ታህሳስ 07 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ መመሪያ
__
ከሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ ከአምቡላንሶች በስተቀር መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ እንዲሁም ከጤና ተቋማት ውጭ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እንዲዘጉ መመሪያ መሰጠቱ ይታወቃል።
ዛሬን ጨምሮ ላለፉት 8 ቀናት የተሰጠው ትእዛዝ ያለ መሸራረፍ ተተግብሯል። በእነዚህ ግዜያት ውስጥ በሲቪሊያን ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን መቀነስ ከመቻሉም በበርካታ አካባቢወች አስደናቂ ኦፕሬሽኖችን በማከናወን የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን እንዲሁም ተሽከርካሪወችን ከጠላት ማርከናል። የጠላትን ወታደራዊ እቅዶችም ማዛባት ተችሏል።
ይሁን እንጅ የተላለፈው መመሪያ ተፈፃሚነት ከዚህ በላይ መቀጠሉ በህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያደርሰውን ጫና በማገናዘብ #ከነገ #ማክሰኞ #ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እና የተቋማት ክልከላ እና ገደቡ የተነሳ መሆኑን እናስታውቃለን::
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም!
ታሕሳስ 07/04/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?
- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል
(መሠረት ሚድያ)- ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ገርጂ፣ ጃክሮድ፣ ሾላ፣ 6 ኪሎ፣ መነን፣ ጎሮ ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተኩስ ሲሰማ ነበር።
በርካታ ነዋሪዎች በድምፁ ተደናግጠዋል፣ መረጃ የሰጠ የመንግስት አካልም የለም።
መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት ተኩሱ ከሰሞኑ ከመንግስት ጋር እርቅ ፈፀሙ በተባሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት የተተኮሰ ነው።
መገናኛ አካባቢ አንዲት ሴት በተኩሱ ምክንያት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉም ታውቋል።
ታጣቂዎቹ የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከሸገር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ወደ ሰማይ እየተኮሱ እንደገቡ የደረሰን መረጃ ያሳያል።
"ታጣቂዎቹ በቅጥቅጥ አና በሃይሉክስ መኪና ተጭነው ሾላ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ተኩስ አየተኮሱ እየተጓዙ ነበር" ያለን አንድ የአይን ምስክር በሁኔታው በርካቶች እንደተደናገጡ ገልጿል።
ህዝብ በሚንቀሳቀስበት ጎዳና ላይ ድርጊቱ መፈፀሙ እንዳሳዘናቸው የገለፁት ነዋሪዎች ህዝብን በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ ቀድሞ ባልተገለፀበት ሁኔታ ማሸበር አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ ሾላ ፖሊሲ ጣቢያ ከሚገኙ አንድ የፖሊስ አባል ድርጊቱን ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶች ከተኮሱ ቦታ በድንጋጤ ሲሸሹ ይታይ እንደነበር ገልፀዋል።
ፎቶ: ፋይል
መረጃን ከመሠረት!
ወቅታዊ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ በሚንቀሳቀስባቸው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ካሉት 31 ቀበሌዎች ውስጥ 28ቱን ፋኖ የተቆጣጠረ ሲሆን ባለው የአፓርታይድ የአብይ አህመድ መንግስት 3 የከተማ ቀበሌዎችን ነው ከሞላ ጎደል የተቆጣጠራቸው ስለሆነም ከሚቆጣጠራቸው ከነዚህ ቀበሌዎች ውስጥ ያሉትን የአማራ ወጣቶች አዝመራ በመሰብሰብ ላይ ከሚወቁበት አውድማ ላይ ጭምር በማፈስ እስትንፋሴን ያስቀጥሉልኛል ብሎ ላሰበው የመጨረሻ ጦርነት ለመዘጋጀት ወረዳው ላይ የአስር ቀን ስልጠና በማሠልጠን ላይ ይገኛል።
ስለሆነም መላው የወረዳው ህዝብም ሆነ የታፈሡ ሠዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር ያፈሳቸውን ሰዎች ፦
የሸዋውን ወደ ጎንደር ፣ የጎንደሩን ወደ ሸዋ ፣ የወሎውን ወደ ጎጃም ፣ የጎጃሙን ወደ ወሎ በማዞር ወይም በማቀያየር እቅዱን እንዲያስፈፅሙለት እየሠራ እንደሚገኝ እና ስልጣነ መንበሩን በድሃ ልጅ ደም ማራዘም ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ህዝቡ ጠንቅቆ እንዲያውቀው ስንል የጥንቃቄ መልዕክታችንን እያስተላለፍን ፦
አሁን ህዝቡ እራሱን ከአፈሳ ለመከላከል የጀመረውን ግብግብ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የብልፅግናው አገዛዝ በማህበረሰቡ ላይ ከምንጣፍ ጎታቹ የአብይ ሠራዊትና ከጋሻ ጃግሬዎቹ ጋር በገጀራ ፥ በዱላ ፥በመጥረቢያና በቢላዋ እራሱን እየተከላከለ ሁሉም በሚባል ደረጃ ማህበረሰቡ ቤትና ንብረቱን ትቶ በዱርና በጫካ መኖሪያውን አድርጓል ።
