15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኔታንያሁን የፍርድ ቤት ቀጠሮ አራዘመ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተራዘመው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኔታንያሁ ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው።
ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ባይገለፅም በዚህ ሳምንት ይዞት የነበረውን ክስ የማድመጥ ቀጠሮ ላልታወቀ ጊዜ ማራዘሙ ተሰምቷል።
አሁንም ቢሆን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በአሜሪካ ጫና የመጣ ነው ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለበርካታ አመታት የቆየ የሙስና ክስ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። #france24
@ThiqahEth
የ80 ዓመቱ ሙሴቪኒ ለ6ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ።
የኡጋንዳው የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ በቀጣይ አመት በሚካሄደው የሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።
የ80 አመቱ ሙሴቪኒ በዓለማችን ረጅም አመት በስልጣን የቆዩ መሪ ሲሆኑ፣ ፓርቲያቸው ናሽናል ረዚስታንስ ሞመንት (NRM) ከ1986 ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል። #aa
@ThiqahEth
"ህንድ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱን አቀናብራለች" - ፓኪስታን
"ይህ መግለጫ ውድቅ መደረግ ነው የሚገባው፣ አንቀበለውም" - ህንድ
ህንድ፣ "የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱን አቀናብራለች" በሚል ከፓኪስታን የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች።
የፓኪስታን ወታደሮችን በጫነ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ13 ወታደሮች ህይወት አልፏል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር "የፓኪስታንን የውስጥ ሰላም ለማናጋት የሚደረግ ሙከራ ዋጋ ያስከፍላል" ብለዋል።
የፓኪስታን ጦር ከክስተቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የህንድ እጅ እንዳለበት ገልጿል።
ጦሩ፣ "ህንድ በዋዚሪስታን የተፈጸመውን የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት አቀናብራለች" ሲል ህንድን ተጠያቂ አድርጓል። ኒው ደልሂ በበኩሏ፣ ከኢስላማባድ የቀረበባትን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "ይህ መግለጫ ውድቅ መደረግ ነው የሚገባው፣ አንቀበለውም" ብሏል። #scroll
ወደ 13 ፓሊሶች በአጥፍቶ ጠፊ መገደላቸውን፣ 14 ንጹሐን መጎዳታቸውን ፓኪስታን ማሳወቋ ይታወሳል።
@ThiqahEth
"የዓለም ስርዓትን ትቀበላለህ አልያ የሚመጣብህን ትቀበላለህ" - ትራምፕ ለአያቶላሕ ኮሚኒ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራንን በድጋሚ አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንቱ "'ኢራን ጦርነቱን አሸንፋለች' የሚባለው ውሸት ነው" ሲሉ አጣጥለዋል።
ትራምፕ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ የሚገኙበትን እንደሚያውቁ የተናገሩ ሲሆን፣ "እርምጃ የመውሰድ ፍላጎት" ግን እንደሌላቸው ገልፀዋል።
"እስራኤልም ሆነች የአሜሪካ ጦር የእሱን ህይወት ሊያጠፉ ስለሚችሉ አልነገራቸውም" ብለዋል።
ይሁን እንጂ፣ "ኢራን ወደ ዓለም ስርዓት መመለስ አለባት አልያ፣ ነገሩ ለእነሱ አስከፊ ይሆናሉ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ትራምፕ ለአያቶላሕ ኮሚኒ ባስተላለፉት መልዕክት "የአለም ስርዓትን ትቀበላለህ አልያ የሚመጣብህን ትቀበላለህ" በማለት አስጠንቅቀዋል።#thefinancialexpress
@ThiqahEth
"ካናዳ ለአሜሪካ ገበያ መክፈል ያለባትን ገንዘብ በሰባት ቀን ውስጥ እናሳውቃታለን" - ዶናልድ ትራምፕ
ትራምፕ ከካናዳ ጋር የሚደረገው የንግድ ውይይት ቁሟል አሉ።
ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ካናዳ በአሜሪካ አርሶ አደሮች ላይ ለአመታት 400% ቀረጥ በማስከፈል የእንስሳት ተዋፅዖ ገበያን ጎድታብናለች ብለዋል።
"በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ድጅታል ታሪፍ ጀምራለች" ያሉት ትራምፕ "ይህ በሀገራችን ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው" ሲሉ ኮንነዋል።
"በግልጽ ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ያለውን የአውሮፓ ህብረትን ፈለግ እየተከተለች ነው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
በዚህ "የተጋነነ" ሲሉ በገለጹት ታሪፍ የተነሳ ሁለቱ ሀገራት የንግድ ድርድር ማድረግ እንዳቆሙ ገልጸዋል።
"ካናዳ ለንግድ ግንኙነት ከባድ ሀገር ናት" ያሉት ፕሬዚደንቱ "ታሪፉ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ንግግሩ የቆመው" ብለዋል።
"ካናዳ ለአሜሪካ ገበያ መክፈል ያለባትን ገንዘብ በሰባት ቀን ውስጥ እናሳውቃታለን" ሲሉ አስፍረዋል። #truthsocial #pbsnews
@ThiqahEth
ትራምፕ "ለኢራን 30 ቢሊየን ዶላር ሊሰጡ ነው" ተባለ፡፡
ገንዘቡ ለኃይል ምንጭነት ብቻ የሚውል የኑክሌር ፕሮግራም (CEPNP) ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወደ ድርድር ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆነች ከድጋፉ በተጨማሪ ማዕቀቦችን ለማንሳትና የታገደባትን በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አራት ሰዎች ተናግረዋል፡፡
ውሳኔው ዙሪያ ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የትራምፕ መንግስት ከኢራን መንግስት ጋር ቀጥተኛ ውይይት መጀመሩን ምንጮቹ አብራርተዋል፡፡
ኢራን እስካሁን ድረስ ስለጉዳዩ የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡ #msn
@ThiqahEth
የአውሮፓ ህብረት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀ፡፡
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መሪዎቹ አክለው፣ ታጋጆች እንዲለቀቁ እና እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲቆም አሳስበዋል። #eureporter
@ThiqahEth
"በኢራን ኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረስን አንቀበለውም" - ፓኪስታን
"ኢራን ፈጽሞ ኑክሌር ሊኖራት አይችልም" - አሜሪካ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ አሜሪካ ኢራን ላይ የፈጸመችውን የቦምብ ጥቃት አውግዘዋል።
ሸሪፍ "በኢራን ኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረስን አንቀበለውም፣ ተገቢነት የሌለው እርምጃ ነው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመድን መተዳደሪያ ደንብ በመጥቀስ ኢራን ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት አብራርተዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ በበኩላቸው፣ "ለኢራን የኑክሌር ፕሮግራም እውቅና መስጠት አስፈላጊ አይደለም" ማለታቸው ተገልጿል።
"ኢራን ፈጽሞ ኑክሌር ሊኖራት አይችልም" ያሉት ሩቢዮ፣ "በጭራሽ ኑክሌር ማበልጸግ አይገባትም" ብለዋል።
ሁለቱ ባለስልጣናት በነበራቸው የስልክ ውይይት በእስራኤል እና ኢራን መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት አብሮ መስራት ጠቃሚ መሆኑን ተወያይተዋል ተብሏል። #thetimesofindia
@ThiqahEth
"ኢራን አሁንም ጥቃት ከተፈጸመባት የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ አትቆጠብም" - ኢራን
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ኮሚኒ የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሁለት ቀን በኋላ የመጀመሪያ ንግግር አድርገዋል።
በዚህ ህዝባዊ ንግግራቸው ስለ ጦርነቱና የተፈጸመው የተኩስ አቁም ተናግረዋል።
ካሚኒ፣ "ኢራን በእስራኤል ላይ ትልቅ ድል ተቀዳጅታለች፣ ለዚህም የታላቋን ኢራንን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
"ኢራን አሁንም ጥቃት ከተፈጸመባት የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ አትቆጠብም" ብለዋል መሪው።
አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በተመለከተ፣ "ትራምፕ የተፈጸመውን ጥቃት አጋነውታል ግን ቀላል ነው" ብለውታል።
"ኢራን በጭራሽ እጅ እንደማትሰጥ መታወቅ አለበት" ሲሉ አክለዋል። #ifpnews
@ThiqahEth
ሀንጋሪ ምን እያለች ነው?
