thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

#Update

"ሁሉም እዛው ኢራን ውስጥ ናቸው" - ሞሳድ

ሞሳድ ዛሬ በሞሳድ ዋና መስሪያ ቤት ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ላለችው ኢራን ምላሽ ሰጥቷል።

"ኢራን የሞሳድ ህንፃ ላይ በሚሳዔል ጥቃት አድርሰናል ብላለች" ያለው የእስራኤል ኢንተሊጀንስ ቢሮ፣ "እንደ እድል ሆኖ ማንም በዚያ የለም" ሲል አስታውቋል።

ሞሳድ አክሎ፣ "ሁሉም እዛው ኢራን ውስጥ ናቸው" በማለት ገልጿል።
#mossacomentary

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በሩሲያ ጥቃት 14 ዩክሬናውያን ሲገደሉ 44ቱ ቆሰሉ።

ሞስኮ ኪቭ ውስጥ 27 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቃት ማድረሷን የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር እሆር ክሊመንኮ ተናግረዋል።

በጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና ዋና ዋና መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።  
#dailyausaf

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የእስራኤል ጦር አዲስ የተሾሙትን የኢራን የጦርነት ወቅት ዋና አዛዥ አሊ ሻድማሊ መገደሉን አስታወቀ።

ዋና አዛዡ ወደ ብሄራዊ ዘብ ዋና ማዘዣ እያቀኑ በነበረበት ወቅት የአየር ላይ ጥቃት እንደፈጸመባቸው ጦሩ አስታውቋል።

ሻድማኒ ወደ ዋና አዛዥነት የመጡት ከአምስት ቀናት በፊት በመጀመሪያው የእስራኤል ጥቃት ነው።

ሻድማኒ የረጅም አመት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥነት ልምድ እንደነበራቸው ጦሩ አስታውቋል።

ኢራን ስለ አሊ ሻድማኒ ግዲያ የሰጠችው ምላሽ የለም። 
#telegraph

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ኢራን በጭራሽ የኑክሌር ፕሮግራም አይኖራትም፣ አለቀ" -  ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚደንት ድናልድ ትራምፕ የኢራን ዜጎች ከቴህራን ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ።

"የሰው ህይወት ማጣት ያሳፍራል" ያሉት ትራምፕ፣ "ኢራን በጭራሽ የኑክሌር ፕሮግራም አይኖራትም፣ አለቀ ስምምነቱን በፍጥነት መፈጸም አለባት" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ስብሰባ ጠርተው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#reuters

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን F-35 ተዋጊ ጀት መትታ መጣሏን አስታወቀች።

ኢራን የእስራኤልን F-35 ጀት መትታ ስትጥል ይህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል። 
#mehernewsagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን በአሁኑ ሰዓት በእስራኤል ላይ የድሮንና ሚሳዔል ጥቃት እየፈጸመች ስለመሆኗ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ኢራን እስራኤል ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች እንደምትገኝ አስታውቃለች።

እስራኤል የኢራን ዜጎች ከቴህራን ለቀው እንዲወጡ ስታሳስብ፣ ኢራንም በቴላቪቭ ለሚኖሩ እስራኤላውያን ተመሳሳይ ጥሪ አቅርባለች። 
#aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ ብዛት ያላቸውን የጦር አውሮፕላኖች ለእስራኤል ላከች።

የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየተጓዙ መሆናቸው ተመልክቷል።

ቬትናም የነበሩት "ዩኤስኤስ ኒሚትዝ" የተሰኙት አውሮፕላኖች፣ "ለአስቸኳይ ዘመቻ ተፈላጊነት" ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየገቡ ይገኛሉ።

አውሮፕላኖቹ በደቡብ ቻይና ባህር ለግዳጅ ተሰማርተው ነበር ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስፈላጊ ከሆነ አሜሪካ ወደ ጦርነቱ ትቀላቀላለች ብለው ነበር።
#aa

