tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1583422

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#WorldCup በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አርጀቲና እና ስፔን ለፍጻሜ ደረሱ።

ከእንግሊዝ ጋር ለዋንጫ ለማለፍ የተጫወተችው አርጀንቲና እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ 0 ብትመራም ድራማዊ በሆነ መንገድ 2 ጎል አግብታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ፍጻሜው ፍልሚያ አልፋለች።

ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ተፋላሚ የሆነችው አርጀንቲና የፊታችን እሁድ ምሽት 4:00 ፈረንሳይን ጥላ ወደ ፍፃሜ ካለፈችው ስፔን ጋር ትጫወታለች።

ቲክቫህ ስፖርት
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethsport

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ተጨማሪ የነዳጅ መስመር ሊዘጋ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች።

አሜሪካ በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተጨማሪ ድብደባ ካካሄደች በኋላ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይና በቀጣናው የሚገኙ ተጨማሪ የነዳጅና የጋዝ መላኪያ መስመሮችን ሊዘጉ እንደሚችል አስጠነቀቀች።

የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ በድሮኖች፣  በአየር እና በባሕር ኃይል በመታገዝ የኢራንን የባሕር መከላከያዎችና የክሩዝ ሚሳዔል ማከማቻዎች ላይ ድብደባ እንደፈጸመ ገልጿል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ዳግም የተባባሰው ጦርነት በሆርሙዝ ሰርጥ የነዳጅ ንግድን በማስተጓጎል የዓለም የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል።

በሌላ በኩል፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወደ ድርድር ካልተመለሰች ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃቶች እንደሚከተሉ አስጠንቅቀዋል።

ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የእርስ በእርስ ጦርነት ከውጭ ጠላት ጋር ከሚደረግ ጦርነት የበለጠ ጎጂ ነው " - ኦባሳንጆ

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ በተካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር።

" በናይጀሪያ እና በኢትዮጵያ መካከል መመሳሰሎች አሉ " ያሉት ኦባሳንጆ " ይሄውም የእርስ በእርስ ቀውስ ችግር አለብን " ብለዋል።

ኦባሳንጆ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ከውጭ ጠላት ጋር ከሚደረግ ጦርነት የበለጠ ጎጂ መሆኑን በማንሳት፣ የናይጄሪያን የጦርነት ታሪክ በማስታወስ ለኢትዮጵያ ሀገራዊው የምክክር ሂደት ያለውን አስፈላጊነት አብራርተዋል።

ሌላው በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በበኩላቸው፣ የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት የሚያግዝ መተማመኛ መሆኑን ገልጸው፣ አፍሪካ ህብረት ሂደቱን እንደሚደግፍ ፤ ሰላምን ለማስረጽ አብሮ እንደሚቆም ተናግረዋል።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁም ልዩነቶች መኖራቸው ተፈጥሯዊ መሆኑን ጠቅሰው፣ በታሪክ፣ በሀብት ክፍፍልና በሌሎች ጉዳዮች የሚፈጠሩ ልዩነቶች በኃይል ሳይሆን በውይይትና በንግግር መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢትዮጵያ የቀይ ባህር መዳረሻዋን ያጣችው በውስጥ ድክመት እንጂ በጠላት ብርታት አይደለም " - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው የብሔራዊ ምክክር ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ለሺህ ዓመታት በባለቤትነት ያስተዳደረችውን የቀይ ባህር በር ያጣችው በጠላት ብርታት ሳይሆን በውስጥ ድክመትና በፖለቲካዊ ሸፍጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ " ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል ያደፈጡ የሚነቁ የዘመናት ያልተቋረጠ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ " በማለት የኢትዮጵያን ታሪክ ከጉንደት እስከ ጉራ፣ ከአድዋ እስከ ማይጨው፣ ከካራማራ እስከ ባድመ ሲፈተሽ፣ ኢትዮጵያ ስትገነባ የሚያደፍጡና ስትጨቃጨቅ እድል ጊዜ ጠብቀው ጣልቃ ሽብልቅ በመግባት መሻቶቿን እንዳትከውን የሚያደርጉ ኃይሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

" በዚህ የሽብልቅ ጉዞ፣ በእኛ ስንፍና በነሱ ጊዜ በመጠቀም፣ የጥንቱን ታሪክ ብንተው፣ በቅርቡ ቀይ ባህርን ያጣንበት አጋጣሚ የዚህ እኩይ ታሪካዊ ክስተት አንዱ መገለጫ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ቀይ ባህር ጉዳይ በተለይ ሲናገሩ፣ " ኢትዮጵያ ለሺ ዘመናት ያስተዳደረችውን፣ በባለቤትነት የያዘችውን፣ ለራሷም ለከባቢውም መጠቀሚያ ያኖረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠ መንግስት፣ ያልተወያየ መንግስት በሸፍጥ ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ እንዲያደርግ ያደረገበት ዋናው ምክንያት በውስጥ ያለን ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻትና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ፣ ስላለ፣ ስለሚኖር አይደለም " ብለዋል።

ሀገሪቱ ስትዳከም ጣልቃ ስለሚገቡ ኃይሎችም ሲናገሩ፣ " ሁልጊዜም ጥቅማችን አሳልፈን የምንሰጠው ስንገነባ ያልነበሩ፣ ስንሿኮት ስንጣላ የሚያንዣቡ አሞሮች ስላሉ ነው " ብለዋል።

" አሞራ ሲታረድ ይመጣል፤ ሲገነባ የለም፤ ህዳሴን ስንገነባ እኛ ጋር አልነበሩም፣ ከተሞቻችን ሲያሸበርቁ እኛ ጋር ያልነበሩ፣ ልማት ስንጀምር እኛ ጋር ያልነበሩ፣ እርስ በርስ ስንጨቃጨቅ ግን ከየት መጡ ሳይባሉ ጥይት ሲያቀብሉ፣ ብር ሲያቀብሉ፣ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ሲያደርጉ ይታያል" ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ " እጅግ የተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ነገር ልብ እንዲል እፈልጋለሁ " በማለት፣ " ምንም ጉዳይ በውስጥ ቢያከራክረን፣ ምንም ጉዳይ በውስጥ ቢያጨቃጭቀን፣ እንዲህ ባለው መድረክ መነጋገር፣ መወያየት፣ መፍታት ስለምንችል፣ ለሌሎች ኃይሎች ጥቅም የኢትዮጵያን መሻትና ብሔራዊ ፍላጎት አሳልፈን የምንሰጥ፣ በታሪክ ውስጥ እንክርዳድ ሆነን የምንታይ ዜጎች ላለመሆን እያንዳንዳችን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ላይ ለሚደራደሩ የውጭ ኃይሎችም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

" በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣቡ አሞሮች ያለኝ መልዕክት፤ ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛ ነን፤ የቅርጫውን ባለቤት የምንወስን እኛ ነን " ብለዋል።

" የተረፈንን የማንፈልገውን ካልሆነ በቀር፣ የትኛውም አሞራ በጉልበት ከየትኛውም ቅርጫ ላይ አንዲት ኪሎ ስጋ መውሰድ አይችልም። ስንፈልግ ስንወድ ለማጋራት ዝግጁ ነን፤ ከፈቃዳችን ውጭ ግን ለሺህ ዓመታት የኖረችና የጸናች ኢትዮጵያ አሁን ባለው ፕሮፖጋንዳ ትዘናጋለች፣ ጥቅሟን አሳልፋ ትሰጣለች ብሎ መገመት ከንቱ ምኞት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

" ከወዲው የእኛን ታሪክ በትክክለኛው መንገድ አገላብጣችሁና አውቃችሁ፣ ቀልባችሁን በመመለስ ለጋራ ጥቅም በጋራ እንድንሰራ ጥሪዬን ላቀርብላችሁ እፈልጋለሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሞባይል ስልክ ለመዝረፍ የተፈጸመ የግድያ ወንጀል

ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 7:00 ሠዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ አቦ መሻገሪያ ድልድይ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው የግድያ ወንጀሉ የተፈፀመው።

በወቅቱ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሠብ ከሳሪስ አቦ ወደ ኮዬ መሄጃ በሚገኝ መንገድ ድልድይ ስር ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፎ ተገኘ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው መግደል ምርመራ፣ የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድኑ በመቀናጀት የሟችን ማንነት ለማወቅ እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመለየት ጥረት ማድረግ ይጀምራል።

ወንጀሉ በተፈፀመ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሟችን ማንነትና እና ወንጀሉን በመፈፀም የጠረጠራቸውን ፦
- እንዳለ ተሰማ፣
- ኤርሚያስ አሰፋ፣
- ያብስራ እንዳለ፣
- ዘካሪያስ ለማ፣
- ናትናኤል ግርማ፣
- ተመስገን ተስፋዬ፣
- ብሩክ ኤርሚያስ፣
- ኢዮብ ጌታቸው፣
- ላምሮት አረጋኸኝ፣
- ኤልሻዳይ ዳዊት እና ኤዶሚያስ ወንድወሰን የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ባደረገው ምርመራ ሟች ዘይኑ ፈድሉ በመንገድ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አንገቱን በመያዝና ደረቱን በጩቤ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ይዞት የነበረውን ሳምሰንግ ስልክ ወስደዋል።

