biyabtc | Unsorted

Telegram-канал biyabtc - How to Earn Online🤔?

59

ይህ ቻናል ቢዝነስ ለመስራት የሚፈልግ ሰው በቀላሉ ሊሰራ የሚችልበትን የቴክኖሎጂ ውጤት ✍ብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ✍ክሪፕቶ ከረንሲ ✍Forex እና Crypto trading 🏦በአለም ላይ በቀን ከ 5.3 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ከሚንቀሳቀስበት የፋይናንስ ማዕከል ውስጥ በመቀላቀል ተጠቃሚ ይሁኑ!! 👉👉 @BitCoin_in_Ethiopia20

Subscribe to a channel

How to Earn Online🤔?

መረጃ የሚሰርቀው የቻርጀር ገመድ
*******************************
ማርክ ግሪን የተባለ የደህንነት ተመራማሪ OMG የተሰኘው የቻርጀር ገመድ የተጠቃሚውን መረጃ በመውሰድ ወደ ሌላ ቦታ እንዲያስተላልፍ አድርጎ መስራቱ ተነገረ፡፡ ይህም ገመድ በተለይ ሀከሮች (የመረጃ መንታፊዎች) ከተለያዩ ኮምፒውተሮችና የሞባይል ስልኮች ላይ የሚፈልጉትን መረጃ ማስተላለፍ እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡ ገመዱ ከተሰካበት ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ያሉ የይለፍ ቃላትንና ሌሎች ምስጢራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ሁነኛ ዘዴ ተደርጎም ተወስዷል፡፡
ከዚህ በፊት የነበረው ላይትኒንግ የተሰኘው ገመድ ስልኮቻችንን ከኮምፒውተር ጋር በማያያዝ ሀይል መሙላት የሚያስችል የነበረ ሲሆን ማርክ ግሪንና ጓደኞቹ ለዚህ ገመድ ማሻሻያ አድርገውለታል፡፡ አሁን ላይ ገመዱ መረጃን አከማችቶ ከመያዝ በተጨማሪ በውስጡ በተገጠመለት የ WiFi ቺፕ አማካኝነት መረጃውን ወደ ሌሎች ቦታዎች ማስተላለፍ ይችላል፡፡
ማርክ ግሪን ይህንን ገመድ በዚህ መልክ ያሻሻለበትን ምንያት ሲናገር በቴክኖሎጂው ዙሪያ ያሉ ሰዎች ይህን ማድረግ አይቻልም የሚል እምነት የነበራችው በመሆኑ፤ በተለይም መረጃን ለማከማቸት እና ለማስተላለፍ የሚረዱ ቁሶችን በገመዱ ውስጥ መግጠም ያስቸግራል ስለሚሉ ይህ እንደሚቻል ለማሳየት እንደሆነ ተናግሯል፡፡
አንድ ሰው ይህን ገመድ በመጠቀም ስልኩን ቻርጅ ሲሞላ ወይም መረጃ ሲያስተላልፍ ገመዱ ስራውን ውስጥ ለውስጥ ይሰራል፡፡ ሀከሮችም ገመዱ የሚሰራውን ስለሚያውቁ ባዘጋጁት የመረጃ ቋት በኩል ሆነው ይጠባበቃሉ፡፡
ይህም የሚያሳየን የምንጠቀማቸውን ኬብሎች ምንነት መለየት እንዳለብን ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራዊ ተቋማትና ድርጅቶች ውስጥ የምንጠቀማቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ምንነት በሙያተኛ ተጣርቶ መጠቀም ይገባናል፡፡
Source
(Technology and Innovation Institute, Ethiopia)

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

'ታሊየም' የተባለው የመረጃ በርባሪዎች ቡድን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር ነበር፡ ማይክሮሶፍት

ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ 'ማይክሮሶፍት' ከሰሜን ኮሪያ ጋር ግንኙነት ያላቸው የመረጃ ጠላፊዎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመዝበራቸውን ገለጸ፡፡
ታሊየም በቀመጫውን በሰሜን ኮሪያ በማድረግ የመንግስት ሰራተኞችን፣ቲንክ ታንኮችን /think tanks/ የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችን እንዲሁም በኑዩክሌር መስፋፋት ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች ኢላማ ካደረጋቸው መካከል እንደሚገኙበት ማይክሮሶፍት ገልጿል፡፡
ማይክሮሶፍት ታሊየም /Thallium/ የተባለ የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን ለመረጃ ስርቆት ሲገለገሉበት የነበረውን የዌብ ዶሜን /web domains/መቆጣጠሩን ገልጿል፡፡
ታሊየም ለአንድ የተወሰነ ግለሰብ ፣ ድርጅት ወይም ንግድ ላይ ያነጣጠረ የኢ-ሜይል ወይም የኤሌክትሮኒክ የግንኙነት ማጭበርበሪያ ዘዴን የሚጠቀም ሲሆን እራሱን ህጋዊ አስመስሎ በመቅረብ ተጠቂዎቹን እንደሚያጠምድ ተነግሯል ፡፡
ማይክሮሶፍት ታሊየም ይጠቀምበት የነበርን 50 የዌብ ዶሜኖችን መቆጣጠሩን ገልጿል፡፡
ቡድኑ በአጥፊ ሶፍትዌሮችን /malware/ በመጠቀም ስርዓተ ኮምፒውተሮችን ለጥቃት ማጋለጥን ጨምሮ ዳታዎችን እንደሚሰርቅ ማይክሮሶፍት ጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡- ሮይተርስ/INSA

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ሲሞቱ የእርስዎ Bitcoin ምን ይሆናል? ችግሩን ለመፍታት የ casa ዓላማዎች ::



የ cryptocurrency ሃርድዌር እና አገልግሎት አቅራቢ casa እንደተናገረው እርሶ ከ ሞቱ በኀላ የ እርሶ bitcoin ላይ የሚገጥመውን ወሳኝ ጥያቄ ለመቅረፍ (Casa Covenant) የሚል መጠሪያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በአጭሩ ይህ ስርዓት እርስዎ ለመረጡት ሰው የ እርሶ bitcoin ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እርስዎ ለመረጡት ሰው ብቻ እንዲያስተላልፉ ያስችልዎታል ፣ እናም እርስዎ ከመሞቶ በፊት አንድ ሰው እነዚህን ገንዘቦች ሊሰርቅ የሚችልበትን አደጋ በሚቀንሱበት መንገድ ነው፡፡

ደንበኛው ሲያልፍ የ bitcoin ወራሹ Estate lawyer Key, Casa’s Recovery Key, and a Safety Deposit Box Key ከትክክለኛዎቹ የሕግ ደረጃዎች ጋር ካሟላ በኋላ የ ቢትኮይኑ ዝውውር እንዲላክለት ያስችላል ፡፡

