bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

-

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses' Students! www.bdu.edu.et Contact @bdu_tana_bot

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

A discussion focusing on Ethio-Sudanese relations is underway at Bahir Dar University, Ethiopia.
---------------------------------------------
--------------------------------
Scholars from Bahir Dar University, Wollo University and Sudanese Universities will be presenting their research papers on the previous relations between the two countries, Ethiopia and Sudan. Also, papers that focus on the future relationship of the two neighboring counties will be presented. The discussion is expected to continue tomorrow.
በኢትዮጽያ እና ሱዳን ግንኙነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ሲሆን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ከወሎ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከሱዳን ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ሙሁራን በኢትዮጽያ እና ሱዳን የቀድሞ ግንኙነት እንዲሁም ወደፊት ስለሚኖረው ጥምረት ትኩረቱን ያደረገ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን እንደሚያቀርቡ ተነግሯል፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሠለጠናቸውን 5117 ተማሪዎች አስመረቀ
---------------------------------------------
-----------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መመረቅ የነበረባቸው እና በኮረና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ የዘገዩ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ 4203፣ በሁለተኛ ዲግሪ 759፣ በሦስተኛ ዲግሪ 10፣ በስፔሻሊቲ 40፣ በፒጂዲቲ ቅድመ ምረቃ 105 በአጠቃላይ 1623 ሴት 3494 ወንድ ተማሪዎችን በድምሩ 5117 ተማሪዎችን ጥር 29/5/2013 ዓ.ም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በክብር እንግድነት በተገኙበት አስመርቋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት “የዘንድሮ ተማራቂዎችን እንደተማሪ በርካታ መሰናክሎችን አልፈው ለዛሬው ቀን በመብቃታቸው "ከመወርቅ" በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግሮች በመከራ ጊዜ እንደ ወርቅ ነጥራችሁ በመውጣታችሁና ለዚህ ታሪካዊ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡” ዶ/ር ፍሬው አክለወም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንዲሆንና በሀገራችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ግምባር ቀደም እንዲሆን ላገዙት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ላሉ የወጣት አደረጃጀቶችና ለሌሎች አጋር ተቋማትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተመራቂዎች ዓለምን እየፈተነ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ ውስብስብ ችግሮችን አልፈው መመረቅ መቻላቸው ታሪካዊ ተመራቂዎች መሆናቸውን አውስተው ተመራቂ ተማሪዎች ሀገርና ቤተሰብ የጣለባቸውን አደራ በአግባቡ እንዲወጡ በሰለጠኑበት የትምህርት መስክ ጠንክረው በመስራት ሀገራቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ተመራቂ ተማሪዎች ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን ለሀገሬ ምን አደረኩላት ብሎ ራስን መጠየቅ እና በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን ጥልቅ ዕውቀት ተጠቅመው በኮረና ቫይረስ ወረርሽ የቀዘቀዘውን ኢኮኖሚ እንዲሻሻል በማገዝ በሀገር ግንባታ ላይ የበኩላችውን አስተዋፆ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለባሕር ዳር ከተማ ብሎም ለክልሉ እንደ ዓይን ብሌን የሚታይ ግዙፍ የዕውቀት ማዕከል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በመመረቂያ ፕሮጀክቶች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት እና የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የወርቅ ዋንጫ ተሸልመዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ፣የባሕር ዳር ዩኒቨረሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ፣ የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋም ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ባማረው እና በተዋበው የዩኒቨርሲቲው ስታዲየም በፖሊስ ማርሽ ባንድ በቀረበ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መዝሙር እና በሙሉ ዓለም የባህል የሙዚቃ ባንድ በቀረቡ የተለያዩ ባህላዊ ውዝዋዜዎች እና ዘመናዊ ሙዚቃዎች በመታጀብ ደምቆ ውሏል፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን: 28/05/2013 ዓ.ም
#BiT

በባህር ዳር ቴክኖሎጂ-ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ 2ኛ እና 3ኛ መደበኛ ተማሪ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BDUGraduation #2012
4 Days Left!
# Congratulations

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን: 21/05/2013 ዓ.ም
#BiT
Notice for 👉 2nd & 3rd year
👉 internship students

