የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባዔ በመጥራት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።
ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንናና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስርና ወከባ በፅኑ አውግዟል።
ዛሬ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ ሕገ ወጥ ድርጊት መፈፀሙን የገለፀው ቅዱስ ሲኖዶስ፤የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ቤተክርስቲያን ፍጹም ታወግዛለች ብሏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26/2015 ዓ/ም ካስተላለፈው ውሳኔና ከሰጠው መግለጫ ጋር ተያይዞ ዛሬ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል(ከላይ ተያይዟል)።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪዎቹ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።
በየካቲት 5/2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር/የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤በማጀብ በዝማሬና በምህላ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወስኗል፡፡
@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ በነገው ዕለት(ሰኞ መስከረም 24፣2014) በሚካሄደው የመንግሥት ምሥረታ መርኃ ግብር ምክንያት የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የመንግሥት ምስረታ መርኃግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ኾነው እንደሚቆዩ ተናግሯል፡፡
1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተክርስትያን
19. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲአፍሪክ ሆቴል
20. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
21. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
22. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
23. ጎርጎሪዮስ አደባባይ መስከረም 24 ቀን 2014 ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ።
መርኃ ግብሩ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2014 ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫዎች ግራና ቀኝ ለአጭር ጊዜም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መኾኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡
እንግዶች በአጀብም ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ኅብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
@Dire_Tube_News
@Dire_Tube_News
በአዋሽ አርባ ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ወታደሮች ተመረቁ!
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በአዋሽ አርባ ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ወታደሮችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡ ተመራቂዎቹ በአዋሽ አርባ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት እና በአዋሽ ጥምር ጦር አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡
Via EBC
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የሱዳን መንግስት ጦር መምዘዙን አቁሞ ከኢትጵያ ጋር በሰላማዊ መንገድ እንዲደራደር የአገሪቱ ምሁራን ጠየቁ፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት ሱዳዉያን ምሁራን፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በቀላሉ የሚለያዩ ባለመሆናቸዉ መንግስታቸዉ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ግፊት እንደሚያደርጉም አስታዉቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ እና የሱዳን ዉጥረት መነሻዉ ምን ይሆን? የሱዳን ህዝብ ፍላጎትስ ምንድነዉ? ስንል ከሱዳናዉያን ምሁራን ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
ዶክተር ኦማር ላሚን አህመድ በሱዳን ዩንቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪ ናቸዉ፡፡
እርሳቸዉ ዘመናትን ስላስቆጠረዉ ስለ ኢትዮጵያና ሱዳን ቤተሰባዊ ግንኙነት አንስተዉ የድንበር ዉዝግቡ የሁለቱ አገራት ፍላጎት ሳይሆን የቅኝ ዘመን ርዝራዦች ፍላጎትና ሃሳብ ነዉ ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ዉዝግባቸዉን በአፈ ሙዝ ሳይሆን የሁለቱን አገራት ህዝብ በማቀራረብ የዲፕሎማሲ ስራን በመስራት ነዉ የሚሉት ሱዳናዊ ምሁር፤ ለዚህም የሁለቱ አገራት መሪዎች የህዝቡን ፍላጎት ማዳመጥ አለባቸዉ ነዉ ያሉት፡፡
ከድንበር ዉዝግቡ ባለፈ ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያልተገባ ጥያቄ እንደምተነሳ ይታወቃል፡፡
ለመሆኑ ግድቡ የሁለቱ አገራት መጨቃጨቂያ መሆን ነበረበት ስንል ዶክተር ኦማር ላሚንን የጠየቅን ሲሆን፤ ሁለቱም አገራት በቂ ዉሃ አላቸዉ፤ ግድቡ የልማት እንጅ የልዩነት አጀንዳ ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡
ሌላኛዉ የሱዳን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አብዱ ኦስማን በበኩላቸዉ፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እና ሱዳን ጦር እንዲማዘዙ እንቅልፋቸዉን አጥተዉ ትርፋቸዉን ለማጋበስ የሚጠባበቁ ሃይሎች ስለመኖራቸዉ አንስተዉ፤ በዚህም ሁለቱ አገራት የእነዚህ መጠቀሚ መሳሪያ እንዳይሆኑ ብልህ ሊሆኑ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡
መንግስት ለመንግስት ከሚደረገዉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በተጨማሪ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር እንደሚገባ ያሳሰቡት ሱዳናዊ ፕሮፌሰር አብዶ ኦማር፣ ለዚህ ደግሞ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሱዳን በቀላሉ የሚለያዩ አይደሉም የሚሉት እነዚህ የሱዳን ዩንቨርሲቲ ምሁራን፤ ይልቁንም ሁለቱ አገራት ጦር እንዲማዘዙ አሰፍስፈዉ የሚጠባበቁ ሃይሎችን ምኞት በጋራ ማምከን ይገባል ብለዋል፡፡
የህዳሴ ግድቡም ሆነ የድንበር ጥያቄዉ በሃይል የሚመለስ አይደለም ያሉት ምሁራኑ፣ የሱዳን ህዝብ ከኢዮትጵያ ወገኑ ጋር ወደ ግጭት መግባት አይፈልግም፤ ስለዚህ የሱዳን ባለስልጣናት በሌሎች ሃይሎች መገፋታቸዉን ትተዉ የህዝባቸዉን ስሜት እንዲያዳምጡ ግፊት እንደሚያደርጉም አስታዉቀዋል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ታሊባን ፓንጅሺርን መያዙን አስታወቀ!
የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ቡድኑ የፓንጅሺርን ግዛት ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩን አስትውቀዋል።ቃል አቀባዩ አያይዝውም የ አፍጋኒስታን መልሶ ግንባታ ላይ ዓለም አቀፉ ማህብርስብ ድጋፍ እንዲያድርግም ጠይቀዋል።የሃገሪቱ ሁኔታ ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ እንዲመልስ እንዲሁም ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ጥረት እንድሚያደርጉም ገልፀዋል።
Asham
የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡
ጳጉሜ 01 የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡ሁሉም በያለበት ሆኖ ለሁለት ደቂቃ "ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤እዘምራለሁ " በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረግ እያከበረ ይገኛል፡፡
በመስቀል አደባባይ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጀነራሎች እና በርካታ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ እና ራሱን ብቻ ከሌሎች ነጥሎ የሚወድ ስግብግብ ቡድን መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታል፡፡
ይህን ፈተና ለማለፍ ብልሃት፣ አንድነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ባለፉት ወራቶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች አሁንም ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አይተናል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን አስቦ እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ከሱዳን በመግባት የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ የሞከረ “ቅጥረኛ” ኃይል መደምሰሱ ተገለጸ
መከላከያ በወሰደው እርምጃ “50 የሽብር ቡድን አባላት መደምሰሱንና ከ70 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰሉን” መግለጫው ጠቅሷል
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮጵያ በአልጀርስ ያለው ኤምባሲዋ ቢዘጋም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ ተገለፀ፡፡
ኢትዮጵያ በአልጀርስ ያለው ኤምባሲዋ ቢዘጋም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ፡፡
ኤምባሲው የሚዘጋው በሪፎርምና ከኮቪድ _19 ጋር በተገናኘ እንደሆነ ቢነገርም፤ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሠው በፋይናንስ ዕጥረት መሆኑን አሻም ዘግባለች፡፡
@Dire_Tube_news
“ሸኔ” በምእራብ ወለጋ ዞን 10 ሰዎችን ማገቱን መንግስት አስታወቀ
ባንክ እና ፍርድ ቤትን ጨምሮ ከ34 በላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይም ዝርፊያ ፈጽሟል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የፈረጀው “ሸኔ” በምእራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ በፈፀመው ጥቃት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን መንግስት አስታወቀ።
የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቡላ ደመረ በወረዳው “ሸኔ” በፈጸመው ጥቃት የንጹሃን የተገደሉ ሲሆን፣ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘርፈው በእሳት ተቃጥለዋል ማለታቸውን ኢዜአ በአፋን ኦሮሞ ገጽ አስነብቧል።
“በጥቃቱ ሸኔ 10 ሰዎችን አግቶ ወስዷል” ያሉት አቶ ቡላ ደመረ፤ 24 ንጹሃን ዜጎችን መግደሉንም አስታውቀዋል።
ቡድኑ የወረዳውን ፍርድ ቤት እና የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሙሉ በሙሉ በእሳት ማጋየቱን በመጥቀስ፤ 4 የመንግስት አመራሮች መኖሪያ ቤቶችንም አቃጥሏል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆንዳላ ቅርንጫፍን አንዲሁም በ34 የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን ያስታወቁት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ በወረዳው የሚገኝ የ2ኛ ደረጃ ትምህት ቤት ንብረት እና የተማሪዎችን ማስረጃ ማውደሙንም ተናግረዋል።
የ“ሸኔ” ታጣቂዎች በአጠቃላይ በወረዳው ከነሃሴ 9፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በፈጸሙት ጥቃት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቡላ ደመረ ገልጸዋል።
“ህብረተሰቡ የሸኔ የሽብር ብድን የጥፋት ተግባርን ተረድቶ በአንድነት በመሆን የቡድኑን የጠላትነት ተግባር ሊያጋልጥ ይገባል” ሲሉም ዋና አስተዳዳው ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን የኢ-ቪዛ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል። ኢ-ቪዛዎን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
