temeozen | Unsorted

Telegram-канал temeozen - "𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

-

"ሕይወት በሞኖር እየባከነ ነው"የ ሕይወት ትርጉም እኛ የምንሰጠው ትርጉም ነው" #ፍልስፍና #ግጥም #ወግ #የሃገር ፍቅር #ውይይት (ወንድvsሴት) #እናትነት #ሠዉ መሆን እና ሌሎች ..... @Hirvana2526 ስለማንኛውም ጥያቄየዎች.... 0934104100

Subscribe to a channel

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

"...ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ። በዚህ አለም ላይ ጥድፊያ ታማችኋል። ሀገራችሁን ትንቃላችሁ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ ሀገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ። በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ። ግብዝናችሁ መጠን የለዉም። ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም፣ ሌላኛዉን በመታወቂያ ታስባላችሁ። ከአንዱም በአግባብ አትኖሩም ዘመናችሁ በምልልስ እና በመዋተት ያልቃል። ምን እንደምትፈልጉም አታዉቁም ፍለጋችሁም አያልቅም። "
ደ/ር #አለማየው_ዋሴ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

- Book shelf 📗📚📖:
ከዛሬ ይልቅ ያለፈው ማክሰኞ እንደ ልደት ቀኔ ነበር፡፡ የእነዚያ የማክሰኞ ዕለት ጥቂት ሰዓታት እሙንነት ወደ ሆነ አዲስ የትህፍስት፣ የሕማም፣ የሕይወት አተያይ የንቃት ጽንፍ የሚመራ በር ነበር፡፡ ከዚያች የማክሰኞ አመሻሽ ጀምሮ ልጽፍልሽ ደጋግሜ መሞከሬ አልቀረም፡፡ ሆኖም ልጽፍልሽ በምቀመጥበት በእያንዳንዷ ቅጽበት ከጥልቅ ውቅያኖስ የሚመነጭ፣ ወይ ካልተደረሰባቸው ካልታሰሱ ግዛቶች የሚነሳ፣ አሊያም ባልታወቁ አማልክት የሚታዘዝ የሚመስል እንደ አንዳች የሚጫን ክቡድ አርምሞ ይቆጣጠረኛል፡፡ ይህንን ደብዳቤ በምጽፍልሽ በዚህች አፍታ እንኳን  በሕይወት ውስጥ እጂጉን አስደንጋጩ ቅንጣት ጭምትና ስዱድ እንደሆነ እየጠሰማኝ ነው፡፡

ከኃያሉ ማዕበል መነሳት በፊት ያሉት ሰዓታትም ሆነ ከአስደሳችም ሆነ ከአስከፊ ክስተቶች ቀጥለው የሚመጡት ቀናት ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ጭምት፣ ጥልቅ፣ በንቅቃናቄ አልባ ነበልባሎችና በተዘረጉ አክናፍ የተሞሉ …
                                   ***     
                                                                                                                      ኒውዮርክ
                                                                                                            እሁድ ጥር 21፣ 1912 እ.ኤ.አ
የአርምሞው ሰዓት ገና ስላላለቀ በትንሹ ስቱዲዮዬ መስኮት በኩል በገሃነምና መንግስተ ሰማያት መካከል በሚተላለፉ ጥላዎች ላይ አፍጥጬ ቆሜልሻለሁ፡፡ ሕይወትን ከዚህ በፊት ቀምሷት እንደማያውቅ እንግዳ ሰው እየኖርኳት እገኛለሁ፡፡ ቀናት በሚፋጁ ሀሳቦች፣ ሌሊቶች እንግዳ በሆኑ ህልቆመሳፍርት ሕልሞች ተሞተዋል፡፡ በቀኑ መጨረሻና በሌሊቱ መጀመሪያ መካከል የሚከሰተው የምሽቱ ጊዜ እንደ አይነርግብ ነው፡፡ ለዚያውም ሰባት እጥፋቶች ያሉት ጌጠኛ አይነርግብ…

በሕይወት ውስጥ ብዙ የሚያንገፈግፍ ደስታ አለ፤ ብዙ ጥዑም የሆነ አሳርም እንደዚሁ… እናም ያንቺው ካህሊል የሆነችን ስዕል እንዴት መሳል፣ ወይ የሆነችን አንዲት መስመር ሀሳብ እንዴት ማስፈር እንዳለበት በቅጡ ይገነዘብ ዘንድ ወደ ሀሴትና ሰቆቃ ጥልቅ ያለማመንታት መዘፈቅ አለበት፡፡
                                  ***
                                                                                                                           
                                                                                                      
                                                       
                                                                                         ኒውዮርክ
                                                                                                     እሁድ ግንቦት 26 1912 እ.ኤ.አ
                               መንፈሴ ዝግጁ ቢሆንም አካሌ ተዝለፍልፎልሻል፡፡
ውድ ሜሪ ደህና አይደለሁም፡፡ መላ ህዋሴ፣ እግዜርን፣ ሕይወትን ምልዓቱን የምገናኝበት አረንጓዴ ከባቢ በመሻት አየቃተተ ነው፡፡ ጸደይ በኮረብቶች መካከል እየተርገበገበች እየደነሰች ሰው የሆነች ጠባብ የጭለማ ክፍል ውስጥ መታጎር የለበትም፡፡ ውጭ የሚያስደንቅ አስደሳች ቀን ሆኗል፡፡ ሆኖም ለባብሼ ለእግር ጉዞ ለመውጣት የሚያበቃ አካላዊ ጥንካሬ የለኝም፡፡

መቼስ አንቺም በጥቀቱ እንኳን ደክሞሽ መሆን አለበት፡፡ አይ አይ… ለካ አንቺ መቼም ደክሞሽ አያውቅም! ህመም አያውቅሽም፡፡ አካልሽ እንደ መንፈስሽ ሁሉ ሁልጊዜ ንቁ፣ ዘወትር ዝግጁ፣ ምንጊዜም ጉጉ ነው፡፡ ልክ እንደ ሊባኖስ ዝግባ የተትረፈረፈ ጥንካሬ ባለቤት ነሽ፡፡

እነዚያ ሰዎች ዛሬ ከሰዓት እንዳይመጡ እመኛለሁ፡፡ እኔ እና አንቺ ብቻ በደኑ ውስጥ በዛፎች መካከል እየተመላለስን እንድናወራ፣ የእንጆሪ ፍሬዎች እንድንበላም ፍላጎቴ ነበር፡፡  
                                    ***
                                                         
                                                                                                            ኒውዮርክ
                                                                                                              ሐሙስ የካቲት 8፣ 1912 አ.ኤ.አ
የሚካኤል አንጀሎ ሶኔቶች(በአስራ አራት ስንኞች የሚቀነበብ የግጥም አንድ ቅርጽ) ከሌላ ከማንኛውም ነገር ይልቅ መንፈሴን የሚያርበተብት አንዳች ነገር አላቸው፡፡ ሚካኤል አንጀሎ ሰውዬውን ከሥራዎቹ መለየት በእጂጉ አዳጋች ነው፡፡ በሚካኤል አንጀሎ ነፍስ ላይ የታተመው ትልቁ ሀቲት በድን፣ ግንዝና ንቅናቄ አልባ ይመስላል፡፡ ወደ መቃብር ጉድጓዱ ያዘገመው እንኳን ራሱም በቅጡ የማያውቀውን የተለጎመ ጉልበት፣ ኃይል (silent power) በልቡ ተሸክሞ ነው፡፡ ሕይወቱን በሙሉ ሊገልጹት የሚያስቸግር ጠጣር ሀዘን ተሸካሚ ሆኖ ያለፈውስ ምናልባት ለዚህ ይሆን?
                                    ***

