በተከለከለ አየር ክልል በረራ አድርገዋል የተባሉ የኢትዮጵያንና የ ኢትሃድ አየር መንገዶችን በአሜሪካ መቀጣታቸው ተሰምቷል።
የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425,000 ዶላር እና የኢትሃድ አየር መንገድን 400,000 ዶላር መቅጣቱ ተገለጸ።
አየር መንገዶቹ የተቀጡት ያለፍቃድ በተቀከለከለ አየር ክልል በረራ ማከናወናቸው በደንበኞች ጥበቃ አቪየሽን ቢሮ ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።
ምርመራው እንዳመለከተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጎርጎሮሳውያኑ 2020 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል የተባበሩት አየር መንገድ መለያ ኮዶችን የያዙ በረራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
አየር መንገዱ ከሀምሌ 2022 እስከ ሚያዚያ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ጄትብሉ አየር መንገድን (B6) ኮድን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና አሜሪካ መካከል በረራዎችን አካሄዷል ሲል የአቪየሽን ድረገጾች ዘግበዋል።
የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል እነዚህ በረራዎች በአሜሪካ ደንቦች መሠረት ተገቢ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን ምርመራው አየር መንገዶቹ ቀደም ብሎ ማሳወቂያ ቢሰጣቸውም በራራዎቹ መቀጠላቸውን ከአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የሱሉልታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥና የፀጥታ አካላት የተገደሉበት ጥቃት
እጃችንን ለመንግሥት መስጠት እንፈልጋለን ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት መሆናቸውን የገለጹ ታጣቂዎች ትናንት ሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ ከተማ አቅራቢያ ሊቀበሏቸው በሄዱ ባለሥልጣናት ላይ በከፈቱት ተኩስ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥና የፀጥታ አካላትን መግደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
በወቅቱ በተከፈተው የተኩስ እርምታ ከተገደሉት በተጨማሪ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊና ታጣቂዎቹን ለመቀበል በስፍራው የተገኙ ሌሎች ሰዎችም መቁሰላቸውን የዓይን ምስክሮቹ ተናግረዋል።
ስለ ጥቃቱ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ የሰጠው ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም።
የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፣ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደረስኩበት ባለው ስምምነት የተቀበላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።
ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ወደ ተሃድሶ ማዕካላት የሚያመሩ በተባሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች የተከፈተ የተኩስ እሩምታ ድንጋጤ መፍጠሩን የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ተናግረው ነበር።
ምንጭ፦ DW
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 በላይ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች መገደላቸው ተሰማ ።
በዞኑ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም. ለሁለት ወራት ለመንግሥት "መረጃ እና ድጋፍ ሰጪ" በሚል ተጠርጥረው በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የነበሩ በርካታ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት "መረሸናቸው" ታውቋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ የአካባቢው ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አለማየሁ 20 ከሚሆኑ የወረዳው ካቢኔዎቻቸው ጋር የግድያው ሰለባ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።
መስከረም መጨረሻ በአካባቢው "ከባድ ውጊያ" መደረጉን ተከትሎ መስከረም 29/2017 ዓ.ም. ወረዳው በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱን እና የመንግሥት ኃይሎች ወረዳውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ይህንንም ተከትሎ "[መከላከያ] የሚሊሻ፣ የፖሊስ አባላትን እንዲሁም ካቢኔዎችን በሙሉ መስመር ላይ ነው ጥሏቸው የሄደው" ሲሉ አንድ ነዋሪ፤ 'ባልተለመደ ሁኔታ' የወረዳው አስተዳደር ከተማዋ ውስጥ መቅረቱን ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም 20 የሚሆኑ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መከላከያ ሠራዊት "ለስምሪት" አካባቢውን ለቆ ሲወጣ "ተቆርጠው" መቅረታቸውን ተናግረዋል።
በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት የአካባቢ አመራሮች "ፈረስ ቤት ሚካኤል" በተባለ የከተማው መውጫ ላይ ተወስደው መረሸናቸውን ሦስት ነዋሪዎች እና የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Via BBC Amharic
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።
👉 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል።
" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።
በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።
በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።
ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።
የተሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ያበቃል
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ህዳር 30/2017 ዓ/ም ያበቃል።
ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
ቀደም ብሎ የተሰጠው ገደብ ጥምቅት 30 የነበረ ቢሆንም ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች ተብሎ እስከ ህዳር 30 ተራዝሞ ነበር።
ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ የገለፀ ሲሆን ፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑም ተናግሯል።
የቤት ባለቤቶቹ ቤታቸውን አድሰው መግባትም ይሁን ማከራየት እንደሚችሉም መናገሩም የሚታወስ ነው።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በመዲዋ የተሰማው ተኩስ ምንድን ነው?