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

# Congratulations to Class of 2020!!
---------------------------------------
10 D A Y S T O G O ! !
Bahir Dar University wishes a Happy Graduation Day to class of 2020 in advance !!
# BDUGraduation
# classof2020

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ በሙሉ፡-
ባሕር ዳር
ጉዳዩ፡- የጉባዔ ተሳታፊ እንዲሆኑ ስለማሳወቅ
----------------------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የዩኒቨርሲቲውን ሙዚየም በኃላፊነት ተረክቦ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን፤ ተማሪዎች፤ ሠራተኞች እና እንግዶች እያስጎበኘ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ይህን ሙዚየም በተሻለ መልኩ አደራጅቶ ለጎብኝዎችና ለመማር ማስተማሩ ሂደት የበለጠ ደጋፊና ምቹ እንዲሆን ‹‹የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም አደረጃጀትና አሰራር ምን መምሰል አለበት?›› በሚል ርዕስ ጥናት በማስጠናት ባዘጋጀው የውይይት ጉባዔ ተገኝተው የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ እየጋበዝን ጉባዔው የሚካሄደው ጥር 25 ቀን ከጥዋቱ 2፡30 በሴኔት አዳራሽ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር!
ማሳሰቢያ
ወደ ወርክሾፑ ሲመጡ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግዎን እንዳይረሱ!
https://bdu.edu.et/content/%E1%88%99%E1%8B%9A%E1%8B%A8%E1%88%9D

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን: 13/05/2013 ዓ.ም

#የጥሪ_ማስታወቂያ

በ2012 ዓ.ም ሁለተኛና ከዛ በላይ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ
#share ያድርጉ

