Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
update
የኮዲንግ ሥልጠና ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች!
በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡
የኦንላይን ስልጠናውን በተሰጡት 8 ሳምንታት ለሚያጠናቅቁ ብቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል፡፡
@DBU11
@DBU111
#Gc_2017
አንድን ዝግጅት እንዲህ ባማረ መልኩ አጠናቆ ማቅረብ ጥበብን ይጠይቃል።አንድ ሆኖ ለደስታ መናበብንም።
ለተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ።
አዘጋጆችም ክብር ይገባችኋል!
@DBU11
@DBU11
የተማሪዎች ጥያቄ ምንድነው?
👉የካፌ የምግብ ሜኑ እና የምግብ ጥራት
👉 የመመገቢያ ሰዓት ውስንነት
👉 የመግቢያ ሰዓት ማጠር
👉 የኮስትሼሪንግ ጉዳይ (በዩኒቨርሲቲው በኮሮና እና በጦርነት ምክኒያት ያልተኖሩ ዓመታት በእዳ መያዝ)
👉 ተማሪን በተመለከተ የሚወጣ እቅድን አስቀድሞ አለማሳወቅ።
(የመግቢያ፣የመውጫ እና የመመረቂያ እቅድ )
👉 የተማሪዎች ህብረት ተሳትፎና ተቀባይነት።
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች ከተማሪዎች ቀርበዋል።
@DBU11
@DBU111
#ለጨዋታ 😁😁😁😁😁
የኮሮና ወረርሽኝ እና ጦርነቶች የጫና በትሩን በልዩነት የ2013 ባች የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ያሳረፈ ይመስላል።
በዚህ ሰዓት (ዛሬ ማለትም ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም) የ 2013 ባች ጁንዬር (2014 ባች) ተማሪዎች ሲንዬሮቻቸውን(2013 ባቾችን) ቀድመው የ GC birthday ceremony እያከበሩ ይገኛሉ። 2013 ዎች ደግሞ ከጁንዬሮቻቸው በመቀጠል በሚቀጥለው ሳምንት ceremony እንደሚያደርጉ ተናግረዋል በመሆኑም ዩንቨርስቲው በዚህ አመት ሁለት ተከታታይ(2013 እና 2014)entry ዎችን ያስመርቃል ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የ2013 ባች ተማሪዎቻቸው አንድ አመት ላግ (ወደ ሗላ እንዲቀሩ) በማድረግ በዚህ አመት ያስመርቃሉ።
አዲስ አበባን ጨምሮ ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ አቻ ዩንቨርስቲዎች የክረምት ትምህርት መርሀ ግብር በማውጣት ጭምር የባከነውን የትምህርት ጊዜ በማስተካከል የሚፈለገውን የትምህርት ክፍል የትምህርት አመት በመጨረስ ማስመረቃቸው ይታወሳል።
በአዲሱ እና በተከለሰው የትምህርት ስርዓት አንድ በበፊቱ የትምህርት ስርዓት(curriculum) 3 ዓመት የሚፈጅበትን አንድ የትምህርት ክፍል ጥናት 4 ዓመት ይወስድበታል በአማራ ክልል የተፈጠረው ሁኔታ ደግሞ 2013 ባቾችን አምስት አመት ወስዶባቸዋል።
የእኛ ዩንቨርስቲ ከህግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የተነሳበትን የቅሬታ ጥያቄ መልሷል።
ሁላችሁም ሰላማችሁ ይብዛ ለፈጣን እና አስተማማኝ መረጃ daily news ን ይቀላቀሉ ሰናይ ቅዳሜ እና እሁድን ተመኝተናል።
@dbu11
@dbu111
‘’ለአከባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ማሽን ገዝቻለሁ’’ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
ደ/ብ/ዩ አዲስ የመውቂያ ማሽን በመግዛት ለዩኒቨርስቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
ዩኒቨርስቲው በ2016/17 ዓ.ም የአዝመራ መሰብሰቢ ወቅት በዋናው ግቢና አንጎለላ በሚገኘው ቴክኖሎጅ ካምፓስ በ27 ሄክታር መሬት ላይ 600 ኩንታል በላይ ይመረታል ተብሎ የሚገመተውን ስንዴና ገብስ የመሰብሰብ ስራ ያከናውነው መሆኑን ገልጦ ፣ ለዚሁ አገልግሎትና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲያገለግል በማሰብ የእህል መውቂያ ማሽን በመግዛት በትናንትናው እለት የሙከራ ስራው ተጠናቆ በዛሬው እለት መደበኛ የመውቃት ስራ እየተሰራ ይገኛል።
