nehmeya | Unsorted

Telegram-канал nehmeya - ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

-

ይህ የየካደ/ም/ቅ ኪዳነ ምህረት እና መድሀኒአለም አካባቢ ወጣቶች ማህበር የቴሌግራም ቻናል ነው። በቻናላችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ አስተያየት ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩ @Mahebranehmyabot ያድርሱን። ከቴሌግራም በተጨማሪ ፌስቡክ ላይም ያገኙናል። https://m.facebook.com/ማህበረ-ነህምያ-ዘ-ኮተቤ

Subscribe to a channel

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya @Nehmeya

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

ዘወረደ(ጾመ ሕርቃል)
ዘወረደ የአብይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ሲሆን ዘወረደ ማለት የቃሉ ትርጉም ወረደ ማለት ነው።በዚህ ሳምንት ቤተክርስትያናችን እየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ፍቅሩን ሊገልፅልን ከሰማያት ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ነስቶ መውለዱን የሚታወስበት የሚዘከርበት ሳምንት ነው።
ዮሐ ፫፥፲፫ ጀምሮ ስለ ጌታችን ወደ ምድር መምጣት በስፋት እናገኛለን።
                     ጾመ ሕርቃል
የአብይ ጾም የመጀመሪያዋን ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል ይባላል ይህም የተባለበት ምክንያት በ614አ·ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉስ እየሩሳሌምን በመውረር ንግስት እሌኒ ካሰራችው ቤተመቅደስ የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን መስቀል እና ሌሎች ንዋየ ቅድሳትን ዘርፎ ከተማዋን አቃጥሎ ወደ ሀገሩ ይመለሳል።በዚያን ጊዜ ከተረፋት መካከል  በ628አ·ም የደረሰባቸውን በደል ለሮሙ ክርስትያኑ ንጉስ ሕርቃል ይነግሩታል።እርሱም ሀዋርያት ሰው የገደለ እድሜውን ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ አላቸው እነሱም የአንተን እድሜ እኛ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ሁሉም
በአግባቡ ጾመውታል።ንጉስ ሕርቃልም ጦር መዞ ኪርዮስ ተዋግቶ የእየሱስ ክርስቶስ መስቀል፣ንዋየት ቅድሳቶችን እና ምርኮኞችንም ይዞ ወደ እየሩሳሌም ተመለሰ።ይህን
በማሰብ እንዲሁም መስቀልህን ከምርኮ እደመለስክ እኛንም ከሀጥያት ምርኮ ነፃ አውጣን ብለን እንጾመለን።ጾመ ሕርቃል ከአብይ ጾም ጋር የምንጾማት ምክንያት ጾሙ በዚህ ወቅት ስለነበረ ነው።
  @Nehmeya     @Nehmeya
✥ በጾማችን ጠላታችን ዲያቢሎስን ድል
የምንነሳበት ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት ያድርግልን
✥ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya @Nehmeya
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ መታሰብያ ክብረ በአል አደረሰን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

†    አቡነ መድኃኒነ እግዚእ   † 

መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ [አዲግራት] ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል [የምሥጢር] መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን [በተለይ ከ፲፫ኛው እስከ ፲፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው] የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ ፦

- ክርስትና ያበበበት::
- መጻሕፍት የተደረሱበት::
- ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
- ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ :-

- አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
- አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
- አባ ሰላማ ካልዕ::
- አቡነ ያዕቆብ::
- ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
- አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
- አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

በተጨማሪም :-

- ፲፪ ቱ ንቡራነ ዕድ::
- ፯ቱ ከዋክብት::
- ፵፯ቱ ከዋክብት::
- ፭ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ፯ቱ እና የ፵፯ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው ፫ቱ ሳሙኤሎች [ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ] : የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም [ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው] የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር ፫ ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም ፻፹ ነው::

" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" [መጽሐፈ ሰዓታት]

" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" [አርኬ]