👉 በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ገርጂ፣ ጃክሮድ፣ ሾላ፣ 6 ኪሎ፣ መነን፣ ጎሮ ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተኩስ ሲሰማ ነበር።
በርካታ ነዋሪዎች በድምፁ ተደናግጠዋል፣ መረጃ የሰጠ የመንግስት አካልም የለም።
መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት ተኩሱ ከሰሞኑ ከመንግስት ጋር እርቅ ፈፀሙ በተባሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት የተተኮሰ ነው።
መገናኛ አካባቢ አንዲት ሴት በተኩሱ ምክንያት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉም ታውቋል።
ታጣቂዎቹ የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከሸገር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ወደ ሰማይ እየተኮሱ እንደገቡ የደረሰን መረጃ ያሳያል።
"ታጣቂዎቹ በቅጥቅጥ አና በሃይሉክስ መኪና ተጭነው ሾላ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ተኩስ አየተኮሱ እየተጓዙ ነበር" ያለን አንድ የአይን ምስክር በሁኔታው በርካቶች እንደተደናገጡ ገልጿል።
ህዝብ በሚንቀሳቀስበት ጎዳና ላይ ድርጊቱ መፈፀሙ እንዳሳዘናቸው የገለፁት ነዋሪዎች ህዝብን በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ ቀድሞ ባልተገለፀበት ሁኔታ ማሸበር አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ ሾላ ፖሊሲ ጣቢያ ከሚገኙ አንድ የፖሊስ አባል ድርጊቱን ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶች ከተኮሱ ቦታ በድንጋጤ ሲሸሹ ይታይ እንደነበር ገልፀዋል።
መሠረት ሚዲያ !
የሰላም አማራጭን መቀበል አዋቂነት ነው- ጃል ሰኚ ነጋሳ
የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመገንዘብ በጫካ የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት የመንግሥትን ጥሪ እንዲቀበሉ የሠራዊቱ የቀድሞ ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ ጥሪ ማቅረባቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡
ጃል ሰኚ ነጋሳ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ÷ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ያደረጉትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ለተደረገላቸው አቀባበል ሕዝብና መንግሥትን አመሥግነዋል፡፡
በክልሉ የተለያዩ ከተሞችን በጎበኙበት ጊዜ የተመለከቷቸው የልማት ሥራዎችና የከተሞች መነቃቃት እንዳስደነቃቸውም አንስተዋል፡፡
የሰላም ጥሪውን የተቀበሉትም የሕዝብና የመንግሥትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ተከትሎ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
እውነቱ የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለው ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ሆኖ ሳለ÷ ስምምነቱ የክልሉን ሰላም የማያረጋግጥ ነው ብለው የተሳሳተ መረጃ የሚያጋሩ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጅ እነዚህ አካላት የላኪዎቻቸውን ፍላጎት በፕሮፓጋንዳ ለማሟላት የሚፍጨረጨሩ፣ ስለ ጦርነት የማያውቁ፣ በክልሉ የደረሰውን ውድመት የማይረዱ እና የእናቶችን እምባ ለማቆም የማይሹ ናቸው ብለዋል።
በአጠቃላይ እነዚህ አካላት በተለያዩ ሀገራት በምቾት ያሉና በሰው እጅ እሳት መጨበጥ የሚፈልጉ ናቸው ሲሉ ጃል ሰኚ ረጋሳ መናገራቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።
እነዚህ ኃይሎች የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ሊያደፈርሱ ቢጥሩም ሳይሳካለቸው ቀርቷል ነው ያሉት፡፡
የተደረሰው ስምምነት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እየተተገበረ መሆኑን አንስተው÷ ይህ እንዲሳካ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና ጥሪውን የተቀበሉ ወዳጆቻቸውን አመስግነዋል፡፡
ሌሎች በጫካ ያሉ የቡድኑ አባላትና የትግል ጓዶቻቸው ቆም ብለው የሕዝቡን ጉዳት በመመልከት እየቀረበ ያለውን የሠላም ጥሪ እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡
ፋና ብሮድካስት
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
#Update
አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ተለቀው ከቤተሰባቸው ተቀላቅለዋል
ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳያገኙ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ፤ ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ እንዳሉት ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሰዉላቸው ከተመለሱ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ ሰባት ሰዓት ግድም መኖርያ ቤታቸዉ መድረሳቸውን አክለው አብራርተዋል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የዛሬው የፕሪምየር ሊግ ውጤቶች፡
አርሰናል 2-0 ማንችስተር ዩናይትድ
ማንችስተር ሲቲ 3-0 ኖቲንግሃም ፎረስት
ኒውካስል ዩናይትድ 3-3 ሊቨርፑል
ዋንጫው የማን ነው?
