bahir_dar_university | Unsorted

Telegram-канал bahir_dar_university - Bahir Dar University,Ethiopia

-

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses' Students! www.bdu.edu.et Contact @bdu_tana_bot

Subscribe to a channel

Bahir Dar University,Ethiopia

#justice_for_dr_andualem_dagnie
Healing Hands Should Never Be Silenced by Guns.

Protect Physicians, Protect Humanity.

ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም

We invite you to participate in the Campaign for Justice.

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በእናንተ ደጋግ ወገኖቻችን ጥያቄ መሰረት ተጨማሪ የባንክ ሂሳብ መከፈቱን እናሳውቃለን።
===============
ከዚህ በፊት በሶስት የዩኒቨርሲቲው ሀኪሞች ስም ከተከፈተው ጥምር የንግድ ባንክ ሂሳብ በተጨማሪ በሌሎች የግል ባንኮች ሂሳብ ስለተከፈተ ከታች በተዘረዘሩት ሂሳብ ቁጥሮች ድጋፍ እንድታደርጉ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Exit Exam Placement
Summer Program: day 6

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የወርልድ ቴኳንዶ ልዑካችን የወርቅ ሜዳሊያውን ተረክቧል

በ68 እና በ53 ኪሎ ግራም የወርልድ ቴኳንዶ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት መሪ ሆኗል።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በአራት የስፖርት አይነቶች በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ዩኒቨርስቲያችን በመሪነት ሁለት ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Academy of Pedagogy Alumni Reunion!

Former graduates of Bahir Dar Academy of Pedagogy (Bahir Dar Teachers College) held a consultative reunion event at Kotebe University of Education (KUE).

The event was organized by graduates of 1970s in partnership with Gash Jember Woldemariam who was pioneer of Adult Education Program in Ethiopia & founding staff & head of continuing education program at Bahir Dar Academy of Pedagogy.

The consultative meeting was opened by Ato Oumer Mohammed (Class of 1972 E.C) welcoming the alumni; forwarding his special gratitude to KUE for hosting event & introducing the reunion’s agenda.

President of Kotebe University of Education, Dr.Berhanemeskel Meskel Tena who himself was a graduate of ‘’Peda” expressed his contentment for meeting his BDTC seniors that included former State Minister of Education, Dr.Tilaye Getie. He underlined that the formation of Academy of Pedagogy alumni association will play a pivotal role for healing the wounds of quality education & upgrading the status of teaching profession in Ethiopia.

Gash Jember Woldemariam who taught diverse courses like Sociology of Education for generations of Peda graduates lead the alumni reintroduction event filling it with a sense of humor & poetry.

The reunion event completed dinning together after ratifying the logo of the association, agreeing on need for producing an establishment document for securing legal status for the association & time for its subsequent meeting.

Ato Bonsa Bayisa (Class of 1972), a member of the organizing committee, finally forwarded his gratitude for those who attended the meeting, both physically & in online platforms, & conveyed his hope for the accomplishment of delegated tasks & a wider participation of alumni in the next reunion event.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 3፡2 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

በኢትዮጵያ ከፍ/ትም/ተቋማት ስፖርት ፌስቲቫል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ አራት የውድደወር ዘርፎች በመወዳደር ላይ ሲሆን እስካሁን ድረስ በሁለት የቴኳንዶ አይነቶች ሁለት የወርቅ ሜዳለያ ያገኘ ሲሆን በእግር ኳስ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር አቻ ወጥቷል፡፡ በሌላ ጨዋታ ደግሞ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ሐረማያ 1 ፡1 ባሕር ዳር
የ2017 ዓ/ም ከፍ/ትም/ተቋማት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለአዲስ ገቢ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ተማሪዎች የህይዎት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

ጥር 19/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት የሰብዕና ግንባታ ማስተባበሪያ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ለገቡ ከአንድ ሺ አራት መቶ በላይ ለሚሆኑ የአቅም ማሻሻያ መርሃ ግብር ተከታታይ ተማሪዎች በ35 አሰልጣኞች ለ3 ተከታታይ ቀናት መሰጠቱን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ገልጸዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ ዓባይ ግቢ የጀማሪ መርሐግብር ተማሪዎች አስተባባሪ ዶ/ር እባቡ ቸኮለ የዚህ ስልጠና አስፈላጊነት ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው በራስ የመተማመን፣ ራሳቸውን የመግለጽና ከሌሎች ጋር የሚኖራቸውን መስተጋብር እንዲሁም የትምህርት አቀባበል ክሕሎታቸው ( Self exploration skill, Interpersonal skill and Academic skill) አሳድገው ለሚቀጥለው ሀገራዊ ፈተና ራሳቸውን ብቁ እንዲያደርጉና ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን አቅም መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