በሌላ አገላለጽ ይህ ስርዓት የሚሠራው የደንበኛው ሞት ትክክለኛ ማረጋገጫ ካገኙ ፣ ተገቢው የሕግ ማሟያዎች ከተከተሉ እና ትክክለኛዎቹ ግለሰቦች ስለ casa ቃል ኪዳን ዕውቀት ካላቸው ብቻ ነው ፡፡

@BiyaBTC @BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
እንዴት ዋላችሁ ውድ ተከታዮቻችን
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️

✒☠ጥቁር መረብ(Dark web)💻📱

✒ጥቁር መረብ የጥልቅ መረብ(Deep web) ትንሹ አካል ሲሆን ከሌላው መረብ( Standard Web) ወይም ኔትዋርክ የተደበቀ ሲሆን በተለመዱት አሳሽ ሶፍትዌር (Browser) ማልትም ፋየር ፋክስ፤ጎግል ክሮም፤ኦፔራ የመሳሰሉት ጥቁር መረብን ማግኘት አይቻሉም፡፡ ጥቁር ድር ብዙን ግዜ በህግ የተከለከሉ እቃዋች የሚሸጡበት እና ከፍተኛ የሆነ የጥቁ ገበያ (Black Market) የሚካሄድበት ቦታ ነው። በጥቁር ድር እንደ ናርኮቲክ, የልጅ ወሲብ(Child porn), የተሰረቁ ክሬዲት ካርዶች, እና ሌሎች ህገወጥ እቃዎች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። በጨለማ(ጥቁር) ድር ውስጥ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ ግብሮች በቢትኮይን (Bitcoin) እና በሌላ ኤሌክትሮ ሜል-መገበያያ ይከናወናሉ።

✒ጥቁር ድር የጥቁር መረብ ትንሽ አካል ሲሆን ሁለት አይነት ነትዋርክ ይጠቀማል።አንደኛው አቻ- ለ-አቻ-ኔትወርኮች(peer to peer network) እና ሁለተኛ ታዋቂ አውታረ መረቦች ያሉ ቶር(Tor)፣ ፍሪኔት(Freenet)፣ አይቱፒ( I2P)፣ ሪፍል(Riffle ) ፣በህዝባዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የሚተዳደሩ ነትዋርክ ያካታል።የጨለማው ድር ተጠቃሚዎች መደበኛ ድርን(standard web) እንደሚከተለው ይገልጹታል፦" ሚስጥራዊ ባለመሆኑ ምክንያት ማንም ሰው ልያጠቃን ወይም መረጃ ልንተውለት እንችለን" ብለው ያምናሉ።

✒ ጨለማ ድር ከሚያስጠቅም ሶፍትዌር መካከል ዋናው እና ተዋቂው አንዱ ቶር ብሮዘር ነው። ቶር ብሮዘር ኦውየንላንድ በመባል የሚታወቀው የኔትወርክ ከፍተኛ ደረጃን (top domain) ቅጥያ(suffix) የሚጠቀም ሲሆን ከፍተኛ የሆነ መመስጠሪያ ስልተ ቀመር (encryption algorithm ) ይጠቀማል። ይህ ብሮዘሩን ተጠቃሚውን ለማግኘት ወይም ጠለፋ(hacking) ለማድረስ የተወሳሰበ ያረገዋል።

✒በጥቁር ድር ያሉ አገልግሎቶች፡

☠ቦትኔት(botnet)
☠የብትኮይን አገልግሎቶች
☠የጥቁር ገብያ
☠የጠለፋ አገልግሎቶች(hacking Service)
☠ማጭበርበር አገልግሎቶች
☠ሽብርተኝነት
🚬አደገኛ እጽ እና ሌሌችም

@BiyaBTC @BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

♦ DV 2021 # ራሳችን_መሙላት እንችላለን! ♦

በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2021 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ Oct 02/2019 - Nov 05/2019 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣ First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል * በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ ፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክይቻላል ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved, as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍConfirmation
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Number ያለበትን ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን DV-2020 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2020 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ።
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር ማድረግ ትችላላችሁ።
Š FB

@BiyaBTC @BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

-ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ
ነጥቦች!--
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው? ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ
እና
ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች!
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር አስቀምጠንላችዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and
Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፤ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፡፡በዋጋም
ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ
የሆን
ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻልም
ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ
ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደ የስክሪን መጠናቸው
የተከፋፈሉ
ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን
ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ
ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን
ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core
i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ
አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ
ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን
ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም
እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ
(copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው
ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ
ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ
አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ
ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከመለዋወጫ አንፃር በሃገራችን Toshibaን የሚያክል
ላፕቶፕ የለም፡፡ከተበላሸ እና እክል ካጋጠመው
በተመጣጣኝ
ዋጋ መለዋወጫ ማግኘት ይቻላል፡፡ Acer ላፕቶፕም
የተሻለ
መለዋወጫ አለው፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP
እና
DELLም የተሻሉ ብራንዶች ሆነው መለዋወጫ ግን
እንደልብ
ማግኘት አይቻልም፡፡

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው?

BBC በአማርኛ ገፁ "ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪፕቶ ከረንሲ ምንድነው?" በሚል ፅሁፍ አስነብቧል።
ፅሁፉን ለማንበብ ሊንኩን👇👇 ይጫኑ!!

https://www.google.com/amp/s/www.bbc.com/amharic/amp/news-47249328


Join
👉 @BiyaBTC
👉 @BiyaBTC
👉 @BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

#tech_news
የኢትዮጵያ ሲምካርድ ከአገር ውጪ በዝቅተኛ ክፍያ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ድርጅቱ በሮሚንግ አገልግሎት ላይ የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የሮሞንግ አግልግሎት ኢትዮጵያዊያን ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለስራ፣ ለትምህርት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከሀገር ሲወጡ ሲም ካርድ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በሄዱበት ሀገር በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ደንበኞች ይህ አገልግሎት ውድ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱበት ነበር። ኢትዮ ቴሌኮም ይሄነን ቅሬታ ለመፍታት ከተለያዩ ሀገራት ኦፕሬተሮች ጋር በመነጋገር የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://news.bitcoin.com/the-most-important-aspect-of-bitcoin-is-the-separation-of-money-and-state/?utm_source=The%20Most%20Important%20Aspect&utm_medium=telegram&utm_campaign=Telegram%20Channel

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

Crypto Analyst: Bitcoin should hit $28,000 in the next 6-12 months - Koinalert
https://www.koinalert.com/crypto-analyst-bitcoin-should-hit-28000-in-the-next-6-12-months/?utm_source=Coinmarketapp&utm_medium=Push%20Notification