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤል ዛሬ ሰነዘረችው በተባለ ጥቃት 59 ፍልስጤማውያንን መገደላቸው ተነገረ።

ሟቾቹ በጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ ለመቀበል በመጠበቅ ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

እስራኤል በኔትዛሪም ኮሪደርና በራፋህ አልማስራዊ የሚገኙ የስደተኞች ጣቢያ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ነው የፍልስጤማውያኑ ህይወት ያለፈው። #aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"እስራኤል ጥቃቷን ካቆመች እኛም እናቆማለን" - ኢራን

"በእስራኤል ጥቃት ከ400 የሚበልጡ የኢራን ዜጎች ህይወት አልፏል" - የሰብዓዊ መብት ተቋም

ባለፉት አራት ቀናት 1,277 ዜጎች ለጉዳት መዳረጋቸውን የኢራን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ደግሞ፣ እስራኤል ከወታደራዊ ስፍራዎች በተጨማሪ በነዳጅ ማጣሪያዎችና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ያነጣጠሩ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች ብለዋል።

ጦርነቱን፣ "አስከፊና አውዳሚ" ሲሉ የገለጹት አራግቺ፣ "እስራኤል ጥቃቷን ካቆመች እኛም እናቆማለን" ሲሉም ተናግረዋል።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ የሰብዓዊ መብት ተቋም በእስራኤል ጥቃት ከ400 የሚበልጡ የኢራን ዜጎች ህይወት ማለፉን አስታውቋል።

ከእነዚህም ውስጥ 197 ንጹሐን ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ወታደሮች ናቸው ብሏል
#ukrainskapravada

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን በ4 ቀናት ውስጥ ለ9ኛ ጊዜ በእስራኤል ላይ ጥቃት አደረሰች።

በዚህ ጥቃቷ በባለስቲክ ሚሳዔል በመታገዝ የሀይፋ ከተማን፣ ኔጌቭ በረሃን እና ክርያትጋት ከተማን አጥቅታለች ነው የተባለው።

ቴህራን በዚህ የአጸፋ እርምጃዋ ወታደራዊ ስፍራዎችን እና የኢንዱስትሪ መንደሮችን ኢላማ እንዳደረገች ተገልጿል።

በዚህ የኢራን ጥቃት የተነሳ እነዚህ ሦስት ከተሞች የሀይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋል ተብሏል።

የእስራኤል ቴክኖሎጂ ማዕከል እየተባለ የሚጠራው የሀይፋ ከተማ የኑክሌር ጣቢያ የሚገኝበት እና የሚሳዔል ማከማቻ ስፍራ እንደሆነ ተገልጿል።

ከስፍራው የወጡ ምስሎች እንደሚያሳዩት ሆነ ሰባት ህንፃዎች በሙሉ በሙሉ በመውደማቸው የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች አደጋውን ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ይገኛሉ። 
#tehrantimes

(እስራኤል በቀናት ውስጥ የሰነዘረችው ጥቃትና የጉዳት መጠን በቀጣይ ይቀርባል)

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የቡድን 7 አባል ሀገራት ስብሰባ በካናዳ መካሄድ ጀመረ።

የኢራንና የእስራኤል ግጭት እንዲሁም የንግድ ጦርነት መጧጧፍ የስብሰባው አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በአልበርት ከተማ የተሰባሰቡት መሪዎቹ  ትራምፕ በተለይ በንግድ ዙሪያ ያልተጠበቀ ውሳኔ ሊያሳልፉ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ መሆናቸው ተገልጿል። #france24

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሞሀመድ ካዜሚ፣ "በእስራኤል ጥቃት ተሰውቷል" - ኢራን

ኢራን የአብዮታዊ ዘብ ኢንተሊጀንስ መምሪያ ዋና ኃላፊው መገደላቸውን አስታወቀች።

ብርጋዴር ጄነራል ሞሀመድ ካዜሚ፣  በእስራኤል ጥቃት ተሰውቷል" ብላለች ኢራን።

ከኢንተሊጀንስ መምሪያ ኃላፊው በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ ኮማንደሮች መገደላቸውን አስታውቃለች።
#mehernewsagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ እስራኤል የኢራንን ጠቅላይ መሪ ለመግደል ያቀረበችውን እቅድ ተቀበሉ።

እስራኤል የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኮሚኒን የመግደል እድል እንዳላት ለአሜሪካ ገልፃለች።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በጦርነቱ ልትሳተፍ እንደምትችልም ጠቁመዋል።
#indiatoday

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በህንድ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ አብራሪውን ጨምሮ 7 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ።

ሄሊኮፕተሯ የሀጂ ተጓዦችን ይዛ ከከዳርናዝ ወደ ጉብትካሺ ስትበር ነው አደጋው የተከሰተው።

በረራ ከጀመረች ከአስር ደቂቃ በኋላ ጫካ ውስጥ ተከስክሳ ተገኝታለች።

በሄሊኮፕተሯ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በትክክል አልታወቀም ተብሏል።

በህንድ ከቀናት በፊት ወደ ለንደን ሲበር የነበረ የኤይር ኢንዲያ አየርመንገድ ተከስክሶ 241 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። 
#mailonline

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በኢራን ላይ የሚቃጣን ጥቃት አልታገስም" - ሁቲ

የሁቲ አማፂ ቡድን አሜሪካና እስራኤል ኢራንን የሚያጠቁ ከሆነ በጦርነቱ እንደሚሳተፍ አስጠነቀቀ።

ቡድኑ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "በቀጠናው አዲስ ዙር ግጭት መፈጠሩ አይቀርም" ሲል አስታውቋል።

"በአሜሪካ ለሚጀመር ጥቃት በከፍተኛ ዝግጁነት ላይ እንገኛለን" ያለው ሁቲ፣ "በኢራን ላይ የሚቃጣን ጥቃት አንታገስም" ሲል አስጠንቅቋል።

"በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ የሚደረግ ጦርነት የኛም ጦርነት ነው" በማለትም አስታውቋል።
#politicalwire

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን የሞሳድን ዋና መስሪያ ቤት ደበደበች።

የኢራን ሚሳዔሎች የእስራኤል ኢንተሊጀንስ አገልግሎት (MOSSAD) ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል።

እስራኤል ሞሳድ ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው ጉዳት የሰጠችው ማብራሪያ የለም። 
#trendnewsagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"የቡድን 7 ስብሰባን ጥየ መውጣቴ ከተኩስ አቁም ጋር አይገናኝም" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ እየተካሄደ ያለውን ስብሰባ በማቋረጥ ወደ ዋሽንግተን ተመልሰዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ማክሮን፣ "ትራምፕ የተኩስ አቁም እቅድ አቅርበዋል" ማለታቸውን፣ "እኔ እንዲህ አይነት ሀሳብ አልወጣኝም" በማለት ውድቅ አድርገውታል።

ዶናልድ ትራምፕ "በስህተት የተሰጠ ሀሳብ መሆን አለበት" ሲሉ እቅዱ እሳቸውን እንደማይመለከት ተናግረዋል።  
#thestraitstimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ የቡድን 7 አባል ሀገራት ስለኢራን ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ አልፈርምም አሉ።

አባል ሀገራቱ በመግለጫቸው እስራኤል እና ኢራን የገቡበትን ጦርነት እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።

በተዘጋጀው ዶክመንት ላይ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ስም አለመስፈሩን በስብሰባው የታደሙ የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል።  

ፕሬዝዳንቱ በካናዳ እየተካሄደ የሚገኘው የቡድን 7 ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ወጥተው ሂደዋል ተብሏል።
#cnn

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የሀይፋ ነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲዘጋ ተወሰነ።

የእስራኤል ባለስልጣናት ኢራን እየፈጸመች ባለው ጥቃት ምክንያት ነው የነዳጅ ማጣሪያው እንደዘጋ ያደረጉት ተብሏል።

የሀይፋ ነዳጅ ማጣሪያ ትናንትና በነበረው የአጸፋ እርምጃ የመጀመሪያው ጉዳት ደርሶበት መታየቱን አልጀዚራ ዘግቧል።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Update

የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) እስራኤል በኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አወገዘች።

እስራኤል ምሽቱን በኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን (INT) ላይ በፈጸመችው ጥቃት ጋዜጠኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
#aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"እውነት እንነጋገር፣ የሩሲያ ታማኝነት ዜሮ ነው" - የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት ሩሲያ እስራኤል እና ኢራንን እንድታሸማግል አልፈልግም አለ።

የአውሮፓ ኮሚሽን ቃል አቀባይ አኑር አልኖውኒ በብራሰልስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ "ሩሲያ በተደጋጋሚ አለማቀፍ ህጎችንና የተመድን ቻርተር ጥሳለች" በማለት ሚናዋን አሳንሰዋል።

"ሩሲያ የምትበረታበት ትልቁ ነገር ጦርነት ነው" ያሉት ቃል አቀባዩ፣ "እውነት እንናገር፣ የሩሲያ ታማኝነት ዜሮ ነው" ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ሩሲያ ለማደራደር ቃደኛ መሆኗን ከገለጹ በኋላ ድጋፋቸውን ለፑቲን ሰጥተዋል።
#anadoluagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤል የኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ላይ ጥቃት ማድረሷ ተሰማ።

ቴላቪቭ ከሰዓታት በፊት በፈጸመችው ጥቃት በጋዛና ሊባኖስ በሚገኘው ቅርንጫፍ ላይም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች ተብሏል።

በዚህ ጥቃት በቀጥታ ስርጭት ዜና ሲያስተላልፉ የነበሩ በጣቢያው የሚሰሩ ጋዜጠኞች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
#irannationaltelevision   #thenationional

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ከ150,000 የሚልቁ ሰልፈኞች እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን ግፍ እንድታቆም ጠየቁ።

የሰብዓዊ መብራት ተሟጋቾችና አክቲቪስቶች በኔዘርላንድ ሄግ በመሰባሰብ እየደረሰ ነው ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም አሳስበዋል።

"እስራኤል የዘር ፍጅት እየፈጸመች ነው" ያሉት ሰልፈኞቹ በጋዛ ያለውን ጦርነት አውግዘዋል።
#middleeastmonitor

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤል 24 ዜጎቿ በኢራን መገደላቸውንና ከ5ዐ0 በላይ መቁሰላቸውን አስታወቀች።

ባለፉት አራት ቀናት በነበረው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት በአጠቃላይ 24 እስራኤላውያን ሲገደሉ ከ500 የሚበልጡት ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

በእነዚህ ቀናት ኢራን ከ300 የሚበልጡ የባለስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ተገልጿል።

ኢራን ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው ጥቃት በእስራኤል በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ አንድ ሚሳዔል መተኳሷን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሁካቤ ተናግረዋል።
#ukrainskapravada

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Update

በሚኒሶታ የዲሞክራቶችን ባለስልጣናት የገደለውን ተጠርጣሪ መያዙን ፓሊስ አስታወቀ።

የሚኒሶታ ምክር ቤት አባልና ባለቤታቸውን "በመግደል" የተጠረጠረው የ57 አመቱ ቫንስ ሉተር ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ከመኖሪያ ቤቱ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ተደብቆ እንደነበር ፓሊስ ገልጿል። 

የአሜሪካ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪው ያለበትን ለጠቆመ 50,000 ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶ ነበር።

ግድያው ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፍትህ እንዲሰጥ አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል።
#gulftoday

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የተያዘ ተጠርጣሪ እንዳልነበር ፓሊስ ከወቅቱ ተገልጾ ነበር።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ብዙ ጥሪዎች እና ስብሰባዎች እየተካሄዱ ነው፣ ብዙ እያደረኩ ነው፣ ለዚህ ሁሉ እውቅና አላገኘሁም፣ ግን ችግር የለውም ህዝቡ ይረዳዋል" - ዶናልድ ትራምፕ

ትራምፕ፣ "በእኔ ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ቢያንስ ሰላም ፈጥረዋል" አሉ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በእስራኤል እና በኢራን መካከል፣ "ሰላም እንዲመጣ ለማድረግ እየሰራሁ ነው" ባሉበት ንግግራቸው በኢትዮጵያ እና ግብፅ መካከል የነበረውን ውዝግብ መፍታት መቻላቸውን እንደተሞክሮ አንስተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የግል የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ምን አሉ?

-"ኢራንና እስራኤል ስምምነት ማድረግ አለባቸው።

-በህንድና በፓኪስታን መካከል ሰላም እንድመጣ አድርጊያለሁ፣ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገውን የንግድ ግንኙነት ተጠቅሜ ከሁለቱ ምርጥ መሪዎች ጋር ባደረኩት ንግግር ጦርነቱን ለማቆም ፈጣን ውሳኔ አሳልፈዋል።

-በመጀመሪያ የስልጣን ዘመኔ ሰርቪያ እና ኮሶቮ የተጋጋለ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ገብተው ነበር፣ ለረዥም አመታት የቆየ ቁርሾ እንደመሆኑ ሊፈነዳ የተቃርበ ጦርነት ነበር፣ እኔ ግን አስቁሜዋለሁ።

-ባይደን ረዥም ርቀት የታለመለትን ጉዳይ በተሳሳተ ውሳኔ ጎድቶት ነበር እኔ በድጋሚ አስተካከልኩት።

-ሌላኛው ኬዝ ግብፅ እና ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ላይ ተፅዕኖ በሚያመጣው ትልቅ ግድብ ላይ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር፣ በእኔ ጣልቃ ገብነት ቢያንስ ሰላም ፈጥረዋል።

-አሁንም በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከልም በቅርቡ ሰላም እንፈጥራለን።

- ብዙ ጥሪዎች እና ስብሰባዎች እየተካሄዱ ነው፣ ብዙ እያደረኩ ነው፣ ለዚህ ሁሉ እውቅና አላገኘሁም፣ ግን ችግር የለውም ህዝቡ ይረዳዋል።

-መካከለኛው ምሥራቅን እንደ አዲስ ታላቅ እናደርጋታለን" ሲሉ አስፍረዋል።
#truthsocial

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በእስራኤል እና ኢራን ግጭት የሟቾች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ።

በእስራኤል ጥቃት 406 ኢራናውያን ሲገደሉ፣ 654 የሚሆኑት ቆስለዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ መልኩ ኢራን እስራኤል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 13 እስራኤላውያን ሲሞቱ የተጎጂዎች ቁጥር ግን  አልተገለፀም።
#associatedpress #dailychampion

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን በጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ማድረሷን ገለጸች።

በቄሳሪያ በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት እና በሀደራ የኃይል ማከፋፈያ ላይ የተቃጣ ጥቃት መፈጸሙን የኢራን ጦር አስታውቋል።

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም።
#khaamapress

@ThiqhEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር የድሮን ጥቃት ተፈጸመ።  

ጥቃቱ የደረሰው በምዕራብ ኢራቅ የአንባር ግዛት በሚገኘው ኢን አልአሳድ  የጦር ሰፈር ነው ተብሏል።

ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመና ምን አይነት ጉዳት እንደደረሰ አሌተገለጸም።
#mna

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በደቡብ አፍሪካ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ49 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ጠፉ።

ከሞቱት ሰዎች መካከል ከትምህርት ቤት ወደ ቤታቸው በመመለስ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት የኢስተርን ኬፕ ግዛት ባለስልጣን ኦስካር ማቡያኔ ተናግረዋል።

በጎርፍ አደጋው የተጎዱ ከ500 በላይ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

ማቡያኔ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መጣሉ ለአደጋው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
#aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…
Subscribe to a channel