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር አካሄደ
---------------------------------------------
-----------------------------
በወንዳለ ድረስ
የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል በ COVID 19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለስ ምክንያት በማድረግ አዝናኝ የኪነጥበብ ስራዎችንና፣አስተማሪ መልዕክቶችን በማቅረብ፣‹‹የእንኳን ደህና መጣችሁ›› ዝግጅት አካሄዷል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ ዝግጅቱን የከፈቱት ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸውም ‹‹የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሀገራዊ ተቆርቋሪነትና የሀላፊነት ስሜት የሚሰማቸው ሊሆኑ ይገባል›› ሲሉ በአፅንኦት ጠቁመዋል፡፡
ባህል ማዕከሉ በዕለቱ ታዋቂውን የሀገራችን የፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን እንግዳ አድርጎ የጋበዘ ሲሆን ዶ/ር ዳኛቸው ‹‹ዩኒቨርሲቲ ምንድን ናት? የዩኒቨርሲቲ ተማሪስ ምን ስነምግባር ሊኖረው ይገባል?›› በሚል ርዕስ ቁልፍ ንግግር አቅርበዋል፡፡ በንግግራቸው ‹‹ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማዕከል ናት፣ዩኒቨርሲቲ የራሷ ዓላማና ግብ አላት፤ ይህንን ለማንም አሳልፋ መስጠት የለባትም፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ሲወጣ ‹ዲስፕሊንድ› (ስነምግባር የታነፀ) አእምሮ ይዞ ሊወጣ ይገባዋል›› ብለዋል፡፡
የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአስዳደር ጉዳዩች ም/ፕሬዚዳንት ተወካይና ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋው ሽፈራው ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎች መመለስ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ከገለፁ በኋላ ኮቪድን የመከላከል ስራን ታሳቢ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን መማሪያ፣ መመገቢያ ክፍሎችን፣ ቤተመፅሀፍትና ቤተ ሙከራዎች በሚገባ አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ኮቪድን በመከላከልም ሆነ ሰላምን በመጠበቅ ሂደት ተማሪዎች ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የስነባህሪ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አቶ ታምሩ ደለለኝ በዝግጅቱ ላይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የጥበብና የሰላም ፍኖተ ካርታ ያቀረቡ ሲሆን ‹‹ትምህርት ማለት የአእምሮ፣ የስነልቦናና የአካል ቅንጅታዊ ዑደት ነውና ሁላችንም ከዚህ እሳቤ አንፃር ራሳችንን ካስተማርን ሰላማችን መጠበቅ እንችላለን›› ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አስቴር ሙሉ ‹‹ሰው ያለ ባህል›› እንስሳ ነው ብለው በመቀጠልም ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ስብዕናዎችን ማጎልበት እና ማጎናፀፍ የሚያስችሉ ባህሎች ባለቤት ናት ብለዋል፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከልም ስብዕናው የጎለበተና የሀገሩን ባህል ጠንቅቆ ያወቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡ ይህንን በማድረግ ሂደትም ወጣቶች ዋና ባለድርሻ አካላት ናችሁና ባህል ማዕከሉ ተልዕኮውን ለማሳካት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አጋዥ ሁኑ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለመተከል ተፈናቃዮች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ
---------------------------------------------
---------------
በሙሉጌታዘለቀ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በተፈጠረው ሰባዊ ቀውስ ለተፈናቀሉ ዜጎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና በባሕር ዳር ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ የአዲስ አምባ (የልደታ ሳይት) ነዋሪዎች በቅንጂት የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡
በድጋፉም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ተቋም በተማሪዎች የተመረቱ ለህፃናትና ለአዋቂዎች የሚሆኑ አልባሳት ያበረከተ ሲሆን በተጨማሪም የድጋፍ ቁሳቁሶችን ከቦታው ድረስ ለማድረስ የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በእለቱ በተደረገው ድጋፍም በአጠቃላይ ከ75 ኩንታል በላይ የተለያዩ የህፃናት እና የአዋቂ አልባሳት፣ከ5 ኩንታል በላይ የተለያዩ የህፃናት እና የአዋቂ ጫማዎች፣ከ40 ካርቶን በላይ ፓስታ፣ 5 ኩንታል መኮሮኒ፣ 5 ካርቶን ዘይት እና የተለያዩ ሳሙናዎችን እንዲሁም ጣፋጭ ብስኩቶችን ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጉዳቱ ሰለባዎች ቦታው ድረስ በመሄድ ተከፋፍሏል፡፡
ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ድጋፍ የማሰባሰቡን ሂደት ያስተባበሩት አቶ ኢሳ አብዲ፣አቶ ቻላቸው ተስፋ እና አቶ አያሌው ውብነህ ሲሆኑ በርክክቡ ወቅት አቶ ኢሳ እንዳሉት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የንፁኋን ወገኖቻችን ግድያና እና ማፈናቀል እንደ ሀገር ሁላችንንም ያሽማቀቀና አንገታችን ያስደፋ እንዲሁም በታሪካችንም ላይ መጥፎ ጠባሳ ያሳረፈ የታሪካችን አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰው በተቃራኒው ደግሞ የአዲስ አምባ (የልደታ ሳይት) ነዋሪዎች ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ ለማድረግ በጠየቅናቸው በሁለት ቀን ውስጥ በከፍተኛ መነሳሳት ያሳዩት የድጋፍ ስሜት እጅግ አስደናቂና ኢትዮጵያዊነትን በግልፅ ያየንበት አጋጣሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ቻላቸው ተስፋ በበኩላቸው እርዳታውን በሁለት ቀን ውስጥ ማሰባሰብ እንዲቻል የተባበሩትን የአዲስ አምባ (የልደታ ሳይት) ነዋሪዎች አመስግነው እርዳታውን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን እንዲደርስ ላደረጉት ለልደታ ቤተ ክርስቲያን የፅዋ ማህበራት እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል፡፡ አቶ ቻላቸው አክለውም ያለወላጅ ለቀሩ ሕፃናትና ጧሪ እና ቀባሪ ላጡ አረጋዊያን እንዲሁም ጉዳቱ የደረሰባቸውን ሁሉንም ወገኖቻችን ለመርዳት ሁሉም የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው በመደራጀት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡.

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 30/04/2013 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
--------------------------------------
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም አካዳሚክ ም/ዲን ኃላፊነት በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም- አካዳሚክ ም/ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 0923 297333 ወይም 0918353494 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

መልካም የገና በዓል !