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

🌐 ብሎክ ቼይን ምንድነው?
======================
ብሎክ ቼይን በሚሊየን የሚቆጠሩ የኮምፒውተር መረጃዎችን ባልተማከለ መልኩ የሚመዘግብ የብሎክ ጥርቅም የሆነ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

✍ይህ ቴክኖሎጂ በባንኮች እጅ የሚገኘውን እና በመንግሥታት ግምጃ ቤት ቁጥጥር የሚደረግበትን የገንዘብ ዝውውርና የመረጃ ፍሰት ያልተማከለ ሚያደርግ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ከገንዘብ ዝውውር እስከ የመሬት ባለቤትነት ምዝገባ ያሉ ሥራዎችን ሊከወንበት እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡

✍የማይሳሳት፣ የማይሰረዝ እና የማይጭበረበር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የማይዘረፍ የአሰራር ሥርዓት ያለው ቴክኖሎጂ ነው፡፡

✍በተለይ በአፍሪካ ምድር አጨቃጫቂና የግጭት መንስኤ የሆነውን የመሬት አስተዳደርን በመመዝገብ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይታመንበታል፡፡

✍ይህ በብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ የተመዘገበ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ደግሞ በሁሉም ኮምፒውተሮች ተመዝግቦ ስለሚገኝ በኃላፊዎችና በሰራተኞች ከሚደርስበት መጭበርበርና ከሶስተኛ ወገን ስርቆት ይገጥመዋል ተብሎ የማይሰጋበት ከስርቆት የፀዳ ያደርገዋል፡፡

✍ለምሳሌ በብሎክቼይን የተመዘገበ አንድ መሬት በሙስና ለሌላ ሰው ቢተላለፍ መረጃው ኮፒ ሆኖ በአለም ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች ስለሚቀመጥ የትም ቦታ ላይ ይህ ስራ እንደተሰራ ስለሚነግረን ሙሰኞችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡

✍ከአፍሪካ ውስጥ ሩዋንዳ ወደዚህ ቴክኖሎጂ በመግባት የመሬት አያያዝን ለማዘመን በቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርማ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምራለች፡፡

✍ኢትዮጵያ ደግሞ የብሎክቼን ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ብቻ የተሳተፉበትን ቡድን የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞችን አስመርቃለች።
👉https://www.facebook.com/EBCzena/videos/2356014261297371/?app=fbl

✍ይህም ኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ውስጥ ዲጂታላይዝ የሆነ ስርዓትን ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ ነው፡፡

✍ብሎክ ቼይን የተሳካና ግልፅ ምርጫም ለማካሄድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

✍ለዲጂታል መታወቂያ፤ የማንፈልጋቸውን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ ለመሸጥ፤ የቅጅ መብትን ለማስጠበቅ፤ ለቤቶች አስተደዳር፤ የእቃ ዝውውርን ለማከናወን፤ ለግብር መክፈያ፤ ለህክምና ስራ (የታካሚዎችን መረጃ ለመያዝ እና ለመሳሰሉት)፤ ለህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር፤ እና ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ የሚውል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

✍ቴክኖሎጂው ክሪፕቶከረንሲ የተባለ ምናባዊ መገበያያ ይጠቀማል። ቢትኮይን ሌላው የክሪፕቶከረንሲ አይነት ነው። ከቢትኮይን በተጨማሪ በርካታ ብሎክ ቼይን የሚጠቀሙ ረቂቅ ገንዘቦች እየተፈጠሩ ነው፡፡ ኢቲሪየም፣ ቢትኮይን ካሽ፣ ዚካሽ የመሳሰሉ የብሎክቼይን ውጤት የሆኑ ረቂቅ ገንዘቦች ናቸው፡፡

================
የዛሬን አበቃን ክፍል ሁለት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይዘን እንቀርባለን!

ምንጭ: ኢኖቬሽን ና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🌺 @BiyaBTC 🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://elibraico.com/?ref=ZZCGITF3KFCPN


Facebook አዲሱን የራሱን ገንዘብ ሲለቅላቹ በደስታ ነው።

Rigister ያድርጉ አዲሱን የFacebook ገንዘብ ያግኙ።

👇👇👇Register & Share
https://elibraico.com/?ref=ZZCGITF3KFCPN
https://elibraico.com/?ref=ZZCGITF3KFCPN https://elibraico.com/?ref=ZZCGITF3KFCPN

For more information
Join 👉👉 @BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

የኳስ ጫወታዎችን በትንሽ ገንዘብ ገምተው ካወቁ ብዙ ገንዘብ የሚያገኙበት ሲስተም ስናመቻችላቹ በደስታ ነው።

ይገምቱ!!! ይሸለሙ!!!

በመጀመሪያ ስትመዘገቡ ነፃ 10 ኮይንሸ ይሰጣችዋል ከዛ አውቃችሁ ከበላቹ በዛው ካፒታላቹን እያሳደጋቹ ትሄዳላቹ።

@BiyaBTC
@BiyaBTC

Join 👇👇👇👇
http://t.me/ArifBettingBot?start=ui374329121
http://t.me/ArifBettingBot?start=ui374329121

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://www.cryptoglobe.com/latest/2019/07/u-s-congressman-mchenry-calls-bitcoin-an-unstoppable-force-at-libra-hearing/

