menfesawimeker | Unsorted

Telegram-канал menfesawimeker - መንፈሳዊ የህይወት ምክር

-

መንፈሳዊ የህይወት ምክር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወዳጄ ሆይ ! መንፈሳዊ ተጋድሎን አትፍራ፥ ከእርሱም አትሽሽ፡፡ ተጋድሎ ከሌለ ምግባር ትሩፋትም የለምና፡፡ እምነትና ፍቅርም ካልተፈተኑ በእውን ከአንተ ጋር ስለ መኖራቸው ርግጠኛ መኾን አይቻልምና፡፡ ለ አስተያየት ወይም መንፈሳዊ ጥያቄ ካሎት @menfesawimekerbot

Subscribe to a channel

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።

እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።

አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው።

ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።

ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።"

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን

@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

አሁንም ለ ጥያቄያችሁ

@menfesawimekerbot ይጠቀሙ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

Ebakachu admetut...Nefsun madan mifelg hulu yadmetew

https://youtu.be/cYTEjugZoV4

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

ሰበር መረጃ

መንግሥት የቤተ ክርስቲያኗን የጥበቃ መሣሪያ እየነጠቀ ነው!

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በኋላ አዲስ መመሪያ ወጥቷል። መመሪያው በየአጥቢያው ለጥበቃ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በአስቸኳይ እንዲወረሱ የሚል ነው። በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዦች የአጥቢያ አስተዳዳሪዎችን እየደወሉ ባስቸኳይ አስረክቡ ማለት ጀምረዋል። በአስኮ ገብርኤል እና በአንዳንድ ቦታዎች ፖሊስ መሣሪያውን ሊረከብ ሲል ሕዝቡ ደርሶ አስቀርቶታል።
የጥበቃ መሣሪያ ፈቃድ ወጥቶለት ቤተ ክርስቲያኗ ለጥበቃ አገልግሎት የምትጠቀምበት ሲሆን ከረጅም ዓመታት በፊት ጀምሮ ጥቅም ላይ ያለ ነው።
በአበውና በባለሥልጣናት ውይይት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉ ከተራዘመ በኋላ መሣሪያ መንጠቅ ለምን አስፈለገ? የሚለው የየአጥቢያውን አገልጋዮች አስደንግጧል።
ሁላችንም በየአጥቢያችን በመሄድ የመሣሪያ ነጠቃውን እናስቀር።
/channel/onesinod

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

" ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ . . ." (2ኛ ጢሞ 1፥9)

መለኮታዊ የሆነውን ተልእኮ ለመፈጸም ከቶ የሰውን ፈቃድ መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር ወደራሱ ሲጠራን ማንንም አላማከረም፤የእኛን የልብ ፈቃድ ከመመልከት ውጪ። ማንም ደግሞ እግዚአብሔር ወደራሱ እንዴት እንደሳበንና ልባችንን እንደነካው ፍጹም የሆነውን ሚስጥር አያውቅም፤ ከድንጋይ ይልቅ ጠጣራ፣ እንኳን የሰውን የአምላክን ማንነት ክዳ በምድረበዳ ልኖረችው ልባችን፡ እንዴት አድርጎ ክርስቶስ በፍቅሩ መዶሻ እንዳፈረከሳት የሚረዳም ሆነ የሚያውቅ ፈጽሞ የለም። እናም ሰውን ደስ ከማስኘት ይልቅ አምላክን መታዘዘ ብርቱ ከሆነ ኪሳራ አውጥቶ ዘላለማዊ ትርፍ የሚስገኝ ነገር መሆኑን ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ነው።

በልብህም ይሁን በአእምሮ ጽላት ላይ የተጻፈውን መልኮታዊ አጀንድ፣ ለእግዚአብሔር ይህን በሕዝቤ መካከል አደርጋለው ብሎ ሲያመልክትክ ለልብህም ሲናገራት ማንን አማክሮ ነው? ባጠገብህስ ማንን ምስክር አስቀምጦ ነው? አምልካዊ እይታውን መንፈሳዊ አይኖችህን አብርቶ በመንግስቱ ውስጥ የድርሻህን እንድትወጣ ያየውን እንድታይ እና እንድትከውን ራዕይን ሲሰጥህ ማንን ተማምኖ ነው? ከዚያ ከውዳቂ ሰፈር እውጥቶ ወደ አላማ እና ግቡ ወደ ሚያደርሰው የከበረ ሰረገላ ላይ ሲያሳፍርክ እርሱን ለመታዘዝና ለመሄድ " አማላክ ሆይ ይህው እኔ ላከኝ" በሚል ልብ በፊት ከመሆን ይልቅ ስለምን በዙሪያ ያልውን ነገር ማይት አስፈለገ? ስለምንስ ካምላክ ይልቅ የሰውን ፍቃድ እንጠብቃልን?? አብርሃም አምላኩን እሺ ባይልና ባይታዘዝ ለዓለሙ መዳን ተስፋ የሆነው የክርስቶስ የኪዳን ዘር ምን ይመስል እንደነበረ ማሰብ ከባድ ነው። ዳዊት ስንቅን ሊያደርስ ሲሄደ ከአምላኩ ይልቅ፡ የሰማውንና የታዘዘው ውንድሞቹን ቢሆን ፍልስጤም በእስራኤል ላይ ምን ያደርግ ይሆን? ከደም መፍሰስ ነጻ ወጥታ የክርስቶስን እግር በሽቱ የጠበችው ማሪያም መቅደላዊት ያንን ለማደረግ ለቧ ከውሰነው ውሳኔ ይልቅ ለደቀመዛሙርቱና በቤቱ ለነበረው ማጉረምረም ታዛ ወደ ኋላ ብትል " ይህ ወንጌል በተነገረበት ስፍራ ሁሉ" የተባለው ስለ እርሷ የተነገረው ምስክርነት ይነገር ይሆን?።

እርግጥ ነው እንዳንድ ጊዜ ተመክሮዎችንም ይሁን ምክሮችን በመልካምነቱ ከሰዎች መቀበል ይሁን፣ መስማትና መተግበር አስፈላጊ ነው፤ ፍጹም በሆነ መንገድ ግን ሰምቶ መልኮታዊውን የአምላክ ትዕዛዝ ለመታዘዝ የሰውን ፍቃድ መጠበቅ ፈጽሞ ስህተት ነው። " ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።" ሐዋ 5፥29
ልንታዘዘው የተገባውን የመልኮትን እጀንዳ ጊዜና ውቅት ልንቀጥርለት አይገባም በፍጹም፤ ዘግይቶ መታዘዝ ካለመታዘዝ አይለይም። እርሱ ነውና ለአላማው የጠራችሁ እርሱን ታዘዙት።

" የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።" 1ተሰ 5፥24

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

"ጸሎት በሕይወት ማዕበል ውስጥ መጠጊያ ወደብ፣ ማእበል ለሚያንገላታቸው መልሕቅ፣ የድሃው ሀብት፣ የባለጸጋው ደህንነት፣ የታማሚው መዳኛ ወይም ጤና ማግኛ ነው። ጸሎት መጥፎ ነገሮችን ያስወግዳል መልካሙን ይጠብቃል።"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
በጸሎትህ ጊዜ አምላክህን አመስግን
የውስጥ ችግርህን አዋየው የፈለከውን ንገረው የውስጥህን አውራው ሁሉም ማድረግ የሚችል አባት ስላለህ እመነኝ ጸልይ ይሰማሀል
ማታ ማታ
።።።።።።የማታ ጸሎት።።።።።።
#ውዳሴ ማርያም የለቱን
# መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 11እስከ 15ያሉትን ምዕራፍ ትጸልያለህ
# 1ጴጥሮስ ምዕራፍ 3 በሙሉ
# እግዚኦ ማሀረነ ክርስቶስ 24
# በእንተ ማርያም ማሀረነ ክርስቶስ 24
የግልህን የውስጥህን አውርተህ
አባታችን ሆይ ጸሎት አድርሰህ ትጨርሳለህ
እግዚአብሔር አምላክ የማታ ሰው ይበለን
የመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎቷ ልመናዋ ይደርብን
አሜን
ማታ 4 ሰዓት ባለንበት በጋራ እንጸልይ
የተለየ ሀሳብ ወይ ይህ ቢሆን ገንቢ ሀሳብ ካላችሁ በውስጥ መስመር ላኩ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

* ሀልወተ እግዚአብሔር *
ሀልወተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው ። እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም የሚሉ አሉና ከሱ እንጀምር ። ታዲያ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል ? ቢሉ ። 1ኛ.በስነ ፍጥረት ይታወቃል ። ም/ቱም ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለና ። ስዕል ካለ ሰዓሊው አለ ፣ ቤት ካለ አናፂ አለ ፣ ሙዚቃ ካለ ሙዚቀኛው አለ ማለት ነው ። ስለዚህ በዚ መሰረት ስናየው ይሄ ሁሉ ስነ ፍጥረት አስገኚ አካል ወይም ፈጣሪ አለው ማለት ነው ። 2ኛ. የሰው ልጆች ዝንባሌ ነው ።ይህም ማለት ግማሹ ሙስሊም ፣ ግማሹ ቡዲስት ፣ ግማሹ ክርስቲያን ፣ ግማሹ ባዕድ አምልኮ አምላኪ የሆነው ነብሱ ከውስጥ የፈጠራት አካል እንዳለ ስለምትጮህ ነው ። ስለዚ ይህም አንዱ የፈጣሪ መኖር ማስረጃ ነው ። 3ኛ.የቀናትና የወቅቶች መፈራረቅ ነው ። ይህም ለምሳሌ መብራት ሲጠፉና ሲመጣ መብራት ሀይል የሚባል አካል እንዳለ እንደምንረዳው ሁሉ ፡ የቀንና የማታ የበጋና የክረምት መፈራረቅም አምላክ እንዳለ ማስረጃ ናቸው ። ፀሀይን በቀን ጨረቃን በማታ ያሰለጠነ ቀኑን ለሰራዊት ሌሊቱን ለአራዊት ያደረገ አምላክ መሆኑን እናውቅበታለን ።የስነ ፍጥረት አይነቱ ብዛቱ ድንቅ ነው ። 1ፀሀይ ሆና ለአለም ሁሉ እንድታበራ ማን አደረጋት ? የዛፎቹ አይነት አንዳንዱ ቅጠሉ ሰፊ አንዳንዱ ቅጠሉ ቀጭን ፣ የአእዋፏቱ አይነት ፣ የአሶችና የሌሎች ባህር ውስጥ ያሉ ነብሳት መኖር ፣ ስናይ ፈጣሪ እንዳለ እንረዳበታለን ። ለውቅያኖሶች ዳርቻዎቻቸውን የወሰነላቸው ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበቦች ያስጌጠ ስራው ድንቅ የሆነ አምላክ የመኖሩ ማስረጃ ናቸው ። ሸክላና ተሽከርካሪ ፣ መርከብና አየር በራሪ ፣ ድልድይና አስፓልት ፣ መኪናና ሌሎችም ሞተር ነክ ነገሮች ፣ ታሪካውያን ህንፆዎች ፣ የሚያስገርሙ ነገሮች ሁሉ ያለ ሰሪ ፣ አትክልትና አዝርዕት ያለ መሬትና ያለ ዘሪ ፣ ልጅ ያለ እናትና አባት እንደማይገኝ ሁሉ ግዑዛንና ግዙፉን ጥቃቅንና ረቂቃን ፍጥረት ሁሉ ያለ ፈጣሪ እንዳልተገኙ እናምናለን ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚታየው ከማይታየው እንደሆነ እናምናለን" እንጂ ዳዊት በመዝሙር 13:1 "ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል" እንዳለው አምላክ የለም አንልም

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

“የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

📖ኦሪት ዘፍጥረት 2፥1-3📖
1.“ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።”
#ሠራዊቶቻቸውም : - በውስጣቸው ያሉት ፍጥረታትንም ሁሉ ፈጥሮ ጨረሰ።
🌍 @yemetshaf_qdus_tinat 🌌
2.“እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።”
#ሰባተኛው_ቀን : - ብርሃንና ጨለማ የተለያዩበት ከስነ ፍጥረት የመጀመርያው ቀን(እሁድ) አንስተን አዳም እስከ ተፈጠረበት(አርብ) ያለውን የብርሃንና የጨለማ ዑደት(ዙር፣መፈራረቅ) ብንቆጥር 6ቀን ይሆናል ስለዚህ ሰባተኛዋ ቀን ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመርያዋ ሰንበት) በአይሁድ "sabbath" የምትባለዋ ናት።የመጀመርያዋ ሰንበት ወይም ቀዳሚት ሰንበት (በተለምዷዊ አጠራር ቅዳሜ) የመባልዋ ምክንያት #እሁድም ሁለተኛዋ ሰንበት(የክርስቲያን ሰንበት፣ሰንበት ዓባይ፣የጌታ ቀን) ተብላ ስለምትጠራ ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር ከመፍጠር ያረፈው በሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚት ሰንበት ላይ ነው።
⏩ @yemetshaf_qdus_tinat

#ዐረፈ : -በስድስቱ ቀናት ከፈጠራቸው ፍጥረታት ተጨማሪ መፍጠርን #አቆመ #ተወ ማለት ነው እንጂ ፈጣሪ ውጣ ውረድ ድካም የለበትም!!።ይህ ቃል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫም ነው። እንዴት? በሰባተኛይቱ ቀን ከስራው ሁሉ ዐረፈ ካለ በኋላ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አይልም አንድ የዕረፍት ቀን ላይ ነው።ፍጥረቱ የሆነው የሰው ልጅ ደግሞ ወደእርሱ እንዲመጣ(እርሱን እንዲያውቅ) በቃሉም እየኖረ እንዲያመልከው ከፈጣሪው ጋር ህብረት እንዲያደርግ ይፈልጋል።
📜 @yemetshaf_qdus_tinat 📜
እስራኤል ከግብፅ ሲወጡ ለአብርሃም ወደ ማለለት ምድር ይገቡና እርሱን እያመለኩ በመንፈሳዊ ሐሳብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖራቸው ነበረ ዓላማው ይህም ለዘለአለማዊው ከእግዚአብሔር ጋር የመኖርን ምሳሌ ነው።በእምነት ቃሉን ሰምተው እየታዘዙት መኖር በመንፈስ ዕረፍቱን መውረስ መካፈል ነው።ነገር ግን ከግብፅ የወጡት ቃሉን ሰምተው አላመኑም ባለመታዘዝ አሳዘኑት ፈጣሪም ከኔ ጋር አንድነት ዕድል ፈንታ የላቸውም አለ።
@yemetshaf_qdus_tinat
⚠️“ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤”— ዘኍልቁ 14፥23

⚠️መዝ94(95)፥10-11 “ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ።ወደ #ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።”

💠ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ዕረፍት በዕብራውያን መልእክቱ ሲያብራራው እንዲህ ይላል
👉“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር #በእምነት_ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።ስለ #ሰባተኛው_ቀን በአንድ ስፍራ፦ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤በዚህ ስፍራም ደግሞ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም።እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ #ዛሬ_ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ #በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ #አንድ_ቀን እንደ ገና ይቀጥራል(ይወስናል)።” ዕብ4፥1-7
🛐 @yemetshaf_qdus_tinat 🛐

3.“እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።”
#ባረከው_ቀደሰውም : - መልካም ነገር እንዲያስገኝ መልካም እንዲሆን መረቀው ለራሱም ለየው።
#በረከቱም እስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ መሪነት ከባርነት ወጥተው አምላካቸውን አውቀው ህግም በተሰጣቸው ጊዜ ከባርነት ወጥተው ብቻ ሳይሆን ከስጋ ስራም በእግዚአብሔር ስራና ዕረፍት ምሳሌ 6 ቀን ሰርተው በሰባተኛይቱ ቀን እንዲያርፉ ሲታዘዙ፤ከሰማይ ይዘንብላቸው የነበረው መና ለነገው ማሳደር አልተፈቀደላቸውም ለቀኑ በቅቷቸው ካደረ መናው ይበላሻል ለየቀኑም አዲስ የዘነበ ይበሉ ነበር በስድስተኛይቱ ቀን ግን ከዘነበው መና የሁለት ቀን ይሰበስቡና በሰባተኛይቱ ቀን መናም አይዘንብም ያደረውም አይበላሽም አርፈው ይመገቡት ነበር (ዘጸ16)።
📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
¹⁰ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
¹¹ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

"ፍትወት ያጠፍኦ ለሂሩት፤ ፍላጎት ቸርነትን ያጠፋል" (መጽሐፈ ገነት)

✨ፈተወ ማለት ፈለገ፣ ወደደ፣ ከጀለ፣ ተመኘ፣ ጎመጀ የሚሉ ፍካሪያት ያለው ቃል ነው። ነገሩ ክፉና ደግ የሚሆነው ግን በአስደራጊ፣ በአድራጊ፣ በአደራራጊ፣ በተደራጊ፣ በድርጊት ነው። ለምሳሌ፦ ፍላጎቱ፣ ምኞቱ፣ ውዴታው፣ እግዚአብሔርን ማየት ከሆነ አስመኝው ራሱ እግዚአብሔር ነው። ተመኝውም መልአክ ነው፣ አብርሃም ነው። መመኛው ሃይማኖት ነው ምኞቱም ሥላሴ፣ ድርጊቱም ጽድቅ ነው፣ ዋጋውም መገለጥ ነው። (አብርሃም አባታችሁ ቀኔን ሊያይ ተመኘ አይቶም ደስ አለው) "መላእክትን የሚያስመኛቸው" እንዲል።
አስመኚው ሰይጣን፣ መመኛው ልብ ጠዋይ፣ ክህደት፣ ፈቃደ ሥጋ፣ ፍቅረ ሢመት፣ ትካዘ ዓለም፣ ሀልዮ መንበር፣ ፍቅረ ዉሉድ፣ ብእሲት ወዘመድ፤ ምኞቱም ሹመት ብዕል ድሎት በጥቅሉ የዓለም የልዕልና ማማ ላይ መውጣት የሆነ ጊዜ ግን "እፎ መልዐ ሰይጣን ውስተ ልብከ፤ ሰይጣን በልብህ ስለምን ሞላ?" የሚያስብል ቅዱሳንን ወደ ታች የሚያስደምም ርኩሰት ይሆናል። የሐ.ሥራ ፭፥፬ እንዲህ ያለው ምኞት ነው ቸርነትን የሚያጠፋ የተባለው።

✨ሰው ሁሉ ቸርነትን አቡሃ ለምሕረት ከሆኑ ከሥላሴ ዘንድ ይሻል። ምሕረትን የሚያገኙ ደግሞ ምሕረትን የሚያደርጉ ናቸው። "ብፁዓን መሐርያን እስመ ሎሙኒ ይምሕርዎሙ፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ይማራሉና" እንዲል። ማቴ. ፭፥፯
ይህ ሳይሆን እነርሱ እየጨከኑ ምሕረት የሚፈልጉ ግን አስደራጊው ሰይጣን ምኞቱ ምሕረት ማድረጊያው ጭካኔ ስለሆነ ፍየል ምሥራቅ ምዝግዝግ ምዕራብ መሆኑ ነው። መድኃኒትን በመርዝ መጠጣት እድን ብሎ ቢጠጡት ማዳኑንስ ቀርቶ መግደሉ ይብስ። የሥላሴን ቸርነት እየፈለጉ መጨከንም ማስማሩ ቀርቶ ያስፈርዳል። ወዲህም ጭካኔ የዲያብሎስ ምሕረት የእግዚአብሔር ስለሆነ ከሰይጣን ተነስቶ ወደ እግዚአብሔር ከመቼ ዕለት ወዲህ ተደርሶ ያውቃል? "እምኀበ እግዚአብሔር ይጸንዕ ሑረቱ ለሰብእ የሰው መንገዱ ከእግዚአብሔር የሆነ እንደሆነ ይቀናል" ተብሎ ነውና የተጻፈው። መዝ. ፴፮፥፴፬

✨ወንድሞቼ ሆይ ሞሕረትን የምንፈልግ ከሆነ ምሕረት ይኑረን። ምሕረትንም ለማድረግ ፍላጎታችን እንጠብቅ። ፍላጎት ምሕረትን ይደመስሳልና። የቀደመው ጠላት ምሕረት አጥቶ የቀረው ምሕረት የለሽ ስለሆነ ነው። ምሕረት የለሽ ያደረገውም ፍላጎቱ ነው። የማይገባውን አምላክነት ተመኘ፤ በክህደት ተመኘ፤ ክፋ ፍላጎቱ በአምላኩ ላይስ እንኳ ጨክኖ አምላክ ነኝ አስባለው። ስለዚህ ምሕረት ያልተገባው ሆነ። ይሁዳ በጌታው ላይ ለመሸጥ ያስጨከነው ክፉ የገንዘብ ፍላጎቱ። ጸሐፍት ጌታን ለመስቀል እንጀራ አበርክተው ያበሏቸውን እጆች ለመቸንከር የጨከኑት ክብርና የሥልጣን ፍላጎት ነው። ሄሮድስ በእናታቸው ወተት ቤተልሔም እስክትነጣ፣ በሕጻናቱ ደም እስክትቀላ እነዚያን ሕጻናት ያረዳቸው ያለ ሽረት ከመግዛት ክፉ መጎምጀት ነው። ኮቲባ ለድንግል ለምን ውኃ አልሰጥም አለች? ቅናቷና ስስቷ ነው።

✨ዛሬም ደም የሚያስፈስስ እኔ ብቻ ልኑር ነው። በሚያለቅሱና እንባን ከማሩኝታ ጋር በሚያቀርቡ ዓይኖች ላይ የሚጨክኑ ሾተል የሚመዙ እጆች ደም የተቀባን እንጀራ መጥገብ የሚልጉ ክፋ ልቦች ያበቀሏቸው ናቸው። በትዳራቸው ላይ የሚደፍሩ ለትዳራቸው ምሕረት የሌላቸው "በቃ ይበተን" የሚሉ ክፉ ምኞት የሚገረኛቸው ናቸው። በርህርኂቷ እመቤት፣ በጽድልቷ ንግሥት፣ በወላዲተ አምላክ ጨክነው ከልባቸው አሰድደው የሚሰድቧት የዛሬ ሄሮድሶችም እኔ ልክበር ልበልጽግ ልብላ ከሚል ምቀኛ ልብ የሚወጣ አሳባቸው ነው። አባቶቻችን የሚገባን መመኘት ጠቢብነት ነው የማያገኙትን ሁሉ መመኘት ግን ምቀኝነት ነው ይላሉ። ሰው በድንግል ማርያም ቢቀና እኔም እኮ ከእርሷ ጋር እኩል ነኝ ቢል አምላክን መውለድ አይችልምና አጉል ምቀኝነት ሆኖ ይቀራል።

✨ሄሮድስ የማይተካከለውን እገላለሁ ብሎ ሕጻናትን እንደገደለ ዛሬም እመቤታችንን ከልባቸው አሰድደው በአእምሮ ሕጻናት የሆኑትን የቤተልሔም እርሷ ልጆችን በምንፍቅና ሾተል ያርዳሉ።
ሄሮድስ እመቤታችንን በእኩይ ፍላጎቱ በርኩስ ቅናቱ አሰድዶ ሞተ። ወዳጄ ቅናትና ምቀኝነት እናታችን ከልባችን አንዳያሰድብን እንጠንቀቅ። ስለረከሱ ሕልሞች ስለሚጣፍጡ የሐኬት እንቅልፎች ውዳሴዋን አቋርጠን የምሕረትን ጠል ያዘለችውን ደመና ከእኛ እንዳትሰደድ እንንቃ። ለሄሮድስ መሰለው እንጂ ርግቢቱስ ገላግልቷን ይዛ በበረሃ ጉያ ውስጥ መዐዛዋን እያወደች ነው። ስለ ክፉ ምኞታቸው ሰማይን ከነ ፀሐይዋ አሳድደው ለጨለሙ ሄሮድሶች ይብላኝ እንጂ እርሷስ በየገዳማቱ "ምስለ ወልድኪ ልዑል በዘባንኪ ኅዙል ጎየይኪ እፎ ድንግል ደወል እምደወል" እየተባለች ትወደሳለች። ብቻ ዘመዶቼ በአንድ በጎ ነገር ላይ "አይ ይቅርብኝ" የሚያስብል አሳብ በመጣ ጊዜ የሰይጣን እንደሆነ አስተውሉ። ለቅዱስ ምኞት ያብቃን!!!
(©መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)

ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

#ኹሉንም_ነገር_ለእግዚአብሔር_እንስጠው
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ወርቅን የሚያነጥር ሰው አንዲትን የወርቅ ቅንጣት ወደ እሳት ውስጥ ጨምሮ እጅግ ንጹህ እስክትኾን ድረስ ይጠብቃታል፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዚሁ ሰዎች እስኪነጹ፣ እስኪለወጡና ባገኛቸው ነገር ጥቅም እስኪያገኙ ድረስ ፈተና ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል፡፡ ይህ ደግሞ ከጥቅምም እጅግ ከፍ ያለ ጥቅም ነው፡፡
ስለዚህ ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም ተስፋ ሊቈርጥ አይገባውም፡፡ ያ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያኽል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኵሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንሔድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቈርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡
ይህን በማስመልከትም ጠቢቡ ሰው እንደዚህ ሲል መክሮናል፡- “ልጄ ሆይ! ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሔድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፤ ልብህን አቅና፤ ኹልጊዜ ታገሥ፤ አታወላውልም፤ በመከራ ብትጨነቅም አትጠራጠር” /ሲራ.2፥1-2/፡፡ “ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ስጠው፡፡” ለምን? እግዚአብሔር ከዚያ መከራ መቼ እኛን ማውጣት እንዳለበት ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ኹሉንም ለእርሱ ልንሰጥ፣ ዘወትር እርሱን ልናመሰግን፣ ኹሉንም ነገር - ጥቅምም ይኹን ቅጣት - በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም ቢኾን ለእኛ ረብሕ የሚኾን ነውና፡፡ አንድ ሐኪም፥ ሐኪም የሚባለው ታካሚውን ገላዉን ሲያጥበውና ሲመግበው እንዲሁም ደስ ወደሚያሰኝ ስፍራ ሲወስደው ብቻ አይደለም፤ በእርሱ (በታማሚው) ሰውነት ላይ የቀዶ ጥገና ምላጭና ቢላ ሲያሳርፍም ጭምር ሐኪም ነው፡፡ አባትም አባት የሚባለው ልጁን ሲንከባከብ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ልጁን ከቤት ሲያስወጣው፣ ሲገሥጸው፣ ሲገርፈውም ያው አባት ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ከሐኪሞችም በላይ ሰውን ወዳጅ እንደ ኾነ በማወቅ፥ ምን ዓይነት የሕክምና ዓይነት እንደሚሰጠን በጥልቀት አንጠይቅ፤ ወይም ደግሞ ለደረሰብን መከራ እርሱን ተጠያቂ አናድርግ፡፡ ከዚህ ይልቅ እርሱ የወደደውን ነገር - ቅጣትም ይኹን ቅጣት የሌለው ነገር - ብቻ ምንም ይኹን ምን በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፡፡ በየትኛውም መንገድም ቢኾን የእርሱ ፈቃድ እኛ እንድንድንና ከእርሱ ጋር አንድ እንድንኾን ነውና፡፡ የትኛው መንገድ ለእኛ እንደሚጠቅምም እርሱ ያውቋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የትኛው መንገድ ወደ እርሱ እንደሚመልሰው ያውቃል፡፡ ኹላችንም እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ልንድን እንደምንችል ያውቃል፡፡ በመኾኑም የሚመራን በዚህ እኛ በምንድንበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ወደየትኛውም መንገድ ቢወስደንም - ልክ እንደ መጻጉዑ - እርሱ እንደሚያዘ’ን ተከትለን መሔድ እንጂ ትልቁ ጉዳያችን በለስላሳና በቀላል አልያም ደግሞ በከባድና በሸካራ ጎዳና እንድንሔድ የሚያዘ’ንን ትእዛዝ መኾን የለበትም (ልንሔድበት የሚገባ’ው መንገድ እርሱ ስለሚያውቀው እንዲሁ መታዘዝ እንጂ የመንገዱን ከባድነት ወይም ቀላልነት የእኛ አጀንዳ ሊኾን አይገባውም፡፡)

(ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልእክታት)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

ሚስትህን አትናቃት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡

እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡

በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡

‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”

“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡

ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡

ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክት እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡

አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡

ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡”

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

✝ አንድ ሰው እግዚአብሔር አስቀድሞ ካነጋገራቸው ሰዎች ጋር እንደተነጋገረ ከእኔ ጋር በቀጥታ አልተነጋገረም ታዲያ የእግዚአብሔርን በረከት እንዴት ልቀበል እችላለሁ ?ለዚህስ እርግጠኛ የምሆነው እንዴት ነው? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ።
ሰው የእግዚአብሔርን በረከት ትእዛዛቱን በመጠበቅ ሊቀበል እንደሚችል እርግጥ ነው ይህ የመታዘዘዝ በረከት ነውና ።

በረከትና ትእዛዛትን በመጠበቅ መካከል ያለው ግንኙነት በኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ በእግዚአብሔር እንዲህ ተረጋግጧል ፦ " የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል ።...አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ ። የሆድህ ፍሬ የምድርም ፍሬ የከብትህም ፍሬ የላምህም ርቢ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል ። አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ ። እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል ።. .. እግዚአብሔር በረከቱ በአንተ ላይ በጎተራህ በእጅህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ያዝዛል ። " [ዘዳ 28*1_8 ] ።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን አሥራት በማውጣት ላይ ያለው የእግዚአብሔር ትእዛዝና እርሱ ለሰው ገንዘብ ላይ ያለው መብት ነው ።
አንድ ሰው ገንዘቤ ለእኔ ሳይበቃኝ እንዴት ከዚያ ላይ አስራት ላወጣ እችላለሁ ብሎ በአድናቆት ሊጠይቅ ይችል ይሆናል ። እውነቱን ለመናገር ግን ያለ በረከት ከሚመጣው ጠቅላላ ገንዘብ ይልቅ ከአሥር አንድ የተቆረጠለት ገንዘብ ይበልጣል ። ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ታላላቅ የገንዘብ ገቢ ኖሮአቸው ምንም ሳይበቃቸው የምንመለከተው ገንዘባቸውን ስላላስባረኩ ነው ።


አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

*ምክረ አጋንንት*

በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ

ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።
# በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
# ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
# እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።
ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
# ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሄር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።።

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

👉ጸሎት ለማድረግ አታቅማማ፤ ሥጋ ከምግብ በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብፃዊ)

ስለሁሉም ነገር ሳታቋርጥ ጸልይ፤ እንዲህ ካላደረግክ ምንም ነገር ያለ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የማታከናውን ትሆናለህ፡፡ ያለጸሎት ራሱን በማንኛውም ዓለማዊ ጉዳዮች የሚያደክም ሰው በመጨረሻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡ (አባ አጋቶን)

እግዚአብሔር ለሰው ምሕረትን ሲያድል አንድ ሰው እንዲጸልይለት ያነሣሣዋል፡፡ በዚህ ጸሎት አማካኝነትም ይረዳዋል፡፡ በመከራ ጊዜ ያለማቋረጥ መሓሪውን አምላክ በጸሎት ጥራው፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለነፍስ ቁስል መድኃኒት ነው፡፡ ሰው በታመመ ጊዜ ዶክተሩ ፍቱን መድኃኒትን ፈልጎ ለበሽተኛው እንደሚሰጠው መድኃኒቱም ወደ ሰውነቱ ገብቶ ሥራ ሲሠራ እንጂ እንዴት እንደሚሰራ እንደማናውቀው በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ስም አዘውትረን ስንጠራ እንዴት ጸሎታችን እንደሰራ ሳናውቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ምህረትና ርኅራኄ በእኛ ላይ ሲደረግ እንመለከታለን፡፡

(አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

መላው የኦርቶዶክስ ልጆች አዲሱን ዓመት በዘፈንና ዳንኪራ ሳይሆን በቤተክርስቲያናቸው በጸሎት ፣ በምህላ፣ የቻለም ደግሞ በመጾም፣ እግዚአብሔርን በመመለመን እንዲቀበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላለፈች።

ቤተክርስቲያን ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው የአዲሱን ዓመት አቀባበል በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ ነው።

በዚህም የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ ታውጇል።

ቤተክርስቲያን ፤ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ስትል ጥሪዋን አቅርባለች።

ምዕመናን በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ አሳስባለች።

ብፁህ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ ፤ " አንዳንድ የዘፈን ግብዣዎችን እየሰማን ነው ፤ ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት የዳንኪራ ግብዣ እየሰማን ነው " ብለዋል።

" ለምንም የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች እየተስተጋቡ ነው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይህን እየሰማን ያለነው መደፋፈሩ በዝቶ ፣ ከመጠን በላይ ኑሮ፣ ንቀቱ በዝቶ፣ ማንአለብኝነቱ እንደልብ ተናጋሪው ፣ ፀብ አጫሪው ሃይ የሚለው ጠፍቶ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው አለኝ ባሉት መረጃ " ቤተክርስቲያን ዘቅዝቆ እሳት ያያያዘ ፣ መስቀል ዘቅዝቆ አንገቱ ላይ ያጠለቀ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊዘፍን ተዘጋጅቷል፤ ግብዣም ተደርጓል። " ብለዋል።

" የሰዎችን መብት መንካት ስለማንችል እንደ ኢትዮጵያውያን እገሌ እገሌ ሳይል ከእንዲህ አይነቱ ማንም ተካፋይ ሳይሆን እንደ ኦርቶዶክሳዊያን ዳግሞ የኦርቶዶክስ ልጆች ለፀሎት ታውጇል ፣ ለጾም ለጸሎት እራስን ከማዘጋጀት ውጭ ምንም ትርፍ የሌለው ከሳንቲም ውጭ ትርፍ ለሌለው የሀገርን ገፅታ የሚንድ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከመሆን #እንድትቆጠቡ " ብለዋል።

" አባቶቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት ለጾም ፣ለጸሎት ለፍቅር፣ ለሰላም ነው ፤ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚሉት አባቶች በዘፈን እና በዳንኪራ እያሳሳቀ ወደ ሞት፣ ወደ ማዕበሉ የሚገፋ ነገር ላይ ተሳታፊ እንድንሆን ቤተክርስቲያን አትፈቅድም ፣ የሃይማኖት ሰዎችም ድርሻ አይደለም " ሲሉ አስግዝበዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " እኔ ምን አገባኝ በሚል በዘመናዊ ስሜት እንደልብ ተካፋይ መሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ነውር ነው ፤ ወንጀልም ነው " ያሉ ሲሆን " ፀብ አጫሪ መሆንም አስፈላጊ ስላልሆነ የኦርቶዶክስ ልጆች በቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ተቀመጡ፤ የሚመለከተው እንደፈለገ ይሁን ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔርን ለምኑ አብረን ተያይዘን እንዳንጠፋ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በጳጉሜን 6 ቀናት ሁሉም ምዕመናን እግዚአብሔር መጪውን ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ የአንድነት፣ ብሶተኛ የማይኖርበት ተራብኩ ተጠማሁ ተፈናቀልኩ ተሰቃየሁ ተንገላታሁ የሚል የማይኖርበት ፣ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ዘመን እንዲሰጠን ጸሎት በማድረግ እናሳልፍ ስትል አደራ ብላለች።

ጸሎት ለሁሉም የታወጀ ሲሆን ፤ ጾምን በተመለከተ የወደደ ይጹም ፤ ያልወደደም / ፕሮግራሞች ቀደሞ የያዘም እንዲጾም አይገደደም በነፃነቱ መጠቀም ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

Ebakachu admetut...Nefsun madan mifelg hulu yadmetew

https://youtu.be/cYTEjugZoV4

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

#በእርሱ #ቊስል #እኛ #ተፈወስን

ጲላጦስም የካህናት አለቆችንና መኳንንትን ሕዝቡንም በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህንን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት እነሆም በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም፡፡ ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም ወደ እኛ መልሶታልና እነሆም ለሞት የሚያደርሰው ምንም #አላደረገም፡፡ እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው (ሉቃ. ፳፫፥፲፬‐፲፮)

ጲላጦስ የጌታችንን ንጹሕ መሆን ካወቀ በኋላ ቀጥቼ #እፈታዋለሁ አለ፡፡ ንጹሕ በመሆኑ ምክንያት የተቀጣ #ከጌታችን በቀር ማን አለ? ጲላጦስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ስለፈለገ ያን ሁሉ ጥያቄና መልስና ሕጋዊውን የፍርድ ሒደት ማስፈጸም ትቶ በንጹሑ ጌታ ላይ ግርፋት እንዲወርድበት ፈረደ፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ #በውርደቱ ፍርዱ #ተወገደ ብሎ #እንደተናገረው ትንቢት ጲላጦስ በእርጋታ ጀምሮት የነበረውን ሕጋዊ የምርመራና የፍርድ ሒደት አሽቀንጥሮ ጥሎ (አስወግዶ) ከሕግ ውጪ በዚያች ቀን በአይሁድ እጅ የተዋረደውን ጌታ ያለ ፍትሕ እንዲገረፍ ወሰነበት፡፡ (ሐዋ. ፰፥፴፫)

ጲላጦስ #ኢየሱስን ይዞ #ገረፈው (ዮሐ. ፲፱፥፩) የጲላጦስ አሳብ #በመሰቀሉ ፈንታ ግርፋት ቢገረፍ ሕይወቱን ካዳንኩለት #ቢቆስል ምንም አይደለም የሚል ነበር፡፡ አይሁድም የግርፋቱን ጽናት አይተው ይሙት ማለታቸው እንደሚቀር ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከትናንት ምሽት ጀምሮ ታስሮ ሲንገላታ ያመሸውን ፣ በሐናና ቀያፋ ግቢ ውስጥ ሲደበደብና በጡጫ ሲመታ ያደረውን ጌታ በምሕረት የለሾቹ የሮም ወታደሮች እጅ እንዲገረፍ አሳልፎ #ሠጠው፡፡

የሮማውያን ግርፋት እንደ አይሁድ ግርፋት በጅራፍ ብቻ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘቂሣርያ እንደገለጠው ጅራፉ በቆዳ ከተሠራ በኋላ በላዩ ላይ ስለታማ የሆኑ የብረት ኳሶች ሾለው የተሳሉ የአጥንት ስብርባሪዎች ይደረጉበታል፡፡ በዚህ አሰቃቂ የግርፋት መሣሪያና በጨካኞቹ ወታደሮች እጅ ወድቀው ሥቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው የሞቱም ብዙዎች ናቸው፡፡

በጅራፉ ላይ የተሠሩት የብረት ኳሶችና የአጥንት ስብርባሪዎች በሚገረፈው ሰውነት ላይ ሲያርፉ ሥጋውን እየነጩ የሚነሡ ስለሆኑ ጅራፉ በሰውነት ላይ ማረፉ ብቻ ሳይሆን ከሰውነት ላይ የሚነሣበትም ቅጽበት እጅግ ለመግለጽ የሚከብድ ሥቃይ የሚያደርስ ነው፡፡ የግርፋቱ መጠን በጨመረ ቁጥር የደም ሥሮችና #አጥንቶች እስከሚታዩ ድረስ የሚጎዳ ፣ የጎድን አጥንቶችን መሰባበር ፣ ከፍተኛ የሆነ ውጪያዊና ውስጣዊ የደም መፍሰስ ፣ የሳንባ መጎዳት የሚያስከትል አሰቃቂ ሒደት ነው፡፡😢

በዚያች ቀን #ጌታችንን ለመግረፍ የተመደቡት ወታደሮች እስራኤልን በብርሃን ዓምድ በሌሊት የመራቸውን #አምላክ #ሙሴና #አሮንን #በደመና ዓምድ ያነጋገራቸውን አምላክ በድንጋይ ዓምድ ላይ ለመግረፍ ዕርቃኑን #አሰሩት፡፡ የካህናት አለቆችን ደስ ለማሰኘት ሲሉም በሙሉ ኃይላቸው በታላቅ ጭካኔ እጅግ ብዙ ግርፋትን አዘነቡበት፡፡ አንድ ገጣሚ እንዳለው በሙሴ አድሮ #የፈጣሪን ክብር ለማየት የለመነው የሰው ልጅ ፈጣሪ በጊዜው #ጀርባዬን #ታያለህ ብሎ የገባለትን ቃል ቢፈጽምለትና ጀርባውን ቢያሳየው ግርፋትን አዘነበበት፡፡ (ዘጸ. ፴፫፥፳፫) በእርግጥም ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ #ከጲላጦስ ግርፋትን ይቀበልበት ዘንድ ጀርባን ፈጠረ እንዳለው አምላክ ሰው የሆነውና ጀርባን ለራሱ ያዘጋጀው ስለ ሁላችን #ኃጢአትን #ግርፋትን ሊቀበልበት ነበር፡፡ 😭

የሮማውያን ግርፋት ቅዱስ ጳውሎስ እንደተገረፈው እንደ አይሁድ ግርፋት በመጠን ተወስኖ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ› እያለ የተገረፈው ሰው በሕይወት ተርፎ እያስታወሰ የሚናገረው ዓይነት ግርፋት አይደለም፡፡ (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፬)
ቤተ ክርስቲያናችን #የጌታችን ግርፋት #ስድስት #ሺህ #ስድስት #መቶ #ስድሳ #ስድስት ጊዜ እንደሆነ ስታስተምር አምስት ሺህ ነው ፣ አራት ሺህ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህን አሰቃቂ ግርፋት በሺህ ለሚቆጠር ጊዜ መገረፉን ግን ሁሉም ሊቃውንትና የታሪክ ሰዎች ተስማምተውበታል፡፡ ጌታችን እጅግ መገረፉን የሚያሳየን መስቀሉን ባሸከሙት ጊዜ በየሥፍራው እስኪወድቅ ድረስ አቅም ማጣቱ ነው፡፡

የጌታን ግርፋቱንስ መቁጠር ቢቻልም እንኳን ሥቃዩን ግን እንዴት ልንቆጥረው እንችላለን? ቤተ ክርስቲያናችን ከሥጋው አልፎ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ ስለ ተገረፈው አምላክ በዕለተ ዓርብ የምታነበውና የምታዜመው ራሱ #ክርስቶስ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት አድሮ ስለሕማሙ የተናገረው የትንቢት ቃል የሥቃዩ መጠን ጥቂትም ቢሆን ለማሰብ ያግዘናል፡-

‹‹እንደ ውኃ ፈሰስሁ #አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ #በአንጀቴም መካከል ቀለጠ…
#አጥንቶቼ ሁሉ #ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ #ተመለከቱኝም …
#አጥንቶቼ #ተነዋወጡ (መዝ. ፳፪፥፲፬፣፲፯፤፴፩፥፲)

ቅዳሴያችን እንዲህ ይላል #የወልድን መከራውን የሚናገር ምን ዓይነት አፍ ነው? ምን ዓይነት #ከንፈር ነው? ምን ዓይነት አንደበት ነው? #የፍቅር #ጌታ #ሕማማቱ በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፤ ሕሊናም ይመታል #ነፍስም #ትንቀጠቀጣለች #ሥጋም #ይደክማል በእውነትም #የጌታችንን ሥቃይ ለመግለጽ ምንም ዓይነት ቋንቋ ምንም ያህል ቅኔ አቅም አይኖረውም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬምም :-
#በክርስቶስ #የተወደዳችሁ ሆይ ኑ! ወዲህ ቅረቡ በዚች ዕለት በዳዊት ከተማ የሆነውን አብረን እንይ #በተስፋው ቃል ሲጠበቁ የነበሩት የተመረጡት #የአብርሃም #ዘሮች ዛሬ ምን እንዳደረጉ እንመልከት! ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል?›› ይላል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው #ስለ #እኛኃጢአት ነበር፡፡ ኦሪት የሚገረፍ ሰው ‹‹የግርፋቱም ቊጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን›› ትላለች፡፡ (ዘዳ.፳፭፥፪) ጌታችን ማንም ስለ ኃጢአቱ ሊወቅሰው የማይችል ንጹሕ ቢሆንም #እግዚአብሔር #የሁላችንን #በደል #በእርሱ ላይ #አኖረ ስለተባለ ግርፋቱም በተሸከመው የእኛ ኃጢአት መጠን ሆነ፡፡

እርሱ #ስለመተላለፋችን #ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ #የደኅንነታችንም ተግሣፅ #በእርሱ ላይ #ነበረ በአጋንንት እጅ ልትገረፍ የጸጋ ልብስዋን አውልቃ ዕርቃንዋን በሲኦል የወደቀች ነፍሳችንን ነጻ ያወጣት ዘንድ እርሱ በጨካኝ ወታደሮች እጅ #ዕርቃኑን #ተገረፈ፡፡

እኛን #ከሚገባን #ግርፋት ያድነን ዘንድ #ኢየሱስ የማይገባውን ግርፋት #ተገረፈ የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ ተነከሩ ከግርፋቱ ጽናት የተነሣ ሥጋው ሁሉ አለቀ #ሐዋርያው #ጴጥሮስ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ በማለት እንደተናገረ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን (፩ጴጥ. ፪፥፳፬፤ኢሳ. ፶፫፥፭)

#ህማማት #በዲያቆ #ሄኖክ #ሀይሌ✍

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡ በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29
የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!!👉🙏🙏

ለማንኛዉም አስተያየትዎ @menfesawimekerbot ይፆፋልኝ ይደርሰኛል::
@menfesawimeker
@menfesawimeker

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

† ጋብቻና የሰው ጥንተ ተፈጥሮ - ፩ †

አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን ጋብቻ በገነት ውስጥ በነበረው የሰው ልጅ ሕይወት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳን ለወደቀው የሰው ልጅ ድጋፍ እንዲኾን እግዚአብሔር የመሠረተው ቢኾንም፥ ከውድቀት በፊት ግን አልነበረም፡፡ እንዲህም ማለታችን በገነት ውስጥ የነበረው ድንግልና አሁን ከምናውቀው ዓይነት ድንግልና እንደሚለይና እጅግ እንደሚልቅ ኹሉ፥ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነትም አሁን ከምናውቀው የባልና የሚስት አንድነት የሚለይና እጅግ የሚልቅ ነበር፡፡ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነት ምሥጢራዊ አንድነት ነው፡፡ ሔዋን ለአዳም ረዳት ኾና ስትሰ’ጠው፥ አሁን በጋብቻ ውስጥ የምናውቀውን ዓይነት ረዳትነት እንድትሰጠው አልነበረም፡፡ አሁን በምናውቀው ዓይነት ጋብቻ ውስጥ ሚስት ለባሏ ረዳት ከምትኾንባቸው ነገሮች ዋናው ነገር፥ ፍትወት ሲበረታበት በዝሙት እንዳይወድቅ ሸክሙን ማቅለል ነው፡፡ ባልም እንደዚሁ ለሚስቱ! በገነት ውስጥ ከውድቀት በፊት የነበረው የሔዋን ረዳትነት ግን እንደዚህ አልነበረም፡፡ የተሰጠችው እንድታወራው፣ እንድታጽናናው፣ እኩል ክብሩን እንድትጋራ፣ በኹለንተናዋ እርሱን እንድትመስል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በእንተ ድንግልና” በተባለ ተወዳጅ መጽሐፉ ይህን ሲያብራራውም እንዲህ ይላል፡-

“እግዚአብሔር ይህን ዓለም ለጥቅማችን ፈጥሮ ከፈጸመና ዝግጁ ካደረገ በኋላ፥ በመጨረሻ ይህ ዓለም ለእርሱ የተፈጠረለትን ሰውን ፈጠረ፡፡ ከተፈጠረ በኋላም የሰው ልጅ በገነት ኖረ፤ ለጋብቻ የሚኾን ምክንያትም አልነበረም፡፡ ሰው ረዳት ያስፈልገው ነበር፤ ወደ መኖርም መጣች (ተፈጠረች)፡፡ ያን ጊዜም ቢኾን [አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡ ከንጹህ ምንጭ ጽሩይ ወንዝ እንደሚፈልቅ፥ እነርሱም (አዳምና ሔዋንም) በገነት በድንግልና ውበት ተጽደልድለው ይኖሩ ነበር፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆም እንዲህ ይላል፡-
“ያን ጊዜ [አሁን የምናውቀው ዓይነት] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡”

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

ስለ ሰባቱ ሰማያት !
♡ጽርሐ አርያም ፦
ሰማየ ሰማያት ፣ ከሰማያት ሁሉ በላይ ያለች ሰማይ ናት ፤ ዳር ድንበሯ ከእግዚአብሔር
በቀር ማንም አያውቀውም፡፡
♡መንበረ ስብሐት ፦
አራት ቅርጽ ያላት ሲሆን ድንኳን ትመስላለች ፤ የምንኖርባትን ዓለም ታክላለች ። ሥላሴ
በፈለጉት መጠንና መልክ ለቅዱሳን ይገለጡባታል ። ሰባት የእሳት መጋረጃም አላት ።
ዘፍ ፳፰፡፲፪-፲፯
ኢሳ ፮፡፩-፪
♡ሰማይ ውዱድ ፦
ኪሩቤል የሚሸከሙት የሥላሴ ዙፋን ነው ።
ሕዝ ፲፡፲፱-፳
♡ኢዮር ፣ ራማ ፣ ኤረር ፦
እነዚህ ሦስቱ የመላእክት ከተሞች ሲሆኑ ከአድማስ እስከ አድማስ የተዘረጉ ናቸው ። ከላይ
ወደ ታች ፣ መጀመርያ ሰማይ ውዱድ ፤ ቀጥሎ ኢዮር ፣ ቀጥሎ ራማ፣ ቀጥሎ ኤረር የተያያዙ
ናቸው ። ስፋታቸውም እኩል ነው ።
♡ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ፦
አራት መዓዘን ፣ 12 በሮች አሏት ፡፡ በውስጧ የብርሃን ሳጥን የተቀረጸ ከሥላሴ ፀዳል
የተሣለባት ታቦት ዘዶር አለች ፡፡ ይህቺም የእመቤታችን ምሳሌ ናት ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፦
ዓይን ያላየው ፤ ጆሮ ያልሰማው ፣ በሰውም ልብ ያልታሰበ ፣ እግዚአብሔር ለሚወዱት
ያዘጋጃት ያላት ይህቺው ናት
፩ኛ ቆሮ ፪፡፱-፲ ። መጠኗም የተወሰነ ነው ።
ባለ ራእዩ ዮሐንስ አዲሲቱ ሰማይ ያላትም ይህቺው ናት
ራእ ፳፩፡፪-፫ በጕበኖቿ የ12ቱ ሐዋርያት ስም ፤ በመድረኮቿ የ12ቱ ነገደ እስራኤል ስም ፤
በአዕማዶቿ የጻድቃን የሰማዕታት ስም ተጽፎባታል
ራእ ፳፩፡፲፩-፲፭ ።
(ስነ ፍጥረት)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

#አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)

ምንጭ፡- ከቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

"ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው። የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።"
📜(መጽሐፈ ምሳሌ፡ 16፥21-24)📜

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

‟መብረቅ ሲጮህ ሰው ሁሉ እንደሚደነግጥ የአንቺንም ስም ሲሰማ ዲያቢሎስ ይደነግጣል። አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ እረፍት አላገኘምና ነው። በአንቺ ታመመ በልችሽ መስቀል ተሰቃየ ስለሆንም ከፍጥረት ሁሉ አንቺን ይጠላል”።
(ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

ጌታችን ለወንበዴው <<በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ > የሚል ልመና እውነት እውነት እልሃለሁ ፤ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ብሎ ወዲያውኑ :መልስ ሰጠ በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ፧ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው ።
በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግስት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት ፡ከቁጣ የራቀ ምህረቱ የበዛው አምላክ :ክፉ ስራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል <የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል ስለዚህ ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ! ይህንን ምህረት ተስፋ አድርገን << ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንት በኃጢአት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ እያልን እንጸልያለን !

#ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሕማማት መጽሐፍ ገፅ 354)

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡

አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ለመዳን፣ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ

Читать полностью…

መንፈሳዊ የህይወት ምክር

+++ አንድ "ግዩር" እንዲኽ ይመክራል +++

(መጋቤ ወብሉይ ወሐዲስ ቀሲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ እንደጻፉት)


ስለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እንውደድ እንጅ ስለ ሰው ብለን እግዚአብሔርን መውደድ አይገባንም ። በእግዚአብሔር ፊት ሰውን መውደድህን ይገለጥልህ እንጅ በሰው ፊት የእግዚአብሔር ወዳጅ ለመምሰል ብለህ የምትኖ ር አትሁን ። ለሰዎች ብለህ እንደወደድከው ለሰዎች ብለህ ልትጠላው ትችላለህ እና።

......


የእግዚአብሔር ሰው መሆን ማለት እግዚአብሔርን መመገብ እንጅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም ። ለመዳን ብለህ እወቅ እንጅ በእውቀትህ የምትድን አይምሰልህ ። የማታውቀውን የምታውቀው ልትኖረው እንጅ እውቀቱ በክርስቶስ ቀኝ ሊያቆምህ አይምሰልህ ። በጎ ነገርን ያወቅሃት ዕለት ብቻ ደስ አይበልህ ፥ የሠራሃት ዕለት እንጅ ፥ በመሥራትህም አትመካ አልፈጸምካትምና ። ከእግዚአብሔር ያወቅሃትን መልካም ነገር ወዲያው ሥራት ፥ እየሠራሃት ያለችህን መልካም ነገር አትልቀቃት ። እየኖርክ ተማር እንጅ እየተማርክ ብቻ ዘመንህን እንዳትፈጽም ተጠንንቀቅ ። ያለ ዕውቀት ብትኖር ከፍርድ የምታመልጥ አይደለምና መቼም ቢሆን ከቤተክርስቲያን ጉባዔያት አትታጣ ፥ በማወቅህ ፍርድ አይቀርልህምና ያወቅኸውን ፈጥነህ ሥራ ።

.....

ቤተክርስቲያንን በኹለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት ዕወቃት ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት ። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን ፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ ። እሊህም ፦ ኪዳን ማስደረስ ፥ ማስቀደስ ና ንስሐ ገብቶ መቁረብ ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው ። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ ።

.....

በሕይወትህ ኹሉ ቤተክርስቲያናዊ ኹን ! ብቻየን ለፋሁበት ብለህ ገንዘብህን ብቻህን አትጨርሰው ። ከምታገኘው ሁሉ ለመድኀኔዓለም ድርሻ አስቀምጥ ። የለመነህን ሰው አትመርምረው ቢቻልህ ስጠው ባይቻልህ እዘንለት እንጅ ። ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አታብጅለት ። መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው ፥ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው ። እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲዖል ሰው ለመሆንህ ዋጋ እንዳለው እወቅ ። ይቆየን መልካም የሆነ እግዚአብሔር ለመልካም የሚሳብ መልካምን የሚያደርግ በመልካሞ የሚጸና በጎ ሕሊና ይስጠን!


አባ ገብረኪዳን
ሰኔ ፲፯ - ፳፻፲፪ ዓም

----------------
ማሳሰቢያ፦ "ግዩር" የሚለው ቃል "መጻተኛ ፣ ስደተኛ..." የሚል ትርጒም አለው። ነገር ግን አባታችን በምን አገባብ እንደተጠቀሙት እርሳቸውን መጠየቅ ሳያሻ አይቀርም

Читать полностью…
Subscribe to a channel