15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"እኛ ጦርነቱ እንዲቆም ፍላጎት ቢኖረንም፣ ሩሲያ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነችም" - ዘለንስኪ
"ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነበር" - በውይይቱ
ሶስት ሰዓት የፈጀው የትራምፕና ዘለንስኪ ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት እየፈጸመች እንደነበር በውይይቱ ተገልጿል።
ዩክሬን እና የአውሮፓ ሀገራት በስብሰባው ዘለንስኪ እንዲካተት ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ባለመሳካቱ በቪድዮ መልዕክት ለማስተላለፍ ተገዷል።
ዘለንስኪ፣ "ምንም እንኳ እኛ ጦርነቱ እንድቆም ፍላጎት ቢኖረንም፣ ሩሲያ ይህን ለማድረግ ፍቃደኛ አልሆነችም" ብለዋል። 3 ሰዓት ከፈጀው የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት በኋላ አጭር የጋራ መግለጫ ከመስጠት ባለፈ ከጋዜጠኞች የቀረበ ጥያቄ አላስተናገዱም።
ሁለቱ መሪዎች ከውይይታቸው በኋላ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ንግግሩ በተደረገበት አላስካ በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸው ላለፉ የሩሲያ አብራሪዎች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
የተናጠል ይሆናል ተብሎ በተጠበቀው የመሪዎች ውይይት ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርክ ሩቢዮ እና ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ የተሳተፉ ሲሆን፣ ከወደ ሩሲያም በተመሳሳይ ሰርጌ ላቭሮቭ እና ዩሪ ኡሻኮቭ ተሳታፊ ሆነው ስብሰባው የሶስትዮሽ ሆኗል።
ትራምፕ በስብሰባው ዩክሬን እንድትሳተፍ ጫና ቢደረግባቸውም፣ ሩሲያን ወደሰላም እንድትመጣ ካልሆነ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ሲያስጠነቅቁ፣ ዘለንስኪ ዩክሬን ግዛቷን ልታጣ እንደምትችል በማወቅ ለሰላም ሲባል የትኛውንም መቀበል እንዳለበት አሳስበዋል። #independent #bbc #thediplomatist
@ThiqahEth
"በጋዛ እርዳታን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይቁም" - የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች
ከ100 የሚበልጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እስራኤልን አስጠነቀቁ።
ድርጅቶቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ "የእስራኤል ባለስልጣናት የህይወት አድን እርዳታ እንዳይገባ ከልክለዋል" ሲሉ ገልጸዋል።
"የህክምና ቁሳቁሶች እና የምግብ እህሎች በግብፅ እና ጆርዳን ድንበር ከቆሙ ወራቶች ተቆጥረዋል" ብለዋል።
እነዚሁ መንግስታዊ ያልሆኑት ተቋማት "በጋዛ እርዳታን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይቁም፣ ሀገራት እና ተቋማት ጫና ማድረግ አለባቸው"ሲሉ ጠይቀዋል።
ዝግ የሆኑ የእርዳታ መግቢያ ድንበሮች እንዲከፈቱም አሳስበዋል። #cbcnews
@ThiqahEth
አሜሪካ ለናይጄሪያ የ346 ሚሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ አጸደቀች።
በስምምነቱ የቦምብ፣ የሚሳዔል፣ የሮኬት እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተካተዋል ተብሏል።
ዋሽንግተን ከአቡጃ ጋር የፈጸመችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት ታሪክ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል። #politicsnigeria #dcsa
@ThiqahEth
"የጋዛ ስደተኞችን አልቀበልም" - ደቡብ ሱዳን
የደቡብ ሱዳን መንግስት ፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ከእስራኤል መንግስት ጋር የተደረገ ስምምነት አለመኖሩን ገለጸ።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ "እነዚህ ሀሳቦች መሰረተ ቢስ ናቸው" በማለት መረጃውን አጣጥሎታል።
"የጋዛ ስደተኞችን አልቀበልም" ያለችው ጁባ "ይህ የመንግስት አቋምም ሆነ ፖሊሲ አይደለም ስትል ገልፃለች።