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ሊብራ፡ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ እና የደህንነት ስጋት
ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ፌስቡክ ወደ ሁለት ቢሊዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ በዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ መተግበሪያዎቹ አማካኝነት ግብይትን እንዲፈጽሙ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል።
ከምዕራባውያን ሃገራት ከወዳጅ ዘመዶች በገንዘብ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገዘንብ የምትቀበለው አፍሪካ፤ ፌስቡክ ይህን መሰል ቀላል እና ቀልጣፍ የገንዘብ ዝውውር ማድረጊያ አማራጭን ማምጣቱ ለአፍሪካ አህጉር ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ተብሏል።
በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት በክሪብቶ-ካረንሲዎች ላይ የላቸው የደህንነት ጥርጣሬ የፌስቡክም ሆነ የሌሎች ዲጅታል ከረንሲዎች ውጤታማነትን ጥያቄ ውስጥ መክታቱ አልቀረም።
ሊብራ ተብሎ በሚጠራው ክሪፕቶ-ከረንሲ 139 ሚሊዮን በአፍሪካ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ግብይት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል።
ባሳለፍነው ዓመት የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች ወዳሉ ሃገራት ገንዘብ መላክ ከየትኛው የዓለማችን ከፍል ብዙ የማስተላለፊያ ወጪን ይጠይቃል። እንደምሳሌም 200 የአሜሪካ ዶላር በዌስተርን ዩኒያን ወይም በመኒግራም ለመላክ 19 ዶላር መላኪያ ገንዘብ ያስከፍላል።
• የደህንነት ስጋት
በሌላ በኩል በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት በክሪብቶ-ካረንሲዎች ላይ የላቸው የደህንነት ጥርጣሬ የፌስቡክም ሆነ የሌሎች ዲጅታል ከረንሲዎች ውጤታማነትን ጥያቄ ውስጥ መክታቱ አልቀረም።
በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የክሪፕቶ-ካረንሲ መጠቀሚያነትን ካገዱ ሃገራት መካከል ናይጄሪያ እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ። ክሪፕቶ-ካረንሲዎችን በመጠቀም የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል።
በዚህም ሕገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ ሃገራት አሉ።
ክሪይፕቶ-ከረንሲን ምንድነው? ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት 'ክሪይፕቶ-ከረንሲን'፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ሲል ይገልጸዋል።
ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል+ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።
ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው።
ሊብራ ከቢትኮይን በምን ይለያል፡ ሊብራ ልክ እንደ ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባለው ሂደት ነው። ልዩነታቸው ሊብራ በሚታወቁ ኩባንያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶ-ከረንሲዎች በመንግሥታት እና በባንኮች አይታተሙም፤ ቁጥጥርም አይደረግባቸውም። የፌስቡኩ ሊብራ ግን በመንግሥታት እና በማዕከላዊ ባንኮች ቁጥጥር ይደረግበታል በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ይኖረዋል።
ሊብራ ከአሁኑ ከቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ ኡበር እና ሰፖቲፋይ ተቀባይነትን አግኝቷል።
የፌስቡክ ዲጂታል ገንዘብ ለአፍሪካውን ሁነኛ የመገበያያ አማራጭን ይዞ ይመጣል የሚሉ በርካቶች እንዳሉ ሁሉ፤ የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎች የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘበ አጠቃቀም ካልተዋጠላቸው በቀላሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ መቻላቸው ስጋትን ፈጥሯል።
የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ አገልግሎቱን ሆነ ብሎ ቢያቋርጥ በፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና በሌሎች መተግበሪያዎች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውር ወዲያው ይቋረጣል። በዚህም ምክንያት ሊብራ ላይ መሞርኮዝ እንደማይቻል ባለሙያዎች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።
• በሃገራችን2የዲጂታል ገንዘብ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል
የድጂታል ግብይቶች ወይም ንግድ በቀጣይ ዓመት በሃገራችን ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በዲጂታል ንግዱ ማንኛውንም ግዥ እና ሽያጭ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ወይም በኢንተርኔት ማከናወን የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡
ከዲጂታል ገንዘቡ ጋር ተያዞ የሚመጡ አወንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች እንደሚኖሩት አያጠያይቅም፡፡
በቀዳሚነት የዲጂታል ገንዘቦች ተግዳሮት ከሆኑት መካከልም የሳይበር ጥቃት ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
ክሪፕቶ ከረንሲዎች በሀገራችን ያለውን የግብይት ስርዓቶች ዘመናዊ እና ወደ ዲጂታል እንዲቀየር ከማድረጉም በተጨማሪ በሸማቹ እና በነጋዴው መካከል ለሚኖረው ተጠቃሚነት የሚኖረው አስተዋፅኦ የላቀ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የዲጂታል ስርዓቱ አማካኝነት የሚፈጠሩ ችግሮችን እና የደህንነት ስጋቶችን መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱም ይታወቃል፡፡
ስርዓቱ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር እና የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ፌስቡክ በሚቀጥለው አመት እተገብረዋለሁ ያለው የዲጂታል ገንዘቡ ሊብራ በሃገራችን ተግባራዊ የመሆኑ እድሉ ሰፊ በመሆኑ የደህንነት ስርዓቱ ማሻሻል እና የኢንተርኔት መሰረተ-ልማቶች መስፋት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡
Š INSA

@BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

😁 የቴክኖሎጂ እውነታዎች

🔰 ዛሬ ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች Internet ይጠቀማሉ ይህም ከዓለም ህዝብ 40 በመቶው ነው።

🔰 በየ57 ደቂቃው ከ570 በላይ አዳዲስ Websites ይፈጠራሉ።

🔰 በየቀኑ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ Google Search ይደረጋል።

🔰 በ2020 ቪዲዮ ከሁሉም ከInternet ትራፊክ 80% ያህሉን ይይዛል።

🔰 40,000 የTwitter ትዊቶች በደቂቃ ይላካሉ በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ማለት ነው።

🔰 በAmerica ከሚደረጉ ከ7 ፍቺዎች መካከል ለአንዱ ፌስቡክ ተጠያቂ ነው።

🔰 በ2020 ከ8.2 ቢሊዮን በላይ መረጃዎች ተሰርቀዋል ወይም Hack ተደርገዋል።

🔰 የመጀመሪያው ኮምፒዩተር ወደ 2.5 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ሲሆን ክብደቱ ወደ 30,000 ኪ.ግ. ይመዝናል።

🔰 NASA ውስጥ የInternet ፍጥነት በሰከንድ 90GB ነው።

🔰 በዓለም ትልቁ ሃርድ ድራይቭ 60TB SSD ነው።

🔰 Bluetooth ኖርዌይን እና ዴንማርክን አንድ ባደረገው ሃራልድ ብሉቱዝ በተባለ ንጉስ ተሰየመ ነው።

🔰 የጉግል መሥራቾች እ.ኤ.አ. በ1999 ጉግል ን በ1 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ፈቃደኞች ቢሆኑም Excite ግን አልተቀበላቸውም። ጉግል አሁን 527 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው።

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

✅ሀከር ምንድን ነዉ?

ሀከር ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን አንድን ኮምፒዉተር ወይም የኮምፒዉተር ኔትወርክ ለራሱ ትርፍ ወይም ለመዝናናት ሰብሮ የሚገባ ነዉ።

    ✅የሀከር አይነቶች | Types of Hackers

ሀከሮች በሶስት ወሳኝ አይነቶች ይከፈላሉ :-

🔸White Hat Hackers :- እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ የመረጃ ብርበራ የማያደርጉ ናቸዉ ስለዚህ ጥሩ ሀከሮች ነዉ የሚባሉት እንዲሁም Security expert በመባል ይታወቃሉ።

🔸Black Hat Hackers :- የነዚህ አይነት ሀከሮች ብዙ ጊዜ crackers ይባላሉ እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ ተግባራትን ያከናዉናሉ ለምሳሌ ልክ እነደ credit card ዘረፋ ባንኮችን ሀክ ማድረግ ወዘተ ክሬዲት ካርድ ዘረፋ ላይ የሚሳተፉ ሀከሮች ካርደር ይባላሉ ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እንቃኛቸዋለን።