"ዩክራንን የህብረቱ አባል ካደረግን ጦርነቱን እንቀላቀላለን ማለት ነው" - ሀንጋሪ
ሀንጋሪ፥ የዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባልነት በመቃወም፣ "ዩክሬንን አባል ማድረግ ለአውሮፓ ህብረት ተጨማሪ ስጋትን ይፈጥራል" ማለቷ ተሰምቷል።
የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን "ዩክሬንን አባል ማድረግ ጦርነትን ማባባስ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በአውሮፓ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ኦርባን "ለአውሮፓ ህብረት ተጨማሪ ስጋትን ይፈጥራል" በማለት ሂደቱን ተቃውመዋል።
"95 በመቶ የሚሆኑት የሀንጋሪ ዜጎች ዩክሬን ወደ አውሮፓ ህብረት እንድትገባ አይፈልጉም" ነው ያሉት ኦርባን።
"ችግሩ ጦርነቱ ነው" ብለው፣ "ዩክሬንን የህብረቱ አባል ካደረግን ጦርነቱን እንቀላቀላለን ማለት ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደሆነ ግን በግልጽ አላብራሩም። #anadoluagency
@ThiqahEth
"ሀገር ሊኖረን ይገባል" - ፕሬዝዳንት ሩቶ
በኬንያ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 8 ሰዎች ተገደሉ።
ኬንያውያን ፖሊስን በህብረተሰቡ ላይ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
በናይሮቢ እየተካሄደ ባለው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊስ አሁንም ጥይት በመተኮስና አስለቃሽ ጭስ በመልቀቅ ተቃውሞውን ለመግታት ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ የተቃውሞ ሰልፉ ሰላማዊ እንዲሆን ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለው፣ "ሀገር ሊኖረን ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። #tukonews
@ThiqahEth
"መንግስት ይህን ህግ በመተግበር ከአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚደረገውን ትብብር ሙሉ በሙሉ ማቆም አለበት" - የኢራን ፓርላማ
የኢራን ፓርላማ የኑክሌር ትብብርን የሚያስቆም አዋጅ አጸደቀ።
ረቂቅ አዋጁ ኢራን ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ጋር የነበራትን ግንኙነት የሚያቋርጥና የኑክሌር ቁጥጥርን የሚያስቀር መሆኑ ተገልጿል።
ረቂቁ፣ "የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክን የኑክሌር ጣቢያዎችሳይንቲስቶች በመጠበቅ የዩራኒየም ምርትን በማሳደግ፣ የሀገር ሉዓላዊነት የግዛት አንድነት ማስከበር" በሚል የተዘጋጀ ነው።
የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ "መንግስት ይህን ህግ በመተግበር ከአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚደረገውን ትብብር ሙሉ በሙሉ ማቆም አለበት" የሚል ሀሳብ አካቷል።
ይህ አዋጅ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ውሳኔ ካገኘ በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የፓርላማው ውሳኔ ወደፊት ኢራንና እስራኤል ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጽዕኖ እንደሚኖረው እየተገለጸ ይገኛል።
ፓርላማው ከቀናት በፊት የዓለማችን ትልቁ የኃይል መተላለፊያ የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ ተመሳሳይ ውሳኔ አሳልፏል። #financialtimes
@ThiqahEth
25 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ።
የእስራኤል ጦር በከፈተው ተኩስ ከ100 የሚበልጡት ቆስለው ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በጋዛና ክሃን የኑስ ከተማ መሆኑን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።#aa
@ThiqahEth
ኢራናውያን "ድል አድርገናል" በማለት አደባባይ ወጡ።
ዜጎች "ኢራን እስራኤልን አሸንፋለች" ብለው በማሰብ በቴህራን አደባባይ የድል መፈክሮችን አሰምተዋል።
ኢራናውያኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ኢራን ጦርነቱን መቋቋም በመቻሏ የመጣ ውጤት እንደሆነ ገልፀዋል።
ኢራን ሳትሸነፍ የተቃጣባትን ጦርነት እንዲትመክት አድርገዋል ያሏቸውን የሀገሪቱን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ኮሚኒን ስም እየጠሩ አወድሰዋል።#almonitor
@ThiqahEth
ኢራን በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሷን እስራኤል አስታወቀች።
ቴህራን የረጂም ርቀት ሚሳዔል በመጠቀም በቤርሳቤህ ከተማጥቃት ማድረሷን የእስራኤል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳትና ውድመት አስከትሏል ተብሏል።
የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው መላካቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። #middleeastmonitor
@ThiqahEth
"በጣም ከባድ የአየር ጥቃት ተፈፅሞብናል" - ዩክሬን
ሩሲያ ከጦርነቱ መጀመር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የተባለውን የአየር ጥቃት ፈፀመች።
ሞስኮ፣ "በጣም ከባድ የአየር ጥቃት" በተባለው በዚህ ጥቃቷ በድምሩ "537 የአየር ላይ ጥቃቶችን ፈፅማለች" ተብሏል።
ከእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ 477 የሚሆኑት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መሆናቸው ተገልጿል።
የዩክሬን ጦር ከተቃጡት ጥቃቶች "249 የሚሆኑትን አክሽፊያለሁ" ብሏል።
ሩሲያ ፈፀመች ስለተባለው ጥቃት የሰጠችው ማብራሪያ የለም። #cbsnews
@ThiqahEth
"ኢራን በ12 ቀኑ ጦርነት የተወሰኑ የኑክሌር ማብላያ ቁሳቁሶች ወድመውባታል" - ዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ
"ኢራን የዩራኒየም ምርትን በወራት ውስጥ ልትመልስ ትችላለች" - ተመድ
ኢራን በእስራኤል እና አሜሪካ ከደረሰባት ጥቃት በኋላ በቅርቡ በአዲስ መልኩ ዩራኒየም የማምረት ስራ እንደምትጀምር የተመድ ኑክሌር ተቆጣጣሪ ቡድን አስታውቋል።
ቡድኑ አክሎ፣ "ኢራን የዩራኒየም ምርትን በወራት ውስጥ ልትመልስ ትችላለች" ሲል ገልጿል።
የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፋይል ግሮሲ ደግሞ፣ "ኢራን በ12 ቀኑ ጦርነት የተወሰኑ የኑክሌር ማብላያ ቁሳቁሶች ወድመውባታል" ብለዋል። #france24
@ThiqahEth
በፓኪስታን 13 ፓሊሶች ሲገደሉ 14 ንጹሐን መጎዳታቸው ተገለጸ።
በዚህም ወደ 13 የሚሆኑ ፖሊሶች በአጥፍቶ ጠፊ መገደላቸው ነው የተሰማው።
በሰሜን ዋዚሪስታን በደረሰው ክስተት 14 ንጹሐን ዜጎች ተጎድተዋል ተብሏል።
አጥፍቶ ጠፊው በፖሊስ ተሽከርካሪ ላይ ቦምብ በመጣላቸው ነው አደጋው የደረሰው። #telegraph
@ThiqahEth
በኮሎምቢያ 22 ሰዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
በቤሎ እና አልቶስ ግዛቶች በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ 8 ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የመሬት መንሸራተት አደጋው በከባድ ዝናብ ምክንያት መከሰቱ ተገልጿል። #aa
@ThiqahEth
ሩዋንዳ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሰላም ስምምነት ፈጸሙ።
ሁለቱ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን ህይወት የቀጠፈው ጦርነት እንዲቆም በአሜሪካ፣ ኳታርና የአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት የስምምነት ፊርማው በዋሽንግተን ተካሂዷል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርክ ሩቢዮ፣ ከሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቨር ንዱንግሬና የኮንጎሌስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴሬስ ካይክዋምባ ባደረጉት ውይይት ስምምነቱ እንዲፈጸም አድርገዋል። #channelstelevision
@ThiqahEth
ጃፓን 9 ሰዎችን የገደለውን ግለሰብ በሞት ፍርድ ቀጣች።
በቅጽል ስሙ ትዊተር ኪለር በመባል የሚጠራው ግለሰብ በደቡብ ቶኪዮ አፓርትመንት በሚኖሩ ሰዎችን "በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ፈጽሟል" ተብሏል።
ይሄው አካልም በሞት ቅጣት እንደተቀጣ ተነግሯል።
የ34 አመቱ ግለሰብ "ወንጀሉን የፈጸመው" ከ8 አመት በፊት በ2017 እንደነበር ተገልጿል።#upi
@ThiqahEth
አሜሪካ በሱዳን ጦር መሪ አልቡርሃንና ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ መሪ ዳጋሎ ላይ ማዕቀብ ጣለች።
ዋሽንግተን በንጹሃን ዜጎች ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅመዋል በሚል በሁለቱም የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ተገልጿል።
ሁለቱም አመራሮች የአለማቀፍ ህግን በግልጽ ጥሰዋል ብላ እንደምታምን ስማቸው ያልተገለፀ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል።
ማዕቀቡ በጦርነቱ የሚሳተፉ ወገኖች የጦር መሳሪያ ግዥ እንዳያደርጉ ክልከላ ይጥላል ተብሏል።
ማዕቀቡ ከዛሬ አርብ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ባለስልጣኑ ተናግረዋል። #shafaqnews
@ThiqahEth
#Update
በኬንያው ተቃውሞ ከ300 የሚበልጡ ዜጎች መጎዳታቸው ተገለጸ።
ከተጎጂዎች መካከል 67 የሚሆኑት በተኩስ ተመትተው በጀሞ ኬንያታ ሆስፒታል ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።
እስካሁን ድረስ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኬንያ ቢሮ አስታውቋል።
ተቃውሞው 20 በሚደርሱ ከተሞች ተስፋፍቷል ተብሏል።
ፖሊስና ልዩ ኃይሎች ተቃውሞውን ለማብረድ አስለቃሽ ጭስና ውሃን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ተዘግቧል።
የተቃውሞ ሰልፉ ባለፈው አመት በግብር ጭማሪ ቅሬታ የተጀመረውና ፕሬዝዳንት ሩቶ ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቀው ዘመቻ አካል ነው ተብሏል።#akipress
@ThiqahEth
"ኔታንያሁን የምትጠብቁበት ጊዜ ላይ ናችሁ" - ትራምፕ።
ትራምፕ የኔታንያሁ የሙስና ክስ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ፣ "አሜሪካ በኢራን ጦርነት ከእስራኤል በኩል ጣልቃ የገባችው በእሱ ምክንያት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ኔታንያሁ በእስራዔልና ኢራን ጦርነት ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል" ያሉት ዶናልድ ትራምፕ "ኔታንያሁን የምትጠብቁበት ጊዜ ላይ ናችሁ" ብለዋል።
የትራምፕ ንግግር በእስራኤል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በገንዘብ ማጭበርበርና እምነት ማጉደል ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2020 የጀመረው የፍርድ ሂደታቸውን እንደማይቀበሉት ቢገልጹም እስካሁን ድረስ መቋጫ አላገኘም። #bbc
@ThiqahEth
"የተፈጠረው ድርጊት በጣም አሳዛኝ ነው" ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሸንባውም
በሜክሲኮ ድንገት በተከፈተ ተኩስ 12 ሰዎች ሲሞቱ 20 የሚደርሱት ቆሰሉ።
ተኩሱ የተከፈተው በጉዋንጃቶ ከተማ ሀይማኖታዊ በዓል ላይ ለመታደም በተገኙ ዜጎች ላይ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ፖሊስ ጥቃት አድራሹ አካል ለጊዜው በመሰወሩ በፖሊስ አለመያዙን አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሸንባውም "የተፈጠረው ድርጊት በጣም አሳዛኝ ነው" ሲሉ የደረሰውን ድርጊት አውግዘዋል።
ሸንባውም አክለው፣ "ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ በሂደት ላይ ነው" ብለዋል። #theweek
@ThiqahEth
በጋዛ የሟቾች ቁጥር 84,000 መድረሱን ሪፓርት ከመላከተ።
ይህ አሀዝ የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ካወጣው 45,650 በ40% እንደሚበልጥ ተገልጿል።
የጋዛ የሞት ዳሰሳ (Gaza Mortality Survey) በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የደረሰውን ጉዳት ይፋ አድርጓል።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ኦክቶበር 7/2023 እስከ ጃንዋሪ 2025 ድረስ ብቻ 75,000 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን አንድ ሪፖርት አመላክቷል።
በግፍ ከተገደሉት ውስጥ 56.2 % እናቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ከጦርነቱ በኋላ ከተወለዱ 357 ህፃናት አራቱ እንደሚሞቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
8,540 የሚሆኑት ከጦርነት ውጭ በተከሰተ (nonviolent) ሞት ነው ህይወታቸው ያለፈው።
ምክንያቶቹም ረሃብ፣ ህመም፣ የጤና አገልግሎት እጥረት እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በዚህ ጥናት ከሰባት ዩኒቨርሲቲና ተቋማት የተውጣጣ አለማቀፍ የምሁራን ቡድን ተሳትፎ አድርጓል።
ቡድኑ የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በየጊዜው የሚያወጣው ሪፖርት የተጋነነ አለመሆኑን አረጋግጧል።
ቡድኑ በጋዛ የሚኖሩ 2000 ፍልስጤማውያንን የፊት ለፊት ቃለመጠይቅ አድርጓል ተብሏል።
ዳታው ከታህሳስ 30/2024 - ጥር 5/2025 ባለው ጊዜ ነው የተካሄደው። #middleeastmonitor
@ThiqahEth
አንድ ባለስልጣንና 6 የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ተገደሉ።
ወታደሮቹ የተገደሉት በደቡብ ጋዛ የካህን የኑስ ከተማ በግዳጅ ላይ እያሉ መሆናቸውን የእስራኤል ጦር ገልጿል።
ጦሩ የተገደሉበት አባላቱ የ605ኛ ተዋጊ ባታሊዮን ስር እያገለገሉ እንደነበር አስታውቋል። #anadoluagency
@ThiqahEth
ኢራን ለእስራኤል ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን ሦስት ሰዎች በስቅላት ቀጣች።
ቴህራን ሌሎች 700 ሰዎችን በዚሁ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው በማለት በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገልጿል።
ኢራን ይህን እርምጃ የወሰደችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ነው። #indiatoday
@ThiqahEth
እስራኤል የኢራንን የራዳር ሳይት ኑክሌር ጣቢያ መደብደቧን አስታወቀች።
ቴላቪቭ ለተቃጣባት ጥቃት በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ቴህራን አጠገብ ከባድ ድብደባ መፈጸሟን የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጽ/ቤት አረጋግጧል።
በአካባቢው ሁለት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የዓይን እማኞችም ተናግረዋል።
በዚህም ከጥቃቱ በኋላ ትራምፕና ኔታንያሁ በስልክ መወያየታቸውን የገለጸው ፅ/ቤቱ፣ እስራኤል ካሁን በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ ከመውሰድ እንደምትቆጠብ አስታውቋል። #malayalamanorama
@ThiqahEth
"ሁለቱም እስራኤል እና ኢራን ስምምነቱን ጥሰዋል" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እስራኤልና ኢራንን "ያደረጉትን አያውቁም" ሲሉ በብስጭት ተናግረዋል።
ትራምፕ አክለው፣ እስራኤልን "ተረጋጊ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ስምምነቱ ተጥሷል ከማለት ውጭ በምን መልኩ እንደተጣሰ አልተናገሩም። #anadoluagency
@ThiqahEth