thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

"ዚንታን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተፈጽሞ ነው ህይወቱ ያለፈው" ኮካድ

የፕሬዝዳንት ጋዳፊ ልጅ በታጣቂዎች ተገደለ።

የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዚዳንት መሀመድ ጋዳፊ ልጅ ሰይፈ አል ኢስላም ጠበቃ ማርሴል ኮካድ በምዕራብ ሊቢያ "ዚንታን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተፈጽሞ ነው ህይወቱ ያለፈው" ብለዋል።

የፈረንሳይ ዜግነት ያለው የአል ኢስላም ጠበቃ "አራት ሰዎች ናቸው እሱን ለመግደል የተሳተፉት" ሲሉ ተናግረዋል።

የቅርብ አማካሪው አብዱራህ አብዱራህማን በበኩላቸው፣ "የደህንነት ካሜራዎቹን በእሳት አደጋ አበላሽተው እሱን ገደሉት" ሲሉ ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ አስረድተዋል።

የ53 አመቱ አል ኢስላም በዓለማቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት (ICC) "በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች" ክስ የእስር ትዕዛዝ አውጥቶበታል።

በ2011 በቁጥጥር ስር ውሎ በ2015 የሞት ፍርድ ቢፈረድበትም በይቅርታ መውጣት ችሎ ነበር።

በ2021 ለምርጫ እንደሚሳተፍ ቢያሳውቅም ምርጫው ተራዝሞ ሳይሳተፍ ቀርቷል። #legit #ndtv

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ከአሜሪካ ጋር ያለንን ትብብር ማሳደግ ፍላጎቴ ነው" - ጉስታቮ

"በቬኔዙዌላ የተፈጠረው ፔትሮ ሀሳቡን እንድቀይር አድርጎታል፣ ለውይይት ዝግጁ ሆኗል" - ትሪምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮን በዋይትሃውስ ጋብዘዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት "በሽተኛ ነው" ሲሉ ከጠሩት ፔትሮ ጋር ለመገናኘትና ውጥረቱን በውይይት ለማርገብ መወሰናቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ጉስታቮ በበኩላቸው፣ በጋዛ ጦርነት "የተወዛገበ ዘር ጨፍጫፊ" ሲሉ ከወቀሱትና ፕሬዘዳንት ማዱሮ ላይ የወሰደውን እርምጃ "እገታ ነው የፈፀመው" ሲሉ ካወገዙት ትራምፕ ጋር "ከአሜሪካ ጋር ያለንን ትብብር ማሳደግ ፍላጎቴ ነው" ብለዋል።

መሪዎቹ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር እና በላቲን አሜሪካ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ "በቬኔዙዌላ የተፈጠረው ፔትሮ ሀሳቡን እንድቀይር አድርጎታል፣ ለውይይት ዝግጁ ሆኗል" ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ እና በአለም ላይ ቀዳሚዋ የኮኬይን አምራች ኮሎምቢያ ላለፉት 30 አመታት የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል ተብሏል። #huffpost

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሩሲያ በአንድ ሌሊት 450 ድሮን እና 70 ሚሳዔል ወደ ዩክሬን አስወነጨፈች።

ሞስኮ ከሁለተኛው ዙር ድርድር በፊት በዩክሬን ላይ ከባድ የአየር ላይ ጥቃት ፈጽማለች ተብሏል።

ጥቃቱ በአምስት የዩክሬን ክልሎች ላይ የተፈፀመ ሲሆን በዋናነት የሀይል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተገልጿል።

የውሃ እና የኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫዎች ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል ተብሏል።

ጥቃቱ ሌሊት ላይ ከተፈፀመ በኋላ ዛሬ ጠዋት ላይ 1 ሺሕ 170 የመኖሪያ አፓርትመንቶች መብራት እንደተቋረጠባቸው ተገልጿል።

በዚህ ጥቃት የሞት ሪፖርት አለመኖሩ ቢገለጽም፣ 10 ሰዎች ግን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሩሲያ በትናንትናው እለት በፈፀመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት 12 የማዕድን ባለሙያዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል። #euronews

@EyobTikuye  @ThiahETH

Читать полностью…

THIQAH

በናይጄሪያ በደረሰ የጭነት መኪና አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከሌጎስ ወደ ኢባዳን በሚወስደው መንገድ በደረሰው በዚህ አደጋ 23 መንገደኞች መጎዳታቸውን የፌደራል መንገድ ደህንነት ኮርፕ (FRSC) አስታውቋል።

የአደጋው ምክንያት ፍጥነት ያስከተለው መጋጨት እንደሆነ ተገልጿል።  #naijanews

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ሀቫና ከዋሽንግተን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ናት ግን ለድርድር የማይቀርቡ ነገሮች አሉ"  የኩባ ዲፕሎማት

ኩባ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ንግግር መጀመሯን ጠቆመች።

የኩባ የውጭ ሚኒስትር ዲዔታ ካርሎስ ፈርናንዴዝ ዲካሲዮ "ትርጉም ያለው እና ሀላፊነት የተሞላበት ድርድር ለማድረግ መዘጋጀታችንን የአሜሪካ መንግስት ያውቃል" በማለት የሀገራቸውን አቋም አንፀባርቀዋል።

ዲካሲዮ "ሀቫና ከዋሽንግተን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ናት፣ ግን ለድርድር የማይቀርቡ ነገሮች አሉ" ብለዋል።

"የህገመንግስት ለውጥ እና ሶሻሊስት መንግስት መቀየር በፍጹም ተቀባይነት የለውም" ሲሉም ተናግረዋል።

"ኤምባሲዎች አሉ፣ ንግግሮች አሉ፣ መልዕክት እንለዋወጣለን፣ ግን በጠረጴዛ ዙሪያ የተደረገ ውይይት አልተካሄደም" ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ'ለት ኩባ ለድርድር እንድትዘጋጅ ካልሆነ ግን ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። #aljazeera

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" - ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በዛሬ የፓርላማ ማብራሪያቸው አሜሪካ ስለህዳሴ ግድቡ በተደጋጋሚ ለምትለፍፈው ጉዳይ እክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ "ለህዳሴ ግድቡን በገንዘብ ረድታለች" በማለት ከሦስት ጊዜ በላይ መናገራቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በዋይትሃውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ "ዩናይትድ ስቴትስ የህዳሴ ግድብን በገንዘብ በማገዟ ኃላፊነት ትወስዳለች" ሲሉ ተደምጠው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ደግሞ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ "በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" ሲሉ እክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

"በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ ጠቋም በሀገር ውስም በከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨክነው በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከናወነ ፕሮጀክት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

አቢይ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች እምብዛም ስለሌሉ ወጣቶች ለስራ አጥነት ጨምር እየተጋለጡ በመሆኑ ምላሽ እንዲሰጡ ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ሲሆን፣ ከዚህ ንግግራቸው አስከትለውም፣ "ግን በዚህ አላበቃም፤ ህዳሴ ከአፍሪካ አንደኛውን ሰርተናልና ሌላ አያስፈልግም እኮ አላለችም ኢትዮጵያ" ብለዋል።

"በአፍሪካ ሦስተኛውንም ኮይሻ እየገነባን ነው ያለነው። የንፋሱን ሳንጨምር። በርካታ ፕሮጀክቶች ይሰራሉ" ነው ያሉት።

"'ፕሮጀክቶ ቋሟል፤ ሜጋ፣ ሜጋ ፕሮጀክት የለም' ለተባለው። እውነት ነው ፕሮጀክት የለም። ግን ከአፍሪካ አንደኛው ኤርፓርት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል" ሲሉ መልሰዋል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

150 ሀገራት በዱባይ "የ2026 የዓለም መንግስታት ጉባኤ (World Governments Summit 2026)"  ይሳተፋሉ ተባለ።

በሀገሪቱ ታሪክ ትልቅ የዓለም ሀገራት በሚሳተፉበት የመጀመሪያ ስብሰባ ከ35 በላይ የሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል ተብሏል።

ስብሰባው ከነገ ፌብሩዋሪ 3 ጀምሮ እስከ 5 "የወደፊት አስተዳደር መቅረፅ" በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከ6000 በላይ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ጉባኤ ከ500 በላይ የሚሆኑት በሚኒስትር ደረጃ የተጋበዙ ናቸው ተብሏል።

በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ
- አስተዳደር፣
- ቴክኖሎጂ፣
- ቱሪዝም፣
- ንግድ፣
- ሎጂስቲክስ፣
- አቪየሽን
- የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ውይይት የሚደረግባቸው አጀንዳዎች መሆናቸው ተጠቁሟል። #indiatoday

@EyobTikuye @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

ኢራን የአውሮፓ ሀገራት ወታደሮችን "የሽብር ድርጅት" ስትል ሰየመች።

ሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ጦር በኢራን የአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል ተብሏል።

የቴህራን ውሳኔ ከቀናት በፊት የአውሮፓ ህብረት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በአሸባሪነት በመፈረጁ የተወሰደ የአፀፋ እርማጃ ነው ተብሏል።

ህብረቱ 15 የኢራን ባለስልጣናትን እና አብዮታዊ ዘብን ከአልቃይዳ እና ሃማስ እኩል በአሸባሪነት ዝርዝር አካቷል።  #militartyny

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የናይጄሪያ ጦር በቦኮሃራም ኮማንደር እና 10 የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ጦሩ "በአማፂ" ሀይሉ አመራሮች እና አባላት ላይ "እርምጃ የወሰደው" በቦርኖ ግዛት ዘመቻ ማካሄድ በመጀመሩ እንደሆነ ገልጿል።

በቦኩሃራም የስልጣን እርከን ሁለተኛ ላይ የሚገኘው እና በሳምቢሳ ደን የሚንቀሳቀሰው አቡ ካሊድ የተባለው አዛዥ ህይወቱ ማለፉን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ካሊድ በቦርኖ ግዛት ዘመቻዎችን በመምራት እና የሎጂስቲክ አቅርቦትን በማሳለጥ ጉዳት እንድደርስ አድርጓል ሲል ወንጅሏል።

በናይጄሪያ ጦር በኩል የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።

ቦኮሃራም በናይጄሪያ መንቀሳቀስ የጀመረው ከ2000 ጀምሮ ነው። በ2009 በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐንን ህይወት ቀጥፏል።

ቡድኑ በ2015 ደግሞ፦
- በካሜሮን፣
- ቻድ
- ኒጀር በፈጸመው ጥቃት ከ2000 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በ100 ሺዎች ተፈናቅለዋል። #anadoluagency

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በጦርነት ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ከፓርት ሱዳን ወደ ካርቱም በረራ ተጀመረ።

በሱዳን በፈረንጆቹ 2023 በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ተቋርጦ የነበረው ከፖርት ሱዳን ወደ ካርቱም የሚደረገው የአየር በረራ በድጋሚ ተጀምሯል።

በዚህም ሲቪል ተሳፋሪዎችን የጫነች የመጀመሪያዋ አውሮፕላን ከሁለት ዓመታት መቋረጥ በኋላ በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፋለች።

ይህ በረራ መጀመሩ የሱዳን አየር መንገድ የትራንስፖርት ዘርፉን ለመደገፍ፣ ከተሞችን በድጋሚ ለማገናኘትና የዜጎችን የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ለመቅረፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑ ተነግሯል።

በረራው ዳግም መጀመሩ ለሱዳን ትልቅ ስኬት መሆኑ ተጠቅሷል። ሂደቱ ለሀገሪቱ አዲስ የሰላም፣ የመረጋጋት እና የማገገም ምዕራፍ ማሳያ ሆኗል።

የሱዳን አቪዬሽን እምብርት የሚገኘው የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስራ አቁሞ መቆየቱ በሀገሪቱ የአየር እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ ነበር። #Menaheria #AnadoluAgency

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፓኪስታን 145 አማፂያን ላይ እርምጃ መውሰዷን አስታወቀች።

እርምጃው በሀገሪቱ ጦር ላይ ከደረሰው ከባድ ጥቃት በኋላ እርምጃ መውሰዱን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ጦሩ የአጸፋ እርምጃውን የወሰደው በባሎቺስታን ነፃነት ጦር (BLA) ላይ እንደሆነ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ቡድኑ በፓኪስታን ላይ የሚፈጽማቸው ጥቃቶች በህንድ እና  አፍጋሃኒስታን እገዛ ነው ሲል ሁለቱን ጎረቤት ሀገራት ተጠያቂ አድርጓል።

ሁለቱም ሀገራት በበኩላቸው፣ በፓኪስታን የውስጥ ጉዳይ እጃቸው እንደሌለበት ከወራት በፊት አስታውቀዋል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል።  

ፓኪስታን "በህንድ ይደገፋሉ" ባለቻቸው "ጥቃት አድራሾች" ከ120 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከሰሞኑ ተናግራ ነበር።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አሜሪካ ኢራንን ካጠቃች ኢራናውያን ጠንካራ ምላሽ ይሰጣሉ፣ በአሜሪካ የተጀመረው ጦርነት ደግሞ በቀጠናው ይስፋፋል" - አያቶላሕ ኮሚኒ

"ተስፋ አደርጋለሁ ስምምነት ላይ እንደርሳለን፣ ከተስማማን ጥሩ ነው፣ ካልተስማማን የሚፈጠረውን እናያለን" - ትራምፕ

ኢራን ህይወታቸው ያለፈ 2 ሺሕ 986 ተቃዋሚዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደርጋለች።

ለሦስት ሳምንታት በቀጠለው አመጽ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ጠቅላይ ድምር ግን 3 ሺሕ 117 ሆኗል።

የኢራን ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የሟቾችን ስም በዝርዝር ማሳወቁን "ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያመጣል" ሲል አስታውቋል።

"የሟች ቤተሰቦች ያለ ድጋፍ አይኖሩም፣ ሟቾቹ የዚህ ምድር ተወላጆች ናቸው" በማለትም ለተጎጂ ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጿል።

በተያያዘ መረጃ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ፣ "አሜሪካ ኢራንን ካጠቃች አካባቢያዊ ጦርነት ይነሳል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

"ጦርነትን የምንጀምር አይደለንም፣ ሌላ ሀገር ማጥቃት አንፈልግም" ብለዋል።

"ግን አሜሪካ ኢራንን ካጠቃች ኢራናውያን ጠንካራ ምላሽ ይሰጣሉ፣ በአሜሪካ የተጀመረው ጦርነት በቀጠናው ይስፋፋል" ሲሉ ገልጸዋል።

በአንፃሩ ትራምፕ፣ "ኢራን ከስምምነት ላይ እንደምትደርስ ተስፋ አለኝ" በማለት ከኮሚኒ የተለየ አስተያየት ሰጥተዋል።

በዚህም፣ "ተስፋ አደርጋለሁ ስምምነት ላይ እንደርሳለን፣ ከተስማማን ጥሩ ነው፣ ካልተስማማን የሚፈጠረውን እናያለን" ነው ያሉት።

የኮሚኒ እና ትራምፕ አስተያየት የተሰማው የሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት ጦርነቱን ለማስቀረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እያደረጉ በሚገኙበት ወቅት ነው።  #theindependent #trtworld

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ዶሃ ሀማስን በመደገፍ፣ በገንዘብ በማገዝ እና በኳታር ቢሮ እንዲከፍት በማድረግ ተባብራለች" - ያየር ላፒድ

የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲ መሪና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ ኳታርን "ጠላት ሀገር" ናት አሉ።

ፖለቲከኛው፣ "ዶሃ ሀማስን በመደገፍ፣ በገንዘብ በማገዝ እና በኳታር ቢሮ እንዲከፍት በማድረግ ተባብራለች" ሲሉ ወንጅለዋል።

"ኳታር ከእስራኤል ደህንነት እና የፖለቲካ ፍላጎት በተቃራኒው ቁማለች" ብለዋል።

ላፒድ በኤክስ ገፃቸው ላይ "ኳታር የእስራኤል ጠላት ሀገር ተብላ እንድትፈረጅ ንቅናቄ ጀምሪያለሁ" ሲሉ አስታውቀዋል።

"ነገ ለኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) ረቂቅ እቅድ አቀርባለሁ" ሲሉም ገልጸዋል። ኳታር በጉዳዩ ላይ የሰጠችው አስተያየት የለም።

ከ2012 ጀምሮ ሀማስ ዋና ቢሮውን ከፍቶ እንዲንቀሳቀስ የፈቀደችው ዶሃ፣ የጋዛ ጦርነት እንዲቆም ከሚያደራድሩት ወገን አንዷ ናት። #thenational #jeusalempost

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በአርጀንቲና በሬክተር ስኬል 4.0 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በሳልታ ግዛት በምትገኘው የዲሎስ አንደስ ከተማ ነው።

በአደጋው የደረሰ ጉዳት አለመመዝገቡም ተገልጿል። #volcanodiscovery

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በህንድ የሚደገፉ ናቸው" በተባሉ ታጣቂዎች ከ120 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከ120 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፓኪስታን ጦር አስታውቋል።

ጦሩ በባሎችስታን ግዛት "አሸባሪዎች" ሲል የጠራቸው ታጣቂዎች ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል።

ከሟቾቹ 33 ንጹሐን ሰዎች፣ 92 የታጣቂ ቡድኑ አባላት እና 15 የመንግስት የፀጥታ አካላት ናቸው ተብሏል።

ታጣቂዎቹ እስር ቤት፣ የፖሊስ ጣቢያ እና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስፍራዎችን ኢላማ ማድረጋቸውን ጦሩ ገልጿል።

የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ በትናንትናው እለት የፓኪስታን ጦር በወሰደው እርምጃ "ቢያንስ 67 ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል" ሲሉ ገልጸው ነበር

ናቅቪ ዛሬ ለደረሰው ጉዳት "ጥቃት አድራሾቹ በህንድ የሚደገፉ ናቸው" ሲሉ ህንድን ተጠያቂ አድርገዋል።

ኒውዴልሂ ከኢስላማባድ ለቀረበባት ክስ የሰጠችው ምላሽ የለም።

የባሎች ሊበሪሽን አርሚ (BLA) ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት እንደሚወስድ አስታውቋል።#theguardian

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ የኢራንን ድሮን መትታ ጣለች።

አንድ የኢራን ድሮን በገልፍ ወደሚገኘው የአሜሪካ አየር ሀይል ሲበር ነው ጥቃቱ የተፈፀመው ተብሏል።

ኢራን ኢላማ ያደረገችው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ ያሰማሩት  ዩኤስኤስ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ ስለተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካም ይሁን የኢራን ባለስልጣናት የሰጡት ማረጋገጫ የለም ነው የተባለው።

የአሜሪካ ባህር ሀይል የኢራንን ጥቃት ማክሸፉ የተሰማው ኢራን እና አሜሪካ ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን በገለፁ ማግስት ነው።#ukdefencejournal #reuters

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የሱዳን ጦር ባደረሰው የድሮን ጥቃት ህፃናት ጨምር ተገደሉ።

የሱዳን ጦር ካዱግሊ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል።

የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች (RSF) ከተማዋን ለቀው ሲወጡ በፈፀሙት የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል።

ከሟቾቹ ውስጥ ሦስቱ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል።

የከተማዋ ነዋሪዎች የሀገሪቱ ጦር ሲገባ በአደባባይ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

ተመድ በካዱግሊ ከተማ የርሃብ አደጋ መከሰቱን ያወጀው ከአንድ አመት በፊት ቢሆንም ያለፉት ሁለት ወራት በተለየ መልኩ የምግብ እጥረት መፈጠሩን አስታውቋል። #dailysabah #swedenherald

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ጋና ለአፍሪካውያን የምትሰጠውን ዜግነት በጊዚያዊነት አቆመች።

አገልግሎቱ የቆመው "በጊዚያዊነት ነው" የተባለ ሲሆን፣ መቼ እንደሚመለስ ግን የተባለ ነገር የለም።

ውሳኔው የተላለፈው "ውድ፣ ውስብስብ እና ከባድ" ነበር የተባለውን አሰራር ዳግም ለመፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል።

ከ2016 ጀምሮ አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው ተወላጆች ለዜግነት የሚያመለክቱበት አሰራር እንደነበር የሀገሪቱ መንግስት አስታውሷል።

ባርነትን ጨምሮ በተለያየ ምክንያቶች ከአፍሪካ የተሰደዱ ሰዎችን አፍሪካዊ ማንነት ለመስጠት በማለት መጀመሩም ተገልጿል።

በዚህ ፕሮግራም ከ1000 በላይ አፍሪካውያን የጋና ዜግነት ማግኘት መቻላቸው ተመልክቷል።   #saharareporters

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በፖላንድ መነሻው ያልታወቀ ድሮን በወታደራዊ ካምፕ አጠገብ ተከሰከሰ።

ከየት እንደተላከ ያልታወቀው ሰው አልባ ድሮኑ አሪየል ቬህክል (UAV) ስሪት መሆኑን የፖላንድ ጦር ገልጿል።

ጦሩ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ያረፈው በወታደራዊ ካምፕ አጠገብ መሆኑ ከፍተኛ ጥርጣሬ ተፈጥሯል ብሏል።

የድሮኑ መነሻ ቦታ እና የተላከበት አላማ በግልጽ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው ሲል አስታውቋል።

የፖላንድ ጦር ካሁን በፊት በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በድንበር አቅራቢያ ከሞስኮ የተላኩ ድሮኖችን መያዙ ይታወቃል። #aa

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሞሮኮ በከባድ ጎርፍ ተመታች።

በጎርፍ የተጎዳችው ሞሮኮ ከ50 ሺሕ በላይ ዜጎቿን ከአካባቢው አስወጥታለች።

የክሳር ኤልከቢር ከተማ ግማሽ የሚሆኑት ነዋሪዎች በአደጋው ምክንያት አካባቢውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል ተብሏል።

በከተማዋ ለሳምንት የጣለው ዝናብ ከባድ ጎርፍ ማስከተሉ ተገልጿል።

ክሳር ኤልከቢር ከተማ ከዋና ከተማዋ ራባት በሰሜን አቅጣጫ 190 ኪሎሜትር ርቃ ትገኛለች ተብሏል።  #asiaone

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሩሲያ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት 12 የማዕድን ባለሙያዎች ተገደሉ።

ጥቃቱ በዩክሬን ኢነርጂ ካምፓኒ (DTEK) ንብረት በሆነ አውቶብስ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።

ድርጊቱ "የሽብር ጥቃት" ሲሉ  የገለጹት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ 16 ሰዎች መጎዳታቸውን በኤክስ ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።

የሩሲያ ጥቃት መፈጸም የተሰማው ሁለተኛው ዙር የአቡ ዳቢ ውይይት ረቡዕ ለማካሄድ ቀጠሮ በተያዘበት ወቅት ነው። #independent

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፓኪስታን 177 የባሎች ሚሊሺያዎች ህይወታቸው ማለፉን አስታወቀች።

ይህ እርምጃ የተወሰደው ዘመቻው ከተጀመረ በ48 ሰዓት ውስጥ መሆኑን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።

ጦሩ በአሁኑ ወቅት በአፍጋኒስታን በሚያዋስነው ድንበር መቀጠሉን ገልጿል። #theindependent

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በአውሮፓ ህብረት እና በኔቶ መካከል ሰፊ ልዩነት ተፈጥሯል" - ካጃ ካላስ

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ፣ "በህብረቱ እና በኔቶ መካከል ሰፊ ልዩነት ተፈጥሯል" በማለት የአህጉሪቱ ደህንነት አደጋ ላይ መውደቁን አሳወቁ።

ከአሜሪካ ጋር ያለው ግንኙነት መላላቱን የጠቆሙት ኃላፊዋ፣ "አውሮፓን ያማከለ ጦር በሙሉ አደጋ ውስጥ ነው" ነው ያሉት።

"አውሮፓ የጋራ ጦር ያስፈልጋታል የሚሉ ሰዎች የጉዳዩን ክብደት አልተረዱም" ሲሉም ተናግረዋል።

"የኔቶ አካል ከሆንክ በቃ የተናጠል ጦር መመስረት አትችልም" ያሉት ኃላፊዋ፣ ማን ለማን ትዕዛዝ ይሰጣል፣ ኳሷ በጠረጴዛው መሀል ትሽኸረከራለች፣ ይህ በጣም በጣም አደገኛ ነው" በማለት አሳሳቢነትቱን አስረድተዋል።

በቅርቡ የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ የአውሮፓ ደህንነት ያለ አሜሪካ እንደማያረጋግጥ መናገራቸው በአንዳንድ አባል ሀገራት ላይ ትችት አስከትሏል።

ትራምፕ አሜሪካ ግሪንላንድን ትጠቀልላለች ማለታቸውን ተከትሎ 8 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጦራቸውን ወደ ግሪንላንድ ልከዋል። #thederrick

@EyobTikuye   @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በጥር 2026 ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የገቡ ስደተኞች ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ተመዘገበ።

በጥር 2026 ብቻ 933 ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል።
ይህም ከ2021 በኋላ ዝቅተኛው የስደተኞች ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር አነስተኛ ነው የተባለ ሲሆን፣ በጥር 2025 የገቡት 1 ሺሕ 098 ስደተኞች እንደነበሩ ተገልጿል።

በዚሁ አመት 41 ሺሕ 472 ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ መግባታቸው እና ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ህገወጥ ስደተኞች ከሀገር መውጣታቸው ተመላክቷል።

ዩናይትድ ኪንግደም ከፈረንሳይ ጋር ያደረገችው ስምምነት ለስደተኞች ቁጥጥር አመቺ ሁኔታ ፈጥሮላታል ተብሏል። #bbc

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የአክሲዮን፣ የወርቅ እና የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ።

በአንድ ሳምንት የወርቅ ዋጋ ሲሸጥ ከነበረበት 5 ሺህ 600 ዶላር ወደ 4 ሺህ 530 ዝቅ አለ።

በዚህም በ6% ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

ብር በተመሳሳይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተሸጠበት ከፍተኛ ዋጋ 120 ዶላር ወደ 75 ዶላር ዝቅ ብሏል።

በዚህም በ12% ልዩነት አስመዝግቧል።

በደቡብ ኮሪያ ነዳጅ በበርሚል 66 ዶላር በመሸጥ ከበፊቱ የ5% ቅናሽ ታይቶበታል ተብሏል።

የገበያ ልዩነቱ የተከሰተው በፕሬዚዳንት ትራምፕ የታሪፍ እርምጃ የተፈጠረው የንግድ ጦርነት ምክንያት ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ በዓለም ገበያ የአክሲዮን፣ ወርቅ እና ነዳጅ ዋጋ መቀነስ ምክንያት በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ በጀት እና የወለድ ችግር ነው ተብሏል።#theguardian #thetelegraph #trtworld

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"እኔ የምፈልገው ካናዳን 51ኛዋ ግዛት ማደረግ ነው። ግሪንላንድ 52ኛዋ፣ ቬንዙዌላ ደግሞ 53ኛዋ ግዛት ሊሆኑ ይችላሉ" - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳ፣ ቬንዙዌላ እና ግሪንላድን "የአሜሪካ ግዛቶች አደርጋለሁ" በሚል ዝተዋል።

"ግሪንላንድን እንገዛታለን እንጂ አንወርም" ያሉት ትራምፕ፣ "ግሪንላንድን 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት የማድረግ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። እኔ የምፈልገው ካናዳን 51ኛዋ ግዛት ማደረግ ነው። ግሪንላንድ 52ኛዋ፣ ቬንዙዌላ ደግሞ 53ኛዋ ግዛት ሊሆኑ ይችላሉ" ሲሉም ተናግረዋል።

ትራምፕ ይህን በአንድ ዝግ የእራት ግብዣ ወቅት መግለጻቸውን የአሜሪካ ጋዜጣ ዘግቧል።

የጄፒ ሞርጋን አለቃ ጄሚ ዲሞን እና የፌዴራል ሪዘርቭ ሊቀመንበር ጄሮም ፓውል በተገኙበት በዚህ ዝግጀት ላይ የትራምፕ ንግግር በአድማጮች ዘንድ ዝምታን እንዳስተናገደ ዘገባው ጠቅሷል።

ትራምፕ ግሪንላንድ የአሜሪካ መሆን እንዳለባት፤ ካናዳን ደግሞ "51ኛዋ ግዛት" አድርጎ የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ሲያነሱ ቆይተዋል። #Sputnik #AmericanNewspaper

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ከራፋህ ድንበር መከፈት በኋላ 20,000 ታካሚዎች ወደ ግብፅ እንደሚሄዱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት ብቻ 150 ፍልስጤማውያን ለህክምና ተጉዘዋል ተብሏል።

ቁስለኞቹ ወደ ግብፅ ሂደው ከታከሙ በኋላ ወዲያውኑ በአንድ ቀን ውስጥ ይመለሳሉ ነው የተባለው።

የራፋህ ድንበር በጋዛ ጦርነት ምክንያት በእስራኤል ከተዘጋ ከአመት ከዘጠኝ ወራት በኋላ በትናንትናው እለት ተከፍቷል።

ድንበሩ የሰብዓዊ እርዳታ፣ የህክምና ቁሳቁስ እና የሰዎች መተላለፊያ በመሆኑ ሁለት አመት ለሚጠጋ ጊዜ መዘጋጀቱ የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ አባብሶታል ተብሏል።   #sputnikafrica

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ሁለተኛው ዙር ውይይት ፌብሩዋሪ 1 ይካሄዳል" - ሩሲያ

"ድርድሩ የሚካሄደው ፌብሩዋሪ 4 እና 5 ነው" - ዩክሬን

የሩሲያ እና ዩክሬን ሁለተኛ ዙር ድርድር የሚካሄድበት ቀን በተደራዳሪ ወገኖች መካከል አወዛጋቢ ሆኗል።

ሩሲያ የአቡ ዳቢው ንግግር በዛሬው ዕለት እንደሚካሄድ ገልጻለች።

በተባበሩት አረብ ኤምሬት መድና አቡ ዳቢ የሚካሄደው የሁለቱ ሀገራት ድርድር የሚካሄደው ዛሬ ሌሊት ፌብርዋሪ 1 መሆኑን የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ አስታውቀዋል።

ፔስኮቭ፣ "ሁለተኛው ዙር ውይይት ፌብሩዋሪ 1 ይካሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል።

በአንጻሩ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ደግሞ፣ ውይይቱ የፊታችን ረቡዕ እና ሐሙስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

"የእኛ የድርድር ልዑክ ሪፖርት አቅርቧል፣ ቀኑ ወደ ቀጣዩ ሳምንት ያልፋል" ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ዘለንስኪ፣ "ድርድሩ የሚካሄደው ፌብሩዋሪ 4 እና 5 ነው" በማለት የዛሬ ሌሊቱ ስብሰባ እንደማይካሄድ ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አደራዳሪዋ ሀገር አሜሪካም ሆነች አረብ ኤምሬት የሰጡት ይፋዊ መግለጫ የለም። #sputnik #thenational

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የኢራቅ ምርጫ በድጋሚ ተራዘመ።

የኢራቅ ፓርላማ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ለሁለተኛ ጊዜ ማራዘሙ ተገልጿል።

ምርጫው የተራዘመው በኢራቅ በሚገኙት የኩርድ ፖለቲካ ሀይሎች ከስምምነት ባለመድረሳቸው ነው ተብሏል።

ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ ሊካሄድ የታሰበው የመጀመሪያው ምርጫ ለዛሬ እሁድ መራዘሙ ቢገለፅም ዛሬም እንደማይካሄድ ታውቋል።

የኢራቅ ህገመንግስታዊ ፍርድቤት ሀገራዊ ምርጫውን በማካሄድ ህገመንግስታዊ ስርዓትን ማክበር እንደሚገባ አሳስቧል። #trtworld

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤል የራፋህ ድንበርን በግማሽ ከፈተች።

ከግንቦት 2024 ጀምሮ ላለፉት አንድ አመት ከዘጠኝ ወራት ተዘግቶ የቆየው ይህ ድንበር ዛሬ መከፈቱን የጋዛ ጤና ሚኒሰቴር አስታውቋል።

እስራዔልን ከግብፅ ጋር የሚያዋስነው የራፋህ ድንበር መዘጋቱ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተፈለገው መጠን እንዳይደርስ እክል መፍጠሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን ያወገዙት አለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እስራኤል ድንበሩን በአስቸኳይ እንዳትከፍት ተደጋጋሚ ጥሪ በማቅረብ ጫና ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም። #ashraqalawusat

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…
Subscribe to a channel