በአሰልጣኝነት ስልጠናውን ከሚሰጡት መምህራን ውስጥ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትም/ክፍል መምህር አቶ ዮርዳኖስ ይበልጣል ይህ ስልጠና ተማሪዎቹ ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የስነ ልቦና ክህሎታቸው፣ ችግር የመቋቋም ችሎታቸውን ለማዳበር የሚያስችል ሲሆን ሌላው ደግሞ ማህበራዊ ግንኙነትን፣ የተግባቦት ችሎታቸውን እንዴት እንደሚያዳብሩ፣ ችግር ሲገጥማቸው እንዴት መፍታት እንደሚችሉ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ችሎታቸውን የሚያዳብር ሲሆን በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በትምህርታቸው ውጤታማ ሆነው መውጣት እንዳለባቸው ስልጠና ተሰጥቷቸል፡፡

አቶ ዮርዳኖስ አያይዘውም ዓላማ እንዴት እንደሚነድፉ፣ ጊዜያቸውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው፣ የአጠናን ስልታቸው ምን መምሰል እንዳለበት፣ ኢንተርኔት እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው፣ ለፈተና ራሳቸውን እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸው፣ በፈተና ወቅት የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መቋቋም እና መፍታት እንዳለባቸው እንዲሁም ልጆች ለደባል ሱስ እንዳይጋለጡ፣ ዩኒቨርሲቲ ላይ ያሉ አገልግሎቶችን በሙሉ የት ላይ ማግኘት እንዳለባቸው ስልጠና እንደተሰጣቸውና ወደፊትም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

ከደብረ ብርሃን ከተማ የመጣችው ተማሪ ሐይማኖት ዝናቡ ስልጠናው ራሳችንን እንዴት መምራት፣ መቆጣጠር እንዳለብን፤ ለሀገራችን፣ ለትምህርታችን እንዲሁም ለቤተሰቦቻችን ዋጋ መስጠት እንዳለብን እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሌሎች ጋር እንዴት አብረን መኖር እንደምንችል እና ችግር ሲገጥመን እንዴት መፍታት እንደምንችል፣ በትምህረታችን እንዴት ውጤታማ እንደምንሆን በስልጠናው አግኝተናል ብላለች፡፡

ሌላው ከባሕር ዳር ከተማ የመጣው ተማሪ በረከት ብርሃኑ በሕይዎታችን የሚገጥሙንን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደምንችል እና ከማህበራዊ ሚድያ ሱሰኝነት በመውጣት ሰአታችንን በአግባቡ መጠቀም እንዳለብን እንዲሁም ከባድ መስለው የሚታዩንን ነገሮች እንዴት ማቅለል እንደሚቻል ከስልጠናው ተንዝቤያለሁ ብሏል፡፡

@bahir_dar_university

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በውድድሩ የመጀመሪያውን ወርቅ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አገኘ

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በወርልድ ቴኳንዶ በወንድ 68kg በአማኑኤል ዳንኤል አሸናፊነት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት የህግ ተማሪው አማኑኤል ዳንኤል እልህ አስጨራሽ በሆነው ውድድር ከ 8፡00ስዓት እስከ ምሽቱ 2፡ዐዐስዓት ድረስ 6 ጨዋታዎችን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

ዩኒቨርሲቲያችን በአራት የውድድር አይነቶች በመሳተፍ ላይ ሲሆን ከአራቱ አንዱን አስቀድሞ ወርቁን በእጁ ማስገባት ችሏል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ቀን፡ 16/05/2017 ዓ.ም
ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)
--------------------------------------
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ Science College አካዳሚክ ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም በወጣው ማስታወቂያ በቂ አመልካች ባለመኖሩ ለተጨማሪ ቀናት ማራዘም አስፈልጓል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ አካዳሚክ ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡-
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ጥር 16 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ የገና በዓልን ከተማሪዎች ጋር አሳለፉ