🔸Grey Hat Hackers :- ግሬይ ሀት የምንላቸዉ በwhite hat እና በblack hat መካከል የሚገኙ hybrid ናቸዉ ይህም ማለት አንዳንዴ black hat አንዳነዴ ደሞ white hat ሀከርስ ይወላዉላሉ ማለት ነዉ

🔷 የሀከሮች ደረጃ | Hacker Hierarchy

🔹Scriptkiddies :- እነዚህ የሀኪንግ ልምድ የሌላቸዉ ግለሰቦች / ቡድን ግን ሀከር መሆን የሚፈልጉ ናቸዉ ሀክ ለማድረግ የሚጠቀሙትም  ready made tool ወይም የተዘጋጀ ሶፍትዌር ነዉ በዙ ጊዜም ልምድ ስለሌላቸዉ እራሳቸዉን harm ያደርጋሉ አንድ ታዋቂ ጥቅስ አለ "Little knowledge is dangerous" ይህም ብዙ ጊዜ የምናየዉ ችግር ነዉ።

🔹Intermediate hackers :- ከscriptkiddies የበለጠ የሀኪንግ ልምድ እንዲሁም እዉቀት ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉ ግን የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት አይችሉም ቢሆንም ጥሩ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉ።

🔹Professional or Elite hackers :- እነዚህ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት ይችላሉ ስለሆነም የትኛዉም አይነት system ሰብረዉ መግባትና ራሳቸዉን የመደበቅ ልምድ አላቸዉ።

🔴ሀከር ለመሆን ምን ይጠበቅብናል? | What Takes to Become a Hacker?

አስታዉሱ ሀኪንግ በአንድ ምሽት master ምናደርገዉ ነገር አይደለም በጣም ትግስት እና hard work ይፈልጋል ብዙ ጊዜ ከአዳዲስ ሀከሮች የማየው ችግር በትንሽ ስራ ትልቅ ዉጤት ይጠብቃሉ ይሄ ደሞ የማይሆን ነዉ ስለዚህ አንድ የሀኪንግ topic ከያዝን ያን topic በደንብ master እስክናደርዉ አንዲሁም በተግባር እስኪሳካልን ድረስ በደንብ መለማመድ ይጠበቅብናል ይሄን የምናደርግ ከሆነ እራሳችን ላይ ለዉጡን በፍጥነት ማየት እንችላለን። በተለይምhacker ለመሆን ከ 5 በላይ የ programming languages ማወቅ ያስፈልገናል ስለዚህ ከ programming ጀምሩ...

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://telegra.ph/ETH-10-15-2

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

በኣለም ላይ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ምን ይጠበቅብናል?

1 - ከፍ ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ኮርሶችን(advanced placement) መውሰድ
እነዚህን ትምህርቶች መውሰድ እና በአሪፍ ውጤት መጨረስ ወደ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የመግባት እድላችንን ያሰፋል

2 በሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድሮች ላይ መሳተፍ

3 የአይምሮአችንን አቅም የሚፈትኑ ፈተናዎችን መውሰድ ለምሳሌ እንደ SAT, SAT SUBJECT TEST, ACT, ACT REASONING TEST, TOEFL, IELTS
የ SAT መለማመጃ ጥያቄዎች

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ብትኮይን ምንድነው....

ቢት ኮይን (Bitcoin) / ክሪፕቶ ከረንሲ
(crypto currency) ምንድን ነው ?
በዚህ ፅሁፍ ቢት ኮይን ምንድን ነው ? እንዴት ነው ሚሰራው የሚለውን እና ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ጠቅለል ባለ መልኩ ብዙ ቴክኒካል ማብራሪያ ውስጥ ሳልገባ ለመግለፅ እሞክራለው። ከስር ሁለት ሊንኮች አያይዣለው። የመጀመሪያው ስለ ቢትኮይን TechTalk With Solomon የሰራው አሪፍ ፕሮግራም፣ ሁለተኛው ደግሞ ቢትኮይን የተዋወቀበት ጽሁፍ (ቴክኒካል የሆነውን ነገር ማወቅ ለሚፈልግ)
ክሪፕቶከረንሲ በአማርኛ ቀጥታ መተርጎም ቢያስቸግርም (በግድ ይተርጎም ከተባል :) ) በሂሳብ ቀመሮች የተመሳጠረ ዲጂታል ገንዘብ እንደማለት ነው። በወረቀት መልክ የማይታተም በዲጂታል መልክ ብቻ የሚገኝ ገንዘብ ብሎ ማሰብ ይቻላል። ቢት ኮይን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የክሪፕቶከረንሲ አይነት ነው። ቢትኮይን ከክሪፕቶ ከረንሲ አይነቶች አንዱ ሲሆን ሌሎች ብዙ አይነት የክሪፕቶ ከረንሲዎች ከቢትኮይን በኋላ ፣ ትንሽ የሞዴል ለውጥ በማድረግ መጥተዋል። ለምሳሌ ኢቲሪየም ፣ላይትኮይን እና የመሳሰሉት። ከጀርባቸው ያለው ቴክኖሎጂ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው።
በመጀመሪያ ቢትኮይን ምን እንደሚሰራ ለመረዳት, ሃሳቡ ለመጀመሪያ ግዜ ሲቀርብ ምን ችግር ሊፈታ ታስቦ እንደመጣ አያያዞ ማየት ያስፈልጋል። አሁን ባለው የገንዘብ ዝውውር ስርአት ውስጥ የገንዘብ ተቋማት (እንደ ባንክ እና የመሳሰሉት) ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህም እንደ ታማኝ ሶስተኛ ወገን በመሆን ሰዎች እንዲገበያዩ እና ገንዘብ እንዲለዋወጡ ያስችላሉ። “ታማኝ ሶስተኛ ወገን” የሚለው ወሳኝ ቃል ነው በእንግሊዘኛው “Trusted Third Party” የሚባለው ማለት ነው። ታዲያ ቢት ኮይን ሊመልሰው ያሰበው (የመለሰው) ጥያቄው ሰዎች በየትኛውም የአለም ክፍል ላይ ሆነው የኢንተርኔት ኔትዎርክን በመጠቀም ያለ ታማኝ ሶስተኛ ወገን መገበያየት ወይንም ገንዘብ መለዋወጥ ይችላሉ ? የሚለውን ነው። በሌላ አገላለጽ ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሳይተማመኑ ፣ ታማኝ ሶስተኛ ወገን በማሃል ሳያስገቡ ፣ የሂሳብ ቀመሮች ላይ ብቻ መሰረት አድርገው መገበያየት ወይንም ገንዘብ መለዋወጥ ይችላሉን ?
ታማኝ ሶስተኛ ወገን ማስገባቱ ጉዳቱ ምንድን ነው ? የሚለውን ጥያቄ ካነሳን ሁለቱም ወገኖች የሚያምኑት አንድ አካል ብቻ ካለ ይህ አካል በሆነ ምክንያት መስራት ያቆመ ጊዜ ሙሉ የገንዘብ ዝውውሩ ቆመ ማለት ነው። በተጨማሪም ይህ ታማኝ ሶስተኛ ወገን ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ስለሚያስፈለገው የገንዝብ ዝውውሩን ውድ ያደርገዋል ( ቢያንስ በ ጽንሰ ሃሳብ ደረጃ)። የእነዚህ ሶስተኛ ወገኖችን ስራ በኮምፒውተር ፕሮግራም መተካት ከተቻለ ከነሱ ጋር ተያያዥነት ያለቸውን ችግሮች ማስወገድ ይቻላል ማለት ነው።