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

#መግለጫ

ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya @Nehmeya

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                  ጾመ ነነዌ
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፬ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም
(፳፻፲፫ ዓ.ም) የካቲት ፲፭ ቀን ትጀመራለች፡፡
ይህቺን ጾም የጾሟት የነነዌ ህዝቦች ናቸው።በዚህችም ከተማ ከመቶ ሀያ ሺህ በላይ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር ትንቢተ ዮናስ ፬፥፲፩ ላይ ተፅፎ እናገኛለን።በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲልቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ
ላከው/ሉቃ.፲፩፥፴ ትንቢተ ዮናስ ፩፥፪/።ዮናስ ግን ወደ ነነዌ ሳይሆን ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብ ላይ ገባ።በመርከቢቱም ላይ ታላቅ መአበል ተነሳ መአበሉኑ ለማስቆምም እጣ ተጣጣሉ እጣውም ዮናስ ላይ ደረሰ ዮናስንም ወደ ባህሩ ጣሉት።ዮናስንም የሚውጥ ታላቅ አሳ አንበሪ እግዚአብሄር አሰናዳ ዮናስም፫ቀን ፫ለሊት በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ቆይ በ፫ተኛው ቀን አሳ አንበሪው የብስ ላይ ተፋው።ዮናስም ወደ ነነዌ ሄዶ  በሶስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለባበጣለች አለ።የነነዌ ሰዎችም ለፆም አዋጅ ነገሩ።ከሰው እስከ እንስሳ አንዳች እንዳይቀምሱ ከብቶችም አንዳይሰማሩ አዋጅ ታወጀ። እግዚአብሄርም ንስሀቸውን ተቀበላቸው ከመቅሰፍትም ዳኑ።በዚህ ምክንያት ይህችን ፆም ፆመ ነነዌ ብለን እንጾማታለን።ለተጨማሪ ትንቢተ ዮናስ ሙሉውን ተመልከቱ።
@Nehmeya     @Nehmeya
✥ ነነዌ ከጥፋት የዳነችው በጾም ነውና እኛም ከዚህች ጾም ጾመን ረድኤት በረከት የምናገኝበት ሀገራችንን ከጥፋት የምናድንበት ይሁንልን።
✥ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

 †††   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  †††
       ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ ፆመ ነነዌ ለስንት ቀን ነው ምትፆመው?
፪ ፆመ ነነዌ የነነዌ ሰዎች የፆሟት ለምንድ ነው?
፫  የዘንድሮ አመት(2013) ፆመ ነነዌ መቼ ይጀምራል ?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
 ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya @Nehmeya

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

             እናቴ እመቤቴ

እናቴ እመቤቴ/ የማትጠፊው ከአፌ/2/
በረከቴ አንቺ ነሽ/ የመስቀል ስር ትርፌ /2/
አምላኬ ሸልሞኝ ለዘላለም ያዝኩሽ
ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ
                 አዝ
በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ፀዳሉ
የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ
ተወዳጁ ልጅሽ ፀጋውን ያብዛልኝ
እድሜዬ እስኪ ፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ
                አዝ
ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንኢ ንኢ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ የማልነጥልሽ
                አዝ
ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ
ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ
አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ
የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ
               አዝ
መች በስጋ ጥበብ ሰው ለአንቺ ይቀኛል
ከአምላክ ከአልተላከ ከፊትሽ ይቆማል
አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ
በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ስላሴ
                 አዝ
ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም
ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም
እኔን በእደ ፍቅርሽ የምትባርኪ
ኦ ምልዕይተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

            በትረ ሙሴ (አርዌ ብርት) 

 ቅዱስ ፓትሪያርኩን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉ በእጃቸው በሚይዙት በትር ላይ የለው እባብ ምንድ ነው ?

አንዳንድ ወገኖች በበትሩ ላይ የሚታዩት አራዊት ዘንዶ ናቸው በማለት ነገርየውን #ከ666 ጋር ለማያያዝ ሲሞክሩ ይታያሉ ። ነገር ግን በፎቶው ላይ እንደሚታየው ዘንዶ ሳይሆን የእባብ ምስል ነው ። እባቡም ደግሞ እንደምትመለከቱት ከመስቀሉ ስር ነው የሚታየው ። ምክንያቱም መስቀል የሁሉም የበላይና እባብ የተሰኘው ዲያብሎስም አናት አናቱን የተቀጠቀጠበት ነውና ።

[ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ ] ማቴ 22፣29 ።

የኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናትን የሚመሩ ቅዱሳን ፓትርያርኮችና ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ኤጲስ ቆጶሳትም በእጃቸው የሚይዙት አርዌ ብርት/መስቀልና የእባብ ምልክት ያሉበት/ በትር ምሳሌነቱ ከመስቀሉ ስር ያለው ሙሴ ለሕዝቡ መዳኛ ያደረገው የናስ እባብ ምሳሌ ነው፡፡ “ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ” ። ዘኍ 2፣ 19 ። ይኼ ምሳሌ መሆኑን ክርስቶስ ሲያስተምር “ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል” ። ዮሐ 3 ፣ 14 በማለት ምሳሌና ጥላ የነበረውን አማናዊ ለማድረግ፣ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ያዩት ሁሉ እንደሚድኑ አመሳስሎ አስተማረበት ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የናሱን እባብ ከራሱ ስቅለት ጋራ ሲያነጻጽረው ያላፈረበትን፤ የእኛ አባቶች የናሱን እባብ ምሳሌ “በትረ ሙሴ” የሚባለውን በግራ እጃቸው፣ የተሰቀለበትን መስቀል በቀኝ እጃቸው ቢይዙ የሚያሳፍር አይሆንም፡፡

የብሉይ ኪዳን ምሳሌ የሆነውን የናሱን እባብ ስናይ እስራኤላውያን የዳኑት በዚህ በፓትርያርኩ በግራ እጃቸው ባለው የናስ እባብ ነው ብለን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈልንን እንድናስታውስና፣ እኛ ግን የዳንነው በቀኝ እጃቸው ባለው መስቀል ላይ በተሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማለት ለመመስከር ሁለቱንም ማለትም ብሉዩንም አዲሱንም፤ የናሱን ምስልና የክርስቶስን መስቀልን ይዘው ይታያሉ፡፡ ሌላው መሪው ሙሴ የናሱን እባብ ይዞ በዓላማ ላይ ሲሰቅለው እንዳዳናቸው፤ እግዚአብሔር አብ ልጁን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ዓለሙን ለማዳኑ መስካሪዎች ስለሆንን “በትረ ሙሴ” የሚል ስያሜ ያለውን በትር የኤጲስ ቆጶሳቱ አለቃ በእጃቸው ይዘው ይታያሉ፡፡ ሙሴ የእስራኤላውያን መሪ ነው፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ ደግሞ የሃይማኖት መሪ ናቸውና ይህን በትር ይይዛሉ፡፡
ሙሴ በትር ይይዝና ተአምራት ያደርግ ነበረ፤ “ይህችንም ተአምራት የምታደርግባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ” ዘጸ 4፣17 ያለው እግዚአብሔር ያለ በትር ተአምር ማድረግ ተስኖት ሳይሆን አንተ መሪያቸውና ቤዛ ሆነህ የምታወጣቸው ነህ ሲለው ነው በትሩን አስይዞ የላከው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ እስጢፋኖስ “ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው” ሐዋ 7፣35 ብሎ የመሰከረለት፡፡ ለክርስቲያኖች ጠባቂና የበላይ አባት የሆኑት ቅዱስ ፓትርያሪኩም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ተብለው አደራ የተቀበሉ ስለሆነ፣ የመሪነታቸው ምልክት ይህን በትር ይይዛሉ፡፡ ዘንግ በትር መያዝ የአባትነትና የጠባቂነት ምልክት ነው፡፡
የዕብራዊያን ሁሉ አባት ያዕቆብ ዘንግ ይይዝ እንደነበረና፣ ልጁ ዮሴፍ “በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ” ዕብ 11፣21 ተብሎ የተጻፈው አባቱ ዘንግ ስለሚይዝ ነው፡፡ በተጨማሪም እረኛው ዳዊት “በትር ይዞ” 1ኛ ሳሙ 17፣43 በጎቹን እንደሚጠብቅና በኋላም የሕዝብ ጠባቂ ንጉሥ ሲሆን በትረ መንግሥት እንደሚይዝ ዘፍ 49፣10 ፤ የአዲስ ኪዳን እረኞችም ጠባቂነታቸውን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብለዋል “...ግልገሎቼን አሰማራ ...ጠቦቶቼን ጠብቅ ...በጎቼን አሰማራ።” ባላቸው መሠረት ከሌሎች ብጹዓን ጳጳሳት ለየት ብለው ለጠባቂነታቸው ምልክት በግራ እጃቸው “በትረ ሙሴ” እና በቀኝ እጃቸው የወርቅ መስቀል ጨብጠው ይታያሉ፡፡                                                            ምንጭ፦ ከመምህር አስቻለው ከበደ የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ።
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 አምላክን የወለድሽ ድንግል ሆይ! በላዬ ያደረውን የኃጢአቴን ሽታ አርቂው በጸሎትሽም መዓዛ እንደ ኪሩቤል ዕጣን ሽታ እንደ ሱራፌልም ጽንሐሕ ጸሎቴ ደግሞ ያማረ የተወደደ እግዚአብሔርም የተቀበለው ይሁን አሜን》
                 አርጋኖን ዘሐሙስ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
✥ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
✥ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

              ጩጌ ማርያም ገዳም
ጩጌ ማርያም  ከጎንደር ከተማ በስተሰሜን በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘን
በወገራ አካባቢ የኮሶየ አምባ ራስ ቀበሌን አልፈን ወደ ገዳማቱ ለማምራት የዘጎል አምባን፡የጅብ ዋሻን ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን አልፈን ወደ ምስራቅ ስንታጠፍ በተፈጥሮ ክብ ቅርፅ ያለውን ቤተ ክርስቲያን መስሎ
የሚታየውን ተራራ እናገኛለን።በዚህ ተራራ ላይ አባ ምዕመን ድንግል የገዳም ህይወታቸውን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
በተራራው ማየ ዮርዳኖስ ፀበልና ዋሻ ቅዱስ ሩፋኤል ክርስቲያን እናገኛለን ቤተ ክርስቲያኑ ቅድስትና መቅደስ ያለው ሲሆን በቅድስቱ ማየ ዮርዳኖስን ያለ ሲሆን ይህንበመጠጣታቸው ስጋቸው ያልፈረሰ  የፍየል አፅሞች
ይገኛሉ።በዚህም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ጳጉሜ 3 ይቀደሳል።
የጩጊ ማርያም ገዳም በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን የመሰረቱትም አባ ምእመነ ድንግል የተባሉ ጻድቅ ናቸው፡፡ገዳሙም ጻድቁ የጸለዩበት እና ከጌታችን ከመድኀኒታች ከእየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ቅዱስ ቦታ ሲሆን የጻድቁ በኣት መጸለያ ዋሻም በስማቸው
“ምእመነ ድንግል” እንደተባለ አለ፡፡
ጻድቁም በሕይወት እንደነ ሄኖክ፣ ኤልያስ፣ ቅዱስ ያሬድ እና አባ ዮሃኒ በህቡእ አሉ ተብሎ ይታሰባል ፡፡የጻድቁ መጸለያ ቦታ በተፈጥሮው የተሸነቆረ መስኮት አለው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ መኻን የሆኑ ሁሉ በመስኮቱ ወጥተው ሲመለሱ ማየ ዮርዳኖሱን ጠጥተው ሲሳሉ
ልጅ ለማግኘት ይበቃሉ፡፡ ይህን ቃል ኪዳን የሚያውቁ ጳጉሜን በሙሉ በማየ ዮርዳኖሱ በመጠመቅ ትልቅ ሐብተ ፈውስ ያገኛሉ፡፡
የዮርዳኖሱን ጸበል የጠጣ ሲሞት ሥጋው
አይፈርስም፣ አይበሰብስም፡፡ እንኳን በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው እንስሳቱ እንኳን አካላቸው ሳይፈርስ ይቆያል፡፡ ለማስረጃ ያህል እንኳን 16 የሚሆኑ ፍየሎች አካላቸው ሳይፈርስ 400 ዘመን ያስቆጠሩ አሉ፡፡
ገዳሙ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ በሁለት የተከፈለ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ በወንዶች ገዳም በኩል ሲገኝ ወደ ሴቶቹ ገዳም ስናመራ ደግሞ አንድ ትልቅ የችብሀ ዛፍ ወድቆ እንደተነሳ ይኸውም ከሰው ልጅ ሞቶ
መነሳት ጋር የተያያዘ እግዚአብሄር
ተአምራትን አሳይቶበታል።ዛፉ ከ15ዓመት በሗላም እንደገና እንደወደቀና በስሩ የፈለቀው ፀበልም ህመምተኞችን እየፈወሰ እንደሚገኝ አባቶች ያስረዳሉ።
      ምንጭ፦ ታዴ የማመይ ልጅ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
✥ ከጩጌ ማርያም ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን።ደጇን ተሳልመን በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን።
✥ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

 †††   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  †††
       ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን ከአሁን ሰአት ጀምሮ ተጀምሯል።ጥያቄዎቹም እነዚህ ናቸው
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
፩ በየወሩ በ6 ከሚከበሩ በአላት 3ቱ ጥቀሱ?
፪ ፍሬ ቅዳሴ ከሚባሉት 5ቱን ጥቀሱ?
፫  ንጉስ ዳዊት ሚስቱን ለመውሰድ ሲል በጦር ሜዳ ላይ ያስገደለው ሰው ማን ይባላል?
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ መልሶቻችሁን እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ በ
 ⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
☞ መልሱን ከ4:00 በኋላ በቻናላችን የምንለቅ መሆናችንን እንገልፃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

           እኔ ለበረከት
እኔ ለበረከት ዘምርልሻለው
የክብር ባለቤት አምላክሽ ልጅሽ ነው
የሰጠሸን ክብር ሳልጨምር ሳልቀንስ
ሞገስ ሆኖልኛል ስምሽን ማወደስ
               አዝ
አሜን ይሁንልኝ ገብርኤል ተናገር
ስላልሽ በእምነት ሆኗል ድንቅ ነገር
ለሰማይ ንጉስ በምድር ዙፋኑ
ክብርሽን ይቀኛል የትውልድ ልሳኑ
               አዝ
ለእግዚአብሔር ቃል ታዞ መኖር የሚቻለው
ክፉ ስራን መናቅ ድንግል ሆይ እንዴት ነው
የሕይወትሽ መፅሃፍ ተዘርግቷል ፊቴ
እኔንም ያስችለኝ እግዚአብሔር አባቴ
              አዝ
በልብሽ ጠብቀሽ የያዝሽውን እውነት
ከሰርጉ አዳርሽ ውስጥ ገለጥሽው በእምነት
ታዳሚው አወቀው ያወቅሽውን ጌታ
ምስክርነትሽ አዘነበ ደስታ
              አዝ
በእምነት መታዘዝሽ ትሕትና ፅናትሽ
በልቤ ሰሌዳ ይቀረፅ በልጅሽ
የሕይወት መዐዛሽ ይሁን መዐዛዬ
የሚነበብ መልእክት ያድርገኝ ጌታዬ
                   አዝ
ለእግዚአብሔር ቃል ታዞ መኖር የሚቻለው
ክፉ ስራን መናቅ ድንግል ሆይ እንዴት ነው
የሕይወትሽ መፅሃፍ ተዘርግቷል ፊቴ
እኔንም ያስችለኝ እግዚአብሔር አባቴ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
✥ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
✥ መልካም  እለተ ሰንበት ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

                 አስራት በኩራት

መስጠት ማለት በኩራት፣ አስራት፣ መባና ልዩ ስጦታን ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲሆን ማቅረብ ነው። ይኸውም ያለንን ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር እንደተቀበልን ማሳያና ለእግዚአብሔር ያለንን አክብሮት ፍቅርና አምልኮ የመግለጫ መንገድ ነው።

የስጦታ ዓይነቶችና ትርጉማቸው

ሀ. በኩራት - በኩር (የመጀመሪያ) ከሚለው ቃል ነው። በኩራት የእግዚአብሔር ነው - ዘፀ 23፡19፣ ዘሌ 23፡10-11

- በኩራት መስጠት ማለት እግዚአብሔርን በነገሮቻችን ሁሉ ማስቀደም ማለት ነው - ዘኁ 3፡13፣ ዘዳ 15፡19

- የበኩራት ስጦታ ትዕዛዝ ነው - ዘፀ 13፡2፣ ዘዳ 26፡2

- የመጀመሪያውን ስንሰጥ ያለን ነገር ይባረክልናል - 1ሳሙ 2፡20-21

ለ. አስራት - ዘፍ 14፡20፣ ዕብ 7፡4-5

- አስራት በብሉይ ኪዳን ከአስር አንድ እጅ ማለት ነው - ዘፍ 28፡22። አስራት በአዲስ ኪዳን ግን ከአስር አንድ እጅ ባለፈ በዘራኸው ልክ ነው - 2ቆሮ 9፡6-7

- አስራት የእግዚአብሔር ንብረት ነው - ሚል 3፡8-10

- አስራት የሚሰጡ (የሚያስገቡ) ሰዎች በታማኝነት የእግዚአብሔርን ንብረት መልሰው ለእርሱ የሚሰጡ ናቸው - ዘዳ 14፡22-23

- አስራትን በማስገባት (በመስጠት) ውሰጥ በረከት አለ - ሚል 3፡8-10

ሐ. መባ - እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ገቢ አስራት አውጥተን ከሚቀረው ድረሻችን ላይ ለወንጌል ስራ፣ ለድሆች መርጃ፣ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የምሰጠው ስጦታ ነው። ይህ አይነቱ ስጦታ በልብ ደስታ በራሳችን ውሳኔ በአቅማጭን መጠንና ከዚያም በላይ የምንሰጠው ይሆናል - ዘፀ 25፡1-5፣ 2ቆሮ 8፡1-2፣ ዘፀ 34፡20

መ. የፍቅር ስጦታ - ለእግዚአብሔር ቤት ስራና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ፍቅርን ለመግለጽ የሚሰጥ ሲሆን በተለያዩ ጊዚያቶች ሊደረግ ይችላል - ሐዋ 11፡27-30፣ ፊሊ 4፡16-18

የምንሰጥበት ምክንያት እና አላማ

ሀ. እግዚአብሔር እንድንሰጥ አዟል - ዘፀ 25፡1-5፣ ዘሌ 25፡31፣ ዘኁ 18፡21

ለ. ስጦታችን የእግዚአብሔርን መንግስት የማስፋፋት ስራና የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ የሚውል ነው - 1ቆሮ 9፡4-14፣ 2ቆሮ 8፡4፣ ፊሊ 4፡15-18

ሐ. በመስጠት እግዚአብሔርን እናከብራለን፣ እናመልካለን - ምሳ 3፡9-10

መ. በመስጠት የእግዚአብሔርን በረከት እንለማመዳለን - ሚል 3፡10-12፣ ሉቃ 6፡10

ሠ. በመስጠት ለእግዚአብሔር ታማኝ እንሆናል (አንሰርቀውም) - ሚል 3፡8-10

እንዴት መስጠት እንዳለብን

ሀ. የምንሰጠው አስቀድመን ራሳችንን ለእግዚአብሔር በመስጠት ነው - ሮሜ 12፡1፣ 2ቆሮ 8፡1-5

ለ. የምንሰጠው በሃዘን (በግድ) ሳይሆን በደስታ ነው - 2ቆሮ 9፡7

ሐ. የምንሰጠው እንደገቢያችን ብቻ ሳይሆን ከጉድለታችንም ጭምር መሆን አለበት - 2ቆሮ 8፡1-5

መ. የምንሰጠው ለሰዎች ለመታየት መሆን የለበትም - ማቴ 6፡1

የምንሰጠው በስጦታችን ለመመካት መሆን የለበትም - ሉቃ 18፡9-14

ስለ ስጦታ ያስተማረንና አስቀድመሞ የሳየን ራሱ እግዚአብሔር ነው። ከስጦታዎች በላይ የሆነውን ስጦታ ለሰው ልጆች ሰጥቷል (ዮሐ 3፡16-30፣ ሮሜ 8፡32)። ይህ በምድራዊ ቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ ላመኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ አድርጓል። ቤተ ክርስቲያን ይህንን የምስራች ለአለም ሁሉ ለማድረስ እንድንችልና የእግዚአብሔርን ቤት ስራ እንድትሰራ አማኞች የታዘዙትን የፈቀዱትን ስጦታ ለወንጌል መስጠት አለባቸው። ይህም በሕይወታቸው ይበዛላቸዋል።
 @Nehmeya  @Nehmeya 
 ✥ እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
 ✥ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

አብይ ጾም
አብይ ጾም ከሰባቱ አፅዋማት ውስጥ አንዱ ነው የሚጾመውም ለ፶፭ ቀናት ሲሆን ከሰባቱ አጽዋማት ረጅሙ ጾም ነው።አብይ ጾም የሚጀምርበት ቀን ነነዌ ጾም በገባ በ፪ተኛው ሳምንት ነው።ብዙ ሰዎች ነነዌ ጾምን ነይነይ የሚሏት በዚህ ምክንያት ነው።አብይ ጾም የሚጀምርበት ቀን ምንግዜም ሰኞ ቀንን የማይለቅ ሲሆን በዚህ አመትም(፪፻፲፪)
የካቲት፲፮ ሰኞ እለት አብይ ጾም ይጀመራል።
             ለምን አብይ ጾም ተባለ?
ከስሙ እንደምንረዳው አብይ ማለት ዋና ማለት ነው።አብይ ጾም የተባለው ጾሙን የጾመው ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ ነው።(ማቴ ፬፥፪)
              ለምን ፶፭ቀን እንፆማለን?
ማቴ ፬፥፪ ላይ እንደምናነበው እየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ቀን ፵ለሊት ሲሆን ቤተክርስትያናችን ግን የምትጾመው ለ፶፭ ቀን ነው ይህም የሆነበት ምክንያት የመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ(ጾመ ሕርቃል)የሚባል ሲሆን ይህ ሳምንት የምንጾመውም ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የአዳም እና ሄዋንን በደል ለመጥፋት ከሰማያት ሰማያት መውረዱን በማሰብ ዘወረደ ብለን እንጾመዋለን።ከሆሳዕና ቅዳሜ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያሉትን ቀናት የጌታችን ህማም እያሰብን ስለምንጾም ህማማት ብለን እጾማለን።የዘወረደ ፯ቀን + የህማማት፰ቀን=፲፭
ከ፶፭ቀን - ፲፭ቀን=፵ቀን ይሆናል።ዘወረደን እና ህማማትን ስለምንጾም ነው ፶፭ ቀን የሆነው።ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የጾመው ከቅድስት እስከ ሆሳዕና ቅዳሜ ያሉትን ፵ቀናት ነው።
                 የአብይ ጾም ሳምንታት
አብይ ጾም ፰ሳምንታት ያሉት ሲሆን እነሱም
     ፩ ዘወረደ                  ፪ ቅድስት
     ፫ ምኩራብ               ፬ መፃጉ
     ፭ ደብረ ዘይት           ፮ገብርሔር
     ፯ ኒቆዲሞስ             ፰ ሆሳዕና   ናቸው።
@Nehmeya     @Nehmeya
✥ ጾሙን ጾመን ረድኤት በረክት የምናገኝበት ያድርግልን።
✥ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya  @Nehmeya
✞እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግል።
✞ ደግ ደጉን የምናደርግበት በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

#EOTC

ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

Credit : EOTC TV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

     በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
               አሐዱ አምላክ አሜን
የአብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ ማህበራችን የየካ/ደ/ም/ቅ ኪደነ ምህረት እና መድሀኒአለም የአካባቢ ወጣቶች ማህበር( ማህበረ ነህምያ) ወደ እነዚህ አድባራት እና ገዳማት ጉዞ አዘጋጅቷል
  ⇨ መጋቢት 4እና5 ምድረ ከብድ
⇨ መጋቢት 12 አጃና ሚካኤል(ደርሶ መልስ)
 ⇨ መጋቢት 19 ሺፈጅ ገብርኤል(ደርሶ መልስ)
⇨ መጋቢት 26 እና 27 ሳማ ሰንበት እና አፄ ዋሻ ማርያም
 ⇨ ሚያዝያ 3 ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት(ደርሶ መልስ)
 ⇨ ሚያዝያ 10 በልበሊት እየሱስ(ደርሶ መልስ)

       በእነዚህ ጉዞዎች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ምዕመናን ኮተቤ ኪዳነ ምህረት ዋናው በር ላይ በሚገኘው አቤኔዜር የሴቶች የውበት ሳሎን ይመዝገቡ።
  ለበለጠ መረጃ ☎ 09–21–22–22–99
                           ☎ 09–11–79–51–47
                           ☎ 09–11–10–95–08

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

 ✥  እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ቅድስት ኪዳነ ምህረት አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን።
✥ መልካም ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
  ፩ ፆመ ነነዌ የምትፆመው ለ3 ቀን ነው።
  ፪ ፆመ ነነዌን የነነዌ ህዝቦች የፆሙበት ምክንያት ፈጠሪ ነነዌን እንደሚያጠፋት በነብዩ ዩናስ በኩል ሲነግራቸው ከጥፋት ለመዳን ብለው የፆሟት ፆም ነች።
  ፫ የዘንድሮ የነነዌ ፆም የሚጀምረው ነገ(የካቲት 15) 2013አ/ም ነው።(እንኳን ለነነዌ ፆም በሰላም አደረሰን)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩ 
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
                መልካም ምሽት

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

@Nehmeya @Nehmeya
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ መታሰብያ ክብረ በአል አደረሰን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

            ማዳንህን
ማዳንህን ጽድቅህን እረፍትህን
ሰላምና ፀጋ በረከትህን
አይቻለሁ ለሕዝብህ ያደረከውን
አሰናብተኝ በሰላም ባርያህ
                 አዝ
እጠባበቅ ነበር የእስራኤልን መፅናናት
ብርሃን እስኪመጣ እስኪገለፅ እውነት
ይህን ሁሉ አየሁ ቆሜ ከመቅደስህ
ዘመኔ ታደሰ ጌታን ስታቀፍ
                አዝ
ኑሮዬን ስገፋ ከአልጋ  ተጣብቄ
እስከምትመጣ ትንቢቱን ጠብቄ
በእርጅና ዗ዘመኔ አረከኝ ጎልማሳ
በክንድቼ ይዤህ ዗ዘለልኩ እንደ እንቦሳ
                አዝ
አሁን እንደ ቃልህ ባርያህን አሰናብት
ከቅዱሳን ጋር እንድኖር በገነት
ከቶ አልበልጥምና እኔ ከአባቶቼ
በፅድቅ ላንቀላፋ ከእቅፍህ ገብቼ
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን ይሁንልን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

  ጩጌ ማርያም ገዳም የሚገኘውን ማየ ዩርዳኖስ በመጠጣቸው ሳይበሰብስ ከ400 አመት በላይ ያስቆጠረው የፍየል አፅም

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ ለዛሬ የነበረን የጥያቄ መልስ መርሀ ግብር የተጠናቀቀ ሲሆን ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። 🙏🙏🙏🙏 🙏🙏 መልሶቹ እነዚህ ናቸው።
  ፩ በየወሩ በ6 የሚከበሩ በአላት ቅድስት አርሴማ፣ቁስቋም ማርያም፣እየሱስ፣
መቅደላዊት ማርያም ናቸው።
  ፪ የፍሬ ቅዳሴያት ብዛት 14 ሲሆን
እነርሱም ፦
፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫. ቅዳሴ እግዚእ
፬. ቅዳሴ ማርያም
፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፰. ቅዳሴ ዘባስልዮስ
፱. ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ
፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
  ፫ ኦሪዮን
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የሚኖረን ሲሆን በቻናላችን ላይ ያለዎትን ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት በ ⇩⇩⇩⇩⇩⇩ 
@Mahebranehmyabot ያድርሱን።
                መልካም ምሽት

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

☞ የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችን ከምሽቱ 2:00 ላይ የሚጀምር ስለሆነ ሁላችሁም እንድትሳተፉ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ማህበረ ነህምያ(ዘ ኮተቤ)

《 ማርያም ሆይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌልም ያመሰግኑሻል። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማህፀንሽ አድሯልና።》
                   ውዳሴ ማርያም
 @Nehmeya  @Nehmeya 
❖ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፍፁም ሰላም ያድርግልን።
❖ መልካም  ቀን  ይሁንልን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel