contributing to the development of a robust community of water professionals committed to sustainable water resource management and conservation.
Bahir Dar University and University of Sinnar Sign Memorandum of Understanding
In a significant move to foster academic excellence and innovation, Bahir Dar University (BDU), Ethiopia, and the University of Sinnar (UoS), Sudan, signed a Memorandum of Understanding (MoU) today. The agreement, signed by Dr. Mengesha Ayene, President of BDU, and Prof. Abderrhman Ahmed Mohammed Ismeil, Vice Chancellor of UoS, establishes a framework for robust collaboration between the two institutions.
Among other things, the partnership will focus on joint research projects, organizing training courses, conferences, and workshops to enhance staff and student capacity, developing innovative teaching methods, curricula, and course designs, and facilitating staff and student exchanges between the two universities. Both institutions expressed their strong commitment to turning this agreement into actionable initiatives, signaling a shared vision for long-term collaboration.
The event marked the culmination of a productive visit by the University of Sinnar delegation, which included Prof. Abderrhman Ahmed Mohammed Ismeil, Vice Chancellor, Dr. Ammar Abdella Ahmed Suleiman, Secretary of Academic Affairs, and Dr. Hysum Ibrahim Mohammed Muhmode, Director of International Relations, University of Gezira.
Since their arrival in Bahir Dar on December 02, 2024, the delegation has engaged in strategic discussions with BDU leadership and visited prominent academic and research facilities at Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology/EiTEX (
This partnership highlights the shared commitment of both universities to advancing higher education through collaboration, resource sharing, and innovation. The MoU lays a solid foundation for impactful projects, enhanced learning experiences, and strengthened academic ties.
BDU and UoS look forward to building on this agreement and exploring additional opportunities to drive academic and research excellence.
JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
#Share #Share
ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ስርአት ስልጠና ተሰጠ
********
ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የአካዳሚክ ክፍሎች ለተውጣጡ መምህራን የዓለም አቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ስርአት (International English Language Tasting System /IELTS/) ስልጠና በፖሊ ግቢ ከህዳር 20 እስከ 24/03/17 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናውን ያዘጋጀው የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክተሩ አቶ ወርቁ አበበ ስልጠናውን የሚሰጡት ለሙያው ቅርብ የሆነ የዩኒቨርሲቲያችን ምሁራን መሆናቸውን ገልጸው የስልጠናው ፋይዳ የጎላ ስለሆነ ሁሉም ሰልጣኝ ትኩረት ሰጥቶ በንቃት እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ያገኘናቸው የዩኒቨርሲቲው የ IELTS አስተባባሪና አሰልጣኝ ዶ/ር አማረ ተስፌ የስልጠናው ዓላማ የመምህራንን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ለማዳበርና መማር ማስተማሩን ለማዘመን እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ፈተናዎችን አዘጋጅተው ተማሪዎችን በአግባቡ ለመመዘን ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ዶ/ር አማረ በማስከተል ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን መማር ማስተማሩን ከማዘመን ባሻገር የውጭ እድል በሚያገኙበት ወቅት የ IELTS ፈተና በቀላሉ ወስደው ውጤታማ እንደሚሆኑ በተጨማሪም ፈተናውን ለመውሰድ የሚፈልግ በርካታ ሰው ስላለ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ውጭ ለአካባቢው ኗሪ ፈተናውን በመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
Call for former graduates of Poly Technic, BiT and EiTEX who are members of Poly-BDU Alumni Association!
Читать полностью…