በመሆኑም እርስ በእርስ ከሚያጋድለን አረመኔአዊ አባገነን መንግስት መንጋጋ ለመላቀቅ ሰልጣኙ ከወረዳችን እንዳይወጣ መላው ማህበረሰባችን መንገድ በመዝጋት እና አመፅ በማንሳት ሠራዊቱን በመበተን ወደ ነበልባል ብርጌድ እንድትቀላቀሉ እና የአብይ አህመድን አባገነናዊ መንግስትን በአፋጣኝ ወደ ግብዓተ መሬቱ እንድናስገባ ስንል ጥሪአችንን እናቀርባለን።
-ነፃነታችንን በክንዳችን
-ድል ለአማራ ፋኖ
-ላንጨርሰው አልጀመርነውም
ከነበልባል ብርጌድ ሚድያና ኮሚኒኬሽን
ፋኖ መምህር አጥናፉ አባተ
#በአዲስ አበባ የቦንብ ጥቃት ደረሰ‼
✍️ትላንትና ምሽት በአዲስ አበባ በሁለት አካባቢዎች የቦንብ ጥቃት መድረሱን የመረጃ የምንጮች ገልፀዋል።
✍️በከተማው አያት አርባ ዘጠኝ እና ሰሚት በሚባሉ አካባቢዎች በድረሱ የቦንብ ጥቃቶች በፖሊስ አባላት እና በተሽከርካሪዎች ላይ የህይወት እና የንብረት ጉዳት መድረሱ ተስምቷል።
✍️የመጀመሪያው ጥቃት የደረሰው አያት አርባ ዘጠኝ አካባቢ በተለምዶ ውሃ ታንከር በሚባለው አካባቢ ሲሆን 3 የፖሊስ አባላት መሞታቸዉ ነው የተገለፀው ።
✍️ሁለተኛው ደግሞ ሰሚት ፔፒሲ አካባቢ ሲቪል ለባሺ ደህንነት አባላት ላይ በደረሰው የቦንብ ጥቃት ሲጠቀሙባት የነበረዉ መኪና በእሳት መቃጠሉ ሲነገር አባላቱ ላይ ጉዳት አድርሰው ከአካባቢዉ ማምለጣቸውን ከምንጮቾ አረጋግጠናል።
ህዳር 20/2017 ዓ.ም
ህዝብ ያሸንፋል💪💪💪
ፒኮክ መናፈሻ ምን ተፈጠረ ??
በትላንትናው እለት በአዲስአበባ ፒኮክ አካባቢ ፖሊስ እና ወጣቶች እንደተጋጩ ተሰማ!!
👉አንድ ሰው ከቀናት በፊት ቤቱን ሲያፈርሱበት እራሱን ማጥፋቱ ተሰምቷል።
በአዲስአበባ ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ የሚገኙ በከተማ ግብርና የሚተዳደሩ ዜጎች እና ከ አብይ አሕመድ ጨፍጫፊ አካላት ጋር የተጋጩት ነዋሪዎች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቦታ በአስቸኮይ እንዲነሱ ና ቤት እንዲያፈርሱ በመደረጉ ነዉ።
በግጭቱ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች መጎዳታቸው የተሰማ ሲሆን ሁለት የጨፍጫፊው ፖሊሶችም ቀላል የማይባል ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተሰምቷል።
ህዝብ ያሸንፋል💪💪
የኦሮሚያ ሪፐብሊክ የመመስረት ሴራ(የፊንፊኔ ዲሞግራፊ ሴራ)
የኮሪደር ልማት በሚል የሚሰራውን ድብቅ ሴራ ማንም በትኩረት ያየው አካል የለም። የኮሪደር ልማቱ ዋና አላማው የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር የተደረገ የፖለቲካ ሴራ ነው። ካለ ጦርነት አዲስ አበባን የራሳችን እናደርጋለን በሚል የተጠነሰሰ ሴራ ነው። ለዚህም የተሰራው ሴራ
1ኛ. መጀመሪያ የአዲስ አበባን አዋሳኝ ፊንፊኔ ዙሪያ የተወሰነውን የአዲስ አበባ ክፍል ጨምረን ሸገር ከተማ በሚል ማካለል
2ኛ. የሸገር ከተማን ካደራጀን በኋላ በውስጡ ያለውን አማራ ቤቱን በማፍረስ እንዳይከራይ አድርጎ ማስወጣት
3ኛ. በአዲስ አበባ ያለውን በተለይ መሃል ከተማ የሚኖረውን አሮጌ መንደር በሚል በፍጥነት ህዝቡን ወደ ዳር የከተማው ጫፍ በማውጣት ሌላ ተቃውሞ እንዳያመጣብን መንገዶቹን እና አረንጓዴ ብልጭልጭ አድርገን ሰርተን ሰፊ ፕሮፓጋንዳ በማስተጋባት የህዝብ ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ
4ኛ. በኮሪደር ልማቱ ስራ ላይ የኦሮሞ ኮንትራክተሮች እና ሰራተኛ 90% በላይ እንዲሰማሩ እና 10% ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ በማካተት የሚነሳ ጥያቄ ካለ ትኩሳት ለማብረድ መጠቀም
5ኛ. የኮንስትራክሽንና እና የግንባታ ስራ እንዲቆም በማድረግ በቀን ስራ የሚተዳደረው አብዛኞቹ አማራ ስለሆኑ በስራ እጦት ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ጫና ማሳደር
6ኛ. ህዝቡ የተነሳባቸውን ቦታዎች በቆርቆሮ ካጠርንና ተነሽዎች ከተረጋጉ በኋላ በኮሪደር ልማት ስም ያተረፍነውን ቦታ ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ባለሀብቶች ብቻ በጥንቃቄ በማስረከብ እነሱም ቢያንስ ከ2,000,000(ሁለት ሚሊየን )በላይ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞችን ከግንባታ ስራ ጀምሮ እንዲቀጠሩ በማድረግ በከተማ የኦሮሞ የበላይነት ማስፈን
6ኛ. በየመንገዱ ዳር ተሰባስበው የሚቆሙ በተለይ የአማራ ተወላጆች የተለያዩ ሰበባሰበብ በመፍጠር ግማሹን ማሰር፣ ቀሪውን በተለይ ጠያቂ የሌላቸውና የማይታወቁትን ባዘጋጀነው የቀብር ቦታ ወስዶ መረሸን በዚህ መልኩ አማራን ከፊንፊኔ ማፅዳት
7ኛ . መርካቶ አንሱ አታንሱ ብለን ግብ ግብ ሳንፈጥር ፅንፈኛው ፋኖ አቃጠለው በሚል በራሳችን በስውር በተለያዬ ግዜ በማቃጠል ዳግመኛ እንዳይሰሩ ቦታውን እያጠሩ ማስቀመጥ
8ኛ. ኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባ ብቻ ከሆነ ተቀባይነቱ ስላጠራጠረ ወደ ክልል ከተሞች በመውሰድ ጥርጣሬ መቀነስና የፊንፊኔውን በፍጥነት በማካሄድ ለቀጣይ ምርጫ ስራ በመጠቀም ቀሪውን ከምርጫ በኋላ የሚጠናቀቅበትን መንገድ መቀየስ
ከዚህ ውስጥ ያልተፈፀመው የቱ ነው ? መረጃው ከውስጥ ከሚሰሩ የፖለቲካ ሴራውን የሚያውቁ ናቸው ያደረሱን ለማንኛውም ይህንን ሴራ ቀድመን ስለተረዳን የቱንም ያህል ብትደክሙ በኮሪደር ልማት ስም የተሰራውን ሴራ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ።
ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም።
የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው?
እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ:
- "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው። ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።"
- "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።"
- "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።"
- "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው"
- "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት"
ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን።
መልካም ቀን።
EliasMeseret
አማራ ክልል!!
በአማራ ክልል ለአንድ ወር በዘለቀው
“የዘፈቀደ እስር” የተያዙ “በሺዎች የሚቆጠሩ” ነዋሪዎች በዳንግላ፣ ኮምቦልቻ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች እንዲሁም በጭልጋ ወረዳ በሚገኙ ጊዜያዊ የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ!!
አምነስቲ፤ “ኢትዮጵያ ለአገራዊ፣ ለአህጉራዊና ለዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ግድ የለሽ ወደመሆን አዲስ ምዕራፍ ገብታለች” ሲል ወቅሷል።
ተቋሙ፤ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን እስር እና የእስረኞች አያያዝ በተመለከተ ከእስር ካምፖች የወጡ ሰዎችን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት እንዳነጋገረ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
አምነስቲ፤ እስሩን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ አራት የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ እንደደረሰበት አስታውቋል።
“አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት፤ ግብረ ኃይሉ በመላው አማራ ክልል የሚገኙ አራት ጊዜያዊ የእስር ካምፖችን በሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መሙላቱን አረጋግጧል” ሲል በጥናቱ ደረሰበትን ገልጿል።
ከመስከረም ወር ጀምሮ በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው “የዘፈቀደ እስር”፤ “በፖለቲካዊ” የፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ “የአስፈጻሚውን አካል ጣልቃ ገብነት የተቃወሙ” ዳኞች፣ አቃብያነ ህግንም ኢላማ ያደረገ እንደሆነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
“አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት፤ ግብረ ኃይሉ በመላው አማራ ክልል የሚገኙ አራት ጊዜያዊ የእስር ካምፖችን በሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መሙላቱን አረጋግጧል” ሲል በጥናቱ ደረሰበትን ገልጿል።
አሁንም የሚደረጉ የዘፈቀደ እስር እንዲቆም ጠይቋል።
BBC
ይህ ሆን ተብሎ እየተደረገ ያለ ነው ምክንያቱም እንደሚታወቀው የረጅም ጊዜ የወሊድ መከላከያዎች ሴቶችን እስከመጨረሻው መሀን የማድረግ እድሉ በጣም ሰፊ ነው። ከስር ዜናውን አንብቡት።
በአማራ ክልል የመንግሥት ጤና ተቋማት ከፍተኛ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አለመኖሩ ተሰምቷል።
የ72 ሰዓታት መከላከያ እንክብልም በብዙ ጤና ተቋማት እንደሌለ ታውቋል። ባሁኑ ወቅት ለተጠቃሚዎች የሚሰጡት፣ በሴቶች ዘንድ እምብዛም ተፈላጊ ያልሆኑት ለ5 እና 10 ዓመት የሚያገለግሉ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶች ናቸው። ሆኖም በመንግሥት ጤና ተቋማት የሌሉት የወሊድ መከላከያ እንክብሎች፣ በግል ጤና ተቋማት በውድ ዋጋ እየተሸጡ እንደሚገኙ መረዳት ተችሏል።
የሚድያ ሰራዊት...?!
አብይ አህመድ ምንም አይነት የሚያወጣውን መግለጫ ከስር ከስር ሚዲያው ላይ ተቀምጠው ጎሽ በርታ ንጉሳችን የሚሉ ናቸው ።
በዚህ መልኩ የሚገኝ ላይክ፣ ኮመንት እና ሼር ጥቅሙ ምን ይሆን?
በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ
በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች። ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል። ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል። 250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች።
ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች። ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ።
የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው።
ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ። ግንባታውን ለማድረግ በአካባቢው ከሚገኘው ደን የተወሰነው ይወገዳል መባሉም ሌላ ሙግት አስነስቷል። በጀርመን ወፍም መብት አላት።
"መንግስት ለሸገር ከተማ ባለስልጣናት በአዲስአበባ የኮንዶሚኒየም ቤት እያደለ ነዉ" ተባለ!!
መንግስት ለሸገር ከተማ ባለስልጣናት በአዲስአበባ የኮንዶሚኒየም ቤት እየሰጠ መሆኑ ተሰማ!!
የሸገር ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተለያዩ የአዲስአበባ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የኮንዶሚኒየም ህንጻዎች ላይ እጣ እየወጣ መኖሪያ ቤት እየተሰጣቸዉ መሆኑን ተጠቅሷል።
ለዚህ እንዲረዳ በሚልም የብድር አማራጭ በሲንቄ ባንክ በኩል እየተመቻቸ ነዉ ያለዉ የመሠረት ሚዲያ ዘገባ ጉዳዩን ያዉቃሉ ያላቸዉ ምንጭ አመታትን ቆጥበዉ ከዛሬ ነገ ይደርሰኛል በሚል የነበራቸዉ የኮንዶሚኒየም ቤት ተስፋ መሟጠጡን እና መሰል ድርጊቶች በሀገር ተስፋ እንድቆርጥ ያስደርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።
#መሠረትሚዲያ
ገና ምን ታይቶ የ 97 እና የ 2005 ተመዝጋቢዎች እርማችሁን አውጡ
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችል ኢህአፓ አስጠነቀቀ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው እና ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ የተሸጋገረው የኮሪደር ልማት፤ የከተማይቱን ነዋሪዎች “ሰብአዊ መብቶች የጣሰ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ዛሬ በሰጠው መግለጫ ወቀሰ። በኮሪደር ልማቱ ሳቢያ“እያየለ የመጣው የህዝብ ብሶት እና ምሬት” በቸልታ ከታለፈ፤ “የህዝባዊ ቁጣ መገንፈል እና ተዛማጅ ጉዳዮችን” ሊያስከትል እንደሚችልም ፓርቲው አስጠንቅቋል።
አዲስ አበባ “ዓለም አቀፍ ደረጃዋን ጠብቃ የመልማቷ ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ” እንዳልሆነ በዛሬው መግለጫ የጠቀሰው ፓርቲው፤ ይሁን እንጂ የከተማዋ ልማት እና እድገት “ከኗሪው ህዝብ መብት መከበር” እና “ከጥቅሞቹ መጠበቅ” ተነጥሎ ሊታይ እንደማይገባ አሳስቧል። ልማቱ “ከዜጎች አጠቃላይ የኑሮ መስተጋብር እና የኢኮኖሚ እድገት ጋር የተጣጣመ” መሆን እንደሚኖርበትም ፓርቲው በአጽንኦት አንስቷል።
የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኢህአፓ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ፤ በከተማይቱ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት “የበርካታ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች” መፍረሳቸውን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየወሰዳቸው ያላቸው እርምጃዎች “የነዋሪዎች ሁኔታ ያላገነዘቡ፣ ምቹ ጊዜን ያልጠበቁ እና ከግምት ያላስገቡ” መሆናቸውንም አመልክተዋል።
((እኛም ህዝባዊ አመፁ የማይቀር ነው እንላለን))
እኔየምለው…
"…በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድን ሥርዓት በክላሽ መጣል አይቻልም" በማለት እሱ ብቻ አውርቶ፣ አስጨብጭቦ በሚወርድበት ሸንጎው ሲደሰኩር የነበረውን የአቢይ አሕመድን ዲስኩር ደጋግመው ሲያሰሙን የነበሩት እና አደንቁሬ የኢትዮጵያ ጎምቱ ሚዲያዎች የባሽር አላሳድ መንግሥት በአንድ ሳምንት ትጥቅ አከርካሪው ተመትቶ መገርሰሱን አልሰሙም እንዴ?
"…ምነ አቢይ አሕመድ ሲጨንቀው፣ ሲጠበው ወደ እነ ኢዩ ጩፋ፣ ወደ እነ እስራኤል ዳንሳ፣ ወደ እነ ዮናታን አክሊሉ፣ ወደ እነ ይዲዲያ ነው ኤዲዲያ ሀገር ወደ ደቡብ ሄዶ ሀገር ሰላም እንደሆነች ለማስመሰል ራሱን በራሱ የሚያረካበትን የደቡብ የዐርባ ምንጭ ጉዞው ላይ ብቻ አተኮሩ? አንድ መስመር ዜና ማንን ገደለ? 😂
"…የበሸር አላሳድ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን ቀይረው፣ መሳሪያቸውን ጥለው ወደ ኢራቅ ሲሰደዱ ቪድዮውን አላዩትም፣ ወይም አልደረሳቸውም? ቤተ መንግሥቱ ሲወረር፣ ማንኪያና ሹካ ሳይቀር ሲዘረፍ አላዩምን?
"…ለማንኛውም እነርሱ ካላሳዩአችሁ እኔ ዘመዴ ሶሪያን በተመለከተ ዛሬ ማታ ተአምር ነው የማሳያችሁ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንቅልፍ አጥታ ወያኔንና ሻአቢያን ስታሰለጥን የነበረችው ሶሪያም ኢትዮጵያ ሳትፈርስ ልክ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና እና ፍልስጤም ዓይናችን እያየ፣ ጆሮአችን እየሰማ እሷም ፈረሰች። አቤት የፈጣሪ ሥራ።
"…የኢትዮጵያም አምባገነን የብልፅግናው አቢይ አሕመድም ጉዳይ እንዲሁ ነው። አርባ ምንጭ በመደበቅ፣ ኦነግ ሸኔን ጠብቀኝ ብሎ ወደ ሸገር በመሰብሰብ፣ ሕፃናትና የአእምሮ ህሙማንን ጭምር ለጦርነት በማፈስ አገዛዙን ማጽናት አይቻልም። የሆነ ቀን የሆነ ቦታ መከላከያው አከርካሪው ሲሠበር ወይም መከላከያው ነቅቶ ከሕዝብ ጋር ሲቆም ሁሉም ነገር ያበቃለታል።
• እነ ፋና፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ ተንፒሱ እንጂ…?
በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚተገበር መመሪያ!
ጎጃም
አልሰማንም እንዳትሉ ተብላችኋል!!
ከሰኞ ህዳር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እቀባ ተደርጓል፤ አልሰማሁም አያድንም። ጥሪ ሳይሆን ወታደራዊ መመሪያ ነው።
ይህንን መመሪያ የጣሰ እንቅስቃሴ የማደናገሪያና ለጠላት ኃይል ሽፋን የመስጠት እንቅስቃሴ ተደርጎ ስለሚታሰብ በእራስ ላይ ውድመትን ያስከትላል።
የእንቅስቃሴ እቀባውን ተከትሎ ህዝባችንም ከመሪዎቻችን የሚተላለፍለትን መመሪያዎች ከወዲሁ በንቃት ይጠባበቅ።
የኦርቶዶክሳውያን የእርድ ዜና…!
"…በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያንን የማረድ አረመኔያዊው ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ወረዳ ለመታረድ መስፈርቱ ብሔር ሳይሆን ሃይማኖት እንደሆነ ነው የሚነገረው። ለምሳሌ ኅዳር 13 /2016 ዓም ከታረዱት 28 ኦርቶዶክሳውያን መካከል በሴሮ፣ ጥር 10 /2016 ዓም በጪሳ ተ/ሃይማኖት ጥምቀተ ባሕር ላይ የታረዱት በሙሉ የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ናችው።
"…ላለመታረድ ኦርቶዶክስ ሆነህ ኦሮሞ ብትሆንም የሚሰማህ የለም። ትታረዳታለህ። መታረድ ብቻ ሳይሆን ከመታረድ የተረፈው ርስቱን እና ሀብት ንብረቱን ለእስላሞቹ ጥሎ እንዲሰደድ ይፈረድበታል። በዚህ ወረዳ ብቻ አምና በመቶዎች የሚቆጠቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያን ታርደዋል፣ ብዙዎች ርስት ጉልታችውን ጥለው ተሰደዋል። ሌላው ቀርቶ በዚህ በያዝነው ሕዳር ወር ብቻ 24 ኦርቶክሳውያን ታርደዋል።
"…በዚህ ወረዳ ያለው ካቢኔ በሙሉ እስላም ስለሆነ እስላሙ በሙሉ እንዲታጠቅ ተደርጓል። አስቀድመው የግል የመሣሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ሆነ በጸጥታ መዋቅር ውስጥ የሚሠሩትን ኦርቶዶክሳውያን ትጥቅ አስፈትተዋቸው ነው ሳይዉሉ ሳያድሩ መጥተው ማረድ የሚጀምሩት። መከላከያ ተብዬዎቹ የተወሰነ ፍተሻ አድርገው ከእያንዳንዱ ሙስሊም ቤት አራት አራት ክላሽ ነው የተገኘው። የሚያስታጥቁት ደግሞ የወዳው ባለሥልጣናት ናችው።
"…አሁን ከህዳር 11 ጀምሮ እስከ ትናንት ሌሊት ድረስ 11 ኦርቶዶክሳውያን የታረዱ ሲሆን የ9ኙ ስም ዝርዝር ደርሶኛል።
① አቶ ዘዉዴ ረዳ (33)ባል
② ወ/ሮ አታለሉ ንጋቱ(27)ሚስት
③ ለዝና ለገሠ (58)አባት
④ ብዙነሽ ለዝና (27)ልጅ
⑤ በላይነህ ጥላሁን (65)
⑥ ተሾመ ስዩም (32)
⑦ ዘላለም ተክለእሸት (30)
⑧ ኃይሌ ወርቅነህ (20)
⑨ አስቻለው ደለለኝ (19)
"…ይሄ ምልክት ነው። ሩዋንዳው ከፊት ነው።
ሰዎች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት አካባቢ በሁለት እና ሶስት ቀናት አጣድፎ እና ቤት አፍርሶ ማባረር፣ ለሰራተኞች ለሁለት እና ሶስት ወራት ደሞዝ አለመክፈል፣ የአካል ጉዳተኞችን እና የ15 አመት ህፃናትን ጭምር አፍሶ ወስዶ ለመልቀቅ በብር መደራደር... ከሰሞኑ ግፎች በጥቂቱ።
የጥቁር ህዝብ የነፃነት ምሳሌ የሆነው ኢትዮጵያዊ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ህብረቱን አጥቶ በአንድነት ድምፁን ማሰማት አቅቶታል።
እሱ እንዳለ ሆኖ ይህን የሚያዙት እና ሚያስፈፅሙት አካላት ግን ቤተሰብ የላቸውም? ልጆች የሏቸውም?
@EliasMeseret
ሰው እንዴት መሰባሰብ አቃተው ??
ዛሬ ጠዋት በጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አነሱ!!!
የተቃውሞው ምክንያት በህዝባችን ላይ ግድያ ይቁም በሚል ነው!!
የፀጥታ ሀይሎች ተቃውሞው እንዳይባባስ ጥረት አድርገዋል። ተማሪዎቹ ቁርሳቸውን ለመብላት ካፌ ከተሰባሰቡ በኋላ ነው ቁርሳቸውን ሳይበሉ ወደ ተቃውሞ የወጡት።
በአዲስ አበባ እና አዳማ የጀመረው አፈሳ እና የገንዘብ ድርድር ወደ ሻሸመኔ እና ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቷል
ሻሸመኔ 010 ቀበሌ ስታድየም ዋናው በር ፊት ለፊት ባለው መጋዘን ውስጥ እና 02 ቀበሌ ምክር ቤት ጀርባ (ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጎን ባለው አዳራሽ) በርካታ ወጣቶች ታጭቀው እንደሚገኙ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።
"ዙሪያ ገባው በሚሊሻ ተከቧል፣ ቤተሰብ አይደለም መጠጋት ለራስም ያሰጋል። ግን ምን እየሆነ ነው ያለው?" ብለው የሚጠይቁት ነዋሪዎች ከመሸ መንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸው እና የሚሊሻው አፈሳ ተባብሶ እንደቀጠለ ተናግረዋል።
"ስልክህን ይፈተሻል ብለው መንገድ ላይ ይቀበሉህና ጠዋት ሚሊሻ ቢሮ ና ይላሉ። ስትሔድ ለማነው የሰጠኸው ተብለህ ወንጀለኛው አንተው። መሮናል። እኔም አንድ የኦሮሞ ወጣት ነኝ የታገልኩት ግን ለዚህ አልነበረም" በማለት መልዕክቱን ያደረሰኝ ደግሞ አንድ የከተማው ወጣት ነው።
🔥#የአፈሳ_መረጃ!!
ዛሬ ማለትም 01/03/2017 ከጠዋት ጀምሮ ደሴ ላይ የብልፅግናው አሽከሮች መንገድ ላይ ያገኙትን ወጣት እያፈሱ ስለሆነ ወጣቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል!!
በተያያዘ መረጃ አዲስአበባ፣ናዝሬትና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወጣት እየታፈነ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ ጣቢያ እየተጫነ ነው!!
ጥንቃቄ ይደረግ
ከታች የዚህን ሌባ ጉድ ተመልከቱ
በ1.8 ቢልየን ብር ከቦታቸው ሳይፈናቀሉ ቤት ይሰራላችኋል ተብለው የነበሩት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት ሳይት ነዋሪዎች በሶስት ቀን ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው።
(መሠረት ሚድያ)- ከስድስት አመት በፊት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ሲጣል በ1.8 ቢልዮን ብር የመኖርያ ቤት ተገንብቶላቸው እዛው እንደሚኖሩ ተነግሯቸው የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች በሶስት ቀን ውስጥ እቃቸው አውጥተው የካዛንችስ ነዋሪዎች ወደሄዱበት ቦታ እንዲሄዱ እንደተነገራቸው ገለፁ።
"ዶ/ር አብይ የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ ባደረጉት ንግግር በአካባቢው ላይ እየኖሩ ለሚገኙ 1,650 አባወራዎች እዛው ፕሮጀክቱ አካባቢ ሰርተን በዘመናዊ ቤት ኑሮ እንዲኖሩ እናደርጋለን፣ ለዚህም የኤግል ሒልስ ባለቤቶች 1.8 ቢልየን ብር ሰጥተውናል ብለው ተናግረው ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች አሁን አዲስ ዱብዳ የሆነ መረጃ ተነግሮናል ብለዋል (ለንግግሩ ቪድዮውን ይመልከቱ)።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 ዓ/ም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎች የተወሰኑ ነዋሪዎችን ሰብስበው በሶስት ቀናት ውስጥ እጣ አውጥታችሁ የካሳንችስ ነዋሪዎች የሔዱበት አካባቢ ትገባላችሁ፣ ተዘጋጁ ብለው ለነዋሪው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደሄዱ ለመሠረት ሚድያ የደረሰው ጥቆማ ያሳያል።
"ነዋሪው በጣም ተደናግጧል፣ እስቲ ብትዘግቡልን እና ህዝብ ቢያውቅልን ስንል አደራ እንላለን" ያሉት ነዋሪዎች ተስፋ አድርገው ለአመታት ቢጠብቁም ቃል ታጥፎ ከከተማ ውጭ እንዲሄዱ መደረጋቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ይህ ከአልሚው ኢግል ለተነሺዎች ቤት መገንቢያ ተብሎ ተሰጥቶ የነበረው 1.8 ቢልዮን ብር የት እንደደረሰ በመንግስት የተባለ ነገር የለም።
አሳዛኝ መረጃ‼️
ደራ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ ‼️
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ሰለልኩላ ከተማ ነው የምኖረው ያሉ አንድ ነዋሪ የሰሞኑን ሁኔታ እንደሚከተለው ገልፀውታል።
"ሰሞኑን የኛ ወረዳ ከፍተኛ የአማራ እልቂት እየተፈፀመበት ይገኛል፣
በተለይ የአማረኛ ተናጋሪ የሆኑ ማህበረሰብ በከፍተኛ ሁኔታ የዘር ማጥፋት እየተደረገበት ይገኛል።
ከባለፈው እሁድ ጥቅምት 17/2/2017 ጀምሮ ከ150 በላይ ማህበረሰብ ውድ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች ቆስለዋል ታግተዋል ቤት ተቃጥሏል ንብረት ተዘርፏል።
በደራ ወረዳ ጉንደ መስቀል ከተማ ሙሉ የከተማው ህዝብ መርዶ እና (ድንኳን)ብቻ ነው።
የደራ ህዝብ በጋራ በአብይ አህመድ እና ከመልስ አብዲሳ ቀጥተኛው ድጋፍ በኦነግ ሼኔ የዘር ማጥፋት ከተጀመረበት ድፍን ሶስት(3)ዓመታት አልፎታል፣ነገር ግን መንግስታዊ ድጋፍ ስላለው የሚደርስለት አካል አላገኘም።
ለዚህ ነው አማራ ክልል ያለው ጦርነት ከክልሉ መውጣት አለበት የምንለው።
በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ስፍራዎች ወጣቶች እየታፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፖች እየተላኩ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ያሉት በተለይ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ የደቡብ ልጆች ላይ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመው ባሳለፍነው ሁለት ሳምንት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩት ተይዘው ተወስደዋል ብለዋል።
የሸክም ስራ የሚሰሩትን እነዚህ ልጆችን አፍሰው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱ በኋላ የተወሰነ ግዜ በእስር አቆይተው ወደ ወታደራዊ ካምፕ እንደሚወስዷቸው ምንጮቻችን ነግረውናል።
ባሳለፍነው ሳምንት ይህ ድርጊት ሲፈፀምበት የነበረው ቦታ ኮዬ ኮንዶሚኒየም አዲስ ከተማ ፖሮጀክት 16 የሚባለው አካባቢ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
"ወዴሳ ወረዳ አንድ ጣብያ አለ፣ በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር፣ አሁን ሸገር ከተማ ከሆነ በኋላ የኦሮሚያ ሚሊሺሻ ነው ያለበት" ያሉን አንድ የመንግስት ምንጫችን ለእያንዳንዱ ሚሊሺያ ኮታ እየተሰጠ ወጣቶችን አፍሰው እንዲያመጡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ሌላኛው ምንጫችን ደግሞ የዚህን የአፈሳ ድርጊት መኖር አረጋግጦ በተለይ በሸገር ከተማ በጠራራ ፀሀይ እየተፈፀመ መሆኑን ተናግሯል።
አብያተ እምነት የሰማያዊ መንግሥት ተልዕኮ ማስፈጻሚያ ኤምባሲዎች በመሆናቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
የብልጽግና መንግሥት የወንዝ ዳር፣ ጫካ፣ ኮሪደር… ወዘተ ፕሮጀክት በሚሉ መጠሪያዎች የሚያከናውነውን የማናለብኝነት ፈረሳና የማፈናቀል ተግባር አስመልክቶ በቅርቡ የአገራችን የበላይ ሕግ የሆነውን ሕገ መንግሥትና የሚመለከታችውን አዋጆች ጠቅሰን በትብብር ፓርቲዎች የጸና አቋማችንን መግለጻችን ይታወቃል።
ከዚኹ የኮሪደር “ልማት” ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች የአምልኮ ሥፍራዎች ሕጋዊ ይዞታዎች ድንበር በማን አለብኝነት እየፈረሰ እንዳለና እንደሚፈርስ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው መገንዘብ ችለናል።
እየፈረሱ ካሉት በዋቢነት የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተደናግል ጠባባት የሴቶች ገዳም ይዞታ ከክብር በወረደ አኳኋን እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን ከየካቲት ፲፪ አደባባይ ከፍ ብሎ ያለውና ከአምስቱ ዓመት የፋሽስት ጣልያን ወረራ ወቅት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥ ታሪክ ያለው የአገር ባለውለታው የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ይዞታም ጠባብ የሆነውን ዐውደ ምሕረት የበለጠ በማጥበብ ከፊት ለፊቱ የገዳሙና የገዳሙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ፈረሳ እንደሚከናወንባቸው ፓርቲያችን መረጃ ደርሶታል።
እነዚህን በዋቢነት ጠቀስን እንጂ ፈረሳው ያነጣጠረባቸው በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው የሚገኙ አብያተ እምነት ቁጥር ብዙ እንደሆነ ተረድተናል።
ባለፉት ጥቂት ተከታታይ ዓመታት በአብያተ ክርስቲያን፣ መሳጅዶች ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የደረሱ ቃጠሎዎች፤ በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ የደረሱ አሰቃቂ ግድያዎች በኢትዮጵያ በትልቁ አገራዊ እሴታችን (ሃይማኖት) ላይ የተጋረጠውን ኹለንተናዊ ጥቃት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ከዚኹ የቀጠለ በሚመስል አኳኋንና በተቀናጀ መልኩ በአዲስ አበባና አካባቢው አብያተ ክርስቲያን ይዞታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው የማፍረስ ተግባር ከውጭና ከውስጥ ተናቦ የሚተገበር መኾኑን መጠርጠር አያዳግትም።
አብያተ እምነት ለሰው ልጅ አጠቃላይ መንፈሳዊና አእምሯዊ ልዕልና ያላቸው ሚና አይተኬ ነው። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ሲሆን ድርብ እውነት ያደርገዋል።
እነዚኽ የእምነት ተቋማት እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው የሚኖሩ በአማካይ ሃያ ሺህ ያክል ዜጎችን የሚያገለግሉ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን በዚኽ ልክ የዕለት ተዕለት አገልግሎት የሚሰጡ ሌሎች ተቋማትን መጥቀስ አይቻልም።
አውሮፓውያን በዘመነ አብርኆት(enlightenment) ሃይማኖትና አብያተ እምነትን አሽቀንጥረው ጥለው ነበር። ሆኖም ባለፉት ፶ ዓመታት በተለይ የደረሰባቸውን የሞራል ኪሣራ፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣ ስግብግብነት፣ እርካታ ማጣት፣ ግለኝነት፣ የተዘወተረ ራስን ማጥፋትና መሰል ዘግናኝ ድርጊቶች በሕዝባቸው ላይ መንሰራፋት አካሄዳቸውን ቆም ብለው እንዲያጤኑ አስገድዷቸዋል።
የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አብዮተኞች እንዲኹ ቅጽር መዳፈር፣ ማፍረስ፣ አሻራቸውን ማጥፋት፣ መጽሐፍትን ማቃጠል፣ የሃይማኖት አባቶችንና ምዕመናንን ማሳደድ በሰፊው ሞክረውት ነበር።
ያ ኹሉ አልፎ ወደቀልባቸው የተመለሱ መሪዎች ሲመጡ ዛሬ ሕዝባቸውን የሃይማኖትና ሞራል ልዕልና ያለው በስልጣኔ ስም ለሚመጣ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት "አይሆንም" ባይ በማድረግ እንዲያውም የዓለሙን ሚዛን በማስጠበቅ ይጠቀሳሉ።
በአገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብያተ እምነት እና በምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው ተከታታይ ጥቃትና የመግለጫችን ጭብጥ የሆነው በአብያተ እምነት ይዞታዎች ላይ ያነጣጠረ የማፍረስ ዘመቻ ይኸው “ያደገው” ዓለም ያለፈበት የጥፋት ጎዳና አገራዊ መገለጫ ነው።
በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር “ልማት” የተጠቀሰው የፈረሳ ሥራ መስመር ላይ ያሉ የምድራውያን የውጭ አገራት መንግሥታት ኤምባሲዎችን እንዳልነካቸው ኹሉ ይልቁን እነዚህን የሰማያዊ መንግሥት ኤምባሲ ሆነው የሚያገለግሉ ተቋማት የፈረሳው ሥራ ፈጽሞ እንዳይነካቸው እናት ፓርቲ በአጽንኦት ያሳስባል።
በብልጽግና መንግሥት የአብያተ እምነት ይዞታዎችን በማፈራረስ የሚተገበር የትኛውም ሥራ እንደ ማንኛውም ምድራዊ መንግሥት የሥርዓቱ እድሜ አብቅቶ በሌላ ሲተካ ወደ ቀደመ ይዞታቸው መመለሳቸው አይቀሬ ነው።
በደርግ ዘመን ዋናው መግቢያ ተዘግቶ ቆይቶ ኢሕአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት የተከፈተውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስታውሷል።
ስለሆነም የብልጽግና መንግሥት ከዚኽ ነባር ሃይማኖት ጠል አካሄዱ እንዲታቀብና የአብያተ እምነት ቅጽሮችን ማፍረሱን በአፋጣኝ እንዲያቆም በጽኑ እናሳስባለን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ታላቅ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ለአማራና የአማራ ደጋፊዎች በሙሉ!
ጨፍጫፊው እና ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አንባገነን አገዛዝ: በአማራ ህዝባችን ላይ
ጦርነት በማወጅ፣ በአሁኑ ሰዓት በሰውአልባ፣ በጦር አውሮፕላን እና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ: የሚፈፀመውን የጅምላ ዘር ጭፍጨፋ በመቃወም በመላዉ ዓለም ለወገኖቻችን ድምፅ ለመሆን!
ሰልፉ የሚደረግባቸው የዓለም ከተሞች ፣
1. Berlin, Germany: October 18, 2024
2. Indianapolis, USA: October 25, 2024
3. Frankfurt, Germany: November 9, 2024
4. Paris, France: November 9, 2024
5. Stockholm, Sweden: November 9, 2024
6. Queensland, Australia: November 9, 2024
7. London, UK: November 10, 2024
8. Washington, D.C., USA: November 10, 2024
9. Pretoria, South Africa: November 10, 2024
10. Minnesota, USA: November 10, 2024
11. Brussels, Belgium: November 10, 2024
12. Geneva, Switzerland: November 12, 2024
13. Oslo, Norway: November 23, 2024
አዘጋጅ: ዓለም አቀፉ የአማራ ግብረሃይል
የሚኖርበት ቤት ለልማት በሚል የፈረሰበት እና ስራ እንዳይሰራ የተከለከለ ወጣት ራሱን አጠፋ‼️
ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ የሆነ አዲሱ ካሳሁን የተባለ ወጣት ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ አካባቢ በሚገኘው 'በፀጋህ ሆስፒታል' ፊት ለፊት ነዋሪ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ራሱን አጥፍቷል።
አዲሱ ነጠላ ከሚሸጥበት ኡራኤል ቤተከርስቲያን አካባቢ ስራ እንዳይሰራ ሁለት ግዜ በደንብ አስከባሪዎች ተባሮ እና ንብረቱም ተወስዶበት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቅርብ ሰው ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ከትናንት በስቲያ ምሽት ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ የሚኖርበት ቤት በነጋታው ጠዋት እንደሚፈርስ ሲነገረው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት እዛው ቤቱ ውስጥ ራሱን እንዳጠፋ ታውቋል።
የልጅ አባት የሆነው እና በቅርቡ የወለደች ባለቤት ያለው ወጣቱ ይህን ድርጊት ከፈፀመ በኋላ ትናንት ስድስት ሰአት ላይ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ቀብሩ እንደተፈፀመ ሰምተናል።
#መሰረት ሚዲያ
=============