የባንክን መሰረታዊ ስራ በጣም አቅልለን እንመልከት። በመጀመሪያ የሰዎችን አካውንት እና ያላቸውን የገንዘብ መጠን ይመዘግባሉ። በመቀጠል ከ አንድ አካውንት ብር ሲወጣ ከዛ ላይ ይቀንሳሉ፣ ሲመጣ ደግሞ ይጨምራሉ። አንድ አካውንት ካለው ገንዘብ መጠን በላይ ለማውጣት ወይንም ወደሌላ ሰው ለማስተላለፍ ከጠየቀ ባንክ ቤቱ ይከለክላል። (ይሄ በጣም መሰረታዊ የሆነው ነገር ሲሆን በትግበራ ላይ ከዚህ በበለጠ ትንሽ የተወሳሰበ ነው)። ስለዚህ አንድ አካውንት በመጀምሪያ ያለውን የገንዘብ መጠን ካወቅን እና የሚሰራውን የገንዘብ ዝውውር መመዝገብ ከቻልን መሰረታዊ የሆነውን የባንክ ስራ በኮምፒውተር ፕሮግራም መተካት ይቻላል ማለት ነው። ወደፊት ለሚመጡ የገንዘብ ዝውውር ጥያቄዎች እስከዛሬ የመዘገብነውን በማየት አካውንቱ በቂ ገንዘብ እንዳለው ማረጋገጥና ከሌለው ደግሞ ዝውውሩን መከልከል ይቻላል።
ታዲያ ይህንን የሚሰራ የኮምፒውተር ፕሮግራም በማዕከላዊ (centralized) አስተዳደር እንዲተዳደር ማድረግ ወደ ተነሳንበት ችግር ይመልሰናል። ማለትም ፕሮግራሙ በማዕከላዊ አስተዳደር የሚተዳደር ከሆነ ይህ አስተዳደር በወደቀ ጊዜ ሙሉ የገንዘብ ዝውውር ስርአቱ አብሮ ይወድቃል ማለት ነው። ስለዚህ ፕሮግራሙን ያልተማከለ ወይንም በትንንሽ የተከፋፈለና በተለያየ ቦታ ላይ የሚገኝ (decentrlized / distributed ) አስተዳደር ማድረግ ያስፈልጋል። ቢትኮይን የሚያደርገውም ይህንኑ ነው። ሰዎች ያላቸውን የገንዘብ መጠን የተመዘገበበትን መዝገብ በ አለም ላይ ለሚገኝ፣ መዝገቡን ማስተዳደር ለሚፈልግ ሰው ይበትናል። ሁሉም አስተዳዳሪዎች በኢንተርኔት ኔትዎርክ የተገናኙ ናቸው። ታዲያ ማንኛውም ሰው ይህንን መዝገብ መቆጣጠር ወይንም ማስተዳደር ሲፈልግ የሚከተለው ህግ አለ። ይህንን ህግ እስከተከተለ ድረስ ማንም ሰው አስተዳደሩ ላይ መሳተፍ ይችላል። ለሚሳተፉ ሰዎች ደግሞ ማበረታቻ ክፍያ ይደረግላቸዋል። በዚህ መሰረት መአከላዊውን አስተዳደር መበተን ወይንም ያልተማከል ማድረግ ይቻላል። በዚህ ስርአት ውስጥ አንድ ሰው ወይንም የተወሰኑ ሰዎች ህጉን ባያከብሩ ወይንም በሆነ ምክንያት መስራት ቢያቆሙ ሲስተሙ አይፈርስም። ይህ ሲስተም የሚፈርሰው ከ 50% (ሀምሳ ፐርሰንት) በላይ አስተዳዳሪዎች ህጉን ሳያከብሩ ሲቀሩ ወይንም መስራት ሲያቆሙ ብቻ ነው።
በሲስተሙ ውስጥ ሁሉም አስተዳዳሪ የራሱ የሆነ የተለየ ፊርማ ይኖረዋል። ይህ ፊርማ ሁለት ልዩ ባህሪያት አሉት። የመጀመሪያው ይህንን ፊርማ አስመስሎ ለማጭበረበር አይቻልም (ወይንም በጣም ከባድ ነው)። ሁለተኛ አንድ ሰው ፈርሞ የላከውን መረጃ በርግጥ ከሱ እንደመጣ ማረጋገጥ በጣም ቀላል ነው። ልብ በሉ ይህ የሚደረገው የተለያዩ የሂሳብ ቀመሮችን በመጠቀም ብቻ ነው። በተጨማሪም በዚህ መዝገብ ላይ የሚገኝ ማንኛውም የአካውንት ቁጥር በሚስጥር ኮድ የተቆለፈ ነው። የሚስጥር ኮዱ የሚኖረው የአካውንቱ ባለቤት ጋር ብቻ ነው። ሌላ ሰው የአካውንቱን ቁጥር ቢመለከት የሚያገኘው በዘፈቀደ የተቀመጡ ቁጥሮች እና ፊደሎች ነው። እነዚህን ፊደሎች በማየት ብቻ ደግሞ የማን አካውንት እንደሆነ ማወቅ አይቻልም።
ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ መዝገቡን እንዴት ሁሉም ቦታ ላይ አንድ አይነት ማድረግ ይቻላል የሚለው ነው። ማለትም አንድ አካውንት የሆነ መዝገብ ላይ 50 ብር ሌላ መዝገብ ላይ ደግሞ 100 ብር አለው ተብሎ መመዝገብ የለበትም። ሁሉም ሰዎች የያዙት መዝገብ አንድ አይነት መሆን አለበት። ይህንን ለመቆጣጠር የቢትኮይን ህግ የሚከተለውን ይደነግ ጋል። ማንኛውም አስተዳዳሪ መዝገቡ ላይ መጻፍ ሲፈልግ መመለስ ያለበት ከባድ (ብዙ የኮምፒውተር ጉልበት የሚፈልግ) የሂሳብ ጥያቄ ይኖራል። ይህንን የሂሳብ ጥያቄ ቀድሞ የመለሰ አስተዳዳሪ የሚከተሉትን መረጃዎች ወደ ሌሎቹ አስተዳዳሪዎች ይልካል። ከዚህ በፊት ለመጨረሻ ግዜ መዝገቡ ላይ የጻፈውን ፣ አሁን ወደ መዝገቡ መጻፍ የፈለገውን እና ያገኘውን የጥያቄ መልስ በዲጂታል ፊርማው ፈርሞ ወደ ሌሎቹ ሁሉም አስተዳዳሪዎች ይልካል። ሌሎቹ አስተዳዳሪዎች ተቀብለው መጨረሻ ላይ የተጻፈው ራሳቸው ከጻፉት ጋር እንደሚመሳሰል ፣ የጥያቄው መልስ ትክክል መሆኑን እና መዝገቡ ላይ ሊጻፍ የተባለው ትክክል መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ መስማማታቸውን ይገልጻሉ። የተሳሳተ ነገር ካለው ደግሞ አለመስማማታቸውን ያሳውቃሉ። ከ 50% (ሀምሳ ፐርሰንት) በላይ አስተዳዳሪዎች ከተስማሙ ሁሉም ራሳቸው ጋር ያለው መዝገብ ላይ የተላከላቸውን ይመዘግባሉ።

