thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

የጋና የጦር አውሮፕላን በአሻንቲ ግዛት ተከሰከሰ።

ንብረትነቱ የጋና አየር ኃይል የሆነ Z9 ሄሊኮፕተር በረራ ላይ እያለ ከራዳር መሰወሩን አየር ሀይሉ ገልጿል።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ በድምሩ 8 ሰዎች ነበሩ ተብሏል።#legit

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ተጠያቂነት ይስፈን" - ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ኤጀንሲ በባህር ላይ በሚጓዙ ስደተኞች ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች ተጠያቂነት እንዲኖር ጠየቀ።

ድርጅቱ፣ "ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው" በተባሉበት ከቅርብ ጊዜው አደጋ በኋላ ማስጠንቀቂያ አዘል ስጋቱን ገልጿል።

በዚህም "እያንዳንዱ የሚጠፋው ህይወት የህገወጥ ስደት የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው" ብሏል።

ተመድ በመሆኑም "በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ተጠያቂነት ይስፈን" ሲል ጠይቋል።

የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ በየመን 154 ኢትዮጵያውያንን ይዛ በተገለበጠችው ጀልባ 56 ሰዎች መሞታቸውን እና 132 አለመገኘታቸውን አስታውቋል።  #thenational

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ከሰነድ ማስረጃዎች ጋር 5000፣ 10,000 ወይም 15,000 ዶላር ገቢ ደረሰኝ ያስፈልጋል" - ቢሮው

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ቪዛን በተመለከተ አዲስ መመሪያ ይፋ አደረድርጓል።

ቢሮው አዲስ ባስተዋወቀው አሰራር መሰረት የአሜሪካ ቪዛ የሚያመለክት ሰው እስከ 15,000 ዶላር በካሽ ተቀማጭ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስቧል።

አሰራሩ "የብዙዎችን አቅም ያላገናዘበ ነው" የሚል ትችት አስከትሏል።

ቢሮው አዲሱን የቪዛ ፕሮግራም አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ "ከሰነድ ማስረጃዎች ጋር 5000፣ 10,000 ወይም 15,000 ዶላር ገቢ ደረሰኝ ያስፈልጋል" ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ካሁን በፊት ያልነበረውን አሰራር "ቪዛ ለማሳደስ በኤምባሲ በኩል ቃለመጠይቅ ማድረግ ያስፈልጋል" ሲል አሳስቧል።

አሰራሩ ሁሉንም ሀገራት እንደማይመለከት የገለጸው ቢሮው፣ "የሚመለከታቸው ሀገራት ዝርዝር ውሳኔው ተግባራዊ ሲደረግ ይፋ ይደረጋል" ሲል ገልጿል።

ይህ ፕሮግራም ለ90 ቀናት የሚቆይ የቱሪዝም ወይም ቢዝነስ ቪዛ ያላቸውን ሀገራት አይመለከትም የተባለ ሲሆን፣ በዚህ ፕሮግራም በብዛት የአውሮፓ፣ እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ተካተውበታል ተብሏል።
#npr

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ልዩ መልዕክተኛው "የመጨረሻ እድል" ያሉትን ለመሞከር ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው ተባለ።

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በዩክሬን ጦርነት የተኩስ አቁም ጉዳይ ለመምከር ወደ ሞስኮ ይጓዛሉ ተብሏል።

ልዩ መልዕክተኛው በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ወይም ሐሙስ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል በዩክሬን "የሰዎች ሞት የሚያበቃበት የተኩስ አቁም ያስፈልጋል" ብለዋል።

ላለፉት ስድስት ወራት ያደረጉት የሰላም ጥረት ባለመሳካቱ ለሩሲያ በመጀመሪያ የ50 ቀናት በመቀጠል የ10 ቀናት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። #abcnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለፕሬዚዳንት ፑቲን የማያቋርጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል" - አሜሪካ

ህንድ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የ25% ታሪፍ ቢጣልባትም ከሩሲያ ነዳጅ መግዛቷን አላቆመችም ተብሏል።

ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የዋይትሃውስ ባለስልጣን "ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለፕሬዚዳንት ፑቲን የማያቋርጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል" ሲሉ ወቅሰዋል።

"የሞዲ መንግስት የነዳጅ ኩባንያዎች ከሩሲያ ነዳጅ እንዳያስገቡ መከልከል ቢችልም ግዥ እንዲቆም የተላለፈ ውሳኔ የለም" ብለዋል ባለስልጣኑ።

እኚሁ ስማቸው ያልተጠቀሰው ከፍተኛ ባለሥልጣን የነዳጅ ግብይት አለመቆሙን ፣"ህንድ በዩክሬን ጦርነት ለሩሲያ ድጋፍ እያደረገች ነው" በማለት ገልጿል። 

በዚህ እርምጃ አሜሪካ ደስተኛ አለመሆኗንም ጠቁመዋል። #thejapantimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ፍልስጤምን ልቀቁ፣ የዘር ማጥፋት ይቁም" - ሰልፈኞች

በሲድኒ ከ100,000 በላይ ዜጎች እስራኤልን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ።

በአውስትራሊያ በሀርቡር ድልድይ በጦርነት ውስጥ የሚገኙትን ፍልስጤማዊያን በመደገፍና የእስራኤልን እርምጃ በማውገዝ የአደባባይ ሰልፍ ተካሂዷል ተብሏል።

ተቃዋሚዎች በሰልፉ ላይ "ፍልስጤምን ልቀቁ፣ የዘር ማጥፋት ይቁም" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል።

የኒው ሶውዝ ዌልስ ፖሊስ ሰልፉን ለመግታት ሙከራ ማድረጉ ተገልጿል።

የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽነር ፒተር ማኬና ሰልፉን ለመበተን የፖሊስ ሄሊኮፕተር መላኩን አስታውቀዋል። #theweek

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia

በሰው መነገድ ወንጀል በተሳተፉ 5 ሰዎች የሞት ፍርድ እንዲወሰን መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የብዙ የሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ያለ ወንጀል መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ ለጋዜጣ ፕላስ ተናግረዋል።

በ2017 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሂደቱ የተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወስን መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በወንጀሉ ተሰማርተው የሚገኙ ወንጀለኞች በአዋጅ ቁጥር አንድ ሺህ 178 መሰረት የሞት ቅጣት፣ የዕድሜ ልክ እስራትና እስከ 25 ዓመት እስራት ያስቀጣል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በህገ ወጥ ድርጊቱ በስፋት ተጠቂ ለሆኑት ወጣቶች በሀገር ወስጥ የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልም ድንበር ተሻጋሪ የተደራጀ ወንጀል መሆኑን አንስተው፤ ይህንንም ለመቆጣጠር ከጅቡቲ፣ ኬንያና ማላዊ ጋር ዓለም አቀፍ ትብበር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። #GazettePlus

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ምግብ የለም፣ ዱቄት፣ ውሃ የለም፣ እኛ ምን እንድናደርግ ነው የሚጠበቀው?" ፍልስጤማውያን

በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን "የመኖር ትግል" እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

"ጋዛ በእስራኤል መር የዘር ማጥፋት እርምጃ በቦምብ ጋይታለች፣ ተርባለች" ብለዋል ነዋሪዎቹ።

"ምግብ የለም፣ ዱቄት፣ ውሃ የለም፣ እኛ ምን እንድናደርግ ነው የሚጠበቀው?" ሲሉም ጠይቀዋል።

ፍልስጤማዊያኑ እስራኤል "እያደረሰችብን ነው" ያሉት ጥፋት አለመቆሙንም ተናግረዋል። #aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ሁለት የኑክሌር ሰርጓጅ መርከቦች ትክክለኛው ቦታ ላይ ይሰፍራሉ" - ዶናልድ ትራምፕ

ትራምፕ ሁለት የባህር ሰርጓጅ ኑክሌር መርከቦች ወደ ዩክሬን እንዲላኩ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

በዚህም፣ "የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ድሜትሪ ሜድቬዴቭ ፀብ አጫሪ አስተያየት ይህን ውሳኔ እንድናሳልፍ አስገድዶናል" ብለዋል።

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ፣ "እነዚህ ውሸት እና ስም አጥፊ ሀሳቦች ከዚህም የበለጡ ይሆናሉ" ሲሉ አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ሁለት የኑክሌር ሰርጓጅ መርከቦች ትክክለኛው ቦታ ላይ ይሰፍራሉ" ብለዋል።

"ቃላቶች ጠቃሚ ናቸው" ያሉት ትራምፕ፣ "ነገር ግን ወደከፋ ቀውስ ያመራል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ግን ይሄ ፍላጎታቸው ላይሆን ይችላል" በማለት አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

የፕሬዚዳንቱ አዲስ ትዕዛዝ የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት ያባብሳል የሚል ስጋት ደቅኗል ተብሏል።  @realdonaldtrump

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#ፎቶ፦ በቬትናም ጎርፍ የ14 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ።

በከባድ ዝናብ ሳቢያ ድንገት የተከሰተው ጎርፍ በሰሜን ቬትናም በምትገኘው የዴን ቤን ከተማ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

ትላልቅ ካምፓኒዎች እና የመንግስት
መስሪያ ቤቶች ወድመዋል ተብሏል።  #reuters

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"አሜሪካና እስራኤል በጥምረት በህዝባችን ላይ ረሃብ ፈርደውበታል" - ሃማስ

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑት ስቲቭ ዊትኮፍን ጉብኝት ተቃወመ።

ቡድኑ ባወጣው መግለጫ፣ "መከራ ውስጥ የምትገኘው ጋዛ ላይ ቁጭት የሚፈጥር ነው" ሲል ጉብኝቱን ተችቷል።

ሀማስ አክሎ፣ "አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት በህዝባችን ላይ ረሃብ ፈርደውበታል" ሲል ወንጅሏል።

ቡድኑ በመግለጫው፣ "ጉብኝት የፕሮፓጋንዳ ሾው ነው" ሲልም አጣጥሎታል።

የዊትኮፍ እና የሃማስን ድርድር "የጦር ጠማቂዎችን ለማበረታታት የሞት ቲያትር እየተወኑ ነው" ብሏል። #anadoluagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ በፍልስጤም ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች።

የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት ለመጠበቅና ሽብርተኝነትን ለመከላከል ያለመ ነው የተባለው ይህ ማዕቀብ እነማንን ኢላማ እንዳደረገ አልተገለጸም።

ከውሳኔው በፊት ትራምፕ በፍልስጤም "በጣም ከባድ" ሲሉ የገለጹት ረሃብ መከሰቱን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ጋዛዊያን በጣም እየተራቡ ነው" ብለዋል።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ የምግብ መጋዘኖችን ለመጎብኘት ጋዛ እስራኤል ገብተዋል ተብሏል።

በቴላቪቭ ከኔታንያሁ ጋር የተወያዩት ዊትኮፍ እስራኤል በአለማቀፍ መድረክ መገለል እየደረሰባት መሆኑን ገልጸዋል።  #thenational

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ጦርነቱ ከዩክሬን ጋር ሳይሆን ከአሜሪካ ጋር ይሆናል" - ሜድቬዴቭ

"ወደ አደገኛ ቦታ እየገባህ ነው" - ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሩሲያን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ድሜትሪ ሜድቬዴቭን አስጠነቀቁ።

ትራምፕ የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን "የቀኝ እጅ ናቸው" የሚባሉትን ሜድቬዴቭን "የከሸፈ" ሲሉ ጠርተዋቸል።

በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው፣ "ሜድቬዴቭ አሁንም ፕሬዚዳንት እንደሆነ ነው የሚያስበው" ሲሉ ያሰፈሩት ትራምፕ፣ "ወደ አደገኛ ቦታ እየገባ ነው" ብለዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ የሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ምክትል ኃላፊ ሜድቬዴቭ በበኩላቸው ትራምፕ የሚሰጡትን ቀነ-ገደብ ተቃውመዋል።

ሜድቬዴቭ፣ "ትራምፕ በሩሲያ እየተጫወተ ነው፣ 50 ቀን ወይም 10 ቀን ይላል፣ ሩሲያ እስራኤል ወይም ኢራን አይደለችም" ብለዋል።

"አሁን ያሉት ዛቻዎች በዚሁ ከቀጠሉ ጦርነቱ ከዩክሬን ጋር ሳይሆን ከአሜሪካ ጋር ይሆናል" ሲሉም ተናግረዋል። #theindependent

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ከእስራዔል ጋር ሰላማዊ የሆነች ራሷን የቻለች እና ሉዓላዊ ፍልስጤም እንድትመሰረት ጥረት እናደርጋለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ካርኔይ

ካናዳ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቷን አስታወቀች።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፍልስጤም ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

ካርኔይ፣ "ለሁለት ሀገርነት መፍትሄ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እናደርጋለን" ብለዋል።

"ከእስራዔል ጋር ሰላማዊ የሆነች ራሷን የቻለች እና ሉዓላዊ ፍልስጤም እንድትመሰረት ጥረት እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍልስጤም መንግስት በ2026 በሚያካሂደው ምርጫ ሃማስን ማካተት እንደሌለበትም ማሳሰባቸው ተገልጿል።

ሁለቱ መሪዎች በጋዛ ስላለው የሰብዓዊ ቀውስ ችግር ተወያይተዋል ተብሏል። #novinite

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"22 ዜጎቻችን በመሞታቸው አዝነናል። ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል፣ 1200 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል" - የአንጎላ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር

በአንጎላ ለተቃውሞ የወጡ 22 ሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል።

የተደረገውን የነዳጅ ጭማሪ በተመለከተ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞቹ ላይ ፖሊስ የኃይል እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል።

ነዳጅ በሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ከ300 ወደ 400 ክዋንዛ ወይም ከ0.33 ወደ 0.44 ዶላር ከፍ ብሏል ተብሏል።

ዜጎች ይህንን ውሳኔ በመቃወም አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ መንግሥት ሰልፉን ለመግታት በወሰደው እርምጃ የዜጎች ህይወት አልፏል፣ ጉዳትም ደርሷል ተብሏል።

የአንጎላ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማኑዌል ሆመም፣ "22 ዜጎቻችን በመሞታቸው አዝነናል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ፣ "ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል፣ 1200 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል" ብለዋል።

አንጎላ በከፍተኛ የኑሮ ውድመት ከሚሰቃዩ የአህጉሪቱ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ብቻ 20% መመዝገቡ ተገልጿል። #gulftimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Update

ስቲቭ ዊትኮፍ ሩሲያ ገቡ።

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ፣ትራምፕ ማዕቀብ ለመጣል ቀነ ገደብ ማስቀመጣቸውን ተከትሎ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ ሞስኮ አቅንተዋል።

ትራምፕ ሩሲያ እስከመጪው አርብ ድረስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ካልደረሰች ማዕቀብ እንደሚጥሉ ዝተዋል።

የልዩ መልዕክተኛው ጉዞ የመጨረሻ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን፣ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ከዚህ በላይ የሚዘልቅ አይደለም ተብሏል።#reuters

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ቀሪውን የጋዛ ክፍል ተቆጣጠር ካልሆነ ስልጣን ልቀቅ"- ኔታንያሁ የእስራኤልን ጦር አዛዥ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የእስራዔል ጦር ጋዛን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ውሳኔ አስተላለፉ፡፡

ኔታንያሁ "ጦሩ እስራዔላዊያን ታጋቾች የሚገኙበትን ስፍራ መቆጣነጠር አለበት" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስራዔል ጦር አዛዥ ሌተናል ጄነራል እያል ዛሚርን፣ "ቀሪውን የጋዛ ክፍል ተቆጣጠር ካልሆነ ስልጣን ልቀቅ" ሲሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

"ውሳኔው ተወስኗል፤ ጋዛን እንቆጣጠራለን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

"ዘመቻው አሁን ካልተጀመረ በእገታ ስር የሚገኙ እስራዔላውያን በረሃብ ይሞታሉ" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ የተሰማው በቅርቡ ሀማስ ያገታቸው እስራዔላውያን በምግብ እና በውሃ እጥረት ተጎሳቁለው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መልቀቁን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ #firstpost

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"የዊትኮፍን ወደ ሞስኮ መምጣት በበጎ ነው የምንመለከተው" - ሩሲያ

የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ወደሩሲያ ያደርጉታል የተባለውን ጉዞ እንደሚደግፉ ተናገሩ።

ፔስኮቭ "እነዚህን ግንኙነቶች አስፈላጊ፣ ትርጉም ያላቸው እና ጠቃሚ አድርገን ነው የምንወስዳቸው" ብለዋል።

"የዊትኮፍን ወደ ሞስኮ መምጣት በበጎ ነው የምንመለከተው" ያሉት ፔስኮቭ "ድርድሩ ቀጥሏል፣ አሜሪካም ዩክሬን እንድትረጋጋ የበኩሏን ሚና እየተወጣች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ "ለዩክሬን ጦርነት የፓለቲካ እና የድፕሎማሲ መፍትሔዎች ተመራጭ ናቸው" ነው ያሉት።

ልዩ መልዕክተኛው "የመጨረሻ እድል" ሲሉ የጠሩትን ሰላማዊ መፍትሄ የመፈለግ ጥረት በቀጣይ ሳምንት ወደ ሩሲያ ያቀናሉ ተብሏል። #abcnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#GrmaAmente

የቀድሞው የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት ሹመት ተሰጣቸው።

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአለም ንግድ ድርጅት ቋሚ መልዕክተኛ ሁነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ሹመቱ የተሰጣቸው ከሁለት ቀን በፊት ኦገስት 02/2025 መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴሩ፣ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡ ያለውን እምነት ገልጿል።

ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም፣ ግርማ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ሥራ መልቀቃቸው መገለጹ አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግብርና ሚኒስትር የነበሩትን ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) በመተካት የኦሮሚያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ የነበሩትን አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚኒስትር አድርገው መሾማቸው ይታወሳል። #mofa

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። 54 አስክሬን በውቅያኖስ ዳር ተጥለው 14 ቱን ወደሆስፒታል ልከናል " - IOM

68 አፍሪካውያን ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

በየመን አብያን ግዛት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስመጧ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውንና ከ74 የሚበልጡ መጥፋታቸውን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

በየመን የአይ ኦ ኤም ተወካይ አቤዱሳቶር ኢሶቭ "በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው" ብለዋል።

ኢሶቭ በሰጡት ቃል፣ "54 አስክሬን በውቅያኖስ ዳር ተጥለው 14 ቱን ወደሆስፒታል ልከናል" ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ተወካዩ ገለፃ ኢትዮጵያውያኑ አደጋው የደረሰባቸው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው። #france24

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በሩሲያ በ24 ሰዓት ውስጥ 10 የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ተከሰቱ

"በ600 አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየ ክስተት ነው" ሲል የሩሲያ ሴስሞሎጂካል ሰርቪስ (RSS)
የአደጋውን ሁነት ገልጾታል።

በካምቻትካ ከተማ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሬክተር ስኬል 8.8 መለካቱን ሰርቪሱ አስታውቋል።

በተጨማሪም ይህ "10 ጊዜ መከሰቱ ከ1952 ወዲህ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው ነው" ብሏል።

በተለያዩ ከተሞች እንደተከሰተ የተገለጸው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኩሪል አይስላንድ በወደብ መሰረተ ልማት ላይ ከባድ ውድመት አድርሷል ተብሏል።   #thepeninsula  #rianovosti

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"እየሩሳሌምን ዋና ከተማ ያደረገ ሉዓላዊ የፍልስጤም ግዛት ሳይመሰረት ትጥቅ መፍታት የማይታሰብ ነው" - ሀማስ

ከእስራኤል ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው ሀማስ ፍልስጤም ሀገር መሆኗ ሳይረጋገጥ ትግል እንደማያቆም አስታወቀ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ "ብሔራዊ መብታችን ሳይመለስ፣ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ ያደረገ ሉዓላዊ የፍልስጤም ግዛት ሳይመሰረት ትጥቅ መፍታት የማይታሰብ ነው" ብሏል።

መግለጫው አክሎ፣ "የፍልስጤም ግዛት ሳይመሰረት የሚቆም ትጥቅ ትግል የለም" ሲል አስታውቋል።

መግለጫውን ያወጣው በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፣ "ሀማስ መሳሪያ ለማውረድ ዝግጁ ነው" ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

ዊትኮፍ ጋዛ ገብተው ለ5 ሰዓት በነበራቸው ቆይታ በአሜሪካ የሚደገፈውን የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) ከጎበኙ በኋላ "ሁኔታዎችን ገምግመናል" ብለዋል።

ሀማስ "ጦርነቱን ለማቆም እየሰራሁ ነው" የሚለውን የትራምፕን አስተዳደር "የአሜሪካ መንግስት የረሃብ እና ዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ሙሉ አጋር ነው" በማለት ወንጅሏል።

የሀማስ መግለጫ የወጣው ካናዳ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጥ እየገፋፉ ባለበት ወቅትም ነው።

ሀገራቱ ከተመድ ጋር በመሆን በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንድረጋገጥ "የሁለት ሀገርነት መፍትሄ" እንደሚያስፈልግ ቢገልጹም፣ ሀማስ ግን ሙሉ በሙሉ ትጥቅ መፍታት እና ህልውናው ማክተም እንዳለበት አሳስበዋል። 
#thenationalnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በሄይቲ በሦስት ወራት ውስጥ ከ1520 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ 609 ተጎድተዋል" - ሪፓርት