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#Congratulations!
**************

Bahir Dar University wins a project that aims to improving the teaching of Science and Mathematics.
In a tripartite collaboration with Juba University and Norwegian University of Science and Technology (NTNU), Bahir Dar University won a project titled “Enhancing teachers’ and teacher educators’ capacity for improving science and mathematics teaching and learning in Ethiopia and South Sudan”.
This project which the university won for the second time has a life span of six years and is funded by Norwegian Agency for Development Cooperation. The project aims to curb the deep-rooted problem in Science and Mathematics education in the Ethiopia and South Sudan. In this regard, it envisages to conducting more and high quality researches that are believed be to foundation stones in solving problems related to Science and Mathematics education.
The project includes scholarship opportunities to be opened up for scholars in Bahir Dar and Juba Universities. A total of 12 PhD (8 from Ethiopia and 4 from South Sudan) and 20 Master’s scholarship opportunities will be available for eligible candidates in the two countries. Moreover, with this project, it is also planned to establish a center for the study of science and mathematics teaching and learning (CSSMTL) at Bahir Dar University, Ethiopia. The project package also includes trainings: to educators at Colleges of Teacher Education and at BDU, and to science and mathematics teachers at schools.
We won this project thanks to the relentless efforts expended by our faculty Dr Dawit Asrat, Mr. Dereje taye, Mr Mulugeta Awayehu and Mr. Ahmed Yibrie. Many Congratulations to YOU all!

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ተገለጸ ፡፡
---------------------------------------------
-----------------------------
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ታህሳስ 21 ውይይት አካሄደ ፡፡
በአብክመ ማህበራዊ ዘርፍ ም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢንዱስትሪዎች በአንድ ሀገር ላለ ማህበረሰብ የሚያበረክቱትን አስተዋፆ ስኬታማ ለማድረግ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ብሎም የአካባቢውን የስራ ባህል፣ አኗኗር፣ ቋንቋና ዕሴቱን ማስገንዘብ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ናታኒየ ካሳ በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ሰላም ተግዳሮቶች በሃገር ውስጥ ሰራተኞች በኢንዱስትሪ ባህል የግንዛቤ ውስንነት እና በውጭ ሃገር ዜጎች ያለው ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ህዝብ ታሪክ፣ ባህልና ስነ ልቦና እንዲሁም አሰራርና ሰራተኞች ህግ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አቶ ናታኒየ ካሳ አክለውም ለውጭ ሃገር ዜጎች ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ህዝቦች ስነ ልቦና፣ ባህልና እሴት ወዘተ ግንዛቤ መፍጠሪያ መፅሃፍ/ሞጁል ማዘጋጀት ለኢንዱስትሪ ሰላም ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ጠቁመው ለወደፊቱ ለውጭ ሃገር ዜጎች ስለ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁበት የተደራጀ ማዕከል ቢኖር ለጥናትና ምርምር እንደ ግብዓት እንደሚያገለግል ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብና የቴክኖሎጂ ሽግግር ኤክስኪዩቲቨ ዳይሬክቶሬት ዳይይሬክተር ዶ/ር ተሰማ አይናለም እንደገለጹት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በባሕር ዳር ከተማ እንዲሁም በክልሉ ላይ ባሉ ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ምርምር ማካሄድና የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠናዎች እንዲሁም የስልጠና ማንዋሎችን በማዘጋጀትና ሌሎችን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በጋራ በመሆን ለመስራትና ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ስራ ለሚጀምሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሰራተኞች ግንዛቤ መስጠት፣ ነፃ የህግ አገልግሎት፣ ምርምርና ማህበረሰብ፣ የማማከር እና መሰል አገልግሎቶችን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for application

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Graduation online Bulletin
-----------------------------
We have published a magazine, a special Graduation online bulletin. It includes Messages of the president, Vice Presidents and other top officials of the university. You can also find the CGPA of the top scorers from each academic unit; top scoring students pictured in their graduation gown.
To find the bulletin, please follow the link herewith: https://bdu.edu.et/sites/default/files/publication/GRADUATION%20ONLINE%20BULLETIN..pdf

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BDUGraduation #2012
2 Days Left!
# Congratulations

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BDUGraduation #2012
3 Days Left!
# Congratulations

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#BDUGraduation #2012
5 Days Left!
# Congratulations

