15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"መካከለኛ ኃይሎች በጋራ መተባበር አለባቸው" - ካናዳ
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ የዓለም ስርዓት ከበፊቱ መቀየሩን ገለጹ።
በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ካርኔይ፣ "በየቀኑ ሃያላን ሀገራት እርስ በርስ በሚላተሙበት ዓለም ውስጥ ነው ያለነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"አሜሪካ መር የዓለም ስርዓት አክትሟል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "መካከለኛ ኃይሎች በጋራ መተባበር አለባቸው" ብለዋል።
"መርህን መሰረት ያደረገው አካሄድ ቀስ በቀስ እየጠፋ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደግሞ፣ ካናዳን በቅርቡ ካቋቋሙት የሰላም ቦርድ ማስወጣታቸውን ገልጸዋል። #telegraph
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ሙሉ እና ተገቢ ካሳ ያስፈልጋል" የአልጄሪያ ፓርላማ
"ለተፈፀመው ሁሉ ይቅርታ" ፕሬዚዳንት ማክሮን
የአልጄሪያ ፓርላማ ፈረንሳይ በቅኝ ግዛት ዘመን የጦር ወንጀል መፈፀሟን ገለጸ።
ፓርላማው ፈረንሳይ ለፈፀመችው ወንጀል ካሳ እንድትከፍል የሚጠይቅ ህግ አፅድቋል ተብሏል።
"የፈረንሳይ የጦር ወንጀሎች" በሚል ያፀደቀው ህግ "አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ደርሷል" ብሏል።
በተጨማሪም "የአልጄሪያ ሀብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ተመዝብሯል" ያለ ሲሆን "ሙሉ እና ተገቢ ካሳ ያስፈልጋል" በማለት አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፈረንሳይ በቅኝ ግዛት ዘመን ወንጀል መፈፀሟን በማመን "ለተፈፀመው ሁሉ ይቅርታ" ሲሉ ጠይቀዋል።
ፈረንሳይ ከ1830-1962 አልጄሪያን በቅኝ ግዛት ማስተዳደሯ ይታወቃል። #trtworld
@ThiqahETH
ኬንያ ከእስራኤል ጋር የስፓይደር አየር መከላከያ ስርዓት ስምምነት መፈጸሟን አስታወቀች።
የጦር መሳሪያ ስምምነቱ 26 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ተገልጿል።
ግዥው የተፈጸመው በረጅም ጊዜ ብድር ሲሆን፣ የተገዛው የአየር መቃወሚያ ሲስተም የኬንያን ጦር የማዘመን ሂደት አካል ነው ተብሏል።
የስፓይደር አየር መቃወሚያ የጦር ጄት፣ ሄሊኮፕተር እና የሰው አልባ አውሮፕላኖችን የማክሸፍ አቅም እንዳለው ተገልጿል። #thejerusalempost
@ThiqahETH
"ጅብ በሰው ልጅ ከሚያደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል አቅሙ ለሌላቸው ህፃናትና አቅመ ደካማ አረጋዊያን ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄና ጥበቃ ማድረግ ያድርግ" - ፓሊስ
"ከመስከረም ጀምሮ አስከ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ 11 ሰዎች በጅብ ተበልተው ህይወታቸውን አጥተዋል" !
በዘንድሮው በጀት አመት ከመስከረም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ብቻ 11 ሰዎች በጅብ ተበልተው ህይወታቸውን እንዳጡ፣ ዘጠኙም ህፃናት እንደሆኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በላይኛው ጡቃ ቀበሌ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6:30 ወደ አንድ አርሶአደር መኖሪያ ቤት ውስጥ ዘልቆ በገባ ጅብ የተነከሰችው የ3 ዓመቷ ታዳጊ ህይወቷ ማለፉንም ገልጿል።
የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ርብርብ የህፃኗን በድን ገላ ከጅብ አፍ ማስጣል ተችሏል ያለው ፖሊስ፣ ህብረተሰቡ ጥቃት አድራሹን ጅብ የገባበት ገብቶ አድኖ ገድሏል ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ አዛውንት እናት በጅብ ተበልተዋል።
ጅብ በሰው ልጅ ከሚያደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል አቅሙ ለሌላቸው ህፃናትና አቅመ ደካማ አረጋዊያን ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄና ጥበቃ ማድረግ እንዳለበት ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
@ThiqahEth
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የሰላም እቅዳቸውን ለተመድ አቀረቡ።
የሱዳን የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል እንድሪስ ባቀረቡት የሰላም እቅድ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ የፀጥታው ምክርቤት መጠየቃቸው ተገልጿል።
አሜሪካ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአረብ ሊግ በበኩላቸው አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል ተብሏል።
ሚያዝያ 2023 የጀመረው የሱዳን የርስበርስ ጦርነት ሶስት አመት ሊሞላው ሶስት ወራቶች ብቻ ቀርተውታል። #ashraqalawusat
@ThiqahEth
የሩሲያ ከፍተኛ ፍርድቤት በ2025 በስለላ ወንጀል ከ460 በላይ ሰዎች ፍርድ ሰጠ።
ይህም በአንድ አመት ውስጥ በተመሳሳይ ወንጀል ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት የፍርድ ውሳኔ ነው።
ሩሲያ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለውጭ ሀገራት በመሰለል ወንጀል ከ1000 በላይ ሰዎች ላይ ፍርድ መስጠቷ ተገልጿል።
በዚህ ወንጀል ከተያዙት ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ወይም 564ቱ የዩክሬን ዜግነት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ተጠርጣሪዎቹ ከ17 እስከ 80 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። #meduze
@ThiqahEth
"ካምቦዲያ እና ታይላንድ በማሌዥያ የፈጸሙትን የሰላም ስምምነት ማክበር አለባቸው" አሜሪካ
አሜሪካ ካምቦዲያ እና ታይላንድ ግጭት እንዲያቆሙ ጠየቀች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፣ "ካምቦዲያ እና ታይላንድ በማሌዥያ የፈጸሙትን የሰላም ስምምነት ማክበር አለባቸው" ብሏል።
"አወዛጋቢ የድንበር ጉዳዮች በንግግር እንዲፈቱ፣ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከድንበር አካባቢ እንዲርቁ እና የንጹሐን ሞት እንዲያበቃ ቁርጠኝነት ማሳየት አለባቸው" ሲል አሳስቧል።
የካምቦዲያ እና ታይላንድ ውዝግብን ለመፍታት የደቡብ ኤዥያ ሀገራት ስብስብ (ASEAN) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሏል።
ቀናት ባስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከ50 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ቆስለዋል። #bernama
@ThiqahETH
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬና ነገ ወደ ደሴ ከተማ በረራ ማቋረጡን አስውቋል።
አየር መንገዱ በደሴ እና አካባቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል።
ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንዲሚያሳውቅ ገልጾ፣ በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል።
@ThiqahETH
"ከ100 በላይ ንጹሐን ታፍነው ወደ ወረዳው ከተማ በ10 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ተወስደዋል" - ፓርቲው
እናት ፓርቲ በምሥራቅ ወለጋ "ከ100 በላይ ንጹሐን ታፍነው" መወሰዳቸውን ገልጾ፣ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ እንዲያስመልሷቸው ጠየቀ።
ፓርቲው ዛሬ ባጋራው መረጃ፣ "ታኅሣስ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ከ100 በላይ ንጹሐን ታፍነው ወደ ወረዳው ከተማ በ10 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ተወስደዋል" ብሏል።
"'ህጻናት፣ አቅመ ደካሞችና እመጫቶች ጭምር ይገኙበታል። ይህ የሆነው በክልሉ የፀጥታ ኃይል ነው' የሚሉት ነዋሪዎች፤ 'አካባቢው ከሳምንት በላይ ተከቧል፤ ህዝቡን እየጫኑ ይወስዳሉ ተው እና ለምን የሚለውን በድብደባና በተኩስ ይገድላሉ፤ ነገ ምን እንደሚገጥመን አናውቅም'" ማለታቸውን ገልጿል።
ፓርቲው፣ በዚህ ጉዳይ ከሳምንት በፊት የማስጠንቀቂያና የነዋሪውን የጭንቅ ድረሱልን ጥሪ ማውጣቱን አስታውሶ፣ "በመንግስታዊ ወዋቅር ንጹሐንን ማንገላታት እንዲቆም፣ ታፍነው የተወሰዱትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደቤታቸው እንዲመለሱ" ሲል ጠይቋል።
@ThiqahETH
#Gambella #EHRC
ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የሰዎች ህይወት መጥፋቱን በማስታወቅ፣ ተጎጂዎች ካሳና ህክምና እንዲያገኙ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰማኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ አሰባሰብኩት ባለው መረጃ በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ገልጿል።
በዚህም የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችንና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት መቋረጡን ተገንዝቤያለሁ ብሏል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የሰላም መደፍረስ በፍጥነት በማስቆም በሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ የንብረት፣ የሥራና ሌሎች ሰብዓዊ መብቶች ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግም አሳስቧል።
በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የፌዴራሉና የክልሉ መንግስታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ብሏል።
በአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖትና የማኅረሰብ መሪዎችን በማሳተፍ ውይይቶችና ዕርቆች እንዲካሄዱ፣ ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻዎች ጋር በትብብር በመሥራት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ሕክምናና ካሳ እንዲያገኙ ጠይቋል። #EHRC
(የኮሚሽኑ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@ThiqahETH
ዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ሁለት የሩሲያ የነዳጅ ታንከሮች መውደማቸው ተገለጸ።
የዩክሬን ጦር ጥቃቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አለማቀፍ ማዕቀብ የተጣለባቸው የነዳጅ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
የደረሰው ጥቃት መስተጓጎል እንደማይፈጥር የገለፁት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፣ የሩሲያ ጦር የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መፈጸሙን ተናግረዋል። #skynews
@ThiqahETH
የአውሮፓ ህብረት አወዛጋቢውን ስምምነት እስከ ጥር ወር ማራዘሙን ገለጸ።
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን የአውሮፓ ህብረት ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር የፈጸመውን የግብርና ስምምነት (EU Mercosur) ለቀጣዩ ወር መራዘሙን ገልጸዋል።
ቮንደርሊን ስምምነቱን ለማፅደቅ ለነገ እሁድ ቀጠሮ ቢያዝም፣ አርሶ አደሮች ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ለሌላ ጊዜ መለወጡን ተናግረዋል። #euractiv
@ThiqahETH
በቻይና የህዝብ ቁጥር በ2 ሚሊየን መቀነሱ ተገለጸ።
የፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ መንግስት በ2026 በሀገሪቱ የውልደት መጠንን ለመጨር የሚያግዝ መመሪያ ያወጣል ተብሎ ይጠቃል።
ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መቀነስ የገጠማት ቻይና፣ ከጥር 2025 ጀምሮ ለሚወለዱ ህፃናት 3600 ዩዋን ወይም የ500 ዶላር የወሊድ ማበረታቻ ስጦታ ማቅረብ ጀምራለች።
ህፃናት ሶስት አመት እስኪሞላቸው ድረስ የገንዘብ ድጎማው እንደማይቋረጥ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም በቅድመ መደበኛ ትምህርት ለህፃናት የሚከፈለው ገንዘብ የወላጆችን ጫና ለመቀነስ እንዲቀር ተወስኗል ተብሏል።
1.41 ቢሊየን ህዝብ ያላት ቻይና 1.46 ህዝብ ካላት ህንድ በመቀጠል በአለም ላይ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር መሆኗን ስታስቲካዊ መረጃዎች ያመላክታሉ። #miamiherald
@ThiqahETH
ቲክቶክ በአሜሪካ ለሽያጭ ለመቅረብ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።
የቲክቶክ ባለቤት በሆነው የባይትዳንስ ኩባንያና ግዥ በሚፈጸሙት የአሜሪካ ኩባንያዎች አማካኝነት የስምምነት ፊርማ ተፈጽሟል።
በስምምነቱ መሰረት የቲክ ቶክ 50 በመቶ ድርሻ ለአሜሪካ ባለሀብቶች እንደሚሸጥ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በባይደን ተዘግቶ የነበረውን ቲክ ቶክ ከመለሱ በኋላ የአሜሪካ ድርሻ ሊኖረው ይገባል በሚል ለ90 ቀናት ለሶስት ዙር ተራዝሟል።
ባይትዳንስ በበኩሉ በአሜሪካ 170 ሚሊየን በላይ ተከታይ ያለውን የቲክቶክን ድርሻ አልሸጥም ሲል ቢቆይም በመጨረሻ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። #techcrunch #cnn
@ThiqahETH
የአውሮፓ መሪዎች ለዩክሬን 90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር መስማማታቸው ተገለጸ።
ከወለድ ነፃ ነው የተባለው ብድሩ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት የሀገሪቱን የጦር እና የገንዘብ ፍላጐትን ለማሟላት ያግዛል ተብሏል።
ይሁን እንጂ መሪዎቹ የታገደውን የሩሲያ ሀብት ለዩክሬን መልሶ ግንባታ እንዲውል መወሰን ላይ አልተስማሙም።
210 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመት የሩሲያ ሀብት በጦርነቱ ምክንያት እንደያተዘ ህብረቱ አስታውቋል። #abcnews
@ThiqahETH
ብራዚል የቻይና ቱሪስቶች እና ኢንቨስተሮች ያለቪዛ እንዲገቡ ፈቀደች።
ብራዚል በ2024 ካስመዘገበችው እድገት 80% የሚሆነው ከቻይና በመጡ ጎብኝዎች እና ባለሀብቶች ነው ተብሏል።
ቻይና ትልቋ የብራዚል የንግድ አጋር እንደሆነች ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም ሁለቱ ሀገራት የብሪክስ መስራች አባል መሆናቸው ግንኙነታቸው የተጠናከረ እንዲሆን አግዟቸዋል ተብሏል። #southchinamorningpost
@ThiqahETH
"የአውሮፓ ህብረት ዲጂታል አገልግሎት (DSA) ህግ ዋነኛ አቀነባባሪ ነው" - አሜሪካ
አሜሪካ የአውሮፓ ህብረት የቀድሞ ኮሚሽነር ቴሪ ብሪተንን ቪዛ ከለከለች።
ብሪተን የአውሮፓ ህብረት በአሜሪካ ቴክኖሎጂዎች ላይ ቁጥጥር እንዲያደርግ ምክረ ሀሳብ በማቅረባቸው መከልከላቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።
"የአውሮፓ ህብረት ዲጂታል አገልግሎት (DSA) ህግ ዋነኛ አቀነባባሪ ነው" ብሏል ቢሮው።
ኮሚሽነሩ፣ "የአሜሪካ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሴንሰርሽፕ እንዲደረግ ጫና ፈጥረዋል" በማለት ወንጅሏቸዋል።
ቴሪ ብሪተን ኃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት የኤለን መስክ ንብረት የሆነው ታይከን የአውሮፓ ህብረት ህጎችን አክብሮ እንዲንቀሳቀስ፣ ካልሆነ ከአውሮፓ ገበያ ለቆ እንዲወጣ አስጠንቅቀዋል ተብሏል።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጄንኖዔል ባሮት በብሬተን ላይ የተላለፈውን የቪዛ ክልከላ በጥብቅ ማውገዛቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ህብረቱ አሜሪካ በቀድሞው ኮሚሽነር ላይ ባስተላለፈችው ውሳኔ የሰጠው ማብራሪያ የለም ተብሏል። #euractiv
@ThiqahETH
የሊቢያ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
ዋና አዛዡ መሀመድ አልሀዳድ በቱርክ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ሲመለሱ አደጋው እንደተከሰተ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ዲበይባህ ባወጡት የሀዘን መግለጫ "ሀገራችንም ሆነ ህዝባችን ትልቅ ሰው አጥተዋል" ብለዋል።
ዲበይባህ "የምድር ሀይል አዛዥ ኮማንደር፣ የወታደራዊ ማኑፋክቸሪንግ ባለስልጣን ዳይሬክተር፣ የጦር አዛዡ አማካሪ እና የካሜራ ባለሙያ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ ነበሩ" በማለት ሁሉም ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ሚኒስትር ሁኔታውን የሚከታተል የልዑካን ቡድን ወደቱርክ እንድልክ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል።
የቱርክ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አሊ የርሊካያ የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ፍንጣሪ በከሲካቫክ ከተማ መገኘቱን ገልጸዋል።
የሊቢያ ጦር ዋና አዛዥ መሀመድ አልሀዳድ በትናንትናው እለት ወደ አንካራ በማቅናት ከቱርክ አቻቸው ያሲር ጉለር እና ከቱርክ የጦር አዛዥ ሰሩክ ባይራክታሮግሉ ጋር ተወያይተዋል።
አደጋው የተከሰተው የቱርክ ፓርላማ በሊቢያ የሚገኘው የቱርክ ጦር ለተጨማሪ አንድ አመት እንዲቆይ ከወሰነ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ተገልጿል። #onmanorama
@ThiqahETH
"በፕሬዚዳንት ትራምፕ አማካኝነት የተደረገው ስምምነት ግልጽነት የጎደለው ነበር" - ታይላንድ
ታይላንድ እና ካምቦዲያ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ተገለፀ።
ሁለቱ ሀገራት ሶስተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘውን ግጭት በዘላቂነት ለማቆም ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሀሳክ ፋዋንታኩ ተናግረዋል።
ፋዋንታኩ "ለቀናት የዘለቁ ገንቢ የሁለትዮሽ ድርድሮች ከተደረጉ በኋላ መግባባት ላይ ተደርሷል" ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለው፣ " ጥቅምት ወር ላይ በፕሬዚዳንት ትራምፕ አማካኝነት የተደረገው ስምምነት ግልጽነት የጎደለው ነበር" በማለት ለግጭቱ ዳግም መቀስቀስ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል።
ስምምነቱ በነገው እለት የደቡብ እስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማህበር (ASEAN) ስብሰባ እየተካሄደባት በምትገኘው ማሌዥያ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል። #theasahishimbun
@ThiqahETH
"አሜሪካ ግሪንላንድ ለማዕድን ሳይሆን ለብሄራዊ ደህንነቷ ታስፈልጋታለች"- ትራምፕ
"ሌላ ሀገርን መውረር አትችልም" - ግሪንላንድ እና ዴንማርክ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጄፍ ላንድሪን የግሪንላንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው የሾሙ ሲሆን፣ ሰየላንድሪ ሹመት ዴንማርክን አስቆጥቷል።
ትራምፕ በፍሎሪዳ በነበራቸው ስብሰባ ላይ "ግሪንላንድን ካያችሁ የሩሲያ እና የቻይና መርከቦችን በአካባቢው አታጧቸውም" ብለዋል።
"አሜሪካ ግሪንላንድ ለማዕድን ሳይሆን ለብሄራዊ ደህንነቷ ታስፈልጋታለች" ሲሉ ተናግረዋል።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን እና የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ ኔልሰን ውይይት ካደረጉ በኋላ የጋራ መግለጫ በሰጡበት ወቅት "ግሪንላንድ የግሪንላንዳውያን ናት" ሲሉ አስታውቀዋል።
"ሌላ ሀገርን መውረር አትችልም" ያሉት መሪዎቹ "የጋራ የግዛት አንድነታችን ይከበራል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል።
የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላስ ራስሙሰን፣ "በዋሽንግተን እርምጃ ተበሳጭቻለሁ፣ በጭራሽ ተቀባይነት የለውም" በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በሀገራቸው ለሚገኙት የአሜሪካ አምባሳደር "ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጠን አስቸኳይ ጥሪ ልከናል" ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ፣ "ለዴንማርክ ሙሉ ድጋፍ አደርጋለሁ" ከማለት ውጭ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጠም ተብሏል። #hurriyetdailynews
@ThiqahETH
ሩዋንዳ ከ10,000 በላይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያናትን መዝጋቷ ተገለጸ
ቤተ ክርስቲያናቱ የተዘጉት በ2018 የወጣውን "የማምለኪያ ቦታ ጤና፣ ደህንነት እና ገንዘብን ማሳወቅ ህግ" ባለማክበራቸው ነው ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ "አብዛኞቹ ቤተክርስቲያናት ወይ ይሰርቃሉ ወይ ለባንዳ ያገለገሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
ካጋሜ "በእኔ ፍላጐት ቢሆን አንድም ቤተክርስቲያን አልከፍትም ነበር" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ "እኛ በፈተናዎች ውስጥ እያለፍን ነው፣ በጦርነት፣ ሀገርን በማስቀጠል ጉዳይ፣ የእነዚህ ቤተክርስቲያኖች ሚና ምንድነው? የስራ እድል ይፈጥራሉ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
የ2018ቱ ህግ የእምነት ተቋማቱ ለሀገር ያላቸውን ሚና ያካተተ አመታዊ የድርጊት መርሃግብራቸውን እንዲያሳውቁ ያስገድዳል ተብሏል። #trtworld
@ThiqahEth
"ሁሉም 315 ተማሪዎች እና መምህራን ተለቀዋል" - የናይጄሪያ መንግስት
"በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ አደጋ እንዳይገጥማቸው እንዲዘጉ ተወስኗል"!
በናይጄሪያ በእገታ ላይ የነበሩት ቀሪ 315 ተማሪዎችና መምህራን መለቀቃቸውን፣ ከእነዚህም መካከል 115 ተማሪዎች መሆናቸው የሀገሪቱ ደህንነት ቢሮ አስታውቋል።
በሀገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ከሚገኘው የቅድስት ማርያም የካቶሊክ ትምህርት ቤት ታጋቾች ከአንድ ወር በኋላ ሁሉም ከታገቱበት መለቀቃቸውን የሀገሪቱ ደህንነት ቢሮ አስታውቋል።
"ሁሉም 315 ተማሪዎች እና መምህራን ተለቀዋል" ያሉት የናይጄሪያ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ (NNSA) ኑሁ ሪባዱ "ታጋቾቹ የተለቀቁት መንግስት ከአማፂያኑ ጋር ከተደራደረ በኋላ ነው" ብለዋል።
ኖቬምበር 21,2025 የታገቱት መምህራንና ተማሪዎች በአሁኑ ወቅት ቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን አማካሪው አረጋግጠዋል።
ታጋቾቹ የተለቀቁት በሶስት ዙር መሆኑን የገለጹት ሪባዱ፣ "በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ አደጋ እንዳይገጥማቸው እንዲዘጉ ተወስኗል" ብለዋል።
በእገታው ምክንያት በደቡብ አፍሪካ የተዘጋጀው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ያልተገኙት ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒቡ በወቅቱ "እግዚአብሔር ከእነሱ ጋር ነው፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፣ አሸባሪዎች አያሸንፉም" ሲሉ ተናግረው ነበር። #independentnewsnigeria
በማዕከላዊ ናይጄሪያ በቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ከ300 በላይ ተማሪዎችና መምህራን በታጣቂዎች ታግተው ተወሰዱ መባሉ ይታወሳል።
@ThiqahETH
ሳዑዲዓረቢያ "ሙስሊም ላልሆኑ ነዋሪዎች" የአልኮል መጠጥ አቅርቦትን አሁን ካለው በበለጠ እንደምታሳድግ አስታወቀች።
የአልኮል ሽያጭ ማከፋፈያው በሪያድ የዲፕሎማቲክ ማዕከል ብቻ ይኖራል ተብሏል።
እስካሁን ይፋ ባይደረግም "ፍላጎት ያላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች" ላይ ትኩረት ያደረገ የአልኮል ሽያጭ እንደሚኖር ተገልጿል።
ነገር ግን ከፈቀደላቸው አካባቢዎች ውጭ የአልኮል መጠጦች እየተሸጡ ይገኛሉ ተብሏል።
ከ1950ዎቹ ጀምሮ የአልኮል ሽያጭን በሀገር አቀፍ ደረጃ የከለከለችው ሳዑዲ፣ ከጥር 2024 ጀምሮ ለዲፕሎማቶች ብቻ እንዲሸጥ ፍቃድ መስጠቷ ይታወቃል። #thenewarab
@ThiqahETH
#ደቡብአፍሪካ
"ጥቃቱ የተፈጸመው እኩለ ሌሊት ላይ በመሆኑ ጥቃት አድራሹን ግለሰብ መያዝ አልተቻለም" - ፓሊስ
በደቡብ አፍሪካ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች ተገደሉ።
ፖሊስ የተፈጠረውን ክስተት የሚያጣራ ቡድን ችግሩ በተፈጠረበት የጆሃንስበርግ ከተማ ማሰማራቱን አስታውቋል።
የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽነር ፍሬድ ኬካና "ጥቃቱ የተፈጸመው እኩለ ሌሊት ላይ በመሆኑ ጥቃት አድራሹን ግለሰብ መያዝ አልተቻለም" ብለዋል።
ከሟቾቹ መካከል የሦስት አመት ህፃንን ጨምሮ ሁለት ሌሎች ህፃናት እንደሚገኙበት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ኬካና የተጎጂዎችን ቁጥር በትክክል አለመታወቁን የገለጹት ኬካና "መረጃዎችን ለማግኘት እየጣርን ነው" ብለዋል።#bbc
@ThiqahETH
"የመብት ጥሰት ይፈጸማል፣ ክፍያ በአግባቡ አይሰጠንም" - ሶማሊያውያን የአየር መንገድ ሠራተኞች
460 የሶማሊያ ዜጎች ቱርካዊ ሀላፊ በሚያስተዳድረው የአደን አደ የሶማሊያ አየርመንገድ የመብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ተናገሩ።
ቅሬታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት የአየርመንገዱ ሰራተኞች "የመብት ጥሰት ይፈጸማል፣ ክፍያ በአግባቡ አይሰጠንም" ብለዋል።
አድማ በማድረግ አደባባይ የወጡት ሰልፈኞቹ "የዘረኝነት ጥቃት እየደረሰብን ነው፣ እንደሰው ከለላ አይደረግልንም" ሲሉ ተደምጠዋል።
በመፈክራቸው አክለውም "ከኬንያውያን ጋር እንኳን እኩል ደሞዝ አይከፈለንም፣ መብታችንን ስንጠይቅ ከስራ እንባረራለን" በማለት ገልጸዋል።
የቱርክ ፋቮሪ ካምፓኒ የሶማሊያ አደን አደ አየርመንገድን ኮንትራት ወስዶ እያስተዳደረ ይገኛል ተብሏል። #somaliwave
@ThiqahETH
ተመድ ሩዋንዳ ከምስራቅ ኮንጎ ለቃ እንድትወጣ አሳሰበ።
የፀጥታው ምክርቤት በስፍራው የተሰማራው አለማቀፍ የሰላም አስከባሪ ሀይል (MONUSCO) ለተጨማሪ አንድ አመት እንድቆይ ወስኗል።
ተልዕኮው 11,500 አባላትን እንደያዘ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
ሁለቱ ሀገራት በአሜሪካ አሸማጋይነት የሰላም ስምምነት ቢፈጽሙም በሳምንት ልዩነት ውስጥ መጣሱ ተገልጿል። #abcnews
@ThiqahETH
"ከ70 በሚበልጡ ISIS ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ኢላማ አድርገናል" - ዩናይትድስቴትስ
አሜሪካ በሶሪያ የአይ ኤስ አይ ኤስ ምሽጎች ላይ ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።
የአሜሪካ ጦር አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር "ከ70 በሚበልጡ የቡድኑ ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ኢላማ አድርገናል" ነው ያሉት።
ኩፐር "በቀጠናው የሚገኙ አጋሮቻችንን እና የአሜሪካ ወታደሮችን በሚያጠቁ አሸባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዳችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
የአሜሪካ መከላከያ ቢሮ ዋና ፀሐፊ ፔት ሄጌት፣ "የተወሰደው እርምጃ ISIS የሚጠቀምባቸው መሰረተ ልማቶች እና የጦር መሳሪያዎችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ጠላቶቻችንን ገድለናል፣ ማርከናል ወደፊትም ይቀጥላል" ብለዋል ሄጌት።
ISIS ባለፈው ሳምንት በሶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት ሶስት የአሜሪካ ወታደሮች ህይወታቸው ሲያልፍ ስድስቱ ቆስለዋል። #ashraqalawusat
@ThiqahETH
"የ35,600 ዶላር ብክነት ያደረሱት" የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትርና ባለቤታቸው የ17 አመት እስር ተፈረደባቸው።
በእስር ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ክሃን እና ባለቤታቸው ቡሽራ ቢቢ በስጦታ መልክ የተቀበሉት ወርቅና ጌጣጌጥ በሙስና ኬዝ ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓቸዋል።
በአዲያላ እስር ቤት የሚገኙት ባለትዳሮቹ በተጠረጠሩበት ወንጀል የ35,600 ዶላር ብክነት ማድረሳቸውን ፍርድ ቤቱ በክስ ዝርዝሩ አስረድቷል።
ክሃን እና ቢቢ የተላለፈባቸውን ፍርድ "የተፈበረከ ክስ" ሲሉ ውድቅ ማድረጋቸውን ጠበቃዎቻቸው ተናግረዋል።
በ2023 ወደእስር የገቡት ክሃን ከ200 በላይ ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን ሁሉንም "የፖለቲካ ሴራ" ሲሉ አጣጥለውታል። #trtworld
@ThiqahETH
9 ዓመት?
የ8 ዓመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ በ9 ዓመት እስራት መቀጣቱን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።
መህዲ መሀመድ ሳዲቅ የተባለ ግለሰብ በወራቤ ከተማ 01 ቀበሌ አለዋብ በተባለ ስፍራ በቀን 19/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ የ8 ዓመት ህፃን ከመንገድ ላይ እጇን ይዞ ወደራሱ ሱቅ ይዞ በመግባት አስገድዶ ደፍሯል።
ጉዳዩ በህግ ታይቶ፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በተከሰሰበት ወንጀል ፈጻሚው በዘጠኝ ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
መረጃው የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ሲሆን፣ በርካቶችም፣ የ8 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ ለደፈረው ግለሰብ የ9 አመት እስራት ቅጣት "ሌሎቹን መሰል ወንጀል ፈጻሚዎችን በርቱ የሚያስብል እንጅ አስተማሪ አይደለም" በሚል እየወቀሱ ናቸው።
@ThiqahETH
በባንግላዴሽ የወጣቶች ንቅናቄ መሪ መገደሉ ከፍተኛ ህዝባዊ አመፅ ተቀሰቀሰ።
ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የምትገኘው ባንግላዴሽ ለምርጫ ዕጩ ሁኖ የቀረበው የተማሪዎች ንቅናቄ አስተባባሪ ሻሪፍ ኡስማን ሀዲ ተገድሏል።
የ32 አመቱ ሀዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲናን ከስልጣን ባነሳው የተማሪዎች ንቅናቄ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።
ሀዲ በዋና ከተማዋ ዳካ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ለህክምና ወደ ሲንጋፖር ቢያቀናም ከስድስት ቀን በኋላ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
በአስተባባሪው ህልፈት የተበሳጩት ሰልፈኞች ስሙን በመጥራት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው ተብሏል። #keralanews
@ThiqahETH