"240,000 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል" - IOM

"በሁለት ወሮበላ ቡድኖች" እየተናወጠች የምትገኘው የላቲን አሜሪካዋ ሀገር ሄይቲ አሁንም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

ተመድ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ 1520 ሰዎች መሞታቸውንና 609 ሰዎች መጎዳታቸውን አመላክቷል።

ይህ አሀዝ በ2025 ሩብ አመት ከነበረው 1617 ሞት እና 580 ጉዳት ጋር እንደሚመሳሰል ገልጿል።

በተመድ የሄይቲ ተወካይ ኡልሪካ ሪቻርድሰን "ዋና ከተማዋን ፖርታፕሪስን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ሪቻርድሰን፣ "በእነዚህ ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 45,000 ዜጎች ተፈናቅለዋል" ብለዋል።

እንደ አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IMO) መረጃ ከሆነ 240,000 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ።

ሄይቲ በ2021 በፕሬዚዳንት ጆቬኔል ሞይሴ ግድያ ከተፈጸመባቸው በኋላ ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ገብታ ትገኛለች።

ሄይቲን ለማረጋጋት ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጣውና በኬንያ የሚመራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በ2024 ወደ ስፍራው አቅንቷል። #unnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የቀድሞው የኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት አልቫሮ ኡርቤ የቤት ውስጥ እስር ተፈረደባቸው።

በሙስና እና ማጭበርበር ወንጀል የተከሰሱት ኡርቤ የ12 አመት እስር እንደተፈረደባቸው ተገልጿል።

ኡርቤ ፈፅመውታል ለተባለው ወንጀል 820,000 ዶላር እንዲከፍሉ ተፈርዶባቸዋል።

አልቫሮ ኡርቤ ማስረጃዎችን በመሰወር እና ፍርድ ቤትን በማጭበርበር ወንጀል ተጨማሪ ክስ ቀርቦባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወንጀል የተቀጡ የመጀመሪያው የኮሎምቢያ መሪ መሆናቸው ተመላክቷል።

የኡርቤ ደጋፊዎች "ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው" በማለት የተላለፈባቸውን ፍርድ ተቃውመዋል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኮሎምቢያን ከ2002 - 2010 መምራት ችለዋል። #aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ሁሉም ኃላፊነት የሚሰሚው ሀገር በእስራኤል ላይ እርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለበት" - ስሎቬኒያ

ስሎቬኒያ ከእስራኤል ጋር የጦር መሳሪያ ንግድ በማቆም የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ሆነች።

ስሎቬኒያ ከእስራኤል ጋር የጦር መሳሪያ "ግዥ፣ ሽያጭ እና ዝውውር" ስምምነት ማቆሟን አስታውቃለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ጎሎብ የእስራኤል ድርጊት አለማቀፍ ህግን የሚፃረር ነው በማለት ወቅሰዋል።

"ፍልስጤማውያን በሰብዓዊ እርዳታ እጥረት ስም በዘዴ እየሞቱ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ጎሎብ አክለውም፣ የአውሮፓ ህብረት የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ "የውስጥ አለመስማማትና ክፍፍል ገጥሞታል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ሁሉም ኃላፊነት የሚሰሚው ሀገር በእስራኤል ላይ እርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለበት" በማለት አሳስበዋል።

ስሎቬኒያ በእስራኤል ላይ ተቃውሞ ስታሰማ ይህ የመጀመሪያ እንደሆነ ተመልክቷል። #luxembergtimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ጄነራል ሚን ህላይንግ የምያንማር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

በምያንማር ምርጫ መካሄዱን ተከትሎ በ2021 ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ኡንግ ሳን ሱኪን በመፈንቅለ መንግስት ያስወገደው ወታደራዊ ጁንታ ከአራት አመት የሽግግር ጊዜ በኋላ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ተብሏል። #theasahishimbun

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የአውሮፓ ህብረት ለሀገሪቱ የደገፈውን 170, 000 ዩሮ "ለግል ጥቅም ያዋሉ" የሊቱንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ለቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጊንታውታስ ፓሉካስ በሙስና ወንጀል መዘፈቃቸውን የሚያሳይ የምርምራ ዘገባ መውጣቱ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን መነሳታቸውን ፕሬዚዳንት ጊታናስ ናውሴዳ አረጋግጠዋል ተብሏል።

ፓሉካስ የአውሮፓ ህብረት ለሀገሪቱ የሰጠውን ድጋፍ ለግል ጥቅም ማዋላቸውን የምርመራ ዘገባው አመላክቷል።

የ49 አመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከህብረቱ የተገኘውን 170,000 ዩሮ ሙሉ በሙሉ ለመዝረፋቸው ተገልጿል። #occrp

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በጋዛ ስልታዊ የዘር ማጥፋት እና የታቀደበት ረሃብ ታውጇል" - የጣሊያን ዶክተሮች

በጣሊያን ከ700 በላይ የህክምና ባለሙያዎች እስራኤልን በመቃወም የረሃብ አድማ መምታት መጀመራቸው ተገልጿል።

በቱስካን ከተማ ያሉ የህክምና ዶክተሮች፣ ነርሶች እና የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች እየተፈጸመ ነው ያሉት "በጋዛ ስልታዊ የዘር ማጥፋት እና የታቀደበት ረሃብ እወጃ" እንዲቆም ጠይቀዋል። 

በከተማዋ በሚገኙ ከ40 በላይ ሆስፒታሎች የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች የረሃብ አድማውን ተቀላቅለዋል ተብሏል።

ባለሙያዎቹ ባወጡት መግለጫ፣ "በጋዛ የሚፈጸመውን እያየን ዝምታን አንመርጥም" ብለዋል።

አድማ ላይ የሚገኙት ዶክተሮች አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ለእስራኤል የሚሰጡትን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያቆሙም አሳስበዋል። #middleeastmonitor

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"የጋዛን ጦርነት ለማቆም ሀማስ ጋዛን ማስተዳደር ያቁም፣ ትጥቅ አውርዶ ለፍልስጤም መንግስት ያስረክብ" - የአረብ ሊግና የአውሮፓ ሀገራት

ቱርክ ሀማስ ትጥቅ እንደመፈታ የቀረበውን ሀሳብ ደገፈች።

የአረብ ሊግ እና የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ጦርነቱ እንዲቆም ሀማስ ትጥቅ እንዲፈታና ጋዛን የማስተዳደር እቅዱን እንዲተው ያቀረቡት እቅድ በቱርክም ተደግፏል።

አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ጦርነቱን ለማቆም የሁለት ሀገርነት እውቅና መስጠትን እንደመፍትሄ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዚህም ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስም ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል።

ባወጡት የጋራ መግለጫም፣ "የጋዛን ጦርነት ለማቆም ሀማስ ጋዛን ማስተዳደር ያቁም፣ ትጥቅ አውርዶ ለፍልስጤም መንግስት ያስረክብ" ሲሉ አስታውቀዋል።

መግለጫው አክሎ፣ "አላማው በአለማቀፍ ማህበረሰብ ተሳትፎ እና ድጋፍ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ የፍልስጤም ሀገር እውቅና መስጠት ነው" ብሏል።

የቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኑህ ይልማዝ ሀገራቸው እቅዱን እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

ነገር ግን የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት "ሀማስ አሸባሪ አይደለም፣ መሬቱን እና ህዝቡን ለመጠበቅ የሚታገል ቡድን ነው" ብለውታል። #turkishminute

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ትራምፕ ኢራን ላይ ምንም መፍጠር ስላልቻሉ፤ የጥቃቱን ክሽፈት በግነት እየሸፋፈኑት ነው"- ኢራን

ትራምፕ ኢራን ላይ ምንም መፍጠር ስላልቻሉ፤ የጥቃቱን ክሽፈት በግነት እየሸፋፈኑት ነው ሲሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ ገለጹ።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ያደረሰውን ውጤት አስመልክቶ በማጋነን እየተናገሩ ነው። ሆኖም ጥቃቱ ምንም አይነት ውጤት አላስገኘም ብለዋል።

መሪው በይፋዊ የኤክስ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባልተለመደ መልኩ በተለይ ኢራን ላይ ያደረሱትን ጥቃት ማጋነናቸውን ገልፀዋል።

ኢራን ላይ ምንም ማድረግ አልቻሉም እና  ነገሮችን በማጋነን እውነቱን ለመደበቅ እየጣሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ወደ ኢራን ዘልቆ በመግባት የኒውክሌር አቅማቸውን አጥፍተናል ማለታቸው ይታወሳል።

የሁለቱ ሀገራት ግጭት በአሜሪካ አመቻችነት በተደረሰ የተኩስ አቁም ስምምነት ተቋጭቷል ተብሏል።
#GazettePlus #Anadolu

@TiqahEth

Читать полностью…
Subscribe to a channel