thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

"ከ200 የሚበልጡ የህክምና ባለሙያዎች ተገድለዋል። 507 ባለሙያዎች ሲቆስሉ፣ 59 ጠፍተዋል" - ሪፖርት

በሱዳን ከ2023 ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች ህይወት ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) ገልጿል።

ጥምረቱ ባወጣው ሪፖርት "ከ2023 ጀምሮ ቢያንስ 234 የህክምና ባለሙያዎች ተገድለዋል፣ 73 የሚደርሱት ዳርፉር ውስጥ በአር ኤስ ኤፍ ታግተዋል" ብሏል።

ሪፖርቱ አክሎ፣ "507 ባለሙያዎች ሲቆስሉ፣ 59ኙ ጠፍተዋል" ነው ያለው።

ጥምረቱ ባወጣው ሪፖርት አለማቀፍ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ ድርጅቶች የህክምና ባለሙያዎች ደህንነት እንድጠብቅ ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቋል።

በጦርነት ውስጥ የሚገኙ ሀይሎች ግጭቱን እንዲያቆሙ ያሳሰበው ቡድኑ፣ የታገቱት እንዲለቀቁ እና የጠፉት መዳረሻቸው እንዲታወቅ አሳስቧል። #aa

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቤልጅየም አርሶአደሮች የአውሮፓ ህብረት የፈጸመውን ስምምነት ተቃወሙ።

የአውሮፓ ህብረት ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር " የግብርና ምርት ስምምነት(EU Mercosur)" ፈጽሟል።

በቤልጅየም ዋና ከተማ ብራሰልስ የተሰባሰቡት አርሶአደሮቹ ስምምነቱን "ኢፍትሃዊ ውድድርን ይፈጥራል፣ የአውሮፓ ግብርናን ይጎዳል" ሲሉ ተቃውመዋል።

አርሶአደሮቹ የእርሻ ትራክተሮችን ይዘው በመውጣት ወደ ብራሰልስ የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል።

የአውሮፓ አርሶአደሮች ፌደሬሽን 10,000 ተቃዋሚዎች መሳተፋቸውን አስታውቋል።   #aa

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"እስራኤል በታሪኳ ትልቁን የነዳጅ ሽያጭ ስምምነት ፈጽማለች" - ኔታንያሁ

እስራኤል እና ኢራን የ35 ቢሊየን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ "ለግብጽ የጋዝ አቅርቦት ለማሟላት ስምምነት ላይ ተደርሷል" ብለዋል።

"እስራኤል በታሪኳ ትልቁን የነዳጅ ሽያጭ ስምምነት ፈፅማለች" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የቀጠናው የሀይል ምንጭ በመሆን ለቀጠናው መረጋጋት የበኩላችንን ሚና እንጫወታለን" ሲሉ ገልጸዋል።

"እስራኤል እስከ 2040 የነዳጅ አቅርቦቱን ለማሟላት ዝግጁ መሆኗን ለመግለጽ እወዳለሁ" ብለዋል ኔታንያሁ።

የተፈጥሮ ነዳጁ 600 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ያመነጫል ተብሎ ከሚጠበቀው የሌቪያታን የነዳጅ ማመንጫ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

እስራኤል እና ግብፅ ባሳለፍነው ነሐሴ ተመሳሳይ የኢንቨስትመንት ስምምነት ቢፈራረሙም በጋዛው ጦርነት ሳቢያ በሳምንታት ውስጥ ፈርሷል ተብሏል። #theindependent

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በሱዳን ከ100 የሚበልጡ ንጹሐን በድሮን ጥቃት ተገደሉ።

በኮርዶፋ ግዛት የተፈጸመው ይህ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል።

የሀገሪቱ ጦር ለተፈፀመው የድሮን ጥቃት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉን ተጠያቂ ቢያደርግም፣ አማፂ ሀይሉ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ ተገልጿል።