የሟችን አስክሬን ኤርሚያስ አሠፋ በተባለው ግለሠብ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B 83677 አ/አ ቪትስ ኮምፓክት ተሽከርካሪ ኮፈን ውስጥ በመክተት ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ደግሞ ኮድ 3-71724 አ/አ በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ በመሆን ተከታትለው በመሄድ  የሟችን አስክሬን ድልድይ ስር ጥለውት መሄዳቸውን በምርመራ ወቅት ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በራሳቸው ፍላጎት ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙ መርተው ማሳየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገ ምርመራ የማስፋት ስራ ለወንጀለ መፈፀሚያ የሚጠቀሙበት ፦
👉 2 ጩቤ፣
👉 3 ሽጉጥ መያዙን ፖሊስ አመልክቷል።

የሟች ዘይኑ ፈድሉ ቤተሰቦች፣ በወንድማቸው ህልፈት እጅጉን ማዘናቸውን ገልጸው ፖሊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ይገኛሉ።

ዛሬ ጥዋት ላይ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የህወሓት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አንድ ቀን በመቐለ የሚያሳልፉት አምባሳደሩ ቀጠናዊ የፀጥታ እና ሰላም ፣ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም ሀገራቸው አሜሪካ በህወሓት አመራሮች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏ የሚዘነጋ አይደለም።

ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሂጅራ ባንክ 1.9 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ !

ሥራ ከጀመረ አምስት አመታት ሊሞሉት ጥቂት ወራት ብቻ የቀሩት እና ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ሂጅራ ባንክ በ2025/26 በጀት ዓመት1.9 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ እና 158 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስገባት መቻሉን አስታውቋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢና ትርፍ፣ ተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰብ፣ በካፒታል መጠን፣ በአጠቃላይ ሃብት፣ በውጭ ምንዛሬ አቅርቦት፣ በዲጂታል ፋይናንሲንግ፣ በደንበኛ ቁጥር፣ በቅርንጫፍ ብዛት ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

ሂጅራ ባንክ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ ሐምሌ አንድ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በዘርፉ የነበረውን የመሪነት ሚና ማሰቀጠል መቻሉን አስታውቋል፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያስመዘገባቸው ታላላቅ ስኬቶች ፡-

📌 አጠቃላይ ገቢ ፦ ባንኩ ከተመሠረተ ጀምሮ ባለፉት አራት ዓመታት ካስመዘገበው አጠቃላይ ድምር ገቢ (2 ነጥብ 965 ቢሊየን ብር) በመብለጥ የዘንድሮው ዓመታዊ ገቢው ብር 3 ነጥብ 55 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ከነበረው በጀት ዓመት አንጻር የ97 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

📌 ጠቅላላ ትርፍ፦ ካለፉት አራት ዓመታት አጠቃላይ የትርፍ ድምር (820 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር) ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ብልጫ በማሳየት 1 ነጥብ 9 ቢሊየን በማድረስ ባንኩ ካገኘው ትርፍ አንጻር በ132 በመቶ የላቀ እድገት አስመዝግቧል፡፡

📌 የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን፦ ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረው 14 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በ115 በመቶ በማሳደግ ብር 31 ነጥብ 45 ቢሊየን ደርሷል።

📌 ተቀማጭ ገንዘብ፦ ባለፈው በጀት ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት 11 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር በመነሳት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በ101 በመቶ በማሳደግ ብር 24 ቢሊየን ማድረስ ተችሏል።

📌 ጠቅላላ ካፒታል፦ ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረበት ብር 2 ነጥብ 42 ቢሊየን በ202 በመቶ (ከ2 እጥፍ በላይ) በማሳደግ ብር 7 ነጥብ 45 ቢሊየን አድርሷል።

📌 የውጭ ምንዛሬ ግኝት፦ ባንኩ ባለፉት አራት ዓመታት በድምሩ ካንቀሳቀሰው የውጭ ምንዛሬ መጠን የ187 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት በማሳየት በበጀት ዓመቱ 158 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ችሏል፡፡

📌 ለደንበኞች የቀረበ ጠቅላላ የፋይናንስ መጠን፦ ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረው የብር 7 ነጥብ 2 ቢሊየን የፋይናንስ አቅርቦት በ133 በመቶ በማሳደግ በበጀት ዓመቱ ብር 16 ነጥብ 78 ቢሊየን በላይ ፋይናንስ ያደረገ ሲሆን፤ ይህም

▪️በሙዳረባህ ብር 1 ነጥብ 33 ቢሊየን (7 ነጥብ 93 በመቶ) እንዲሁም
▪️በቀርደል ሐሰን (ነፃ ብድር) ብር 341 ነጥብ 72 ሚሊየን (2 ነጥብ 03 በመቶ) ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቧል፡

📌 የቅርንጫፍ ብዛት፦ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ውስጥ 41 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት 170 አድርሷል።
9. ዲጂታል ፋይናንሲንግ፡- 3,871 ለሚደርሱ በአነስተኛና መካከለኛ ሥራ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች ያለ ማስያዣ ብር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን የኢሙራበሃ ፋይናንሲንግ ማቅረብ ችሏል፡፡

📌 ዲጂታል ባንኪንግ፡- ባንኩ በበጀት ዓመቱ የዲጂታል ባንኪንግ አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር 2 ነጥብ 24 ሚሊየን ማድረስ የቻለ ሲሆን አጠቃላይ በዲጅታል ባንኪንግ የገንዘብ ዝውውር መጠኑ ብር 41 ነጥብ 72 ቢሊየን (የ86% ዕድገት) እንዲሁም የግብይት መጠኑ 261 ሺህ 982 (የ519 በመቶ ዕድገት) ማድረስ ችሏል፡

📌 ዘካና ወቅፍ፡- ባንኩ በሀገራችን የፋይናንስ ተቋማት ታሪክ ፈር ቀዳጅ በመሆን በበጀት ዓመቱ ከአጠቃላይ ትርፉ ላይ ተቋማዊ ዘካ ብር 8 ሚሊየን እንዲሁም ለወቅፍ ብር 2 ሚሊየን በማውጣት ሸሪዓዊ ግዴታውን መወጣት ችሏል፡፡

📌 ያለትርፍ የቀረበ የፋይናንስ አገልግሎት፡- ባንካችን ሸሪዓን መሰረት በማደረግ የሚሰራ ባንክ እንደመሆኑ መጠን የመቃሲድ አል ሸሪዓ መርህን የቢዝነሱ ተልዕኮ አካል በማድረግ ዘላቂነትና ኃላፊነትን መሰረት ያደረገ ኢንቨስትመንት ላይ ያለ ምንም ትርፍ በቀርድ አል-ሐሰን (Benevolent Loan ) ከፋይናንሲንግ ፖርትፎሊዮው ብር 341 ነጥብ 72 ሚሊየን (2.03 በመቶ) የሚደርስ የፋይናንሲንግ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

📌 ሐረመይን አገልግሎት፡- ሂጅራ ባንክ ሐጅ የማድረግ ታላቅ ምኞት ኖሯቸው የገንዘብ እጥረት ለገጠማቸው ምዕመናን ልዩ የሐረመይን አገልግሎት በማዘጋጀት፣ ለጉዞው የሚያስፈልገውን 50 በመቶ ወጪ ያለምንም ትርፍ (በቀርድ አል-ሐሰን) በብድር መልክ ማቅረብ ችሏል።
በዚህም ልዩ ዕድል እስከተጠናቀቀው በጀት ዓመት ድረስ 35 ምዕመናን የዕድሜ ዘመን ህልማቸውን እውን በማድረግ የሐጅ ሥነ-ሥርዓታቸውን በስኬት እንዲፈጽሙ አስችሏል።

ባንኩ እነዚህ ስኬቶች አውን ይሆኑ ዘንድ ድጋፍ ላደረጉ የአክሲዮን ባለቤቶች፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትና በየእርከኑ ያለው የመጅሊስ መዋቅር፣ የባንካችን የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት፣ መርጠውና አምነው አብረውት ለቆዩ ክቡራን ደንበኞቹ እንዲሁም በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሲሰሩ ለነበሩ የዴሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ አመራሮችና ውድ ሠራተኞቹ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ሂጅራ ባንክ ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ!!!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ነገ ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ይጀመራል። ጉባኤው 30 ቀናት (አንድ ወር) ይቆያል።

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ ተመካካሪዎች ስሜታዊነትን አስወግደውና ኢትዮጵያን ማዕከል አድርገው የሰላሙን መንገድ ያቀናሉ የሚል ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ጉባኤተኞቹ በአምስት መቶ ተከፋፍለው ለ30 ቀናት በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ የሚወያዩ ሲሆን፥ ይህም በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ተመልክቷል።

የጉባኤውን መጀመር ዋዜማ በማስመልክትም በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የመከላከያ ማርሽ ባንድ የሙዚቃ ትርዒት ሲቀርብ ውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በእንቦጭ አረም ላይ ሲሰራ የነበረው የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ፈርሷል " - የአማራ ክልል የአካባቢ ባለስልጣን

የጣና ሐይቅን እና በክልሉ የሚገኙ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን ከብክለት፣ ከአረም(እንደ እንቦጭ) ወረራ እና ከመጥፋት አደጋ ለመታደግ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 2004 ዓ.ም ተቋቁሞ የነበረው የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ መፍረሱን የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአረም ዝርያ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ የሆኑት አቶ ድልነሳው ስመኘው " በኤጀንሲው ስር ይሰሩ የነበሩ ተግባራት በሙሉ በክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሰሩ ኤጀንሲው በክልሉ የመንግስት አደረጃጀት በአዋጅ እንዲፈርስ ተደርጓል " ብለዋል።

አክለውም " በኤጀንሲው ስር የነበሩ ተግባራቶች በአካባቢ ጥበቃ ስር ሊሰሩ ስለሚችሉ ኤጀንሲው ለብቻው መሆኑ አያስፈልግም በሚል ነው እንግዲህ ሪፎርሙ የተደረገው " ሲሉ ገልጸዋል።

" አረጀንሲው ፈርሶ ተግባራቶቹ ወደ ባለስልጣኑ እስከሚመጡ ድረስ በርካታ ስራዎች ሳይሰሩ ቆይተዋል፣ ግን ኤጀንሲው በዘንድሮው አመት የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ ያቀደውን ከ100% በላይ አሳክተናል፣ ነገር ግን ተቋሙ ሳይፈርስ አመቱን በሙሉ ቢሰራ አሁን ከተሰራው በላይ የተሻለ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ግልጽ ነው " ብለዋል።

" በኤጀንሲው ስር ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ስር ተካተዋል፣ በተቋሙ ሲሰሩበት የነበረውን መደብ ይዘው ነው የመጡት " ሲሉም አስረድተዋል።

" አሁን በአዲስ አደረጃጀት የተመሰረተው የተስፋፊና መጤ የአረም ዝርያ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በሚል ነው። እንቦጭ አንዱ ተስፋፊና መጤ የአረም ዝርያ ስለሆነ እንቦጭ የዚህ አካል ይሆናል፣ ሌሎች እንደ ሀገርም እንደክልልም የሚታወቁ በስፋት ችግር የሆኑብን የአረም ዝርያዎች ስላሉ እሱን የማስወገድ ስራ ከህብረተሰቡ ጋር ሆነን ስንሰራ ቆይተናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሌላው ደግሞ የብዝሃ ህይወት እና የስነ ምህዳር ጥበቃ የሚባል ዳይሬክቶሬትም ተቋቁሟል። ይህን የተቋቋመው በኤጀንሲው ላይ የነበሩ ተግባራትን ይበልጥ ለማሳለጥ ታስቦ ነው " ሲሉ አክለዋል።

በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን የገለጹት አቶ ድልነሳው " የመከላከል ስራው በሰው ሃይል ብቻ ሳይሆን ማሽኖችም ያስፈልጋሉ። ነገር ግን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ካምፕ ሳይት ላይ ያሉ መሽኖችን መጠቀም አልቻልንም፣ ምክንያቱም ከማሽኑ ጋር የሚንቀሳቀስ የሰው ሃይል አለ፣ ነዳጅና ሌሎችም የሎጂስቲክስ  አይነቶች አሉ። በካምፑ ያሉትን ማሽኖች መጠቀም አልተቻለም። ባህርዳር ከተማ የመጡ ሁለት የካናዳ ማሽኖች ስለነበሩ በእነሱ እንቦጭን የማረም ስራ ተሰርቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ የአለም የብዝሀ ሕይወት መጠባበቂያ ማዕከል (Biosphere Reserve) ሆኖ የተመዘገበውን የጣና ሐይቅን ጠብቆ ለማቆየት፣ አሁን ላይ በሰው ኃይልም ሆነ በማሽን የሚደረገው የማረም ሥራ ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል አቶ ድልነሳው ጠቁመዋል።

አረሙ በሁለት ሳምንት ውስጥ ራሱን በእጥፍ የሚያሳድግና ዘሩ እስከ 30 ዓመታት መቆየት የሚችል በመሆኑ፣ ችግሩን ከምንጩ ለመቅረፍ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

​ለዚህም በዋናነት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎችን የያዘው የላይኛው ለም አፈር በደለል መልክ ወደ ሐይቁ የሚገባበትን የጎርፍ ፍሰት ለመግታት ተፋሰሱን ሙሉ በሙሉ ማልማትና ወደ ሐይቁ የሚገባውን የእንቦጭ አረም የምግብ ግብዓት መጠን መቀነስ ቀዳሚው ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም፣ ያለውን እንቦጭ ወደ ኮምፖስት ማዳበሪያና ሌሎች ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎች በመቀየር ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ በመግለጽ፤ ተግባሩ በነጻና በክፍያ የሚሳተፈውን ኃይል ጨምሮ ከፍተኛ በጀትና የቴክኒክ ሙያ የሚጠይቅ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት በአስቸኳይ በገንዘብና በሙያ ሊረባረቡ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፎቶ ፦ ፋይል

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሀገር ቤት ገንዘብ ሲልኩ ለላኪም ለተቃባይም ምቹ አማራጮች ባሉት አቢሲንያ ሬሚት ይጠቀሙ!

ሲልኩም 12% ጉርሻ ይጠብቅዎታል!

አሁኑኑ መተግበሪያውን ከApp Store ወይም Google Play ያውርዱ፣ በቀላሉ ይመዝገቡ እና አገልግሎቱን ይጠቀሙ።

https://onelink.to/abyssiniaremit

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል።

ማዕቀፉ መምህራን በክረምት ስልጠና ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የሚሸጋገሩበት መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ማስገባት መቋረጡን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በቀጣይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተዘጋጀ የስልጠና ማዕቀፍ፣ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

በ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠናውን ለመስጠት ስምንት አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ለክረምት ስልጠናው የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦

1. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
4. መቐለ ዩኒቨርሲቲ
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
8. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ተቋማት እና የስልጠናው አሰጣጥ አግባብነት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በክረምት መምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ከ2011 ዓ.ም በፊት ስልጠና ጀምረው ያላጠናቀቁ መምህራን ከዚህ በፊት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ
ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 100% በአንድ ጊዜ የሚጭምሩ አከራዮች አሉ። ከ100% በላይ የሚጨምር አለ። ይሄ በፍጹም ስግብግብነት ነው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የቤት ኪራይ በተመለከተ አጠናሁት ያለው ጥናት የአከራይን መብት " ከግምት ውስጥ ያላስገባ " እና ተጨማሪ ጊዜና ሀብት ያባከነ የሚል ትችት ቀርቦበታል።

ይህ የተባለው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባዔ በተካሄደበት መድረክ ሲሆን የም/ቤት አባላት ካነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች መካከል ከሰሞኑ የወጣው የ11.5% የቤት ኪራይ ጨማሪ ጉዳይ ይገኝበታል።

የምክር ቤት አባሉ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ " አከራይና ተከራይን በተመለከተ የወጣው ህግ ክፍተቶች ያሉበት፣ ህብረተሰቡን በማወያየት የአከራዩንም የተከራዩንም ስሜትና ፍላጎት በማገናዘብ አማካኝ የሆነ ነገር ይዞ ያልወጣ " ብለውታል።

በቀረበው ሪፖርት ከ500 ሺሕ በላይ የአከራይና ተከራይ ግንኙነቶች እንዳሉ መስፈሩን፣ ይህም በአባወራ ደረጃ መሆኑን ጠቅሰው፣ " በስሩ አራት ሰዎች አሉ ብለን ከወሰድን 2 ሚሊዮን ህዝብ ነው። ስለዚህ በዚህ ደረጃ ክብደት ሰጥተን ማየት አለብን " ሲሉ አፈጻጸሙ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

አከራይና ተከራይን የተመለከተው ህግ በየዓመቱ የኪራይ መጠን እየተጠና እንዲጨመር ያስቀምጣል ያሉት ሲሳይ (ዶ/ር)፣ " ዘንድሮ ተጠና ተብሎ የቀረበው ጭማሪ በሁለት አመቱ ነው። ስለዚህ አዋጁ ለአከራዮች የሰጠውን መብት እንኳ እየነፈግን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የተከራዮች ብቻ ሳይሆን የአከራዮችን መብትም ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል። ግንኙነታቸው ሰላማዊ እንዲሆን " ብለዋል።

" የእንጨት የነበረን ቤት አሻሽሎ በብሎኬት ሰርቶ አከራዩ ኪራይ እንዲጨምር የሚያደርግ አሰራር አለ ወይ ? ለእድሳት ላወጣው ወጭ ለማካካስ የኪራይ ጭማሪ ማድረግ ይችላል ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

የ2019 ዓ/ም የቤት ኪራይ ጭማሪ 11.5% እንዲሆን የተወሰነበት ጥናት የማዕከላዊ ስታቲክስ (CSA) ካወጣው ጥናት (ዓመታዊ የዋጋ ጭማሪ ከ10 እስከ 13%) ተመሳሳይ ስለሆነ ከዛ መውሰድ እየተቻለ ተጨማሪ ጥናት በማድረግ ጊዜና ሀብት ባክኗል ፤ ይህም አስፈላጊ አይደለም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ደግሞ፣ " ጥናቱ ሳይንሳዊ ነው " በማለት ሌላ ከማጥናት ይልቅ " የCSA ጥናት ቢወሰድ ተመሳሳይ ነው " መባሉን " ተመሳሳይ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተውበታል።

" CSA የሚያጠናው ጥናት ሀገራዊ ነው፤ እኛ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን ችግር መሰረት አድርገን ነው ያጠናነው " የሚል መሞገቻም አቅርበዋል።

የጥናቱ መስፈርቶች ፦
- የCSAን ጥናት፣
- የቤት ፍላጎትና አቅርቦት ክፍተተት (30%)
- የዜጎች የመክፈል አቅም (15%)
- የቤት ጥገና እና ማሻሻያ ወጭ (15%)
- ከተማ ላይ ያለ የህዝብ ብዛት ለወጥ፤ ታሳቢ ተደርጎ ከ100% ተይዞ የተጠና መሆኑን ቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምን አሉ ?

" በተጨማሪ አጠናን በአጋጣሚ እርስዎ (ዶ/ር ሲሳይ መንስግስቴ) እንዳሉት ሆነ። የቤት ኪራይ መጨመር ግድ የሚልበት ሁኔታ ካለ እስከ 11.5% ድረስ እንዲሆን ጣሪያውን ነው የሚያስቀምጠው፤ ከዚያ ማለፍ አይቻልም።

በከተማችን ባደረግነው ጥናት 100% በአንድ ጊዜ የሚጭምሩ አከራዮች አሉ። ከ100% በላይ የሚጨምር አለ። ይሄ በፍጹም ስግብግብነት እንጅ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይና ለዚያ ተብሎ የሚደረግ እንዳልሆነ አይተናል።

ተከራይን ከቤት ለማስወጣትም ሲፈለግ ተመሳሳይ ድርጊት እንደሚፈጸም አይተናል። ህጉ የተከራዩንም የአከራዩንም መብት የሚጠብቅ ሁሉንም ወገን ያማከለ አሰራር ስለሆነ በአሰራር ስርዓቱ መግባት ግድ ይላል።

በደረስንበት ልክ ህጉ ላይ ያልገቡትን ግን ህጉ ላይ በተቀመጠው መንገድ እየቀጣን ማስተካከያ እያደረግን የምናስተገብር ይሆናል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት
#AddisAbaba

ከለሊት 11:30 ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

ነገ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ይደረጋል።

ውድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ለገሀር፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ብሔራዊ ቴአትር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ንግድ ባንክ፣ ጋንዲ ሆስፒታል ፣ ጊዮን ሆቴል በማድረግ መስቀል አደባባይ ፍጻሜውን ያነኛል።

ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ)
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
- ከAU መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ)
- ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት)
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ)
- ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ)
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ)
- ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ)
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ)
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ)
- ከAU መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ)
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
- ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
- ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)
- ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
- ከአገር አስተዳደር መብራት ወደ ብሔራዊ ቲያትር  (አገር አስተዳደር መብራት)
- ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ (ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ)   ... እሁድ ከለሊቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ፕሮግራሙ ፍፃሜ ድረስ እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።

በተገለፁት መስመሮች ላይ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም ተከልክሏል።

ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🎓" ከ2010 ዓ/ም እስከ 2015 ዓ/ም የዲግሪ ተመራቂዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ፈተና ሊፈተኑ ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተና ህዝብ አደናጋሪ ነው።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (በፌስቡክ እና ቲክቶክ) ላይ የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያዘጋጀውንና ለህዝብ አስተያየት ይፋ ያዳረገውን አዲስ ረቂቅ መመሪያ በማዛበት፣ " ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ ሲባል በድጋሚ ፈተና ሊሰጣቸው ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ እና ህዝብን የሚያደናግር ነው።

የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገው መመሪያ በትክክል እነማንን ነው የሚመለከተው ?

ይህ መመሪያ/አሰራር የሚመለከተው በቀድሞው ዲፕሎማ (10+3፣ 12+2 ወይም ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ስልጠና) ተመርቀው፣ ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) ወይም ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙትን ብቻ ነው።

እነዚህ ዜጎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ አሁን በያዙት የትምህርት ደረጃ/የያዙት ዲግሪን መሰረት ተደርጎ የሚሰጠውን ፈተና መውሰድና ማለፍ ይኖርባቸዋል።

በአጭሩ የሚመለከተው ወይም ተፈጻሚነቱ :-
- ለዲግሪ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ የተማሩ እና የተመረቁ።
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ነው።

በመደበኛው መንገድ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው (ለምሳሌ የ12ኛ ክፍል ማለፊያ አምጥተው) የገቡ፣ ወይም ከዲፕሎማ ተነስተው የCOC ፈተና አልፈው ዲግሪ የጫኑ እና የተመረቁ ዜጎችን ይህ መመሪያ አይመለከታቸውም። የትምህርት ማስረጃቸውም ያለ ምንም ተጨማሪ ፈተና እንደ ቀድሞው ይረጋገጥላቸዋል።

መመሪያው በአሁኑ ወቅት በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለና እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ አስተያየት ክፍት የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 4 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አስፈላጊው በጀት እንዲመጣ ተደርጎ ተማሪዎቹ በግቢው እንዲቆዩ ተደርጓል " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከትግራይ ክልል የመጡ ተማሪዎች፣ በክልሉ አለ ባሉት " አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ " እና የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደማይችሉ ገልጸው፤ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የክረምት ማደሪያ (ዶርሚተሪ) እንዲፈቅድላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት አቤቱታቸው፤ ወደ ክልሉ መመለሳቸው ከአካላዊ ደህንነት ስጋት ባለፈ፣ የጀመሩትን የከፍተኛ ትምህርት ጉዞ ሙሉ በሙሉ ሊያቋርጥባቸው እንደሚችልም መግለጻቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ክረምቱን እንዲያሳልፉ የተፈቀደላቸው መሆኑን ከተማሪዎቹ ሰምቷል።

ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ ተከትሎ እስከሚቀጥለው የትምህርት አመት ድረስ አስፈላጊውን የምግብ እና የዶርም አገልግሎት እያገኙ በግቢው እንዲቆዩ የተፈቀደላቸው መሆኑን ገልጸውልናል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኔኬሽን ዳይሬክተር ኤልያስ ወርቁ (ዶ/ር) ይህንኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ " አስፈላጊው በጀት እንዲመጣ ተደርጎ ተማሪዎቹ በግቢው እንዲቆዩ ተደርጓል" ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄይሉ ኡመር (ዶ/ር) ተማሪዎቹ በግቢው ያሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ላቀረቡት ቅሬታም ምላሽ የተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊው ነገሮች እየተደረጉ ይቆያሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ኤባ ሚጀና(ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያቀረቡት ቅሬታ ደርሷቹ ነበር ? በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ከትግራይ ክልል መጥተው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎችስ ጉዳይ? ስንል ጠይቀናል።

በምላሻቸው እስካሁን ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህን አይነት ቅሬታ አለመድረሱን ገልጸው መሰል ቅሬታዎች ካሉ የሚያጣሩ መሆኑን አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 3 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሳምንት ውስጥ ወደ መቐለ እንደሚመለሱ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ በትግራይ ክልል መቐለ ያደረጉት ጉብኝት በቀጠናዊ ሰላምና ፀጥታ፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የክልሉ አመራር አቶ አማኒኤል አሰፋ፣ አምባሳደር ማሲንጋ ከክልሉ አመራሮች የቀረቡላቸውን ሀሳቦች ለፌዴራል መንግሥት ካቀረቡ በኋላ በሳምንት ውስጥ ወደ መቐለ እንደሚመለሱ ገልጸዋል።

" አሁን ያሉ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ዝግጁ ነን ፤ ይህንንም ለአምባሳደሩ አስረድተናል " ብለዋል።

በተጨማሪም፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በቅርቡ ያደረጉት ጉብኝት በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ መካከል የነበረውን ውጥረት ለማርገብ የተፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፤ የቀድሞው የክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አምባሳደሩ ሰዎችን ወደ ምክንያታዊነትና ሰላማዊ ውይይት ለማምጣት ላደረጉት ጥረት አመስግነዋቸዋል።

ከተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ እና ከማኅበረሰብ መሪዎች ጋር መገናኘታቸውን በመጠቆምም አድንቀዋል።

አቶ ጌታቸው፣ አምባሳደሩ ከጄኔራል ታደሰ ወረደ ጋር እንዳይገናኙ መደረጉን ጠቁመዋል።

" በትግራይ ያለው ቡድን ሕዝቡን መደራደሪያ በማድረግ ጥቅም ለማግኘት የሚሄድበት መንገድ አደገኛና ውጤት የሌለው " መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አምባሳደሩ ከጄኔራል ታደሰ ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸው " ቡድኑ ዲፕሎማሲን ወደ ታጋች ድርድር የመቀየር ባህሪው ማሳያ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" መጀመሪያ በካሬ 35 ሺሕ ብር የነበረውን ክፍያ አሁን 'በካሬ 82 ሺሕ ብር ሆኗል' በሚል ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አደረጉብን " - ለቤት የተደራጁ መምህራን

መምህራን በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዚህ ቀደም በተጀመረው አሰራር መሰረት በካሬ 35 ሺሕ የነበረው ክፍያ አሁን " በካሬ 82 ሺሕ ብር ተደርጎ፣ 25% የቅድሚያ ክፍያው ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጎበታል " ሲሉ መምህራን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቅርበዋል።

መምህራን የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማህበራቸው በኩል በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይስተዋላሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከንግድ ባንክ ጋር ከዚህ ቀደም መፈራረሙ ይታወሳል።

በወቅቱ እንደተገለጸው፣ ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሃግብር የሚከናወን ሲሆን፣ 25 በመቶ የመንግስት ሠራተኛው ቆጥቦ፣ 75 በመቶ የባንክ ብድር የሚቀርብለት፣ ብድሩን በ20 ዓመታት የሚከፈልበት ነው።

መምህራኑ በወቅቱ በስምምነቱ ጥሩ ቢሆንም " 25 በመቶ የመቆጠብ አቅም የለንም " ብለው የነበረ ሲሆን፣ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሰጡት ምላሽ፣ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።

መምህራኑ አሁንስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" መምህራንን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ያደርጋል በሚል በወጣው መመሪያ መሰረት እያንዳንዳቸው 110 አባላት የያዙ 60 ማህበራት በከተማዋ ተደራጅተዋል።

ቦታው ተለይቶ ከተሰጠን ወዲህ አንዳንድ ኮንትራክተሮች የተወሰነ ግንባታ ጀምረው ነበር፤ የተወሰኑት አልጀመሩም። ግን መጀመሪያ በካሬ 35 ሺሕ ብር የነበረው ክፍያ አሁን በካሬ 82 ሺሕ ብር ሆኗል በሚል ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አደረጉብን።

በወቅቱ የነበረው በካሬ 35 ሺሕ ብር ነበር።  ከከፈልን በኋላ ሲጓተት ቆይቶ ከወር በፊት ግንባታውን ጀመሩ። ግን በኋላ ASTU ጥናት አጥንቶ በካሬ 82% ደርሷል ተባለ። በዚህም ለምሳሌ 3 ሚሊዮን የነበረ ውል ወደ 9 ሚሊዮን ሆኗል።

ጉዳዩን የሚያውቀውን የአዲስ አበባ መምህራን ማህበርን ስንጠይቅ 'እኛ ሳናውቅ እንዴት እንዲህ አይነት ነገር ይሆናል ?' የሚል ምላሽ ነው የሰጡን። ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀናል።

ቤቱ ይጠቅመናል ብለን 25% የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ የከፈልነው ከሁለት፣ ሦስት ማይክሮፋይናንስ ተበድረን ነው። የጋራ መኖሪያ ቤት እድል ተጠቃሚ ከሆኑት ወደ 660 መምህራን አብዛኛዎቹ ተበድረው ነው የከፈሉት።

በዛ ላይ ባንክ ያመቻቸልን 75 በመቶ ብድር በምን ውል እንደሚከፈል አልታወቀም። 14% ነው የተባለው ኢንተረስቱ። ጫማ፣ ልብስ መቀየር የከበደን ሰዎች ነን። አብዛኞቻችን ችግር ላይ ወድቀናል " ብለዋል።

25 ፐርሰንቱን 400 ሺሕ፣ 500፣ 700 ሺሕ እንደየካሬው ብዛት ቅድሚያ ከፍለው ካጠናቀቁ በኋላ ግንባታ ሊጀመር ሲል " የግንባታ እቃ የዋጋ ለውጥ አለ " በሚል የተጨመረባቸው ገንዘብ ከሁለት እጥፍ በላይ መሆኑን ገልጸው፣ ለመክፈል አቅማቸው ስለማይፈቅድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመምህራኑ ቅሬታ ምላሽ የጠየቀው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ መምህራን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለዘመናት ሲጠይቅ መቆየቱን አስታውሶ፣ ስለክፍያ ጭማሪ ግን ጉዳዩን የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ማብራሪያ እንዲሰጥ መርቷል።

የአ/አ ከተማ መምህራን ማህበር ምን መለሰ ?

የከተማዋ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶለሳ የስልክም ሆነ የፅሑፍ መልዕክት ባይመልሱም፣ ቅሬታ አቅራቢ መምህራኑ የማህበሩ ም/ፕሬዝዳንት ናቸው ያሏቸው፣ እሳቸው ደግሞ "የማህበሩ አመራር ነኝ" ያሉት አቶ አናንያ ደርሶ ግን የመምህራኑን ቅሬታ ይዘን ላቀረብነው ጥያቄ የተሰወነ ማብራሪያ ሰጥተውናል።

በሚያውቁት መረጃ መሰረት፣ " ASTU (የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) ባደረገው ጥናት መሰረት አጠቃላይ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታን በአማካሪነት ይዞታል፤ ካለው ወቅታዊ የዋጋ ንረት አኳያ የተወሰኑ ማሻሻያዎች አድርጓል " ብለዋል።

" ባለኝ መረጃ፥ ከመምህራኑ ለኛ ተፅፎ በዚህ ተጨምሯል፤ በዚህ ልክ ሆኗል የሚል የደረሰን ነገር የለም። ይደውላሉ እንጅ በደብዳቤ የመጣ ነገር የለም " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነገር ግን መምህራኑ በከፈቱት የዋትሳፕ ግሩፕ "ከፍተኛ ጩኸት/ቅሬታ" እንዳለ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሌሎች የሚመለከታቸውን ተቋማትን ለማናገር ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

ጊዜ ፣ ቦታ እና ኔትወርክ ሳይገድበን ከምንወዳቸው ጋር እንደልብ እንገናኝ! 📞💚

የሳምንት በ30 ብር ብቻ 120 ደቂቃ በመግዛት ከሳፋሪኮም (07) ወደ ቴሌ (09) እንደልብ ይደውሉ።

አሁኑኑ *777*1# ብለው ይደውሉ!

#SafaricomEthiopia #VoicePackage

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalDialogue🇪🇹

" ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ይህ ምክክር ፍሬያማ ይሆናል" ሲሉም አሳስበዋል " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) 

👉 " ይህ ጉባኤ በቀላሉ የማይደገም ነው ! "

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ደጋግሞ የሚታየውንና በኃይለቃል ጀምሮ በኃይል እርምጃ የመደምደም የፖለቲካ ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማቆም ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በሀገራዊ የምክክር ጉባዔ የመክፈቻ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ፥ በቀጣዮቹ ሳምንታት ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፈው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ አዲስ ታሪክ የምትጽፍበት "የብዕርና የብራና" ታሪካዊ አጋጣሚ ሲሆን፣ በቀላሉ የማይደገምና በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ግዙፍ ዓላማ ያለው መድረክ መሆኑ ተናግረዋል።

" አንዳንድ አጋጣሚዎች ከታሪክ ብዕርና ብራና ፊት ያቆማችኋል፤ ዛሬ የምንገኝበት መድረክም ሀገርን የሚጠቅምና ለዘመናት የሚታወስ ታሪክ ለመጻፍ ዕድል የሚሰጥ ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በኃይለቃል ተጀምሮ በኃይል እርምጃ የሚደመደምበትን አዙሪት በንግግርና በውይይት የመተካት ወቅት ላይ እንደተደረሰም ገልጸው፣ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ባህልን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።

ተወያዮች ከአካባቢያቸው ወጥተው ለኢትዮጵያ፣ ለዛሬ ሳይሆን ለነገ፣ ለራሳቸው ሳይሆን ለልጆቻቸው እንዲመክሩም ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦች የሚያነሱትን ጥያቄ በመደማመጥ እና ማንም ሳይጎዳ በጋራ መጠቀም የሚያስችሉ መፍትሔዎችን መፈለግ የምክክሩ ስኬት መሠረት እንደሚሆን ገልጸዋል።

" ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ይህ ምክክር ፍሬያማ ይሆናል" ሲሉም አሳስበዋል።

ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፥ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ የሰላም፣ የተስፋና የመደማመጥ ባህል መገንባት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፣ በሀገር ውስጥ በሚደረግ ውይይትና በይቅርታ ችግሮችን በመፍታት ኢትዮጵያን ከውጭ ጣልቃ ገብነት መጠበቅ እንደሚቻል ገልጸዋል።

(ሙሉ ንግግራቸው ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ይህ ጉዳይ የአንድ ሰሞን አጀንዳ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር። ...ለታርጋ ከ60 ሺህ እስከ 120 ሺህ ብር ድረስ በደላሎች ይጠየቅ ነበር " - ተገልጋዮች

ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ በታርጋ (ሰሌዳ) እና በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ፤ በታክሲ ማህበራት አደረጃጀትና ስምሪት ዙሪያ ፤ ይፈጸማል ተብሎ በተጠረጠረ የሙስናና የሕገወጥ አሰራር ጉዳይ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ደላሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህን እርምጃም የወሰደው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሆኑንም አመልክቷል።

ፖሊስ፣ ምርመራ መቀጠሉን የገለጸ ቢሆንም የአመራሮቹን ሆነ የሌሎቹን ተጠርጣሪዎች ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።

በሌላ በኩል፣ በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች፣ ለታርጋ (ሰሌዳ) ማውጫ በሚል ስም እንደየተሽከርካሪው አይነት ከ60 ሺህ እስከ 120 ሺህ ብር ድረስ በደላሎች አማካኝነት እንዲከፍሉ ይጠየቁ እንደነበር ገልጸዋል።

እንደ ባለቅሬታዎቹ ገለጻ፣ በተለይ 7 ሰው የሚጭኑ የኤሌክትሪክ ባጃጆችና ባለ ሁለት ጎማ ሞተር ሳይክሎች ባለቤቶች ላይ ጫናው የበረታ ሲሆን፣ ለትራንስፖርት ቢሮ በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም ተገቢ ምላሽና የሚሰማቸው አካል ሳያገኙ እንደቆዩ አመልክተዋል።

" ትራፊክ ፖሊስ 'ታርጋ ከሌለ መንዳት አትችሉም' ይለናል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በጥቅም ትስስርና በጉቦ እንጂ ታርጋ አይሰጥም ነበር። ለረጅም ጊዜ በዚህ ችግር ተሰቃይተናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ባለንብረቶቹ አክለውም፣ " በእነዚህ ሕገወጥ አሰራሮችና ደላሎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ አስደስቶናል " ያሉ ሲሆን ነገር ግን ጉዳዩ የአንድ ሰሞን አጀንዳ እና የሚዲያ ወሬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር አሳስበዋል።

ጥፋተኞችም ተለይተው ሲቀጡ ማየት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ‎ሕብረተሰቡ በሀዋሳ ከተማ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ፦
- በታርጋ (ሰሌዳ) አሰጣጥ፤
- በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ
- በታክሲ ማህበራት አደረጃጀትና ስምሪት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃና ጥቆማ ማድረስ ከፈለገ በነፃ የስልክ መስመር 7614 እንዲሁም በመደበኛ ስልክ 0462201046 ማድረስ እንደሚቻል አሳውቋል።

ሕብረተሰቡ ጥቆማውን ከማድረስ ወደኋላ እንዳይል ያስገነዘበው ፖሊስ " በየትኛውም የስልጣን እርከን በሚገኝ ህገወጥ አካል ላይ እርምጃው ይቀጣል " ሲል አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalDialogue🇪🇹

ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል፡፡

በምክክር ጉባኤው ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ቪድዮ ፦ AMN

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

" የትራፊክ መጨናነቅ ስለሚያጋጥም አማራጭ መንገዶች ተጠቀሙ " - ትራፊክ ማኔጅመንት

ነገ ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። ለዚሁ ጉባኤ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የጉባኤው ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በሲኤምሲ መስመር የተባበሩት አደባባይ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር ጠዋት እና ማታ ሲገቡና ሲወጡ የሚጓዙባቸው መስመሮች ማለትም ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በሳህሊተ ምህረት እንዲሁም ከኢትዮ ቻይና መስመር በሳህሊተ ምህረት እስከ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚያጋጥም የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሳውቋል።

በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ጉባኤው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በመስመሮቹ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ከወዲሁ መልዕክት ተላልፏል።

ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ግልግል
ግብር በቴሌብር!

ሰነድ ማዘጋጀትና ሰልፍ መሰለፍ ቀረ፤ የዓመቱን ግብር በቴሌብር አሁኑኑ እንክፈል!

የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የአዲስ አበባ (ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ)፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን፣ የሱማሌ፣ የሐረሪ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ገቢዎች የግብር ክፍያ በአስተማማኝ ሁኔታ አሁኑኑ በቴሌብር ይክፈሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንከፍል እንዲህ ነን!

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያገረሸው ጦርነት በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ።

በእስያ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን አንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.9 በመቶ አሻቅቦ በበርሜል 84.87 ዶላር ደርሷል።

በአሜሪካ ገበያ ደግሞ በ2 በመቶ ጨምሮ በበርሜል 79.75 ዶላር እየተሸጠ ነው።

ግጭቱ ተባብሶ በመቀጠሉ ሰኞ ዕለት የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በ3 በመቶ ገደማ የጨመረ ሲሆን በአራት ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ነጋዴዎች በሚሰጡት ምላሽ ዓለም አቀፍ የጅምላ ገበያ ዋጋ ከቅርብ ወራት ወዲህ እየዋዠቀ ነው።

አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት መጨረሻ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ዘግታለች።

ወሽመጡ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ ዘይት እና የተጣራ የተፈጥሮ ጋዝ የሚተላለፍበት ዋነኛ መስመር ነው።

አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢታይም ሚያዝያ ወር ላይ ከነበረው እጅግ ያነሰ ነው። ሚያዚያ ወር ላይ የአንድ በርሜል ብሬንት ዋጋ 120 ዶላር ደርሶ ነበር።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሊትል ስቴፕስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት

🎓 ታላቅ የምሥራች ለወላጆች! 🎓

ሊትል ስቴፕስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ከ7 ዓመታት በላይ በአውስትራሊያን እና በካምብሪጅ ስርዓተ ትምህርት ከመዋዕለ ህፃናት እስከ መሰናዶ ሁለት ተማሪዎችን በብቃት ሲያስተምር ቆይቷል።

አሁን ደግሞ በወሰን 02 አዲስ ቅርንጫፍ በመክፈት ከህፃናት ማቆያ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርት መስጠት ጀምሯል።

📚 ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ተጀምሯል!

የልጆቻችሁን የወደፊት ስኬት ከዛሬ ይጀምሩ!
📞 ወሰን 02 ቅርንጫፍ
0929 930180 / 0996 326464/ 0116 733258
📞 ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ - ህፃናት ማቆያ   
0977 509045/ 0948 191982
📞 ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ (ከመዋዕለ ህፃናት - 3ተኛ ክፍል) 0935 945594
📞 ሰሚት 72 ቅርንጫፍ/
0938 11 7722

✨ Little Steps International School
A Big Journey Starts with A Little Steps !

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🛑 የ3.69 ቢሊዮን ብር ብክነት ፤ የ132 ሚሊዮን ብር ቅንጡ መኪናዎች ግዢ  - በመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ የተገኘው የኦዲት ሪፖርት !

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በ2018 እስከ 2025 እ.ኤ.አ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ስር በተከናወኑ የዌልመል እና የጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት፣ 3.69 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ሕገ-ወጥ የዋጋ ማስተካከያና ተጨማሪ ወጪ፣ ከባድ የውል ጥሰቶች፣ ደካማ ክትትል እና ከፍተኛ የሕዝብ ገንዘብ ብክነት መኖሩን አስታውቋል።

ኦዲቱ እንደሚያሳየው፣ በሁለቱም ፕሮጀክቶች ውስጥ " የዋጋ ማስተካከያ አይፈቀድም " የሚለው የውል ድንጋጌ ተጥሶ በተደጋጋሚ የውል ማሻሻያዎችና ያልተገቡ የሥራ ለውጥ ትዕዛዞች ተፈጽመዋል።

በአንዳንድ የግንባታ ክፍሎች በጀቱ እስከ 168.64 በመቶ ድረስ ሲጨምር፣ የአማካሪ ውሎችም እስከ 276.84 በመቶ ድረስ ከፍ ብለዋል።

የፕሮጀክቶቹ ሥራ፦
- የቅድመ ግንባታ አዋጭነት ጥናት አለመደረግ፣
- ደካማ የኢንጂነሪንግ ዲዛይን፣
- ውጤታማ ያልሆነ ክትትል፣
- የአስተዳደር ውሳኔ ችግር እና የተቋራጮችና የአማካሪዎች የአቅም ውስንነት ምክንያት ከ38 ወራት በላይ ዘግይተዋል። ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ በውሉ መሠረት መጣል የነበረበትን የመዘግየት ቅጣት በተቋራጮቹ ላይ አልተገበረም።

በተጨማሪም የተቋራጮችንና የአማካሪዎችን አፈጻጸም በወጪ፣ በጥራትና በጊዜ የሚገመግም መደበኛ ሥርዓት ባለመኖሩ ችግሮችን በወቅቱ ለማረም እንዳልተቻለ ሪፖርቱ ያስረዳል።

ኦዲቱ በጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ የሕዝብ ገንዘብ በውሉ ውስጥ ላልተካተቱ ቅንጡ ተሽከርካሪዎች ግዥ ላይ መዋሉንም አጋልጧል። ከእነዚህ ውስጥ አንድ የ2023 ሞዴል V6 ተሽከርካሪ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ሲሆን፣ ሁለት የ2023 ሞዴል Toyota Prado ተሽከርካሪዎችም 83 ሚሊዮን ብር ወጪ አስከትለዋል።

እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለቴክኒካል ክትትል ተገዙ ቢባልም፣ ተሽከርካሪዎቹ በመጨረሻ በተቋራጩ እጅ መግባታቸውን መ/ቤቱ ገልጿል።

በሌላ ግኝት ደግሞ፣ 75 ሚሊዮን ብር የፈጀ 7 የመስክ ተሽከርካሪዎች ግዥ የተጠናቀቀ የግንባታ ስራ እንደሆነ በማስመሰል በተጭበረበረ ጊዜያዊ የክፍያ ማረጋገጫ በኩል ተፈጽሟል። ይህም ለተቋራጩ ተጨማሪ 6 ሚሊዮን ብር ትርፍና የአገልግሎት ክፍያ እንዳስገኘ ሪፖርቱ ይጠቁማል።

በተጨማሪም ሁለቱም ፕሮጀክቶች የአካባቢና የማኅበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ እንዲሁም ከሚመለከታቸው ተቋማት የሚጠየቁ ፈቃዶችን ሳያሟሉ መተግበራቸውን ኦዲቱ አመልክቷል።

በምስራቅ ባሌ ዞን ራይቱና ጊነር ወረዳዎች መካከል የሚገኘው የጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት 4,145 ሄክታር መሬትን በመስኖ ለማልማትና ከ9,000 በላይ አርሶ አደሮችን ለመጥቀም የታቀደ ቢሆንም፣ እስከ 2025 (እ.ኤ.አ) ድረስ የአማካሪ አገልግሎትን ጨምሮ ወደ 2.3 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ በ2021/22 ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጋር የነበረው ውል ከተቋረጠ በኋላ፣ ለአለማየሁ ከተማ ኮንትራክተር ነው የተሰጠው።

በተመሳሳይ በዴሎ መናና በሀረና ቡሉቅ ወረዳዎች የሚገኘው የወልመል ፕሮጀክት 12,040 ሄክታር መሬትን ለማልማት ታቅዶ ነው የተነሳው። ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ በ2018/19 በድምሩ 2.9 ቢሊዮን ብር ለአለማየሁ ከተማ ኮንትራክተርና ለኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቢሰጥም፣ " ባልተጠበቁ የዲዛይን ችግሮች " በሚል ምክንያት በጀቱ በእጅጉ ጨምሯል። እስከ 2025 ድረስ መንግሥት ለሎት አንድ  ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ፣ ለሎት ሁለት 2.3 ቢሊዮን ብር፣ ለአማካሪ አገልግሎትም 164 ሚሊዮን ብር ቢያወጣም የፕሮጀክቱ አፈጻጸም አሁንም ውስን ሆኖ መቆየቱን ኦዲቱ አመልክቷል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለችግሮቹ መነሻ የተቋማዊ አስተዳደር ድክመትን በመጠቆም፣ ሚኒስቴሩ ዘመናዊ የመስኖ ፖሊሲ፣ የተሟላ ስትራቴጂና የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ሳይዘረጋ ከፍተኛ ካፒታል የሚጠይቁ ፕሮጀክቶችን መጀመሩ ለዚህ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ገልጿል።

በመጨረሻም ሚኒስቴሩ የተመከሩትን የማስተካከያ እርምጃዎች በጊዜው ካልተገበረ፣ ጉዳዩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕግና የወንጀል ተጠያቂነት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ይህ መረጃ ከካፒታል ጋዜጣ ነው የተወሰደው።

ሃምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EthiopianAirlines

" አጠቃላይ የወጣው ወጪ 1.4 ቢሊዮን ብር ነው " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ሲመረቅ ባደረጉት ንግግር፣ የአየር መንገዱ የደብረ ማርቆስ ከተማ የበረራ አገልግሎት ታሪክ ከ50 ዓመታት በፊት የጀመረ እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ አየር መንገዱ "ዳሽ-6" (Dash-6) የተባሉትን አውሮፕላኖች ከአገልግሎት ውጪ ሲያደርግ፣ በረራው ላለፉት 20 ዓመታት በላይ ተቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል።

ለበረራው መቋረጥ ዋናው ምክንያት አየር መንገዱ ለሀገር ውስጥ በረራዎች የመደባቸው አውሮፕላኖች ትላልቅ በመሆናቸውና በጊዜው የነበረው ማኮብኮቢያ እነዚህን አውሮፕላኖች ማሳረፍ ባለመቻሉ እንደነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

በዚህም የተነሳ የአካባቢው ማኅበረሰብ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ አድካሚ የሆነውን የአባይ ወንዝ ሸለቆ በማቋረጥ፣ 300 ኪሎ ሜትር በመኪና መጓዝ ብቸኛ አማራጭ ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል።

አቶ መስፍን ለአካባቢው ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ " ዛሬ አዲስ አበባ ወይም ባሕር ዳር ከ1 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ደኅንነቱና ምቾቱ በተጠበቀ የአየር ትራንስፖርት መጓዝ ችላችኋል ፤ የዘመናት ጥያቄያችሁም መልስ አግኝቷል " ብለዋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ጣቢያው የሙከራ በረራ ሲጀመር በሳምንት 3 በረራዎች ብቻ ይበቃል የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በቀን 3 እና በሳምንት 21 በረራዎች መድረሱን ይፋ አድርገዋል።

ይህ እውነታ በአካባቢው ምን ያህል የታፈነ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎት እንደነበር የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱን ዝርዝር መረጃ በተመለከተም፣ አውሮፕላን ማረፊያው 2,400 ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ያለው በመሆኑ በመደበኛነት Q400 አውሮፕላኖችን፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖችን ማሳረፍ እንደሚችል አስታውቀዋል።

ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች ከ4 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን፣ አጠቃላይ የወጣው ወጪም 1.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት መጀመሩ ኢንቨስተሮችና ቱሪስቶች ወደ አካባቢው እንዲመጡ በማስቻል ለአካባቢው የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩት የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያዎች 5ኛው፣ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉት ደግሞ 25ኛው መሆኑን ጠቅሰዋል።

በቀጣይ ግንባታቸው እየተጠናቀቀ ያለ 2 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ አብስረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 5 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እኛ ብንኖርም ባንኖርም መበቀላችን አይቀሬ ነው "  - ሞሽታባ ኻሜኒ

👉 " [እኔ ከተገደልኩ] ኢራንን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ ጥቃት ለአንድ ዓመት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ተሰጥቷል " - ትራምፕ


በአሜሪካና በኢራን መካከል የተደረገው ተኩስ አቁም ስምምነት የፈረሰ ሲሆን የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ዛቻዎችን እየተለዋወጡ ይገኛሉ።

አሜሪካና እስራኤል በከፈቱት ጥቃት አባታቸው የተገደሉባቸው የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞሽታባ ኻሜኒ፣ የአባታቸውን ደም መበቀል "አይቀሬ" መሆኑን ገልጸዋል።

" ይህ በቀል የአገራችን ፈቃድ ነው። ያለምንም ጥርጥር መፈጸም አለበት " ያሉት የ54 ዓመቱ መንፈሳዊ መሪ ' ይህ ጉዳይ በእኔም ሆነ በሌሎች ባለሥልጣናት ህልውና ላይ የሚመሠረት አይደለም። እኛ ብንኖርም ባንኖርም ይህ ጉዳይ መፈጸሙ አይቀሬ ነው ብለዋል።

መንፈሳዊ መሪው በአባታቸው ስርዓተ ቀብር ላይ ያልተገኙ ሲሆን የአባታቸውን ደም መበቀል እንደማይቀር የገለጹ በፅሁፍ ባሰራጩት መልዕክት ነው።

በሌላ በኩል፥ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ " 1000 ሚሳይሎች ተቀባብለው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ተደግነዋል "  ሲሉ ዝተዋል።

ኢራን ልትገድላቸው እንደዛተች የገለጹት ትራምፕ ይህ ከሆነ፣ ኢራንን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ ጥቃት ለአንድ ዓመት እንዲፈጸም ትዕዛዝ መሰጠቱን፣ የአሜሪካ ጦርም ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

መረጀው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ኤኤፍፒን ዋቢ በማድረግ ነው ያስነበበው።

ሃምሌ 4 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ ለሚካሄድ አስቸኳይ ግንባታ ሲባል ከጀሞ 1 ወደ ጀሞ 3 የሚወስደው መንገድ ለ15 ቀናት ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል በላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ አስቸኳይ የቦክስ ከልቨርት ግንባታ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ሲባል ከነገ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዝግ እንደሚደረግ ገልጿል።

በመሆኑም፦

- ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደውን መንገድ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች፤ በላፍቶ ሆስፒታል ጀርባ አድርገው ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ እንዲጓዙ፤

- ከጀሞ ሦስት አደባባይ ወደ ጀሞ አንድ ሚጓዙ አሽከርካሪዎች፣ በሀጫሉ ሁንዴሳ ጎዳና አድርገው በቫርኔሮ አደባባይ በኩል መጓዝ የሚችሉ መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ጠቁሟል።

ሃምሌ 3 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የቤት ኪራይ ጭማሪ

" የ11.5% ጭማሪ አነስተኛ ይመስላል፤ በዓለምአቀፍ ደረጃ ሲታይ ግን እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ ነው የተደረገው " - የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት

👉 " ሞሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሥር ያሉ ሱቆች ቀድመው የገዙ የሚያከራዩበት ዋጋ ለመስማት የሚዘገንን ነው! "

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ጠዋት ይፋ ያደረገው የ11.5% የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ " እጅግ ከፍተኛ " ፣ " አብዛኛው ተከራይ ከፍተኛ ጭማሪ ከተደረበትና ከተፈናቀለ በኋላ ይፋ የተደረገ " በመሆኑ የዘገዬ ውሳኔ መሆኑን የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ለቲክቫህ ኢትዮጵያን ገለጸ።

የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ በሰጡን ቃል፣ " 11.5% የሚለው ጭማሪ ከኛ ሀገር የዋጋ ግሽበት አንፃር ተመጣጣኝ ቢሆንም ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲታይ ከፍተኛ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በሌሎች ሀገራት የቤት ኪራይ ጭማሪ የሚደረገው ቤቱን ለማስጠገን የሚያስፈልግ ወጭ ታሳቢ ተደርጎ ከነጠላ አሀዝ ያላለፈ ጭማሪ ነው " ያሉት አቶ ቁምላቸው፣ " የኛ 11.5% ጭማሪ አነስተኛ ይመስላል፤ በዓለምአቀፍ ደረጃ ሲታይ ግን እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ ነው የተደረገው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለዛውም ለቤቶቹ ፦
- ጥገና ለማድረግ፣
- ቀለም ለመቀባት፣
- ቤት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ለማስተካከል ጭምር ነው ? ጭማሪ የተደረገው የሚለው ሳይታሰብ ለዋጋ ግሽበት ብቻ የተደረገ ጭማሪ ነው " ብለውታል።

የከተማዋ ቤቶች ልማት አስተዳደር ደግሞ፣ ጭማሪው " በጥናት የተደገፈ ፣ የነዋሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ፣ አከራዮች ወቅታዊውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ " የሚያስችል ብሎታል።

የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በሌላ በኩል፥ " የቢሮው ውሳኔ እንደ መነሻ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም፣ ማስተካከያው ይፋ መደረግ የነበረበት በግንቦትና ሚያዚያ ወር ነበር፤ በጣም የዘገየ ነው " ብሏል።

" አብዛኛው ተከራይ ከኪራይ ከተፈናቀለ፣ ከፍተኛ የኪራይ ጭማሪ ከተደረገበት በኋላ ነው ውሳኔው ይፋ የተደረገው " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተከራዮች በበኩላቸው፣ የኪራይ ጭማሪው 11.5% ሆኖ ከመወሰኑ በፊት ፦
• " ቤቴን ላድስ ነው"
• " ቤተሰብ ሊገባበት ነው " በሚል ሰበብ የተጋነነ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ቅሬታ እያቀረቡ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለዚህ ምን አይነት መፍትሄ ያስፈልጋል ? ሲል ድርጅቱን ጠይቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ፣ " የዚህ መመሪያ አንዱ ፈታኝ ነገር አፈጻጸሙ እንዴት ይሆናል ? እግር በእግር ተከታትሎ ማን ያስፈጽመዋል ? " የሚለው መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ በፊት ቤቱ ተከራይቶበት የነበረው ዋጋና አሁን ስንት እንደሚሆን ስለሚታወቅ የጭማሪው አፈጻጸም ስርዓታዊ እንዲሆን አሳስበዋል።

" ዛሬ ይፋ የሆነው ውሳኔ፣ እንዴት ይፈጸማል ? ማስፈጸሚያ ስልቱ ምንድን ነው ? የሚለው ግልጽ አይደለም " ብለው በጥናቱ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ አመልክተዋል።

" እንዲህ አይነት ጥናቶች ሲደረጉ እንደ እኛ አይነት የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችን፣ ተከራዩን፣ አከራዩን በግልጽ ማወያየት ይገባል " ብለዋል።

ጉዳዩ በአከራዮችና ተከራዮች መካከል ጭቅጭቅ እንዳያስከትል አፈጻጸሙ ለወረዳ ብቻ ሳይተው የበላይ የመንግስት አካል መከታተል አለበት ባይ ናቸው።

ከ50 እስከ 100% ኪራይ ጭማሪ እንደተደረገ፣ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦
° ባለአንድ መኝታ ቤት ከ9፣ 10 ሺሕ ተነስቶ እስከ 22 ሺሕ ብር እንደደረሰ፤
° 15፣ 16 ሺሕ ብር ሲከራይ የነበረው ባለሁለት መኝታ ቤት 28፣ 30 ሺሕ መከራየትና መጠራት እንደተጀመረ ከዚህ ቀደም ማሳወቃቸውንም አስታውሰዋል።

" አሁን የወጣው ውሳኔ ቀድሞ ባስቸኳይ ይፋ እንዲደረግ፣ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበን ነበር " ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ " ያን ካሳሰብን በኋላ ዛሬ ይፋ የሆነው ውሳኔ የዘገዬ ነው " ሲሉም ተችተዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ፣ " ዋጋ ጭማሪው እና የውል እድሳቱ መነሻ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ብቻ ነው " ሲል አስታውቋል።

የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በሌላ በኩል በሰጠን ገለጻ፣ በቤት ኪራይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች፣ የንግድ ዘርፎች ላይ እንዲሁ ተመሳሳይ የዋጋ ጣሪያ የትርፍ ህዳግ ሊወሰን ይገባል ሲል በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ስለአጠቃላይ ችግሩና መፍትሄው አክለው ምን አሉ ?

" ለቤት ኪራይ መወደድ ትልቅ ጫና የፈጠረው በኮሪደር ልማቱ በርካታ ቤቶች ፈርሰው በቂ ተጨማሪ ቤት ባለመገንባቱ በቤት ኪራይ ላይ የመጣው ጫና ነው። ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት፤ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፤ የኑሮ ውድነት አለ።

መንግስት በተለይ ለደመወዝተኛው የዋጋ ግሽበቱን ታሳቢ ያደረገ የደመወዝ ጭማሪ ሊያደርግ ይገባል። ላለው የዋጋ ግሽበት አንዱ ምክንያት የመኖሪያ ቤት እጥረት ነው። እጥረቱ በዘላቂነት ሊቀረፍ የሚችለው በተለያዩ አማራጮች መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ነው።

ሌላው ፥ በቤት ኪራይ ከፍተኛ ጭማሪ የሚያደርገው ህገወጥም፣ ህጋዊም ደላላ ነው። ከቤት ባለቤት ደውሎ 'ይህን ያህል ላከራይልህ' በማለት። ዘላቂው መፍትሄ በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን ደላላ በማስወጣት አከራዩ እና ተከራዩ የሚገናኝበትን የቴክኖሎጂ መተግበሪያ መዘርጋት ነው። 

በተያያዘ፥ ከፍተኛ የቤት ግንባታ ማድረግ፤ የሊዝ ዋጋ መቀነስ ይገባል።

የኛ ሀገር ሊዝ እነ ኒዮርክ፣ ለንደን ያስከፍሉታል ከሚባለው አያንስም በሚል ነው የሚተቸው። ስለዚህ በካሬ ሜትር የሊዝ ዋጋ መቀነስና የመሬት አቅርቦቱን ሌሎች አማራጮችን ፈልጎ መፍትሄ ማማጣት ያስፈልጋል።

ያለው ችግር የመኖሪያ ቤት ብቻ አይደለም። የንግድ ቤቶችም በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚከራዩት። በከፍተኛ ዋጋ የተከራየ ነጋዴ ባለሱቅ ያንን ዋጋ የሚጭነው ሸማቹ ላይ ነው። ሞሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሥር ያሉ ሱቆችን ቀድመው የገዙ ሰዎች የሚያከራዩበት ዋጋ ለመስማት የሚዘገንን ነው፤ ይሄ መስተካከል አለበት።

ለንግድ የኪራይ ቤቶችም ታሪፍና የዋጋ ጣሪያ ሊቀመጥ ይገባል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ " በአከራዮች ላይ በጣም ስለተጋነነ እንጅ አንዳንድ አከራዮች ደግሞ ልጆች የሚያስተምሩት ባለአንድ መኝታ ቤት ካላቸው ያን አከራይተው፣ ከከተማ ወጣ ያለ ቤት ተከራይተው ነው። የኑሮ ውድነቱ በአከራዩም በተከራዩም ስለሆነ ይህን ችግር ለመፍታት አስታራቂ መፍትሄ ያሻል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel