15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"አሜሪካ ኢራን የኑክሌር ባለቤት እንድትሆን አትፈቅድም፤ ስምምነቱን የማትቀበለው ከሆነ የኃይል እርምጃ እንወዳለን" - ፕሬዚዳንት ትራምፕ
ትራምፕ አሜሪካ ከመካከለኛው ምሥራቅ ልትወጣ እንደምትችል ጠቆሙ።
ውሳኔው የመጣው በዋሽንግተንና በቴህራን መካከል፣ "በኑክሌር ፕሮግራም" ላይ የተደረጉ ውይይቶች ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ነው ተብሏል።
"ወታደሮቻችን አካባቢውን ለቀው መውጣት አለባቸው" ያሉት ትራምፕ፣ "ምክንያቱም አደገኛ ቦታ ይሆናል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግር፣ "አሜሪካ ኢራን የኑክሌር ባለቤት እንድትሆን አትፈቅድም፤ ስምምነቱን የማትቀበለው ከሆነ የኃይል እርምጃ እንወዳለን" ሲሉ ተደምጠዋል።
በተያያዘ መረጃ አሜሪካ በኢራቅ የሚገኘው ኤምባሲዋ የሚገኙ ሰራተኞችን በግማሽ መቀነሷ ተሰምቷል። #reuters
#ThiqahEth
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 20 ተሽከርካሪዎች እርስበርስ በተጋጩበት አደጋ 9 ሰዎች ተጎዱ።
በፉጃይራህ ከተማ በደረሰው አደጋ ከአልሂና ወደ ድባ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ ተገልጿል።
ከትራፊክ መጨናነቅና መንገድ መዘጋት ውጭ የከፋ አደጋ አልደረሰም ተብሏል።
የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች በስፍራው ደርሰው የህክምና አገልግሎት እየሰጡና የትራፊክ ፍሰትን እየተቆጣጠሩ ይገኛሉ ተብሏል።
የአደጋው መንስኤ አንድ ተሽከርካሪ በእሳት ስትቃጠል በፍጥነት የሚጓዝ መኪና በዝግታ ሲጓዙ ከነበሩ ሌሎች መኪናዎች ጋር በመጋጨቱ እንደሆነ ተገልጿል። #gulfnews
@ThiqahEth
የኬንያ ባንኮች ብድር የማይመልሱ ግለሰቦች መበራከታቸውን ተከትሎ ለኪሳራ መጋለጣቸው ተገለጸ።
የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ (CBK) 10% የነበረውን የወለድ መጠን ከጥር 2025 ጀምሮ ወደ 9.5 ዝቅ አድርጓል።
በሀገሪቱ የሚገኙ የንግድ ባንኮች የሚያቀርቡትን ብድር በ15.4% ቀንሰዋል ተብሏል። #tukonews
@ThiqahEth
#Tigray
"ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፣ አንወጣም" - የፕሬዝዳንቱን ጽ/ቤት ጥሰው የገቡ ተፈናቃዮች
ዛሬ በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱ ተፈናቃዮች የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ጽሕፈት ቤት ግቢን ጥሰው መግባታቸውን ዲደብልዩ ዘግቧል።
በመቐለ ሰልፍ ያካሄዱት በትግራዩ ጦርነት ከምዕራብ ትግራይና ሌሎች የኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ መንግስት ወደ ቀያችን እንዲመልስን ብንጠይቅም ምላሽ አጥተናል ሲሉ በምሬት ገልጸዋል።
ተፈናቃዮቹ፣ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት ከፅሕፈት ቤቱ በራፍ ቆመው ምላሽ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ እንደቆዩ፣ ረፋዱ ላይም የክልሉን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ግቢ ጥሰው እንደገቡ ተመልክቷል።
"ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ፥ ከዚህ አንወጣም" ማለታቸውን #DW ዘግቧል።
@ThiqahEth
እንግሊዝ በፍልስጤማውያን ላይ "ግጭት በማስነሳት" ኬዝ በሁለት የእስራኤል ሚኒስትሮች ማዕቀብ ጣለች።
ማዕቀብ የተጣለባቸው የፍልስጤምን የሀገርነት እውቅና ፈፅሞ የማይቀበሉ ናቸው የተባሉትን የእስራኤል ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤንግቪር እና የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ናቸው።
በዚህም የእንግሊዝ መንግስት "በዌስት ባንክ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ ግጭት በማስነሳት" ኬዝ ማዕቀቡ እንደተጣለባቸው ገልጿል።
ማዕቀቡ ወደ እንግሊዝ እንዳይገቡ ከማድረግ በተጨማሪ በእንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።
በሚኒስትሮቹ ላይ ከእንግሊዝ በተጨማሪ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድ እና ኖርዌይ ማዕቀብ የጣሉ ሀገራት ናቸው። #skynews
@ThiqahEth
በኦስትሪያ ትምህርት ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ከሟቾች በተጨማሪ 30 ሰዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የግራዝ ከተማ ከንቲባ ኤልኬ ካህር ተናግረዋል።
ጥቃቱ የተከፈተው በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ሲሆን፣ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ወዲያውኑ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል። #upi
@ThiqahEth
"በወታደራዊ ስምሪቱ ዙሪያ የግዛቲቱ አመራሮች እውቅና የላቸውም " - ካሊፎርኒያ
የካሊፎርኒያ ገዥ ትራምፕ ወታደሮችን ወደ ሎስአንጀለስ መላካቸውን ተቃወሙ።
የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም "ወታደሮቹ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ሳይሟላ ነው የመጡት ምግብ፣ መጠጥ እና መጠለያ የለም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ወታደሮቹ ወለል ላይ ነው የሚተኙት" ያሉት ኒውሶም "ይህ ደግሞ ክብር ነክ እርምጃ ነው" በማለት ውሳኔውን ተቃውመዋል።
በወታደራዊ ስምሪቱ ዙሪያ የግዛቲቱ አመራሮች እውቅና የላቸውም ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ፍሰት ለመቆጣጠር በሚል 2000 ብሄራዊ ዘብ ወደ ሎስ አንጀለስ ላኩ መባላቸው ይታወሳል።
በዚህም ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ሲወስድ ተስተውሏል። #indiatoday
@ThiqahEth
በሎስ አንጀለስ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ፍሰት ለመቆጣጠር 2000 ብሄራዊ ዘብ ወደ ሎስ አንጀለስ ልከዋል።
ድርጊቱን የተቃወሙ ስደተኞች ወደ ስፍራው ከተላኩት ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
ተቃዋሚዎቹ የፌዴራል ኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ስም እየጠሩ ትችት ያዘለ መልዕክት ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።
ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገልጿል። #cnn
@ThiqahEth
"መርከቧ ወደ ጋዛ እንዳትገባ ለጦሩ ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ" - እስራኤል
"በእኛ የሚደርሰው በፍልስጥኤማውያን ላይ ከሚደርሰው አይበልጥም" - አክቲቪስት ግሬታ ተንበርግ
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ታዋቂዋን አክቲቪስት ግሬታ ተንበርግን ይዛ የመጣችውን የእርዳታ መርከብ እንደማያሳልፍ ገለጸ።
ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ "መርከቧ ወደ ጋዛ እንዳትገባ ለጦሩ ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ" ብለዋል።
ካትዝ ለአክቲቪሴቷ "ወደጋዛ ስለማትገቢ መመለሱ የተሻለ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የአየር ንብረትና የአካባቢ ጥበቃ አክቲቪስት የሆነችው ተንበርግ በበኩሏ "በፍልስጥኤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ማስቆም ግዴታ አለብን" ብላለች።
ለፍልስጤም ያላትን አጋርነት በተደጋጋሚ ያሳየችው አክቲቪስቷ "ልንሞትም እንችላለን" ያለች ሲሆን ነገርግን "በእኛ ላይ የሚደርሰው በፍልስጥኤማውያን ላይ ከሚደርሰው አይበልጥም" ስትል ተናግራለች። #abcnews #politico #yahoonews
@ThiqahEth
በኮሎምቢያ ፕሬዚዳንታዊ እጩው በጥይት ተመቱ።
ሴናተር ሚጉዌል ቱርባይ የምርጫውን ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል ተብሏል።
ሚጉዌል ራሳቸው ላይ የተመቱ ሲሆን፣ አሁን በምን ሁኔታ እንዳሉ አልተገለጸም ተብሏል።
የደረሰባቸውን ጥቃት ያወገዘው ፓርቲያቸው ዴሞክራቲክ ሴንተር ፓርቲ (DCP) ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።
"ጥቃቱ አግባብነት የለውም" ያለው የሀገሪቱ መንግስት በበኩሉ፣ ተኩስ ከፍቶ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል። #indiatoday
@ThiqahEth
"የድርድር ልዑካን አባላት ልውውጥ በሚደረግበት ቦታ አልተገኙም" - የሩሲያ ልዑካን ቡድን
ሩሲያ ዩክሬን የቆሰሉ ወታደሮችን የመቀበል ፍላጎት የላትም አለች።
ሩሲያና ዩክሬን በቱርክ በነበራቸው ሁለተኛ ዙር ውይይት የቆሰሉ፣ የተጎዱ እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማምተዋል።
በስምምነቱ መሰረት ሩሲያ 6000 የዩክሬን ወታደሮችን ለማስረከብ የተዘጋጀች ቢሆንም ዩክሬን አልተገኘችም ተብሏል።
ሁለቱ ሀገራት በመጀመሪያ ዙር በነበራቸው ስምምነት 1000 የጦር እስረኞችን ተለዋውጠዋል። #sputniknews
@ThiqahEth
ሰሜን ኮሪያ የኢንተርኔት መቆራረጥ ገጥሟታል።
በተፈጠረው የኢንተርኔት መስተጓጐል ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዌብሳይት እና የብሔራዊ ሚዲያ (KCNA) ድረገጽ ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው ተገልጿል።
ክስተቱ ከውጭ ከተቃጣ የሳይበር ጥቃት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑም ሆነ ስላለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል። #asiaone
@ThiqahEth
"ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም" - አሜሪካ
"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" - የአውሮፓ ህብረት
አሜሪካ "ገለልተኛ ተቋም አይደለም" ባለችው በአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አራት ዳኞች ላይ ማዕቀብ ጣለች።
ዳኞቹ በአሜሪካ የሚገኝ ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።
የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ፣"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" ሲል ማዕቀቡን ተችቷል።
ህብረቱ "የዳኝነት ባለሙያዎቹ ያለጫና በነፃነት መስራት ይኖርባቸዋል" ሲል የአሜሪካን ውሳኔ ተቃውሟል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ ተቃውመዋል። #france24
@ThiqahEth
"ከኤለን መስክ ጋር የተፈፀሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" - ዶናልድ ትራምፕ
"ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" - ኤለን መስክ
የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል።
ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ፕሬዝዳንቱና ባለሀብቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የገቡበት ውዝግብ የቴስላን ኩባንያ ለኪሳራ ዳርጓል።
የዓለም ቁጥር አንድ ባለሀብቱ መስክ ፕሬዝዳንት ትራምፕን "ያለ እኔ ድጋፍ ምርጫ ማሸነፍ አይችሉም ነበር" ብሏቸዋል።
"የትራምፕ አስተዳደር በታሪፍ ጭማሪ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የአሜሪካን ኢኮኖሚ እየጎዳ መጥቷል" በማለትም ተችቷል።
ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ለኤለን መስክ ድጎማ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
"በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭዎችን ለመቆጠብ ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን መሰረዝ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
በትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ትልቅ ድጋፍ ያደረገው መስክ በፕሬዚዳንቱ አስተዳደር ሹመት እስከማገኘት ደርሷል። #timeslive #theirishtimes
@ThiqahEth
ቻድ ለአሜሪካ ዜጎች የቪዛ አገልግሎት አገደች።
እርምጃው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት ላይ ላሳለፉት ውሳኔ የአፀፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ማህማት እንድሪስ "ቻድ የምትሰጠው ቢሊዮን ዶላርም ሆነ እቅድ የላትም፣ ነገር ግን የራሷ ክብርና ኩራት ያላት ሀገር ናት" ሲሉ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዱላሂ ሳብሬ በበኩላቸው፣ በውሳኔው መገረማቸውን ገልጸው፣ በተለይ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ መሆኑ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። #nzherald
@ThiqahEth
#Ethiopia #Mpox
"በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች ቁጥር 18 መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በበሽታው ከተያዙት ታማሚዎች መካከል የአንድ ወር ህፃን ሕይወት አልፏል" - ጤና ሚኒስቴር
ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የMpox በሽታ ታማሚ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከተገኘ ጀምሮ እስከ ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ 102 የላብራቶሪ ምርመራዎች መደረጋቸውን አስታውቋል።
"በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች ቁጥር 18 መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በበሽታው ከተያዙት ታማሚዎች መካከል የአንድ ወር ህፃን ሕይወት አልፏል" ብሏል።
እስካሁን ከተያዙት 18 ሰዎች መካከል 5ቱ ሙሉ ለሙሉ ማገገማቸውንም ገልጿል።
በሽታው የተለያዩ ዝርያዎች እንዳሉት፣ ከታማሚዎች በተወሰደ ናሙና የዘረመል ምርመራ ተደርጎ በተገኘው ውጤት ክሌድ 1ቢ (Clade 1b የተባለው የዝርያ አይነት መሆኑን ተረጋግጧል።
"ይህ የቫይረስ ዝርያ በአንጻሩ ከፍተኛ የሚባል የስርጭት መጠን ያለውና በዚህ የቫይረስ ዝርያ ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሞት መጠን በአንጻሩ ከፍተኛ እንደሆነ በሌሎች ሀገራት በተገኘ ልምድ ለማወቅ ተችሏል" ተብሏል።
በሽታውን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፣ የበሽታው ምልክቶች ካጋጠሙ #በ8335 ወይም 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ እንዲሰጥ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
@ThiqahEth
ደቡብ ኮሪያ ወታደሮቿን የድምፅ ማጉያ እንዳይጠቀሙ አዘዘች።
መረጃዎችን ለማስተላለፍ የሚጠቅሙ የድምፅ ማጉያዎች በጊዜያዊነት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ታግደዋል ተብሏል።
ሴዑል ክልከላ የጣለችው ከሰሜን ኮሪያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ በሰፈሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ላይ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። #afp
@ThiqahEth
"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" - ኤለን መስክ
ቢሊየነሩ መስክ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ትራምፕን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈርኳቸው ፅሑፎች "በጣም የተጋነኑ ነበሩ" አሉ።
"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" ያሉት መስክ፣ ለጸጸት የዳረጋቸው የትኛው አስተያየት እንደሆነ በግልጽ ባይናገሩም የተወሰኑትን አጥፍቷቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፣ ከኤለን መስክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት "ያበቃ ጉዳይ ነው" ቢሉም "የተለየ ችግር የለብኝም" ብለዋል።
ትራምፕና መስክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እርስበርስ አወዛጋቢ አስተያየቶችን ተለዋውጠው ነበር። #timeslive
ከመንግስታዊ ኃላፊነት የተነሱት መስክ ትራምፕ በተለያዩ ሀገራት ላይ የሚያሳልፉትን የታሪፍ ውሳኔ "አስቀያሚ ነው። የአሜሪካን ኢኮኖሚ ይበልጥ ያዳክመዋል" በሚል፤ የዋይትሐውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት፣ "አስተያየቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ አይቀይረውም"በሚል የመጀመሪያ ትችት ተወራውረው ነበር።
እንዲሁም ትራምፕ፣ "ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" ሲሉ፣ መስክ ደግሞ "ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" በመባባል ተቃቅረው ነበር።
ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ሁለቱ አካላት ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው፣ የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር መቀነሱም ከሳምንት በፊት ተዘግቦ ነበር።
በኋላም ትራምፕ መስክን፣ "ለዲሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ብለው ነበር።
@ThiqahEth
"በካሊፎርኒያ ያስተዋልነው በሰላምና ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃትን ነው" - ትራምፕ
የትራምፕ ውሳኔ "ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀምና የፀብ አጫሪነት ድርጊት ነው" - ካሊፎርኒያ
ትራምፕ የአሜሪካ ጦር የተመሰረተበትን ቀን ለማክበር በሰሜን ካሮላይና ይገኛሉ።
ፕሬዚደንቱ ባደረጉት ንግግር፣ "ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው" በሚል ተቃውሞ ያስከተለባቸውን በሎስአንጀለስ ያደረጉት ወታደራዊ ስምሪት ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።
"የዚህ ትውልድ ጀግና ወታደሮች በወራሪዎች እና በሦስተኛ ወገን ህግ አልባዎች ደማቸውን አያፈሱም" ብለዋል።
"በካሊፎርኒያ ያስተዋልነው በሰላምና ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃትን ነው፣ አመጸኞች የውጭ ባንድራን ሲያውለበልቡ ነው" ብለው፣ "መንግስት ሎስአንጀለስን ነፃ ያወጣል" በማለት ተናግረዋል።
ወታደሮቹ የተሰማሩት የፌዴራል ንብረት እና ዜጎችን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ዴሞክራቱ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ የትራምፕን ውሳኔ "ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀምና የፀብ አጫሪነት ድርጊት ነው" በማለት አውግዞታል። #asiaone
@ThiqahEth
#Update
የመብት ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ ከእስራኤል መውጣቷ ተገለጸ።
የአካባቢ ጥበቃ አክቲቪስት ተንበርግ ወደ ስዊድን እንድትመለስ ማድረጉን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ግሬታ ተንበርግ ከሌሎች 3 ሰዎች ጋር በመሆን ወደቤንጉሪን አየርመንገድ መሸኘታቸውን አስታውቋል።
አንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባልና ሌሎች 8 የሚደርሱት ደግሞ የመመለሻ ፎርሙን (Deportation paperwork) ለመሙላት ፍላጎት አላሳዩም ብሏል።
አክቲቪስት ተንበርግ ከሌሎች 11 የመብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ጋዛ በሚገቡበት ወቅት በእስራኤል ጦር ተይዘው ነበር። #foxnews
@ThiqahEth
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ።
ጋዜጠኛ ተስፋለም እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን "ኢትዮጵያን ኢንሳይደር" አሳውቋል።
(ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል) #EthiopianInsider
@ThiqahEth
"እኛን ማጥቃት የሚፈልግ፣ ሩሲያም ትሁን ሌላ መዘዙ አስከፊ ነው" - ማርክ ሩቴ
የኔቶን በጀት በ400% ማሳደግ ይገባል ተባለ።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (NATO) "እየጨመሩ መጥተዋል" ያላቸውን ስጋቶች ለመቀነስ የአየር እና የሚሳዔል አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ዋና ፀሐፊው ማርክ ሩቴ ተናግረዋል።
ሩቴ በለንደን ቻታም ሀውስ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ስጋቶች በተለየ መልኩ ከሩሲያ እና ቻይና እንደሚመነጩ ተናግረዋል።
ዋና ፀሐፊው፣ "ኔቶ በአንድ አመት የሚያመርተውን የመሳሪያ አቅም ሩሲያ በሶስት ወር እያመረተችው ነው" ሲሉ በንፅፅር አስረድተዋል።
ነገር ግን "እኛን ማጥቃት የሚፈልግ፣ ሩሲያም ትሁን ሌላ መዘዙ አስከፊ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። #anadoluagency
@ThiqahEth
የእስራኤል ጦር ግሬቴ ተንበርግን የያዘችውን መርከብ አገደ።
መርከቧ ወደ ጋዛ ለመግባት 200 ኪሎሜትር ሲቀራት እንድትቆም መደረጓ ተገልጿል።
መርከቧ ከተንበርግ በተጨማሪ ሌሎች 12 የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ይዛለች ተብሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ግሬታ ተንበርግን እና የሰብዓዊ እርዳታ የጫነችው መርከብ ወደ ጋዛ እንዳትገባ ለእስራኤል ጦር ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ ማለታቸው ይታወሳል። #foxnews
@ThiqahEth
"ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለዲሞክራቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዳያደርግ አስጠነቀቁ።
"ለድሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንቱ ይገጥመዋል ስላሉት አደጋ በዝርዝር አልተናገሩም። #nbcnews #aa
@ThiqahEth
"የፑቲንን ደም አፍሳሽ ጦርነት ማስቆም የሚችሉት ቁልፍ ሰው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ብቻ ናቸው" - ቻንስለር መርዝ
"ለተወሰነ ጊዜ እንዲዋጉ መተው ሳይሻል አይቀርም" - ዶናልድ ትራምፕ
የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ መርዝ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አሜሪካ ይገኛሉ።
ከትራምፕ በኋላ ወደ ስልጣን የመጡት መርዝ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና የዩክሬን ጦርነት መክረዋል።
"በሩሲያ ላይ ጫና ፈጥረው ጦርነቱን ማስቆም የሚችሉት ቁልፍ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ብቻ ናቸው" ብለዋል።
ፕራምፕ በበኩላቸው፣ ወደ ኃላፊነት ከመጡ ጀምሮ ስምምነት እንዲደረግ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው "ለተወሰነ ጊዜ እንዲዋጉ መተው ሳይሻል አይቀርም" ሲሉ ጥረታቸው እንዳልተሳካ ተናግረዋል።
"ስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ አይተሀል? ዳኛው ለተወሰነ ደቂቃ እንድፋለሙ ይተዋቸዋል፣ ከዚያ ሂዶ ያለያያቸዋል" በማለትም በምሳሌ አስደግፈው ተናግረዋል። #npr
@ThiqahEth
"አሜሪካ ያለመስክ ኩባንያ ምንም አትሆንም ትቀጥላለች" - ዶናልድ ትራምፕ
"ስለቴህራን የኑክሌር ፕሮግራም የምትነግሩን እናንተ እነማን ናችሁ!" - አያቶላህ ኮሚኒ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት የማይፈጸም ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ዛቱ።
አሜሪካ ኢራን ዩራኒየም እንድታመርት አትፈቅድም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምርቷን ካላቆመች ግን ዋሽንግተን የቴህራንን የኑክሌር ጣቢያ ኢላማ ያደረገ ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል ጠቁዋል።
"ማምረት የሚቀጥሉ ከሆነ፣ በእርግጥ እኔ አልፈልገውም ግን አማራጭ አይኖረንም እናደርገዋለን" ሲሉ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
ነገር ግን የኢራን ባለስልጣናት በዩራኒየም ምርት ላይ እንደማይደራደሩ ገልጸዋል።
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኮሚኒ "ስለቴህራን የኑክሌር ፕሮግራም የምትነግሩን እናንተ እነማን ናችሁ" ሲሉ ነቅፈዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከቅርብ አጋራቸው ኤለን መስክ ጋር ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በተናገሩበት ወቅት "ስለኤሎን ምንም አላስብም መልካሙን ሁሉ እመኝለታለሁ" ብለዋል።
"አሜሪካ ያለመስክ ኩባንያ ምንም አትሆንም ትቀጥላለች" ነው ያሉት ትራምፕ።
አሁን ላይ "በቻይና፣ በሩሲያ እና በኢራን ስራ ተጠምጃለሁ" ያሉት ትራምፕ "አሜሪካ ከእኔ ውጭ ያለማንም እገዛ መኖር ትችላለች" ሲሉ ተደምጠዋል። #ynetnews
@ThiqahEth
"ከ40 በላይ በሚሆኑ የአልሸባብ አመራሮችና አባላት ላይ እርምጃ ተወስዷል" የሶማሊያ ጦር
ሶማሊያ ከአለማቀፍ ተባባሪ አካላት ጋር በመተባበር በአሸባሪነት በተፈረጀው አልሸባብ እርምጃ መውሰዷን ገለጸች።
ዘመቻው በሂራን ክልል እንደነበር የገለፀችው ሞቃዲሾ፣ ቡድኑ የሚጠቀምባቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን አስታውቃለች።#allafrica
@ThiqahEth
ሩሲያ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 4 ዩክሬናውያን ሲገደሉ 53 ቆሰሉ።
የኪቭ ከተማ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዘለቀው የሩሲያ ጥቃት በዋናነት የኢንደስትሪ ማዕከላትን ኢላማ ያደረገ ነው ብለዋል።
ሞስኮ በእነዚህ ሁለት ቀናት ከ500 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ኪቭ ማስወንጨፏን ከንቲባው ገልጸዋል። #upi
@ThiqahEth
እንኳን 1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።
ቲቃህ ኢትዮጵያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የእምነቱ ተከታዮችን በዓል ለምትጋሩ ወዳጆች በሙሉ መልካም በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ ይመኛል።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
@ThiqhEth
"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው" - እስራኤል
እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አቪቻይ አድራየ በሀዳት፣ ሀረት ኸሪክ እና ቡርጂ አልባራን የሚገኙ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።
"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው" ብለዋል ቃል አቀባዩ።
በእስራኤልና ሊባኖስ መካከል ባሳለፍነው ህዳር ወር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የእስራኤል ጦር ከሂዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል። #aljazeera
@ThiqahEth