ደቡብ ሱዳን ምላሽ የሰጠችው አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን እስራኤል በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያንን ወደጁባ ለማዘዋወር ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን መናገራቸውን ተከትሎ መሆኑን "ዋሽንግተን ታይምስ" ዘግቧል።
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ወደ ደቡብ ሱዳን ልታዘዋውር መሆኑ ተገልጾ ነበር።
በዚህም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን፣ "ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው" መባሉን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
@ThiqahEth
"ኔታንያሁ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው" - ከፍተኛ የእስራኤል ባለስልጣን
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ወደ ደቡብ ሱዳን ልታዘዋውር መሆኑ ተገለጸ።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን፣ "ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ አክለውም፣ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ልዩ የልዑካን ቡድን ወደ ጁባ ይልካሉ" ብለዋል።
በፍልስጤማውያን ወደ ጁባ መዘዋወር ጉዳይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውይይት መጀመሩን የደቡብ ሱዳን ጂፕሎማቶች አረጋግጠዋል ተብሏል።
ኔታንያሁ ፍልስጤማውያን በፍቃደኝነት እንዲለቁ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ነገር ግን አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ውሳኔ እየተቃወሙት ይገኛሉ። #sudanpost
@ThiqahEth
የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት በፖሊስ ተያዙ።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዮዔል ባለቤት ኪም ኪዮን ሂ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸው ተገልጿል።
በእስር ላይ የሚገኘው ባለቤታቸው ዮን ሱክ ዩዔል በስልጣን በነበሩበት ወቅት "በምርጫ እጩ መረጣ ወቅት ጣልቃ በመግባት፣ በማጭበርበር፣ በብልሹ አሰራር" መሳተፋቸውን ካረጋገጠ በኋላ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዮዔል ባለቤት የእስር መያዣ ሲያውቁ ሰነዶችን አጥፍተዋል ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮዔል ባሳለፍነው ህዳር ለሰዓታት ባስተላለፉት የወታደራዊ አስተዳደር ከስልጣን ተባረው በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። #bowenisland
@ThiqahEth
የኮሎምቢያ ፕሬዚደንታዊ እጩ ህይወታቸው አለፈ።
ከሁለት ወር በፊት ጥቃት የተፈጸመባቸው የኮሎምቢያ ሴናተርና ፕሬዚዳንታዊ ሚጉዌል ኡራይብ መሞታቸው ተገልጿል።
ኡራይብ በ2026 ለሚካሄደው ምርጫ በቦጎታ ግዛት ዘመቻ ላይ እያሉ ጥቃት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
የ39 አመቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በሳንቴፌ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቢቆዩም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም ነው የተባለው።
የኮሎምቢያ አቃቤ ህግ ጥቃቱን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል። #timeslive
@ThiqahEth
አውስትራሊያ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ ገለጸች።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ የፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ካናዳ ፍልስጤም ሀገር እንድትሆን ያቀረቡትን እቅድ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀረበው የሁለት ሀገርነት መፍትሄ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።
አልባኔስ ከካቢኔ አባሎቻቸው የሚነሳው ተደጋጋሚ ጥያቄ ይህን ውሳኔ ለማሳለፋ እንዳስገደዳቸው ተመላክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋዛን ከጦር ቀጠና ማውጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። #thewashingtontimes
@ThiqahEth
#AddisAbaba
አዲስ አበባ በመጪዎቹ ዓመታት ኮድ አንድ ታክሲዎችን ትታ ወደ አውቶብስ የትራንስፖርት ስርዓት ልትገባ ስለመሆኗ ተዘገበ።
የከተማዋ የወደፊት የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከኮድ አንድ ታክሲዎች ይልቅ አውቶብስና ከ25 ሰው በላይ የሚጭኑ ሜትር ታክሲዎችን የሚያበረታታ ስለሆነ ከተማዋ ወደዚያው የትራንስፖርት ስርዓት ትገባለች ሲሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል።
አንድ አውቶብስ የ8 ታክስዎችን ያህል ይጭናል፣ ከመንገድ መጨናነቅ፣ ከተመጣጣኝ የጉዞ ታሪፍ፣ ከነዳጅ ቁጠባና ከአየር ብክለት አንፃር አውቶብስን ጨምሮ ከ25 ሰው በላይ የሚጭኑ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ለከተማዋ ተመራጭ ነው ብለው፣ ማህበረሰቡ ብዙሃን ትራንስፖርት የመጠቀም ልምዱን እንዲያሳድግ መክረዋል።
ከተማዋ ውስጥ ያሉ ኮድ_አንድ_ታክሲዎች አብዛኛዎቹ አሮጌና የከተማዋን የታክሲ መስፈርት ስለማያሟሉ ጭምር ከትራንስፖርት ስርዓቱ መውጣታቸው ግድ ነው ማለታቸው ተሰምቷል።
ኮድ አንድ ታክሲዎች ከትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ሲሆኑ ሰዎችን ከስራ ገበታ አያፈናቅልም? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊው፣ በመንግስት ድጋፍ ኮድ አንድ ታክሲዎችን ከ25 ሰው በላይ ወደ ሚጭኑ ሜትር ታክሲዎች የማሳደግ ሥራ ይሰራል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በአዲሱ የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከ2018 ጀምሮ ከጀሞ በቄራ አድርጎ ፒያሳ የሚደርስ ፈጣን የአውቶብስ መንገድ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ከሁለት ዓመት በኋላም አዲስ አበባ ከታክሲዎች ጋር የማይገናኝ ፈጣን የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚኖራት ተጠቁሟል።
@ThiqahEth
"የሱዳንን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ሲቪል መር አስተዳደር እንዲመሰረት እንፈልጋለን" - አቡዳቢ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሱዳን የርስበርስ ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቀረበች።
አቡዳቢ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፃለች።
መግለጫው "ሰላምን መረጋጋትን እና የነገን ተስፋ መፈለግ ይገባል" ብሏል። "የተኩስ አቁም እንዲደረስ፣ ንጹሃን እንዲጠበቁ እና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀናል" ሲል ገልጿል።
መግለጫው አክሎም፣ "የሱዳንን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ሲቪል መር አስተዳደር እንድመሠረት እንፈልጋለን" ነው የሚለው።
ኤምሬትስ ከሱዳን የሚቀርብባትን ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ የመስጠት ውንጀላ "ሆን ተብሎ የተሰራ ፕሮፓጋንዳ" ስትል አጣጥላዋለች። #khaleejtimes
@ThiqahEth
"ከጋዛ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ዘር ማጥፋትን እንቃወማለን፣ የፍልስጤምን ድርጊት እንደግፋለን" - ሰልፈኞች
የለንደን ፖሊስ ከ460 በላይ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።
የፍልስጤም ተሟጋቾች እስራዔል በፍልስጤውያን ላይ የምትፈጽመውን ግፍ ለመቃወም በፓርላማ አዳራሽ ፊት ለፊት መሰባሰባቸው ተገልጿል።
ተቃዋሚዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር መንግስት እስራኤል ላይ ማዕቀብ መጣልን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቀዋል።
በሰልፉ ወቅት "ከጋዛ ላይ እጃችሁን አንሱ"
ዘር ማጥፋትን እንቃወማለን፣ የፍልስጤምን ድርጊት እንደግፋለን" በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ይህንን ተከትሎ የከተማዋ ፖሊስ ከ460 በላይ የሰልፉ ታዳሚዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
ዩናይትድ ኪንግደም እንደ "የሽብር ተግባር" በመቁጠር በሀገሯ የሚደረጉ የፍልስጤም መብት ተሟጋቾችን እንቅስቃሴ አግዳለች ተብሏል። #reuters
@ThiqahEth
"አሜሪካ ፍልስጤምን ሀገር የማድረግ እቅድ የላትም፣ እዚያ አቅም ያለው መንግስት የለም" - ጄይ ጂ ቫንስ
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ቫንስ ሀገራቸው ፍልስጤም ሀገር እንድትሆን ፍላጎት የላትም አሉ።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ "እዚያ አቅም ያለው መንግስት የለም" በማለት ገልጸዋል።
ቫንስ ይህን ያሉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉባት ባለችው እንግሊዝ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ላሚ ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።
እስራኤል በጋዛ የምትፈጸመውን ግፍ እንድታቆም አሜሪካ ጫና ማድረግ እንዳለባት አሳስበዋል ተብሏል።
እንግሊዝ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ በሁለት ሀገርነት መፍትሄ መርህ ፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። #indiatoday
@ThiqahEth
"ከፍተኛ የሞት መጠን ከተመዘገበባቸው መካከል ይህ ጥቃት አንዱ ነው" - ተመድ
"የሽብር ወንጀል እየተፈጸመ የሚደረግ የሰላም ስምምነት የለም" - የዲአር ኮንጎ መንግስት
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 319 ንጹሃን በኤም 23 አማፂ ቡድን ተገደሉ።
በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው የM 23 አማፂ ቡድን በሰሜን ኪቩ ግዛት የንጹሃን ጭፍጨፋ መፈጸሙ ተገልጿል።
"አመፂ ቡድኑ ገደላቸው" ከተባሉ ንጹሃን መካከል 48 ሴቶች እና 19 ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ "ተጎጂዎችን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል።
ተርክ፣ "ከፍተኛ የሞት መጠን ከተሰዘገበባቸው ጥቃቶች መካከል ይህ አንዱ ነው" ሲሉ የድርጊቱን ዘግናኝነት አብራርተዋል።
"በንጹሃን ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መቆም አለባቸው" ያሉት ኮሚሽነሩ "ጥቃት አድራሾች ተጠያቂ እንዲሆኑ" ጠይቀዋል። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት በበኩሉ የደረሰውን ጥቃት አውግዟል።
የመንግስት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ "የሽብር ወንጀል እየተፈጸመ የሚደረግ የሰላም ስምምነት የለም" ሲሉም አስታውቀዋል። ቃል አቀባዩ "የተደረጉ ስምምነቶች በግዴለሽነት ተጥሰዋል" ሲሉ ቡድኑን ወንጅለዋል።
የሀገሪቱ መንግስት እና አማፂ ቡድኑ ጦርነቱን ለማቆምና ዘላቂ ስምምነት ለመፈፀም ባሳለፍነው ሰኔ ወር የመጀመሪያ ስምምነታቸውን በዋሽንግተን ተፈራርመዋል። #aljazeera #anadoluagency #abcnews
@ThiqahEth
ቤኑ 176 ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጸች።
የቤኑ ብሄራዊ ፖሊስ በክህደት፣ እገታ፣ ዘረፋና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ተሳታፊ ሆነዋል ያላቸውን ዜጎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
እነዚህ ፖሊሶች ባሳለፍነው ሀምሌ ወር የተከሰቱ መሆናቸውን የቤኑ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኢፌኒ እነማሪ ተናግረዋል። #dailytrust
@ThiqahEth
አሜሪካ ፕሬዚዳንት ማዱሮን በቁጥጥር ስር ላዋለ 50 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ቃል ገባች።
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ በቬኔዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል ተብሏል።
እ.ኤ.አ በ2020 ማዱሮ ላይ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር ክስ የከፈተችባቸው አሜሪካ፣ ፕሬዚደንቱ ያሸነፉባቸውን ያለፉትን ሁለት ዙር ምርጫዎች እውቅና እንደማትሰጥ ገልፃለች። #bbc #france24
@ThiqahEth
"ሌላ ስምምነት እስኪደረግ ድረስ የተፈፀመ ስምምነት የለም" - ትራምፕ
"ትራምፕ ለሁለተኛ ዙር ውይይት ሞስኮ እንድመጡ የግብዣ ጥሪ አቅርቢያለሁ" - ፑቲን
ተጠባቂው የፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ተካሂዷል።
የሁለቱ መሪዎችዝግ ስብሰባ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያተኮረ ቢሆንም በዚህ ዙር መቋጨት አልቻለም። 3 ሰዓት የፈጀው የአላስካው ንግግር ተከታዮቹን 10 የውይይት ነጥቦች ያካተተ እንደነበር ተገልጿል።
ትራምፕ በውይይቱ አብዛኛው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተደርሷል ብለዋል። ይሁን እንጂ "ሌላ ስምምነት እስኪደረግ ድረስ የተፈጸመ ስምምነት የለም" ብለዋል። ቀሪ ነገሮች በቀጣይ ይስተካከላሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ፑቲን ደግሞ ጦርነቱን ለማቆም "በክብር ፍቃደኛ ነኝ"፣ ግን ሩሲያ "የጦርነቱ መንስዔ እንድታወቅላት ትፈልጋለች" ብለዋል። ዩክሬንና የአውሮፓ ሀገራት ውይይቱን ገና ከጅምሩ ለማደናቀፍ መጣራቸውን ገልፀው እንድያቆሙ አሳስበዋል። ፑቲን ትራምፕ የ2020 ምርጫን አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ጦርነቱ አይነሳም ነበር ብለዋል።
ትራምፕ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቁም፣ ፑቲን ትራምፕን ለሁለተኛ ዙር ውይይት ሞስኮ እንዲመጡ "የግብዣ ጥሪ አቅርቢያለሁ" ብለዋል። ፑቲን ትራምፕን ወደሞስኮ አቅንተው ቀጣዩ ዙር ውይይት በዚያ እንድካሄድ ግብዣ ያቀረቡ ሲሆን ትራምፕ "ደስ የሚል ነገር ነው፣ አስብበታለሁ" ብለዋል።
ፑቲን "ወዳጅነት የተሞላበት" ላሉት የትራምፕ የውይይት ግብዣ አመስግነው፣ ሩሲያና አሜሪካ ወደኋላ ተመልሰው ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ አሜሪካን ለማበልጸግ ያለውን ትጋት ያደነቁት ፑቲን፣ ሩሲያም የራሷ "ብሄራዊ ጥቅም" እንዳላት መታወቅ አለበት ብለዋል። (ተጨማሪ አለን)
@ThiqahEth
"ፑቲን ለሰላም ዝግጁ ነው" - ትራምፕ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በፊት አስተያየታቸውን ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል።
በዚህም የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን "ጦርነቱን የመቋጨት ፍላጎት አላቸው ብየ አምናለሁ" ብለዋል።
ከውይይቱ ጥሩ ውጤት እንደሚጠብቁ የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ፣ "ፑቲን ለሰላም ዝግጁ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ፕሬዚዳንት ዘለንስኪም ሰላም ይፈጥራል ብየ አስባለሁ" በማለት ተናግረዋል።
በአላስካ የሚደረገው የትራምፕና የፑቲን ስብሰባ ከሰዓታት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። #novinite
@ThiqahEth
#ኢትዮጵያ #ሰሜንናደቡብወሎ
ሰሜን ወሎ ዞን ብቻ ከ260 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው አመቱ ማለፉ ተነገረ።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኙ 958 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሲሰጥ የነበረው በ615ቱ ብቻ እንደነበር የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።
በ2017 ዓ/ም በዞኑ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በትምህርት ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል ያሉት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሰጠ ታደሰ፣ በዚህም ከ260 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለ2018 የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች ምዝገባ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑና እስካሁን 873 የትምህርት ተቋማት ጥገና እንደተደረገላቸው ቢናገሩም፣ ምን ያህሉ ውድመት እንደደሰሰባቸው ግን አልገለጹም።
ተማሪዎችን እስከ ነሃሴ 19 ቀን ድረስ መዝግቦ ለማጠናቀቅ፣ የ2018 የትምህርት ዘመን መስከረም 5 ቀን እንደሚጀመር ገልጸው፣ 492 ሺህ 176 ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና በደቡብ ወሎ ዞን በክልሉ ባለው ጦርነት ሳቢያ በዞኑ ካሉ 1 ሺሕ 279 ትምህርት ቤት 464 የሚሆኑት ዝግ ሆነው አመቱ መጠናቀቁ ተመልክቷል። መረጃው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ነው።
@ThiqahEth
በአራት የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ የሰደድ እሳት መከሰቱ ተገለጸ።
በግሪክ፣ ስፔን፣ አልባኒያ እና ቱርክ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነ የሰደድ እሳት ተከስቷል ተብሏል።
በአራቱም ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአደጋው ለመፈናቀል መገደዳቸው ተገልጿል።
አደጋው በተለየ መልኩ ባጠቃት ግሪክ ለተልዕኮ ከተሰማሩ የድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች ውስጥ 15ቱ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው።
እስካሁን በሰደድ እሳት አደጋው ከዚህ በተጨማሪ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም ተብሏል። #theindependent
@ThiqahEth
"ጋዛን ለማስተዳደር በዋይትሐውስ ተመርጫለሁ" - ሰሚር ሀሊለህ
ፍልስጤማዊው ባለሀብት የጋዛ አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን አወጁ።
ባለሀብቱ ሰሚር ሀለሊህ በጦርነት የደቀቀችውን ጋዛን ለማስተዳደር "ዝግጁ ነኝ። ጋዛን ለማስተዳደር በዋይትሐውስ ተመርጫለሁ" ብለዋል።
ሀሊለህ፣ "ገለልተኝነት፣ የአስተዳደር ልምድና የህዝብ ተቀባይነት መኖር" ዋና መስፈርቶች መሆናቸውን ገልፀው፣ እሳቸው ሁሉንም እንደሚያሟሉ አብራርተዋል።
አሜሪካ በሹመቱ ዙሪያ ከእስራኤል፣ ሀማስ እና ከፍልስጤም መንግስት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ትመክርበታለች ብየ አስባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁን ኤንጂ በሀኒለህ ሹመት ዙሪያ ሹማኛለች ካሏት አሜሪካም ይሁን ከሀማስና የፍልስጤም አስተዳደር የተሰጠ ማረጋገጫ የለም ተብሏል። #mem #channeli24
@ThiqahEth
በስደተኞች ካምፕ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ተፈፀመ በተባለው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በሱዳን መጠለያ ካምፕ ላይ በተፈፀመ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።
በዚህም በምዕራብ ዳርፉር ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በስደተኞች ካምፕ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።
ጥቃቱን የፈፀመው የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ነው ተብሏል። #bbc
@ThiqahEth
"ፑቲን የሚታመን ሰው አይደለም፣ ከተቻለ ማስወገድ ነው" - ስታርመር
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር የትራምፕ እና ፑቲን ውይይት የተለየ ውጤት እንደማያመጣ ተናገሩ።
ምክንያት ያሉት ደግሞ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባህሪ ተለዋዋጭ ነው በሚል እንደሆነ ተገልጿል።
ስታርመር በአላስካ ይካሄዳል በተባለው የአሜሪካ ትራምፕ እና የሩሲያ አቻቸው ፑቲን የሁለትዮሽ ስብሰባ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ "ግዴታ መሳተፍ አለባቸው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ፑቲን የሚታመን ሰው አይደለም፣ ከተቻለ ማስወገድ ነው" ሲሉ የተደመጡት ስታመር፣ ነገር ግን "የፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥረት እንደግፋለን" በማለትም ተናግረዋል።
ኬር ስታርመር ይደረጋል የተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት "ፕሬዚዳንት ፑቲን ራሳቸውን የሚያደራጁበት፣ ጦራቸውን የሚያጠናክሩበት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል" ሲሉ ገልጸዋል። #theindependent
@ThiqahEth
"ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዋል፣ ለያለ እድሜ ጋብቻ ተጋልጠዋል፣ በአማፂ ኃይሎች ለትጥቅ ትግል በኃይል ተመልምለዋል" - የህፃናት አድን ድርጅት
በሞዛምቢክ በጦርነት ከተፈናቀሉት 60 ሺሕ ሰዎች ከ30 የሚሆኑት ህፃናት መሆናቸው ተገለፀ።
በሞዛምቢክ በካቦ ደልጋዶ ግዛት በተከሰተ ግጭት 30,000 ህፃናትን ጨምሮ 60, ሰዎች መፈናቀላቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን የተሰኘው አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅት አስታውቋል።
በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በሐምሌ አጋማሽ የተጀመረው ግጭት እስካሁን ድረስ አለመቆሙ ተገልጿል።
ቢሮው ባወጣው መግለጫ በግጭቱ "የታጠቁ ወገኖች የፖሊስ ጣቢያዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ማዕከላትን ኢላማ አድርገዋል" ብሏል።
ከመፈናቀላቸው በተጨማሪ "ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዋል፣ ለያለ እድሜ ጋብቻ ተጋልጠዋል፣ በአማፂ ኃይሎች ለትጥቅ ትግል በኃይል ተመልምለዋል" በማለት አስረድቷል።
በአሁኑ ወቅት ዕለታዊ ድጋፎችን እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል። #savethechildreninternational
@ThiqahEth
"በሽፋ ሆስፒታል አንድ ጋዜጠኛዬ በእስራኤል ጥቃት ተገድሎብኛል" - አልጀዚራ
"ጋዜጠኛ ሳይሆን የሃማስ የህዋስ መሪ ነበር" - እስራኤል
የ28 አመቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አናስ አል ሻሪፍ በምስራቅ ጋዛ በስራ ላይ እያለ መገደሉን አልጀዚራ አስታውቋል።
ጣቢያው ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "በሽፋ ሆስፒታል አንድ ጋዜጠኛዬ በእስራኤል ጥቃት ተገድሎብኛል" ብሎ፣ "ጥቃቱ በጋዛ የሚካሄደውን ህገወጥ ወረራ በተመለከተ ድምፅ የሚሆኑትን ለማስቆም የተደረገ ሙከራ ነው" በማለት ተቃውሟል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ ሟቹ "ከሀማስ አመራሮች ጋር ቅርብ ግንኙነት ነበረው" በማለት ወንጅሏል።
ጦሩ ባወጣው የማስተባበያ መግለጫ "ጋዜጠኛ ሳይሆን የሃማስ የህዋስ መሪ ነበር" ብሏል።
"በእስራኤል ንጹሃን ላይ በተፈጸሙ የሮኬት ጥቃቶች ላይ እጁ አለበት" ሲል ወቅሷል። ለዚህም የደህንነት እና የሰነድ ማስረጃዎች እንዳሉት ገልጿል።
@ThiqahEth
"ዩክሬንን ለመቀራመት የሚደረግ ውይይት አዋጭ አይደለም" - የዩክሬን አጋር የአውሮፓ ሀገራት
6 የአውሮፓ ሀገራት የትራምፕንና የፑቲንን የተናጠል ውይይት ተቃወሙ።
ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፊንላንድ እንዲሁም ፖላንድና እንግሊዝ በመሪዎቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ "የሀገር ሉዓላዊነት የሚባለው ጉዳይ ሊከበር ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
የዩክሬን አጋር የተባሉት እነዚህ የአውሮፓ ሀገራት "ዩክሬንን ለመቀራመት የሚደረግ ውይይት አዋጭ አይደለም" ብለዋል።
ሀገራቱ "በውይይቱ ዩክሬን መሳተፍ ይኖርባታል" በማለት ጠይቀዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው፣ "የዩክሬን ሰላም ያለዩክሬን ተሳትፎ አይወሰንም" ብለዋል።
"ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች የዩክሬንን እና የአውሮፓን ደህንነት መጠበቅ አለባቸው" ሲሉም ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ "ኪቭ ያልተካተተችበት የትኛውም ስብሰባ ውጤት አይኖረውም" በማለት የሁለቱን መሪዎች ስብሰባ ተቃውመዋል። #politico
@ThiqahEth
"ከኛ ተፃራሪ የሚሆን ውሳኔን አንቀበልም" - ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ትራምፕ እና ፑቲን በአካል ሊገናኙ ነው መባሉን ተከትሎ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘለንስኪ በዚህ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ልጥፋቸው በውይይቱ እሳቸውም እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ "ኪቭ ያልተካተተችበት የትኛውም ስብሰባ ውጤት አይኖረውም" ብለዋል።
አክለውም፣ "ከኛ ተፃራሪ የሚሆን ውሳኔን አንቀበልም" በማለት ፑቲንና ትራምፕ ብቻ የሚያካሂዱትን ውይይት ነቅፈውታል።
የሁለትዮሽ ንግግሩ የሚያመጣውን ውጤት "የሞተ መፍትሄ" በማለት ገና ከወዲሁ ተቃውመውታል።
"ዩክሬናውያን መሬታቸውን ለወራሪዎች አይሰጡም" ያሉት ዘለንስኪ ሀገራቸው ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። #telegraph
@ThiqahEth
"35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል" - አሜሪካ
"ዛሬ ሰላምን መስርተናል" - አዘርባጃን
"ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ጉልህ ስራ ተሰርቷል" - አርሜኒያ
አርሜኒያና አዘርባጃን በአሜሪካ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ፈጸሙ።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለአስርት አመታት የዘለቀውን ግጭት ያስቆማል የተባለ ስምምነት በዋሽንግተን ፈጽመዋል ተብሏል።
የአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሌቭ ከአርሜኒያው አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽኒያን ጋር በዶናልድ ትራምፕ አሸማጋይነት ውይይቱ መካሄዱ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን "ረጅም ጊዜ የወሰደ ታሪካዊ ስምምነት ነው" ብለውታል።
አዘርባጃንና አርሜኒያ ከ1980ዎቹ ጀምሮ በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛትጦርነት ውስጥ እንደነበሩ ያስታወሱት ትራምፕ ግጭቱን "እስከወዲያኛው ይወገዳል" በማለት ተናግረዋል።
ትራምፕ፣ "35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል" ያሉ ሲሆን፣ "የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት አሊቭ ደግሞ "ዛሬ ሰላምን መስርተናል" ብለዋል።
የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሺኒያን በበኩላቸው፣ "ለሁለቱ ጉልህ ሀገራት ግንኙነት ስራ ተሰርቷል" በማለት ገልጸዋል።
በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ሀገራት የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የንግድ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲጀመሩ እና ለተፈፃሚነቱ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። #bbc
@ThiqahEth
አሜሪካ ለዝምባቡዌ ዜጎች ቪዛ መስጠት አቆመች።
በሀራሬ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ እግዱ የተጣለው በብሄራዊ እና የህዝብ ደህንነት ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
ውሳኔው የተላለፈው በቀጥታ ከዋሽንግተን ነው ብሏል። #africannews
@ThiqahEth
ሩሲያ ለቻይና ነዳጅ በርካሽ ዋጋ መሸጥ ጀምራለች ተባለ።
ሩሲያ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ የነዳጅ ሀብት ሽያጭ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮባታል ተብሏል።
ሞስኮ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የአለም አቀፍ ንግድ እንቅስቃሴዋ ገደብ ተጥሎበታል።
ቻይና የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ብትሆንም፣ አሁን ግን በርካሽ ዋጋ የመሸመት እድል ማግኘቷ ተገልጿል።
ከጦርነቱ መጀመር በኋላ ህንድ የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ከፍተኛ ጠቀሜታን አግኝታለች ተብሏል።
ነገር ግን አሜሪካ ህንድ ነዳጅ ከሩሲያ መግዛት እንድታቆም ያሳሰበች ሲሆን ካልሆነ ግን ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠንቅቃለች።
አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ማዕቀብ ሩሲያን ማዕቀብ ቢጥሉባትም ነዳጇን በህንድ በኩል እየገዙ ሲጠቀሙ መቆየታቸው ተገልጿል። #oilprice
@ThiqahEth
"ከትራምፕ ጋር እንገናኛለን ብየ ተስፋ አደርጋለሁ" - ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቀጣይ ሳምንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሊገናኙ እንደሚችሉ ጠቆሙ።
ፑቲን፣ "ከትራምፕ ጋር እንገናኛለን ብየ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ከፑቲን አስተያየት ቀደም ብለው "ከፑቲን ጋር በቅርቡ የምንገናኝበት ጥሩ እድል አለ" ሲሉ ተናግረዋል።
ፑቲን ይህን ያሉት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዚዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር በሞስኮ ከተወያዩ በኋላ ነው ተብሏል።
ሁለቱ መሪዎች የሚገናኙበት ቦታ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደሆነ ተገልጿል። #timescolinist
@ThiqahEth