ፕሬዚዳንቱ በሁሉም ግቢዎች ተዘዋውረው የበዓል ቀን የተማሪዎች የምሳ ግብዣ ላይ ተገኝተው ከተማሪዎች ጋር የምሳ ሰዓት አሳልፈዋል።
ዶ/ር መንገሻ በዩኒቨርስቲው ግቢዎች ማለትም በፔዳ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በሰላምና በፖሊ ግቢዎች በሁሉም የምግብ አዳራሾች ተገኝተው የተማሪዎችን የበዓል መዋያ ልዩ ዝግጅት በመመልከት ለተማሪዎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከፕሬዚዳንቱ ጋር የዩኒቨርሲቲዉ የስራ ኃላፊዎች፦ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር እንዲሁም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተገኝተዋል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

"የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ጥናት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት” በሚል መሪ-ቃል አውደ ጥናት በፔዳ ግቢ ተካሂዷል፡፡
በአውደ ጥናቱ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ፤ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፤ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እስከዳር ግሩም፤ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲ ፋኩሊቲ አባላት እና ተማሪዎች በመድረኩ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሂውማኒቲ ፋኩሊቲ ዲን ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን እንደገለጹት ጉባኤው ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት” በሚል መሪ-ቃል የመወያያ አጀንዳ የሆነበት ምክንያት የሀገር በቀል እውቀት ለሀገራዊ እድገት የሚያበረክቱትን ወሳኝ ሚና አጉልቶ ለማሳየትና የተቋማት የትኩረት ነጥብ ለማድረግ በመፈለግና ቅንጅታዊ አሰራርን ለመመስረት በማለም ነው ብለዋል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከሀገራዊ የእድገት ስትራቴጅዎች ጋር በማዋሃድ ማህበረሰቦች ዘላቂ ልምዶቻቸውን ሳይንሳዊ ከሆነው አስተሳሰብ ጋር በማዋሃድ መጠቀም እንዲችሉ ለማበረታታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሃገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶች ያሉንን ሃብቶች ከመሰነድና እውቀቱን ለትውልድ ከማሻገር በተጨማሪ ለምርምርና ለፈጠራ ማእከል በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆን አንገብጋቢ የሆኑ አለማቀፋዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ሀገር በቀል እውቀቶች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል ዶ/ር ዋልታንጉስ፡፡
ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን አክለውም ሀገር በቀል እውቀቶች በአገሬው ተወላጅ ማህበረሰቦችና በተፈጥሮ መካከል ያለውን የተወሳሰበ ግንኙነት የሚያንጸባርቁ ሲሆን በሰዎች እንቅስቃሴ፤ በጤናና በስነ-ምህዳር መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅም ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር በቀል እውቀትን ወደ ዘላቂ የልማት ማእቀፎች በማቀናጀት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ የሀገር በቀል አመለካከቶችን በስርዓተ ትምህርትና በምርምር አጀንዳዎች ውስጥ በማካተት ዩኒቨርሲቲዎች ከባህላዊ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የአካባቢ ተግዳሮቶችን የሚፈታ ትምህርት ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
ሀገር በቀል እውቀት ሰፊ ቢሆንም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማእከል አደርጋቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘርፎች መካከል ትምህርትና ህክምና በመሆናቸው በነዚህ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን ብለዋል ዶ/ር ዋልታንጉስ መኮንን፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እስከዳር ግሩም በበኩላቸው ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ድርሳኗ የከተበቻቸው ዘመናትን ያስቆጠሩ ባህላዊ የእውቀት ማዕከላትና ተቋማት ያሏት ታሪካዊ ሃገር መሆኗን ገልጸው ተቋማቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የእውቀት፤ የፍልስፍና እና የጥበብ እንዲሁም የምርምር ጥናት ማእከል ሆነው በርካታ ሊቃውንትን አፍርተዋል ብለዋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት የገነባቻቸው አገር በቀል የእውቀት ማእከላትና ተቋማት በየዘርፎቹ የሚኖራቸው ሚና የጎላና ከፍተኛ ቢሆንም በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ አበው ሀብቶቻችን በወጉ ሳንጠቀምባቸው ለውስብስብ ችግሮች እየተዳረግን እንገኛለን ብለዋል ወ/ሮ እስከዳር ግሩም፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ የሀገር በቀል እውቀት ምንጭ ማእከላት ያላቸውን ሙሉ አቅም ለሀገራዊ ልማት በማዋል ረገድ አስተዋጾ አላቸው፡፡ ስለሆነም ሃገር በቀል እውቀቶችን ከልማት አጀንዳዎች ጋር በማዋሃድ ለባህል ደጋፊና ለአካባቢ ተስማሚ ለሆነ ዘላቂ እድገት አስተዋጾ ማድረግ እንዲያስችሉ አድርጎ ማስተሳሰር እና ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በዶ/ር ማረው ዓለሙ፤ የድጓ ማስመስከር ትምህርት ስነ ትምህርታዊ ፋይዳ በቅድስት ቤተልሔም የሚል ገላጭ ጥናት እና በዶ/ር ተመስገን በየነ፤ የባህል ህክምና ዕውቀት ሥርዓትና ተግባር አውዳዊ ትንተና በደቡብ ጎንደር ዞን በሚሉ ርእሶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ከታዳሚው ሰፋ ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው በጽሁፍ አቅራቢዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የዶ/ር ጀማል መሐመድ ተፅፎ ለንባብ የበቃው "ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙሃን" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ተመረቀ