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#አፋልጉኝ
' ባየቻት አከለ ትባላለች #አካውንቲንግ ተማሪ ነች ዩንቨርሲቲ ጥሪ ካረገ ጀምሮ ወደ ካምፓስ ከመጣች ጀምሮ ስልኳ አይሰራም እባካችሁ በዚ ስልክ እንድትደውል ንገሩልኝ..... ወላጅ እናቷ በእግዚአብሔር ተባበሩኝ'
ስልክ @bdu_tana_bot ላይ ጠይቁን

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮለጅ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል አዲስ ለሚጀምረው የዶክትሬት ድግሪ ፕሮግራም ያዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት አስገመገመ
---------------------------------------------
---------------------------------
በሙሉጌታ ዘለቀ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮለጅ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ በነፍሳት ሳይንስ (Entomology PhD curriculum) ስርዓተ ትምህርት ግምገማ በበይነ-መረብ አካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የባዮሎጂ ትምህረት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ሲሳይ መንክር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ማስፋት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዞ የሳይንስ ኮለጅ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ በነፍሳት ሳይንስ ስርዓተ-ትምህርት (Entomology PhD curriculum) አዘጋጅቶ በውስጥ ምሁራን ከተገመገመ በኋላ በሙያው የጠለቀ እውቀት ባላቸው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን መገምገሙን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር መላኩ ዋለ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የስርዓተ ትምህርቱ አዘጋጅ እንዳሉት በትምህርት ክፍሉ በሁለተኛ ድግሪ ከ450 በላይ ተማሪዎች ተመርቀው አሁንም PhD ለመማር የሚጠይቁ በርካቶች በመሆናቸው ትምህረት ክፍሉ አዋጭነቱን ከግምት በማስገባት የፍልስፍና ዶክትሬት ድግሪ በነፍሳት ሳይንስ (Entomology PhD curriculum) ስርዓተ ትምህርት ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ስርዓተ ትምህርቱን በመስኩ ልምድ ባላቸው ምሁራን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ፍርዱ አዘረፈኝ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር መላኩ ግርማ በበይነ መረብ በማስገምገም ከፍተኛ ግብዓት መገኘቱን ዶ/ር መላኩ ዋለ ተናግረዋል፡፡
የሰው ልጅና የተለያዩ የእፅዋት ዘሮች በጎጂ ነፍሳቶች በተለያየ መልኩ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ዶ/ር መላኩ ተናግረው ስርዓተ ትምህርቱ የሚደርሰውን የጉዳት መጠን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መቀነስ ይቻል ዘንድ የመፍትሄ ሀሳብ ሊያመነጭ የሚችል የሰው ሀይል በማፍራት ረገድ ለግብርናው ዘርፍ ጥሩ እድል ይዞ እንደሚመጣ ጠቁመዋል፡፡ ዶ/ር መላኩ አክለውም አዲስ የሚከፈተው ፕሮግራም ከትምህርቱ ባህሪ አንፃር ቤተ-ሙከራና ሌሎች ቁሳቁሶችን በብዛት የመጠቀም ባህሪ ስላለው ዩኒቨርሲቲው በችግሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ጠቅሰው ለጊዜው ግን በከተማችን ካሉ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት እንዳቀዱ ተናግረዋል፡፡
በስርዓተ ትምህርቱ ግምገማ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ዲን ዶ/ር ሙሉጌታ አድማሱ እንዳሉት የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ በነፍሳት ሳይንስ (Entomology PhD curriculum) መከፈቱ በግብርናው ዘርፍ ምርታማ እንዳንሆን አንበጣን ጨምሮ በርካታ ነፍሳቶች የሚያደርሱትን የጉዳት መጠን ለመቀነስ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማስመረቅ ምርትንና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ ስርዓተ ትምህርቱን በማፀደቅ ፕሮግራሙን በአጭር ጊዜ ወስጥ እንዲከፈትና የሚገቡ ተማሪዎችን ለመሳብና የቆይታ ጊዜያቸው የተሳካ እንዲሆን ቤትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ዩኒቨርሲቲው እንደሚያመቻች ዶ/ር ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡
College of science, BDU holds a PhD in Entomology curriculum review
Department of Biology virtually conducted curriculum review for the new PhD program (PhD in Entomology) it is opening in the near future.
In the opening, the head of the department of Biology Dr Sisay Menkir, welcomed all to the workshop and highlighted that opening of PhD programs in various fields is a right call for universities like Bahir Dar University which is now recognized as a research university in the country. Speaking about the rigorous reviewing process that the new curriculum has to pass through he said the curriculum was reviewed by internal reviewers and also by two external reviewers one from Addis Ababa University and the other from Hawassa University.
Dr Melaku Wale who prepared the curriculum recalled that the department has graduated about 450 students in the Master’s degree level, and there has been an urge for the opening of a PhD program. Dr Melkau added the curriculum was under scrutiny by two external reviewers: Dr Firdu Azerefegn from Hawassa and Dr Melaku Wale from Addis Ababa universities. Dr Melaku remarked that the life of humans and different specious of plants has been endangered by different harmful insects and the opening of the new program is believed to produce professionals who can come up with ideas potentially lessening or eradicating the danger caused by harmful insects. This, according Dr Melaku, is a good opportunity for the agricultural sector. He noted that by virtue of its nature programs of this nature demand a lot of laboratory and material inputs; therefore, he urged the university to take the assignment of fulfilling some more resources in the time ahead.
Dean of post Graduate studies Dr Mulugeta Admasu believed that with the opening of the program, it will able to reduce the damage caused by many insects including locusts and subsequently enhance production and productivity in the agricultural sector. Dr. Mulugeta added the university will provide various support, including housing, to open the program in a short period of time and to attract eligible students and make their stay successful.