@DBU11
@DBU11
ሃገር አቀፍ ውድድር
የእግርኳስ እና አትሌትክስ ሃገር አቀፍ ውድድር፥ የተወዳዳሪዎች ምልመላ ዛሬ 9:00 በዩኒቨርሲቲው ዋና ስቴዲየም ይካሄዳል።
@DBU11
@DBU111
👉እስከ ነገ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ። የተማሪዎች ዲን ጽህፈት ቤት በ ቀን 04 ያወጣውን ማስታወቂያ ያላነበባችሁ። የዩንቨርስቲው መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ ሐገር አቀፍ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለሚካሔደው ስፓርታዊ ውድድር ፌስቲቫል ለመሳተፍ ማስታወቂያው ላይ በተጠቀሱት ውድድሮች ለመሳተፍ ከላይ በተያያዘላችሁ አድራሻ ተመዝገቡ።
@DBU11
@DBU111
#AD
አስደሳች ዜና ለተመራቂ ተማሪዎች !
በቅርቡ ተመራቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች Like human hair (synthetic human) በተመጣጣኝ ዋጋ ግቢያችን ድረስ ማስመጣት ጀምረናል።
Like human hair ለምርቃት፣ ለተለያዩ Photoshoots ፣ለልደት እንዲሁም ሽክ ብላችሁ መሄድ ለምትፈልጉበት ቦታ ሁሉ ዌቭ አልያም ፓይስትራ መሠራት የሚችል ምርት እኛ ጋር ታገኛላችሁ።
በ24 inch እና በ28 inch እንደምርጫችሁ
እዘዙን።
ለበለጠ መረጃ 0902994137 ይ ደ ው ሉ።
@DBU11
@DBU111
🛎 #A_Reminder
ለ አዲስ ገቢ የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ!
በዚህ ዓመት የመጀመሪያ የሆነው የኪነጥበብ ድግስ ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት የመጀመሪያ ተወዳጅ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ እየጠበቃችሁ ይገኛል፡፡
በዚህም ዝግጅት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ለነባሮች _ አስደሳች የኪነት ማዕዶችን በሙዚቃ፣ በስነ-ፅሁፍ እና በተውኔት ረድፍ ይዘን ቅዳሜ 05/04/17 ከቀኑ 8፡30 PR አዳራሽ እንጠብቃችኋለን፡፡
“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”
@dbu111
@dbu_entertainment
የዋይፋይ አገልግሎት በብልሽት ምክንያት መቋረጡን ተከትሎ ከ መረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት በማስታወቂያ የተላለፈ መልዕክት 👆👆👆👆
@dbu11
@dbu111
እንኳን ደህና መጣችሁ
በዚህ ዓመት የመጀመሪያ የሆነው የኪነጥበብ ድግስ
[በሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን]
ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት የመጀመሪያ ተወዳጅ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ እየጠበቃችሁ ይገኛል፡፡በዚህም ዝግጅት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ለነባሮች _ አስደሳች የኪነት ማዕዶችን በሙዚቃ፣ በስነ-ፅሁፍ እና በተውኔት ረድፍ ይዘን ቅዳሜ 05/04/17 ከቀኑ 8፡30 PR አዳራሽ እንጠብቃችኋለን፡፡
“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”
የካፌ ጭማሬ በጀት
በተማሪዎች ምገባ ላይ የተደረገዉ ማሻሻያ ለአንድ ተማሪ በቀን ከሚያስፈልግ ወጪ ጋር የሚመጣጠን እንዳልሆነ መነሃሪያ ሬድዮ ያነጋገራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ገልፀዋል።
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው መልካሙ ለመነሃሪያ ሬድዮ እንደገለፁት ከሆነ "በነበረው የምግብ ሜኑ ወይም ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሚጨምር ነገር አይኖርም በማለት ከ22 ብር ወደ 1 መቶ ብር ከፍ ማለቱ መልካም ምላሽ ቢሆንም አሁንም ካለው የገበያ ንረት አንጻር በቂ በጀት አይደለም" ሲሉም ገልፀዋል።
በተጨማሪም አቶ አለምነው ለሬድዮ ቃለመጠይቁ እንደገለፁት ይህ ውሳኔ ከመጪው ጥር ወር 2017 ዓም ጀምሮ ተማሪዎችን ለመመገብ የማንችልበት አቅም ላይ እንደርስ የነበረውን ሊያረጋጋ የሚችል ውሳኔ እንጂ በአቅርቦትና በምግብ ሜኑ ላይ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይታሰብም ብለዋል።
@DBU11
@DBU111
በዛሬው ዕለት ዓለም አቀፍ የጸረ ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ቀን በግቢያችን ተከብሯል።
ይህ ቀን በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመከላከልና ግንዛቤ ለመፍጠር በማሰብ የሚከበር ነው።
የ16 ቀን የፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ "የሴቷ ጥቃት የእኔም ጥቃት ነው ፤ ዝም አልልም'' በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል ።
በመድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አዲስ አስፋወሰን ውይይት አካሂደዋል ።
በውይይቱም አካል ጉዳተኞችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት ማምጣት አለብን የሚል ሀሳብ ተነስቷል ።
በተጨማሪም የሴቶችን ጥቃት በተመለከተ በአገራችን የወጡ ህጎች በአግባቡ አለመፈፀም አልያም ቸል ማለት፣ ጉዳዩን ለመተግበር አስፈላጊ የሆነ የበጀት ምደባ አለመኖር እና በማህበረሰብ ተፅዕኖ ጥቃቶች ወደ ህግ ባለመቅረባቸው ጥቃቶች እንዲስፋፉና በታሰበው ልክ መቆጣጠር እንዳይቻል ማድረጉን ከተማሪዎች ጋር በተደረገው ውይይት ተጠቁሟል።
በመጨረሻም ሴቶችን መጠበቅ የሆነ አካል ሃላፊነት ሳይሆን የእያንዳንዳችን ስራ መሆኑን አፅንኦት ተሰቷል።
ዝግጅቱን ሆሄ ተስፋ ኪነጥበብ ቡድን ከሴት ተማሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ፕሮግራሙን ደማቅ አድርገውታል።
@dbu11
@dbu111
ማስታወቂያ
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሰቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
በተለያዬ ምክንያት non-cafe ላመለጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የምናካሂደው ከታህሳስ 1/2017 እስከ ታህሳስ 04/2017 ድረስ ብቻ መሆኑ ታውቆ ለምዝገባ ስትመጡ
1.የተመዘገባችሁበትን ስሊፕ
2.ዩኒቨርስቲው የሰጣችሁን መታወቂያ
3.የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ኮፒ ሲሆን ፡ NG; Fx ያለባችሁ ተማሪዎች ደግሞ ግሬድ ሪፖርት በመያዝ በተጠቀሰው ቀን እንድትመዘገቡ በማለት እናሳስባለን፡፡
👉 ማሳሰቢያ
📍የምዝገባው ሰዓት ጠዋት ከ3፡00-5፡00 ከሰዓት 8፡00-10፡00 ብቻ፡
📍የምዝገባ ቦታ በመግቢያ በር ቲክ ማድረጊያ ቦታ፡፡
📍ምዝገባው በአካል መቅረብን ይጠይቃል፡፡
@dbu11
@dbu111
ማስታወቂያ
ለደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ
ሰኞ በ30/3/2017ዓ/ም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ አለማቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን የኤች አይቪ ኤድስ ቀን እና የአካል ጉዳተኞች ቀን ይከበራል፡፡
በመሆኑም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በ PR አዳራሽ በመገኘት የፕሮግራሙ ታዳሚ እንትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
በዕለቱ ልዩልዩ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች
ይቀርባሉ፡፡
ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ
@DBU11
@DBU111
@DBU_ENTERTAINMENT
#Gc_2017
አንድን ዝግጅት እንዲህ ባማረ መልኩ አጠናቆ ማቅረብ ጥበብን ይጠይቃል።አንድ ሆኖ ለደስታ መናበብንም።
ለተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ።
አዘጋጆችም ክብር ይገባችኋል!