www.evisa.gov.et
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ኤርትራ አስታወቀች
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደሚደግፍ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሚያወግዝ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር አስታወቀ፡፡
የግንባሩ ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ ይህን ያስታወቁት የኤርትራ አብዮትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው፡፡
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በምትከተለው የተዛባ ፖሊሲ እና በምታደርገው ጣልቃ ገብነት ምክንያት የቀጣናው ሀገራት በግጭት መታመሳቸውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡
ሀገራቸው ኤርትራ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበለው አረጋግጠዋል፡፡
"የአፍሪካ ቀንድን ለመበታተን ይፈልጋሉ፤ በሶማሊያ ያደረጉትን እና ዛሬም በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለውን ተመልከቱ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ምን ያገባቸዋል፤ ይህ የውስጥ ጉዳይ አይደለምን?" ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
አሜሪካ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ያለችው አሸባሪው ህወሓትን ዳግም ወደስልጣን ለማምጣት ያላትን ፍላጎት ስለማይቀበሉ ነው በማለት ይመልሳሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሚፈጠር አለመረጋጋት በጥቅሉ በቀጣናው ሰላም ላይ በተለይ ደግሞ በኤርትራ ሰላም ላይ ቀጥተኛ ስጋት ይደቅናል ነው ያሉት፡፡
የአሜሪካ አጀንዳ የአፍሪካ ቀንድን መበታተን ነው፤ የእኛ ምርጫ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ ጋር በትብብር በመስራት ሰላምን ማረጋገጥ ነው ብለዋል የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት ልትሰጥ ነው፡፡
ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ድረስ ለ22 ሚሊዮን ዜጎች ኮሮና ቫይረስ ክትባት ልትሰጥ መሆኗን አስታውቃለች፡፡የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ 20 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ለመከተብ ታቅዷል ብለዋል፡፡እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ 2.4 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎቿን የከተበች ሲሆን በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት 22 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች እስከ 2021 ድረስ ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ እስከ 10ሺህ ያህል ዜጎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 308ሺህ 134 የደረሰ ሲሆን 276 ሺህ 842 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።እንደዚሁም 4 ሺህ 675 ያህል ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡
Via Ethio FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማዔል ኡመር ጌሌህ ጋር ዛሬ በስልክ እንደተወያዩ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የሁለቱ መሪዎች የስልክ ውይይት በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጠነ እንደነበር ኢምባሲው ገልጧል።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከፍ እንዲል ተወሰነ!
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ ስርጭት ለመቀነስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል፡፡
ስለሆነም እ.ኤ.አ ከመስከረም 1 ቀን 2021 ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበሰቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲያስቀመጡ የሚገደዱትን የመጠባበቂያ መጠን ከነበረበት 5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡
ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡
በባንኮች በኩል የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀም ላይም ማሻሻያ እንደተደረገ ብሔራዊ ባንክ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
Via EBC
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ለሽያጭ የቀረቡ አሻንጉሊቶች
ያሎትን አሻንጉሊቶች እንዲሁም የህፃናት መገልገያዎች እንገዛዎታለን
......
አኩኩሉ አዳዲስ እና ያገለገሉ የህፃናት እቃዎች ገዢ እና ሻጭ
በቴሌግራም አድራሻችን /channel/akukulu_kids_store
ወይም በስልክ ቁጥር
+251 921895986// +251 909536339 ደውለው ያሳውቁን።
መተከል ዞን ግድያው ቀጥሏል።
ትላንት በዚሁ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 5 የጸጥታ ኃይሎች እና 1 የቻይና ዜጋ በታጣቂዎች ተገድለዋል።
ይህንንም ግድያ የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።
ትላንት አመሻሽ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ፤ በመንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ አንድ ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ መገደላቸውን ቢሮው ገልጿል።
በትላንቱ ጥቃቱ የተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች፤ አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል እና አራት የፌደራል ፖሊሶች ናቸው። ከእነርሱ በተጨማሪ ሁለት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ የመንገድ ሰራተኞች ፤ ከግልገል በለስ ወደ ጉባ በሚወስደው የ70 ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ እንደነበር የክልሉ ሰላም ግንባትና ፀጥታ ቢሮ አሳውቋል።
የግልገል በለስ – ጉባ መንገድ ከአዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ፣ አንጅባራ እና ቻግኒ አድርጎ ወደ ህዳሴው ግድብ የሚወስድ ዋነኛ መንገድ ነው።
Credit : www.ethiopiainsider.com
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርገው ድርድር ቱርክን እምነት እንደምትጥልባት አስታወቀች፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትናንትናዉ እለት እንዳስታወቁት ሀገራቸው ከቱርክ ጋር የነበራትን ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የምትፈልግ መሆኗን እና ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞም ከኢትዮጵያ ጋር በትጥቅ ግጭት ውስጥ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሜህ ሽክሪ ከብሉምበርግ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግብፅ “ከአንካራ ጋር መደበኛ ግንኙነቷን ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ” እና ፈጣን እርምጃዎችን ለማግኘት ጓጉታ የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ሥራ መሰራት አለበት ብለዋል።
በቱርክ ዋና ከተማ እየተካሄደ ባለው የሁለተኛ ዙር ውይይቶች “አሁንም ውጤቱን መገምገም አለብን” ብለዋል።
ግብፅ ያልተፈቱ ጉዳዮች እንዲፈቱ ለተጨማሪ እድገት በሩ ክፍት ይሆናል ብለዋል ሽክሪ።
ቱርክ ለሙስሊም ወንድማማቾች ህብርት ድጋፍ ታደረጋለች በሚል ቅራኒ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይባስ ብሎም ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሙርሲ በ 2013 በወታደራዊ ሀይል ከሥልጣን መውረድ ጋር ተያይዞም ግንኙነታቸው ተዳክሟል።
ቱርክ ትሪፖሊ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘውን የሊቢያ መንግሥት ስትደግፍ ፣ ግብፅ ደግሞ በምሥራቃዊው ኃያል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራውን ትደግፋለች።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኅዳር ወር መመረጣቸውን ተከትሎ ሁለቱ አገራት በክልሉ ውስጥ ያለውን የሀይል ሚዛን ለመከፋፈል እየተገፋፉ ነው፡፡
የዓባይ ግድብን በተመለከተም ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ላይ ግብፅ ለድርድር ቁርጠኛ መሆኗን እና ከማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ግጭት ለመራቅ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።
የግብፅ ባለሥልጣናት ቀደም ሲል ሁሉም አማራጮች ክፍት እንደሆኑ ተናግረው ነበር ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።
እንዲሁም የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤልሲሲ የውሃ ድርሻ ለሀገራቸው የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን እና ሊታለፍ የማይችል “ቀይ መስመር” ነው ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ሱዳን አጓጉዟል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ከአውነት የራቀ ነው፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን ህገ ወጥ የጦር መሰሪያ ወደ ሱዳን ጭኖ ማስገባቱንና በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች መያዙን በሱዳኑ ዜና አገልግሎት የተሰራጨው ዘገባ ከአውነት የራቀ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ያጓጓዘው የአደን የጦር መሳሪያ ህጋዊና በአየር መንገዱ የንግድ ትራንስፖርት አስፋላጊውን ህጋዊ ሰነዶችን ያሟላ መሆኑን ገልጿል፡፡
የአደን የጦር መሳሪያውን ወደ ሱዳን ለማጓጓዝ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍቃድ ማግኘቱንም ነው አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡
የአደን የጦር መሳሪያ ጭነቱ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ለረጅም ጊዜ ተይዞ አስፋላጊው የማጣራት ስራ ሲሰራ መቆየቱንና የማስረከቡ ሂደትም በመጓተቱ በሱዳን የአድን የጦር መሳሪያዎቹን ያስጫነው ድርጅት በሱዳን ፍርድ ቤት አየር መንገዱን በመክሰስ መሳሪዎቹን እንዲያስርክበው ወይም 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ካሳ እንዲከፈለው መጠየቁንም አየር መንገዱ አመልክቷል፡፡
ይሁን እንጂ የአደን የጦር መሳሪያዎቹን ወደ ሱዳን ለማጓጓዝ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍቃድ አግኝቶ ላስጫነው ወገን ለማስረከብ ሌሎች አስፈላጊ ህጋዊ ስርዓቶችን አሟልቶ ወደ ወደ አገሪቱ ያስገባው መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የግብርና ፖሊሲ ተሻሽሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡ ተሰማ
ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ በሥራ ላይ የቆየው የግብርና ፖሊሲ ተሻሽሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡ ተሰማ፡፡
መረጃው የተሰማው የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ፣ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡
የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርጋል የተባለለት ይህ አዲስ የግብርና ፖሊሲ፣ በማክሮ ኢኮኖሚ አጥኝዎች ተጠንቶና ተግምግሞ፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መላኩን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
መጭውን በዓላት ምክንያት በማድረግ 108 አማራጭ የገበያ ቦታዎች ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮዉ ቀጣዩን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ እየሰራ ካለው ስራ አንዱ ህብረተሰቡ አማራጭ እና ተደራሽ የገበያ ስፍራ እንዲያገኝና የሚፈልጋቸውን ምርቶች በቀጥታ ከአምራች ገበሬው ማግኘት እንዲችልና እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ቢሮዉ ለጣቢያችን በላከዉ መግለጫ አሳዉቋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት የተዘጋጀ መሆኑን ቦሮዉ ጠቁሟል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት በማረጋጋት በተለይም የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ እንደ እንቁላል እና አይብ ያሉ የእንስሳት ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበልጥ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል።
ከነዚህም ውስጥ 56 የቁም እንሰሳት የገበያ ስፍራዎች ሲሆኑ 52ቱ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች ናቸው ተብሏል፡፡አዳዲስ የግብይት ቦታዎቹ በሁሉም ክፍለ ከተሞች አገልሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን መሸጫ ስፍራዎቹ ከአርሶ አደሩ በቀጥታ ተቀብለዉ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንዲችሉ የተዘጋጁ አማራጭ የገበያ ስፍራዎች መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡
Via Ethio FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ እና ራሱን ብቻ ከሌሎች ነጥሎ የሚወድ ስግብግብ ቡድን መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታል፡፡
ይህን ፈተና ለማለፍ ብልሃት፣ አንድነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ባለፉት ወራቶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች አሁንም ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አይተናል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን አስቦ እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
አንጋፋው ሙዚቀኛ አርቲስት አለማየሁ እሸቴ አረፉ
ተማር ልጄ፣ አዲስ አበባ ቤቴ እና በሌሎች ታዋቂ ስራዎች የሚታወቁት አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ዛሬ ነሀሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አርፈዋል
ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛል
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ የቴሌኮም አገልግሎት ኩባንያዎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡ ተሰማ።
በአፍሪካ 195 የቴሌኮም ኦፐሬተሮች ያሉ ሲኾን፤ ኢትዮ ቴሌኮም በግዝፈት፣ በደንበኛ ቁጥር እና በአገልግሎት ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ያለው ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሙኒኬሽንስ ወይም በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል GSMA የተባለ ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ተቋም ያወጣው ሪፖርት ነው።
GSMA በዓለም ዙርያ ከ750 በላይ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን በአባልነት አቅፎ የያዘ እና ኩባንያዎቹን በሥራቸው ልክ ጥራት እና ደረጃ ሰፍሮ የሚናገር ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።ይኸው ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮምን ከአፍሪካ ሁለተኛ ከዓለም ደግሞ 28ኛ እንዳለው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ቻይና፣ አሜሪካ እና ሕንድ የመሳሰሉ ሀገሮች በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌላውም ቀዳሚ በመሆናቸው፣ በእነዚህ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች ከ1 እስከ 27ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ቀጠና ማስፋፍያ ያደረገው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የ4G እና LTE Advanced የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አስጀምሯል።
በቀጠናው 28,000 ደንበኞች የዳታ ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏክል።የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት አመቱ 106 ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስፋፊያ እየተሰራ ነው ብለዋል።ኢትዮ ቴሌኮም የዴታ አጠቃቀም በብርቱ በሚታይባቸው የሐገሪቱ ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እያስጀመረ መሆኑ ተሰምቷል።
Via Sheger FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአምስት ቀናት የጾምና የጸሎት ምህላ አዋጅ መታወጁን የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለጸ
@Dire_Tube_news
የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አገር አቀፍ የጾምና የጸሎት ምህላ አዋጅ መታወጁን አስታውቋል፡፡
የጾምና ጸሎት ምህላው ከጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነገ፤ ነሐሴ 27/2013 ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተገለፀ፡፡
ሚኒስተሯ ሪይቸል ኦማሞ፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዋልታ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ሚኒስትሯ ባለፈው ግንቦት 30/2013 በተመሳሳይ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መምጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ ድርጊትን ለሚጠቁም ማበረታቻ ለመስጠት ደንብ አወጣ።
ማበረታቻው የሚሰጠው እንደ ጥቆማው ውጤታማት ነው ተብሏል።ደንቡ በከተማዋ ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የወጣ መሆኑን የከተማው ከንቲቫ ፅ/ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫ አስታውቋል።ህገ ወጥ ተግባራት ይፈፀምባቸዋል ብሎ የዘረዘራቸው ተግባራትም ከመሬትና ከግንባታ ጋር፣ከጦር መሳሪያ፣ከውጭ ምንዛሬ ዝውውር፣ ከሀሰተኛ ሰነድ እና የገንዘብ ህትመት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ነው።
በእነዚህ ተግባራት ላይ በመደበኛ ሕጎች የሚፈጸመው እንዳለ ሲሆን፤ ይህ ደንብ በቅርብ ጊዜያት እየተንሰራፉ የመጡ በመንግስትና በሕዝብ ንብረት ላይ የሚሰሩ እና ነዋሪውን የሚያማርሩ ሕገወጥ ተግባራት ላይ እንዲያተኩር መደረጉን አብራርቷል ደንቡ የጥቆማዎቹን አቀራረብ ሥርዓት እና ለጠቋሚዎቹ ስለሚሰጥ ማበረታቻ ምጣኔ የሚገልጹ ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡ያም ሆኖ ለማበረታቻው የሚከፈለው ገንዘብ እንደ ጥቆማው ውጤታማት መሆኑን አስተዳደሩ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሰነድ ተመልክቷል።
DW
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
*ኢንሹራንስ እና ባንኮች ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ
*የዋጋ ግሽበቱን ለመግታት ብሄራዊ ባንክ አዳዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ውሳኔ አሳልፏል
*
ኢንሹራንሶች ከአመታዊ ገቢያቸው 15% የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ። ውሳኔው ከነሃሴ 26 ጀምሮ ይተገበራል።
ባንኮች ከጠቅላላ አመታዊ የብድር ክምችት 1% የልማት ባንክ ቦንድ መግዛት ይጀምራሉ።
የባንኮች መጠባበቂያ መጠን ከጠቅላላው ተቀማጭ 10% እንዲሆን ተወሰነ። ቀደም ሲል 5% እንደነበር ይታወሳል።
ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ 50% ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ይደረጋል። ቀደም ሲል 30% በመቶ ነበር።
የውጭ ምንዛሬ ያስገኘ ደንበኛ ያለገደብ የሚቀመጥለት የውጭ ምንዛሬ መቶኛ 40% እንዲሆን ተወስኗል። ይህ መጠን 31.5% ነበር።
Via Capital Newspaper
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት (USAID) መጋዘኖችን በአሸባሪው ህወሓት መዘረፋቸው ተገለጸ
አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋልያሉት ዳይሬክተሩ ይህ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ሀገሪቱ አሁን ችግር ላይ ስላለች አይደለም ብለዋል፡፡
ይልቁንም ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃለነ ነው ያሉት፡፡
አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩትን ያልተረጋጋጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለም ሲሉም ለኢብኮ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
በመጪው መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news