15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
#ኢቦላ
በኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ 15 ሰዎች ሞቱ።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወረርሽኙ እንደ አዲስ ማገርሸቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ወረርሽኙ ድንገት መከሰቱን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ 28 ሰዎች በበሽታው ተይዘው መገኘታቸውን የድርጅቱ መረጃ አመላክቷል።
አዲሱ የኢቦላ ወረርሽኝ የተከሰተው በሁለት የሀገሪቱ ከተሞች ማለትም ቡላፔ እና ምዌካ መሆኑ ተገልጿል።
#southchinamorningpost
@ThiqahEth
"ፀብ አጫሪ ድርጊቶችን እያየን ስለሆነ ኤፍ 16 ጀቶችን አሰማርተናል" - ፕሬዚዳንት ማዱሮ
"የቬንዙዌላ ባለሥልጣናት የዶሮ ጨዋታ እየተጫወቱ ነው" - ፕሬዚዳንት ትራምፕ
የቬኔዙዌላ የጦር ጄቶች የአሜሪካ መርከቦች በሚገኙበት ወታደራዊ ስፍራ ሲበሩ መገኘታቸው ተገለጸ።
የጦር ጄቶቿን በዚህ ስፍራ ስታሰማራ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ፣ "ፀብ አጫሪ ድርጊቶችን እያየን ስለሆነ ኤፍ 16 ጀቶችን አሰማርተናል" ብለዋል።
"ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ወደጦርነት እንገባለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ "በአሜሪካ ጦር ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ከሆነ መትተን እንጥላቸዋለን" ብለዋል። "የቬንዙዌላ ባለሥልጣናት የዶሮ ጨዋታ እየተጫወቱ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት በሚል ዩ ኤስ ኤስ ጃሰን ዱንሃም የተሰኙ መርከቦችን ወደ ቬንዙዌላ አሰማርተዋል። #anadoluagency
@ThiqahEth
#Ethiopia
ህዳሴ ግዱቡ ቢጠናቀቅም “ኤሌክትሪክ መቼም ቢሆን በነጻ አይሆንም" ሲል ተቋሙ ተናገረ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው ከተነሱት ነጥቦች መካከል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት ጉዳይ አንዱ ሲሆን፣ ግድቡ ቢጠናቀቅም ማህበረሰቡ ነጻ የኤሌክሪክ አገልግሎት እንደማያገኝ ተቋሙ በይፋ ገልጿል።
“ኤሌክትሪክ መቼም ቢሆን በነጻ አይሆንም አሁን ባለው ሁኔታ" ያለው ተቋሙ፣ "የህዳሴ መጠናቀቅ ኤሌክትሪክን ነጻ ያደርጋል በሚል በህብረተሰቡ እየተነሳ ያለው አስተያየት ትክክለኛ ስላልሆነ መታረም ይገባዋል” ብሏል።
“ህዳሴው እንደተገነባ ወዲያውኑ መብራት ይደርሳል የሚል እሳቤ አለ፡፡ ይሄ ሀሳብ ትክክለኛ አለመሆኑን ማንሳት ይቻላል” ሲልም አክሏል፡፡
እሰካሁን 54 በመቶ የኤሌክትሪክ ሽፋንን ለመድረስ ከአንድ ምዕተ ኣመት የዘለለ ጊዜ ወስዷል ያለው ተቋሙ፣ “ስለዚህ ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስ አሁን ህዳሴ ስለተመረቀ በተወሰኑ ጊዜያት ውስጥ ያን ማሳካት ይቻላል የሚለው ትክክለኛ ሀሳብ አይደለም” ሲል ተደምጧል፡፡
፧
አክሎም፣ “ነገር ግን አሁን ተደራስነቱን ለማሳደረግ የመንሰራውን ሥራ ይፋጠንልናል የሚለው ትክክለኛ ሀሳብ ነው” ብሏል።
የህዳሴ ግድቡ ዓመታዊ ኃይል የማመንጨት አቅሙ 15 ሺሕ 760 ጊጋ ዋት እንደሆነ፣ ይህም እስካዛሬ ኢትዮጵያ የነበራትን የኃይል ምንጭ በእጥፍ የመጨመር ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው አስረድቷል፡፡
ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በፊት 33 በመቶ፣ ከ7 ዓመታት በፊት 44 በመቶ ሽፋን እንደነበራት፣ ህዳሴ ኃይል ማመንጨት ሲጀመር ወደ 54 በመቶ መድረሱን፣ ግድቡ ከዚህ በኋላ ደግሞ የኤሌክትሪክ ሽፋንን የበለጠ እንደሚያደርገው ተመልክቷል፡፡
(ተጨማሪ አለን)
@ThiqahEth
ትራምፕ የአውሮፓ ሀገራት ከሩሲያ ነዳጅ እንዳይገዙ አስጠነቀቁ።