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን : 18/05/2013 ዓ.ም
የጥሪ ማስታወቂያ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!
መልካም በዓል
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን :02/05/2013
#BiT

ለአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Important Notes for #First Year Students

You may have a better view of the notice from: https://bdu.edu.et/sites/default/files/Attachement/Notice%20%282%29.pdf

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ማስታወቂያ
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም 1ኛ ዓመት ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ- የምትገቡባቸውን ግቢዎች ስለማሳወቅ
---------------------------------------------
--------------------------
እንደ አማራጭም የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ማስታወቂያውን ማግኘት ይችላሉ፡- https://
bdu.edu.et/content%E1%89%A3%E1%88%95%E1%88%AD%E1%8B%B3%E1%88%AD-%E1%8B%A9%E1%8A%92%E1%89%A8%E1%88%AD%E1%88%B2%E1%89%B2-%E1%89%A02012-%E1%8B%93%E1%88%9D-1%E1%8A%9B-%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B5-%E1%88%88%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%AB%E1%89%BD%E1%88%81-%E1%89%B0%E1%88%9B%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%88%99%E1%88%89-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%89%B5%E1%8C%88%E1%89%A1%E1%89%A3%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8C%8D%E1%89%A2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%B5%E1%88%88%E1%88%9B%E1%88%B3%E1%8B%88%E1%89%85

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for training
To all PhD first year students
**************************
Bahir Dar University Office of Postgraduate is facilitating Critical Thinking Training for PhD First Year Students. The training will be delivered by Dr. Dagnachew Assefa
Date: Tir 3-7, 2013 E.C
Venue: Peda Campus, Auditorium
Time: 3:00 (local time).

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ
በሶሻል ሳይንስ እና አለምአቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት " የፓለቲካ ታህድሶ ተግዳሮቶችና እድሎች" በሚል ርእሰ ጉዳይ በቀድሞዉ ሰኔት አዳራሽ ዉይይት ተደርጓል።
*****************************************
********************
በመድረኩ የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት-ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ፣ የአስተዳድር ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ብርሃኑ ገድፍ እና ሌሎችም አመራሮች ታድመዋል። አቶ ብርሃኑ ዉይይቱን በንግግር እንዲጀመር ያደረጉ ሲሆን ፣ ዶ/ር ታዬ ደምሴ ፕሮግራሙን መርቶታል። በተጨማሪም በመድረኩ አምስት ያህል ጭብጦች በተወያዮች ቀርበዋል።
እነዚህም ውስጥ አንዱ ጭብጥ ለውጡን እንደገና በአንክሮ ማጤን በሚል ርዕሰ በመምህርት መስከረም አበራ ቀርቧል። መምህርት መስከረም ለውጡ ሲጀምር የነበረው ተስፋን እና አሁን መሬት ላይ ያለዉ ነባራዊ ሃቅ የተራራቀ መሆኑን ሁነቶችን በመጥቀስ አስረድተዋል። እንደ መምህርቷ ይልቁንም ከጅምሩ የለውጥ መሪ ተብለው እውቅና በተሰጣቸው ልሂቃን መካከል ሳይቀር ልዩነች መፈጠሩንም ተናግረዋል። ከዚህም በላይ አምባገነንነት፣ አፈና እና የተረኝነት አዝማሚያ መኖሩንም ጠቁመዋል።
ሌሎች ሁለት ጭብጦች የአማራ ብሄርተኝነትን ማአከል ያደረጉ ነበሩ። በዚህ ዙሪያ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ዲን የሆኑት አቶ ተገኝ ዘርጋዉ የአማራ ህዝብ ጥያቄና ምላሹ በሚል ከ ህገ መንግስቱ በመነሳት ተንትነዉ አቅርበዋል። በዚህም የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ፈርጀ ብዙ መሆናቸውን አምነው ዋናው ግን ህገ-መንግስታዊ መሆኑን አብራርተዋል። አቶ ተገኝ የአማራ ህዝብ ችግር ህገ መንግስቱ የፈጠረዉ በመሆኑ ምላሹም ህገመንግስታዊ ማሻሻያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ዉህብእግዜር ፈረደ የአማራ ህዝብ ትግል በሚል ጭብጥ ሃሳባቸውን አጋርተዋል። በዚህም የአማራ ህዝብ እና የሃገረ መንግስት ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ የገባ መሆኑን በመጠቆም የችግሩን መውጫ መንገዶች አመላክተዋል።
በአራተኛ ደረጃ የመወያያ ጭብጥ የነበረው ሃገሪቱ የምትገኝበትን ጅኦፓለቲካዊ ሁኔታ የሚዳስስ ነበር። አቅራቢዉ ረዳት ፕሮፌሰር ባንታየሁ ሽፈራዉ ናቸዉ። አቶ ባንታዬሁ ሃገሪቱ የጀመረችዉ የለውጥ ጉዞ በተቃራኒ ራዕይ ያላቸው የፓለቲካ ሃይሎች ፍትጊያ ምክንያት የተጠበቀውን ያክል ተቋማዊና ህገ-መንግስታዊ ለውጥ ያላመጣ መሆኑን ጠቁመው ችግሩ በዚህ ከቀጠለ ከሃገሪቱ ጅኦፓለቲካዊ ውጥረት እንፃር ወደከፋ ችግር ሊገባ እንደሚችል አመላክተዋል።
በመጨረሻ ላይ የመወያያ ጭብጥ ያቀረቡት አቶ አንተነህ ብርሃኑ ሲሆኑ የጭብጣቸዉ ማጠንጠኛ ርዕስ ጉዳይ የፓለቲካ ተግባቦት ና የፓለቲካ ሽግግር የሚል ሲሆን በዚህ ጉዳይ ለሽግግር ተግዳሮቶችና እድሎች ያሉ መሆኑን አብራርተዋል። የማህበራዊ ሚዲያ እና የነቃ ወጣት መኖሩ የፓለቲካ ሽግግር ሂደትን ሊያሳልጥ እንደሚችል ጠቁመዋል። ይሁንና ማህበራዊ ሚዲያ ና ወጣቶች ተነሳሽነት ጉዳዮች በአግባቡ ካልተከወኑ ጉዳታቸዉ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ዶ/ር ታደስ አክሎግ እና ረዳት ፕሮፌሰር እምቢአለ በየነ በአወያይነት መድረኮችን የመሩ ሲሆን በመድረኩ በሳል እና ገንቢ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበዉ በተወያዮች በኩል ምላሽ ተስጥቶባቸዋል።

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

HAPPY NEW YEAR-2021!
----------------------------
Bahir Dar University wishes all celebrating students, staff and partners a very happy New Year!
We are holding a brief social event on Wednesday, 30 December, 2020 at Wisdom building garden with our international staff and students. We invite all celebrating university community members to join us for the meet-up and celebrate the coming of the New Year with solidarity and hope!
All Covid-19 protocols will be strictly followed throughout the event!

@bahir_dar_university

Читать полностью…
Subscribe to a channel