15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
በሱዳን ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ።
ሆስፒታል ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የህክምና አገልግሎት በማግኘት የነበሩ ታካሚዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል።
ሟቾቹ ቢያንስ ከ4ዐ በላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።
ዳይሬክተሩ ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ ባይገልጹም ከሟቾቹ መካከል ህፃናት እንደሚገኙበት ተናግረዋል። #reuters
@ThiqahEth
"ኢራን የሚሳዔል ጥቃት በመፈጸም ስምምነቱን ጥሳለች" - እስራኤል
"ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የተፈጸመ ጥቃት የለም" - ኢራን
"ኢራን የሚሳኤል ጥቃት አድርሳለች" ያለችው እስራኤል በመከላከያ ሚኒስትሯ በኩል በኢራን ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር አዛለች።
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ "ኢራን የሚሳዔል ጥቃት በመፈጸም ስምምነቱን ጥሳለች" ሲሉ ወንጅለዋል።
ኢራን በበኩሏ የቀረበባትን ወቀሳ "የተሳሳተ ሪፖርት ነው" በማለት እንደማትቀበለው ገልፃለች።
"ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የተፈፀመ ጥቃት የለም፣ ጥቃት አልሰነዘርንም" ብላለች። #reuters
@ThiqahEth
"ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ በእስራኤል እና ኢራን መካከል ሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጓል" - ትራምፕ
ትራምፕ በኢራንና በእስሳኤል መካከል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
ምን አሉ?
"ስምምነቱ እስራኤል እና ኢራን በሚቀጥሉት 6 ሰዓታት አንዳንድ ሂደቶችን ሳወቁ በኋላ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።
በመጪዎቹ 12 ሰዓታት ደግሞ ጦርነቱ በምን ጉዳይ መቋጨት እንዳለበት ምክክር ይደረጋል።
ኢራን ከ12 ሰዓታት በኋላ፣ እስራኤል ደግሞ ከ24 ሰዓታት በኋላ በይፋ ጦርነቱን ያቆማሉ። የ12 ቀናቱ ጦርነት መቆም ለአለም ህዝብ ደስታ ነው።
በእያንዳንዱ የተኩስ አቁም ሁለቱም ወገኖች ሰላማዊ እና አክባሪ መሆን አለባቸው።
ሁለቱም ሀገሮች እስራኤል እና ኢራን የ12 ቀኑ ጦርነት እንድቋጭ ላሳዩት ቁርጠኝነትና ብቃት እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።
ይህ ጦርነት ለአመታት የመዝለቅ እድል ነበረው። ቀሪውን የመካከለኛው ምስራቅ ያጠፋው ነበር፣ ግን በጭራሽ አይሆንም።
"እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ እግዚአብሔር ኢራንን ይባርክ፣ እግዚአብሔር መካከለኛ ምስራቅን ይባርክ፣ እግዚአብሔር አሜሪካን ይባርክ፣ እግዚአብሔር መላው አለምን ይባርክ" ብለዋል።
@ThiqahEth
ኢራን በኳታር እና ኢራቅ የሚገኘውን የአሜሪካ ጦር ሰፈር ደበደበች።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሁለቱም ሀገራት የሚገኙት የጦር ሰፈሮች ላይ ከባድ የሚሳዔል አደጋ ማድረሱን ገልጿል።
ቴህራን አሜሪካ በጦርነቱ የምትሳተፍ ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የጦር ሰፈሮችን እንደምታጠቃ በተደጋጋሚ አስጠንቅቃለች። #aljazeera
@ThiqahEth
#Ethiopia
"አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል" - አገልግሎቱ
የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት፣ "በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር /ግሪድ/ ባጋጠመ ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል" ሲል አስታውቋል።
"የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን እየገለጸን፤ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳውቃለን" ብሏል። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
@ThiqahEth
የኢራን ፓርላማ ዓለም አቀፍ ንግድ የሚካሄድበት ታላቁ የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት ተስማማ።
ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አሜሪካ በፈጸመችው ጥቃት ምክንያት ሰርጡ እንዲዘጋ የህዝብ እንደራሴዎች የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።
የሆርሙዝ ሰርጥ የዓለም አቀፍ ኃይል ንግድ የሚካሄድበት ትልቅ መንገድ ነው።
ይህ ሰርጥ ከተዘጋ የአለም የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል የሚል ስጋት ደቅኗል ተብሏል። #politico
@ThiqahEth
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የረጅም ርቀት ሰጂል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፉን ገለጸ።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ፣ ኢራን ውስጥ በሚሳዔል ማምረቻዎች ላይ 20 ኢላማቸውን የጠበቁ ጥቃቶች መፈጸሙን ገልጿል።
በተያያዘ ፈረንሳይ ከሁለቱም ሀገራት ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ አስታውቃለች። #ynetnews
@ThiqahEth
ህንድ ዜጎቿን ከኢራን ማስወጣቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አስታወቀ።
የህንድ መንግስት "ዘመቻ ሲንዱ" ሲል በጠራው ዘመቻ ከእስራኤል ጋር በጦርነት ላይ ከምትገኘው ኢራን ዜጎቹን አስወጥቷል።
እስካሁን 110 ህንዳውያን ከኢራን መውጣታቸውን የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጧል። #dna
ዜጎቹ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተመለሱት እስራኤልና ኢራን እየተሰናዘሩት ባለው አውዳሚ ጦርነት ባደረባው ስጋት ነው።
@ThiqahEth
"ጦርነቱ በእርግጠኝነት በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" - ዞሃር ፓልቲ
ፐየቀድሞው የሞሳድ ዳይሬክተር"ጦርነቱ በቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" ማለታቸው ተሰምቷል።
የቀድሞው የእስራኤል ኢንተሊጀንስ ሀላፊ ዞሃር ፓልቲ እስራዔል ኢራንን በተመለከተ ምን ልታደርግ እንደምትችል ቀድሞም የታወቀ ነገር ነው ብለዋል።
"ከጠረጴዛ የተሰወረ ምንም ነገር የለም" ያሉት ፓልቲ "ጦርነቱ በእርግጠኝነት በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል" ሲሉ ተናግረዋል። #skynews
ፓልቲ ምንን ተንተርሰው ለዚህ ንግግራቸው እርግጠኛ እንደሆኑ አልታወቀም።
@ThiqahEth
"መጀመሪያ ሩሲያን አሸማግል ቭላድሚ፤ ለዚህኛው በኋላ ትጨነቃለህ ብየዋለሁ" ዶናልድ ትራምፕ
ኢራን እና ሩሲያን ለማወያየት ፑቲን ያቀረቡትን ሀሳብ ትራምፕ በስልክ በነበራቸው ውይይት ተቀብለውት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ውድቅ አድርገውታል።
ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን ላቀረቡት የድርድር ጥያቄ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።
ትናንት አውርተን ነበር ያሉት ትራምፕ፣ "አንድ ነገር አድርግልኝ፣ መጀመሪያ ሩሲያን አሸማግል ቭላድሚር፣ ስለዚህኛው በኋላ ትጨነቃለህ ብየዋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ኢራን ያላቸው ጥልቅ ወታደራዊ ትብብር የሩሲያን ገለልተኝነት ሁኔታ አጠራጣሪ አድርጎታል ተብሏል። #kyivindependent
@ThiqahEth
"የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ አካባቢውን ወደ አውዳሚ ጦርነት ይወስደዋል" - ሩሲያ
ሩሲያ በኢራንና እስራኤል ጦርነት አሜሪካ ከድርጊቷ እንድትቆጠብ አሳሰበች።
የሩሲያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰርጌ ሬያብኮቭ፣ "የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ አካባቢውን ወደአውዳሚ ጦርነት ይወስደዋል" ብለዋል።
ሬያብኮቭ፣ "ሞስኮ ከሁለቱም ከእስራኤል እና ኢራን ጋር ውይይት እያደረገች ትገኛለች" ሲሉ ተናግረዋል። #yemennewsagency
@ThiqahEth
"የተኩስ አቁም ያደረግነው ያለአሜሪካ አሸማጋይነት ነው" - ህንድ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከፓኪስታን ጋር የነበረው ግጭት እንዲቆም አሜሪካ ያደረገችው አስተዋጽኦ የለም ብለዋል።
"ህንድና ፓኪስታን ከአራት ቀናት ውጊያ በኋላ የተኩስ አቁም ያደረጉት በሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ አመራሮች ውይይት እንጅ በአሜሪካ አሸማጋይነት አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ ባለፈው ወር የነበረው ግጭት "ሁለቱ የደቡብ እስያ የኑክሌር ታጣቂ ሀገሮች በአሜሪካ አደራዳሪነት ተኩስ አቁመዋል" ብለው ነበር።
ምንም እንኳን ትራምፕ የሀገራቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ቢገልጹም ሞዲ ግን የሦስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አልነበረም ብለዋል። #asiaone
@ThiqahEth
"ወደፊት በመጥፎ መንገድ ካልሄደ፣ ቲክቶክ አሁን ላይ ጥሩ ቅርጽ ይዟል" - የአሜሪካው ፕሬዚዳንት
ትራምፕ ለቲክቶክ ተጨማሪ 90 ቀናት ፈቀዱ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክ የተሰኘው የተንቀሳቃሽ ምስል መተግበሪያ "ብሔራዊ ደህንነት ስጋት" ነው በሚል የባይደን አስተዳደር ካገደው በኋላ በ24 ሰዓት ውስጥ በመሻር ወደ አገልግሎት መልሰውታል።
"ወደፊት በመጥፎ መንገድ ካልሄደ፣ ቲክቶክ አሁን ላይ ጥሩ ቅርጽ ይዟል" ሲሉ ተናግረዋል።
ባለቤትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሆነው ይህ መተግበሪያ በአሜሪካ እንዲታገድ የተወሰነ ቢሆንም፣ ትራምፕ ግን የተወሰነ ድርሻውን ለአሜሪካ መሸጥ እንዳለበት አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ የቲክቶክ መተግበሪያ እንዳይዘጋ ተመሳሳይ ውሳኔ ሲያሳልፉ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። #nbcnews #thekoreaherald
@ThiqahEth
"አያቶላሕ አሁን መግደል አንፈልግም" - ትራምፕ
"የአያቶላሕ መገደል ጦርነቱን አያባብሰውም" - ኔታንያሁ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ "አሜሪካ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የት እንደተደበቀ ታውቃለች፣ ግን አሁን መግደል አንፈልግም" አሉ።
"በቀላል ኢላማ ውስጥ ነው ያለው፣ ደህና ነው ፣ ግን ይዘን ማምጣት አንፈልግም" ነው ያሉት።
ፕሬዚዳንቱ "ነገር ግን ህፃናት በሚሳዔል እንዲያልቁ፣ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲሞቱ አንፈልግም" ሲሉም አክለዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ሀገራቸው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ ላይ ግድያ የመፈጸም ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል።
"አያቶላሕ ቢገደሉ በቴላቪቭ እና በቴህራን መካከል ያለውን ጦርነት እያባባሰውምሟ እንዲያው ጦርነቱ ቶሎ ይቋጫል" በማለትም ተናግረዋል።
"ወደ ዝርዝር ጉዳዮች መግባት አልፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስቶችን እንደገደልን ግን ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። #aa #gulftoday
@ThiqahEth
"የኢራንን ሰማይ ተቆጣጥረነዋል" - ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ካሁን በፊት በጦርነቱ ተሳትፎ እንደሌላት ሲገልጹ ቢቆዩም "አሁን ላይ የኢራንን ሰማይ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረነው እንገኛለን" ሲሉ ተናግረዋል።
"ከአሜሪካ ውጭ ይህን ማንም አያደርግም" ብለዋል ትራምፕ።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው፣ ትራምፕ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለማስቆም "ተጨማሪ እርምጃ" ሊወስዱ ይችላሉ ብለዋል።
ቫንስ የአሜሪካን ወታደራዊ ጣልቃገብነት በተመለከተ የሰጡት ሀሳብ የለም። #hurriyetdailynews
@ThiqahEth
"እባካችሁን ስምምነቱን አትጣሱት" - ትራምፕ
እስራኤል የትራምፕን የተኩስ አቁም ስምምነት እቅድ መቀቀሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ተናግረዋል።
ኔታንያሁ ደግሞ፣ "ነገር ግን ስምምነቱ የሚጣስ ከሆነ የሀይል እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢራን ለስምምነቱ እውቅና መስጠቷን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ኢራን ለስምምነቱ መተግበር የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በዘገባው ተጠቅሷል።
ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉን በገለጹበት ወቅት ኢራንም ሆነች እስራኤል ግብረ መልስ ከመስጠት ተቆጥበው ቆይተው ነበር።
ትራምፕ "የ12 ቀናቱ ጦርነት መቆም ለአለም ህዝብ ደስታ ነው" ሲሉ ያበሰሩትን የተኩስ አቁም ስምምነት "እባካችሁን ስምምነቱን አትጣሱት" ሲሉ ተማጽነዋል። #dailymail
@ThiqahEth
"እስራኤል ትራምፕ ባቀረቡት እቅድ ትስማማለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባወጡት መግለጫ ሀገራቸው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካኝነት ለቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት መተግበር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
"እስራኤል ትራምፕ ባቀረቡት እቅድ ትስማማለች" ያሉት ኔታንያሁ "ለጥረታቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕን አመሰግናለሁ" ብለዋል። #aljazeera
@ThiqahEth
ኳታር ሙሉ በሙሉ የአየር ክልሏን ዘጋች።
ከኳታር በተጨማሪ ሌሎች አራት ሀገራት ማለትም ኦማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ ኢራቅ እና ኩዌት የአየር ክልላቸውን በከፊል ዘግተዋል ተብሏል።
አሜሪካና እንግሊዝ ዜጎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዲጠለሉ አስጠንቅቀዋል።
ማስጠንቀቂያው የመጣው ኢራን በኳታር የሚገኘውን አል ኡዳይድ ወታደራዊ ስፍራ መደብደቧን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። #aljazeera
@ThiqahEth
# Update
"የተቋረጠው ኃይል መመለስ ጀምሯል" - አገልግሎቱ
"የተቋረጠው ኃይል መመለስ ጀምሯል" ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
"አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በከፊል የተቋረጠው ኃይል በተወሰኑ አካባቢዎች መመለስ ጀምሯል።
በተቀሩት አካባቢዎችም በየደረጃው መልሶ ኃይል የማገናኘት ስራ እየተሰራ በመሆኑ የተቋረጠው ኃይል ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትብቁ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን" ብሏል።
@ThiqahEth
"ዋነኛው የመርከቦች መጓጓዣ መዘጋት የለበትም" - አሜሪካ
አሜሪካ በኢራን ውሳኔ ቻይናን ተማፀነች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ቻይናና ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ከመዝጋት እንዲታስቆማት ጠይቀዋል።
ሩቢዮ "ዋነኛው የመርከቦች መጓጓዣ መዘጋት የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው፣ "የትኛውም መስተጓጎል በአለም ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል" ብለዋል። #bbc
@ThiqahEth
ትራምፕ ሀገራቸው በኢራን በሚገኙ ሦስት የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ "ስኬታማ" ያሉትን ጥቃት መፈጸሟን ገልጸዋል። ይህን ተከትሎ፦
ተመድ፥ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "እያደር እየባሰ የመጣ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን የሚችል የግጭት ስጋት አለ። ይህ ደግሞ ለአካባቢው ለንጹሃንና በአጠቃላይ ለዓለም አስከፊ ነው። ወታደራዊ መፍትሔ አይኖርም፣ ዲፕሎማሲ ብቻ ነው ወደፊት የሚወስደን" ብለዋል።
አውስትራሊያ፦ የአውስትራሊያ መንግስት "የኢራን ኑክሌር እና ባለስቲክ ሚሳዔል ፕሮግራም ለዓለማቀፍ ሰላም ስጋት መሆኑ ግልጽ ነው። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሰላም ጊዜው አሁን ነው ማለታቸውን እንደግፋለን፣ በቀጠናው ያለው ደህንነት የተናጋ በመሆኑ ግጭት እንዲቆም እንጠይቃለን።"
ሜክሲኮ፦ የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ሁለቱ ወገኖች ለውይይትና ለድርድር ዝግጁ መሆን አለባቸው፣ ሰላማዊ ግንኙነትን መገንባት አስፈላጊ መሆናቸውን መግለጽ እንወዳለን።"
ቬንዙዌላ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቫን ጊል፣ "ቬንዙዌላ አሜሪካ በኢራን ላይ የወሰደችውን እርምጃ ታወግዛለች። አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደርስ እንጠይቃለን።" ቦሊቪያ፦ ቦሊቪያ የአሜሪካን ጥቃት ካወገዙት ሀገራት ተርታ ተመድባለች። "በናንታዝ፣ ኢስፋሀንና ፎርዶው የተፈጸመው ጥቃት አግባብ አይደለም።"
ኩባ፦ የኩባ ፕሬዝዳንት ሚጉዌል ዲያዝ ጥቃቱን ተቃውመዋል። "አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ጣቢያ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን። እርምጃው በመካከለኛው ምስራቅ አደጋ የደቀነ ነው፣ የተመድን ቻርተርና አለማቀፍ ህግ የጣሰ ነው።"
ኒውዝላንድ፦ "ቀጣይነት ያላቸው ወታደራዊ እርምጃዎች አስጊ ናቸው፣ ሌላ ውጥረት ማስወገድ የተሻለ ነው። ለዚህ ደግሞ ገንቢ ውይይቶች የሚካሄዱበት ዲፕሎማሲ ወሳኝ ነው።"
ሲሉ የዓለም ሀገራት ተናግረዋል።
@ThiqahEth
ኢራን ከደቂቃዎች በፊት ወደ እስራኤል ሀይፐርሶኒክ ሚሳዔል አስወነጨፈች።
ሚሳዔሉን የተጠቀመችው በአዲስ የጥቃት ዘመቻ እንደሆነ ተገልጿል።
የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት ስድስተኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሁለቱም ወገን በከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታገዙ እርምጃዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። #irannationaltelevision
@ThiqahEth
"ኢራን ስህተት ሰራች" - ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ ለአያቶላህ ኮሚኒ አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል።
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኮሚኒ ከሰዓታት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው "ኢራን እጅ አትሰጥም" ካሉ በኋላ አሜሪካ በጦርነቱ ከተሳተፈች "የማይጠገን ውድመት ይደርሳል" ብለው ነበር።
ትራምፕ ለኮሚኒ ንግግር "መልካም እድል ብያለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
"60 ቀን ነበራቸው ስህተት ሰርተዋል" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። #timesofindia
@ThiqahEth
ውድ እና የምናከብራችሁ ቤተሰቦቻችን አላስፈላጊ፣ ጸብ አጫሪ ንግግሮች እየተበራከቱ በመሆናቸው የአስተያየት መስጫውን ለጊዜው መዝጋታችንን በአክብሮት አሳወቅን።
@ThiqahEthFamily ይቅርታ🙏
"የእስራኤል ጥቃት በኢራን ሳትቀደም በፊት ቀድሞ የተሰነዘረ እንጂ ኢራንን ማጥፋትን ታሳቢ ያደረገ አይደለም" - በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር
"የጦርነቱ ዓላማ ኢራንን ማጥፋት ሳይሆን እስራኤልን ማዳን ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሤ (ዶ/ር) ትላንት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ?
በተደጋጋሚ "ኢራን የኒኩሊየርና የባለስቲክ ሚሳኤሎች ባለቤት ልትሆን አይገባም። እስራኤል ወደ አውዳሚ ጦርነቱ የገባቸው የህልውና አደጋ ስለተጋረጠባት ነው።
ጦርነቱ ከመፈንዳቱ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል 60 ቀናትን የፈጀ ድርድር ተካሂዷል። ኢራን በድርድሩ ወቅት ሳይቀር እስራኤልን የማጥፋት እቅዷን ለማሳካት እንቅስቃሴ ውስጥ ነበረች።
እስራኤል ራሷን ከመጥፋት ለመታደግ የገባችበት ጦርነት ፍትሃዊ ነው፤ የእስራኤል ጥቃት በኢራን ሳትቀደም ቀድሞ የተሰነዘረ እንጂ ኢራንን ማጥፋትን ታሳቢ ያደረገ አይደለም።
ኢራን እስራኤልን ብቻ ሳይሆን መላው አውሮፓን ሊያወድም የሚችል የኒኩሊየር መሳሪያ ዝግጅት ላይ ነበረች። ኢራን አላማዋ እስራሴልን ማጥፋት እንደሆነ በግልጽ እና በተደጋጋሚ አሳውቃለች። ይህም ከንግግር አልፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ የእስራኤል መንግስት ዜጎቹን ከጥፋት የማዳን ኃላፊነቱን ለመወጣት ወደዚህ ጦርነት ለመግባት ተገዷል" ብለዋል።
ኢራን እስራኤልን ማጥፋት የፈለገችበት ምክንያት ምንድን ነው?" የሚለውን ጥያቄ፤ “ኢራን የኒኩሊየር ባለቤት መሆን የፈለገችው እስራኤልን ለማጥፋት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የድንበር ግጭት የለንም፡፡ ከ2 ሺሕ ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ከሚገኝ ርቀት ተነስተው ከ10 ሚልዮን የሚበልጡ ዜጎችን ከታሪካዊ ቦታቸው ማጥፋት የፈለጉበት ምክንያት ግልጽ አይደለም” ሲሉ መልሰዋል።
#AhaduRadio
(ኢራን መግለጫ ከሰጠች የምናቀርብ ይሆናል)
@ThiqahEth
"የአሜሪካ ጥቃት የማይጠገን ውጤት ያስከትላል። ኢራን እጇን አትሰጥም" - አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ከተጀመረ በኋላ የመጀመሪያ ንግግር አድርገዋል።
በብሔራዊ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈው ንግግራቸው፣ "ኢራን የአየር ክልሏ እየተጣሰ ዝምታን የምትመርጥበት ምክንያት የለም፣ ወታደራዊ ጣልቃገብነትንም በቸልታ አታልፈውም" ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እጃቸውን እንዲሰጡ ባስተላለፉት መልዕክት ዙሪያ፣ "ሀገራችን በደማቸው ዋጋ የከፈሉ ሰማዕታትን አታረክስም፣ ኢራን እጇን አትሰጥም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ለአሜሪካ ባስተላለፉት የማስጠንቀቂያ መልዕክት፣ "የአሜሪካ ጥቃት የማይጠገን ውጤት ያስከትላል" ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚኒ፣ "በግድ የሚደረግ ጦርነትንም ሆነ በግድ የሚመጣ ሰላም አንፈልግም" ብለዋል። #outlookindia #telegraph
@ThiqahEth
የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት ለስድስተኛ ተከታታይ ቀናት ቀጥሏል።
ሁለቱም ሀገራት አንዱ በአንዱ ላይ ሚሳዔል አስወንጭፈዋል።
ሀገራቱ በጥቃታቸው ወታደራዊ ስፍራዎችን እና የኑክሌር ጣቢያዎችን ኢላማ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።#gulftoday
@ThiqahEth
"አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን ኢራንን ለማጥቃት ከተጠቀሙበት ከአካባቢው እናጠፋቸዋለን" - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
ኢራን በመካከላቸው ምስራቅ የሚገኙትን የአሜሪካን ወታደራዊ ሰፈሮች ልታጠቃ እንደምትችል አስጠነቀቀች።
ቴህራን ፕሬዝዳንት ትራምፕ አያቶላህ ኮሚኒን በተመለከተ ያወጡትን ማስጠንቀቂያ አውግዛለች።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሌሊቱን ባወጣው መግለጫ፣ "አሜሪካና ምዕራባውያን ቀጠናዊ ቦታዎቻቸውን ኢራንን ለማጥቃት ከተጠቀሙበት ከአካባቢው እናጠፋቸዋለን" ብሏል።
"እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ውጤታቸው ለሌሎች የአካባቢው ሀገራተት አስከፊ ነው" ሲል አስታውቋል። #khaamapress
@ThiqahEth
ኢራን የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባት ባለስልጣናቱ ማረጋገጣቸው ተነገረ።
የእስራኤል ደጋፊ ናቸው የተባሉ የበይነመረብ ጠላፊዎች በኢራን የሰፓህ ባንክ ላይ የሳይበር ጥቃት ፈጽመዋል ተብሏል።
የሰፓህ ባንክ ለኢራን ብሄራዊ ዘብ እና ለኑክሌር ፕሮግራሞች ቀጥተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ባንክ መሆኑ ተገልጿል።
በሳይበር ጥቃቱ የኤቲኤም አገልግሎቶች መቋሰጣቸው፣ የነዳጅ ማደያዎች ተስተጓጎላቸው፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው ተነግሯል።
ጥቃቱ መፈጸሙን የኢራን ባለስልጣናትም አረጋግጠዋል። #ynetnews
@ThiqahEth
"ለሩሲያ ተጨማሪ 6000 ወታደሮችን ለመላክ ፍላጎት አለን" - ሰሜን ኮሪያ
የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ለሩሲያ ተጨማሪ 6000 ወታደሮችን የመላክ ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል።
ፕሬዚደንቱ ይህን ያሳወቁት በፕዮንግያንግ ከሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ኃላፊ ሰርጌ ሾይጉ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።
ሰርጌ ሾይጉ በበኩላቸው በጦርነቱ ለተሳተፉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ክብር ለመስጠት እያሰበች እንደሆነ ገልጸዋል።
ወደ ሩሲያ ይላካሉ የተባሉት ወታደሮች በዩክሬን ኃይሎች የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያግዙ ናቸው ተብሏል። #joins
@ThiqagEth