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

3.1 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቪኤልሲ ፕሌየር ለጥቃት ተጋልጧል
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3.1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የሚታመነው የቪኤልሲ ማጫወቻ 'VLC player' አደገኛ የሚባል የደህንነት ክፍተት እንዳለበት የጀርመን የብሄራዊ የሳይበር አደጋ ምላሽ መስጫ ማእከል(ሰርት) ይፋ አደርጓል፡፡
ማንኛውም አካል በነጻ ከኢንተርኔት ላይ አውርዶ መጠቀም የሚችለው ሶፍትዌር እስካሁን የክፍተት መሙያ እንዳልተለቀቀለት ተጠቁሟል፡፡
በቪኤልሲ ላይ የተፈጠረው የሶፍትዌር ክፍተት አደገኝነት ደረጃው በከፍተኛ የሚመደብ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ህገ-ወጦች ክፍተቱን በመጠቀም በርቀት ሶፍትዌሩን መቆጣር የሚያስችላቸው ሲሆን ክፍተቱ የአገልግሎት መስተጓጎል denial-of-service፣ ያለፍቃድ መረጃዎችን መውሰድ እንዲሁም ያለተጠቃሚው ፍቃድ ፋይሎችን እንዲቆጣጠሩ ያደርጋል ሲል የጀርመን ሰርት ጠቁሟል፡፡
ለተጋላጭነት የተዳረጉት የቪኤልሲ ምርቶች እስከ ቅርብ ጊዜው 'VLC media playe'r እትሙን ጨምሮ በሁሉም ምርቶች ላይ የተከሰተ መሆኑም ታውቋል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ የቪኤልሲ ማጫወቻው ላይ በተከሰተው ክፍተት ሳቢያ የደረሰ ጥቃት ይፋ አልሆነም ሲል ዊ ሊቭ ሴኪዩሪቲ አስነብቧል፡፡
ŠINSA

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የማጭበርበር ስራ እየሰሩ ላሉ ግለሰቦች ግንዛቤ ልስጣቹ~

የተለያየ አፕልኬሽን App የሚመስል ሰርተው እሱን በምትጭኑት ጊዜ የሞላቹትን ካርድ ወደ ራሳቸው ይወስዱባችዋል እና ከማንኛውም ጉሩፕ (Group) ላይ የሚላክ አፕ App ባታወርዱ ይመከራል። ከቻናሎች ላይ ባላፊነት የሚሰሩ ቻናሎች ላይ ብቻ በማውረድ ወይን ከPlay store ውስጥ ማውረድ ነው ያለባቹ።
~~~~~~~~~~~
የሚሰሩት አፕ ሚመስለው ውስጡ
👉 ( *806*ስልካቸው*ሚወስዱባቹን ብር# )
👆👆ይሄንን አፕ App አስመስለው ሰርተው ከዛ አውርዳቹት ስትከፍቱት የሚፈልጉትን ብር እናንተ ከሞላቹት ካርድ ላይ ወደ ራሳቸው ያስተላልፋሉ።

።።።።።።።።

ሌላ ደግሞ በተሞላ በ25 ወይም ከዛ በላይ በሆነ ካርድ ላይ የ5 ብር ካርድ ቁጥር በመለጠፍ ብራቹን ሚበሉ ስላሉ ካርድ ተረካቢዎችም ሆናቹ ካርድ ሞሊዎች አይታችሁ እንድትገዙ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን ።

==============:
ሼር በማድረግ ላላወቁ ድረሱላቸው
==============

@BiyaBTC
@BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

Very Interesting & meaningful msg to share: @ocitsc Share😘 Share
If:
A B C D E F G H I J K LM N O P Q R S T U V W X Y Z
is equal to:
1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26
Then,
.
H+A+R+D+W+O+R+K ;
8+1+18+4+23+15+18+11=98%
.
K+N+O+W+L+E+D+G+E ;
11+14+15+23+12+5+4+7+5=96%
.
L+O+V+E;
12+15+22+5 = 54%
.
L+U+C+K ;
12+21+3+11 = 47%
.
None of them makes 100%. Then what makes 100%?
.
Is it Money? NO!
M+O+N+E+Y= 13+15+14+5+25=72%
.
Leadership? NO!
.
L+E+A+D+E+R+S+H+I+P=
12+5+1+4+5+18+19+8+9+16=97%
.
Every problem has a solution, only if we perhaps change our "ATTITUDE"...
.
A+T+T+I+T+U+D+E ;
1+20+20+9+20+21+4+5 = 100%
.
It is therefore OUR ATTITUDE towards Life and Work that makes OUR Life 100% Successful.
.
Amazing mathematics
..
▪️If you agree Share at least for 5 friends,

@BiyaBTC
@BiyaBTC
@BiyaBTC

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

#update ቻይና እንደ ቢትኮይን ያለ ዲጂታል የኢንተርኔት የመገበያያ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶከረንሲ ስራ ላይ ልታውል መሆኗን አስታወቀች፡፡ ለ5 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት መቆቱንና ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉን ነው የሀገሪቱ ብሔረዊ ባንኩ ያስታወቀው፡፡ ስልክን በመጠቀም ያላንዳች ባንክ ገንዘብ ዲጂታል በሆነ መልኩ ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለው ክሪፕቶከረንሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ትኩረት እያገኘ መጥቷል፡፡

ምንጭ፡-ኢንዲፔንደንት/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ያስታወቁት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተመራ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን በቻይና በተዘጋጀላቸው የኢኮኖሚ አውደ ጥናት ላይ በተሳተፉበት ወቅት ነው፡፡

ሚኒስትሩ በቻይና ግዙፉ የባሉበት ነጋጅ (ኦን ላይን ግብይት ፈፃሚ) ከሆነው አሊባባ ቡድን ጃክ ማ ጋርም ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በዘርፉ ልምድ ያለው አሊባባ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው የጠየቁ ሲሆን የአሊባባ ቡድንም ልምዳቸውን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ያሉት ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገውታል ብለዋል፡፡ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ልኡካን ቡድኑ የአሊበባን ዋና ቢሮ ጎብኝቷል፡፡

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

አማረኛን ጨምሮ በ42 የአለም ቋንቋዎች የአንድሮይድ ስልክ ቫይረስ እየተሰራጨ መሆኑ ተጠቆመ
፨፨@BiyaBTC ፨፨
፨፨@BiyaBTC ፨፨
የአንድሮይድ ስልኮች ቫይረሱ አማረኛ ቋንቋን ጨምሮ በ42 የዓለም ቋንቋዎች አጥፊ ሶፍትዌሮች በአጭር የጽሁፍ መልእክቶች (SMS) እየተሰራጭ ይገኛል፡፡
የደህንነት ምርቶች አቅራቢ ተቋም ኢሴት (ESET) ተመራማሪዎች ይፋ ባደረጉት መረጃ የራንሰምዌር ጥቃቱ አጥፊ ሊንኮች እና አጭር የጽሁፍ መልእክቶችን በመጠቀም ተጠቃሚዎችን ለአደጋ እንደሚዳርግ ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ መልክ የተከፈተው የአንድሮይድ ስልኮችን ያነጣጣረው የሳይበር ጥቃት መረጃዎችን በመቆለፍ ክፍያ የመጠየቅ እና ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተግባር "ransomware” መሆኑም ታውቋል፡፡
የሳይበር ጥቃቶቹ እየተፈጸሙ ያሉትም የተጠቃሚውን ስነ-ልቦና እና የቀደሙ ትርክቶችን በማጥናት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት "ማህበራዊ ምህንድስናአካላትም በመምረጥ እና ደካማ ጎንን በመለየት ነው፡፡
የሚላኩት የአጭር የጽሁፍ መልእክቶች በተጠቃሚው ስልክ ውስጥ ያሉ አብዛኛውን መረጃዎች በመመስጠር ለመረጃዎቹ ማስከፈቻ ገንዘብ እንደሚጠይቁ ተጠቁሟል፡፡
መረጃው የተቆለፈባቸው አካላትም ከ94 እስከ 188 የአሜሪካ ዶላር ለመረጃው ማስከፈቻ እንደሚጠየቁ ታውቋል፡፡
የአጭር የጽሁፍ መልእክቶች በ42 የተለያዩ ቋንቋዎች አማካኝነት የሚሰራጩ ሲሆን አማረኛ ቋንቋም ለጥቃት ኢላማነት ከተመረጡ ቋንቋዎች መካከል ይገኝበታል፡፡
ችግሩን ለመከላከል የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች ለስልኮቻቸው የሚጠቀሙትን መተግበሪያዎች ከጉግል የአፕሊኬሽን ስቶር ማውረድ (downloads) እንደሚገባቸው የደህንነት ምርት አቅራቢ ተቋሙ መክሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ተጠቃሚዎች በየጊዜው የሚቀርበብላቸውን የአፕልኬሽን ማሻሻያ (up-to-date) ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ እና የሚቀርቡ የመተግበሪያ ዳውንሎድ አድርጉ ግብዣዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
ŠINSA

፨፨ @BiyaBTC ፨፨
፨፨ @BiyaBTC ፨፨

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://news.bitcoin.com/how-governments-steal-your-money-and-conceal-it-through-inflation/

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

🔰Bitcoin is the first decentralised peer to peer cryptocurrency invented by Satoshi Nakamoto, a software developer in 2008 and released it open public in 2009, and this is when the first bitcoin transaction took place.

🔰It's independent on government or central authority or banks. No one has control over bitcoin.

🔰It's real money for the people not government .

🔰Since 2009, there has been increasingly mass adoption of bitcoin as the fastest, easiest way at a very low cost transaction charges compared to other forms of money transfers like western union, money gram, xpress money etc.

🔰Bitcoin protects individuals from the devastating institutionalised crimes of the state by allowing them to avoid central banks and retain the private data that constitutes power over their lives.

🔰Satoshi knew that banks and fiat were massive failure or far worse. Under the guise of promoting financial stability and protection, they looted wealth of individuals through mechanism such as Inflation and transfered it to those in authority.

🔰Equally to lose one's life savings through inflation, confiscation, mismanagement and other criminal acts by central banks can be devastating. Restitution maybe more easily made after all a dollar is dollar but the return of funds is often unlikely.

LET'S ADOPT BITCOIN,
SAVE IN BITCOIN,
EARN BITCOIN
ACCEPT BITCOIN.

Happy earnings
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸
Xtradechain Global Team
💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

https://m.youtube.com/watch?v=2vu4tY88GHk

Читать полностью…

How to Earn Online🤔?

🤔ስልኮን ለምን አላማ ይጠቀሙበታል?

👤ቻት ለመደራረግ?

👨‍💻የቀኑን ወሬ ለማወቅ?
ወይስ አንድ ተዋቂ ሰው የሚለቀውን ፎቶ ላይክ ለማድረግ?

🏦ከዚህ የሚበልጥ በስልኮ online ሀብት ማካበት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

✍ቢዝነሱ ምንድነው?
✍እንዴት ነው የሚሰራው?
✍የቀን የሳምንት እና የወር ገቢስ ምን ያህል ነው?

✍Blockchain technology
✍Crypto Currency
✍Bitcoin
✍forex(foreign exchange)
🚨 Ft

ቤትዎ ቁጭ ብለው ስልኮን ወይም ኮምፒውተርዎን ብቻ በመጠቀም አሴት(ሀብት) ይገንቡ።

በ አለም ላይ ከሚንቀሳቀሰው ትሪሊዮን ዶላር ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ይሁኑ!!!!
የገንዘብ ነፃነትዎን ያግኙ!!!
ህልምዎን እውን ያድርጉ!!



በዚህ ምርጥ ና አስገራሚ የዓለማችን ቢዝነስ
For more information:
👇👇👇👇👇
@BitCoin_in_Ethiopia20
==================

join 👇👇
@BiyaBTC

🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀
💰💰💰💰💰💰💰🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆✈✈✈✈🚔🚔🚔🚔🚔🚍🚍

Читать полностью…
Subscribe to a channel