የኃይል ግዥ ሂደቱ አሁን ባለበት ከቀጠለ የዩክሬን ጦርነት እንዲባባስ ያደርጋል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ከአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር በነበራቸው የቪዲዮ ውይይት በሩሲያ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ትራምፕ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ከሩሲያ በተጨማሪ አጋር ባሏት ቻይና ላይም ነው። ትራምፕ ቻይና በዩክሬን ጦርነት ለሩሲያ ትልቅ ድጋፍ እያደረገች ነው በማለት ወንጅለዋል።
ሞስኮ ጦርነቱን ያራዘመችው ከቤጂንግ አስተማማኝ ድጋፍ ስለምታገኝ ነው ብለዋል። ትራምፕ ከአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስለሚኖራቸው ውይይት ጠቁመዋል።
ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም ከፑቲን ጋር እንደሚገናኙ ግን ተናግረዋል። #radiofreeeurope
@ThiqahEth
በአፍጋኒስታን የሟቾች ቁጥር 2 ሺሕ 205 መድረሱ ተገለጸ።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው መቆሙን ተከትሎ በአደጋው የሞቱት ሰዎች አስክሬን ከፍርስራሽ እየተለቀመ እንደሚገኝ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።
በዚህም ከቀናት በፊት 1 ሺሕ 411 ደርሷል ተብሎ የነበረው የሟቾች ቁጥር ወደ 2 ሺሕ 205 ከፍ ማለቱ ተገልጿል።
ለተጎዱ ሰዎች የነፍስ አድን እርዳታ ማድረስ መጀመሩን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
በአፍጋኒስታን በቅርቡ በሁለት ከተሞች ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቷል። #thewashingtontimes
@ThiqahEth
"ዌስት ባንክን መቆጣጠር ቀይ መስመር ነው" - አረብ ኤምሬት
የተባበሩት አረብ ኤምሬት እስራኤልን አስጠንቅቃለች።
የሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ሚኒስትር ድዔታ ላና ኑሰይበህ፣ "ዌስት ባንክን መቆጣጠር ቀይ መስመር ነው" ብለዋል።
"የአብርሃም አኮርድ ስምምነትን የሚጥስ እርምጃ ይሆናል" ያሉት ኑሰይበህ፣ "የቀጠናዊ ውህደት ፍላጎትን ያሰናክላል" ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት ከ26 አመት በኋላ በ2020 በትራምፕ አማካኝነት ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማምተዋል። #cnn #gulfnews
@ThiqahEth
"ለቻይና ድል ብዙ አሜሪካውያን ሞተዋል" - ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን፣ ኪም እና ዢ በአሜሪካ እያሴሩ ነው ሲሉ ወነጀሉ። ሶስቱ መሪዎች በቻይና ከወታደራዊ ትርዒት ጎን ለጎን መወያየታቸው ተገልጿል።
"ዥ ምንም እንኳን በአሜሪካ ላይ እያሴራችሁ ቢሆንም ለፑቲንና ኪም ሰላምታየን አድርስልኝ" ያሉት ትራምፕ "ፕሬዚዳንት ዥ አሜሪካ ለቻይና ነፃነት የከፈለችውን መስዋዕትነት ያስታውሱታል?" ሲሉ ጠይቀዋል።
"ለቻይና ድል ብዙ አሜሪካውያን ሞተዋል" ብለዋል ትራምፕ። #foxnews
@ThiqahEth
እስራኤል ለ60,000 ተጠባባቂ ወታደሮቿ ጥሪ አቀረበች።
ጥሪው የቀረበው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የኔታንያሁን "ጋዛን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር" እቅድ ካረጋገጡ በኋላ ነው ተብሏል።
ጥሪ የቀረበላቸው የተጠባባቂ ጦር አባላት በቀጣዩ መስከረም እንደሚቀላቀሉ ተገልጿል።
እስራኤል 130,000 ተጠባባቂ ጦር እንዳላት የመከላከያ መረጃዎች ያመላክታሉ። የጋዛ ዘመቻ እቅድ ሊራዘም እንደሚችልም ተጠቁሟል።#bbc
@ThiqahEth
በአፍጋኒስታን በትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ወደ ካቡል ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ከተሳቢና ሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ አደጋው እንደደረሰ ተገልጿል።
