15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
#ደቡብሱዳን
ደቡብ ሱዳን ሁለት ባለስልጣናትን በቁጥጥር አዋለች።
ጦሯ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር እና የማዕከላዊ ባንክ ሊቀመንበርን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተገልጿል።
የገንዘብና ፕላን ሚኒስትር ማሪያን ዶንግሪን እና የባንኩ ገዥ ሞሰስ ማኩር ደንግ ናቸው በፖሊስ የተያዙት።
ነገር ግን መንግስት የቀድሞዎቹ ባለስልጣናት የተያዙበትን ምክንያት ይፋ አላደረገም። #sudanpost
@EyobTikuye @ThiqahEth
#NorthKorea #US
"በሰላማዊ መንገድ አብሮ ለመስራትም ይሁን ለጦርነት ለሁሉም ዝግጁ ዝግጁ ነን" - ኪም ጆንግ ኡን
ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አሳወቀች። ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካ ጋር ለመወያየት በራቸው ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።
"ከአሜሪካ ጋር አብረን የማንሰራበት ምክንያት የለም። ይህ የሚሆነው ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ያለንበትን ሁኔታ አምና ከተቀበለች ነው" ብለዋል።
ኪም "በሰላማዊ መንገድ አብሮ ለመስራትም ይሁን ለጦርነት ለሁሉም ዝግጁ ዝግጁ ነን" በማለት ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው በ2019 ወደ ሰሜን ኮሪያ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ኪም ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
ትራምፕ በዘመናዊ የአለም ታሪክ የሰሜን ኮሪያን ምድር የረገጡ የመጀመሪያው የአሜሪካ መሪ መሆን ችለዋል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Cuba
ኩባ ወታደሮቹ በፍሎሪዳ የተመዘገበ ጀልባ ላይ የነበሩ አራት ሰዎችን መግደላቸውን ገለጸች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ተጎጂዎቹ የአሜሪካ ዜጎች መሆናቸውን እያጣሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
የኩባ መንግስት በጀልባዋ ላይ ሽብር ለመፍጠር የተላኩ አስር ሰዎች እንደነበሩ አስታውቋል። ከሞቱት አራት ሰዎች ውጭ ስድስቱ መቁሰላቸው ተገልጿል።
የኩባ መንግስት ግለሰቦቹ በባህር በኩል ወደ ሀገሪቱ በመግባት ሽብር እና አመፅ ለመፍጠር አላማ ያነገቡ እንደነበሩ ጠቁሟል።
ሀቫና እነዚህ ግለሰቦች ከአሜሪካ የተላኩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልፃለች።
ዋሸንግተን እና ሀቫና ከቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ መያዝ በኋላ ግንኙነታቸው ይበልጥ ተካሯል። #telegraph
@EyobTikuye @ThiqahEth
ሲሪላንካ የቀድሞውን ብሄራዊ የኢንተለጀንስ ኃላፊ በቁጥጥር ስር አዋለች።
ሜጀር ጄነራል ሱረሽ ሳሊ በቁጥጥር ስር የዋሉት፣ በ2019 የፋሲካ በዓል ላይ በተከሰተው የቦምብ ጥቃት በመጠርጠራቸው መሆኑ ተገልጿል።
ጄነራሉ በአሁኑ ወቅት ጡረታ ወጥተው ከሚገኙበት ቤታቸው ነው ተይዘው የተወሰዱት ተብሏል።
የ2019ኙ ጥቃት የ279 ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ፣ 500 ሰዎች ተጎድተዋል። ከሟቾቹ ውስጥ 45ቱ የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። #easterneye
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Brazil
በብራዚል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 30 ሰዎች ሲሞቱ 39 ተጎዱ።
200 ሰዎች በአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ታግዘው በህይወት መገኘታቸው ተገልጿል። ከ3000 በላይ የጁዝድፎራ ከተማ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።
የጎርፍ አደጋው ለቀናት በጣለ ዝናብ አማካኝነት መከሰቱ ተገልጿል። የጁዝድፎራ ከተማ አስተዳደር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Update
"በተደጋጋሚ የምትወራው 'ቀይ ቦኔት' ብቻ ናት" - ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ
ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተይዘው "የተሰወሩ"፣ በቤተሰቦቻቸው በኩል እስካሁን ድረስ "ያሉበት አልታወቀም። ተጨንቀናል" የተባለላቸው ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተነግሯል።
ከእነዚህ ዜጎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የቀድሞ ብሔራዊ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ገነት አራጌ ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ ግለሰቧ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ/ም "ቀይ ቦኔት በለበሱ" አካላት መወሰዳቸውን ቤተሰቦቿ ሲገልጹ ነበር።
ታዲያ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ዛሬ (ማክሰኞ የካቲት 17/2018 ዓ/ም) ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ለዚሁ ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።
በኢሰመኮ ዋና መ/ቤት በተሰጠው በዚሁ መግለጫ ቲቃህ ኢትዮጵያም ተገኝቶ የነበረ ሲሆን፣ ዋና ኮሚሽነሩ ለዚሁ ጉዳይ ምላሽ ያሉትን መስጠት ሲጀምሩ "ሰዎች ይሰወራሉ፤ ይቆያሉ። ባለቤት ነኝ የሚል ሰው አይገኝም። በተደጋጋሚ የምትወራው ግን 'ቀይ ቦኔት' ብቻ ናት" ሲሉ ተደምጠዋል።
"ይህን 'ቀይ ቦኔት' የመንግስት አካል ያድርገው ሌላ አካል ያድርገው። ሰውን አንድ ቦታ አስቀምጦ የማስገደድ" ሁኔታ "የተለመደ" መሆኑንም ገልጸዋል።
አቶ ብርሃኑ፣ ለእሳቸው የደረሳቸው በጉዳዩ ላይ ያተኮረ መረጃ እንዳልቀረበ ተናግረው፣ "የዘርፉን የሥራ ኃላፊ" ተጠይቀው ሊያብራሩ እንደሚችሉ ከመጠቆም ውጭ ሰዎቹ ስላሉበት ሁኔታ ቀጥተኛ ማብራሪያ አልሰጡም።
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ሩሲያም የኑክሌር መሳሪያ የማትጠቀምበት ምክንያት የለም" - ሜድቬዴቭ
የአውሮፓ ሀገራት ኑክሌር ለዩክሬን ከሰጡ ምላሽ እንደምትሰጥ ሩሲያ አሳወቀች።
ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ ለዩክሬን የኑክሌር መሳሪያ ለመስጠት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።
ይህን ተከትሎ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት እና የብሄራዊ ደህንነት ምክትል ኃላፊ፣ ድሜትሪ ሜድቬዴቭ የሁለቱ ሀገራት እቅድ "አለማቀፍ ህግን ይጥሳል" ብለዋል።
"የጦርነቱን ሁኔታ በፍጹም ይቀይረዋል" ሲሉ ያስጠነቀቁት ድሜትሪ ሜድቬዴቭ "ሩሲያም የኑክሌር መሳሪያ የማትጠቀምበት ምክንያት የለም" ብለዋል።
ደም አፋሳሹ የሩሲያ እና ዩክሬይን ጦርነት መቋጫ እርቆት ዛሬ አራተኛ አመቱን ደፍኗል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahEth
ሜክሲኮ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት "2000 ወታደሮችን አሰማሁ" አለች።
የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ የሆነው ነመሲዮ ኦሴጉዌራ ሰርቫንቴስ መገደሉን ተከትሎ በሜክሲኮ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም ቀጥሏል።
ሀገሪቱ ተጨማሪ ወታደሮችን ያሰማራችው የተከሰተውን አመፅ ለመግታት መሆኑ ተገልጿል።
ሰርቫንቴስ የተገደለባት የጃሊስኮ ከተማ መንገዶች ተዘግተዋል፣ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፣ ሱቆች ተዘግተዋል።
በቅፅል ስሙ ኤልመንቾ እየተባለ የሚጠራው የቡድኑ መሪ የተገደለው የሀገሪቱ ጦር ባደረገው የተደራጀ ዘመቻ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ሜክሲኮ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት "2000 ወታደሮችን አሰማሁ" ብላለች። #militarnyi
@EyobTikuye @ThiqahEth
"የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ-መረብ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ተሰርዟል" - ባለስልጣኑ
ይህን ያለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ነው።
ባለስልጣኑ ምን አለ?
"አዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የሚዲያ ስነ ምግባርን፣ የኢትዮጵያ ሕጎች እና የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ አደገኛ ተግባር በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሬጉላቶሪ ስራዎች የተረጋገጠ እና በዜጎች በርካታ ጥቆማና ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ባለሥልጣኑ ይህንኑ ድርጊት በመመርመር አዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን እንዲታረም እና ከአጥፊ አካሄዱ እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ ምክር ሲሰጥ ቢቆይም ለመታረም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
በተጨማሪም በሚዲያ ዘርፉ ላይ የሙያ ስነምግባር እና የሀገርና የህዝብ ብሔራዊ ጥቅም አክብሮ እንዲሰራ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ለመታረም ፈቃደኛ አልሆነም።"
በመሆኑም፣ "ከዛሬ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተሰርዟል" ብሏል።
@EyohTikuye @ThiqahEth
#Telegram
ሩሲያ በቴሌግራም መስራች ላይ ምርመራ ጀመረች።
ፓቨል ዱሮቭ በሞስኮ "የሽብርተኞችን መልዕክት በማስተላለፍ" የወንጀል ምርመራ ተከፍቶላቸዋል ተብሏል።
ዱሮቭ እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም የቴሌግራም ካምፓኒ ግን በተደጋጋሚ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎታል።
ሩሲያ በቅርቡ ቴሌግራምን የሚተካ "ማክስ" የተሰኘ ሀገር በቀል የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ ያፋ አድርጋለች።
መንግስት ሁሉም ዜጎች አድሱን መተግበሪያ በስልካቸው እንዲያወርዱ ትዕዛዝ አስተላልፏል። #theindependent
@EyobTikuye @ThiqahEth
የአውሮፓ ህግ አውጪዎች ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን ስምምነት ሊያግዱ ነው።
የአውሮፓ ፓርላማ ቁልፍ የንግድ ስምምነቶችን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንዳይሆኑ መወሰኑን አስታውቋል።
ፓርላማው ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከአውሮፓ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ15% ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ነው።
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ትናንት "ስምምነት ስምምነት ነው" ሲሉ አዲስ ታሪፍ ሊጣል እንደማይገባ አሳስበዋል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahEth
#NEBE
"ህጋዊ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ያከበረ ነው" - በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈውን "የአወዛጋቢ" የምርጫ ክልሎች ውሳኔ የስምረት ፓርቲው አቶ ጌታቸው ረዳ ሲቃወሙ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር የሆኑት በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ ደግሞ ውሳኔውን ደግፈዋል።
በለጠ (ዶ/ር) ባጋሩት ፅሑፍ፣ "የምርጫ ቀጠናዎችን በተመለከተ መንግስት የወሰነው ውሳኔ ህጋዊ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ያከበረ ነው" ብለዋል።
"ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጡ ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ህግ እንዲያከብሩ እናሳስባለን" ሲሉም አስፍረዋል።
በለጠ (ዶ/ር) ይህን ያሉት አቶ ጌታቸውን ረዳ የምክር ቤቱን፣ ውሳኔ መቃወሙን በተመለከተ ፓርቲያቸው ስምረት ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ ያጋሩትን ፅሑፍ በማያያዝ ነው።
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Lithuania
"የአውሮፓ ህብረት የሀንጋሪን ድምጽን በድምፅ የመሻር መብት ሊያሻሻል ይገባል" - ሊቱንያ
ሀንጋሪ ዩክሬን የሩሲያን ድሩዝባ የነዳጅ ማስተላለፊያን መልሳ ካልከፈተች የአውሮፓ ህብረት ያፀደቀውን የ90 ቢሊዮን ዩሮ ብድር እንዳይሰጥ አግዳለች።
የሊቱኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከስቱቲስ ቡድሪ፣ "ለዩክሬን 90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር እና በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ሁሉም ነገር እንዳለቀ ነበር ያሰብነው" ሲሉ የሀንጋሪን አቋም ተቃውመዋል።
ቡድሪ "የአውሮፓ ህብረት የሀንጋሪን ድምጽን በድምፅ የመሻር መብት ሊያሻሻል ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል።
"የሀንጋሪ የተለየ አቋም በእውነት ያስፈራል" ብለዋል።
ከሩሲያ ነዳጅ በማስገባት ከጀርመን በመቀጠል ቀዳሚ የሆነችው ሀንጋሪ በጦርነቱ ምክንያት በመጎዳቷ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ስትቃወም ቆይታለች። #euronews
@EyobTikuye @ThiqahEth
#NEBE
አከራካሪ ቦታዎች "ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ" ተወሰነ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል "የይገባኛል" ጥያቄ የሚየሳባቸው አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ/ም የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ እየተዘጋጀባቸው ያሉ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንኑ መረጃ ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጻፈልኝ ባለው ደብዳቤ መሰረት አከራካሪ ሆነው የቆዩት፦
-የሁመራ፣
-አዲረመፅ፣
-ኮረም ኦፍላ፣
-ጠለምት እና
-ራያ አላማጣ የሚገኙ የምርጫ ክልሎች
ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው ለብቻቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን ቦርዱ ገልጿል።
በእነዚህ ቦታዎች የተነሳው "የይገባኛል" ውዝግብ፣ "በህገ መንግስታዊ ውሳኔ ሊፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ" መወሰኑን ምክር ቤቱ እንዳሳወቀውም ቦርዱ ዛሬ ያጋራው ደብዳቤ ይገልጻል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ ይህንን የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በዚሁ ደብዳቤ በይፋ አሳውቋል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
"በሜክሲኮ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ላይ በተፈጸመው ዘመቻ ሌሎች ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል" - ሌቪት
አሜሪካ በኤልሜንቾ ግድያ የኢንተለጀንስ ድጋፍ አድርጋለች ተባለ።
በሜክሲኮ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ላይ በተፈጸመው ዘመቻ ሌሎች ሶስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዋይትሃውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ተናግረዋል።
ሌቪት ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው እና ሁለት ደግሞ መማረካቸውን ገልፀዋል። "ዩናይትድ ስቴትስ ለሜክሲኮ መንግስት የኢንተለጀንስ ድጋፍ አድርጋለች" ብለዋል።
"-ታፓልፓ፣
-ጃሊስኮ እና
-ሜክሲኮ ከተሞች ዘመቻው የተፈፀመባቸው ቦታዎች ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ኤልሜንቾ ለሜክሲኮም ለአሜሪካም ዋና ኢላማ ነበር" ሲሉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Update
"የአሜሪካ ፀብ አጫሪነት የታየበት ነው" - ሩሲያ
ኩባ ውስጥ በጀልባ የተፈጸመውን ጥቃት ሩሲያ አወገዘች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፣ "የአሜሪካ ፀብ አጫሪነት የታየበት ነው" በማለት ገልፃለች።
ዛካሮቫ "በፍሎሪዳ የተመዘገበው ጀልባ በኩባ ባህር ዳርቻ ላይ መገኘቱ ግጭት አባባሽ ነው" ብለውታል።
የኩባ መንግስት በበኩሉ፣ አራት ሰዎች የሞቱበትን ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
አሜሪካ ስለጉዳዩ በሰጠችው መግለጫ ጀልባው የአሜሪካ መሆኑን እያጣራች እንደሆነ ገልፃለች። #telegraph
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Iran #US
የአሜሪካ እና የኢራን ሦስተኛ ዙር ድርድር ዛሬ ይካሄዳል ተባለ።
በጄኔቭ የሚካሄደው የዋሽንግተን እና የቴህራን የኑክሌር ድርድር ቀነ ቀጠሮ አልተያዘለትም ነበር።
ድርድሩ የሚካሄደው አሜሪካ የሀይል አማራጭን ልትጠቀም እንደምትችል እየገለጸች ባለችበት ወቅት ነው።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ በኢራን የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ ለመጠቀም ፍላጎት እንደነበራቸው ተገልጿል።
አሜሪካ ጥቃት ከፈጸመች በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እንደምታደርስ ኢራን አስጠንቅቃለች። #abcnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Niger
ኒጀር "17 የአማፂያን" ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መውሰዷን አስታወቀች።
የሀገሪቱ ጦር ለአምስት ቀናት በወሰደው እርምጃ ከ33 በላይ ሚሊሺያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ጦሩ ባካሄደው "የፀረ ሽብር" እና "ፀረ ወንጀል" ዘመቻ የቡድን ከባድ መሳሪያዎች መማረኩን አስታውቋል።
ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ 48 ኪሎግራም አደንዛዥ እፅ እና 23,250 ሊትር ነዳጅ መያዙንም ገልጿል።
ኒጀር ከአይኤስ (ISIS) ጋር በተያያዙ በጂሀዲስት ታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ደረሰብኝ ሲል ቆይቷል። #trtworld
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Turkey
የቱርክ ኤፍ 16 ጄት ተከስክሶ የአብራሪው ህይወት አለፈ።
አደጋው የተከሰተው ባልከሲር በሚገኘው የቱርክ አየር ሀይል መሆኑን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በጀቱ ውስጥ ሌሎች ሰዎች አለመኖራቸውን አረጋግጫለሁ ያለ ሲሆን፣ ጄቱ በረራ ከጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ የሬድዮ መገናኛዎች እና የመረጃ ልውውጦች ማቆማቸው ተገልጿል።
የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን የቱርክ ፍትህ ሚኒስትር አከን ጉርሌክ ተናግረዋል።
በትናንትናው እለት በኢራን በደረሰ ተመሳሳይ የሄሊኮፕተር አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahEth
#SOMALIA 🇸🇴
6.5 ሚሊዮን የሶማሊያ ዜጎች ረሃብ ተጋርጦባቸዋል ተባለ።
በሀገሪቱ 6.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች በረሃብ ውስጥ ይገኛሉ ያለው ተመድ፣ እስከ ቀጣዩ ወር ሚያዝያ ድረስ የሰብዓዊ እርዳታ ሊሰራጭ እንደሚገባ አሳስቧል።
በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ ረሃብ እንዲከሰት ማድረጉ ተገልጿል።
የሶማሊያ መንግስት ባለፈው ህዳር ወር ብሄራዊ የድርቅ አደጋ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። ድርቁ መንስኤ በሀገሪቱ ለአመታት ዝናብ ባለመጣሉ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል። #ashraqalawusat
@EyobTikuye @ThiqahEth
ትራምፕ በሀገራት ላይ እጥለዋለሁ ያሉትን 15% ታሪፍ በ10% ተፈጻሚ ማድረግ ጀመሩ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካሁን ቀደም በሁሉም ሀገራት ላይ ከፍተኛ ቀረጥ እንደሚጥሉ ቃል ቢገቡም አዲሱ ዓለም አቀፍ ታሪፍ በ10% መጠን ተፈጻሚ ሆኗል።
ባለፈው አርብ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ ቀደም ሲል የጣሉትን ሰፊ ታሪፍ ካገደ በኋላ ፕሬዝዳንቱ ከሁሉም ሀገር በሚገቡ እቃዎች ላይ 10% ዓለም አቀፍ ታሪፍ እንደሚጥሉ ተናግረው ነበር።
ቅዳሜ ዕለት ደግሞ መጠኑ 15% ይሆናል ቢሉም ዛሬ ማክሰኞ የወጡ ይፋዊ ሰነዶች ግን ትራምፕ ታሪፉን በ10% እንደጀመሩት ያሳያሉ።
የኋይት ሃውስ ባለሥልጣናት ቀረጡን ወደ 15% ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን ይህ ለውጥ መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን አልታወቀም።
ትራምፕ እርምጃውን የወሰዱት በሀገሪቱ የ1974ቱ የንግድ ህግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ነው። ይህ ህግ ፕሬዝዳንቱ የኮንግረሱ ፈቃድ ሳይጠይቁ ለ150 ቀናት የሚቆይ ታሪፍ እንዲጥሉ ይፈቅድላቸዋል። #Bbc
@ThiqahEth
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ አክቲቪስት ቀንቲን ደረንቄ ግድያ የፈረንሳይን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል።
ፈረንሳይ የአሜሪካን መግለጫ ከፖለቲካ ፍላጐት የመነጨ ነው በማለት አጣጥላዋለች።
ይህን ተከትሎ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን ኖዔል ባሮት አምባሳደር ቻርለስ ኩሽነርን ለማብራሪያ ጠርተዋል። #time
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Update
"አዲስ ስታንዳርድ 'ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ደርሰውታል' የሚለው ክስ ከእውነት የራቀ ነው" - ዋና አዘጋጁ
የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር ባለስልጣኑ ያቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።
ገለጹ በተባለው መሰረት፣ "አዲስ ስታንዳርድ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ደርሰውታል የሚለው ክስ ከእውነት የራቀ ነው።"
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን "ቀደም ሲል ስለነበሩ የሕግ ጥሰቶችም ሆነ ስለተወሰዱ እርምጃዎች ለአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል በይፋ ያሳወቀው ነገር የለም” ነው ያሉት።
የጋዜጣው አሳታሚ የሆነው ጃኬን ፐብሊሺንግ (JAKENN Publishing PLC) መብቱን ለማስከበርና የሕግ የበላይነት መከበሩን ለማረጋገጥ ያሉትን የሕግ አማራጮች እየገመገመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
በኢራን የጦር ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት ሰዎች ሞቱ።
ህይወታቸው ያለፈው ዋና አብራሪው፣ ረዳት አብራሪው እና ሁለት ንጹሐን ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል።
አደጋው የደረሰው፣ በስልጠና ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል። የአደጋ ባለሙያዎች በስፍራው በደረሱበት ወቅት ሁሉም ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል።
የአደጋው መንስዔ ገና ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።
ነገር ግን የአየር ፀባይ፣ የሄሊኮፕተር ቴክኒካል ወይም የአብራሪዎች ችግር መሆኑ እየተጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል። #yenisafaq
@EyobTikuye @ThiqahEth
የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት የተቀሰቀሰው ልክ በዛሬዋ እለት ፌብሩዋሪ 24/2022 ነበር።
ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የታዩ አበይት ክስተቶች ምን ምን ናቸው!?
የአለማቀፍ ስትራቴጂ ጥናት ማዕእከል (CSIS) ባወጣው መረጃ 1.2 ሚሊዮን ሩሲያውያን ሞተዋል።
በተመሳሳይ 500,000 እስከ 600,000 የዩክሬን ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። ሀገራቱ በውይይቶች 1000 እስረኞችን ተለዋውጠዋል።
ከኢኮኖሚ እድገት አኳያ የነዳጅ ሽያጯ የጨመረው ሩሲያ ከጦርነቱ በፊት በአለም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ 11ኛ ደረጃ ላይ ነው የነበረችው በ2025 9ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የአለማቀፍ ገንዘብ ድርጅት (IMF) መረጃ ያመላክታል።
በእነዚህ አራት አመታት ሩሲያ 20% የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት ተቆጣጥራለች። ፖላንድ፣ ጀርመን እና ቼክ ሪፐብሊክ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የዩክሬን ስደተኞችን ተቀብለዋል።
ቤተሰብ ያላቸው፣ በባህል እና በቋንቋ የሚቀራረቡ አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ ሩሲያ መግባታቸውም ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሳምንት ውስጥ ይጠናቀቃል ያሉት ጦርነት አራተኛ አመቱን አስቆጥሯል። ጦርነቱን ለማቆም የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም መፍትሔ ግን ማምጣት አልቻሉም።
ካሁን በፊት በቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት እና ስዊዘርላንድ የተደረጉ ጥረቶች ውጤታማ አልሆኑም።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ጦርነቱን በወር ውስጥ እንደሚያስቆሙት ቃል ቢገቡም፣ በስልጣን ላይ ሁለተኛ አመታቸውን አስቆጥረው ጦርነቱን ማስቆም አልቻሉም። #straightstimes #aa #politico
@EyobTikuye @ThiqahEth
ይፈጸም ይሆን❓
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ 2,000 ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከውጭ ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ ከሚጣለው ታሪፍ የሚገኘውን ገቢ በመጠቀም፣ በ2026 ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ "የ2,000 ዶላር ክፍያ ለመፈጸም" ማቀዳቸውን አሳውቀዋል።
ይህ "የታሪፍ ትርፍ ድርሻ" ተብሎ የተሰየመው ክፍያ በ2026 አጋማሽ ወይም ማብቂያ ላይ ለዜጎች ሊደርስ እንደሚችል ፕሬዝዳንቱ ፍንጭ ሰጥተዋል።
ይሁን እንጂ ክፍያው ተግባር ላይ እንዲውል በመጀመሪያ በአሜሪካ ኮንግረስ በኩል የህግ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል። ሆኖም እስካሁን ድረስ በምክር ቤቱ የጸደቀ ምንም ዓይነት ውሳኔ የለም።
እንዲሁም፣ የአሜሪካ የገቢዎች አገልግሎት (IRS) ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫም ሆነ የተቆረጠ የክፍያ ቀን እንዳለም አልተነገረም።
በተያያዘ፣ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ ከታሪፍ የሚሰበሰበው ገቢ ለዚህ መጠነ ሰፊ ክፍያ ከሚያስፈልገው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ጋር ሲነጻጸር በቂ ላይሆን ይችላል። #Menaheria
@EyobTikuye @ThiqahEth
#NEBE
"የአገራችንን ሰላም የበለጠ ከማወክ ውጭ ሌላ ትርጉም ኣላቸው ብየ ኣላምንም" - አቶ ጌታቸው ረዳ
"ህገመንግስታዊ ስርዓትን አልበኝነትን የሚያውጅ ነው" - ፓርቲያቸው ስምረት
የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አቢይ (ዶ/ር) የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ፣ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአወዛጋቢ ቦታዎች ውሳኔ ተቃወሙ።
ምርጫ ቦርድ ዛሬ ያጋራውን ደብዳቤ በማያያዝ ባጋሩት ፅሑፍ፣ "የዚህኛው ደብዳቤና ደብዳቤው መነሻ ኣደረኩት የሚለው የፌደረሽን ምክርቤት ኣፈጉባኤ ደብዳቤ የአገራችንን ሰላም የበለጠ ከማወክ ውጭ ሌላ ትርጉም ኣላቸው ብየ ኣላምንም" ብለዋል።
ፓርቲያቸውም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን መቃወሙን አትቷል። በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል "አወዛጋቢ" በተባሉ የምርጫ ክልሎች የተወሰነውን ውሳኔ "ህገ መንግስታዊ ስርዓትን አልበኝነትን የሚያውጅ ነው" ብሎታል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Nepal
በኔፓል በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 25 ቆሰሉ።
ከሟቾቹ ውስጥ የዩናይትድ ኪንግደም እና የኒውዝላንድ ዜጎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
አደጋው የተከሰተው ከቱሪስቷ ፖክሃራ ከተማ የተነሳ አውቶብስ ወደ ዋና ከተማዋ ካትማንዱ ሲጓዝ በነበረበት ወቅት ነው። አውቶብሱ በዳዲንግ ግዛት በሚገኘው የትሪሹ ወንዝ መግባቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahEth
#Greenland #US
"ሁሉም መድኃኒት የያዙ መርከቦች በአሁኑ ወቅት በአላባማ በሚገኘው የባህር ሀይል ለጉዞ ተዘጋጅተዋል" - ትራምፕ
"አያስፈልገንም፤ እናመሰግናለን" - ኔልሰን
የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ- ፍሬድሪክ ኔልሰን የዶናልድ ትራምፕን እርዳታ እንደማይፈልጉ ገልጹ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ ጀልባ ወደግሪንላንድ እንደሚልኩ ተናግረው፣ "ብዙ ሰዎች ታመዋል፣ አገልግሎት እያገኙ አይደለም" ብለዋል።
"ሁሉም መድሃኒት የያዙ መርከቦች በአሁኑ ወቅት በአላባማ በሚገኘው የባህር ሀይል ለጉዞ ተዘጋጅተዋል" ሲሉም ገልጸዋል።
የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ- ፍሬድሪክ ኔልሰን በበኩላቸው "ለህዝባችን ነፃ ህክምና የሚሰጥ የህዝብ ጤና አገልግሎት አለን" ብለዋል።
"አያስፈልገን፤ እናመሰግናለን" ነው ያሉት።
ኔልሰን ለትራምፕ "ግሪንላንድ ለድርድር ዝግጁ ናት" ያሉ ሲሆን "በማህበራዊ ሚዲያ የዘፈቀደ አስተያየት ከምትሰጥ እኛን አውራን" በማለት ገልጸዋል።
ትራምፕ "አሜሪካ ግሪንላንድን ለብሄራዊ ደህንነት ትጠቀልላለች" ማለታቸው ከአውሮፓ ሀገራት ውዝግብ አስከትሎባቸዋል። #pbsnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
የሜክሲኮ ጦር "የተደራጀ የወንጀል መሪ" ላይ "እርምጃ" መውሰዱን አስታወቀ።
የጃሊስኮ አዲስ ትውልድ መሪ ሩበን ኦስጉዌራ ወይም በቅፅል ስሙ "ኤል ሜንቾ" በተቀናጀ ዘመቻ ህይወቱ አልፏል ተብሏል።
የኤልሜንቾ ቡድን ሀገሪቱን ከፍተኛ የአደገኛ እፅ ዝውውር እና የግጭት ማዕከል አድርጓታል ተብሏል።
የቡድኑ መሪ መገደሉን ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ላይ ከባባድ የጥፋት ድርጊቶች ተፈጽመዋል።
የኤልሜንቾ መገደል ሜክሲኮ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ወቀሳና ዛቻ እንድትድን ቢያደርግም ሀገራዊ ቀውስ ግን አስከትሏል።
በአሁኑ ወቅት በርካታ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን የተቃጠሉ ተሽከርካሪዎች፣ ሱቆች እና የነዳጅ ማደያዎች መኖራቸው ተገልጿል።
በሀገሪቱ አንዳንድ ከተሞች ላይ የተኩስ ልውውጥ መከፈቱን እና በርካታ ሰዎች ለሞት ለአካል ጉዳት ተጋላጭ ሆነዋል። #thekoreaherald
@EyobTikuye @ThiqahEth