ለካ እንዲህ ያምራል - የምስራቅ ወገግታ፣
ለካ እንዲህ ዉብ ነው - የሰማይ ፈገግታ፣
ለካ ልብ ይሰርቃል - የንፋስ ኮሽታ፣
ለካ እጣን ያስንቃል - የእርጥብ አፈር ሽታ፣
ደጁ ላይ እስኪደርስ - የሞት ኮቴ ዳና፣
ሰው የኑሮን ዋጋ መቼ ይረዳና?
(በ.ስ)
“. . .ህይወት ምን ያህል ሚጢጢ እንደሆነች ለመረዳት ራሱ አጭር ናት” ይላሉ የዘርፉ ምሁራን። ;)
እንዴት ከርማችሁ?
"ተቀምጦ መነሳትን የመሰለ ቀላል ድርጊት ለማከናወን ተስፋ እንደሚያስፈልግ የሚገባው ጥቂት ሰው ብቻ ነው።"
፠፠፠
የስንብት ቀለማት
Adam Reta.
They say there is story behind ol of those windows, but can every story be told?
. . . አለ'ኣ?
አንዳንዴ ይደክም የለ mnamn ምን ሁናችሁ ነው? ቢሉን አንድ ሁለት ብለን ምንዘረዝረው መዓት ጉድ ባይኖረንም ዝም ብሎ doesn't it feel like we are መጠግር'ing ol the shit load this አለም is producing tirelessly?
. . .
አይዞኝ!
(Zm blen yene ፌጦ enbabal mnamn esti💚😉)
ያኔ መጣህ ሲሉኝ
እቤታችሁ በር ስበር ብደርስ፤
"ወይ አሁን'ኮ አጎቱን ሊጠይቅ ደጋ ወጣ" አሉኝ::
የመጣህባትን በቅሎ እያየሁ ከቤታችሁ ጭቃ ምርግ ላይ እየነጨሁ የበላሁት አፈር. . .ዛሬም አፌን ይመረኛል!
እኔንም አጎቴ'ን ልጠይቅ እያልክ እዋርካው ስር ማይፃፈውን አርገን ነበራ!
ሌላ መላ'ኳን አታበጅም?
አንኮላ!
( ከትንሽዬ ነብስ የተቀዳ:: )
የገዛ ምራቄ ትን ብሎኝ ነቃሁ። ጣር ነበረው ፤እምባ ነበረው፤' ልሞት ነው?!'
አይኔን ሳልገልጥ [አልችልምም ነበር] ጠርሙሱን በዳበሳ አንስቼ ለ እስትንፋሴ ደረስኩላት። [ውሃ ።]
እንደተኙ መቅረት እንዲህ ቅርብ ለሆነው ምን አስፈቀረሽ?!
ለምን እንሶስላ ሞቅሽ? ለምን ፍልሰታ አስቀደስሽ?
አበባየሆሽ እንዳትጨፍሪ ለምን ከለከሉሽ? ለምን ጆሮሽን ተበሳሽ? ለምን አፍሽን ተሳምሽ? ለምን ቡን ጠጣሽ? ለምን እጣን ወደድሽ? ጠይም መልከ ጥፉ ለምን አማረሽ? ለምን አስቴር አወቀን ወደድሽ?
የገዛ ምራቅሽ እስትንፋስሽን ሊቆልፍ ሲነሳ ለምን ተንደፋድፈሽ አተረፍሻት ማለፊያ 'ዋን ቀን ስትናፍቂ አልነበረም? ስቃይሽ እንዲያበቃ ስትሳይ
አልነበረም? [እናቱን inner self ]
[ስለሚያልፍ ነዋ!]
[እንኳን እሰይ ደግ ] ትኩሳት ፀጥ ትንታ ድፍት በሚያደርጋት ነፍሴ አፈቀርኩ፤ እንዲህ ባጠረ ዘመኔ ባልወድህ ኖሮ ምን ሰራሽ ስባል ምን እላለሁ ?!
[መኖርን ነው ምናፈቅረው] ቶሎ ስለሚቀር።
[ሰባው 'ንም ዘመን አንድ ጥግ ቁጭ ብለን ቢያልፍስ?!]
ስለሚቀር ነው ስለሚሄድ የተለፋለት ። ለኗሪ ማን ይደክማል ?!
[[እንኳንም ስራ አልፈታሁ]]
Zion💚
"ወደፊት ህመም አይደለም፣ አለመታየት ነው የሚገድለን:: ሁሉም ሀብት ለመሰብሰብ ይንጦዘጦዛል:: ታድያ ማን ማንን ልብ ይላል? ሀሜተኛ አታሳጣኝ፣ አሽሟጣጭ አታሳጣኝ፣ የእለት አሽሙረኞች ስጠን ማለት ደግ ነው::"
አጥብያ ÷ አለማየሁ ገላጋይ!
ዘዊኬንድ ለትግራይ ድጋፍ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር አበረከተ።
አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማደረጉን WFP USA አሳውቋል።
ዘዊኬንድ ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ ውስጥ በረሃብ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ WFP USA አስታውሷል።
More : https://t.co/9vS6PfQQFj
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
እከሳለሁ እንጂ እመነምናለሁ
ፍቅር ማን ገሎ እሞትልሃሁ. . ..
ፍቅር ሰው ገደሉ ሲሉም አልሰማሁ
ያከሳል ያጠቁራል እኔም አውቃለሁ. . . .
.
.
.
ለእኛ ስላለው ፍቅር በመስቀል ተስቅሎ ስለሞተልን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለ እየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!!
https://t.me/joinchat/AAAAAEW89N4Tq_hB6Om1nw
ፍላጎትህ ጠፍቶህ ያውቃል? ሰፍ ብለህ የጠበከው ነገር ሲቀር ሳታዝን ሳትደሰት it is what it is ብለህ ታውቃለህ? አለመከፋትህ አስደንግጦህ አያውቅም?
ስሜት አልባህ መሆንህ ምናምን?
ህይወት ቀለም አጥታብህ ታውቃለች?
አሞኝ ነው ርቦኝ ብለህ 'ሚሰማህን መለየት አቅቶህ ያውቃል?
ካላወክ ልትረዳኝ አትችልም::
Elilta K
. . .
"የህፃን ልጅ ጉንጭ አይሳምም!" ተብላችሁ የአራስ ልጆች ትንሽዬ እግር ስማችሁ አታውቁም?
. . . we were that precious በከንፈር እንኳን ለመነካት እናሳሳ ነበር:: አሁን ጎዳና ላይ ተዘርግፎ ከምንም ያልቆጠርነው ልጅ at some point እናቱ ከእርሱ በፊት ወልዳ አታውቅም'ና አንገቱ እንዳይቀጭ እቅፍ ድግፍ አደርጋ ይዛው ነበር::
ወ ላ ድ::
ሁላችንም ተወልደን ነው:: ረስተነዋል መሰለኝ' አንጀታችን ከተላወሰ ቆየ:: ተጨካከንን ሞናምን::
. . . እዝነት ከሌለው ሰው፤ ጠዋት ተነስቶ ዳዊት ቢደግም ለሊት ተነስቶ ሱቢህ ቢሰግድ ምን ጥቅም አለው?
መች ነው ከልባችሁ ደስ ያላችሁ?
. . .ደስታችን "ትዝ ይለኛል ልጅ እያለሁ እናቴ ለእንቁጣጣሽ ልብስ ገዝታልኝ" ምናምን ያህል መራቁ ልብ አይሰብርም?
መች ነውስ የተከፋችሁት?
. . . ከላይ የፃፍኩት ራሱ ያስከፋ የለ?
ስትሰክሩ የምትዘረግፉት እንባ ተሸክማችሁ አትዙሩ! ማርያምን ህይወት አጭር ናት ደስ ብሏችሁ ዋሉ!
. . . ደስ እንዲላችሁ አርጋችሁ ዋሉ!😍
እናቱን ግን ለምንድነው "Dear Customer your Account 1********2521 has been credited with ደሞዝ"
ምናምን የሚል text የማይደርሰኝ😭
ዲሽታ ጊና ድረስ!
ልተዉህ ያሰብኩት ትላንት ነበር። ወይም ከሰአታት በፊት። ወይ ደሞ አሁንም እያሰብኩ ነዉ። መንገድ ከጀመርኩ ቆየሁ። እርምጃዬ ከትንፋሽህ ሊርቅልኝ አልቻለም እንጂ ጉዞ ካሰብኩ ቆየሁ። ታዉቅ የለ? ለብዙ ነገሮቼ ድንበር አበጅቼ የምኖር ድኩም ነኝ። የህይወት እሳት ከጎረቤት የማልበደር ፤ እንባዬንም ሳቄንም ብቻዬን የማንጎራጉር ፤ ለምን ወደቅሽ? እንዴት ቆምሽ? ቢሉኝ ራሴን ለነገሮች ሁሉ መጥራት ያለማመድኩ ነኝ። የመጣሁት ወደ አንተ ብቻ ነዉ። የቆምኩት ጥላህ ስር ነዉ። እግርህ ስር ተኝቼ ነዉ አለሜን የሳልኩት።
...
ታዲያ ማን ነበር ጥፋተኛዉ? ገላችን እርስ በእርሱ እንዲራራቅ ማነዉ መንገድ ጠራጊ? ልቦቻችን ተደናቅፈዉ እንዲወድቁ መንገዱን በአንጃ ግራንጃ የሞላዉ የማንኛችን እጅ ነዉ? ቀድሜህ ሄድኩ ወይስ አርፍደህ መጣህ? አንተዬ እንዴት ነበር የነበርነዉ? እንዴት ነዉ የሆነዉ? ያደረግነዉና የሆነዉን የተቆራረጡ ምስሎቹን ብናገጣጥም ከነበረዉ ጋ ልክ ይሆናል? ያጎደልነዉ ካርታ የለም?
Ruth💚
|መኃልይ መኃልይ ዘ ነፍስሽ series|
#1
በተረፈ ማለት. . .ምንም አለማወቃችን አይገርምም?
ድንቁርናችን?
. . . ቅድም taxi ውስጥ አልጠጋም ብላን በሆዳችን "ገገማ" ያልናት ሴትዮ:: ዩኒፎርም የለበሱ ልጆች ባየች ቁጥር አይኖቿን እንባ የሚሞላባት ሚስክንዬ እንደሆነች አለማወቃችን አይገርምም?
እንኳን ማርያም ማረችሽ ያሏት አፎች <<የበሽተኛው ልጅ እናት>> የሚሏት ድሃ ነፍስ እንደሆነች አለማወቃችን ምናምን?
በየፀበሉ በየሃኪም ቤቱ በሽተኛ ልጇን አዝላ የምትዞር ብኩን እንደሆነች::
ለትከሻቸው የምትበዛባቸው ሰዎች እግር ስር እየዋለች አምላኳን ጥርስ ነክሳበት ስታበቃ. . .እደጁ የምትንሰቀሰቅ ባለ ሀይማኖት ሳይሆን ባለ እመነት የሆነች እመቤት እንደሆነች አለማወቃችን አይገርምም!?
ወላ አይደብርም?
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
ያው ይገባቹሃል!😉
@teyimp
መች ነው ፤ ከእነዚህ እጆች ወጥተቼ ራሴን ሰማያዊው bus ውስጥ መንግስትን ከሚያሙ ባለ ገብስማ ፀጉሮች መሃል ያገኘሁት?
በየወሬያቸው መሃል ስለ ሸዋ ዳቦ ሰልፍ መርዘም ከሚያማርሩ ሰዎች'ጋ ረዥም ሰዓት ማውራት እንዴት ቻልኩበት?
እያማረርኩ ነበር ማለት ነው?(መቼስ ቢሮ ዘይት መጣ'ኮ በሚል ወሬ መሃል ስለ ውብ ከናፍሮች አይወራ!?)
መች ነው በቅጡ "ያ ልጅ" ያላሉኝ አፎች "ያ ሰውዬ" ለማለት የፈጠኑት?
ቀስ በቀስ ቀን ላይ ቀናት እየደረብኩ ሳይሆን ድንገት ትላንት ከልጅነት በካልቾ ቂጤን ተብዬ ዛሬ <<ትልቅ>> የሆንኩ ይመስለኛል::
ይሄን መርሳት እወዳለሁ::
ግን "ለአቶ" ምናምን እያሉ ደብዳቤ እየፃፉልኝ በየት በኩል::
ምድረ ተግዳሮታሞች!
@teyimp
"ጆሮ ቆራጩ ሰውዬ እንደማይመጣ ÷ ውሸት እንደሆነ ማን ነገረሽ?
እንዲሁ በእድሜ አውቀሽው አይደለ:: አሁንም ብዙ ውሽት እየኖርሽ ይሆናል ÷ በእድሜሽ ልታውቂ. . ."
Leul Zewelde.
"የሞት ሞትን ትሞታለህ::"
ሲለን'ኮ?
ከሚወዳችሁ ልብ ገፅ ላይ በመረሳት ጨቃኝ ስለት ትፈቀፈቃላችሁ ማለቱ ነው::
ከሚወዳችሁ ልብ ውስጥ አትውጡ!