ከዕለታት የሆነ ዕለት የተጻፈ                                                                                                         
ሚያዚያ 2013 ዓ.ም
*
ለእኔ እንግዳ ከሆነ ከማላውቀው ክልል ስትበሪ የመጣሽ የገነት ወፍ ሆይ አሁን ሰዓቱ ለእብደት ሜዲቴሽን ሩብ ጉዳይ ሆኗል።

በጃፓን አንድ ንጉሥ ነበረ። ይህ ንጉሥ አንድ ቀን በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም ሰዓሊያን ሰብስቦ ከመካከላችሁ ‹‹የሚመስል ሳይሆን እውነተኛ(real) የሆነ ስዕል የሚስል አንድ ሰው እፈልጋለሁ፡፡›› አለ። ሁሉም ሰዓሊያን ከባዱን ኃላፊነት ለመሸከም ሲያመነቱ አንድ ሰዓሊ ግን ‹‹ዜ ያለገደብ ከተሰጠኝ እውነተኛ (real) የሆነ ስዕል እኔ መስራት እችላለሁ። ነገር ግን ሠርቼ እስክጨርስ ድረስ ማንም ሰው እንዲያይብኝ አልፈልግም›› አለ።

ተፈቅዶለት ስራውን ጀመረ። አንድ፣ ሁለት፣ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ንጉሡ ጅጅት ብሎ ጃጀ። በመጫረሻ ሰዓሊው ስዕሉ መጠናቀቁን አብስሮ ንጉሡን ብቻ ይዞ ወደ ስዕሉ አዳራሽ ገባ።

የሳለው በር እና መንገድ ነበር። ንጉሡና ሰዓሊው ያንን የስዕል በር ከፍተው ከገቡ በኋላ ይሄው እስከዛሬ አልተመለሱም።

እኔም እንደ ንጉሡና ሰዓሊው የምትሃቱን በር ከፍቼ ወደ ምንም መሄድ ያምረኛል። ብናኝ፣ ፍናኝ አንዳች ሆኜ እስከስም መጓዝ ያምረኛል። ካንቺ ጋ ቢሆን ደግሞ…
.
.
.

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ሐገሬን እምዬን እወዳታለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ማንነቴ ነች፡፡ ኢትዮጵያዊነት ምልክቴ ነው፡፡ ዘመዶቼ የስጋዬ ክፋዮች ናቸው፡፡ ነገር ግን የወገኖቼን አስተሳሰብ አልወደውም፡፡ እትብቴ የተቆረጠበትን ሰፈር እወደዋለሁ፡፡ አመለካከቱ ግን ይደብረኛል፡፡ አብሮአደጎቼ የአሁኑ ማንነቴ መገለጫዎች ናቸው፡፡ በመልካም የቀረፁኝ እንዳሉ ሁሉ በክፋትም ያሰለጠኑኝ አሉ፡፡ ወገኔ ዘመደብዙን ያከብራል፤ ብቸኛውን ግን ይደፍራል፡፡ ገንዘብ ያለውን ያመልካል፤ ደሃውን ይንቃል፡፡ አማኙ ያገሬ ሰው ለሆዱ ሲል እምነቱን ይጥላል፤ ለጥቅምና ዝና ሲል ሕሊናውን ይከዳል፡፡ እምነቱ የይምሰል ነው፡፡ ማተቡ አንገቱ ላይ የተንተለጠለ ጌጥ እንጂ ከልቡ ጋር የተዋሃደ አይደለም፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን ስንቱ ትልቅ ትንሽ ሆነ!? ስንቱ ፊቱና ጀርባው ተለያየ?? ስንቱ ጉዱ ተገለጠ!?

የሐገሬ ሰው ለሴት ያለው አመለካከት ያናድደኛል፡፡ ሴትን የወንድ የግል ዕቃ አድርጎ የሚመለከት ማህበረሰብ ውስጥ ነው ያደግኩት፡፡ ወንድ ልጅ ሲወለድለት የሚደሰት፤ ሴት ልጅ ስትወለድለት ያን ያህል የማይፈነጥዝ ማህበረሰብ ውስጥ ነው ጥርሴን የነቀልኩት፡፡ ለምን እንደሆነ አላውቅም የሀገሬ ሰው ለድብቅ ነገር ትርጉም ይሰጣል፡፡ የውሽማን ፍቅር በግጥሙ፣ በሽለላውና በዘፈኑ የሚያቆለጳጵስ ነው የኔ ወገን፡፡ ክፉ ነገርን በኪነጥበቡ የሚያሽሞነሙን ነው ወገኔ፡፡ ጨለማ ይመቸዋል፡፡

አዳም ረታ በመረቅ መፅሐፉ፡- ‹‹የሰው እንጂ የሰፈር ጠባብ የለውም፡፡ ሰፈራችን አንጎል የለውም፡፡ ባይገባውም ያድማል›› ያላት ነገር ልቅም ያለች እውነት ነች፡፡ የአካባቢዬ ሰው ሲወድም ሲጠላም በቡድን ነው፡፡ አድመኝነት ምልክቱ ነው፡፡ ያደግኩበት ቀዬ በተናጠል አስቦ አይወድም፤ መርምሮ አይጠላምም፡፡ ጥላቻውና ፍቅሩ ሰዎች በነገሩት የሚመሰረት እንጂ አይቶና ፈርዶ አይደለም፡፡ ሳያውቅህ ይጠላሃል፤ ሳይቀርብህ ይወድሃል፡፡ ግራ የገባ ነገር!

አለቃ ገ/ሃናን አንድ ሰው ቀርቦ ‹‹እርሶ አዋቂ፣ ምጡቅ ሆነው ሳለ ለምን ህዝቡን አያስተምሩም?›› ቢሏቸው ‹‹ለዚህ ህዝብ ቁምነገር ብትነግረው አይሰማህም፤ ፌዝ ግን ይወዳል›› አሉ ይባላል፡፡ እውነት ነው! ወገኔ ፌዝ ይወዳል፡፡ አብሮ መብላትና መጠጣት፤ መሳቅ መጫወት፤ መተራረብና መጠቋቆም ያስደስተዋል፤ አብሮ መስራት ግን አልለመደም፡፡ ልስራ ብሎ ቢጀምር እንኳን ኋላ ላይ ይካካዳል፡፡ ስራ እና ቁምነገር ላይ ወደኋላ የሚል ማህበረሰብ ነው የኔ ማህበረሰብ፡፡

ያደግኩበት መንደር ይናፍቀኛል፤ ሰፈሬን እወደዋለሁ፤ ያሳደገኝ ማህበረሰብ የማንነቴ ዋልታ ነው፡፡ ነገር ግን አስተሳሰቡ አይጥመኝም፡፡ ደረቅ ነው ወገኔ፡፡ አያስብም፣ አያሰላስልም፤ አያነብም፤ አይመረምርም፡፡ የግለሰቦችን መብት አያከብርም፡፡ እንደፈለግክ የመሆን ነፃነትህን ይገዳደርሃል፡፡ አንተንና ሃሳብህን አይለይም፡፡ ትናንትህን ከዛሬህ እያምታታ በባለፈው ማንነትህ ይፈርጅሃል፡፡ አስተሳሰብህ ለየት ሲልበት ስምና አቃቂር ያወጣልሃል፡፡ እሱ ከሚያውቀው ውጪ አዲስ አስተሳሰብ ሲሰማ ያወግዛል፡፡ እውነት አንፃራዊ መሆኑን የደረሰበት ኢምንት ነው፡፡ አዕምሮው ላይ ቆልፎበታል፡፡

ሠለሞን ደሬሳ፡- ‹‹አንዳንድ ነገሮች አሉ አሥር ጊዜ ተጠይቀው፤ አሥር ጊዜ ተመልሰው፤ አሥር ጊዜ የሚጠየቁ››... እንዳለው የሀገሬ ሰው ሁሌም ጥያቄ ይሆንብኛል፡፡ ብወደውም እጠይቀዋለሁ፤ የስጋዬ ቁራጭ፣ የአካሌ ክፋይ ቢሆንም ሃሳቡን እሞግተዋለሁ፡፡ አስተሳሰቡ ስለማይጥመኝ ብዬ አልተወውም፡፡ አመለካከቱ አይስብም ብዬ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም፡፡ ለምን እለዋለሁ! ለምን እንደዚህ ሆንክ ያገሬ ሰው?? ለምንድነው ትናንትን የምትደግመው?

#ሞጋቿነኝ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ኣልሰማህም (ለምትጥለኝ)


ግዜ ጣለው ብለህ
መነሳት ኣይችልም
መውጫ የለው አና
የሌለበት ኣቅም
በዛለ ጉልበቱ
ኣይወጣም ዳገቱ
ኣሁን አድል ኣለኝ
ደስታው ላሳጣበት
ሃዘን ልለቅበት
አንባው ላፈሰው
አንደ ምንጭ ውሃ
መንገዱ ላይቀና
አንደ ቀርከሃ
ውስጡ አስኪመስለው
አንደተጣለ
በኣስፈሪ በረሃ
ሂወት ላይኖረው
አንደ ቁም ሬሳ
ሞትም ምኞት ይሁንበት
ጭራሽ ላይሆንለት
ማን አንደሆነ
ግራ አስኪገባበት
አንኳንስ ካሉት
ከሞቱት የባሰ
ሳቅ አስኪረሳ
ሁሌ አያለቀሰ
ብለህ ካሰብክ
ተሳስተሃል
አኔ ኣልሰማህም
ኣንተ ኣብቅቶልሃል
ምንም ባላገኝ
ደስታዬ ኣየጠፋም
ሂወት ይቀጥላል
መኖሬ ኣይበቃም

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ጧፍ አንደ ፀሀይ ( እናት)


ኣየው ስታበራ
ኣየው ስትደምቅ
ጧፍ ምታክል
ፀሐይ ስታስንቅ
ሌት ይሁን ቀን
የማታስታውቅ
ብርሃኗ ግዙፍ
የፍጡራን ደቂቅ
ረቂቅ ሚስጥር
የሆነች ተኣምር
ሁሌ ኣንድ ቀን
ግዜን ማይቆጠር
ዕለት የለ ከነ ወሩ
ዓመት ኣይታወቅ
ከነ መፈጠሩ
ህፃንነት አንዲሁም ወጣትነት
አርጅና አንዲሁም ጎልማሳነት
የለም አንዲህ ዓይነት ተፈጥሮነት
ኣንቺ ካለሽ በኣለም ላይ
ላይፈጠር የኔ ስቃይ
ሆነሽኛል ጥላ ከልካይ
ኣንቺ ጧፍ ፀሀይ መሳይ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

አራት ዓይነት እብደት...
በኤፍሬም ሥዩም
.
➊
ብቸኝነት ብርዱ ገላህን ቀዝቅዞ
ከሰው መሀል አንተን ለብቻህ ሰቅዞ
መጠየቅ ስትጀምር ...
ለምን!...እንዴት?...ስትል?
ጥያቄህ በራሱ እብደት ነው የሚባል
ኡፍፍፍ...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!
.
➋
መጠየቅ ሰልችቶህ ከሕዝቦች ስትርቅ
በራስህ ዓለም ላይ ህሊናህ ሲራቀቅ
አፍህ ዝም ባለ
እብድ መባል አለ።
ኤጭ!...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!
.
➌
የሕዝብ ሁሉ ሀሳብ የእብደት ሲመስልህ
ያንተ አሳብ የእውነት....
እውነት እንደሆነ ውስጥህን ሲሰማህ
እብዱ ትባላለህ።
ኤዲያ!...
አውቆ የሚተኛ ሕዝብ መሀል ነቅተን፣
አቦ ተሰቃየን!
.
➍
ዓለሙም እብድ ነው!
ግና ያለም እብደት ካንተ የሚለየው
አንተ የምታብደው ለዓለም ስትል ነው
ዓለሙ ያበደው አንተን ሊያሳብድ ነው።
ወገን ተሰቃየን!
አውቆ በተኛ አቋመ ቢስ መሐል...
ለብቻችን ነቅተን
አወይ ተሰቃየን!!
.....
ኤፍሬም ሥዩም ( ኑ ግድግዳ እናፍርስ!)

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

እኔ እና ጨረቃ
በአብረቅራቂው ጨለማ ተከብቤ
የፀጥታው ሙዚቃ ጠግቤ
የማይናፈቀው ናፍቆትሽን ናፈቅሁት
የማይጠላው ብቸኝነቴን ጠላሁት
የማይፈራው ፍርሃቴን ፈራሁት ፡፡
የማይጠፋው ፍርሃቴን ለማጥፋት
ረጋ ብዬ በፍጥነት
ዕርቃኔን ተከናንቤ
ብቸኝነቴን ደርቤ
የዓለም ፀጥታ ናፍቄ
የቤቴን ጩኸት ለቅቄ
በዕርጋታ ጊዜ ሳልፈጅ
ራመድ ራመድ…………..
ከሰፊው ቤቴ ጩኸት ተገላገልሁ
ከጠባቡ ዓለም ፀጥታ ተቀላቀልሁ፡፡
ያኔ…….
የእሩቋ ጨረቃ
ከቤቴ ጣራ አንድ እርምጃ ርቃ
በጥቁር ብርሃን ደምቃ አሸብርቃ
በአግራሞት አይታኝ ስታበቃ
“ዛሬ ምን ነካህ ጃል
ፊትህ በደስታ በርቶ አጨናንቆሃል?”
ብላ ስትጠይቀኝ
“የማይበላው ውበት የምትመግበኝ
የማይጠገበው ፍቅር የምታጠግበኝ
በማይጠጣው ሕይወት የምታረካኝ
መቼም የማትለየኝ
ወዴት ሔደች ትታኝ
አፋልጊኝ ፍቅሬን”
አልኳት ፡፡
ጨረቃም ፈርታ ለመናገር
ሳትተነፍስ አንድም ቃል
ዝም ልትለኝ ነበር፡፡
ዕንባዬን ስታይ ግን
በከንፈሯ ከንፈርሽ አሳየችኝ
ጥርት ባለ ቋንቋ አዋየችኝ
ያለሸበት ቦታ ነገረችኝ
አንቺን አሳየችኝ...
ምልክት እንዲሆን
ከከንፈር ከፀጉርሽ
ምልክት ሰጠችኝ...
የኔ ጨረቃ የኔ ናፍቆት👸

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

የኔ ወድዋ እናቴ ግጥም 😘
@Temeozen
Happy mothers day😍
#በሀፍታዋይ🙏👰

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ስምንተኛው_ንጉስ 👑እህተ ማርያም//የዘመኑ ፓስተሮች 🔔
ስለ ስምንተኛው ንጉሥ (በላቸው አብዬ) እንዲሁም እህተ ማርያም 🔔እናም የዘመኑ ፓስተሮች #አገራችን እየሆኑ ላሉት መልካም እና ተስፋ አዘል ጉዳዬች በ YouTube እና በቴሌግራም ይከታተሉን አገራችንን ሰላም ያድርግልን#አሻም🙏
/channel/smntegnawnigus8

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ምን ኣይነት ጣጣ ነው
ትንሽ ብትቆይብኝ
ጠቦኝ በጣም ጨንቆኝ
ድምፅሽ ሢጠፋብኝ
ምሥልሽ ብዥ ብሎብኝ
ቀናት ሣምንታት .....
ወራት 'ና ኣመታት
ያደረግን መሥሎኝ....
ኣንዴ ሥከሥሽ
ኣንዴ ሥዋሥሽ
ይህኔ እኮ እንቺ ...
ምንም ኣልመሠለሽ
ምን ያህል እንደቆየሽ
ለኔ ዘመን የመሠለኝ
ይህ ትንሽ ቆይታሽ...
እንደው ግን ታውቅያለሽ
በየቀኑ ሙቼ እንደምነሣ
ተገንዤ እንደምፈታ
በፍቅርሽ ኣበሣ...
ሁሌ እንደምገረፍ
ሥቃይ እንዳለብኝ
በጣም ትልቅ ሥቃይ
ቀጥረሽኝ እንዳትቆይ
ወይም እንዳትቀሪ
ወይም ...ወይም
እኔ'ጃ ብቻ ኣለኝ ሥቃይ
ምን ኣይነት ጣጣ ነው???
ምንድነው የምቀባጥረው
ግን ምን እያልኩኝ ነበር
በቃ ግን እወድሻለሁ
15.08.08

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

#የት_ነህ?!

ተሸነፍኩኝ መሰል፣ በገና ለገና፣ ትመጣለህ ብዬ፤
ባልያዝነው ቀጠሮ፣ ስጠብቅህ ነበር፣ የኔ ሰው ገላዬ።

እቀጠሮ ቦታ፣ ከደረስኩኝ ቆየሁ፤
ከሁለት ብርጭቆ ጋር፣ የምትወደውን መጠጥ አዝዣለሁ፤
ዓይንህን እያየሁ፣ ሳወጋህ እንዲመሽ፣
ላንተ ሚሆን ቦታ አዘጋጅቻለሁ፤
ለጠየቀኝ ሁላ፣ "ሰው አለው" እላለሁ።

ያለሁበት ቦታ፣ ብዙ ጥንዶች አሉ፤
በአብሮነት መርከብ ላይ፣ ፍቅር ይቀዝፋሉ።

እያየኋቸው ነው ...
አሁን ይላፋሉ
ደግሞ ይስቃሉ
ይንሾካሾካሉ
ደግሞ ይጮሃሉ...
ሳቃቸው ደስ ይላል
ስሜት ሚኮረኩር፣ ሙዚቃ ይመስላል።

እነሱን እያየሁ፣ አንተን አስባለሁ፤
ወንበሩን እየሳብኩ፣ ተጫወት እላለሁ፣
ብርጭቆ አጋጫለሁ፤
ልክ እንዳወራኸኝ፣ አንገቴን ነቅንቄ፣
ብቻዬን 'ስቃለሁ።

ምን ነካት? እያለ፣ ሰው ሁሉ ያየኛል፤
እነሱን ተዋቸው፣ አጠገቤ መስለህ፣ ሩቅ የሆንክብኝ ውዴ ናፍቀኸኛል።

ሲጎራረሱ ሳይ፣ ለ'ኔ ሚሰነዘር፣ እጅ አማረኝ መሰል፣ አስተናጋጅ ጠራሁ፤
"ምን ይምጣልሽ?" ቢለኝ፣
"እሱ ሚወደውን አምጣልኝ" ብያለሁ።

"እሱ ማ'ነው?" አለኝ፣ "ምንድነው ሚወደው?"
እውነቱን እኮ ነው፣ ምን ብዬ ልንገረው?
አንተ ልጅ ግን ማነህ?
በመሸ በነጋ፣ ለምን ነው 'ማስብህ?

አይግረምህና....
የሀሳቤ ዳርቻ፣ የትም ማረፍ ሲችል፤
ብትኖርም ባትኖርም፤ ይሄድ ይሄድና፣ ባንተ ነው 'ሚጠለል።

ሊታዘዘኝ መጥቶ፣ እንዳጎነበሰ፤
እሱን ረስቼ፣ ሀሳቤ ወዳ'ንተ ከንፎ ገሰገሰ።

መስተናገድ ትቼ....
"የእውነት ተረት" አልኩት
አለኝ "የመሰረት"

"አንድ ልጅ ነበረ፣ ስወደው የኖረ፤
እመጣለሁ ብሎ፣ ላ'መታት የቀረ፤
እኔን አስጠብቆ፣ የቀረ ሲመስለው፤
ባልያዝነው ቀጠሮ፣ ውሎው ከ'ኔ ጋር ነው፤
እባክህ ታዘዘው።"

"የኔ እመቤት" አለኝ፣ ወንበሩ ባዶ ነው፤
ማንስ ነው የሚያዘኝ? ምንድነው 'ማመጣው?
እንኳንስ ወንበሩን፣ መላ እኔነቴን፣ አንተ ነግሰህበት፣ እኮ እንዴት ሆኖ፣በያዝኩልህ ቦታ፣ ምንም ሰው ያልታየው?!

ነደደኝ።

አለመኖርህን፣ ደጋግሞ ሲነግረኝ፤
አ'ጠይቀኝ ዛሬ፣ እንዴት እንዳመመኝ፤
እንዴት እንደከፋኝ፣ እንዳንቆራጠጠኝ፤
ባዶ የሆንኩ ያህል፣ ቀን እንደመሸብኝ፤
እንዳጎነበስኩኝ፣ እየተንሰፈሰፍኩ እንዳለቃቀስኩኝ፤

እውነቱን ነው ልመነው? አንተ ልጅ የለህም?!
መምጣት ታስባለህ? ወይ አልተነሳህም?!

አትመጣም...🤔
እ?!

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

🇪🇹🇪🇹#ደራሲ ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ በራስ ሆቴል አዳራሽ (ግጥምን በጃዝ ላይ) ከተናገረው...🇪🇹🇪🇹

ኢትዮጵያን አናውቃትም! አውቃታለሁ የሚል ደፋር ነው ። ከምናስባት ሁሉ በላይ የማትገመት ሀገር ናት። እኛኮ ያልሞከርነው ክፋት የለም ። እንደ ሂትለር ዘር ተኮር ስብከትን አስፋፍተናል ። እንደ አይሁድ ሰውን እርቃኑን ሰቅለናል ፤ በድንጋይ ወግረን ገድለናል ። እንደ ስታሊን ቁልቁል ሰቅለን ገርፈናል ፤ አሰቃይተናል ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ሩዋንዳን ከበተነው የዘር ተኮር ጥላቻ ስብከት በላይ ተሰብከናል ፤ ሶማሊያን መንግሥት አልባ ካደረገው በላይ ችግር ተፈጽሞብናል ፤ ሶሪያን ካፈራረሰው በላይ ሴራና ግጭት ተከናውኖብናል ። ተከፋፍለንና ተበታትነን እንድንጠፋ እስከመገንጠል መብት ተሰጥቶናል ። ይህ ሁሉ ተሞክሮም ግን አለን ። ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ልዩ ምሥጢር ካልሆነ በቀር ማነው የሚያኖራት ?