አደጋው የደረሰው በህያት ግዛት ነው ተብሏል። #radiogov
@ThiqahEth
"ክብረ ወሰን የሆነ ግድያ ተፈጽሟ። 308 ባለሙያዎች ቆስለዋል 125 ታግተዋል" - ተመድ
በኢትዮጵያ ጨምሮ በ2024 ብቻ 383 የእርዳታ ሰራተኞች መገደላቸውን የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ቢሮ አስታወቀ።
"ግማሽ የሚሆኑት ህይወታቸው ያለፈው በጋዛ ነው፣ 60 የሚደርሱት የተገደሉባት ሁለተኛዋ ሀገር ሱዳን ናት" ሲሉ የቢሮው ኃላፊ ቶም ፍሌቸር ተናግረዋል።
"በኢትዮጵያ እና በሶሪያ 14 የእርዳታ ባለሙያዎች ተገድለዋል" ብለዋል።
"ክብረ ወሰን የሆነ ግድያ ተፈጽሟል" ያሉት ኃላፊው ጉዳዩን "አሳሳቢ" ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም "308 ባለሙያዎች ቆስለዋል 125 ታግተዋል" ብለዋል።
"ግድያው በጦርነት ውስጥ ንጹሐንን ማዳን እንደሚገባ የቀረበ የጥሪ ደወል ነው" በማለት የእርዳታ ሰራተኞችን ኢላማ ማድረግ እንዲቆም አሳስበዋል።
"ግድያ ይፈጸማል፣ ተጠያቂነቱ ዜሮ ነው" ሲሉ አጥፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳልተቻለ አብራርተዋል።
ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ሞት የተመዘገበው በ1997 ሲሆን 297 ባለሙያዎች ተገድለው ነበር ብለዋል። #pbsnews
@ThiqahEth
የትራምፕ እና የዘለንስኪ ስብሰባ በተመለከተ መሪዎች ምን አሉ?
ትራምፕ፣ "ጦርነቱ በአንድ ወይም በሁለት ሳምንት ውስጥ ይቆማል፣ ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱ እንድቋጭ ይፈልጋሉ" ብለዋል።
"እኔ ያስቆምኳቸው ስድስት ጦርነቶች የተኩስ አቁም አልተደረገባቸውም፣ ያን ያክል አስፈላጊ አይደለም። ሩሲያ ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና እንድሰጥ ፍቃደኛ ናት" ሲሉም ገልጸዋል።
ዘለንስኪ ደግሞ፣ "ከትራምፕ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገናል ለዚህም አመሰግነዋለሁ፣ ትራምፕ ግጭቱ እኔደሚቆም ተስፋ አላቸው" ብለዋል።
እንዲሁም የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ "በመጨረሻም የተጋረደብንን ግድግዳ ሰብረነዋል" ብለዋል። "የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ መርዝ "በቀጣዩ ስብሰባ የተኩስ አቁም ሊደረግ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በበኩላቸው፣ "ይህ ጥሩ እርምጃ ነው፣ ባለፉት ሶስት አመታት ከሩሲያ ይህን በጎ ምላሽ አይተን አናውቅም" ነው ያሉት።
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ደግሞ፣ "የሶስትዮሽ ስብሰባ ከመደረጉ በፊት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተፈፃሚ መሆን አለበት" ብለዋል።
እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር "ስለዩክሬን ደህንነት ስናወራ ስለአውሮፓ ደህንነት እያወራን መሆኑ መታወቅ አለበት" ሲሉ ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ደግሞ፣ "በሩሲያ በሀይል የተወሰዱ ህፃናት ወደሀገራቸው ዩክሬን ተመልሰው ማየት አለብን" ብለዋል። #uatv
@ThiqahEth
"ዘለንስኪ ጦርነቱን ማቆም ትችላለህ፣ ወይም መዋጋትህን ቀጥል" - ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለሰላማዊ ድርድር ቁርጠኛ እንዲሆኑ አሳሰቡ።
ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የግል የማህበሩ ሚዲያ ትስስር ገፃቸው ላይ "ሩሲያ ዝግጁ ናት አንተ መዘጋጀት አለብህ" ሲሉ ዘለንስኪን አስጠንቅቀዋል።
"ዘለንስኪ ጦርነቱን ማቆም ትችላለህ፣ ወይም መዋጋትህን ቀጥል" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ትራምፕ "ጦርነቱ እንዴት እንደተጀመረ አስታውስ፣ ኦባማ ነው ያለጦርነት ከ12 አመት በፊት ክሪሚያን አሳልፎ የሰጠው" ብለዋል።