#PremierLeague #Arsenal #ManchesterUnited #Liverpool #ManchesterCity
የቀድሞ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ የነበሩት አቶ ጥላሁን ሞላ ከማረሚያ ቤት አመለጡ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን የቀድሞ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ የነበሩት አቶ ጥላሁን ሞላ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም ወንጀል ተጠርጥረዉ በህግ ጥላ ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተጣራባቸዉ ካለበት ፖሊስ ጣቢያ ማምለጣቸው ተገለጸ፡፡
አቶ ጥላሁን ሞላ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩበት ከሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከእስረኛ ማቆያ ህዳር 08 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ አምልጠው መጥፋታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
በእለቱ የጥበቃ ተረኛ ፖሊስ አባሎችም በቁጥጥር ስር በማድረግ በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብሏል።
የሀዲያ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ተሾመ ባቲሶ ማንም ከህግ የሚያመልጥ እንደሌለ በመግለጽ ጥፋተኛ እና በወንጀል የሚጠረጠር ሁሉ በህግ እንዲጠየቅ ለማድረግ ፖሊስ ብርቱ ክትትል ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የተጠርጣሪውን ለመያዝ ፖሊስ የቅርብ የሚባሉ ሰዎችንም እየመረመረ እንደሚገኝና እስካሁን ግን ምንም የተገኘ ፍንጭ እንደሌለም አዲስ አስነብቧል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
" በምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ነው ከፅህፈት ቤቱ ያወጣው " - በድብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት መግለጫ አውጥቷል።
ደርጅቱ በመግለጫው ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዜዳንት ውክልና አንስቶ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታውሷል።
' ቡድን ' ሲል የገለፀው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የጊዚያዊ አስተዳደር በመምራት ላይ የሚገኘውን ህወሓት " የህዝብ ውክልና የያዙ ምክር ቤቶች እውቅና በመንሳት እና ውሳኔዎቻቸው በመጣስ በማን አለበኝነት ምስለኔዎች በመሾም አስተዳደራዊ እና ህዝባዊ ስራዎች እያደናቀፍ ይገኛል " ሲል ከሷል።
የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ህገ-መንግስት ላይ የተቀመጠውን የህዝብ እና የመንግስት ከፍተኛ መገለጫ የሆነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመጣስ በህዝብ ላይ አምባገነንነት ለመጫን በሙሉ አቅሙ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብሏል።
" ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ከፅህፈት ቤቱ በማውጣት በራሱ ምስሌኔ የአስተዳደሩ ፅህፈት ቤት ለመቆጣጠር መክሮዋል " ሲል አክሏል።
" ህገ-ወጥ ሙከራው ከግለሰባዊ አምባገነንነት የሚነሳ ነው " ያለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ አባላቱ ትግላቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማስታውስ ፣ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ህጋዊ ተጠያቂነት ፣ ህግ እና ስርዓት እንዲያስከብሩ በማለት ጥሪ አቅርቧል።
መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመቀሌ ነው
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡
የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል ፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የወሲብ ንግድ በአደባባይ እንደስራ መታየት ጀምሯል
ቤልጂየም በሰኔ ወር 2024 የወሲብ ንግድን እንደ ማንኛውም የስራ ዘርፍ በህጋዊ መንገድ መስራት እንዲቻል ፈቅዳለች፡፡
ሀገሪቱ ዜጎች ወደ ወሲብ ንግድ ለመግባት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ መያዝን እንደ መስፈርት ያስቀመጠች ሲሆን ህጉ መጽደቁ በድብቅ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማትን ማስደሰቱ ተገልጿል።
በዚህ ህግ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች አገልግሎቱን ለደንበኞቻቸው ለመስጠት ከተቋቋሙ ድርጅቶች እና ፈላጊዎች ጋር መዋዋል እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ብራሰልስ አሁን ደግሞ በዚህ ስራ የተሰማሩ ዜጎች እንደ ማንኛውም ሰራተኛ የጡረታ፣ የጤና ደህንነት ክፍያ፣ ዓመታዊ እረፍት፣ የህመም እና የወሊድ ፈቃድ ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዳለች፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።
ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
አዲሱ ከንቲባ ከነገ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት : " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም : አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያም መንግስት የመደበው ብቻ ነው : በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም : ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።
ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
ምንጭ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
አርቲስት መሠረት መብራቴ በሎስአንጀለስ ሲቲ ካውንስል ተሸለመች !
