thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

"በ7ኛው ዙር ምርጫ ራሴን በዕጩነት ላለማቅረብ መወሰኔን ለሕዝቤ ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ" - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ምን አሉ?

"ባለፉት ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ በኩሩው የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ተመርጨ፣ እናንተን ወክዬ፣ ለሕዝባችን ሀቀኛ ድምፅ በመሆን ለማገልገል በመቻሌ ታላቅ ክብርና ኩራት ይሰማኛል።

በመጪው 7ኛው ዙር ምርጫ ራሴን በዕጩነት ላለማቅረብ መወሰኔን ለሕዝቤ ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ።

ለዚህ ውሳኔ ያበቃኝ ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ካለው ተጨባጭ ነባራዊ  ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው" ብለዋል።

"ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል አለመኖሩ እና በፖርላማ ውስጥ ተጨማሪ 5 ዓመታትን በመቆየቴ ለህዝቤ የሚያበረክተው የረባ ጥቅም የሌለው መሆኑንም ተረድቻለሁ" ብለዋል።

ስለዚህ የ6ኛው ዙር ፓርላማ እስኪጠናቀቅ ድረስ ባሉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደራሴነት ስራየን ቀጥየ ሰኔ መጨረሻ ላይ የዚህን ዙር የአገልግሎት ዘመኔን የማጠናቅቅ ሲሆን፤ ወደፊት ሀገሬን እና ህዝቤን እንዴት ለማገለግል እንደምፈልግ የማሳውቅ ይሆናል" ሲሉም ጠቁመዋል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሌተናል ጄነራል ቭላድሚር አሌክሲቭ በሞስኮ ከተማ በጥይት ተመቱ።

የሩሲያ ጦር ኢንተሊጀንስ ኤጄንሲ (RMIA) ም/ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ቭላድሚር አሌክሲቭ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ተብሏል።

ሰውነታቸው በተለይ በጀርባቸው በኩል በተደጋጋሚ በብዙ ጥይት መመታታቸው በምርመራ ተረጋግጧል ተብሏል።

የጥቃቱ ፈፃሚ እስካሁን አለመታወቁን ጉዳዩን የያዘው የምርመራ ቡድን አስታውቋል።

ሌተናል ጄነራል ቭላድሚር አሌክሲቭ በ2016 በሳይበር ጥቃት ማቀነባበር ወንጀል አሜሪካ፣ ከ2019 ጀምሮ ደግሞ በአውሮፓ ሀገራትም ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል ተብሏል።

የጄኔራሉ ላይ ጥቃት የተሰማው ሩሲያ እና ዩክሬን በአሜሪካ አሸማጋይነት በአቡዳቢ ውይይት አድርገው እስረኞችን ለመለዋወጥ እና የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል ከተባለ በኋላ ነው።

ሩሲያ ከጦርነቱ በኋላ ከአምስት በላይ ታላላቅ ጄነራሎቿን በሞስኮ በሚፈጸም ጥቃት አጥታለች። #meduza

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ በናይጀሪያ የተፈጸመውን የንጹሐን ጭፍጨፋ አወገዘ።

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ፍትህ እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

ጉተሬዝ በደረሰው ጥቃት ከልብ ማዘናቸውን ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለናይጄሪያ ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።

ለተጎጂዎች ማገገምን የተመኙት ዋና ፀሐፊው፣ ተመድ ጥቃት ያደረሱ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ለማድረግ የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ ተናግረዋል። 

በናይጄሪያ ክዋራ ግዛት አሸባሪዎች በፈፀሙት ጥቃት ከ200 በላይ ንጹሐን ህይወታቸው አልፏል። #newsagencyofnigeria

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ናይጄሪያ የሞት ሜዳ መሆኗን ያሳያል" - የቀድሞው የናይጄሪያ ባለስልጣን

የቀድሞው የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቲኩ አቡበከር በሀገሪቱ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አወገዙ።

የፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒቡ የቅርብ ሰው የነበሩት አቡበከር፣ "ይህ ወንጀል የተፈጸመው በሀገሪቱ ሦስት ግዛቶች ማለትም ክዋራ፣ ቤትሱ እና ካትሲና ግዛት ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ናይጄሪያ የሞት ሜዳ መሆኗን ያሳያል" ሲሉ የፕሬዝዳንት ቲኒቡን አስተዳደር ገልጸዋል።

አቡበከር፣ "ግድያው የተፈጸመበት ክስተት እና ፍጥነት መንግስት ዜጎቹን መጠበቅ እንደማይችል ያሳየ አጋጣሚ ነው" በማለት ወቅሰዋል።

"ብዙ አስክሬን እያየን የቲኒቡ ባዶ ውግዘት ምንም አይሰራም፣ የፀጥታ አካላት ንቁ መሆን አለባቸው ምላሽ ሰጭ ሳይሆን ቅድሚያ መከላከል የሚችሉ መሆን አለባቸው" ሲሉም አሳስበዋል።  #peoplesgazette

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የተፈጠረው ግጭት "ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አመላካች ነው" - ኧርቪን ማሲንጋ

አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በቅርቡ በጠለምት እና በራያ፣ በአፋር የተፈጠረው ግጭት "ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አመላካች ነው" አሉ።

ማሲንጋ፣ "ባሳለፍነው ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ነገር ለሰላምና መረጋጋት ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የሚያስታውስ ነው" ብለዋል።

አምባሳደሩ፣ "እኔ ምክንያታዊ ሆኜ በንቃት እወያያለሁ፣ ጠንካራ ስራዎችን እሰራለሁ፣ ያ ነው ለዘላቂ ሰላም አዋጭ መንገድ" ሲሉ መናገራቸውን ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመላክታል።  #usembasssyaddisababa

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤል ወደ ፍልስጤም የእርዳታ ድርጅት (UNRWA) የሚሄደውን ኤሌክትሪክ እና ውሃ አቋረጠች።

ድርጅቱ እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገባ የሰብዓዊ እርዳታ መከልከሏን ቀጥላበታለች ብሏል።

-የምግብ፣
-ውሃ፣
-ህክምና እና
-መጠለያ ቁሳቁሶች መግባት አልቻሉም ሲልም አስታውቋል።

በግብፅ እና በዮርዳኖስ ተከማችተው የሚገኙት የእርዳታ ግብዓቶች በእስራኤል ውሳኔ ምክንያት ማስገባት አለመቻሉን ገልጿል። #middleeastmonitor #trtworld

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፓኪስታን የተገደሉ ሚሊሺያዎች ቁጥር 216 መድረሱን አስታወቀች።

ለሳምንት በዘለቀውና ዛሬ በተጠናቀቀው ዘመቻ የአማፂያኑ አመራሮችን እና ወታደራዊ አቅም ማዳከሙን የፓኪስታን ጦር አስታውቋል።

ጦሩ በባሎቺስታን ሊበሪሽን አርሚ (BLA) ላይ በወሰደው እርምጃ የውጭ ሀገር የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ብሏል።

በዚህ ዘመቻ 50 ንፁሃን እና 22 የሀገሪቱ ጦር አባላት ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።

የፓኪስታን ጦር እርምጃ የወሰደው ለወራት የተደረጉ የድርድር ጥረት ባለመሳካቱ ነው ተብሏል። #aljazeera

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Update

ሩሲያ እና ዩክሬን እስረኞችን ለመለዋወጥ ተስማሙ።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ "ውጤታማ ውይይት ተደርጓል" ካሉ በኋላ በአምስት ወር ውስጥ በመጀመሪያ ዙር 314 እስረኞችን ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

"ተጨማሪ ውጤቶችን ለማየት ድርድሮች በመጪዎቹ ሳምንታት ይቀጥላሉ" ሲሉም ገልጸዋል።

የሦስትዮሽ ውይይቱ ለሁለተኛ ቀን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። #europelive

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ በፍልስጤም ለሚገኙ ተረጂዎች የሚያቀርበውን እርዳታ 20% ቀነሰ።

የፍልስጤም ስደተኞች የተመድ እርዳታ (UNRWA) የሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ማሽቆልቆል ለእርዳታ አቅርቦቱ መቀነስ ምክንያት እንደሆነው አስታውቋል።

ለጋሽ ሀገራት የገንዘብ እገዛ ለማድረግ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል።

የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቅርቡ "ተመድ የማይቀር የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ገብቷል" ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ አሜሪካ የአለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከትላልቅ አለማቀፍ ተቋማት መውጣቷ የገንዘብ አቅም እንድዳከም አድርጓል ተብሏል። #anadoluagency

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፓርላማው ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።

እንዲሁም፦
- የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

-የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)

- የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)

- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ

- የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) የቦርድ አባላት ሆነው ተሾመዋል።

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ለመጭው አርብ የተያዘው የአሜሪካና ኢራን ውይይት ተሰርዟል?

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በኤክስ ገፃቸው፣ "ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው የኑክሌር ውይይት አርብ ጠዋት 4 ሰዓት በሙስካት ይካሄዳል" ብለዋል።

በዚህም "ተሰርዟል" ተብሎ የተነገረለት፣ የኢራን እና የአሜሪካ ውይይት በተያዘለት ቀነ ገደብ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

አራግቺ፣ "ሁሉንም አስፈላጊ ሂደት ላመቻቹት የኦማን ወንድሞቻችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ብለዋል።

ድርድሩ በተያዘለት ቀጠሮ የሚካሄደው የአረብ እና ሙስሊም ሀገራት መሪዎች የፕሬዝዳንት ትራምፕን አስተዳደር ካሳመኑ በኋላ ነው ተብሏል።

የዋሽንግተን ባለስልጣናት ስብሰባው በተያዘለት ፕሮግራም እንዲካሄድ እና የኢራን ባለስልጣናት የሚሉትን እንዲሰሙ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል።

ባለስልጣናቱ ለአረብ ሀገራት መሪዎች ፍቃዳቸውን እንደገለጹ፤ ነገር ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው መናገራቸውን አስታውቀዋል።

አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ድርድር እንድታስቀጥል የሚጠይቁ ቢያንስ የዘጠኝ ሀገራት ባለስልጣናት መልዕክት መላካቸው ተገልጿል።

ውይይቱ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ የአሜሪካን አጋሮች ባከበረ መልኩ እና  ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን በሚያስቀጥል ሁኔታ እንድደረግ ተወስኗል ተብሏል።

በሌላ በኩል፦ እንደ ኢራን ኒውስ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ፣ የኢራን እና የአሜሪካ ውይይት ተሰርዛል ተብሎ ከሰዓታት በፊት ተዘግቧል።

የተሰረዘው የኢራን ባለስልጣናት "ከኑክሌር ፕሮግራም ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ለመወያየት ፍቃደኛ አለመሆናቸውና ማዕቀብ እንዲነሳላቸው በመጠየቃቸው ነው" ተብሎ ነበር። #x @aragchi #iraqinewsagency

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Update

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሩሲያ እና የዩክሬን የአቡዳቢ ውይይት መካሄድ ጀመረ።

በአሜሪካ አደራዳሪነት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ሁለተኛው ዙር ድርድር በዩናይትድ አረብ ኤምሬት እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ እስከ ሐሙስ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል።

ውይይቱ በምን ላይ እንደሚያተኩር በዝርዝር አልተገለጸም ተብሏል።

ሁለተኛው ዙር ድርድር መደረግ የነበረበት እሁድ ቢሆንም በዩክሬን ፍላጎት ተራዝሞ ዛሬ ለመካሄድ ችሏል። #rfe

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ቢያንስ 21 ፍልስጤማውያን "በእስራኤል ጥቃት" መገደላቸውን የሺፋ ሆስፒታል ገለጸ።

ከሟቾች ባሻገር የተጎጂዎች ትክክለኛ ቁጥር ደግሞ በትክከል አለመታወቁን የሆስፒታሉ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ከጋዛ ጦርነት በኋላ በእስራኤል የተገደሉት የፍልሥጤም ዜጎች ቁጥር ከ71 ሺሕ 800 በላይ መድረሱ ተገልጿል። #thewashingtontimes

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን የኤችአይቪ መድኃኒት በሰዎች ላይ ሙከራ አደረገች።

መድሃኒቱ ፍቃደኛ በሆኑ 20 ሰዎች ላይ በሙከራ መሰጠቱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሀገሪቱ 8 ሚሊዮን የሚደርሱ ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ ተገልጿል።

ይህም በአፍሪካ ትልቁ የቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ያለባት ሀገር አድርጓታል ተብሏል።

በ2023 በተደረገ ጥናት በሰብ-ሰሀራ አፍሪካ 25.6 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካ የሞከረችው መድሃኒት ውጤታማ ከሆነ ለቀጠናው ተስፋ  እንደሚሆን ተገልጿል። #eyewitnesnews

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በኤፍ-35 ተዋጊ ጄት ነው ተመትቶ የወደቀው፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" - የአሜሪካ ባህር ሀይል

የኢራን ድሮን በአሜሪካ ጦር መመታቱን አሜሪካ ማረጋገጫ ሰጥታበታለች።

የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ሲጓዝ እንደነበር የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ አስታውቋል።

የመርከቡ የባህር ኃይል ካፒቴን ቲም ሃውኪንስ፣ "የኢራን ሻህደድ-139 ድሮን ግልጽ ፍላጎቱ በማይታወቅበት ሁኔታ ወደ ጦር መርከቡ እየተጠጋ ነበር" ብለዋል።

"በኤፍ-35 ተዋጊ ጄት ነው ተመትቶ የወደቀው፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" ሲሉም ገልጸዋል።

ካፒቴኑ፣ "መርከቡን እና በመርከቡ የሚገኙ የባህር ሀይል አባላትን ለመጠበቅ የወሰድነው እርምጃ ነው፣ የተጎዳብን ሰው የለም" በማለት አብራርተዋል።

ኢራን ተፈጽሟል ስለተባለው ጥቃት እና ስለወደመባት ድሮን የሰጠችው ማብራሪያ የለም። #thewashingtonpost

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጃፓን የ3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘ።

ግንቦት 2018 ዓ/ም በኢትዮጵያ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጃፓን መንግስትና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የ3 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ለዚህም ሁለቱ አካላት ዛሬ በአዲስ አበባ መፈራረማቸው ተዘግቧል።

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አለፈ።

መስጊድ ላይ በተፈጸመው በዚህ ፍንዳታ ከሟቾች በተጨማሪ 169 ሰዎች ከባድ ጉዳት ማስተናገዳቸው ተገልጿል።

በዋና ከተማዋ በሚገኝ አንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የሟቾች እና የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል የኢስላማባድ ከተማ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢርፋን ሜሞን ተናግረዋል።

ፖሊስ የጥቃቱን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።

የፓኪስታን ፕሬዚዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ፣ በደረሰው ጥቃት ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል አልተገኘም።

የፓኪስታን ጦር ለአንድ ሳምንት በቆየው ዘመቻ ከ200 በላይ የባሎች አማፂያን ላይ እርምጃ መውሰዱን ባስታወቀ ከሁለት ቀን በኋላ ነው የቦምብ ፍንዳታው የተከሰተው።  #novinite #thewarpolitics

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የአቡዳቢው ውይይት በተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ።

በሁለተኛው ዙር የሦስትዮሽ ውይይት ከዩክሬን፣ ከሩሲያ እና ከአሜሪካ የመጡት ልዑካን ጦርነቱን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ውይይት አድርገዋል ተብሏል።

ውይይቱ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ባልተፈቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የተኩስ አቁም አተገባበር ሂደት በዋናነት የውይይቱ ማዕከል ነው ተብሏል።

ከውይይቱ በኋላ በወጣው የጋራ መግባቢያ ስምምነት እንደሚያሳየው "ገንቢ ነበር" የተባለው ውይይት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማተኮሩን አመላክቷል።

ውይይቱ በቀጣይ ሳምንት ለሦስተኛ ዙር ይቀጥላል ተብሏል። #ukrinform

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በናይጄሪያ በተፈጸመ ጭፍጨፋ 200 ሰዎች ተገደሉ።

በሀገሪቱ የክዋራ ግዛት ዘግናኝ ጥቃት መፈጸሙን ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒቡ አስታውቀዋል።

ቲኒቡ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላት ግድያ ወደተፈጸመበት አካባቢ መሰማራታቸውን አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በናይጄሪያ መንግሥት አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው የቦኮሃራም አማፂ ቡድን ነው ተብሏል። #peoplesgazette

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ኢራን ውይይቱን የፈለገችው ከጥቃት ለመዳን ነው" - ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራን የድርድር ፍላጎት "ከፍርሃት የመነጨ" መሆኑን መናገራቸው ተሰምቷል። ይህን ያሉለት ነገ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን የአሜሪካና ኢራን ውይይት ነው።

ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "እኛ እንድናጠቃቸው አይፈልጉም" ብለዋል። "ኢራን ውይይቱን የፈለገችው ከጥቃት ለመዳን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት ውይይት ነገ አርብ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። #shafaaqnews

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

314 እስረኞችን ሊለዋወጡ ነው።

ዘለንስኪ የአቡዳቢው ውይይት፣ "ቀላል አይደለም ግን ገንቢ ነው" ብለዋል። ይሁን እንጂ ከዩክሬን ጋር እስረኞችን ለመለዋወጥ መስማማታቸውን አልሸሸጉም።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ የአቡዳቢው ውይይት "ውስብስብ" መሆኑን ጠቁመዋል።

በአንጻሩ፣ ዘለንስኪ የፖላንድ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ተስክን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ሩሲያ እና ዩክሬን #314_እስረኞችን_ለመለዋወጥ መስማማታቸውን ገልጸዋል።

"ዩክሬን የሩሲያን ጭቆና የሚያስቆም ትክክለኛ ስምምነት ትፈልጋለች" ሲሉም ተናግረዋል።

በአሜሪካ አደራዳሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱ ሀገራት ውይይት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ጠቁመዋል።  #theguardian

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የካቲት 7 እና 8 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ይካሄዳል" - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ የካቲት 7 እና 8/2018 ዓ/ም 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ይካሄዳል ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ቲቃህ በመግለጫው የተገኘ ሲሆን፣ በዚህም የካቲት 4 እና 5 ደግሞ 48ኛው መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ወይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትሮች ስብሰባ በአፍሪካ ህብረት ይካሄዳል ማለታቸውን ሰምቷል።

ጎን ለጎን የካቲት 6 ደግሞ የአፍሪካ እና ጣሊያን ጉባዔ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ መሪ ሀሳብ፣ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት" የሚል መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ የመሪዎች ጉባዔ የባህር በር የማግኘት መብቷን እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ስላላት አቋም ለዲፕሎማቶች የምታንጸባርቅ መሆኑም ተገልጿል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በዩክሬን ኦፊሻል 55,000 የዩክሬን ወታደሮች መስዋዕት ሆነዋል" - ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በዩክሬን በሩሲያ ጦርነት የሞቱት ወታደሮችን ቁጥር ይፋ አደርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ፣ "በዩክሬን ኦፊሻል 55,000 የዩክሬን ወታደሮች መስዋዕት ሆነዋል" ብለዋል።

"ከሞቱት በላይ የጠፉት ይበልጣሉ" ሲሉም ተናግረዋል።

ነገር ግን ከሁለቱም ወገን በጦርነቱ የተጎዱ ወታደሮች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን በላይ መሆናቸውን ገለልተኛ ተቋማት አስታውቀዋል።

ከሳምንት በፊት ይፋ የተደረገ ጥናት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሩሲያ ወታደሮች ህይወታቸው አልፏል፣ ቆስለዋል ወይም ደግሞ ጠፍተዋል ብሏል።  #trtworld

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የፍልስጤም ራስ ገዝነት አላማ ካላረጋገጠ በሰላም ቦርድ የመቆየት ፍላጐት የለንም" - ኢንዶኔዥያ

ኢንዶኔዥያ ዶናልድ ትራምፕ ካቋቋሙት የሰላም ቦርድ ልትወጣ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

ፕሬዝዳንት ፕራቦ ሱቢያንቶ "የሰላም ቦርድ ከእኛ ፍላጐት ጋር የማይጣጣም ከሆነ የመቀጠል ግዴታ የለብንም" ማለታቸውን የኢንዶኔዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፕሬዚደንቱ "የፍልስጤም ራስ ገዝነት አላማ ካላረጋገጠ በሰላም ቦርድ የመቆየት ፍላጐት የለንም" ብለዋል።

"መጀመሪያ በጋዛ ሰላም ማስፈን፣ በመቀጠል በመላው ፍልስጤም ሰላም ማረጋገጥ፣ በመጨረሻም ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት፣ ያን ነው ማሳካት የምንፈልገው" በማለት አስረድተዋል።

ፕሬዝዳንቱ "የቦርዱ ፖሊሲዎች ከእኛ አቋም ጋር ካልተዛመዱ ራሳችንን ከተሳትፎ እናገላለን" ሲሉ ተናግረዋል።   #thestraightstimes

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ኒው ዴልሂ የሩሲያን ሀይድሮካርበን መግዛቷ ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ ያደርጋል" - ሩሲያ

ሩሲያ ህንድ ከማንኛውም ሀገር ነዳጅ የመግዛት ነፃነት አላት ስትል አስታወቀች።

የክሬሚሊን ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ "ሩሲያ ለህንድ ብቸኛ ነዳጅ አቅራቢ አለመሆኗን ታውቃለች" ብለዋል።

"እኛም ሆን ሌሎች አለማቀፍ የኢነርጂ ባለሙያዎች ህንድ ከተለያዩ ሀገራት ነዳጅ እና ፔትሮሊየም እንደምትገዛ እናውቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።

"ኒው ዴልሂ የነዳጅ ግብይት ማቆሟን በተመለከተ እስካሁን አላሳወቀችንም" ያሉት ቃል አቀባዩ፣ "በህንድ የነዳጅ ስትራቴጂ አዲስ ነገር የለም" ሲሉ ገልጸዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ "ኒው ዴልሂ የሩሲያን ሀይድሮካርበን መግዛቷ ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ ያደርጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ዛካሮቫ "በህንድ ከሚገኙ አጋሮቻችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትናንት ህንድ ከሩሲያ የምትገዛውን ነዳጅ እንደምታቆም፣ በምትኩ ከአሜሪካ ለመግዛት መስማማቷን አስታውቀዋል። #theweek

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia #AddisAbaba

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዲስ ሹመት ሊሰጣቸው ነው?

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር እንደዘገበው ከሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲ/ዳንኤል ክብረት "የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በፓርላማ ሊሾሙ ነው።"

"የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባል እንዲሆኑ ከታጩት ዘጠኝ ግለሰቦች ውስጥ ስድስቱ አዳዲስ ናቸው" ብሏል ዘገባው።

ይህም የሚፈጸመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው ተብሏል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ህንድ እና አሜሪካ የንግድ ስምምነት ፈጸሙ።

በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ በህንድ ላይ ጥላው የነበረው 50% ታሪፍ ወደ 18% ለመቀነስ እና ህንድ ከሩሲያ የምትገዛውን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተወስኗል።

ስምምነቱ ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከውን ነዳጅ 25% ይቀንሳል ተብሏል።

በ2025 ህንድ ወደ ሀገር ውስጥ ካስገባችው ነዳጅ የሩሲያ ነዳጅ ገበያ 33% እንደሸፈነ ተመላክቷል።

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት፣ ህንድ የቬንዙዌላን ነዳጅ እንድትገዛ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ አሁን ላይ በተደረገው ስምምነት የቬኔዙዌላ ነዳጅ በሩሲያ ተተክቶ ለህንድ ገበያ ይቀርባል። #smidgital

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በግሪክ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ስደተኞቹን ለማትረፍ አራት የባህር ጠባቂ ጀልባዎች እና በሄሊኮፕተር እገዛ 24 ሰዎች ከአደጋው ተርፈው ለህክምና ተወስደዋል ተብሏል።

ጀልባዋ ከየት እንደተነሳች እና ስንት ሰዎችን እንደጫነች ትክክለኛ መረጃ አለመገኘቱን የግሪክ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ስደተኞቹ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና አፍሪካ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚመርጡት በግሪክ በኩል ያለውን መግቢያ በር እንደሆነ ተገልጿል።  #novinite

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የምዕራባውያን 'ተኩስ አቁም የማስፈጸም' ዕቅድ የይስሙላ ነው" - ተንታኝ

-አሜሪካ፣
-አውሮፓ እና
- ዩክሬን ሩሲያ የዩክሬንን የሰላም ስምምነት "ከጣሰች" ተግባራዊ እናደርጋለን በሚል በቅንጅት አዘጋጅተውታል የተባለው የ" 'ወታደራዊ ምላሽ' "ዕቅድ፤ የዘለንስኪን አገዛዝ ለማባበል ያለመ ነው ሲሉ ሩሲያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ኮንስታንቲን ብሎኪን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

እነዚህ ተስፋዎች ዩክሬንን ወደ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመገፋፋት የታሰቡ ሊሆኑ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ጉዳዩ ገጽታን የመጠበቅ ነው፤ ምዕራባውያን ዩክሬንን እየተዋት እንዳልሆነ እና "የተወሰኑ ቁርጠኝነት እያሳዩ" እንደሆነ ለማሳየት ነው ብለዋል።

"ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚገቡት ቃል የግድ በተባለው መሰረት ይፈጸማሉ ማለት አይደለም" ነው ያሉት።

ዩክሬን፤ ከምዕራባውያን ደጋፊዎቿ ጋር በመሆን ሩሲያ የሰላም ስምምነቱን "ከጣሰች" ለሚሰጠው ደረጃውን የጠበቀ ምላሽ መስማማቷን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።

ዕቅዱ "የአሜሪካን ጦር የሚያካትት እና በምዕራባውያን የሚደገፍ የተቀናጀ ወታደራዊ ምላሽ" በመጨረሻ አማራጭነት አስቀምጧል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ የገለጸች ቢሆንም፤ ማንኛውም የኔቶ ጦር በሀገሪቱ ውስጥ መሰማራቱ ተቀባይነት እንደሌለው እና ውጥረቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቃለች። #Sputnik

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ስፔን ከ16 አመት በታች በሆኑ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ገደብ ልትጥል ነው ተባለ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በቀጣይ ሳምንት ህጋዊ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።

ሳንቼዝ በዱባይ የመንግስታት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር "የጥላቻ ንግግር፣ የወሲብ ድረገጾች እና ሀሰተኛ መረጃ በወጣቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል" ብለዋል።

"ልጆቻችን መጓዝ በሌለባቸው መስመር እያለፉ ነው፣ ይህ ከዚህ በኋላ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ እድሜን መሠረት ያደረገ እርምጃ እንድወስዱ ጠይቀዋል።

አውስትራሊያ ባለፈው ህዳር ወር ከ16 አመት በታች ለሚገኙ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያን በመከልከል የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

ፈረንሣይ ተመሳሳይ ውሳኔ ለማሳለፍ መዘጋጀቷን ፕሬዚዳንት ማክሮን ጠቁመዋል። #theguardian

@EyobTikuye  @thiqaheth

Читать полностью…
Subscribe to a channel