የዝግጅቱ ቪዲዮ ከላይ ተያዟል
@DBU11
@DBU11
የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ይዘን የወጣነው የአገልግሎት ጥያቄ በትላንትናው እለት በቂ ምላሽ አላገኘንም በማለት በዛሬው እለት ቀጥሎ በይፋ የተካሔደ ሲሆን የዞን እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኮማንድ ፖስት አመራሮች ጨምሮ የፀጥታ አካላት በተገኙበት የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራር አቶ አለባቸው እና የተለያዩ የስራ ክፍል ሓላፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ቅሬታ ከተነሳበት ከትላንትናው መልስ የተሻለ ምላሽ ሰጥተዋል።
የተነሱት ጥያቄዎች ትላንት daily news የዘገባቸው ሲሆን ዛሬ ደግሞ አዩ ዘሐበሻ በቴሌግራም ገፁ አስነብቧቸዋል daily news የተለያዩ የግል ሚድያዎችም ሽፋን እንደሰጧቸው ተመልክቷል።
የዩንቨርስቲው የስራ ክፍል ሐላፊዎች (አመራሮች) በሰጡት ምላሽ
1. ከምግብ ሜኑ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ከትምህርት ሚንስተር የተላከው የምግብ ሜኑ ይተገበራል።
2. የዋይፋይ አገልግሎትን በተመለከት ለአገልግሎት የተዘጋጁትን ነገር ግን የማይሰሩ የዋይፋ ሮውተር ሞደሞችን እናስተካክላለን ነገር ግን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የውል ሒደት ላይ ስለሆንን በትንሽ ጊዜያቶች በየብሎኮች የዋይፋይ አገልግሎት ያለ እንከን ታገኛላችሁ።
3 .ከመብራት ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት በሀይል መቆራረጥ ምክንያት ዳታ ሴንተሩ ተቃጥሎብናል( ለችግር ምክንያት የሆነ ጥፋት አጥፍቶብናል )ነገር ግን በቅርቡ ይስተካከላል። የመንገድ ዳር መብራቶችም ይስተካከላሉ።
4.በህክምና አገልግሎት የተነሱት ጥያቄዎችም ግዴታ ክሊኒክ መስጠት ያለበትን አገልጎሎት ይሰጣል ከአቅሙ በላይ ከሆነ መድሐኒት አቅርቦቱም ከሌለው ሪፈር ያደረጋል ሰራተኞችም በዲስፕሊን አገልግሎት ይሰጣሉ ይህ እንዲሆን እንከታተላለን።
5 . የግቢው አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞችም ሰነ ምግባር በተሞላበት መልኩ ይሰራሉ።
6. የወጭ መጋራት ጋር በተገናኘ ለሚመለከታቸው ሓላፊዎች ጥያቄ ልከናል እየተነጋገሩበት ነው መልስ ነገ ይዘው ይመጣሉ። ኢንተርንሽፕ ግን ትምህርት ክፍሉ የትምህርት ስርዓቱ የሚያዘውን መተግበር ግዴታ አለበት ተፈፃሚ ይሆናል።
7.የመመገቢያ እና መግቢያ ሰዓት ተነጋግረን እናንተን በሚጠቅማችሁ መልኩ ለውጥ የሚኖረው ከሆነ እናያለን።
8. ላውንጅ እና ሱቅ ከዋጋ ማጭበርበር እና ጥራት የእናንተን ጥቆማ እና መረጃ አድርሱን እንጅ የምንወስደውን እርምጃ እንወስዳለን።
9. calendar issue በዩንቨርስቲያችን ሶስት አይነት ካላንደር አለ የተፈጠረውም ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት ነው የሆነው ሆኗል ወደፊት የሚሆነው ግን መሆን ያለበት ይሆናል።
የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ከምንም በላይ ግን ጥያቄያችሁን አንድም ጥፋት ሳታጠፉ በዚህ መልኩ በማቅረባችሁ እናመሰግናለን ኮርቸባችሗለሁ ነው ያሉት።
ተማሪዎችም ይኽንን በተግባር አውርዳችሁ አሳዩን ካልሆነ ግን ጥያቄያችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።
@DBU11
@DBU111
በዛሬው እለት የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በዩንቨርስቲያቸው ገጠመን ባሉት የአገልግሎት ችግር ጥያቄ አነሱ።
በዚህም የፀጥታ አካላት እና የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው መልካሙ ተማሪዎችን ቀርበው አነጋግረዋል።
የፀጥታ አካላትን እና የዩንቨርስቲው የስራ ክፍል ሓላፊዎችን ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ ለመስማት እና ለመቀበል ስለመጣችሁ በማለት ምስጋናቸውን አድርሰው ተማሪዎቹ በዋናነት ሲያነሱት የነበረው የአግልግሎት ችግር
👉1. ከምግብ (ካፌ) አገልግሎት ጋር ተያይዞ ነው ። በዚህም ከትምህርት ሚንስተር ለዩንቨርስቲዎች ተሻሽሎ የተላከው የምግብ ሜኑ ተግባራዊ ይሁን(ይሻሻል)።
# የመመገቢያ አዳራሹ(ካፌ) ወንበሮች እና የመመገቢያ (ዕቃ) ሳህኖች ንፅህና ይጠበቅ።
# የራት መመገቢያ ሰዓት ይሻሻል።
ሲሆን ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ ደግሞ ፡-
2. ቢያንስ በዋና ዋና መንገዶች የምሽት መብራት ይስተካከል ቀን ላይ በፕሮጀክተር ለመማር በመብራት መቆራረጥ ስለተቸገርን አማራጮች ይመቻቹ።
3 . የምግብ ግዥ እና ዝግጅት ላይ የተማሪ ተወካይ ይሳተፍ ።
4.የወጭ መጋራት ሒሳብ በዩንቨርስቲ ቆይታችን ልክ እንዲሰላ ።
4. የዋይፋይ አገልግሎት ይስተካከል እንዲሁም
5. የጥር ተፈታኞች የመመረቂያ ጊዜ በይፋ (በግልፅ) ይነገረን መሰል ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ጥያቄዎቹን ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የነበሩ ሲሆኑ daily newsም በቀደሙት ዜናዎቹ ዘግቧቸው ነበር።
የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው ጥያቄያችሁን ስነ ስርዓት በጠበቀ መልኩ ጠይቁ እኔም ስራዬን (ሀላፊነቴን) በመወጣት መልኩ እሰራለሁ።
# ፍላጎቴም ስራየም የእናንተን ምቹ የትምህርት አካባቢ መፍጠር ነው እንጅ ሌላ ጉዳይ የለኝም።
👉 የምግብ ሜኑን በተመለከተ የተጠቀምኩት ከተላከልን የሜኑ መስፈረት በጀቱ የሚፈቅድልንን ዝቅተኛውን ሬሾ ነው።
አካባቢው የሚፈቅደውን የግብዓት ግዥም ከግምት አስገብተን እንሰራለን መተግበር የምንችለውን እንተገብራለን ብለው የመለሱ ሲሆን በዛው ቅፅበት ብዙሀኑ ተማሪ ስብሰባውን አቋርጦ ወጥቷል። ነገር ግን ዲኑ ከጥቂት ተማሪዎችጋ ተጨማሪ ነገሮችንም ለመነጋገር ሞክረዋል።
@dbu11
@dbu111
የፈጠራ ሀሳብ ላላችሁ አዲስ ሀሳብ ማሳደግ ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ:- የ ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ፣ኢንኩቤሽን እና ሽግግር ማእከል ባስተላለፈው ማስታወቂያ ideal hub ን በመቀላቀል ሀሳባችሁን ወደተግባር ለመለወጥ እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ።
ለመመዝገብ👉 @DBU_ideal_bot
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት👉
/channel/Ideal_hub
ሁለቱንም ስትሪሞች ማለትም ማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ከ አዲስ ገቢ እስከ መጨረሻ አመት ተማሪዎችን በሙሉ ያካትታል።
@DBU11
@DBU11
#AD
ያኪን ሜካፕ እና ጥፍር
ፕሮግራም አለቦዎት🤔? እንግዲያውስ ወደኛ ዘንድ ብቅ ይበሉና አምረው ተውበው ይመለሳሉ..
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
➟ Makeup 💄 ➟ Gel polish 🧫
➟ Nalis💅 ➟ Aclyric 🎀
➟ Pedicure🦶
በስራችን እጅጉን ይደሰታሉ 👌
➫For Wedding 👰
➫For Birthday 🎂
➫For Bridal 🧝♀️
➫ For any programs
ለግቢ ተማሪዎች ብቻ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድረገናል። ሳያመልጦ በእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ‼️
Location :-📍ደ/ብርሃን ሆስፒታል ፊት ለፊት
(የድሮ መናኸሪያ) ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ
ለበለጠ መረጃ ☎️ 0907445803
☎️ 0902516515 ይደውሉልን
ጥብቅ ማሳሰቢያ
የማሻሻያ ትምህርት (Remidial) ተምሪዎችን ጥሪ በተመለከተ በተለያዩ መንገዶች እየተላለፈ ያለው ጥሪ ሃሰተኛ መሆኑንና ፤ጥሪው ሲካሄድ ዩኒቨርሲቲው በራሱ የመረጃ ገፆች እንደሚያሳውቅ አውቃችሁ ጥሪውን በትዕግስት እንድትጠባበቁ ዩኒቨርሲቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።
@DBU11
@DBU111
ለሁሉም 2017ዓ.ም ሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ:-
ውድ የግቢያችን የሰኔ 2017 ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ እያልን ቅዳሜ ማለትም በ12/04/2017 ዓ.ም GC BIRTHDAY የሚከበርበት የማይደገም ቀን ስለሆነ በእለቱ ላይ በሚኖረው ፕሮግራም ላይ ሁላችሁም ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናስተላልፋለን ።
በፕሮግራሙ አግባብ ያለው የሾው ውድድር እና የፎቶ ፕሮግራም ይኖራል::
በተጨማሪ በዲፓርትመንቶች መካከል ውድድሮች ስለሚኖሩ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን።
⚠️ማሳሰቢያ:- እዚህ ፕሮግራም ላይ የሚለበሰውን ተመሳሳይ ልብስ ለማሰራት ከየዲፓርትመንቱ የተወከሉ ተማሪዎች ስላሉ እስከ ማክሰኞ 6:00 ሰአት ድረስ 250 ብር ገቢ እንድታደርጉላቸው እናሳስባለን።
አዘጋጅ:- ተመራቂ ተማሪዎች
@DBU11
@DBU111
በዛሬው ዕለት የሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድን የዓመቱ የመጀመሪያ መድረኩን በደማቅ ሁኔታ አቅርቦ ዋለ።
የግቢያችን ብቸኛው የኪነጥበብ ቡድን ሆሄ ተስፋ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ፥ ለነባር ተማሪዎች ደግሞ የዓመቱ የመጀምሪያውን መርሀ ግብር አሰናድቶ መጨረሱን ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም ግጥም፥ ሙዚቃ፥ ተውኔት እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን በአስደሳች መልኩ አቅርቧል።
ለአዲስ ገቢ አባላትም ምዝገባ መጀመሩን ያሳወረ ሲሆን በተለይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዛሬ 5/04/2017 ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ግልጿል።
@dbu11
በሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ተመሳሳይ የምግብ ሜኑ እንደሚኖር ትምህርት ሚንስቴር ማስታወቁን daily news ገልፆ የነበረ ሲሆን በቀን 3/04/2017 ለሁሉም ዩንቨርስቲዎች በላከው ደብዳቤ ዝቅተኛውን መስፈርት መሰረት በማድረግ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ከምግብ ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ ልኳል።
ትምህርት ሚንስቴር በ 03 ገፅ አባሪ አድርጎ የላከውን ዝርዝር የደብዳቤ መግለጫ እና የምግብ ሜኑ ዝርዝር ከላይ ማየት ትችላላችሁ።
@dbu11
@dbu111
የ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሴት ተማሪዎች ማህበር አዳዲስ አባላትን
እየተቀበለ መሆኑን ያውቃሉ ???
ማህበራችን በቀደሙት አመታት ሴት ተማሪዎቻችን በ አካዳሚክ ፣
በኢኮኖሚክ ፣ በ ፀረ -ፆታዊ ጥቃት እና
በዐ~ፕላን የውይይት ስራዎች ላይ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን አንቺም በዩኒቨርሲቲ
ቆይታሽ በዚህ መሰል የበጎ ~አድራጎት ስራዎች ላይ መሳተፍ የምትፈልጊ ከሆነ ከቀን ዐ2 /04/2017 እ ስ ከ 04/04/2017 ዓ.ም ድረስመመዝገብ የምትችይ መሆኑን እንገልፃለን ።
መመዝገቢያ ሰዓት: በ ስ ራ ሰ ዓ ት
መመዝገቢያ ቦታ: አስተዳደር ህ ን ፃ G+2 ቢሮ ቁጥር 38
በአገልግሎታችሁ ዘመን ማብቂያ ላይ የዕውቅና ሰርተፍኬት ይኖራል!!!
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ እና የሴት ተማሪዎች ማህበር
@dbu11
@dbu111
ደግሞ ሌላ ቅናሽ (AD)
ህትመት ዲዛይንን ጨምሮ
ከ150 ብር- 500 ብር ብቻ
ጥራታቸውን የጠበቁ የቲሸርት እና ሌሎች የህትመት ስራዎችን ለተማሪዎች በልዩ ቅናሽ ይዘን ቀርበናል።
በተለያዩ የቲሸርት አይነቶች፣በተለያዩ የህትመት ኳሊቲዎች ከነፃ የዲዛይን ስራዎች ጋር ለእናንተ ውድ ተማሪዎች አቀረብን
ሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ
ለበለጠ መረጃ
0940219376
Telegram @shikret07
@natiTg2
አድራሻ
ደብረብርሃን ከተማ ከስላሴ ቤተክርስቲያን ቀጥሎ ያለው አዲሱ ህንፃ(ከቤዛ ዳቦ ቤት ከላይ) 1ኛ ፎቅ ላይ ያገኙታል
መብራት ከጠፋ 3 ቀን
አስራት ወልደየስ ጤና ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎች መብራት ጠፍቶብናል። ጄኔሬተር እስከ ምሽት 4 ሰዓት ብቻ ነው የሚሰራው። ያለብንን የጥናት ስፋት መሸፈን አልቻልንም በማለት ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
መፍትሔ መስጠት የሚችል አካል አለሁ ይበላቸው።
@DBU11
@DBU111
ከዚህ በሗላ በሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የተጋነነ የምግብ ሜኑ ልዩነት ላንመለከት እንችላለን።በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን Tikvah-Ethiopia በቴሌግራም ገፁ ዘግቦታል።
ከዚህ ቀደም የነበረው እለታዊ የነፍስ ወከፍ የተማሪዎች የምግብ ወጭ 22 ብር የነበረ ሲሆን በተደረገው ማሻሻያ 100 ብር መግባቱን ተከትሎ በሑሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የሚቀርበው የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ መሆን እንዳለበት ትምህርት ሚንስቴር አስቷውቋል።
በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።
@dbu11
@dbu111
#AD
መቶ ብር በ25 ብር እየተሸጠ ነው
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ25 ብር አዲስ ሲም ካርድ ሲያወጡ የ100 ብር የአየር ሰዓት እና 500mb ኢንተርኔት ዳታ ከ500 ደቂቃ የድምፅ ጥሪ ፓኬጅ ጋር ይመረቅላችኋል ብሏል።
ይህንን አገልግሎት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ለማግኘት
0936370157
0714935861
እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ።
@DBU11
@DBU111
በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ መደረጉን ለትምህርት ሚንስቴር ከተላከው ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።በማሻሻያውም ከ22 ብር ወደ 100ብር አድጓል‼️
ለትምህርት ሚኒስቴር በተፃፈው ደብዳቤ
"የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።"ተብሏል።
@DBU11
@DBU111