ታህሳስ 25/2017 ዓ. ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የጋዜጠኝነትና ስነተግባቦት መምህርና ተመራማሪ በሆኑት ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ የተደረሰ ጋዜጠኝነትን የሚመለከቱና ሌሎች ከ22 በላይ መጣጥፎች በመድብልነት የተዘጋጁበትና የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መጣጥፎችንና ወጎችን ያካተተ ‹‹ ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙኃን›› በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በመጽሐፉ ምረቃ ላይ የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ንግግራቸው መጽሐፉ ከደራሲው ልምድ፣ ትምህርት ዝግጅት የሚቀዳ ወደ ፊት የመጭው ዘመንን በተለይ ጋዜጠኛን አርሞና አስተካክሎ ወደፊት የሚመራ እንደሚሆን እምነት እንዳላቸው ተናግረው ለመማር ማስተማርና ለምርምር መነሻ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ አክለውም ደራሲው በኢትዮጵያ የመገኛ ብዙኃንና ጋዜጠኞች ላይ እርማት የሚያስፈልግበት ነገር እንዳለ የሚያሳይ ርዕሰ ጉዳይ ይዘው መምጣታቸውንም ተናግረዋል። ዶ/ር መንገሻ አክለውም በመጭው ዘመን ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በበጋጠኝነትና በጋዜጠኞች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ፕሮጀክቶችን ከወዲሁ ለመጀመር መንገድ ይሆነናል ብየ አስባለሁ፡፡ ትምህርት ክፍሉ በቀጣይ ዘመን ትውልድ አወንታዊ ተፅዕኖ እንዲኖርዎት በተለይ የጋዜጠኛ ሚና ምን መሆን አለበት? ወደዚህ ሙያ የሚመጡ ተማሪዎችን እንዴት እናስገባ? ምን አይነት እገዛ እናድርግ? ምሁራን በዚህ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ከተቋም ወይ ከሌላ ከፕሮጀክት ምን እናድርግ ? በሚሉ ሃሳቦች ላይ የሚሳካልኝ ከሆነ ለመስራት ቃል እገባለሁ በማለት ለደራሲው የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጋዜጠኝነትና ስነተግባቦት ት/ክፍል መምህርና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ገብሩ ከመጽሀፉ ለቅምሻ ቅንጭብጭብ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡

ዶክተር ሰለሞን ተሾመ ከፎክሎር ት/ክፍል ስለ መጽሐፉ ከባህል አንጻር ያዩትን ምልከታ አካፍለዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ አጠቃላይ የማህበረሰቡን ማንነት፣ ባህል፣ እውቀት በአንድ ግለሰብ እይታ የታየውን የተገነዘበውን የተማረውን ልምድ ያደረገውን ሀሳብ በሰላ ብዕሩ ልዩ በሆነ የስነጽሑፍ ችሎታው አቅርቦልናል፤ እንዲሁም ማንም ሊደፍራቸው የማይችሉ ሀሳቦች በመጽሐፉ ተነስተዋል በማለት ከባህል አንጻር ከዩኒቨርሲቲያችን ግቢ ውስጥ ካለ የደንገል ተክል ጥቅም ጀምሮ እስከ የአፋር ዳጉ፣ የህንድ አለባበስ፣ የሳውዲ ጉዞ አለባበስ፤ ስለ መውሊድ በአል አከባበር፣ በሰቆጣ በኩል የራሳችንን ማንነት፣ ባህል፣ ችግሮች፣ ኋላቀርነትና በጣም የመጠቁ ነገሮች እንዲሁም የፖለቲካ ባህላችንን አሳይቶናል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፉ እንደ መጣጥፍ ለአንድ ጋዜጠኛ ወይም የተግባቦት ተማሪ እንዴት እንደሚጽፍ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ስለ ድርሰቱ አይነት፣ የድርሰቱ የሽፋን ገፅ ስዕል ትርጓሜ፣ የትረካውን አይነት፣ መቼቱን እንዲሁም በድርሰቱ ውስጥ ስላሉት መጣጥፎች ከስነጽሑፍ አንጻር ሰፋ ያለ ገለጻ ያደረጉት የስነጽሑፍ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አንተነህ አወቀ ሲሆኑ የጋዜጠኝነት መምህር የሆኑት አቶ ሐሰን ዑስማን ደግሞ በድርሰቱ ውስጥ ከጋዜጠኝነት አንጻር ወደ ሙያው የሚገቡትንም ሆነ በዘርፉ ተሰማርተው ለሚገኙት ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ ብለዋል፡፡

አቶ ሐሰን አክለውም ለዛሬ ተማሪዎች ለነገ ጋዜጠኞች ናሙና ይሆናሉ በሚል በመጽሐፍ ዝግጅቱ ስር ከተካተቱት መጣጥፎች በርካታ ነገሮችን መቅሰም እንደሚቻል፣ ጋዜጠኝነት ምንነት፣ ስራው ምን እንደሆነ፣ ምን መሆን እንዳለበት፣ የሚሰራበት ቋንቋ ምን እንደሆነ፣ የቋንቋ አጠቃቀምና የሀሳብ አደረጃጀት ጠንቅቆ ማወቅ እንዳለበት ከድርሰቱ አንጻር ገለጻ አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ከታዳሚዎች ለተነሱት አስተያየቶች የደራሲው ምላሽ የተሰማ ሲሆን የመጽሐፉ ደራሲ ዶ/ር ጀማል ሙሀመድ መጽሐፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ስላስመረቀላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የተሰጡ ሃሳቦች ለቀጣይ ስራቸው ማዳበሪያነት እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። በመጨረሻም ደራሲው በምረቃው ላይ ለተገኙት የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ ለተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ለተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የሐገር በቀል ዕውቀት ምንጭ ማዕከላቶቻችን ለዘላቂ ባሕል ልማት

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የዶክተር አንዷለም ዳኜ ቤተሰቦች ሊደገፉ በሚችሉባቸው ኹኔታዎች ውሳኔ አሳለፈ።

ባሕር ዳር: ጥር 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዶክተር አንዷለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሠራት ባለባቸው ተግባራት ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ዩኒቨርሲቲው የዶክተር አንዷለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሠራት ባለባቸው ሥራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸው እና በሕይዎት ዘመናቸው ያከናወኗቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦዎችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

ዶክተር አንዷለም የተሰጣቸውን ጸጋ ሳይሰስቱ በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎች እና በሙያው ላገለገሏቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበሩ እንቁ ባለሙያ ነበሩ።

ዶክተር አንዷለም ዳኘ ገና በ37 ዓመታቸው ሕይወታቸውን ያጡ ናቸው። ህጻናት ልጆችን ትተው ያለፍ እና ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌላቸው ናቸው።

የቀረበላቸውን በርካታ ዓለም አቀፍ የሥራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገናቸውን ለማገልገል የቆረጡ ነበሩ። በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበራቸውን ልዩ አበርክቶ እና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣሩ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሰው ያለፍ ናቸው።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሙያዊ አቅም ተጠቅመው ራሳቸውን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥተው ያለፍ ታላቅ ባለሙያ እንደነበሩ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቻቸው የሚመሰክሩላቸው ድንቅ ሐኪም የነበሩ መኾኑን ዩኒቨርሲቲው በጥልቀት አይቷል፡፡

