thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

"ኔታንያሁ ስለኳታሩ ጥቃት አላሳወቀኝም" - ፕሬዚዳንት ትራምፕ

ትራምፕ እስራኤል በኳታር ላይ ስለፈጸመችው ጥቃት መረጃ እንደሌላቸው ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "ኔታንያሁ ስለኳታሩ ጥቃት አላሳወቀኝም" ሲሉ ተደምጠዋል።

"ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ስለሁኔታው የነገረኝ ጥቃቱ ከተፈጸመ ከደቂቃዎች በኋላ ነው" ብለዋል ትራምፕ።

ፕሬዝዳንቱ ኳታርን "ሁነኛ አጋራችን ናት" ሲሉ ገልጸዋታል። በዚህ ጥቃት የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አለመኖሩን ገልጸዋል። #asiaone

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

4200 ሱዳናውያን በጎርፍ መፈናቀላቸው ተገለጸ

በዚሁ የጎርፍ አደጋ በአልጃዚራህ ከተማ 550 ቤቶች መፍረሳቸውን ተመድ አስታውቋል።

የጎርፍ አደጋው ጦርነትን ሸሽተው ለተፈናቀሉ ዜጎች ተጨማሪ ችግር መሆኑን አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

ሱዳን ከሰኔ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ከፍተኛ ዝናብ እንደምታስተናግድ ተመላክቷል። #anadoluagency

@ThqiahEth

Читать полностью…

THIQAH

የአረብ ሀገራት የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው።

አስቸኳይ ስብሰባውን የጠራችው ኳታር መሆኗ ተገልጿል። የሀገራቱ መሪዎች ወደ ዶሃ እየገቡ ነው ተብሏል።

እስራኤል ዶሃ ላይ በፈጸመችው ጥቃት አምስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት በወቅቱ ጥቃቱን አውግዘዋል። #aljazeera

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በአጋሮቻችን ላይ የሚቃጣን ጥቃት እንቀለብሳለን" ኔቶ

ኔቶ "ኢስተርን ሴንትሪ" ያለውን ወታደራዊ ልምምድ በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ ጀመረ።

ዘመቻው የጀመረው የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን የፖላንድን አየር ክልል ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑን የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ተናግረዋል።

ሩቴ "በአጋሮቻችን ላይ የሚቃጣን ጥቃት እንቀለብሳለን" ሲሉ ተናግረዋል። ዋና ፀሐፊው "ወታደራዊ ልምምዱ የአየርና የምድር ሀይሎችን ያካተተ ነው" ብለዋል።

"የጥላትን ጥቃት መቋቋም የሚያስችል፣ ከዚያም ባለፈ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን" በማለት አክለዋል።  

ፖላንድ ከቀናት በፊት የአየር ክልሏን ጥሰው የገቡ አራት የሩሲያ ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች። #theinsider

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በኮንጎ 86 ተማሪዎች በጀልባ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

ጀልባዋ የሰጠመችው ከመጠን በላይ ሰዎችን በመያዟ ነው ተብሏል።

በባስንኩ ግዛት በተከሰተው በዚህ አደጋ ምን ያክል ሰው በህይወት እኔደተረፈ አልተገለፀም። #indiatoday

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሴናሮ 27 አመት ተፈረደባቸው።

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዚዳንት ቦልሴናሮ በመንግሥት ግልበጣ ሙከራና ሌሎች አራት ክሶች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ሉላዳ ሲልቫ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ጌራልዶ አልኪም እና የከፍተኛ ፍርድቤቱን ዳኛ አሌክሳንደር ማሮስ ላይ ግድያ ሊፈጽሙ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል ተብሏል። #aa

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

እንኳን ለ2018 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ ውድ የቲቃህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በዓሉና አዲሱ ዓመት ደስታን የምትጎናጸፉበት፣ ክፉን የማትሰሙት፣ በበረከት የምትትረፈረፉበት፣ ሰላም፤ ፍቅር፤ ደስታ፤ መረጋጋት የሰፈነበት እንዲሆንላችሁ ቲቃህ ኢትዮጵያ ይመኛል።

መልካም አዲስ አመት፣ መልካም በዓል!

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የኤሌክትሪክ መኪና ዋጋ በአንድ አመት ውስጥ 53 በመቶ ጨምሯል ተባለ።

በአለማቀፍ ደረጃ ያለው የኤሌክትሪክ መኪና ግብይት ከባለፈው አመት ሲነፃፀር ከግማሽ በላይ ልዩነት እንዳለው ተገልጿል።

በ2025 የመጀመሪያው 36% እድገት አሳይቶ እንደነበር ተመላክቷል። #rte

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ቪዲዮ፦ እስራኤል ጥቃት መፈጸሟን ኳታር አስታወቀች።

ኳታር በእስራኤል ጥቃት እንደተፈፀመባት አስታውቃለች። በዶሃ ከተማ ከፍተኛ ፍንዳታ መከሰቱን ከስፍራው የወጡ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያሳያሉ። #telegraph

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ዛሬ ላይ ነፃነቴን አጥቻለሁ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሽዋንትራ

የታይላንድ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በእስር ቤት ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተናገሩ።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ታክሲን ሽዋንትራ፣ "ዛሬ ላይ ነፃነቴን አጥቻለሁ" ብለዋል። "ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚያሳልፍብኝን ውሳኔ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ" ሲሉም ተናግረዋል።

የ76 አመቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጣይ ሳምንት ከእስር ቤት ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቢሊየነሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሽዋንትራ በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ አንድ አመት
ሆኗቸዋል። #asiaone

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#GERD

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ (ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ተመረቀ። የ14 ዓመታት የግንባታ ጉዞ፣ የልፋት ውጤት በዛሬው እለት በደስታ እየተገለጸ ይገኛል።

ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ጥብቅ ወዳጆች እንኳን ደስ ያላችሁ!

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የቀይ ባህር ኬብል መቆረጡ ተገለጸ።

በእስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ የኃይል መቆራረጥ አስከትሏል መባሉን የኢንተርኔት ተቆጣጣሪው አካል ኔት ብሎክ ገልጿል።

በቀይ ባህር የኃይልና የኢንተርኔት ማስተላለፊያ ላይ ለደረሰው አደጋ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተብሏል።

ነገር ግን ኔት ብሎክ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙት ኬብሎች ጉዳት አጋጥሟቸው ስራ አቁመዋል ሲል አስታውቋል።

በዚህ የኃይል መቆራረጥ ፓኪስታንና ህንድ ተጋላጭ ሆነዋል ተብሏል። #thejapantimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ደቡብ ኮሪያ ዜጎቿን ለመመለስ የቻርተር አውሮፕላን ትልካለች" - ካንግ ሁንሲክ

ደቡብ ኮሪያ የታሰሩት ዜጎቿ እንዲለቀቁ ከስምምነት ላይ መድረሷን አስታወቀች።

በተደረገው ውይይት መሰረት ሁሉም የታሰሩ ዜጎች እንደሚለቀቁ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንታዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ካንግ ሁንሲክ ገልጸዋል።

ኃላፊው "ደቡብ ኮሪያ ዜጎቿን ለመመለስ የቻርተር አውሮፕላን ትልካለች" ብለዋል። "መንግስት ሁሉንም ዝግጅቶች አጠናቋል" ሲሉም ተናግረዋል።  

አሜሪካ በሀዩንዳይ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሚሰሩ ከ300 የሚበልጡ የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን አውላለች። #npr

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#ዛይወረዳ

ሰሞኑን በጸጥታ አካላት ታሰሩ የተባሉ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ሰባቱም አመራሮች ዛሬ ምሽት መፈታታቸውን ፓርቲው ገልጾልናል።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የመከላከያ ቢሮ ስያሜን ወደ "የአሜሪካ የጦር ቢሮ" ሊቀይሩ ነው ተባለ።

ትራምፕ አዲሱን ስያሜ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ አንድ ከፍተኛ የዋይትሃውስ ባለስልጣን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ የመስሪያ ቤቱን ስያሜ ለመቀየር የወሰኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ አልተገለጸም።

ውሳኔውን የፔንታጎን ኃላፊ ፔቴ ሄግሴት ያስፈጽማሉ ተብሏል። #thejapantimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ድምፅ በመሆናችን ኩራት ይሰማናል" - ስፔን

"የስፔን ባለሥልጣናት ተቃዋሚዎች አደባባይ እንዲወጡ እያበረታቱ ነው" - እስራኤል


በስፔን ቩዌልታ ከተማ እስራኤልን የሚያወግዙና የጋዛ ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቁ ሰልፎች ተካሂደዋል።

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ "ድምፅ በመሆናችን ኩራት ይሰማናል" ብለዋል። "አለማቀፍ ማህበረሰብ የሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር እንድነሳ መልዕክት አስተላልፈናል" ሲሉም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል እስራኤል የስፔንን ጠቅላይ ሚኒስትር "ክብር የሌላቸው" ስትል ወቅሳለች።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር "የስፔን ባለሥልጣናት ተቃዋሚዎች አደባባይ እንዲወጡ እያበረታቱ ነው" በማለት ወንጅለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝን "መርህ አልባ መሪ ናቸው" ሲሉ ወርፈዋቸዋል።

ሁለቱ ሀገራት በጋዛ ጦርነት ድፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ከሻከረ ወራት ተቆጥረዋል። 
#thenatiinal

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ብዛት ያላቸው የሶማሊ ወታደሮች ተማርከዋል" - አልሸባብ

"ከ60 በላይ የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፤ ከ50 በላይ ደግሞ ቆስለዋል" - የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር

አልሸባብ የሶማሊያ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረሱ ተነግሯል። ከአልቃይዳ ጋር ትስስር እንዳለው የሚነገርለት ቡድኑ "ብዛት ያላቸው የሶማሊ ወታደሮች ተማርከዋል" ሲል አስታውቋል።

ቡድኑ በኬልደር ክልል በኀጸመው ጥቃት ተሽከርካሪዎችንና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን "ዘርፏል" ተብሏል።

በአልሸባብ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ የሶማሊያ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አብድ ፋሬይ እንደሚገኝበት የፌዴራል ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

አልሸባብ ካሁን በፊት በመንግሥት ስር የነበረችውን የካልዴር ግዛት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት "ተቆጣጥሯል" ተብሏል።

የሶማሊያ ጦር በተቃራኒው የአልሸባብን ጥቃት በመመከት 60 ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ጦሩ ከአካባቢው ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአልሸባብ ታጣቂዎች በኤልዴር አውራጃ የከፈቱትን ጥቃት መመከት መቻሉን የሶማሊያ መከላከያ ሚንስቴር አሳውቋል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አህመድ ሞዓሊም ፊቂ፣ "ከ60 በላይ የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፤ ከ50 በላይ ደግሞ ቆስለዋል" ብለዋል፡፡

በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ዳዱላህ እና ሳቢር የተባሉ ሁለት ከፍተኛ የአልሸባብ መሪዎች ይገኙበታል ያሉት ሚኒስትሩ ታጣቂዎቹ የሞቱ አባላቶቻቸውን አስከሬኖች ትተው ለማፈግፈግ መገደዳቸውን አመልክተዋል። 
#suna #horseedmedia

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሱሽላ ካርኪ የኔፓል የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

ካርኪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በይፋ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የሀገሪቱ ፓርላማ ፈርሶ በመጋቢት 2026 ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ገደብ ተቆርጧል ተብሏል።

ከካርኪ ሹመት በኋላ ተጥለው የነበሩ የሰዓት እላፊ ገደቦች እንዲነሱ መወሰኑ ተገልጿል።

የቀድሞዋ ከፍተኛ ዳኛ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተመላክቷል። #arabnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በሩሲያ በሬክተር ስኬል 7.4 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

በካምቻትካ ከተማ ከተማ የተከሰተው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ 39 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለው የአሜሪካ ጂዖሎጂካል ሰርቬይ (USGS) አስታውቋል።

በዚህ ከተማ ተመሳሳይ አደጋ ሲከሰት ከጥር ወር ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። 

በሰዎችና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን የተባለ ነገር የለም። #telegraph

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ራችማንድራ ፓደል የኔፓል የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል። ፓደል፣ "የተቃዋሚዎችን ጥያቄ ለመመለስ ሁሉንም ጥረቶች እያደረግን ነው" ብለዋል።

"ሁሉም ወገኖች ነገሮች እንደሚስተካከሉ በዚህ ሊተማመኑ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል።

በነበረው ተቃውሞ 34 ሰዎች መሞታቸውንና 1,368 ሰዎች መጎዳታቸውን ፕሬዚደንቱ አስታውሰዋል።

በግርግሩ 14 ሺሕ 307 እስረኞች ማምለጣቸውን የኔፓል ፖሊስ ቃል አቀባይ ቢኖድ ጊማየር አስታውቀዋል።   #yenisafaq

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"አሁን ሳስበው ኔታንያሁ ታጋቾች ይለቀቃሉ የሚለውን ተስፋ ገድለውታል" - ጠቅላይ ሚኒስትር አልጣሂ

ኳታር እስራኤላውያን ታጋቾች ላለመለቀቃቸው እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች።

የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ አብዱረህማን አልጣሂ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ መንግስት "አሳፋሪ ድርጊት እየፈጸመ ነው" ሲሉ ከሰዋል።

"ከታጋች ቤተሰቦች ጋር አውርቻለሁ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ሁሉም ቤተሰቦቻቸው እንዲፈቱ ይፈልጋሉ" ብለዋል።

አልጣሂ፣ "አሁን ሳስበው ኔታንያሁ ታጋቾች ይለቀቃሉ የሚለውን ተስፋ ገድለውታል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ሁሉም ታጋቾች እስራኤል ውስጥ ነው ያሉት" ሲሉም ጠቁመዋል

እስራኤል ከሶስት ቀን በፊት በዶሃ ላይ የፈጸመችውን ጥቃትም አውግዘዋል። #thewashingtontimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሰባስቲያን ላኮርኑ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማክሮን ትናንት ከኃላፊነታቸው በተነሱት ፍራንኮስ ባዮሩ ምትክ በዛሬው እለት ላኮርኑን  ሹመዋል ተብሏል።

የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት በኤሊሴ ቤተ መንግሥት ተካሂዷል። ላኮርኑ ካሁን በፊት የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

በፈረንሳይ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ አምስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ወደ ስልጣን መጥተዋል። #anadoluagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ፖላንድ የሩሲያ ሰው አልባ አራት አውሮፕላሮችን መትታ ጣለች።

ዋርሳው የሞስኮ ጦር የአየር ክልሏን እንደጣሰባት ገልፃለች። የሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ተመትተው የወደቁት በኔቶ እገዛ እንደሆ አስታውቃለች። 

ሩሲያ በጉዳዩ ላይ የሰጠችው ምላሽም ይሁን ማስተባበያ የለም ተብሏል። #bowenisland

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የኔፖል ጠቅላይ ሚኒስትር ካድጋ ፕራሳድ ኦሊ ስልጣናቸውን ለቀቁ።

ኦሊ በሚመሯት ሀገር የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ከስልጣን የለቀቁት ተብሏል።

በኔፖል አሳሳቢ የተባለውን የሙስና መንሰራፋት በመቃወም ባለፉት ሶስት ቀናት ሀገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄድ ቆይቷል። #foxnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የፈረንሳይ መንግስት ፈረሰ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንኮይስ ባዮሩ ስልጣን ለቀዋል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ስልጣን የለቀቁት የመተማመኛ ድምፅ ባለማግኘታቸው እንደሆነ ተገልጿል። ህግ አውጪዎች ባደረጉት ምርጫ ከ364 ድምፅ ማግኘት የቻሉት 194 ብቻ ነው ተብሏል።  

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግስታቸውን አፍርሰው እንደ አዲስ የሚያዋቅሩ ይሆናል። #anadoluagency

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ሁለት ፍልስጤማዊ በኢየሩሳሌም ባደረሱት ጥቃት 6 እስራኤላውያን ተገደሉ።

የፍልስጤም ዜግነት ያላቸው ታጣቂዎች በአውቶቡስ መናሀሪያ ላይ ተኩስ የፈፀሙ ሲሆን ከሟቾቹ በተጨማሪ 12 ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ጥቃት አድራሾቹ በስፍራው በነበረ አንድ የእስራኤል ወታደር ወድያውኑ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል።#pbs

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ለመልቀቅ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሺባ

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺገሩ ኢሺባ ስልጣን ለቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገዥው ሊበራል ድሞክራቲክ ፖርቲ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ኢሺባ፣ "ከዚህ በላይ በኃላፊነት መቆየት እንደሌለብኝ ተረድቻለሁ" ብለዋል።

"ለመልቀቅ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ነው ያሉት። ይሁን እንጂ ኢሺባ ተተኪያቸው እስከሚረከባቸው ድረስ በሀላፊነት ይቆያሉ ተብሏል።

ሺገሩ ኢሺባ በጥቅምት 2024 ነበር ወደ ስልጣን የመጡት። #thestraitstimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ ከ300 የሚበልጡ የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋለች።

የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ቢሮ ህገወጥ ናቸው ያላቸውን ከ300 የሚበልጡ የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

እነዚህ ዜጎች ሀዩንዳይ እና ኤል ጂ በተባሉት የደቡብ ኮሪያ ካምፓኒዎች የሚሰሩ እንደሆኑ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም ደቡብ ኮሪያ በአሜሪካ የታሰሩ ዜጎቿን ለማስለቀቅ እንደምትሰራ አስታወቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾ ህዩን ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

"ዜጎቻችን እንዲለቀቁ የቻልነውን ሁሉ እንሞክራለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "በጣም ተሰምቶኛል፣ ዜጎቻችንን የማስለቀቅ ከባድ ኃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል" ብለዋል። #asiaone

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia #Education

ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሞባይል ስልክ ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት ተከልክሏል" ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል ነው ብሏል።

የ2018 ዓ/ም ት/ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ/ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ሲልም ገልጿል። መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#ዛይወረዳ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የጉምዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) በካማሽ ዞን ዛይ ወረዳ የሚገኙ ሰባት አመራሮች ታስረውብኛል አለ።

እስራቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ያለው ፓርቲው የክልሉ አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ አሳስቧል።

@ThiqahEth

Читать полностью…
Subscribe to a channel