በተለያዩ ፊልሞች ፣ ቴአትሮች እና በማስታወቂያ ስራዎቿ አድናቆት የተቸራት ፤ ጎን ለጎንም በምታበረክተው የበጎ አድራጎት አገልግሎት የበርካቶችን አክብሮትና ፍቅርን የተጎናፀፈችው አርቲስት መሠረት መብራቴ በሎስአንጀለስ ከተማ Los Angeles city council እና U.S Africa institute በጋራ ባዘጋጁት “Humanitarian award” የካውንስሉ አባላት በተገኙበት የእውቅና እና የክብር ሽልማት ተበርክቶላታል።
ካውንስሉ አርቲስቷ ለኢትዮጵያ የህፃት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል በበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት እየሰጠች ያለውን አገልግሎት በማክበር በተለይም በአሜሪካን ሀገር የነበራትን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በመጥቀስ የተለየ እውቅና እንደሚሰጠውና ለዚህ አገልግሎቷም አክብሮት እንዳለው በመግለፅ የእውቅናና የክብር ሰርተፊኬት አበርክቶላታል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ይህ ጉዳይ ወዴት እያመራ ነው ?
ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን የዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ጉዳይ አድርገውት ሰንብተዋል።
አሁንም ድረስ መልስ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑም እሙን ነው !
ሚዲያዎቻችን ይዘውት የሚመጡት ማህበራዊ ጉዳዮች በደንብ ተመርምረው ለተመልካች መቅረም እዳለባቸው የሚያሳይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ፕሮግራም ነው ።
እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ከዚህ ቀደም በ ሰይፉ ፕሮግራም ላይ መቅረቡ የሚታወስ እና የቅርብ ጊዜ ትውስታ ጭምር ነው ።
ሁለት ጥንዶች በዚህ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ጉዳይ ለቧለቤቷ በመለገሷ እና ብዙ የጭንቅ ጊዜያቶችን አብረው በማሳለፋቸው ከዛም በስተመጨረሻ ያሰቡት ተሳክቶ ንቅለ ተከላውን አከናውነው ወደ ሀገር መመለሳቸውን አይተን ተደንቀን አመስግነን አልፈናል ።
በዚህኛው ፕሮግራም ደግሞ በተመሳሳይ ታሪክ ተመልካች ደስታውን ሳያጣጥም ፕሮግራሙ በተላለፈ ማግስት የተባለው ሁሉ ውሸት እንደሆነ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ሀብታሙ በ tiktok መንደር ብቅ ማለቱ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ላይ ጭምር ትልቅ ነጥብ በማስጣል አነጋጋሪነቱን ቀጥሏል ።
ይህ ጉዳይ ከ ሩሐማ ይልቅ ለማን ያመዝናል ? የሚለውን በጥልቀት ማየት ይኖርብናል ፤ ባለጉዳዩ እና ሊደነቅ የሚገባው ሀብታሙ ሆኖ ሳለ እሷ በዛ ፕሮግራም ላይ ብቻዋን የመቅረቧ ምክንያት ምንድነው ? ሀብታሙ በፕሮግራሙ ላይ ያለመገኘቱ ምክንያት በትክክል ተጠቅሷል ወይ ? እሱንስ ለማናገር የሞከረ አካል አለ ወይ? እነዚህና መሠል ጥያቄዎችን በዚህ ሾው አዘጋጆች ላይ ያስነሳል !
በርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰይፉ ምንም አይነት መረጃው እንደሌለው እሙን ቢሆንም ፤ ነገር ፕሮግራሞቻችንን በምን ያህል ትኩረትና ጥልቀት መመርመርና ማቅረብ እንዳለብን ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ።
በቂ መረጃ ካልተገኘ ደግሞ ማዘግየት ካልሆነም ማስቀረት ይዞ ከሚመጣው መዘዝ የተሻለ አማራጭ ነው ።
በዚህ ጉዳይ የጉዳዩ ባለቤት የሆነችው ሩሐማን ጨምሮ ሰይፉ ሾው ፕሮግራሙ መልስ ሊሰጡበት ይገባል ።
ከዚህ በማስቀጠል ሀብታሙ አሁን ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የስነ ልቦና እርዳታ ሊደረግለት ያስፈልጋል። ቀድሞ ካለበት ማንነቱ ወጥቶ አሁን ያለበትን ማንነት የያዘው እንዲሁም በተለያዩ ሱሶች ተዘፍቆ የሚገኝበት ምክንያት እሷ እንደሆነች በይፋ በ YouTube ሚዲያ ቀርቦ የተናገረ ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያ በሆነው tiktok ጭምር እሱም በቀጥታ ስርጭት live በማስገባት እንዲሁም አንዲት የሱ የወንድሙ ሚስት ነኝ የምትል ቤተሰቡን ጨምሮ ተመሳሳይ የሆነ ሀሳብ ሲያነሱ ተመልክተናል ።
ስለዚህ የዚህን ጉዳይ እውነት ለማወቅ እነዚህ ሰዎች ይቅርታ ተጠያይቀው ህይወታቸውን በጋራ መቀጠል የሚችሉበት ሁኔታ ካልሆነም በሰላማዊ መንገድ ተለያይተው የየራሳቸውን ህይወት እንዲኖሩ እና ሀብታሙም ወደ ቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ የተቻለው ሁሉ መደረግ አለበት ።
በዚህ ሳምንት የሰይፉ ሾው ፕሮግራም ይህን ጥያቄ ይመልሳል ወይንስ አይመልስም ?
እናንተስ ምን ሀሳብና አስተያየት ይኖራቹሀል ?
የቃላት ጦርነቱን በይፋ ጀምረውታል !
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከሠላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባለላቸውን የመነቃቀፍ መንገድ በይፋ ጀምረውታል ።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሰሞኑን በራሳቸው ሚዲያ በኩል በአንደበታቸው ስለኢትዮጵያ እና በቀጠናው ስላሉ አለመስማማቶች በተለይም ግብፅና ሱማሊያ ላይ ትኩረት አድርገው የተናገሩት ኢትዮጵያን የመቃወም እንዲሁም በውስጥ ጉዳዮቿ ለምሳሌ ያህል ህገመንግስቷን አንስተው የሰነዘሩትን የትችት ንግግር የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ ያሳቀ እና ያስገረመ ጉዳይ መሆኑን በመንግስት ሚዲያ በሆነው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን መስኮት የተላለፈው ትንታኔ በግልፅ ሲናገር ተመልክተነዋል ።
በርግጥ የሁለቱም መንግስታት አለመግባባት ከተጀመረ ውሎ ቢያድርም ሁለቱም በይፋ ይህን ነገር ባለማሳወቃቸው ምክንያት በሠላም እና በፍቅር መኖር የሚፈልገውን የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ግራ ሲያጋባ የቆየ ጉዳይ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ።
በተለይም ኤርትራ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳይ ስታነሳው የነበረው ክስ እና የስልክ ግንኙነትን እስከማቋረጥ እንዲሁም በረራዎች እንዲቋረጡ ያደረጋትን ሁኔታ የሁለቱም ሀገራት መንግስታት የሚያውቁበት ሌላ የተለየ ምክንያት እንዳለ ብንጠረጥርም በተለይም ኢትዮጵያ አሁን ላይ አለመግባባቶች ውስጥ ከገባችባቸው ሱማሊያ እና ግብፅ ጋር የኤርትራው መንግስት ያላቸው የጠበቀ ግንኙነት ከማስታረቅና ከማስማማት በተቃራኒው መሆኑ ጉዳዮን የእውነት መቃቃር እንዳላቸው በግልፅ የሚያሳይ ጉዳይ ሆኖ አይተነዋል ።
ሰሞኑን የኤርትራው መንግስት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሰጡትን አስተያየት መሠረት በማድረግ "የራሷ እያረረባት " በሚል የስላቅ ቃላት በፋና ብሮድካስት የተሰጠው ትንታኔ ሁለቱም የቃላት ጦርነቱን በይፋ ስለመጀመራቸው ማረጋገጫ ሆኖ አጊንተነዋል።
ሁለቱም በመገናኛ ብዙሃኖቻቸው የሰጡት አንዱን በአንዱ የማጣጣል እና የማንቋሸሽ ንግግር ሁለቱም ከመስማማት እና ህዝቡን አንድ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን መንገድ የመረጡበት ሁኔታ እና ከዚህም በላይ ሊባባስ እንደሚችል ይታመናል።
በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት በግልፅ በራሱ አንደበት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቀጠናውና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች በሰጧቸው ሀሳቦች ላይ መልስ ምት ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።
ሱሌማን አብደላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ ተዘገበ
በሳዑዲዓረቢያ መቀመጫዉን በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችን በማቅረብ የሚታወቀዉ ሱሌማን አብደላ ለበርካታ ጊዜያት በሀገሪቱ መንግስት በቁጥጥር ስር ዉሎ በእስር ላይ ይገኝ ነበር።
ሱሌማን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም ሲያንጸባርቅ የነበረ ሲሆን በሳዑዲዓረቢያ መንግስት ተይዞ እስር ላይ ቆይቷል።
ሱሌማን ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠቱን መሠረት ሚዲያ ዘግቧል። ሱሌማን በኢትዮጵያ ምን እንደሚጠብቀዉ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። እስካሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ሱሌማን አብደላን መረከቡን አላሳወቀም።
Via መሠረት ሚዲያ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
"መንግሰት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ አለበት"- ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ ) ባወጣው መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት እየገቡ ካሉ ታጣቂ ሀይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት መንግስት ለህዝቡ ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
ኢዜማ በመግለጫው አክሎም "ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሐድሶ ሥልጠና የሚገባ ታጣቂ ኃይል በሙሉ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ መሆን አለበት" ብሏል::
በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡
ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡
"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም" ሲልም አሳስቧል::
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የሶማሊያ መንግስት ወደ ጁባላንድ ክልል ኪስማዮ የሚደረጉ በረራዎችን ከልክሏል
የሶማሊያ መንግስት የበረራ ክልከላውን ያሳለፈው ከጁባላንድ ክልል ያጋጠመውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምንጮችን ጠቅሶ ኢስት አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጁባላንድን በበላይነት ለመቆጣጠር መሞከሩን ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች በደቡብ ምስራቅ ጁባላንድ እያሰፈረ ይገኛል፡፡
የሶማሊያ አየር መንገድ ወታደሮቹን ወደ ጁባላንድ ለማስፈር የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደተቃወመ የተገለፀ ሲሆን፤ የሶማሊያ መንግስት በክልሉ በረራ እንደይደረጉ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
የጁባላንድ ተቀዋሚ ፓርቲ መሪ እና የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ካየር÷ የፌዴራል መንግስት ወደ ጁባላንድ የሚደረጉ በረራዎችን መከልከሉ ተገቢ ያልሆነ የግዴለሽነት ውሳኔ እንደሆነ ገልጸዋል።
የፖለቲካ ተንታኞች የሶማሊያ መንግስት በጁባላንድ በረራ እንዳይደረግ ክልከላ መጣሉ ግዛቷን በመነጠል ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሰረቶችን ለማዳከም ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ውሳኔውን ተከትሎም ስትራቴጂክ ወደ ሆነችው የኪስማዮ ከተማ የሚደረጉ የትራንስፖርት አገልገሎቶች የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
የጁባላንድ ክልል የፌዴራሉ መንግስት ከህገ-መንግስት ውጪ ጣልቃ በመግባቱ የተነሳ በመካከላቸው ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወቃል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
"ምንም የማውቀው ነገር የለም ፣ ጥሪም አልደረሰኝም በኃላፊነት ቦታ ሳይሆን በሙያዬ አግዛችኋለሁ ነው ያልኳቸው" አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ
እስከ እኩለ ለሊት የቆየ ቀረፃ ጨርሼ ስልክ ስከፍት በርካታ ወዳጆቼ ተመረጥሽ የሚል ነገር ሰምተን ነው የሚል መልእክት ልከዋል።
በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ ነበር ያየሁት።
በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ የሚል የስልክ ምላሽ ሰጥቻለሁ። መረጃ ዎች ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ።
ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለ ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፣ በቦታውም አልነበርኩም፣ ጥሪም አልደረሰኝም።
አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እያሉ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎት ከበር ላይ ተይዘው ወደ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ዛሬ ጠዋት ወደ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አምርተው ከታዬ ደንዳኣን ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል።
“ወደዛ እንደወሰዷቸው ሰምተን ዛሬ ጠዋት ሄደን ነበር፤ ዛሬ አግኝተነው ወጥተናል፤ ቀጥሎ የሚሆነውን እንጠብቃለን” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ታዬ ህዳር 23 ቀን በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ትላንት ህዳር 25፣ 2016 ዓ/ም ከእስር ቤት እንደተለቀቁ ከበር ላይ “ምስክ ባደረጉ” ሰዎች መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል።
“ተለቋል ማለት አይቻልም፤ ከቤተሰቦቹ ጋር አልተገናኘም፤ እራሳቸው ናቸው ገብተው የወሰዱት፤ ከሰዓት 11 ሰዓት አካባቢ ከእስር ቤት ሊወጣ ሲል ቤተሰብ ሳያየው ትፈለጋለህ በለው ወስደውት ሄዱ። ከበላይ አካል የተጻፈ ያሉትን ደብዳቤ ይዘው ነበር። ምን እንደሆነ ግን አላነበብንም” ብለዋል።
የጸጥታ ኃይሎቹን ብዛት እንደማያውቁ የገለጹት ወ/ሮ ስንታየሁ፤ “የሲቪል ልብስ የለበሱ እና ማስክ ያደረጉ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ ደምብ ልብስ የለበሱ አካላት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በሁለት ፓትሮል ተሽከርካሪ ቂሊንጦ አካባቢ ሲዘዋወሩ እንደነበር ሰምተናል” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
አቶ ታዬ ፍርድ ቤቱ በዋስትና እንዲለቀቁ ከወሰነላቸው በኋላ ለሁለት ቀናት እስር ቤት ማሳለፋቸውን የገለጹት ወ/ሮ ስንታየሁ፤ ይህም የሆነው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ላይ የቀን ስህተት በመኖሩ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል። “የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ይህን ነገር እየጠበቀ የነበረ ይመስላል። ጥቃቅን ምክንያቶችን ሲደረድሩ ነበር” ብለዋል።
የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደኣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ታህሳስ 2 ቀን በጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
መረጃው የአዲስ ስታንዳርድ ነው
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
በላሊበላ ከተማ በጸጥታ ስጋት ምክንያት 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸው ተገለጸ
በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት በላሊበላ ከተማ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸውን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊው ዲያቆን አዲሴ ሲሳይ ከ180 በላይ አስጎብኚዎች ከሥራ ውጭ መሆናቸውንና የቱርዚም ዘርፍ መቀዛቀዙ የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲዳከም ማድረጉን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።
ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።
ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።
ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።
የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።
በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።
ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን 6 አዳዲስ ሹመቶች ሰጥተዋል
ከስድስቱ ሽመቶች ሁለቱ በደብረፅዮን ገ / ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተሾሙትን በማንሳት የተሰጠ ነው።
በዚሁ መሰረት ፕሬዜዳንቱ ከህዳር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚፀና በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ በመሆኑ የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በመሻር በብርሃነ ገ/ዮሱስ ተክተዋል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ምክትል የስራ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው ከህዳር 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የዓዲግራት ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ረዳኢ ገ/ሄር ምትክ ኪ/ማርያም ወ/ሚካኤል ምክትል የቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ፕሬዜዳንቱ በጡሮታ በተገለሉት ሓዱሽ ካሱ ምትክ ዶ/ር ገብሩ ካሕሳይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አድርገዋቸዋል።
ኮማንደር ተስፋይ ገ/ማርያም በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል ማጣራት ሃላፊ ፤ ኮማንደር ጌታቸው ኪሮስን በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል መከላከል ሃላፊ እንዲሁም አቶ ሃይላይ ኣብራሃ በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የሰው ሃይል ልማት ዘርፍ ሃላፊ አደርገው ሹመዋል።
በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው በተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ምትክ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ደብዳቤ መሾማቸው ይታወሳል።
@tikvahethiopia
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
በኡጋንዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱ ተሰማ
በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ከሳምንታት በፊት በደረሰ የመሬት መንሸራተት ከ100 በላይ ሰዎች እስካሁን ደብዛቸዉ ጠፍቷል።
የሟቾች ቁጥር እስካሁን 28 መድረሱ የገለፀዉ የሀገሪቱ ፖሊሲ ከሟቾቹ ዉስጥ ህፃናትም ይገኙበታል ብለዋል።
የዩጋንዳ ቀይ መስቀል ማህበር የነፍስ አድን ስራዎች እየሰራ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ስጋቱን ገልፆል።
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ሀገሪቱ ያስተናገደችዉ ከባድ ዝናብ በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል።
አሁን አደጋዉ ባጋጠመበት አካባቢ በ ፈረንጆች 2010 የሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ተመሳሳይ አደጋ ያጋጠመበት ነዉ ተብሏል።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት የአካባቢውን ነዋሪ ከአደጋ ለመጠበቅ ጥረት ቢያደርግም የተሳካ አለመሆኑ ተጠቅሷል።
ዘገባዉ የ ሮይተርስ ነዉ።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
የኦሮምያ ክልል መንግስት የሰላም ስምምነት የተፈራረመው በቡድኑ ቅቡልነት ከሌለው አመራር ጋር ነው” - የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት
መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው ጃልሰኚ ነጋሳ እንደማይወክለው ገልጿል፡፡
የተደረገው ስምምነት ከቡድኑ ጋር የተደረገ ስምምነት አድርጎ እንደማይወስደውም ነው ቡድኑ የጠቆመው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ትላንት ህዳር 22 ቀን የሰላም ስምምነት የፈረሙት ከወራት በፊት በስነምግባር ጉድለት ካባረርኳቸው አመራር ጋር ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አስታውቋል።
የኦሮምያ ክልል መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የሰላም ስምምነት ፈርመዋል ሲል መግለጹ ይታወቃል።
ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አፈንገጠው የወጡ ተደርጎ በመንግስት በኩል እየቀረበ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰት ነው ሲል የገለጸው መግለጫው የህዝቡን ስነልቦና ለመግዛት በሚል በመንግስት በኩል የቀረበ ማታለያ ነው ሲል ተችቷል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
ኬንያ እና ኡጋንዳ አለመግባባት ውስጥ የገቡትን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሊያሸማግሉ መሆኑን ሩቶ ተናገሩ
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጰያ እና ሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አለመጋጋት ውስጥ ሊከት የሚችለውን ችግር በውይይት እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርጉ በትናንትናው እለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን እየተዋጉ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ያላት ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ አዲስ አመት ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለመገንባት የተፈራረመችው ስምምነት ሞቃዲሹን አስቆጥቷል።
ይህ ፍጥጫ ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለው ግድብ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ውስጥ ለገባችው ግብጽ እንድትቀርብ አድርጓታል።
"የሶማሊያ ሰላም መሆን ለቀጠናው ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው እና ቀጣናው ለኢንቨስትመንት የተመቸ እንዲሆን ያደርጋል" ብለዋል ሩቶ በቀጣናዊ የሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ በሰጡት መግለጫ።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በቱርክ አንካራ የተደረጉ በርካታ ንግግሮች ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ መፍትሄ አላመጡም።
የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ ሞሀሙድ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ሞሀሙድ ከስብሰባው ጎንለጎን ከሩቶ እና ሙሴቬኒ ጋር መገናኘታቸውን ገልጿል፤ ነገርግን ስለንግግሩ ጉዳይ ምንም አላለም።
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በቀጣናዊ መሪዎች የሚቀርቡ የመፍትሄ ሀሳቦች በአዲስ አበባ በኩል ተቀባይነት አለማግኘታቸውን እና በቱርክ እየተካሄደ ያለው ንግግር ፍሬያማ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ቀደም ሲል ለሮይተርስ ተናግረዋል።
በሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሷል።
ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የገባችው ስምምነት የማንንም ፍላጎት የማይጻረር መሆኑን እና የተፈጠረውን አለመግባባትም በውይይት ለመፍታት እንደምትፈለግ በተደጋጋሚ ገልጻለች።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
/channel/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L