በመኾኑም የዶክተር አንዷለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤ ባለቤታቸው ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ ዓቅም ያላቸው በመኾናቸው በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የሚቀጠሩበት ኹኔታ እንዲመቻች፤ ዶክተር እንዷለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሠሩት እርሳቸው ናቸው።

ክፍሉን እስከ ህልፈታቸው ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበረ በመኾኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስማቸው ዶክተር አንዷለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም ተወስኗል።

የአንዷለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነትን በቋሚነት ለመዘከር እና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምላቸው፤ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስማቸው BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም ተወስኗል።

ለ40ኛ ቀናቸው መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶክተር አንዷለም የሕይወት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ተወስኗል።

ይህ ውሳኔም በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ተግባሩን ለማሳለጥ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በኩል የሚሠሩ ዝርዝር ሥራዎችን የሚከታተል የሥራ ባልደረቦቻቸውን ያቀፈ ኮሚቴም ተቋቁሟል፡፡

በመጨረሻም የአንዷለም ዳኘን(ዶ.ር) የግፍ ግድያ አስመልክቶ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ተቋም ፍትሕን አጥብቆ የሚሻ ሲሆን ክስተቱ የአንድ ጊዜ አጋጣሚ ብቻም ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያጣውን በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ አገልግሎት ኀላፊ አድነው በለጠን ጨምሮ እየተደጋገመ የመጣ እና ለሕብረተሰቡ አገልጋይ የሆኑ እንቁ ሃኪሞቻችንን ደህንነት እንዲሁም የማሕበረሰቡን የጤና አገልግሎት በእጅጉ እየተፈታተነ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን እና ጥልቅ ምርመራ አድርገው በግድያው ላይ እጃቸው ያለበትን አካላት በአፋጣኝ ለሕግ እንዲቀርቡ ተጠይቋል።

ይህ ጉዳይ በቋሚነት መፍትሔ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶች እንደሚደረግም ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

via የአሚኮ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት
•••
የፊታችን ቅዳሜ ማለትም በ01/06/2017 ዓ.ም በሆስፒታላችን ሐኪምና ቦርድ አባል በነበሩ ውድ ወንድማችን ዶ/ር አንዱዓለም ዳኘ ድንገተኛ ህልፈት መታሰቢያ የሚሆን የሻማ ማብራት ፕሮግራም #በአፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታል ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል:: ስለሆነም የሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ ሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶቹ በፕሮግራሙ ላይ እድትገኙ ተጋብዛችኋል::

"አፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታል"

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

እንኳን ደስ አላችሁ!
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ላይ በሴቶችና በወንዶች በሁለቱም ፆታ የወርልድ ቴኳንዶ በተለያዩ ክብደት ውድድሮች አንደኛ በመውጣትና በማሸነፍ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለተወዳዳሪ ልዑክ ቡድኑ በሙሉ ፣ ለአሰልጣኞችና ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!!

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

በ68 እና በ58 ኪሎ ግራም የወርልድ ቴኳንዶ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት መሪ ሆኗል።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በአራት የስፖርት አይነቶች በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ዩኒቨርስቲያችን በመሪነት ሁለት ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሴቶች -53ኪ/ግ ወርልድ ቴኳንዶ በየአብስራ በቀለ አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘ

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ዛሬ ባሕር ደር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ፌስቲቫሉ በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Five Scholars at Bahir Dar University Achieve Associate Professor Rank

BDU, (January 27, 2025) – Bahir Dar University celebrates the academic excellence of five distinguished faculty members with their recent promotion to the esteemed rank of Associate Professor. This achievement recognizes their exceptional contributions to teaching, research, and service.
The rigorous promotion process, guided by the university's Faculty Development Guidelines, evaluated candidates across multiple dimensions, including teaching excellence, research productivity, and service to the university and community. Each of the promoted scholars exceeded the required 80% threshold, achieving impressive scores.

1. Dr. Gorawu Goshu (College of Agriculture and Environmental Sciences), specializing in Ecohydrology & Water Quality, demonstrated a strong commitment to research and teaching excellence, achieving a score of 96.01%.

2. Dr. Zerihun Nigusse (College of Agriculture and Environmental Sciences), specializing in Agricultural Economics, was recognized for his outstanding contributions, achieving a score of 98.64%.

3. Dr. Mezgebu Ashagre (College of Agriculture and Environmental Sciences), also specializing in Wildlife Ecology and Conservation, received a score of 96.73% for his significant contributions to the field.

4. Dr. Yayeh Bitew (College of Agriculture and Environmental Sciences), specializing in Agronomy, achieved a score of 97.79%, reflecting his dedication to research and teaching.

5. Dr. Getachew Tizazu (College of Science), specializing in Condensed Matter Physics, achieved a score of 96.35% for his exceptional contributions to the university.

This recognition underscores Bahir Dar University's commitment to fostering a vibrant and intellectually stimulating environment that supports the growth and development of its faculty. The university extends its heartfelt congratulations to these esteemed scholars on this significant milestone in their academic careers.

Congratulations!

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ማስታወቂያ
የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ጊዜን በድጋሚ ስለማሳወቅ
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዚህን በፊት መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ፈተናውን ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች (አዲስና በድጋሚ ለመፈተን ያመለከታችሁ በሙሉ) ፈተናው የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
 ተጨማሪ መረጃዎች በምዝገባ link እና በተለያዩ የግንኙነት ዘዴዎች በየጊዜው የምናዋሳውቅ በመሆኑ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ በክብር እንግዶች ፊት ሲያልፍ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

Call for Paper
Calling All Scholars & Researchers!

The Faculty of Humanities at Bahir Dar University invites you to submit abstracts for the 11th Annual Conference on Language, Culture, and Communication!

Theme: "Indigenous Knowledge and the Interplay of Language, Art, Culture, and Communication for a Sustainable Future"

Sub-themes:

✍️Linguistics, Language Practices, and Policies in the Context of Indigenous Knowledge
✍️Literature, theatre, film, music, folklore, and social values
✍️Media, diversity, information management, and crisis communication
✍️Indigenous knowledge and its roles in societal transformation
✍️Geez Manuscripts as a Source of Indigenous Knowledge

Important Dates:

Abstract Submission Deadline: March 24, 2025
Notification of Acceptance: April 8, 2025
Final Paper Submission Deadline: May 8, 2025
Conference Date: May 23, 2025

#Submission:

Send your abstracts and final papers to: ayuguad2019@gmail.com

Organized By:
Faculty of Humanities
Graduate, Research, and Community Engagement V/Dean’s Office

Visit: www.bdu.edu.et


JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሕጻናትና አቅመ ዳካማ አረጋዊያን ጋር የገና በዓልን አሳልፈዋል

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዝግባ ሕጻናትና አረጋዊያን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት በመረዳት ላይ ለሚገኙ ወገኖች የምሳ ግብዣ በማድረግ በዓልን አሳልፈዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ተገኝተው ድርጅቱን በመጎብኘት ለዚህ መልካም ተግባር ትኩረት ለሰጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች አድናቆታቸውን ችረዋል።

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን!
መልካም የገና በዓል!!

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

#Announcement
Second Round of GAT Training

To Interested PG Applicants
The Science College and Faculty of Humanities at Bahir Dar University are pleased to announce the second round of GAT training scheduled for Tir 1-4, 2017 E.C.

The training will focus on the following key areas:
Verbal Reasoning: Tests reading comprehension, vocabulary, and the ability to understand and analyze written material.
Quantitative Reasoning: Measures mathematical skills, including arithmetic, algebra, geometry, and data analysis.
Analytical Writing: Assesses critical thinking and the ability to articulate complex ideas clearly (in versions of the GAT that include a writing component).

Training Schedule:
Tir 1-2, 2017 E.C.: Online Training
Portal for Online Training:https://lms.bdu.edu.et
Tir 3-4, 2017 E.C.: Face-to-Face Training
Venue for Face-to-Face Training: Science College Smart Rooms, Peda Campus

Coordinators:
Prof. Tsegaye Kassa: 0920761042
Dr. Ayenew Guadu: 0967610008

Trainers: Experts from the Departments of Mathematics and English Language and Literature
We encourage all interested postgraduate applicants to take advantage of this valuable opportunity to prepare for the NGAT.