"እንደዚያም ሆኖ ያኔ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ አላለችም ነበር" በማለት ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ አስተያየታየው ዩክሬን ክሪሚያን መልሳ መቆጣጠርም ሆነ የኔቶ አባል መሆን እንደማትችል አስታውቀዋል። #irishindependent
@ThiqahEth
ሁቲ በእስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃት ፈጸመ።
ጥቃቱን ተከትሎ በቴላቪቭ፣ ቤርያኮቭ፣ ሎድ፣ ሄርዚሊያ እና እየሩሳሌም ከተማ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሳይረኖች መሰማታቸው ተገልጿል።
የእስራኤል ጦር "የአየር መቃወሚያዎችን ተጠቅመን ስጋታችንን ቀልብሰናል" ብሏል።
ይህን ከማለት ውጪ ጦሩ ሚሳዔሎቹ በእስራኤል ግዛት ስለማረፋቸውም ሆነ ሙሉ በሙሉ ስለመክሸፋቸው የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ ግን የለም።
የየመኑ "አማፂ ቡድን" ሁቲ በፈጸመው ጥቃት የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩም የተገለጸ ነገር የለም ተብሏል። #ynetnews
@ThiqahEth
"የተቃጡብንን ሁሉንም የሳይበር ጥቃቶች አክሽፈናል" - የደቡብ ኮሪያ ጦር
የደቡብ ኮሪያ ጦር 9262 የሳይበር ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ገለጸ።
የሳይበር ጥቃቱ የተፈፀመበት እ.ኤ.አ በ2025 ግማሽ አመት ውስጥ መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ዩዮንግ ዊዎን ተናግረዋል።
ዊዎንግ ጥቃቱ ካለፈው አመት 2024 ጋር ሲነፃፀር የ45% ብልጫ እንዳለው አብራርተው፣ "የተቃጡብንን ሁሉንም የሳይበር ጥቃቶች አክሽፈናል፣ የደረሰብን ጉዳት የለም" ብለዋል።
"ከጥቃቱ ጀርባ ያሉትን ተዋናዮች መግለጽ ባያስፈልግም አብዛኛው ግን በሰሜን ኮሪያ የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጠናል" ሲሉም ገልጸዋል።
ጦሩ ለነዚህ ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ የመውሰድ ሙሉ አቅም እንዳለውም ተናግረዋል። #thestraightstimes
@ThiqahEth
"ፑቲን ቁርጠኝነት ካላሳየ ትራምፕ ጫና ማሳደር ይኖርበታል" - ባለሙያዎች
የፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን ውይይት ያለስምምነት ተጠናቋል።
የሁለቱ ሃያላን ሀገራት መሪዎች በአላስካ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የዲፕሎማሲና አለማቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች አስተያየታቸውን አጋርተዋል ።
ባለሙያዎቹ መሪዎቹ ስብሰባ ማድረጋቸውን በበጎ ጎን አንስተው፣ ነገር ግን ግጭቱን የሚያስቆም አለመሆኑ ቅሬታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ "ትራምፕ የተኩስ አቁም እንድደረግ መገፋፋት ካልሆነ ማዕቀብ መጣል አለባቸው" ብለዋል።
"ፑቲን ቁርጠኝነት ካላሳየ ትራምፕ ጫና ማሳደር ይኖርበታል" በማለት ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ ባለፈም ስለስብሰባው ለዩክሬን ባለስልጣናት ገለፃ እንዲያደርጉ መክረዋል።
የትራምፕ አስተዳደር "ከተስፋ ባለፈ ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣት ይጠበቅበታል" ብለዋል። #atlanticcouncil
@ThiqahEth
#Ethiopia #ህዳሴ
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።
@ThiqaEth
“ሁለት ሚሊዮን ቶን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀትን የህዳሴ ግዱቡ ሥራ መጀመር ይቀንሰዋል” - አቶ ሞገስ መኮንን
ዋዜማ ላይ ስላለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ዛሬ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግድቡ ወደ ስራ መግባት 2 ሚሊዮን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀትን ይቀንሳል ብሏል።
"ህዳሴ ግድቡ በዓመት የሚያመነጨውን 15 ሺሕ 760 ጊጋ ዋት ለማመንጨት ሌሎች የኃይል ምንጮችን ብንጠቀም ወደ አየር የምንለቀው የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠን እስከ 2 ሚሊዮን ቶን የሚደርስ ነው፡፡ ይህንን 2 ሚሊዮን ቶን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀት የህዳሴ ግዱቡ ሥራ መጀመር ይቀንሰዋል” ነው ያለው።
ይህን ያሉት የተቋሙ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን፣ በሌላ በኩል በግድቡ መጠናቀቅ፣ “የአንድ ወገን ተጠቃሚነት ከዚህ በኋላ ሙሉ ለሙሉ አክትሟል ወደሚል ምዕራፍ ተሸጋግረናል” ብለዋል፡፡
“ግብፅና ሱዳን ለዘመናት ብቻቸውን ሲጠቀሙ የነበሩበት ኢ-ፍትሃዊ የአጠቃቀም ሥርዓት ህዳሴ ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጁ በሆነ ሰዓት ኢ-ፍትሃዊነት ወደ ጎን ተትቷል” ብለው፣ "ፍትሃዊ አካሄድ ወደፊት እንዲመጣ፣ ወደ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያሻጋግር ድልድይ የተዘረጋበት ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡
"የህዳሴው መጠናቀቅ የግብጽን ውሃ ድርሻ ይቀንሳል" በሚል ለሚነዛው ወሬ እውነታው በተቃራኒው መሆኑን ሲናገሩም፣ “የግብፅ ውሃ ድርሻ የሚቀንስበት አሰራር የለም” ነው ያሉት።
የህዳሴ ገንዘብ ምንጭ ምንም አይነት የውጭ እርዳታ፣ ብድር ያልታከለበት፤ የፋይናንስ ምንጩ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነበት መሆኑ ከሌሎቹ ፕሮጀክቶች የተለየ እንሚያደርገው ተገልጿል።
@ThiqahEth
"ህንድ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ይቅርታ ትጠይቃለች" አሜሪካ
ህንድና አሜሪካ የንግድ ስምምነት ላይ የመድረስ እድል አላቸው ተብሏል።
የአሜሪካ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሆዋርድ ሉትኒክ ህንድ ወደ ድርድሩ ለመመለስ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባት አሳስበዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ከትራምፕ ጋር መግባባት ላይ መድረስ አለባቸው" ሲሉም ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለው፣ "ህንድ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ይቅርታ ትጠይቃለች" ብለዋል። ምክንያት ያሉት ደግሞ ትራምፕ ህንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንዳትገዛ ቢያስጠነቅቁም አሁንም መግዛት መቀጠሏን ነው።
ካልሆነ ግን እንደ ሩሲያ እና ቻይና ማዕቀብ ሊጣልባት እንደሚችል ጠቁመዋል። #trtworld
@ThiqahEth
"የአሜሪካ ቪዛ በውዴታ የሚገኝ እንጂ መብት አይደለም" - በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን ተጓዦች አዲስ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፏል።
በማህበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ "ህገወጥ መጠጦችን መጠቀምና ማንኛውንም የአሜሪካ ህግ መጣስ የአሜሪካ ቪዛ አያስገኝም" ሲል ገልጿል።
በትምህርትም ሆነ በጉብኝት በቀጣይ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ያሰቡ ሰዎች ከእነዚህ ወንጀሎች እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ኤምባሲው፣ "የአሜሪካ ቪዛ በውዴታ የሚገኝ እንጂ መብት አይደለም" ብሏል።
"ቪዛ ከተሰጠ በኋላም የአሜሪካ ቪዛ ምርመራ ማድረግ አይቆምም" ያለው ኤምባሲው፣ "ህጉን ተላልፈው ከተገኙ ቪዛውን እንቀማችኋለን" ሲል አስታውቋል። #usembassyaddisabbaba
@ThiqahEth
ግብፅና ሱዳን ምን እያሉ ነው?
"የህዳሴው ግድብ የስጋት ምልክት ነው" - ሱዳን እና ግብፅ
ግብፅ እና ሱዳን ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ ያላትን ፖሊሲ እንድትቀይር መጠየቃቸው ተሰምቷል።
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች በካይሮ ውይይት አካሂደዋል ተብሏል።
ሚኒስትሮቹ ከውይይታቸው በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ "ምክክሩ የኢትዮጵያን ግድብ የሚመለከት ነበር" ብለዋል።
"በነበረን ውይይት ግድቡ አለማቀፍ ህግን እንደሚጥስና ለኛ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚፈጥር ተመካክረናል" ሲሉ ገልጸዋል።
ሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በመግለጫቸው፣ "የህዳሴው ግድብ የስጋት ምልክት ነው" ብለውታል።
በካይሮ በነበረው ውይይት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲና የውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ሀኒ ስዌላም የተገኙ ሲሆን፣ ከሱዳን በኩል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኡማር ሰድቅ የተመራ ልዑካን ቡድን ተገኝቷል።
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን በመጪው አዲስ አመት መስከረም ላይ ለማስመረቅ ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ተናግረዋል። #trtworld
@ThiqahEth
በፖርቱጋል 15 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
በሊዝበን ከተማ አንድ የቱሪስት ተሽከርካሪ ከድልድይ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የተከሰተው ተብሏል።
በዋና ከተማዋ በደረሰው አደጋ ከሞቱት መካከል የውጭ ዜጎችም እንደሚገኙ ተገልጿል። #novinite
@ThiqahEth
አፍጋኒስታን ለሁለተኛ ጊዜ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተመታች።
ድጋሚ የተከሰተው አደጋ በሬክተር ስኬል 5.2 መለካቱን የአሜሪካ ጂዖሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል። በዚህኛው አደጋ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።
ከሁለት ቀን በፊት የተከሰተው አደጋ የ1 ሺሕ 411 ዜጎችን ህይወት ሲቀጥፍ፣ 3 ሺሕ 124 የሚሆኑት ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል። #thepeninsula
@ThiqahEth
ከ2500 በላይ ሲሞቱ፣ ከ100,000 በላይ ዜጎቿ በኮሌራ መጠቃታቸውን ሱዳን ገለጸች።
ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 1575 የኮሌራ ኬዞች መመዝገባቸውን እና 22 ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአንድ አመት ውስጥ በሀገሪቱ 18 ግዛቶች የተያዙት ሰዎች ቁጥር 101 ሺሕ 450 መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ከአመቱ ውስጥም የ2515 ሰዎች ህይወት አልፏል ያለው ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ያለውን የእርስበርስ ጦርነት ለበሽታው መስፋፋት እንደ ምክንያት ወስዶታል። #newsaz
@ThiqahEth
"ወደ ዩክሬን ወታደሮች አንልክም፣ ነገር ግን የአየር ሀይል ድጋፍ ልናደርግ እንችላለን" - ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም እየሰሩ መሆናቸውን በድጋሚ ተናግረዋል።
ትራምፕ "ዩክሬንን ለመርዳት በቻልኩት መጠን ሁሉ ፍቃደኛ ነኝ" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዚደንቱ "ወደ ዩክሬን ወታደሮች አንልክም፣ ነገርግን የአየር ሀይል ድጋፍ ልናደርግ እንችላለን" ብለዋል ትራምፕ።
ዶናልድ ትራምፕ ይህን አስተያየት የሰጡት ከዩክሬን ፕሬዚዳንት እና የአውሮፓ መሪዎች ጋር በዋይትሐውስ ከተወያዩ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። #skynews
@ThiqahEth
በናይጄሪያው የጀልባ መስጠም አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች የት እንደገቡ ማወቅ አልተቻለም ተባለ።
እስካሁን 10 ሰዎች ብቻ በህይወት ተገኝተዋል ተብሏል።
አደጋው ወደገበያ ሲሄዱ በነበሩ ሰዎች ላይ መፈጠሩን የናይጄሪያ ብሄራዊ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።
ሰዎቹ የጠፉት ሶኮታ በተባለችው ግዛት መሆኑንም ገልጿል።
ኤጀንሲው ባለፈው ወር በተመሳሳይ አደጋ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውሷል።
በናይጄሪያ ባለፈው የፈረንጆች አመት 2024 ብቻ 326 ሰዎች በጀልባ አደጋ መሞታቸውን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል። #abcnews
@ThiqahEth
በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን የጋዛን ጦርነት በማውገዝ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ሰልፈኞቹ የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መንግስት ከሀማስ ጋር ድርድር እንዲያደርግና ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።
እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው የታገቱባቸው ዜጎች እንዲለቀቁላቸው ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል።
እስራኤላውያን ባካሄዱት ሰልፍ የሀገራቸውን ባንድራ እና የታጋቾችን ፎቶ ጎን ለጎን ይዘው ታይተዋል።
ሰልፉን ተከትሎ አንዳንድ የንግድ ተቋማት እና ዝግ እንደነበሩ ተገልጿል። #aljazeera #thearabweekly
@ThiqahEth
ሦስት የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ከዘለንስኪ ጋር አሜሪካ ገብተዋል።
ትራምፕ በአላስካ ከፑቲን ጋር ከተወያዩ በኋላ ዘለንስኪን በነጩ ቤተመንግሥት ጋብዘዋል።
ይህን ስብሰባ ለመታደም የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ መርዝ ዘለንስኪን ተቀላቅለዋቸዋል ተብሏል።
ከሦስቱ መሪዎች በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን መገኘታቸው ተገልጿል። #bbc
@ThiqahEth
31 ሱዳናውያን በድንገተኛ ጥቃት ተገደሉ።
በሰሜን ዳርፉር በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ላይ ተፈፅሟል ተብሏል።
በዚህም 31 ተገደሉ የተባለ ሲሆን፣ ከሟቾቹ ውስጥ 7 ህፃናትና አንዲት ነፍሰጡር እናት እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ከሟቾቹ በተጨማሪ 13 ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል።
ጥቃቱ በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እንደተፈጸመ ቢገለፅም፣ ቡድኑ እስካሁን ድረስ ሀላፊነት አልወሰደም። #yahoonews
@ThiqahEth
በፓኪስታን የሟቾች ቁጥር 400 ደረሰ።
በካይበር ክልል በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ400 በላይ መብለጡን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።
የግላሲያ ወንዝ ሙላት ባስከተለው አደጋ 74 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተብሏል። #dailyausaf
@ThiqahEth
በፓኪስታን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ320 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የጣለው ከባድ ዝናብ ባለፉት 48 ሰዓታት እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ አድርሷል ተብሏል።
25ቱ ሟቾች ፓኪስታን በምታስተዳድረው የካሽሚር ግዛት፣ አምስቱ ደግሞ በጊልጅት ባልቲስታን ከተማ የሚኖሩ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በካይበር ግዛት ብቻ 307 ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ አስተዳደር ባለስልጣን ቃል አቀባይ መሐመድ ሱሀይል ገልጸዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ወ ደስፍራው መላካቸውን ሱሀይል ተናግረዋል።
"አደጋ ወደ ደረሰበት ቦታ ለመግባት መንገዱ አዳጋች ቢሆንም፣ ባለሙያዎቹ ህይወት ለማዳን ሲባል ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግራቸው ተጉዘዋል" ነው ያሉት።
የሀገሪቱ ሜትሮዎሎጂ ቢሮ በመጪዎቹ ቀናትም ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ ትንበያውን አስቀምጧል።
623 ፓኪስታናውያን በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። #thestraightstimes
@ThiqahEth