4008
وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
https://youtu.be/Z-hDxdwyPoA?si=6QkliD2hzs5GaxiK
Читать полностью…
◆▮ውይይት▮◆
"ሰባዐ ሰገል እነማን ናቸው?"
"ላኢላሃ ኢለላህ የሚለው ቃል ስምንት ጥርሶች ያሉት ቁልፍ ነው"
◍ ኡስታዝ ወሒድ
◍ ወንድም አሕመድ
🆅🆂
◍ ወገናችን ኦፖል
ሌሎችም
የጀነት ወጣቶች
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
52፥24 ለእነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሳለፍ ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ
"ወሊድ" وَلِيد ማለት "ወጣት ልጅ" ማለት ሲሆን "ዊልዳን" وِلْدَان ማለት ደግሞ "ወጣቶች ልጆች" ማለት ነው፥ በተመሳሳይ "ጉላም" غُلَام ማለት "ወጣት ልጅ" ማለት ሲሆን "ጊልማን" غِلْمَان ማለት ደግሞ "ወጣቶች ልጆች" ማለት ነው። አምላካች አሏህ ሙተቂን ለሆኑት ባሮቹ በጀነት የሚያስተናግዷቸውን አስተናጋጆች "ዊልዳን" وِلْدَان ወይም "ጊልማን" غِلْمَان በማለት ይጠራቸዋል፦
56፥17 በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ يَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَانٌ مُّخَلَّدُونَ
52፥24 ለእነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሳለፍ ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ይዘዋወራሉ" ለሚለው የገባው ቃል "የጡፉ" يَطُوفُ ሲሆን "ያስተናግዳሉ" ማለት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ "የጡፉ" يَطُوفُ የሚለውን ወልመካ እና ወሰክ የሆኑ ሚሽነሪዎች "ይዳራሉ" በማለት ይቀጥፋሉ፥ ቅሉ ግን "የጡፉ" يَطُوفُ የሚለውን "ይዳራሉ" ተብሎ የተረጎመ አንድ የቁርኣን ትርጉም የለም። ሰዎች የአሏህን ቤት ሲጎበኙ በመዘዋወር ዙሪያውን ይዞራሉ፦
22፥29 በጥንታዊውም ቤት "ይዙሩ"፡፡ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ይዙሩ" ለሚል የገባው የግሥ መደብ "የጦወፉ" يَطَّوَّفُوا ሲሆን "ይዳሩ" ማለት ነው? "ጦዋፍ" طَواف የሚለው ቃል "ጧፈ" طَافَ ማለትም "ዞረ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ዙረት" ማለት ነው፥ "ጧኢፊን" طَّائِفِين ደግሞ የሚዞሩት አማኞች ናቸው። ስለዚህ አንድ ቃል ብዙ ትርጉም ካለው ዐውደ ንባቡ ያላማከለ ትርጉም ለማሰጠት መሞከር እጅግ ሲበዛ ቂልነት ነው። የጀነት ወጣቶች የሚያስተናግዱት ወይን ጠጅ የሚያሰክር አይደለም፦
37፥45 ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ يُطَافُ عَلَيْهِم بِكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ
56፥18 ከወይን ጠጅ ምንጭ በብርጭቆዎች፣ በኩስኩስቶች እና በጽዋም በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ፡፡ بِأَكْوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ
56፥19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ
"ሃ" هَا ማለት "እርሷ" ማለት ሲሆን "ሃ" هَا የሚለው ተውላጠ ስም "የወይን ጠጅ ምንጭ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ቃል ነው፥ ይህ ሆኖ ሳለ "አይሰክሩም" ለሚለው የገባው ቃል "ዩንዚፉን" يُنزِفُون ሲሆን ሚሽነሪዎች "አይደሙም" ማለት ነው" በማለት የጀነት ወጣቶች ከአማኞች ጋር የግብረ ሰዶም ተራክቦ ሲያደርጉ እንደማይደሙ ለማስመሰል ይዳዳሉ።
፨ሲጀመር "ከእርሷ" ማለትም "ከወይን ጠጇ አይደሙም" በሰዋሰዋዊ አወቃቀር ትርጉም አይሰጥም።
፨ ሲቀጥል ግብረ ሰዶም በኢሥላም እጅግ አጸያፊ ኃጢአት ነው።
፨ሢሰልስ "ነዘፈ" نَزَفَ ማለት "ሰከረ" "ደማ" በሚል ይመጣል፥ ነገር ግን እዚህ ዐውድ ላይ "ላ ዩንዚፉን" لَا يُنزِفُون የሚለው "አይሰክሩም" እንጂ "አይደሙም" ለማለት እንደማያስኬድ የምናውቀው "የራስ ምታት አያገኛቸውም" የሚለው ኃይለ ቃል መቀመጡም ነው፦
37፥47 በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ
56፥19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ
"ፊ ሃ" فِيهَا ማለት "በእርሷ ውስጥ" ማለት ሲሆን "እርሷ" የተባለችው "ጀናህ" ናት፥ "ዐን ሃ" عَنْهَا ማለት ደግሞ "ከእርሷ" ማለት ሲሆን "እርሷ" የተባለችው "የወይን ጠጅ ምንጭ" ናት። ዱንያህ ላይ ያለው የወይን ጠጅ የራስ ምታት እና ስካር አለው፥ በጀናህ ውስጥ ያለችው ግን የራስ ምታት እና ስካር የላትም።
፨ ሲያረብብ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" اِسْم المُشْتَرِك ማለት "ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ"Homonym" ነው፥ ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት አረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፥ መታየት ያለበት ቃሉ ብቻ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብም ጭምር ነው። ለምሳሌ፦ "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ላከ" ማለት ነው፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አሏህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَـٰذَا الَّذِي بَعَثَ اللَّهُ رَسُولًا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ላከ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለት ነው፥ ነገር ግን "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ቀሰቀሰ" ወይም "አስነሳ" ማለት ነው፦
36፥52 «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሰቀሰ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አቃመ" أقَامَ ማለት ነው፥ ስለዚህ "አሏህ መልእክተኛ አድርጎ የቀሰቀሰው ይህ ነው" ወይም "ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ላከን" ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባ ነው። ሌላ ምሳሌ ከባይብል "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ነው፦
ሚክያስ 7፥18 እንደ አንተ ያለ "አምላክ" ማን ነው? מִי־אֵ֣ל כָּמֹ֗וךָ
እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤል" אֵל ሲሆን "ኤሎሃ" אֱלוֹהַּ ለሚል ምጻረ ቃል ነው፥ ነገር ግን "ኤል" אֵל ማለት "ኃይል" ማለትም ነው፦
ሚክያስ 2፥1 በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! "ኃይል" በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል። הֹ֧וי חֹֽשְׁבֵי־אָ֛וֶן וּפֹ֥עֲלֵי רָ֖ע עַל־מִשְׁכְּבֹותָ֑ם בְּאֹ֤ור הַבֹּ֙קֶר֙ יַעֲשׂ֔וּהָ כִּ֥י יֶשׁ־לְאֵ֖ל יָדָֽם׃
https://youtu.be/jXKL0vEAfL8?si=aDnTBUI6vviCi88z
Читать полностью…
◆▮ውይይት▮◆
"ባይብል እንደት ነብያትን አዋረደ"
"ኢየሱስ እራቁቱን ተሰቀለ ኑህ ሰክሮ እራቁቱን ሆነ " ሉጥ ከልጆቹ ወለደ ሌላው ነብይ በኢትዮጵያ እራቁቱን ይሄድ ነበር የሚሉ እና "ሌሎችም የተዳሰሱበት"።
ክፍል2
◍ ወንድም ዒምራን
◍ወንድም ኢብራሂም
◍ሌሎችም
🅥🅢
◍ ከብዙ ወገኖች ጋር
ርእስ ነገረ ድህነት በኢስላም እና በክርስትና እስሚዝ 🎙 አቡ ሳለህ🎙 ...
https://youtube.com/watch?v=2RkSD5E-LZ8&si=jJfulxXjVJH7Ykr8
ዛሬ ማታ ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።
/channel/path_of_the_prophets
ቴሌ ግራም
https://vt.tiktok.com/ZSj5SNEQv/
ቲክቶክ
ማንም እንዳይቀር
ክርስቲያኖች ግን እንደት ተቀበላችሁት ይህን መጽሐፍ?!
https://youtube.com/watch?v=9fChjuICVaQ&si=1CIApMm0wuGJd3KC
ኡስታዝ ወሒድ ገብቷል
/channel/path_of_the_prophets?livestream=8d2bc9ab657bbc866c
◆▮ውይይት▮◆
"እስልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ"
◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ወንድም አሕመድ
◍ ወንድም ኢብራሂም
◍ ሌሎችም
🅥🅢
◍ ከብዙ ወገኖች ጋር
የግብፅ ሥላሴ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
በሥነ ሥላሴ ጥናት"Triadology" ከክርስትናው ሥላሴ በፊት ሦስት የተለያየ ፊት ያላቸው "ሥሉስ አምላክ"Triple Deity" በተለያየ የዓለም ክፍሎች ይታምባቸው ነበር፥ ከእነዚያ አንዱ የግብፅ ሥላሴ ነበር። ግብፅ "እስክንድሪያ" ተብላ የተቆረቆረችው 331 ቅድመ ልደት በግሪክ ንጉሥ በታላቁ እስክንድር ሲሆን የግሪክ ቋንቋ በእስክንድሪያ ተጽዕኖ ስሳደረ አብዛኛውን የግብፅ ባህል በግሪክ ቋንቋ የተዘጋጁ ናቸው።
ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በኮይኔ ግሪክ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪያስ" τρῐᾰ́ς ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ በግዕዝ "ሥሉስ" ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ሥላሴ" ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው።
"ፕሮሶፓን" πρόσωπον ማለት "ፊት" "ገጽ" "መልክ" ማለት ሲሆን በግብፅ ከጥንት ጀምሮ ሦስት ፊቶች ያላቸው ነገር ግን አምላክነትን የሚጋሩ "ኦሲሪስ" Όσιρις አባት አምላክ፣ "አይሲስ" Ἶσῐς እናት አምላክ እና "ሆረስ" Ὧρος ልጅ አምላክ ይመለኩ ነበር።
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" Ο Θεός ο πατρὸς ማለት "አባት አምላክ"God the Father" ማለት ሲሆን እርሱም ኦሲሪስ ነው፣
፨ "ቴስ ቴያ ቴስ ሜትሮስ" τῆς θεά τῆς μητρὸς ማለት "እናት አምላክ"Goddess the Mother" ማለት ሲሆን አይሲስ ናት፣
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο υἱός ማለትም "ልጅ አምላክ"God the Son" ማለት ሲሆን ሆረስ ነው።
Strudwick, Helen (2006). The Encyclopedia of Ancient Egypt. New York: Page 118.
ኤጵፋኒዮስ ዘሳልሚስ"Epiphanius of Salamis" ከ 320 እስከ 403 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ የቆጵሮስ ኤጲስ ቆጶስ ሲሆን "The Panarion of Epiphanius of Salamis" የተባለ ዕውቅ የታሪክ መጽሐፉ ገጽ 637 ላይ "ኮሊሪዲያን"Collyridian" ብሎ የሚጠራቸው የክርስትና ጎጥ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ "ማርያማውያን"Mariamites" ናቸው፦
"ኮሊሪዲያን ድንግል ማርያምን እንደ አምላክ ያመልኩ ነበር፥ እነዚህ ጎጥ ድንግልን በማላቅ በግጻዌ መለኮት ውስጥ ስለሚያካትቱ ማርያማውያን ይባሉ ነበር"።
Readings in Biography: A Selection of the Lives of Eminent Men of All Nations <by William Cooke Taylor> Page 192.
የማርያማውያን ሥላሴ ከግብፅ ሥላሴ የተኮረጀ ሲሆን አባት፣ እናት ማርያም እና ልጅ ኢየሱስ የተባሉ ሦስት አካላት ናቸው። ፕሮፌሰር ጆን ሆልመስ"John Holmes" ማርያማውያን ማርያምን ከሥላሴ ሦስት አካላት አንዷ እንደሆነች አድርገው ያምኑ እንደነበር አበክረው ተናግረዋል፦
"ማርያማውያን በዚህ ስያሜ የተጠሩት ማርያም ስለሚያምልኩ እና ከአባት እና ከልጅ ጋር ከመለኮታዊ የሥላሴ አካላት አንዷ አርገው ስለሚያምኑ ነው"።
The Eclectic Magazine: Foreign Literature science and Art. By John Holmes Agnew, Walter Hilliard Bidwell, volume 21, page 40.
ሚሽነሪው የሥነ መለኮት ምሁር ጊልበርት ሪድ"Gilbert Reid" የማርያማውያን ሥሉስ አምላክ"Tritheism" አባትን፣ እናትን እና ልጅን እንደሚያቅፍ ተናግረዋል፦
"ክርስትናን በተመለከተ በዐረብ አገር የተወከለው ሥሉስ አምላክ እንጂ ግልጽ ያልተበከለ አምላካዊነት አልነበረም፥ ሰማያዊ አባት፣ የአምላክ እናት ማርያም እና ልጃቸው ኢየሱስ ሥሉስ አምላክ ሆነው ይመለኩ ነበር"።
Gilbert Reid – The Biblical World: Volume 48, Number 1, Page 12.
"ትራይቴይዝም"Tritheism" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "ትሪ" τρῐ እና "ቴዎስ" θεός ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ቴዎስ" θεός ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በላቲን "ትሪኒ" trīni ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪኒታስ" trīnitās ማለት ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ "ትሪኒቲይ"Trinity" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ሦስትነት"threeness" ማለት ነው።
የማርያማውያን ሥላሴ ልክ እንደ ዮሐንስ ተዐቃቢ"John Philoponus" ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ፈቃድ፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ ሕይወት አላቸው ስለሚሉ በዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ዘንድ "ሦሉስ አምላካውያን ወይም የሦስት ባሕርያት አማንያን" የሚል ነቀፌታ ይደርስባቸዋል፥ ዮሐንስ ተዐቃቢ ከ 490 እስከ 570 ድኅረ ልደት በእስክንድርያ ይኖር የነበረ ሲሆን "ሥላሴ በከዊን አይገናዘቡም" በማለቱ እና ፈቃድን ለባሕርይ ሳይሆን ለአካል ስለሚሰጥ "ሦስት ባሕርያት" ይላል በሚል የሐሰት ክስ በ 680 ድኅረ ልደት በ3ኛው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ተወግዟል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 85 ቁጥር 23
"ሐሰትን የያዙ ሌሎችም "ሥላሴ በባሕርይ እንደሆኑ ይናገራሉ"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 91 ቁጥር 11
"ሦስት አማልክት እና ሦስት ባሕርያት ከሚሉት መናፍቃን ጋር አንድ በሚሆን ድንቁርናው የሚመካ ተዐቃቢ የሚባል ዮሐንስ እንደ ተናገረ ይህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አነጋገር አይደለም"።
የዘመናችን የፕሮቴስታንት ሥላሴ ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው በሚል "ማኅበራዊ ሥላሴ"Social Trinity" እሳቤ የሚታወቁ ሲሆኑ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አካልን እንጂ ባሕርይን ታሳቢ ስለማያረጉ ከዮሐንስ ተዐቃቢ ጋር ያመሳስላቸዋል። እሩቅ ሳንሄድ ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ቀደም "የአስተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት" በሚል መጣጥፋቸው ላይ፦ "ሦስት አካል ናቸው" ስንል ደግሞ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት አላቸው" ማለታችን ነው፥ አካል የሚለውን ቃል የምንጠቀመው እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት እንዳለው ለማሳየት ብቻ ነው" በማለት እያንዳንዱ አካል የየራሱ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ እንዳለው ጦምረዋል።
ወደ ነጥባችን ስንመለስ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ማርያማውያን የክርስትና ጎጥ "ሦስት ነው" የሚሉትን ሆነ ዐበይት ክርስትና "ሦስት ነው" የሚሉትን አምላካችን አሏህ «ሦስት ነው» አትበሉ" በማለት ሁለቱንም ድንበር አላፊያን ይገስጻቸዋል፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
ኢስላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች መልሶቻችንነብያችንን ጅኒ ደፈሯቸው እያሉ ለሚዋሹት ውሸት መልስ*"የዓንሻ ጋብቻ"ሌሎች...
https://youtube.com/watch?v=YkfLDRgrCDE&si=kXRBD4OhA_F5yGao
سورة المؤمنون ٤٣-٦٧
Surah Al Muminoon 43-67
ሡራህ አል-ሙእሚኑን ከ43-67
@slmatawahi
እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤል" אֵל ሲሆን "አምላክ" በሚል ፍቺ ብቻ ይዤ "አምላክ በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል" ትርጉም ይሰጣል? ግግም ብዬ "በመኝታ ላይ ስለ ተራክቦ የሚያስብ ሲነጋ አምላክ በእጁ ነውና አምላክን ተራክቦ ያደርገዋል" ብል እችል ይሆናል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አንደኛ ትርጉም አይሰጥም፣ ሁለተኛ አምላክ በሰው እጅ አይደለም፣ ሦስተኛ ዐውዱን ያላማከለ ሰጊዎታዊ ሥነ አፈታት ነው።ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ከላይ ያለውንም የቁርኣን አንቀጽ በዚህ መልክ እና ልክ ቆፍጠን ብላችሁ ተረዱት ለሰዎችን አስረዱት እንጂ "እኛ ያልወጠወጥነው ወጥ አይጣፍጥም" ብሎ መጀባነን አዋጪ አይደለም፥ በዘርፉ የተሰማሩ የቋንቋው መስክ ምሁራን እያሉ "እኔ ዐውቃለው" ብሎ ማንቃረር ከዘፋኙ በላይ መወዝወዝ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
/channel/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
https://vm.tiktok.com/ZMh7NvtDN/
ልጆችዬ ዝሃራ ነኝ ክርስቲያን ወገኖች አካውንቴን ሰላዘጉት ከፍቻለሁ አድስ ፎሎው አድርጉ ዱዩት አድርጉ እና ፎሎው አስደርጉኝ
ቁርአን የጨለመን ህይወት በብርሃን የሚሞላ፣
የተሳሳተን የሚገስፅና የሚያመላክት...
ውበቱ ማራኪ ተደምጦ የማይጠገብ
የማያቋርጥ የልብ ብርሃን ነው።
ወንድም አቡ በክር
ማኅበራዊ ሥላሴ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
21፥22 በሁለቱ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
"ማኅበር" ማለት የእርስ በእርስ ግኑኝነት ሲሆን በሥነ እውነት ጥናት"Metaphysics" እያንዳንዱ ማንነት ከሌላው ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ ነው፥ በነገረ ሥላሴ ጥናት ውስጥ ማኅበራዊ ሥላሴ"Social Trinity" ማለት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንዱ ከሌላው ጋር ያላቸው ግንኙነት እና በዕውቀት፣ በስሜት እና በፈቃድ ያላቸው የእርሱ በእርስ መስተጋብር ነው። ለምሳሌ፦ ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር የእርስ በእርስ ትውውቅ ማኅበራዊ ግኑኝነት እና መስተጋብር ነበር፦
ዮሐንስ 10፥14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል። ἐγώ εἰμι ὁ ποιμὴν ὁ καλός, καὶ γινώσκω τὰ ἐμὰ καὶ γινώσκουσί με τὰ ἐμά,
ኢየሱስ እና ተከታዮቹ እርስ በእርሱ የሚተዋወቁበት የየራሳቸው ዕውቀት አላቸው፥ "ግኖሲስ" γνῶσῐς ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን ልክ እንደ ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር የእርስ በእርስ ትውውቅ አብ እና ወልድ እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ፦
ዮሐንስ 10፥15 እንዲሁ አብ እንደሚያውቀኝ እኔም አብን አውቀዋለው። καθὼς γινώσκει με ὁ Πατὴρ κἀγὼ γινώσκω τὸν Πατέρα,
አብ ወልድን የሚያውቅበት የራሱ መለኮታዊ ዕውቀት እንዳለው ሁሉ ወልድም አብን የሚያውቅበት የራሱ ሰዋዊ ዕውቀት አለው፥ እርስ በእርስ ትውውቅ ሁለት የተለያዩ ማንነት እንደሆኑ ማሳያ ከሆነ "አብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ልብ(ዕውቀት) ነው" የሚለው የኩነት"mode of existence" ትምህርት ውኃ በላው።
"ስሜት" ማለት "ፍቅር እና ጥላቻ" "ደስታ እና ሀዘን" ነው፥ "አጋፔ" ᾰ̓γᾰ́πη ማለት "ፍቅር" ማለት ሲሆን አብ ወልድ ሲወድ ወልድም አብን ይወዳል፦
ዮሐንስ 3፥35 አባት ልጁን ይወዳል። ὁ Πατὴρ ἀγαπᾷ τὸν Υἱόν,
ዮሐንስ 14፥31 ነገር ግን እኔ አብን እንደምወድ ዓለም ይወቅልኝ። ἀλλ’ ἵνα γνῷ ὁ κόσμος ὅτι ἀγαπῶ τὸν Πατέρα,
አብ እና ወልድ እርስ በእርስ ከተዋደዱ የየራሳቸው ስሜት እንዳላቸው አመላካች ነው፥ አብ ወልድን የሚወድበት የራሱ መለኮታዊ ፍቅር እንዳለው ሁሉ ወልድም አብን የሚወድበት የራሱ ሰዋዊ ፍቅር አለው።
"ቴሎ" θέλω ማለት "ፈቃድ"will" ማለት ሲሆን እያንዳንዱ ማንነት ከሌላው ማንነት የሚለየው የራሱ "ፈቃድ" አለው፥ አብ የራሱ ማንነት ስላለው የራሱ መለኮታዊ ፈቃድ እንዳለው ሁሉ ወልድም የራሱ ማንነት ስላለው የራሱ ሰዋዊ ፈቃድ አለው፦
ሉቃስ 22፥42 ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ ፈቃድ እንጂ። πλὴν μὴ τὸ θέλημά μου ἀλλὰ τὸ σὸν γινέσθω.
እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈቃድ" ለሚለው የገባው ቃል "ቴሌማ" θέλημά ነው፥ ኢየሱስ አብን "አንተ" ሲል ማንነትን ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ "ፈቃድ" የሚለው "አንተ" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ "የ" በሚል አጋናዛቢ ዘርፍ ስለመጣ ማንነትን ዋቢ ያደረገ ነው። "ፈቃድ ምንነትን ታሳቢ ያደረገ ነው" የሚለው ፍልስፍና አርስጣጣሊሳዊ ትንተና"Aristotelian Analysis" ነው፥ የቀጰዶቅያ አበው"The Cappadocian Fathers" የሚባሉት ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣ የባስልዮስ ታናሽ ወንድሙ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ የጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ቅርብ ጓደኛ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ፈቃድ ምንነትን ታሳቢ ያደረገ ነው" የሚለው እሳቤ የቀዱት ከአርስጣጣሊስ ነው።
"አካል" የሚለው የግዕዙ ቃል "አከለ" ማለትም "በቃ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ብቃት" ማለት ነው፥ አካል "የግብር እና የፈቃድ ባለቤት" ነው። ዐዋቂ እና ታዋቂ እንዲሁ አፍቃሪ እና ተፈቃሪ ትርጉም የሚኖረው በሁለት አካላት ነው፥ አብ እና ወልድ የተለያየ ማንነት ስላላቸው እርስ በእርሳቸው ያወራሉ። አብ እራሱን "እኔ" እያለ ወልድን "አንተ" እያለ ሲያናግር በተመሳሳይ ወልድም እራሱን "እኔ" እያለ አብን "አንተ" እያለ ያናግር ነበር፦
ዮሐንስ 17፥11 "እኔም" ወደ "አንተ" እመጣለሁ። κἀγὼ πρὸς σὲ ἔρχομαι.
ማርቆስ 1፥11 "እኔ" የምወድህ ልጄ "አንተ" ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል። Σὺ εἶ ὁ Υἱός μου ὁ ἀγαπητός, ἐν σοὶ εὐδόκησα.
የፕሮቴስታንት የሥላሴ አማንያን"Trinitarians"፦ "ሦስት የሥላሴ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው" ብለው ስለሚያምኑ የእነርሱ ሥላሴ "ማኅበራዊ ሥላሴ" ነው፥ አንዱ አምላክ በዕብራይስጥ "ኤሎሂም" אלהים ስለተባለ "ኤሎሂም ሥላሴ ነው" የሚል እምነት አላቸው። "ኤሎሃ" אלוהּ ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ኤሎሂም" אלהים ማለት "አማልክት" ማለት ነው፥ ሥላሴ የሚባሉ አማልክት በጽንፈ ዓለማት ውስጥ በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 በሁለቱ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው "የሲፉን" يَصِفُون ሲሆን "ባሕርይ ካደረጉለት"They attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን እራሱን ባልገለጸበት ሲፋህ መወሰፋቸው ሺርክ ነው። አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፦
53፥43 አሏህ "ከሚያጋሩት" ሁሉ ጠራ፡፡ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
/channel/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
https://youtu.be/fSyrEk96OXA?si=B4EXCLz-zOcTq5A5
Читать полностью…
🛑አሁን ቀጥታ ስርጭት
📚 رياض الصالحين
ክፍል - 112
(50) باب الخوف
رقم الحديث 404
🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
ሼር በማድረግ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያድርጉ
የላይቩ ሊንክ
/channel/SheikhMuhammedZainAdam?livestream
الْقُرْآن حَيَاة القلوب🍃
من يسمع القرآن بورك قلبهُ،
كيف الذي يتلو الكتاب المُنزلا.!
ርእስ ቁርአን እና ሳይንስ ኡስታዝ አቡ ሙዓውያ
https://youtube.com/watch?v=TvFIBtg0nUg&si=9xAFQA8EOatNNnbt
ቁርአን የልብ ብርሃን
የመንፈስ እርካታ
የህይወት መመርያ
የማንነታችን ፈውስ ብዙ ነገራችን ነው
Al-Qiyamah القيامة
: Islam Sobhi اسلام صبحي
በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሦስቱን አካላት እነማን እነደሆኑ ቁርኣን ቢጠቅስ ኖሮ እያንዳንዱ አንጃ "የእኛን ሥላሴ በቅጡ አልተረዳውም፥ ቁልመማዊ ሕፀፅ አፅፆአል" ተብሎ ከሁለቱ ወገን በአንዱ ክስ ይቀርብ ነበር። ኢየሱስን የላከ አንድ አምላክ አሏህ ሆኖ ሳለ ያንን አንድ አምላክ ከሦስቱ ማንነቶች አንዱ ማንነት ነው" ማለት በእርግጥ ክህደት ነው፦
5፥73 እነዚያ «አላህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ ثَالِثُ ثَلَاثَةٍ
"Certainly they are unbelievers who say: "Allah is one of three". (Farook Malik Translation)
ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 5፥73 "የላቀው አሏህ ንግግር፦ "እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ" ማለት "ከሦስቱ አንዱ ነው" ማለታቸው ነው ። قوله تعالى: { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ }. أي أحد ثلاثة.
ኢብኑ ዐባሥ ዐበይት የሥላሴ አማንያን የሚሉትን ታሳቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" እንደሆኑ ሲያስቀምጥልን ጀላለይን ደግሞ ማርያማውያንን የሚሉትን ዋቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ እናትን" እንደሆኑ አስቀምጦልናል፦
ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 5፥73 "እነዚያ «አሏህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፥ መርቁሢያህ፦ "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" አሉ"። { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ } وهي مقالة المرقوسية يقول أب وابن وروح قدس
ተፍሢር ጀላለይን 5፥73 «እነዚያ "አሏህ ሦስተኛ" ያሉ በእርግጥ ካዱ» አማልክት «ሦስት» አሉ፥ እርሱ(አሏህ) ከእነርሱ አንዱ ነው፥ ሁለቱ ኢየሱስ እና እናቱ ናቸው" ይህንን የሚሉት ከነሷሪይ ፊርቃህ ናቸው"።
{ لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ } آلهة { ثَلَٰثَةً } أي أحدها والآخران عيسى وأُمّه وهم فرقة من النصارى
"ፊርቃህ" فِرْقَة ማለት "ጎጥ" "አንጃ" ማለት ነው፥ ኮሊሪዲያን በአንድ ወቅት የነበረ አሁን ላይ የጠፋ የክርስትና ጎጥ"sect" ነው። ዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ሥላሴያቸው ከሂንዱ ሥላሴ የተቀዳ ሲሆን የኮሊሪዲያን ሥላሴያቸው ደግሞ ከግብፅ ሥላሴ የተቀዳ ነው፥ "ክርስቲያን ነን" የሚሉት ሁለቱም የየራሳቸውን ሥላሴ በጥቅሉ ቁርኣን በአንድ ድንጋይ "ሦስት ነው አትበሉ" በማለት ሁለቱንም አእዋፍ መቷቸዋል። ደግ አረገ! "ክርስትና የበቀለው ከዐረማዊነት ነው" የምንለው በምክንያት ነው። የክርስትና ታሪክ ምሁር ኤድዋርድ ጊቦን "History of christianity" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ ክርስትና ዐረማዊነት"paganism" እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"አረማዊነት በክርስትና ድል ቢነሳም ክርስትናም በዚያው መጠን በአረማዊነት ተበክሏል"።
History of christianity (Edward Gibbon) page XVI(16)
የሥላሴ አማንያን ክርስቲያኖች ሆይ! ነቢያት እና ሐዋርያት የማያውቁት እና ውስብስብ ከሆነው የክርስትና ሥላሴ ወጥታችሁ በተውሒድ እንድታምኑ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
/channel/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
➧ኢብኑ ተይሚያ ~የሱንናዉ አንበሳ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
◉ክፍል 01
✍️ስም፣ዉልደትእና ተያያዥ ነጥቦች!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
♦️ሙሉ ስማቸዉ፦አሕመድ ኢብን ዐብዲል ሐሊም ኢብን ዐብዲ ሰላም ኢብን ዐብዲላህ ኢብኒል ኸድር ኢብን ሙሐመድ ኢብን ተይሚያ ይባላል።
♦️የትዉልድ ቦታቸዉ፦ሐራን ትባላለች። ስለዚህ ''አልሐራኒ"ማለትም "ሐራናዊ"/የሐራን ሃገር ሰዉ/በመባል ይታወቃሉ።''ሐራን"በሚል መጠሪያ የሚታወቁ በርከት ያሉ አካባቢዎች አሉ። የሳቸዉ ትዉልድ ቦታ ሐራን ግን ዛሬ በሰሜን ምስራቅ ቱርክ ጫፍ ከሶሪያ ድንበር በጥቂት ርቀት ላይ ትገኛለች።
♦️የትዉልድ ዘመናቸዉ፦ ከእናታቸዉ ሸይኻ ሲቱ ኒዕም አልሐራንያ እና ከአባታቸዉ ዐብዱል ሐሊም ኢብን ተይሚያ በረቢዑል አወል 10/661ተወለዱ። ይህ ወደ ፈረንጂ አቆጣጠር ሲቀየር ጃንዋሪ 22/1263 ይሆናል።
♦️የኖሩበት ሃገር፦በ667ሂ.የስድስት አመት ልጂ ሳሉ የትዉልድ አካባቢያቸዉን ሐራንን ተታሮች ሰላጠቋት ወላጂ አባታቸዉ ቤተሰባቸዉንና ኪታቦቻቸዉን በመያዝ በፍጥነት በሌሊት ተጉዘኹ ደማስቆ ከመግባታቸዉ ለጥቂት ተርፈዋል።ከዚያ በኋላ ኑሯቸዉ በዚያዉ ሆነ።
♦️ኩንያቸዉ፦ አቡል ዐባስ ነዉ፣የዐባስ አባት።ግና ይሄ ኢስላም እዉቅና የሰጠዉ የዐረቦች ሱንና እንጂ ዐባስ የሚባል ልጂ አልነበራቸዉም።እንደዉም ከነጭራሹ እድሜ ልካቸዉ አላገቡም።
♦️ቅፀል መጠሪያቸዉ፦ በግዜ በነበረዉ ወግና ልማድ መሠረት በርካታ ታላላቅ ምሁራን"ሙሕዩዲን"ዒዘዲን" ''ጀላሉዲን" "አሣሩዲን" "ከማሉ ድን" "ፈኽሩዲን'" ፣የሚል ቅፀል ከስማቸዉ ይቀድም ነበር። ወይ ደግሞ በዚህ ቅፀል ይጠሩ ነበር። ታድያ ኢብኑ ተይሚያም"ተቅዩዲን" በሚል ቅፀል ይታወቁ ነበር።
♦️አካላዊ መገለጫዎች ሁኔታቸዉ፦ ቆዳቸዉ ነጭ ሲሆን የራሳቸዉ ፀጉር ጥቁር ሆኖ እስከ ጆሯቸዉ ድረስ ይወርዳል።ፂማቸዉ ጥቂት ሽበቶች አሉበት።ቁመታቸዉ መካከለኛ፣ትከሻቸዉ ሰፊ፣ሲናገሩ ድምፃቸዉ ከፍ ያለ፣ አንደበተ ርቱዕ ነበሩ። ሲያነቡ ፈጣን ናቸዉ። ሃይለኝነት ቢንፀባረቅባቸዉም ነፍሳቸዉን በመቆጣጠር በይቅር_ባይነት ያሸንፉታል። አይኖቻቸዉ ተናጋሪ ምላስ ይመስላሉ።ሲናገሩ ከአፍቸዉ ላይ ቃላት ይደራረባሉ።
♦️ጎሳቸዉ፦ የኑመይር ጎሳነዉ።"አንኑመይሪ"እየተባሉ የሚጠሩት በዚህ ሰበብነዉ። ይህ ጎሳ የዓሚር ኢብኑ ሶዕሶዐህ ጎሳ ንኡስ ክፍል ነዉ።
♦️ይህንን ሐቅ የኢብኑ ተይሚያህ የተማሪዎቻቸዉ ተማሪ የሆኑት ኢብኑ ናስሪዲን አድዲመሽቂ(842 ሂ)እና መሕሙድ ኢብኑ ሙሐመድ አልዐደዊ (1,032)ጠቅሰዉታል። እንድያዉም በአንዳንድ ኪታቦቻቸዉ ላይ ይሄዉ ኒስባ ተገኝቷል ። በክር አቡ ዘይድም ይህንኑ ሀሳብ አፀድቀዋል።(አልመዳኺል:16) ስለዚህ ኢብኑ ተይሚያህ አንዳንዶች እንደሚሉት ኩርድ ሳይሆኑ በቋንቋም በዘርም ዐረብ ናቸዉ ማለት ነዉ።
✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል .......................
የምስራች ከቁርአን ቀጥሎ ትልቁን ኪታብ ሶሂሁ አልቡኻሪን መቅራት ለምትፈልጉ ሁሉ
ለመመዝገብ
አኅት ዘሃራ ሙስጠፍን፦ /channel/Zhara_mustefa
እኅት ዝሃራ ኢማምን ፦ @Zehar678
ያናግሩ