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና (CPD) ዕውቅና ሰጪ ተቋም ሆኖ ፈቃድ አጊኝቷል።

ኮሌጁ ለሌሎች ማዕከላት ዕውቅና የመስጠት ፈቃድ (CPD Accreditor) ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን አሳውቋል።

ይህም ኮሌጁ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችለው ሲሆን፤ ፈቃዱ ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና Continuing Professional Development (CPD) የሚሰጡ ከ250 ተቋማት እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…

Bahir Dar University,Ethiopia

ደማቅ የስነጽሁፍ ምሽት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲ ፋኩሊቲ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ት/ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪዎች የስነፅሑፍ ኮርስን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የጥበብ ምሽት አዘጋጅተዋል፡፡

ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ክፍት የነበረው ይህ መድረክ የተለያዩ የኪነጥበብ ዘውጎች ያላቸው ስራዎች በተማሪዎች ቀርበውበታል፡፡
በመክፈቻው መርሃ ግብር የሲኒማና ቴአትር ጥበባት መምህር አቶ ግርማው አሸብር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የስነጽሁፍ ምሽቱ የተዘጋጀው ለተማሪዎቹ ኮርስ ማሟያነት ሲሆን እግረ መንገዱንም ለግቢው ማህበረሰብ በአዝናኝነትና በአስተማሪነታቸው የተመረጡ ስራዎች ለመድረኩ በተማሪዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው በቀጣይም የስነጽሁፍ ምሽቶች ውስን በሆነ ጊዜ ለግቢው ማህበረሰብ ቢቀርቡ ሊኖራቸው የሚችለውን ፋይዳ አስገንዝበዋል፡፡

የኮርሱ መምህር የሆኑት አቶ ግርማው አክለውም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሰጡ ኮርሶች በተግባር መደገፍ ያለባቸው መሆኑን በመናገር የ2ኛ ዓመት የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ተማሪዎችም የስነጽሁፍ መግቢያ ኮርሳቸውን ምክንያት በማድረግ በክፍል ውስጥ የተማሩትን በመድረክ ለማሳየት እና ስነጽሁፍ በመድረክ እንዴት ይህንመከወን እንዳለበት ለመለማመድ ሲባል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አሳውቀዋል።

በመርሃ-ግብሩ በትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች የተዘጋጁ ግጥሞች፣ መነባንብ፣ ቅኔ እና ሀገራዊ መልዕክት ያላቸው የሙዚቃ ስራዎች ቀርበው ታዳሚዎቹን ሲያዝናኑ አምሽተዋል፡፡ በዕለቱ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተጋባዥ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በመድረኩ ታድመዋል።
በመድረኩ በታዳሚነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር ለማ ካሳዬ የቀድሞ የባህል ማዕከል የተማሪነት ዘመን ተሳትፏቸውን በማስታወስ ትዝታቸውን አካፍለዋል፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ወደዚህ መድረክ በኪነጥበብ ክዋኔ መጋበዛቸውን በማስታወስ ቀድሞ በተማሪነታቸው ጊዜ ሲጫወቷቸው ከነበሩ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊያን ዜማዎች ውስጥ የኤፍሬም ታምሩን ዜማዎች ለታዳሚው አንጎራጉረዋል፡፡ ዶ/ር ለማ አክለውም በቀጣይ ይህን አይነት ቋሚ የስነ-ጽሁፍ መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል፡፡

የሂውማኒቲ ፋካሊቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት ዶ/ር ተመስገን በየነ የመርሃ ግሩን መዘጋጀት በማድነቅ መማር ማስተማር ሂደቱ በተግባር መደገፉ ለተማሪዎች ጥሩ እድል የሚሰጥ መሆኑን በማስታወስ የተለያዩ የጥበብ ዘውጎች በአንድ መድረክ ሲቀርቡ ውብ በመሆናቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ተመስገን አክለውም ይህ አይነት የጥበብ መድረኮች በሲኒማና ቴአትር፣ አዲስ በተከፈተው የሙዚቃ ጥበብ መርሃ ግብር ፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ባህል ማዕከል በትብብር በመደበኛ መርሃ ግብር እየተዘጋጀ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

JOIN👇👇👇
@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

#Share   #Share

Читать полностью…
Subscribe to a channel