ጥቃቱ በህፃናት ትምህርትቤት እና በሆስፒታል ላይ በመከሰቱ የአደጋው መጠን ከፍተኛ ሊሆን ችሏል ተብሏል። #aljazeera

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቦትስዋና ወጣቶች ለዩክሬን ጦርነት እየተመለመሉ እንደሚላኩ ተገለጸ።

ብዛት ያላቸው የሀገሪቱ ወጣቶች በስራ ቅጥር እና በስልጠና ሰበብ ወደ ሩሲያ መላካቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

የቦትስዋና መንግስት ወጣቶችን እየመለመሉ በሚልኩ ኤጄንሲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ዜጎች ከሀሰተኛ መረጃ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት፣ የስራ አጥነት ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልጿል። #outlook

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቀድሞው የኮንጎ "አማፂ ቡድን" መሪ ሮጀር ሉምባላ የ30 አመት እስር ተፈረደባቸው።

ሉምባላ ከ2002 እስከ 2003 በምስራቅ ኮንጎ ለተፈጸመው ወንጀል በፈረንሳይ ፍርድቤት እስር ተፈርዶባቸዋል።

ሁለተኛው የኮንጎ ጦርነት እየተባለ በሚጠራው ዘመን በጎረቤት ኡጋንዳ እየታገዘ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸመ ተገልጿል።

ሉምባላ "የፈረንሳይ ፍትህ የእኔን ጉዳይ የመመልከት ስልጣን የለውም" በማለት ፍርድቤት ሳይቀርብ ቆይቷል። #bbc

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10 ሺሕ በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" - ድርጅቱ

ተመድ የኤርትራ መንግስት እስረኞችን መልቀቁን በበጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።

ድርጅቱ፣ ይሁን እንጅ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲፈቱም ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።

ኤርትራ በቅርቡ ለ18 አመት በእስር ላይ ለነበሩ 13 ዜጎች ምህረት አድርጋለች ተብሏል።

እርምጃውን "አበረታች" ሲል የገለፀው የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ(OHCHR) "አሁንም በእስር ላይ ያሉ ከ10,000 በላይ የግፍ እስረኞች እንዲለቀቁ ጫና ማሳደር ይገባል" ብሏል።

"እስር ላይ ከሚገኙት መካከል ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሀይማኖት አባቶችና ተማሪዎች ይገኙበታል" ሲል አስታውቋል። #unnews #As

@ThiqshEth

Читать полностью…

THIQAH

የአሜሪካ ጦር በፓስፊክ ውቅያኖስ በፈጸመው ጥቃት የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።

ሦስት ጀልባዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ያረጋገጠው የአሜሪካ የደቡብ ኮማንድ "ምክንያቱም አደገኛ እፅ እያዘዋወሩ ነበር" ብሏል።

ጦሩ "የእፅ አሸባሪዎችም እርምጃ ተወስዶባቸዋል" በማለት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች የወንጀል ተባባሪ እንጂ ንጹሐን አለመሆናቸውን አስታውቋል።

ዘመቻው በአሜሪካ ጦር ዋና ኃላፊ ፔት ሄጌት ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ተገልጿል።

ስለደረሰው ጥቃት ገለልተኛ ሪፖርት ማግኘት አልተቻለም። #yenisafaq

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ብሌስ ማትረወሊ የዩናይትድ ኪንግደም የስለላ ድርጅት (M16) ዋና ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።

ማትረወሊ ተቋሙን ለመምራት የተሾሙ የመጀመሪዋ ሴት ዳይሬክተር መሆናቸው ተገልጿል።

አዲሷ ኃላፊ የምዕራቡ ዲሞክራሲ ላይ ስጋት ላሏቸው የውጭ አካላት ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።

ብሌስ ማትረወሊ ሪቻርድ ሞሬን በመተካት ነው የሀገሪቱ የውጭ የስለላ ድርጅት ኤም 16 ለመምራት ሀላፊነት የተረከቡት። #politico

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ጆዜ አንቶኒዮ የቺሊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

የቀኝ ዘመም ሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይዋ አንቶኒ በምርጫው 58.17% ድምፅ አግኝተዋል።

ተፎካካሪዋ የቀድሞው የሰራተኛ ሚኒስትር ጃራ ጎት በበኩላቸው፣ 41.8 ድምፅ አግኝተዋል።  #anadoluagency

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በአውስትራሊያ በጀዊሽ ማህበረሰብ በዓል ላይ በተፈጸመ ጥቃት 11 ሰዎች ሲገደሉ፣ 29 ቆሰሉ።

በቦንዲ ቢች ከተማ ሲከበር በነበረው የሀኑካህ በዓል ላይ ሁለት ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኦፊሰር ማል ላንዮን ገልጸዋል።

ጥቃቱ የጸረሴማዊነት አካል ነው ቢባልም የአውስትራሊያ መንግሥት "የሽብር ድርጊት" ሲል ፈርጆታል።

ከጥቃት አድራሾቹ አንዱ በተወሰደበት እርምጃ ህይወቱ ሲያልፍ፣ ሌላኛው በቁጥጥር ስር መዋሉን ኦፊሰሩ ተናግረዋል። #rns

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" - ዶናልድ ትራምፕ

በሶሪያ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው ተነግሯል።

አይኤስአይኤስ (ISIS) በማዕከላዊ ሶሪያ ባደረሰው ጥቃት ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች እና አስተርጓሚ የነበረ የሀገሪቱ ዜጋ ሲገደሉ ሌሎች ሶስት ወታደሮች ተጎድለዋል።

ጥቃቱን ያደረሰው የቡድኑ አባል የነበረ ግለሰብ ፓልምይራ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በፈጸመው ጥቃት ነው። 

ስለክስተቱ አስተያየታቸውን የሰጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥቃት የደረሰበት አደገኛ ቦታ በሶሪያ መንግስት ስር አይደለም" ብለዋል።

"የሶርያ ፕሬዚዳንት አልሻራም ሀዘኑን ገልጿል" ያሉ ሲሆን "በወታደሮቻችን ላይ ለተፈፀመው ጥቃት የበቀል እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም አክለዋል። #euronews

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" - መንግስት

የማይናማር መንግስት "ከ30 በላይ ንጹሐን" የቀጠፈውን ጥቃት አስተባብሏል።

የወቅቱ የማይናማር መንግስት በራኪን ግዛት በሚገኘው ሆስፒታል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጦ፣ ነገር ግን "ጥቃቱ ንጹሐን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ አልነበረም" ብሏል።

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ጁንታ "የሞቱት ንጹሐን አይደሉም፣ የአሸባሪው ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው" ሲል የደረሰበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ "የራኪን ግዛት ከ2024 ጀምሮ በአርካን አማፂ ኃይሎች (AA) ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው፣ ሆስፒታሉን የሚገለገሉበትም የታጠቁ ሀይሎች ናቸው" ነው ያለው።

ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በተፈጸመው የአየር ላይ ጥቃት 33 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ፣ 76 መቁሰላቸውና 27 የሚሆኑት በጽኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። #anadoluagency

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ከ30 የሚበልጡ የየመን ወታደሮች በአማፂ ሀይሎች ተገደሉ።

ከሟቾቹ በተጨማሪ 45 ወታደሮች መቁሰላቸውን አለማቀፍ እውቅና የተሰጠው የሊቢያ መንግስት አስታውቋል።

የሀገሪቱ መንግስት ለደረሰው ጥቃት በሀይደራባት ከተማ የሚንቀሳቀሱትን የኤስ ቲ ሲ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል ተብሏል። #reuters

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

አማራ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 35.8 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለጸ

ባንኩ በተያያዘው 2018 በጀት ዓመት በ5 ወራት ብቻ ከ 3.55 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እስከ ህዳር 2018 35.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ እድገቱም 82 በመቶ መሆኑንም አስረድቷል።

ካፒታል ጋዜጣ ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት፤ ባንኩ ከታክስ በፊት 1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል። 591,884 አዳዲስ የደንበኞችን ሒሳብ በመክፈት አጠቃላይ የደንበኞችን ቁጥር 2.68 ሚሊዮን አድርሷል።

የውጭ ምንዛሪ በማሰባሰብ ረገድ፤ 76.58 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ313 በመቶ ብልጫ አለው የተባለ ሲሆን፣ ባንኩ ከተመሰረተ ጀምሮ ያቀረበው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያ ወደ 31.3 ቢሊዮን ብር በማሳደግ በ53.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። #Capital

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የአውሮፓ ሀገራት በአርሶአደሮች ተቃውሞ ስለገጠመው የግብርና ምርት ስምምነት (EU Mercousur) ምን ምላሽ ሰጡ?

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "የአውሮፓ ህብረት በአባል ሀገራቱ አርሶአደሮች ጥቅም ላይ መደራደር የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።

ጣሊያን በበኩሏ የስምምነቱ ፊርማ "የአርሶአደሮችን ደህንነት የሚያስጠብቁ አስተማማኝ ሁኔታዎች" እስኪሟሉ ድረስ እንዲዘገይ ጠይቃለች ተብሏል።

ጀርመን እና ስፔን "የአውሮፓን የወጪ ገበያ ያሳድገዋል" በማለት የስምምነቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አርሶአደሮች አሁንም በአውሮፓ ፓርላማ አጠገብ በመገኘት ድንች እና ቲማቲም መንገድ ላይ በመጣል፣ እንጨት በማቃጠል፣ 150 የእርሻ ትራክተሮችን በማጓጓዝ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ተብሏል። #anadoluagency

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቬኔዙዌላን የነዳጅ ታንከሮች ላይ እገዳ ጣሉ።

ፕሬዝዳንቱ እገዳውን አስመለክቶ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ "ቬንዙዌላ እስከዛሬ በደቡብ አሜሪካ ታሪክ  ታይቶ በማይታወቅ ጦር ተከባለች" ሲሉ አስፍረዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ሁሉንም ነዳጅ፣ መሬት እና ካሁን በፊት ከእኛ የሰረቋቸውን ሁሉንም ንብረቶች ለዩናይትድስቴትስ ካልመለሱ ከዚህም በላይ አይተውትይጨመራል፣  በማያውቁት ሁኔታ ይደነግጣሉ" በማለት ገልጸዋል።

አክለው "ህጋዊ ያልሆነው የማዱሮ መንግስት ከተሰረቁ ጣቢያዎች የመነጩ ነዳጆችን እየተጠቀመ ራሳቸውን፣ የእፅ አሸባሪዎችን፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ ግድያ እና እገታን እየደገፈበት ነው" ብለዋል።

"የእኛን ንብረት በመዝረፍና በሽብር፣ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሌሎችም ወንጀሎች የቬኔዙዌላ መንግስት በውጭ የአሸባሪ ድርጅቶች ውስጥ ተካቷል" ሲሉ አስታውቀዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ አስተያየታቸው "በመሆኑም ዛሬ ሁሉም ከቬንዙዌላ የሚገቡ እና የሚወጡ የነዳጅ ታንከሮች እንድቆሙ እና ሙሉ ማዕቀብ እንድጣልባቸው አዝዣለሁ" ነው ያሉት።

"ወንጀለኛው የማዱሮ አገዛዝ በደካማው የባይደን አስተዳደር ዘመን ወደአሜሪካ የላካቸው በፍጥነት ወደ ቬንዙዌላ እየተመለሱ ነው" በማለት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ መቋረጡን አስረድተዋል።

"አሜሪካ ወንጀለኞችን፣ አሸባሪዎችን ወይም ሌሎች ሀገራትን ለዘረፋ፣ ለስጋት እና ለየትኛውም ጥፋት አትፈቅድም" ያሉት ትራምፕ "በተመሳሳይ መልኩ ጥፋተኛ አገዛዝ ነዳጃችንን፣ መሬታችንን እና ሌሎች ሀብታችንን እንዲወስድብን አንፈቅድም፣ ሁሉም ወደአሜሪካ መመለስ አለባቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የአሜሪካ ሴኔት ለ2026 የመከላከያ በጀት 901 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ።

ሴኔቱ በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የመከላከያ በጀት አፅድቋል።

ከበጀቱ ውስጥ 4 በመቶው ለዩክሬን የሚሰጥ ድጋፍ ነው። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዋጁን በፊርማቸው ህግ አድርገው ያፀድቁታል ተብሏል። #samaatv

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሀገራት ብዛት 39 ደረሰ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ20 ሀገራት ላይ የጣሉትን የጉዞ እገዳ አራዝመዋል።

ከሀገራቱ በተጨማሪ የፍልስጤም ባለስልጣናትም የጉዞ ክልከላው እንደሚመለከታቸው ተናግረዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ሌሎች አምስት ሀገራትን ሙሉ በሙሉ ያገደ ሲሆን ተጨማሪ 15 ሀገራት ከፊል እገዳ እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

በዚሁ ውሳኔ መሰረት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሀገራት ጠቅላላ ብዛት 39 ደርሷል።

ሙሉ በሙሉ ከታገዱት ውስጥ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ የመን፣ ኢራ፣ ማይናማር ይገኙበታል።

አዲስ ሙሉ እገዳ የተጣለባቸው አምስት ሀገራት ደግሞ ሶርያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማሊ እና ኒጀር ናቸው።

ከፊል እገዳ ከተጣለባቸው 15 ሀገራት ውስጥ ደግሞ አንጎላ፣ ቤኒን እና ሴኔጋል ተካተዋል። #euronews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ለመረጃ መንታፊዎች የሚያጋልጡ ጎጅ የስልክ አጠቃቀሞች  ምንድን ናቸው?

-ያልተረጋገጡ አፕሊኬሽኖችን በስልካችን መጫን፦ ብዙዎቻችን ከዋናው የሶፍትዌር  መደብር (Play Store/App Store) ውጭ ያሉ አፕሊኬሽኖች በተለያዩ ድረ-ገጾች አማካኝነት እንጭናለን። እነዚህ አፕሊኬሽኖች ስልካችንን ለመሰለል/መረጃ ለመሰረቅ የተዘጋጁ ቫይረሶችን ሊይዙ ይችላሉ።

-የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን (Updates) አለማድረግ፦ የስልክ አምራቾች በየጊዜው የደህንነት ማሻሻያዎችን ይለቃሉ። እነዚህን ማሻሻያዎች ችላ ማለት ጠላፊዎች በድሮው የሶፍትዌር ስሪት ያሉ ክፍተቶችን ተጠቅመው ወደስልካችን ሰርገው እንዲገቡ ያጋልጣል።

-ለሁሉም አፕሊኬሽኖች "ፈቃድ"  መስጠት፦ አንድ አፕሊኬሽን ስንጭን "Allow" የሚል ምርጫ ይጠይቀናል። ለአንድ ፎቶ ማቀናበሪያ አፕሊኬሽን ስልክ ቁጥሮችን፣ ያሉበትን ቦታ እንዲያይ ፈቃድ መስጠት አላስፈላጊ እና ለመረጃ ስርቆት ያጋልጣል።

-ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የዋይፋይ (Public Wi-Fi) አጠቃቀም፦ ነፃ የዋይፋይ ኔትዎርኮች በቀላሉ ለመጠለፍ የተመቹ ናቸው። በእነዚህ ኔትዎርኮችን ተጠቅመን የባንክ አካውንት መክፈት/ሚስጥራዊ መረጃዎችን መላላክ ከፍተኛ አደጋ አለው።

-አጠራጣሪ ሊንኮችን መክፈት፦ "ሎተሪ ደርሶዎታል"፣ ወይም "ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል" በሚሉ አሳሳች መልዕክቶች ያሉ ሊንኮችን መጫን ስልካችንን ለጠላፊዎች አሳልፎ ይሰጣል።

-ቀላል የይለፍ ቃላትን መጠቀም፦ እንደ "1234"፣ "0000" ወይም የልደት ቀንን የመሳሰሉ በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃላትን መጠቀም ስልካችን በእጃችን ቢሆን እንኳ በሩቅ ሆኖ ለመገመት ለሚሞክር የመረጃ መንታፊ ስራውን ያቀልለታል። #INSA

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ቡርኪናፋሶ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን የናይጄሪያ ወታደሮች አለመልቀቋ ተገለጸ።

11 የሚደርሱ የናይጄሪያ አየር ሀይል አባላት በሲ-130 የጦር ጄት የአየር ላይ ቅኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት በቡርኪናፋሶ ግዛት ውስጥ ማረፋቸው ተገልጿል።

የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት "የአየር ክልሌን ጥሰዋል" በማለት ወታደሮቹን እና የጦር ጄቱን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የቡርኪናፋሶ መንግስት ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ሁለቱ ሀገራት ላለፉት ስድስት ቀናት ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ቢያደርጉም ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። #dw #politicsnigeria

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በሞሮኮ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ37 ሰዎች ህይወት አለፈ።

የሞሮኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር "ድንገተኛ ጎርፍ በአንድ ሌሊት 70 መኖሪያ መንደሮችን እና 10 ተሽከርካሪዎችን አውድሟል" ብሏል።

ሚኒስቴሩ "ትምህርትቤቶች ለሶስት ቀናት ዝግ ሆነዋል" ሲል ገልጿል።

አደጋው የተከሰተው ከዋና ከተማዋ ራባት በ320 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሳፊ ከተማ ነው።

በከተማዋ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ተገልጿል። #hurriyetdailynews

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የናይጄሪያ ፖሊስ 161 ህገወጥ የእፅ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ህገወጥ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎቹ የተያዙት በደልታ ክልል አግቦር ከተማ እንደሆነ ገልጿል።

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ 110 ወንዶች እና 51 ሴቶች መሆናቸውን የደልታ ክልል ፖሊስ ቃል አቀባይ ብራይት እዳፍ ተናግረዋል።

በኢንተለጀንስ በተደገፈው ዘመቻ ብዛት ያላቸው የአደንዛዥ እፆች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከተያዙት ውስጥ የካናዳ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች እንደሚገኙበት ቃል አቀባዩ አብራርተዋል። #dailypost

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ዝምባብዌ የውጭ ሀገራት ዜጎች በታክሲ እና በዳቦ ቤት ስራዎች እንዳይሰማሩ ከለከለች።

14 የስራ ዘርፎች የስራ እድል ለመፍጠር በማሰብ ለሀገር ውሰጥ ዜጎች ቅድሚያ እንድሰጥ ተወስኗል።

ከእነዚህም ውስጥ የፀጉር ቤት፣ የውበት ሳሎን፣ የጥበቃ አገልግሎት፣ የቅጥር ኤጀንሲዎች፣የማስታወቂያ ኤጀንሲዎች፣ የብረታብረት ምርት እና የመድኃኒት ችርቻሮ  ተካተዋል።

ከዚህ ባለፈም በውጭ ዜጎች የበላይነት የተያዘው የኢንዱስትሪ ዘርፍ 75% የሚሆነው በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች እንድንሸጋገር መወሰኑ ተገልጿል።

ዝምባብዌ ከፍተኛ ስራ አጥነት ከሚስተዋልባቸው የአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። #zbc #iol

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"የሁሉም የስፓርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከዛሬ ጀምሮ ተሰርዟል" - አገልግሎቱ

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሁሉም የስፓርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከዛሬ (ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም) ጅምሮ መሰረዙን አስታውቋል።

የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የህዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑንም ገልጿል።

ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ብሏል አገልግሎቱ።

ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ እንዲያቋርጡ አዟል።

ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች  አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ፣ አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ እንደማይቻል አስታውቋል። #ELS

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ በሱዳን የባንግላዴሽ ወታደሮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አወገዘ።

ስድስት የባንግላዴሽ የሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን የገለፀው ድርጅቱ፣ የሟቾችን ማንነት በምስል ይፋ አድርጓል ተብሏል።

የሰላም አስከባሪዎቹ በተልዕኮ ላይ በነበሩበት ወቅት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በፈጸመው የድሮን ጥቃት ተገድለዋል።

ወታደሮቿ የተገደሉባት ባንግላዴሽ ሀዘኗን በመግለፅ፣ ከተመድ ጋር አብራ መስራቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። #aljazeera

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ቤላሩስ ለ123 የፖለቲካ እስረኞች ምህረት አደረገች።

መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው አሜሪካ ቤላሩስ ወደ ውጭ በምትልከው የማዳበሪያ ምርት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተከትሎ ነው።

በይቅርታ ከወጡት መካከል በ2020 የተደረገውን ፀረ መንግስት ተቃውሞ የመራችው ማሪያ ኮላስኒኮቫ እና የሰላም ኖቤል ተሸላሚው አሌስ ቢያሊያትስኪ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

አሜሪካ የፕሬዝዳንት ሉካሽንኮ መንግስት በ2021 ያካሄው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ አይደለም በሚል የቤላሩስ መንግስት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

ፕሬዚዳንት ሉካሽንኮ በዩክሬን ጦርነት ሀገራቸው ለሩሲያ እንደምትወግን በግልጽ ድጋፍ ማሳየታቸው ተገልጿል። #radiofreeeurope #skynews

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በውይይታችን የሀይል እርምጃዎች እንዲቆሙና ንጹሐን ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እንዲቀሩ አሳስቢያለሁ" - ማሌዥያ

ማሌዥያ ካምቦዲያ እና ታይላንድ የገቡበትን ጦርነት እንዲያቆሙ አሳሰበች።

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር የተናጠል የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "በውይይታችን የሀይል እርምጃዎች እንዲቆሙ እና በንጹሐን ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እንዲቀሩ አሳስቢያለሁ" ብለዋል።

ኢብራሂም "በመጪው ማክሰኞ በሚካሄደው የእስያ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እልባት እንዲበጅለት በአጀንዳ መልክ ይነሳል" ሲሉ ጠቁመዋል።

አምስተኛ ቀኑን በያዘው የታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሟቾች ቁጥር 48 ሲደርስ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ማሌዥያ ከወራት በፊት የነበረውን የሁለቱን ሀገራት ግጭት በማስቆም በዋና ከተማዋ ላምፑር የሰላም ስምምነት እንዲፈጾም ማድረጓ ይታወሳል። #straightstimes

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ገዳ ባንክ የሀብት መጠኑን 10 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገለጸ

የባንኩ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ የተካሄደ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ 2024/ 2025 የበጀት ዓመት የስራ ሪፖርቱን አቅርቧል።

በሪፖርቱም ላይ ባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 10.1 ቢልየን ብር መድረሱን ያሳወቀ ሲሆን፣ ይህም የእቅዱን 94 በመቶ ያሳካው ነው። ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃጸር 80.4 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ሁሴን ሀሰን፣ አሁን ላይ ያለው የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 7.1 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸዋል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲወዳደር የ92.5 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ በበጀት ዓመቱ የ4.33 ቢልየን ብር ዝውውር ማድረጉን፣ በአሁኑ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ባለ አክሲዮኖችም 31 ሺህ 518 ማድረሱ ተገልጿል። #TiritaFm

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ በአልሸባብ ላይ የጣለውን ማዕቀብ አራዘመ

የተመድ የፀጥታው ምክርቤት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው "የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን" ላይ የተጣለበትን ማዕቀብ ገምግሟል።

ሁሉም 15ቱ አባላት የምክር ቤቱ አባላት የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል።

አልሸባብ የሶማሊያን መንግስት ለመጣል ላለፉት 16 አመታት ሲታገል ቆይቷል።

ከ2024 ጀምሮ በቡድኑ ላይ ተደጋጋሚ ዘመቻዎችን እንደፈፀመ የገለጸው የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር፣ 220 ጥቃቶችን አድርሶ 868 የሚሊሺያ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። #aa

@ThiqahETH

Читать полностью…
Subscribe to a channel