15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኩባ የሚገባው ነዳጅ መቆም በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ "ውይይት" ያስፈልጋል አሉ።
"ስምምነት ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ብየ አስባለሁ፣ ያኔ ኩባ ነፃ ትሆናለች" ብለዋል።
ትራምፕ "ኩባ ከዋሽንግተን ጋር መስማማት ከቻለች ሰብዓዊ ቀውስ አይፈጠርም" ሲሉ አብራርተዋል።
"ኩባ ለአሜሪካ ያልተለመደ እና ልዩ ስጋት ፈጥራለች" በማለትም ነዳጅ በሚያቀርቡላት ሀገሮች ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጉየል ዲያዝ ደግሞ፣ እርምጃውን "የአሜሪካ መንግስት ተፈጥሮ ፋሽስት፣ ወንጀለኛ እና ዘር ጨፍጫፊ መሆኑን የሚያሳይ ነው" ሲሉ መኮነናቸው ይታወሳል። #sputnikAfrica
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የኢሚግሬሽን ማስከበር ዘመቻ ነበር፣ አለ፣ ይቀጥላል" - ዳኛ ካትሪን ሜንዴዝ
የፌደራል ዳኛ የኢምግሬሽን ፖሊስ ከሚኒያፖሊስ እንዲወጡ የቀረበላቸውን አቤቱታ ውድቅ አደረጉ።
የዲስትሪክቱ ፍርድ ቤት ዳኛ ካትሪን ሜንዴዝ "የኢሚግሬሽን ማስከበር ዘመቻ ነበር፣ አለ፣ ይቀጥላል" ብለዋል።
"በሚኒሶታ ልብ ሰባሪ ሁኔታ እየተፈጠረ ቢሆንም ICE አይወጣም" በማለት ገልጸዋል።
ዳኛዋ "የሚኒሶታ ግዛት አስተዳዳሪዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያስገባቸው ኃይሎች የፈጸሙትን ጥቃት እና ህገወጥነት ማረጋገጥ አልቻሉም" ሲሉ ተናግረዋል።
ዳኛ ሜንዴዝ ይህን ቢሉም፣ የኢሚግሬሽን አሰራርን የተቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካዊያን በኒዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ቺካጎ እና ዋሽንግተን ዲሲ አደባባዮች ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የሀገራችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን" በማለት የጀመሩትን ሰነድ አልባ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ዘመቻ ለማስፈጸም ከ3000 በላይ የፌደራል ሀይሎች በሚኒያፖሊስ ከተማ ተሰማርተዋል።
የሚኒሶታ ገዥ ቲም ዋልዝ እና የሚኒያፖሊስ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ ትራምፕ ወደ ከተማዋ ያስገቧቸውን ኃይሎች እንዲያስወጡ ጠይቀዋል። #bbc
@EyobTikuye @ThiqahEth
በናይጄሪያ ከ100 በላይ ኃይሎች የሁለት ፓርቲዎችን ስብሰባ አስተጓጎሉት።
የላቦር ፓርቲ (LP) እና አፍሪካ ዲሞክራቲክ ኮንግረስ (ADC) ፓርቲዎች በሌጎስ ከተማ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ በረብሻው ምክንያት አልተካሄደም ተብሏል።
ይሄው ቡድን አባላቱ በሁለቱ ፓርቲዎች አባላት ላይ ድብደባ በመፈጸም ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል።
የፓለቲካ ፓርቲዎቹ በናይጄሪያ በ2027 በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ቅድመ ምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ነው አመጹ የተከሰተው ተብሏል።
የሌጎስ ከተማ ፖሊስ በበኩሉ፣ ሁለቱ ፓርቲዎች ህዝባዊ ውይይት እንዲያደርጉ ፍቃድ አልሰጠሁም ብሏል። #peoplesgazette
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የአሜሪካ መንግስት ተፈጥሮ ፋሽስት፣ ወንጀለኛ እና ዘር ጨፍጫፊ መሆኑን የሚያሳይ ነው" - ኩባ
የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጉየል ካናል ዲያዝ ትራምፕ ያሳለፈውን ውሳኔ ተቃወሙ።
ትራምፕ ለኩባ ነዳጅ በሚያቀርቡ ሀገራት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈቅደውን ረቂቅ አዋጅ በትናንትናው እለት በፈረሙበት ወቅት "ኮሚኒስት ሀገር ኩባ ለአሜሪካ ያልተለመደ እና ልዩ ስጋት ፈጥራለች" ብለዋል።
ይህን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዲያዝ፣ "በውሸት እና መሰረተ ቢስ በሆነ አረዳድ ለሀገራችን ነዳጅ የማቅረብ ሉዓላዊ መብት ያላቸውን ሀገራት በታሪፍ አስፈራርተዋል" ሲሉ ተችተዋል
ፕሬዝዳንቱ፣ "ይህ እርምጃ የአሜሪካ መንግስት ተፈጥሮ ፋሽስት ወንጀለኛ እና ዘር ጨፍጫፊ መሆኑን የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ዲያዝ፣ "የአሜሪካ ህዝብ ጥቅም በግለሰቦች ተጠልፏል" በማለት አጥብቀው ወንጅለዋል።
አክለው፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ማርክ ሩቢዮ ከኩባ ቤተሰብ እንደተገኘ ጠቅሰው "ኩባ አሜሪካዊ ግን ፀረ ኩባ" ሲሉ ጠርተውታል። #aljazeera
አሜሪካ ለኩባ ነዳጅ የሚያቀርቡ አገራት ላይ ታሪፍ እንደምትጥል ማስጠንቋ ይታወሳል። የቀደመውን ዘገባ ያንብቡ፣ /channel/thiqahEth/5354
@EyobTikuye @ThiqahETH
በኮንጎ በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ የነበሩ ከ200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
በምሥራቅ ኮንጎ በሚገኘው ሩባያ የማዕድን ማውጫ ስፍራ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደርሷል ተብሏል።
የማዕድን ማውጫ ስፍራው ኤም 23 አማፂ ቡድን በሚያስተዳድረው የኪቩ ግዛት ውስጥ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከሟቾቹ ውስጥ የተወሰኑት አስክሬናቸው በጭቃ በመሸፈኑ ማውጣት አልተቻለም ተብሏል።
ጉዳት የደረሰባቸውን ከአደጋው አካባቢ 30 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው ጎማ ከተማ በመላክ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል። #thejerusalempost
@EyobTikuye @ThiqahETH
ፓኪስታን ቢያንስ "67 ታጣቂዎች" ላይ እርምጃ መውሰዷን አስታወቀች።
የፓኪስታን ጦር በባሎችርታን ግዛት በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ ወሳኝ ድል ማሳካቱን የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ ገልጸዋል።
ናቅቪ በዚህ ዘመቻ 10 የፓኪስታን ፖሊስ እና 11 ንጹሐን ዜጎች ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ እርምጃው የተወሰደው በኢራን እና አፍጋኒስታን አዋሳኝ አካባቢዎች ነው።
የባሎችስታን ግዛት የፓኪስታንን ማዕከላዊ መንግስት የሚቀነቀነው የባሎች ሚሊታንትስ ግሩፕ (BMG) ዋና መቀመጫ ነው። #cnn #Reuters
@EyobTikuye @ThiqahETH
በናይጄሪያ የህገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎቹ በተያዙበት ወቅት 14 ሰዎች ከእገታ ማስለቀቁን የኦንዶ ግዛት ፖሊስ አዛዥ አባዮሚ ጂሞህ አስታውቀዋል።
ጂሞህ በአዘዋዋሪዎች እጅ የተገኙት 14 ሰዎች ከቻድ፣ ቶጎ እና ሌሎች ሀገራት የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የፖሊስ አዛዡ የህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ለተጨማሪ ምርመራ ለብሄራዊ የወንጀል ምርመራ ዲፓርትመንት (SCID) መላካቸውን ገልጸዋል። #dailypost
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ተመድ በመፍረስ አደጋ ላይ ነው" - ጉተሬዝ
የተባበሩት መንግስታት (ተመድ) ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ተባለ።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "ተመድ በመፍረስ አደጋ ላይ ነው" ብለዋል።
ጉተሬዝ፣ "የማይቀር የገንዘብ ውድቀት ከፊታችን ተጋርጦብናል" ነው ያሉት።
ዋና ፀሐፊው ለአባል ሀገራት አምባሳደሮች በፃፉት ደብዳቤ፣ "የአባልነት ክፍያ እና በጀት አስተዳደር ያልጠፋ በጀት መመለስ አለበት" ሲሉ አስፍረዋል።
ድርጅቱ ለገንዘብ እጥረት የተጋለጠው "አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ በማቋረጧ ነው" ተብሏል። #ilna
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ሞስኮ ሂጄ ፑቲንን ማግኘት ለእኔ በፍጹም የማይሆን ነገር ነው" - ዘለንስኪ
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ የክሬሚሊንን ግብዣ ውድቅ አደረጉ።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ዘለንስኪ ለድርድር ሞስኮን እንዲጎበኝ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ደግሞ በሰጡት ምላሽ፣ "ሞስኮ ሂጄ ፑቲንን ማግኘት ለእኔ በፍጹም የማይሆን ነገር ነው" ብለዋል።
"ተመሳሳይ ነገር ስለሆነ እኔ ልጋብዘውና ይምጣ" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ "ፑቲን ኪቭ እንዲመጣ እኔ ጋብዠዋለሁ" በማለት ተናግረዋል።
ዘለንስኪ፣ "የሞስኮው ግብዣ ፑቲን በአካል ለመገናኘት ፈቃደኝነት እንደሌለው የሚያሳይ ነው" ሲሉ ተቃውመውታል።
በየትኛውም መንገድ ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ ድርድሮች መገኘት እንደሚችሉ ገልጸው፣ "በሞስኮ እና በቤላሩስ የሚደረጉ ድርድሮችን እኔ አልቀበላቸውም" ብለዋል።
ምክንያቱን ሲያብራሩም፣ "ሩሲያም ሆነች ቤላሩስ በእኛ ላይ ጦርነት አውጀውብናል" በማለት አስረድተዋል።
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች መካከል የፊት ለፊት ውይይት እንድደረግ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። #reuters
@EyobTikuye @ThiqahETH
ደቡብ አፍሪካ በሀገሯ የሚገኝ አንድ የእስራኤል ኤምባሲ ባልደረባ አባረረች።
ኤሪል ሴዲማን በደቡብ ኬፕታውን ግዛት ከጎሳ መሪዎች ጋር ያልተፈቀደ ውይይት ማድረጋቸው ከሀገር ለመውጣት ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
የዲፕሎማቱ ውይይት "ዲፕሎማሲያዊ እሴቶችን የጣሰ ነው" ያለችው ጆሀንስበርግ "በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል" ስትል ወንጅላለች።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ እና አለማቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ሴድማን በ72 ሰዓት ውስጥ ከሀገር ለቆ እንዲወጣ አሳስቧል።
ዲፕሎማቱ ወደፊት በየትኛውም ሁኔታ ወደደቡብ አፍሪካ እንዳይገባ በሚኒስቴሩ ክልከላ ተጥሎበታል።
ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ጦርነት እስራኤል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅማለች በሚል በአለማቀፍ የወንጀለኛ ፍርድቤት (ICJ) ክስ መመስረቷ ይታወቃል። #thenewarab
@EyobTikuye @ThiqahEth
አሜሪካ ለኩባ ነዳጅ በሚያቀርቡ ሀገራት ላይ ታሪፍ እንደምትጥል አስጠነቀቀች።
ትራምፕ በኩባ ላይ ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስተላልፈውን ውሳኔ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
አዋጁ በየትኛውም የነዳጅ አቅራቢ ሀገር ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ይደነግጋል ተብሏል።
ይህ እርምጃ በዋናነት ሶስቱን የኩባ ወዳጅ ሀገራት ማለትም
-ሩሲያ፣
-ቻይና
-ኢራን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት "ኩባ የአሜሪካ ቀንደኛ ጠላቶች በግዛቷ እንዲንቀሳቀሱ ፈቅዳለች" ብለዋል። #europeanpravada
@EyobTikuye @ThiqahEth
"የዩክሬን የህብረቱ አባልነት ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓም አስፈላጊ ነው" - ዘለንስኪ
ዩክሬን በቀጣይ አመት የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል መዘጋጀቷ ተገለጸ።
አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣን "ዘለንስኪ ሀገራቸው ዩክሬን በ2027 የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆን አላማ ይዘዋል" ብለዋል።
ዘለንስኪ የአውሮፓ ህብረት አባል መሆን "ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና ይሰጣል" የሚል እምነት አላቸው ተብሏል።
"የዩክሬን የህብረቱ አባልነት ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓም አስፈላጊ ነው" ሲሉ መናገራቸውን አስረድተዋል።
የአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን የሶስትዮሽ ውይይት አሜሪካ ቅድሚያ ለኢራን በመስጠታቸው መራዘሙ ተገልጿል። #theguardian
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ኢራን ወደምትባለው ቦታ ለመሄድ የተዘጋጀ ቡድን አለን" - ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር እቅድ መያዛቸውን አስታወቁ።
ዶናልድ ትራምፕ "ወታደራዊ ጥቃትን ለማስወገድ አሁንም እየተወያየን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ኢራን ወደምትባለው ቦታ ለመሄድ የተዘጋጀ ቡድን አለን" በማለት በቀጣይ ወደ ቴህራን የሚያቀና ልዑካን ቡድን መኖሩን ጠቁመዋል።
ፕሬዚዳንቱ "በጣም ትላልቅ እና ሀይለኛ መርከቦች አሉን፣ ወታደራዊ ጥቃት እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ገልጸዋል።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የድርድር ንግግር የተሰማው አሜሪካ አርማዳ የጦር መርከብ ማሰማራቷን ከገለጹ ከቀናት በኋላ ነው። #thenewarab
@EyobTikuye @ThiqahETH
"አዲስ ጦርነት አንፈልግም" - የአውሮፓ ህብረት
የአውሮፓ ህብረት አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር አሳሰበ።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሀላፊ ካጃ ካላስ "ኢራን ላይ የሚፈፀመው ጥቃት የአውሮፓ ሀገራትን በጣም ይጎዳል" ብለዋል።
ካላስ "ቀጠናው በአዲስ አመት አዲስ ጦርነት አይፈልግም" ሲሉ ተናግረዋል።
ካላስ ይህን አስተያየት የሰጡት የአውሮፓ ህብረት የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በአሸባሪነት ከፈረጀ በኋላ ነው። #euractive
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ፑቲን ለአንድ ሳምንት ኪቭን ላለማጥቃት ተስማምቷል" - ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው አቻቸው ቪላድሚር ፑቲን ጋር መወያየታቸውን አሳወቁ።
ፕሬዚደንቱ በካቢኔ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር "ፑቲን ለአንድ ሳምንት ኪቭን ላለማጥቃት ተስማምቷል" ሲሉ ገልጸዋል።
"እኔ በግሌ ፕሬዚዳንት ፑቲንን ኪቭን እና ሌሎች ከተሞች ላይ ጥቃት እንዳያደርስ ጠይቄዋለሁ እሱም ተስማምቷል" ብለዋል ትራምፕ።
የትራምፕን አስተያየት በተመለከተ ከሩሲያ በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ የለም መባሉ ተዘግቧል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
"እያወሩን ነው፤ በስርዓት እየተነጋገርን ነው" - ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ እና የኢራን ውይይት መቀጠሉን ጠቆሙ።
ዶናልድ ትራምፕ "እያወሩን ነው፣ በስርዓት እየተነጋገርን ነው" ሲሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውይይት ያለበትን ሁኔታ አስረድተዋል።
ካሁን በፊት በኢራን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ ያሰሙት ፕሬዝዳንቱ "ንግግሮች የሆነ ተቀባይነት ያለው ውጤት እንደሚያመጡ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።
"አንዳንድ ሰዎች 'የኢራን ባለስልጣናት ኑክሌር ላይ የሚያስማማ ድርድር አያደርጉም' ይላሉ፣ እነሱ ምን እንደሚያደርጉ ግን አላውቅም ንግግሮች ቀጥለዋል" ሲሉ ተናግረዋል። #theguardian
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ድርድሮች ቅርፅ ይዘዋል ተስፋ ሰጪ ናቸው" - አሊ ላርጃኒ
ቴህራን ከዋሽንግተን ጋር ውጤታማ ውይይት እያደረገች መሆኑን ጠቆመች።
የኢራን ከፍተኛ ብሄራዊ ፀጥታ ካውንስል ዋና ፀሐፊ አሊ ላርጃኒ ከአሜሪካ ጋር "በጋራ መከባበር" ላይ የተመሰረተ ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ላርጃኒ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ፣ "በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለመቀነስ መሻሻሎች ታይተዋል" ብለዋል።
"የተቀያጀ አካሄድ" ያሉትን ውይይት "ድርድሮች ቅርፅ ይዘዋል ተስፋ ሰጪ ናቸው" ሲሉ ገልጰውታል።
"የተፈበረከ የሚዲያ ጦርነት ነው ያለው" በማለት ስለግጭት የሚወራውን ውድቅ አድርገዋል። #trtworld
@EyobTikuye @ThiqahETH
አሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ ለህንድ አቀረበች።
ዋሽንግተን ከአንድ አመት በፊት የቬኒዙዌላን ነዳጅ በመግዛቷ በህንድ ላይ የ25% ታሪፍ ጥላለች።
አሁን ደግሞ ህንድ ከሩሲያ የምትገዛውን ነዳጅ በቬንዙዌላ እንድትተካ መጠየቋ ተሰምቷል።
ከሩሲያ ነዳጅ መግዛት የዩክሬን ጦርነትን እንደመደገፍ አድርጋ የምትቆጣጠረው አሜሪካ ህንድ ላይ ልትጥለው የነበረውን የ50% ቀረጥ ላልተወሰነ ጊዜ አራዝማለች።
አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በቁጥጥር ስር ካዋለች በኋላ የቬንዙዌላን የነዳጅ ሀብት በበላይነት ማስተዳደር ጀምራለች።#ukriform
@EyobTikuye @ThiqahEth
ተመድ በቆጵሮስ ያሰማራውን ሀይል ለተጨማሪ አንድ አመት አራዘመ።
የፀጥታው ምክርቤት ባደረገው ስብሰባ የተመድ የቆጵሮስ ሰላም አስጠባቂ ተልዕኮ (UNFICYP) እስከ ጥር 31/2027 እንደሐቆይ ወስኗል ተብሏል።
በዩናይትድ ኪንግደም የተመራው ስብሰባ 13 አባላት በሙሉ ድምፅ ሲያጸድቁት ሶማሊያ እና ፓኪስታን ድምፅ ተዓቅቦ አድርገዋል ተብሏል።
በቆጵሮስ የተሰማራው ሀይል ከ1964 ጀምሮ በስፍራው እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ተመድ የሰላም አስከባሪ ሀይል ያሰማራው በግሪክ እና በቱርክ መካከል የይገባኛል ጥያቄ በመነሳቱ ነው። #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
ቢያንስ 29 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ።
ግድያው የደረሰው "እስራኤል በምዕራብ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት ላይ ባደረሰችው ጥቃት" ነው።
ከሞቱት ባሻገር የተረጂዎችን ሁኔታ ማወቅ አለመቻሉን የህክምና ምንጮች ገልጸዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ከባለፈው ጥቅምት ጀምሮ "በአጠቃላይ 524 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸው" ማለፉ ተገልጿል።
በተጨማሪም 1 ሺሕ 360 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።
በእነዚህ አራት ወራት ውስጥ እስራኤል 1 ሺሕ 450 ጥሰቶችን በመፈጸም ጥቃት አድርሳለች ነው የተባለው።
የሁለት አመቱ የጋዛ ጦርነት 90% የከተማዋን መሰረተ ልማት አውድሟል። መልሶ ለመገንባትም 70 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል። #trt #AnadoluAgency
@EyobTikuye @ThiqahETH
በኢራን ሁለት ፍንዳታዎች ተከስተዋል።
ከደቂቃዎች በፊት በተከሰተው በዚህ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል።
እነዚህ ድንገተኛ ፍንዳታዎች በአህፋዝ ከተማ በሚገኝ የነዳጅ ጣቢያ ላይ ነው፡ የተከሰቱት ተብሏል።
የኢራን ባለስልጣናት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎ መክሸፉን ገልጸዋል።
በነዳጅ ጣቢያው አጠገብ የነበረ የአብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ ኮማንደር ኢላማ ተደርጎ ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።
ምክንያቱ ባልታወቀው አደጋ የደረሰው ጉዳት አልተገለጸም።
ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት ኢራን ከአሜሪካ በኩል ጥቃት ሊፈፀምባት ይችላል የሚል ከፍተኛ ውጥረት ባለበት ወቅት ነው። #theindependent
@EyobTikuye @ThiqahEth
የሶርያ መንግስት ከኩርድ ታጣቂዎች ጋር ስምምነት ፈጸመ።
በስምምነቱ መሰረት የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች (SDF) በሂደት በሀገሪቱ ጦር ስር ይካተታሉ ተብሏል።
የፌዴራሉ መንግስት ሶርያን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስነውን የሲማልቃ ድንበር እንደሚቆጣጠርም ተገልጿል።
አሜሪካ እና ሌሎች አለማቀፍ የስምምነቱ ተሳታፊ አካላት የተፈጸመውን ስምምነት "ታሪካዊ እምርታ" ሲሉ አድንቀውታል።
ሁለቱ ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ልዩነታቸውን ለመፍታት ያሳዩት ተነሳሽነት ለሶርያ አንድነት እና መረጋጋት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
የኩርድ ታጣቂዎች ከመሀመድ አልሻራ መንግስት ጋር በመተባበር የበሽር አሃሳድ መንግስትን ለመጣል ከፍተኛ ትግል አድርገዋል።
ከወቅቱ የአልሻራ የሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ደግሞ፣ "ጥቅማችን አልተከበረም" በሚል ዳግም ወደ ግጭት ውስጥ ገብተዋል። #thetimesofisrael
@EyobTikuye @ThiqahETH
"እኛም የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ተወካይ ቢንቨልዲት ላይ 72 ሰዓት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደናል" - ጌዲዮን ሳር
ደቡብ አፍሪካ በሀገሯ ይገኝ የነበረን አንድ የእስራኤል ኤምባሲ ባልደረባ ማባረሯን ነግረናችሁ ነበር።
አሁን ደግሞ እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተሰምቷል።
በቴላቪቭ የሚገኙት የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ዲፕሎት ሻውን ኤድዋርድ ቢንቨልዲት በሦስት ቀናት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።
ትዕዛዙን ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር ናቸው ተብሏል።
ጌዲዮን ሳር በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ፣ "ፕሪቶሪያ ሀሰተኛ ጥቃት አድርሳብናለች" በማለት የእስራዔል ዲፕሎማት ከደቡብ አፍሪካ መባረሩን ተቃውመዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ "መሰረተቢስ የተናጠል እርምጃ ነው" ሲሉ ተቃውመዋል።
"እኛም የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ተወካይ ቢንቨልዲት ላይ በ72 ሰዓት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደናል" ብለዋል።
ሚኒስትሩ "ወደፊት ሁኔታዎችን እየገመገምን ተጨማሪ ውሳኔዎችን እናሳልፋለን" በማለት ገልጸዋል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፋ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ደረጃን የሚጥስ ነው" - የአልጀዚራ ሚዲያ ተቋም
አልጀዚራ እስራኤል ቻናሉን በሀገሯ በመዝጋቷ ለዩቲዩብ ካምፓኒ ቅሬታውን ገለጸ።
እስራኤል ከዩቲዩብ ካምፓኒ በተሰጣት ጥቆማ መሰረት አልጀዚራ እና አልማያዲን የተባሉ ሚዲያዎች ለ90 ቀን እንዳይታዩ ዘግታለች።
ይህን የተቃወመውና ለዩቲዩብ ካምፓኒ የቅሬታ ደብዳቤ ያስገባው አልጀዚራ "የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፋ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ደረጃን የሚጥስ ነው" በማለት እርምጃውን አውግዟል።
"ዩቲዩብ እስራኤል አልጀዚራን እንድትዘጋ የወሰነበትን መንገድ አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል።
ጣቢያው አክሎም፣ "አለማቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ገለልተኛ ሚዲያን ጫና ከሚያሳድሩ መንግስታት መጠበቅ ሲኖርበት ዩቲዩብ በተቃራኒ መፈጸሙ የማይጠበቅ ነው" ብሏል።
የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች በኃይል በተቆጣጠሯቸው የፍልስጤም ግዛቶች ኔትወርክ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውንም አስታውቋል።
ዩቲዩብ ከአልጀዚራ ለቀረበበት ቅሬታ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም ተብሏል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahETH
"በማዳጋስካር ብቻ 202 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል" - ማዕከሉ
በማዳጋስካር እና ኮሞሮስ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) ወረርሽኝ መቀስቀሱ ተገልጿል።
"በማዳጋስካር ብቻ 202 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል" ሲል የአፍሪካ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል (Africa CDC) አስታውቋል።
በኮሞሮስ ዘጠኝ ሰዎች ተይዘዋል ተብሏል።
ወረርሽኙ በሀገሪቱ ካሉት 114 የጤና ዲስትሪክቶች 20 በሚሆኑት መስፋፋቱን አመላክቷል።
በሁለቱም በሽታው በተከሰተባቸው ሀገራት የመድኃኒት ስርጭት መጀመሩን የገለጸው ተቋሙ፣ በአፍሪካ ለድንገተኛ ወረርሽኝ በቂ የበጀት ድጋፍ ሊኖር እንደሚገባ አሳስቧል።
በምሥራቅ አፍሪካ ለአመታት የጤና ስጋት ሆኖ የዘለቀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ የተረጋገጠው ከወራት በፊት ነበር። #peoplesgazette
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ስምምነቱ ለራሷ UK በጣም አደገኛ ነው" - ትራምፕ
"ትራምፕ ተሳስቷል። ...ትራምፕ ራሱ በሚያዝያ ወደቻይና ለመሄድ በእቅድ ላይ ነው" - ብሪያንት
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ኪንግደም ከቻይና ጋር ያደረገችውን የንግድ ስምምነት ተቃውመውታል።
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ወደ ቻይና በማቅናት ከፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ጋር የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መፈጸማቸው ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በሰጡት አስተያየት፣ "ስምምነቱ ለራሷ ለዩናይትድ ኪንግደም በጣም አደገኛ ነው" ሲሉ ተቃውመዋል።
"የቻይናውን ፕሬዚዳንት ዢን በጣም አውቀዋለሁ" ያሉት ትራምፕ፣ "ለካናዳም ጭምር አስቸጋሪ ነው ብየ አስባለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስትር ክሪስ ብሪያንት ደግሞ፣ "ትራምፕ ተሳስቷል" ሲሉ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።
"እኛ ከቻይና ጋር ግንኙነት የምናደርገው ዓይታችንን አስፍተን ነው" ብለዋል።
ሚኒስትሩ፣ "ትራምፕ ራሱ በሚያዝያ ወር ወደቻይና ለመሄድ በእቅድ ላይ ነው" ሲሉ አጋልጠዋል። #politico #bbc
@EyobTikuye @ThiqahETH
ኢብራሂም ትራኦሬ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተኑ።
የቡርኪና ፋሶ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በቡርኪናፋሶ ያሉ ጠቅላላ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያፈርስ አዲስ አዋጅ ማጽደቁ ተሰምቷል።
በዚህ አዋጅ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሚበተኑ ሲሆን፣ እርምጃው በተለይ በህዝቡ መካከል የፓለቲካ መከፋፈልን ያስቀራል ተብሎለታል።
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ኢራን ጦርነት ጀማሪ አትሆንም ግን በሙሉ ሀይሏ ራሷን ለመከላከል ትገደዳለች" - ኢራን
የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት መንግስት "የጦርነት ጊዜ ዝግጅት" ማድረጉን ገለፁ።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የጦርነት ስጋት ባየለበት ወቅት ብሄራዊ ዝግጁነት መደረጉን ምክትል ፕሬዚዳንት መሀመድ ሬዛ አሬፍ ተናግረዋል።
አሬፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ኢራን ጦርነት ጀማሪ አትሆንም ግን በሙሉ ሀይሏ ራሷን ለመከላከል ትገደዳለች" ብለዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ "የጦርነቱ ፍፃሜ በጠላቶች ብቻ አይወሰንም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ስትራቴጂያችን በድርድር እና በሎጂክ ማመን ነው ከተጀመረ ግን አፀፋ መስጠት የሚጠበቅ ነው" ብለዋል።
ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ውይይት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት "ጥሩ ሂደት ታይቶበታል" የሚል አጭር መልስ ሰጥተዋል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ዘለንስኪ ወደ ሞስኮ እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበናል" - ፔስኮቭ
ሩሲያ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ሞስኮን እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረበች።
ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ለሰላም ድርድር ወደ ሩሲያ እንዲያቀና የክሬሚሊን ቤተመንግሥት ጥሪ አቅርቧል ተብሏል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ከሰዓታት በፊት ባወጡት መግለጫ፣ "የፑቲን እና የዘለንስኪ የፊት ለፊት ውይይት በሩሲያ ብቻ ነው የሚካሄደው" ብለዋል።
ፔስኮቭ፣ "ሌሎች የድርድር ቦታዎችን በተመለከተ ተገቢ አይደለም፣ ከሞስኮ ውጭ የሚደረጉ የመሪዎቹ ውይይት በሩሲያ ዘንድ ተቀባይነት የለውም" ሲሉም አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ፣ "ዘለንስኪ ወደ ሞስኮ እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበናል፣ ግን እስካሁን ከዩክሬን በኩል የተሰጠን ምላሽ የለም" በማለት ገልጸዋል።
የሩሲያ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ፣ የግዛት ጉዳይ የሰላም ድርድሩ ብቸኛ እንቅፋት አለመሆኑን ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ የሞቱ ወታደሮችን አስክሬን ልውውጥ አድርገዋል። በዚህም ሩሲያ 1000 የዩክሬን ወታደሮችን አስክሬን ስትሰጥ፣ ዩክሬን 38 የሩሲያ ወታደሮች አስክሬንን መልሳለች ተብሏል።
ሁለቱ ሀገራት ባሳለፍነው ሳምንት በአቡዳቢ የፊት ለፊት ድርድር ካደረጉ በኋላ ሁለተኛ ዙር ለማካሄድ በመስማማት ተለያይተዋል። #NDTV
@EyobTikuye @ThiqahETH
ብሪታንያ እና ቻይና የነፃ ንግድን ለማሳደግ ተስማሙ።
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቻይና የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ከቻይናው አቻቸው ዢ ጂፒንግ ጋር የጋርዮሽ ጥምረት ለማሳደግ መወያየታቸውን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።
ስታርመር፣ "በድንበር ደህንነት እና በህግ ማስከበር ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምተናል" ብለዋል።
"ከዓለም ትልቅ ኢኮኖሚ ካላት ቻይና ጋር በጋራ መስራት ጥሩ እድል ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በግልጽ ለመነጋገር እና ዘላቂ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ተነጋግረናል" ሲሉ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዢ በበኩላቸው፣ "በዓለማቀፍ ህግ መመራት ለሀገራቱ ጤናማ ግንኙነት መሰረት ነው" ብለዋል።
"ቻይና በየትኛውም ለየትኛውም ሀገር ስጋት የመሆን ፍላጐት የላትም" ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከቪዛ ነፃ መግባት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተገልጿል። #indiatoday
@EyobTikuye @ThiqahETH