ሳስበው ክፋትን ሁሉ ሞክረን ስለጨረስን አሁን መልካም ነገር የሚሞከርበት ጊዜ ላይ ነው ። ካሁን በኋላ በዚህች ሀገር ላይ ያልተሞከረ አዲስ ክፋት ፈልጎ ሊያገኝ የሚችል ስለማይኖር ሁሉም በጎ በጎውን ማሰብና መሥራት መጀመሩ አይቀርም ። ለኢትዮጵያ የተሻለ ጊዜ እየመጣ ነው ።

"ኢትዮጵያን አውቃታለሁ" የሚል ሰው ድፍረቱ ይገርመኛል ። እኔ እንደማላውቃት ነው ማውቀው ። ኢትዮጵያን አናውቃትም ። ፈጽሞ አላስተዋልናትም ። ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት ሀገር ስለሆነች ከሌላ ሀገር በተቀዳ ሐሳብ ልትመራ አትችልም ። ማንም ሀገር የሌለው የራሷ የሆነ ጥበብና እውቀት አላት ። በድህነት መነፅር ስለምናያት ነው እንጅ... ልዩና ማንም የሚመኛት ሀገር ናት ።

አንዳንዱ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀኛል ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የምታገለው ፣ ሕዝቡ ከእኔ ጋር ነው..." ሲል ይሰማል ። ምን ማለቱ ነው ? የትኛው ሕዝብ ? ፌስቡክ ላይ ያለው ? ሚዲያ ያለው ? ፖለቲከኛው ? ሃይማኖተኛው ? ወይስ የቱ? መለየት አለበት ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀውም የሚሰማውም ሰው ያለ አይመስለኝም ። እያስተዋልን እንናገር ።
@Temeozen

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

#BREAKING

ዛሬ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አምጥቃለች።

' ET-SMART-RSS ' በስኬት መምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በይፋዊ ፌስቡክ ጉፁ ላይ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ይህ መስኮት ከአንቺ  ጋር  ካልሆነ በድን ኦና ነው ሚሆንብኝ። ከሌሎች መስኮቶች በምን እለየዋለሁ? ለሁሉም ነገር ትርጉም የምትሰጪልኝ አንቺ ነሻ! አስቀድሞ ድንጋይ የነበረ እሱ አንቺ እና እኔ ከተቀመጥንበት በኋላ ግን ቅርስ፣ ትዝታ ይሆናል። አስቀድሞ በቡና ቤትነት ብቻ የማውቀው የሆነ ቤት አንቺን ለአንድ ቀን ብቻ ከቀጠርኩበት በኋላ ግን ቤተመቅደሴ ነው። የነቃች ነፍስ ስላለችሽ ጥላሽ ያረፈበትን ሁሉ ታሻግሪዋለሽ (your very existence transcend everything)- አንድ ቀን ጣቶችሽ ጣቶቼን የነኳቸው ዕለት ያኔ ለዘለዓለም እንዳልተኛ ሆኜ ለምባትት ለእኔ ወዮልኝ…

በይ የገነት ወፍ ሆይ ልሰናበትሽ… አሁን ለእብደት ሜዲቴሽን ሙሉ ሰዓት ሆነ…
***
ያለፈውን ዘመን እንድናፍቅ (nostalgic) ከሚያደርጉኝ መካከል  የደብዳቤ ልውውጦች ናቸው፡፡ ካህሊል ለሕይወት ዘመን አጋሩ፣ ወዳጁ የነፍስ ጓደኛው ለዚህችው ሜሪ ሐስከል በጻፈው አንድ ደብዳቤ ላይ ‹‹I talk to you, as I talk with my own heart. You and my destiny are inseparable… and what is there to hide from one’s own destiny?›› ይላል፡፡ እናም እነዚህ ደብዳቤዎችን ማንበብ የካህሊል ጅብራን ነፍስ እርቃኗን መስታውት ፊት ቆማ ከመመልከት በላይ ነው፡፡ በመጨረሻ ኦሾ ‹‹The prophet›› የተሰኘ የጅብራን መጽሐፍ ላይ በሰራው አንድ ሺህ ገጾች ያሉት ‹ኮሜንትሪ› ስለ ካህሊል የተናገራቸው አስደማሚ ገለጻዎች በኩል ወደ ወደ መውጫ በሩ ላማትር፡፡ 
 
‹Kahlil Gibran… the very name brings so much ecstasy and joy that it is impossible to think of another name comparable to him. Just hearing the name, bells start ringing in the heart which doesn’t belong to the world. Kahlil Gibran is pure music, a mystery such that only poetry can grasp it, but only sometimes.
…[He] is a man who is the most of this beloved earth. Centuries have passed; there has been great name but khalil Gibran is a category in himself. I can’t conceive that even in the future there is a possibility of another man of such deep insight into the human heart, into the unknown that surrounds us.››

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ከካህሊል ጅብራን ጥቂት ደብዳቤዎች ለቅምሻ…
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
          *
                                                                                              
ቀጥሎ የማስነብባችሁን ደብዳቤዎች በቅርቡ መተርጎም ከጀመርኩት ካህሊል ጅብራንና ሜሪ ሐስከል የተለዋወጧቸው ደብዳቤዎች ‹‹Beloved prophet››  ጥንቅር ላይ የተወሰዱ ናቸው። በመጨረሻ ‹‹ከዕለታት የሆነ ቀን የተጻፈ›› በሚል ርዕስ ሥር ያቀረብኳት ደብዳቤ ከወራት በፊት በእኔው የተከተበች መሆኗ ነው፡፡ እኔ የፃፍኳት...
እነሆ…

     *** 
                                                                                                                    ኒውየርክ
                                                                                                                                                     አርብ ህዳር 10፣ 1911
በአረብኛ ‹‹በልቤ ያለውን የምናውቀው አላህና እኔ ነን፡፡›› የሚል አንድ የቆየ መዝሙር አለ፡፡ እናልሽ ዛሬ የመጨረሻቹን ሦስት ደብዳቤዎችሽን ደግሜ ካነበብኩ በኋላ  ጮክ ብዬ ‹በልቤ ያለውን የምናውቀው አምላክ፣ ሜሪና እኔ ነን፡፡› ብያለሁ፡፡ ቢሆንልኝ ሌሎች ሰዎች በቀላሉ ይገነዘቡኝ ዘንድ ልቤን በመዳፎቼ ይዤ ብዘዋወር እወዳለሁ፡፡ ምክንያቱም እኛ ሰብዓዊያን መሰሎቻችን እንዲረዱን፣ እንዲያውቁን ከመፈለግ የሚልቅ ሌላ ጥልቅ መሻት የለንም፡፡ ሁላችንም በጋን ውስጥ እንደሚያድር ኩራዝ በውስጣችን የታፈነው ብርሃን ለዓለም ወጥቶ ቢታይ ምኞታችን ነው፡፡

የመጀመሪያው ገጣሚ የዕብድ በሚመስሉ ቃላቱ በሚያላግጡ የዋሻ ውስጥ ነዋሪዎች የፌዝ ሳቅ ስላቅ በእጅጉ ተሰቃይቶ መሆን አለበት፡፡ ምናልባት የፀሐይ ግባቱ አስደናቂ የብርሃን ድግምት በነፍሱ ጥልቅ ሥርቻ የፈጠረውን መደነቅ መሰሎቹ ይረዱለት ዘንድ ለማግባባት ደጋኑን፣ ቀስቶቹን፣ የአንበሳ ቆዳውን ያለውን ነገር ሁሉ ለማባበያነት በስጦታ አቅርቦም ይሆናል፡፡

እናስ ኪናዊ ለፈጠራ የመቅበጥበጥ ስሜት የሚለኩሰው ይህ ያለመታወቅ፣ ልብ ያለመባል፣ ያለመደመጥ፣ ራሽን ለማስመስከር የመፈለግ ቁጭት አይደለምን? ጥበብ ለጥበብነቱ ብቻ ይከወን ማለት በእርግጥም የከበረ አባባል ነው፡፡ ሆኖም የመዓልትና የሌሊትን ንብርብር ጸጥተኛ ትህፍስትን ይጋራን ዘንድ የሆነን ሰው ስሁት የመንፈስ ብርሃን ማንቃት፣ መለኮስ የበለጠ ክቡር እና አስደናቂ አይሆንምን? እውነተኛ ጥበብ እምቅ ውበቱን ለሰዎች መግለጽ የሚችል ተጨባጭ ሊሆን ይገባላ፡፡
  
ስቱዲዮዬ በእጂጉ ማራኪ ናት፡፡ ከዚህች ስቱዲዮ ውጪ በሌላ የትም ቦታ በቤቴ የሆንሁ ያህል ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ እና ደግሞ እየሰራሁ ነበር፡፡ ለእኛ ዘወትር ምልዓቱን በማደን ተቅበዝባዥነት ለተሰለፍን፣ ንጡልነታችን እንደ ሽርሽር ለሚቆጠርብን ኪነታዊያን፣ ዘለዓለም ከማይረካ የመፈለግ ጥማታችን ውጭ ሌላ ምን አለን? 
                                 ***
      
                                                                                                          
                                                                                                                    ኒውዮርክ
                                                                                                             ረቡዑ የካቲት 7፣ 1912 እ.ኤ.አ
ዛሬ ልቤ ምልዑ ሆኖልሻል፡፡ እንግዳነት፣ ስክነትና ጽሞና ያረበባቸው ጥላዎች አጥለቅልቀውታል፡፡ ለምን አትዪም? ትናንት ማታ በሕልሜ ኢየሱስን አየሁታ፡፡ የተለመደ ወዳጃዊነት የሚነበብበት ፊት፣ ትላልቅ፣  የእሳት ላንቃ የመሰሉ እሳት የሚተፉ ጸጥተኛ ዓይኖች፣ አዳፋ ቡኒ ግራጫ መጎናጸፊያ፣ ረጂም የከዘራ ምርኩዝ፣ እና ደግሞ የተለመደ በአርምሞ፣ በአባባይ ልስልስ ስሜት ወደ ሕይወት የሚማትር ገር መንፈስ…

ኦ… ሜሪ ሜሪዬ ለምንድን ነው በየዕለቱ፣ በየምሽቱ ኢየሱስን በሕልሜ ደጋግሜ የማላየው? የእርሱን ግማሽ በሚያህል መሰጠትስ እንኳ ሕይወትን መገርመም የማልችለው ለምንድን ነው? በዚህ ዓለም ላይስ እንደ እርሱ በጣም ተርታ፣ ቀላልና ገር ሆኖ ግን ደግሞ መግነጢሳዊ የወዳጅነት የስበት ግለት ያለው አንድስ እንኳን ሰው ማግኘት ያልቻልኩት ለምንድን ነው? 
                                 ***
ሐምሌ 8፣ 1914
                                                                                                                                ኒውዮርክ
ውድ ሜሪ አንቺ እጅግ የበዛ ሰዎችን የመረዳት መክሊት የተሰጠሽ ሰው ነሽ፡፡ ሕይወትን አዳይ ነሽ፡፡ አንቺ ለመጋራት ሳይሆን ሕይወቱን ለማበልጸግ የሆነን ሰው እንደሚወዳጅ ታላቅ መልዓክ ነሽ፡፡ በኑረት ዘመኔ ከአንቺ ጋር መተዋወቄ ከምልዓተ ዓለሙ ተፈጥሯዊ ስልተ ምትና ስልተ ስሪት ውጪ የሆነ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡

‹‹ዘማድማን› በተሰኘ መጽሐፌ እንደገለጽኩት የሚረዱን ሰዎች ከሕይወታችን ውስጥ የሆነውን ነገር በቁጥጥራቸው ሥር ያደርጉብናል፡፡ አንቺ ጋ ይሄ የለም፡፡ የአንቺ እኔን መረዳት ከማውቃቸው ሁሉ በተለየ ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሰላማዊ ነው፡፡ ባለፈው የመጨረሻ ጉብኝትሽ ልቤን በመዳፍሽ ይዘሽ ከላዩዋ ላይ ነቁጥ የምታክል ጥቁር ነገር አገኘሽ፡፡ በዚያችው ቅጽበት ጥቁሯ ነጥብ ለዘለዓለም ከልቤ ላይ ተፋቀች፤ እኔም ሙሉ ለሙሉ ከእስራቴ ነጻ ወጣሁ፡፡

ይሄው አሁን ደግሞ የተራራ ላይ ብህትውና ላይ ነሽ፡፡ በበኩሌ በረቂቅ፣ ስውር፣ ውብ መሬቶች ላይ አርምሞን ከመለማመድ በላይ የሚያስደስት ምንም ነገር እንደሌለ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ተወዳጇ ሆይ ምልዓቱን ሀሰሳን የተራበች ነፍስሽ በአንድ ሰሞን ጀብድ ብቻ እንደማትረካ አውቃለሁና አጉል መዳፈርን ተጠንቀቂ፡፡ ምክንያቱም ለዳግም የሀሰሳ ጉዞ ወደ ተራራ መውጣት ትችይ ዘንድ ደኅንነትሽ መረጋገጥ አለበት፡፡ ቤቴ በላክሻቸው ‹አሪቲና ጠጅሳር› መልካም መዓዛ ታውዶልሻል፡፡ ስለላክሽልኝ እግዚአብሔር ይባርክሽ፡፡ 
                                            ***   
                                                                                                                ኒውዮርክ
                                                             ቅዳሜ ጥር 6፣ 1912 እ.ኤ.አ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ያየው ዓይኑ ይብራ


የአንዱን ህመም ህመማችን
ደስታውን ደስታችን
ፈገግታው ሳቃችን
ለቅሶው እምባችን
ከተለያየ ወንዝ ባህርን ፈጥረን
እንድንቆይ ያደረገን
የምንጠራው ፍቅር ብለን
አሁንስ የት ይሆን
በአፈር እና ድንጋይ እንደቆመ ተራራ
ለሚመጣው ሁሉ ምንም ሳንፈራ
ዘር ሳንቆጥር
ሳንቀንስ ስንደምር
እኔነት ቀርቶ
ለእኛነት እንድንዘምር
ያደረገን ፍቅር
ለግዜው ስላጣነው
ይንገረን ያየ ሰው
ድንገት ካያቹት እንዲህ በሉልን
እናቃለን ውስጥህ እንዳስቀየምን
ጥላቻን መርጠን አንተን እንዳስራቅን
አንድነትን ትተን መልያየታችን
መኖርን ፈርተን ለሞት መቅረባችን
እናማ ፍቅር ሆይ አንተ ነህ እግዝሄር
ወዲህ እንዳመጣሀን ያለምንም ብሄር
እናማ ፍቅር ሆይ አንተ ነህ ፈጣሪ
ልባችን አድረገው ለሰው ልጅ አክባሪ
እናማ ፍቅር ሆይ ፀፀታችን አይተህ
በሰራነው ሁሉ መቀየምን ትትህ
ይቅርታችን ተቀብለህ
የአፋችን ሳይሆን
ልባችንን አይተህ
የተጠማነው ፍቅር
ከኛ ጋር አኑረህ
ላለፍነው ሳይሆን
ለሚመጣው ብለህ
እሩቅ ቢሆንም
ናልን ተመልሰህ
በሉልን አደራ
አንይህ ተከፍተህ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ዱርዬው ቄስ


ምፅዋት ለፅድቅ ምፅዋት ለአምነት
ምፅዋት ለሰማያት ምፅዋት ለገነት
አያለ የሚጮህ ኣንድ ዱርዬ ኣባት
ከፊታችን ቆሞ ከደጀ ሰላሙ
ስጡ ይል ነበር ለሁሉ አንደ ኣቅሙ
ማር በሚመስል በለስላሳ ኣንደበት
ምአማን በሚማርክ ባልታወቀ ውሸት
ህዝቡም ትዝ ሲለው የሰራውን ሃጥያት
መንግስተ ሰማዩን ልውረሰው በማለት
ከኪሱ ሙስና ኣውጥቶ ጣለለት
አኔም ይህ ኣይቼ ለአግዚሄር ኣዘንኩለት

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

𝐁𝐞 𝐜𝐨𝐧𝐟𝐢𝐝𝐞𝐧𝐭.
𝐁𝐞 𝐬𝐮𝐜𝐜𝐞𝐬𝐬𝐟𝐮𝐥.
𝐁𝐞 𝐛𝐞𝐚𝐮𝐭𝐢𝐟𝐮𝐥.
𝐁𝐞 𝐢𝐧𝐭𝐞𝐥𝐥𝐢𝐠𝐞𝐧𝐭.
𝐁𝐞 𝐡𝐚𝐫𝐝𝐰𝐨𝐫𝐤𝐢𝐧𝐠.
𝐁𝐞 𝐜𝐚𝐫𝐞𝐟𝐫𝐞𝐞.
𝐁𝐞 𝐦𝐨𝐝𝐞𝐬𝐭.
𝐁𝐞 𝐝𝐫𝐢𝐯𝐞𝐧.
𝐁𝐞 𝐟𝐨𝐫𝐠𝐢𝐯𝐢𝐧𝐠.
𝐁𝐞 𝐜𝐫𝐞𝐚𝐭𝐢𝐯𝐞.
𝐁𝐞 𝐫𝐞𝐥𝐚𝐱𝐞𝐝.
𝐁𝐞 𝐦𝐨𝐭𝐢𝐯𝐚𝐭𝐞𝐝.
𝐁𝐞 𝐞𝐝𝐮𝐜𝐚𝐭𝐞𝐝.
𝐁𝐞 𝐭𝐡𝐨𝐮𝐠𝐡𝐭𝐟𝐮𝐥.
𝐁𝐞 𝐤𝐢𝐧𝐝.
𝐁𝐞 𝐝𝐞𝐭𝐞𝐫𝐦𝐢𝐧𝐞𝐝.
𝐁𝐞 𝐠𝐨𝐨𝐝.
𝐁𝐞 𝐮𝐧𝐬𝐭𝐨𝐩𝐩𝐚𝐛𝐥𝐞.
𝐁𝐞 𝐤𝐧𝐨𝐰𝐥𝐞𝐝𝐠𝐞𝐚𝐛𝐥𝐞.
𝐁𝐞 𝐬𝐲𝐦𝐩𝐚𝐭𝐡𝐞𝐭𝐢𝐜.
𝐁𝐞 𝐡𝐨𝐧𝐞𝐬𝐭.
𝐁𝐞 𝐰𝐨𝐫𝐭𝐡𝐲.
𝐁𝐞 𝐬𝐭𝐫𝐚𝐢𝐧𝐠𝐡𝐭𝐟𝐨𝐫𝐰𝐚𝐫𝐝.
𝐁𝐞 𝐜𝐨𝐮𝐫𝐭𝐞𝐨𝐮𝐬.
𝐁𝐞 𝐩𝐨𝐥𝐢𝐭𝐞.
𝐁𝐞 𝐠𝐞𝐧𝐭𝐥𝐞.
𝐁𝐞 𝐬𝐭𝐫𝐨𝐧𝐠.
𝐁𝐞 𝐨𝐩𝐞𝐧.
𝐁𝐞 𝐥𝐨𝐯𝐢𝐧𝐠.
𝐁𝐞 𝐟𝐮𝐧𝐧𝐲.
𝐁𝐞 𝐬𝐞𝐥𝐟𝐥𝐞𝐬𝐬.
𝐁𝐞 𝐞𝐧𝐜𝐨𝐮𝐫𝐚𝐠𝐢𝐧𝐠.
𝐁𝐞 𝐠𝐞𝐧𝐞𝐫𝐨𝐮𝐬.
𝐁𝐞 𝐡𝐚𝐦𝐛𝐥𝐞.
"𝐉𝐔𝐒𝐓 𝐁𝐄 𝐘𝐎𝐔"
@Temeozen

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ብቻ ነው።

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ያቺ በፍልስፍናዊ
ኣንደበት
እዚህ ምድር ላይ የለችም
ያልኳት
ትኖራለችም ብየ
ያላስብኳት
ቁጭ ብላ ኣየዋት
ትላንት
ከኔ ፊት ለፊት
ለሥላሣ እየጠጣች
የበደላት ፍቅረኛዋ
ይቅርታ እያረገችለት
ልጅትዋም
ልጁም
ኣውቃቸዋለው ሁለቱም
የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ
ልጁም ይወዳታል
እሷም ይገባታል
ግን .....
ምን ብያሥቀይማት
ምን ቢበድላት
በጣም እንደሚወዳት
ደጋግሞ ነገራት
ታድያ....
እሥዋም የወንድ ልጅ እምባ
ኣላስችልሽ ቢላት
ሆድዋ ባባ......
ለኳ እውነት ነበር(ልጁ)
የነገረኝ ፍቅር
የለም ያልኩት እኔ
ትላንትና ኣየሁት ባይኔ
የልጅትዋ ትልቅነት
የልጁ ቅንነት
ፍቅር የለም ፍፁም
እንዳልል አረገኝ
የነዚህ ሁለት ፍቅረኛሞች:
ለካ ህይወት ....
የማትጠገብ.....
የማትሰለች ናት
ፍቅር ከሰጠናት።
ክርክር ተገጥሞ
ያውም የፍቅር ክርክር
ዳኛ ኣስጠርትው
ህይወት(life) እንድትመሰክር
ለካ እንድል ኣረጉኝ
እኚህ ሁለት እንቡጥ
ፍቅረኛሞች.....
ተጣልተው ታርቀው
ተጣልተው ታርቀው
መጣላትን ጠልተው
መቀያየምን ጥለው
ባይችሉትም ችለው
መዋደድን ወደው
ፍቅርን መርጠው ......
ያለፈውን ትተው
እይዋቸው አብረው
ከልብ ተቀራርበው።
እኔማ........
ከጥግ ተቀምጬ
ስመለከታቸው
ተለቃቅሠው
ተሳስቀው
ሳያቸው ተቃቅፈው
ተሰማኝ ውስጤ
ኣንዳች ነገር ሲሰማው
ሳይጠጣ ለስላሳው
ሣይቀመስ ችፕሡ
ረክተው ጠግበው ነበሩ እነሱ።
እንዳልተለቃቀሱ
ተቃቅፈው ለመሄድ ተነሱ
እኔም .................(ፍቅረኛሞች ተጣልተው ሲታረቁ እንዳየሁት የፃፍኩት)06,06,2008 06:21am

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

✍️ ግጥምና vs ገጠመኝ ✍️
"ሕይወት በሞኖር እየባከነ ነው"የ ሕይወት ትርጉም እኛ የምንሰጠው ትርጉም ነው"
#ፍልስፍና
#ግጥም
#ወግ
#የሃገር ፍቅር
#ውይይት (ወንድvsሴት)
#እናትነት
#ሠዉ መሆን እና ሌሎች ..... @Hirvana2526
ስለማንኛውም ጥያቄየዎች.... 0934104100
/channel/TemeOzen

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

ከ80 በላይ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪና ቱባ ባህል ያለሽ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዬ ሰላምሽ ብዝት ይበል Good Night #Ethiopiaዬ

ያ ባቢሎን እኛን በታተነን
ይሄው እስከዛሬ የእውነት ፍቅር አጣን
ቢዘፈን የለ ቢዘመር የለ
እንደው ምን ይሻላል
የምድር ስራ እንጂ ሚያስጠይቅ
በሱፊት ስንቆም ዘር አያጸድቅ

የምድር ስራ እንጂ ሚያስጠይቅ
በሱፊት ሲቆም ዘር አያጸድቅ
የሚያቅፋት የለ ሚጠርጋት የለ
ሰማይ እያት አቤት ማማሯ
ወይኔ ምድር አንቺ ከኔ እኔም ካንቺ
ፍቅር ጠፋ ፍቅር ጠፋ
ዘንበል ብለህ እየን አንድ አባቴ
አዳም አባቴ አዳም ወንድሜ
አንቺና ሄዋን አንድ አጥንቴ
እኔምከዛ መጣሁ አንችም ከዛ መጣሽ

አሪቅ ዲሽታ ጊባ አሪቅ ዲሽታ ጊና

ያ ባቢሎን እኛን በታተነን
ይሄው እስከዛሬ የእውነት ፍቅር አጣን
ቢዘፈን የለ ቢዘመር የለ
እንደው ምን ይሻላል
የምድር ስራ እንጂ ሚያስጠይቅ
በሱፊት ስንቆም ዝር አያጸድቅ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

"ስለ ንግግር ንገረን? "
አሉ እሱም እንዲህ በማለት መለሰላቸው ፦
" የምትናገሩት ከሀሳቦቻችሁ ጋር ሰላም መፍጠር ሲያቅታችሁ ነው። በልባችሁ ውስጥ ባለው ጭር ያለ ስፍራ መኖር ሳትችሉ ስትቀሩ፣ በከናፍሮቻችሁ ውስጥ ትኖራላችሁ ንግግርም አቅጣጫን የሚያዛንፍ ጊዜ ማሳለፊያ እና መደሰቻ ነው ...እናም በአብዛኛው ንግግራችሁ(ወሬያችሁ) ውስጥ የማሰብ ችሎታችሁ በከፊል ይሞታል ። ሃሳብስ በህዋ ላይ እንደምትበር ወፍ አይደለምን ?
በፍርግርግ ብረት በተሰራ የቃላት መረብ ውስጥ ከተዘጋባትስ ክንፎቿን ትዘረጋ እንደሆን እንጂ ልትበር ትችላለችን...?
በእናንተ መካከል ለብቻቸው መሆንን በመፍራት ወሬኞችን የሚፈልጉ አሉ። ምክንያቱም የብቸኝነት ፀጥታ ለአይኖቻቸው እርቃኑን የቀረውን ራሳቸውን አጋልጦ ያሳያቸዋልና ሁሌ ከእሱ ለመሸሽ ይፈልጋሉ...ደግሞም ሳያውቁት ወይም ቀደም ብለው ሳያስቡበት የሚያወሩ እና በዚህ ንግግራቸው ራሳቸው እንኳን የማያውቁትን እውነት ገልጠው የሚያሳዩም አሉ...
በውስጣቸው እውነትን የያዙ ፣ ነገር ግን በቃላት የማይናገሩትም አሉ። እንደዚህ ባሉት ሰዎች ልብ ውስጥ የእውነት መንፈስ ዜማ በሚደረድር ትርታዊ ፀጥታ ውስጥ ይኖራል...
ጓደኞቻችሁን በመንገድ ዳር ወይም በገበያ ቦታ ስታገኙዋቸው በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ፣ ከናፍራችሁን ያንቀሳቅስ ፤ ምላሳችሁንም ይምራ።
የጽምፆቻችሁ ድምፅም ለጆሮዋቸው ጆሮ ይናገር..የወይንን ጣዕም ሁሌ እንደሚያስታውስ ሁሉ ፣ የጓደኞቻችሁ ነፍስ የልባችሁን እውነት ጠብቆ ያቆያል አይደለምን? ቀለሙ(ጣዕሙ) በተረሳ ጊዜ ግን ዕቃውም አይታወስም ። "
# ካህሊል_ጂብራን_The_prophet

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

You ask me: what is right, what is wrong?

I say to you to be awake is right.

To be asleep is wrong.
I don't determine acts wrong and right as such.

My focus is your being.

My effort is that you are there in your being then whatever you do is right. -

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

አየሽ አለማወቅ ቀጣሽ
ሰው አያሳጣሽ አና
አንቺ ግን ሰው አጣሽ
እሱን ተይው ግን ከኔ ከፍታ ወረድሽ
አየሽ የስራሽ ይስጥሽ
በጥዋቱ ተነስቼ
እርግማን ጀመርኩ ማመስገን ትቼ
የሌላውን እንጃ ዛሬ ግን መረረኝ
ለመወደደሽ በየ ሰለ ሰማሁ ያለሽኝ
ቆይ ቆይ
ማመን እና ማፍቀር ተምታታሽ መሰለኝ
አየሽ ወንድ ጅል ይባላል
እወነትም ልሆን ይችላል
ሴት ግን መሰሪ ናት ሰይጣን
ያንቺ ግን ይለያል መሰለኝ
ያሁን ቀርቶ የድሮውን ነው ነው 'ምያመኝ
አየሽ አንቺ እንኳን ገብቶሽ
ቀለል አድርገው አለሽኝ
እኔ ትላንት ና ነገ የኔ አይደሉም
ዛሬ ነው ምወድሽ ሌላው ኔ አላውቅም
ግን በትላንት አልጋ ተኝተሽ
ጆሮየ ነው? እኔን በሌላ ስም ጠራሽ?
ወይም የትኛው አልጋ ከማን ጋ እንዳለሽ ጠፋሽ?
በውሸት ውሸት በምክንያት ምክንያት ደርድረሽ
አደራ እንዳፈርስሽ
ቆይ የትላንቱ አልጋ ትዝ ሲልሽ ነው?
አይንሽ ምትጨፍኚው የሚሸሸው ልብሽ
ህልም እና እውን እሚምታታብሽ?
እኔ አፈቅርሻለሁ ስለዚህም ነው
በሁሉም ስህተትሽ ልክ የምትሆኚው
እንጂማ አንቺ ባትሆኚ የፍቅር አንድየ
ባረፍኩ ነበር ድሮ ድሮ ጥየ

Читать полностью…

"𝐎𝐳𝐞𝐧 𝐓𝐞𝐦𝐞 𝐎𝐳𝐞𝐧"

This release features Gigi singing (Live) her original songs mixed with some Ethiopian traditional tunes – all sung in Amaharic – bridging African styles, Reggae, Dub, Avant-Funk,/Jazz, World Beat, Trance, and Ambient music. It features the following incredibly talented group of musicians:

Bill Laswell: Material founder, legendary bassist, producer, reconstructionist, inventor of Herbie Hancock’s mega-hit “Rockit”, creator of the first and only landmark full album remix-constructions on the music of Bob Marley, Miles Davis & Carlos Santana, cofounder of the Axiom Label w/Chris Blackwell, veteran of over 700 recordings to date.

Abegaz Shiota: Keyboardist, acclaimed producer/arranger of Ethiopian pop culture, has worked with most all of the important artists there.

Hamid Drake: Master drummer.

Aiyb Dieng: Senegalese percussionist.

Dominic Kanza: Post Modern African guitarist, master of many advanced styles.

The album includes two guest musicians: Steven Bernstein on trumpet / slide trumpet; and Peter Apfelbaum on tenor saxophone, flute, percussion. Both are composers, arrangers and world class band leaders in their own right.

Читать полностью…
Subscribe to a channel