thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

የሁቲ የጦር አዛዥ መሀመድ አልጋማሪ ከ12 አመት ልጃቸው ጋር በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ።

እስራዔል ከጋዛ የሰላም ስምምነት በኋላ በየመኑ አማፂ ቡድን ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተገልጿል።

የእስራኤል ጦር አልጋማሪ በንጹሐን ሞት ተጠያቂ እንደነበር ከህልፈቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።  

ሁቲ ባወጣው የሀዘን መግለጫ የአልጋማሪን ሞት አረጋግጧል። #longwarjournal

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ እና ፑቲን ለሁለተኛ ጊዜ ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ።

ሁለቱ መሪዎች ውይይታቸው በዩክሬን ጦርነት ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።

ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን የሚገናኙት በቡዳፔስት መሆኑ ተጠቁሟል።

መሪዎቹ ካሁን በፊት በአላስካ ተገናኝተው በመከሩበት ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው በሞስኮ ሁለተኛ ዙር ውይይት ለማካሄድ ተስማምተው ነበር። #indiatoday

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በኬንያ በኦዲንጋ የሀዘን ስነስርዓት በተከፈተ ተኩስ የንጹሐን ህይወት አለፈ።

በካሳሪ ስቴዲየም ሲካሄድ በነበረው የሸሽኝት ፕሮግራም ላይ አመጽ ተነስቶ ቢያንስ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በሽኝቱ አመጽ መነሳቱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ጉዳቱን የደረሰው የናይሮቢ ፖሊስ በሀዘን ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ በከፈተበት ወቅት ነው ተብሏል።

በትናንትናው እለት ህይወታቸው ያለፈው  የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንንጋ የቀብር ስርዓት እሁድ እንደሚካሄድ ተገልጿል። #anadoluagency

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለሁለት ቀን ወይም 48 ሰዓት ይቆያል ተብሏል።

ለጦርነቱ መጀመር ሁለቱም ሀገራት አንዱ አንዱን ተጠያቂ አድርገዋል ተብሏል።

ለሶስት ቀን በቆየው ጦርነት 12 ንጹሐሃን መሞታቸውንና ከ100 በላይ መቁሰላቸውን የታሊባን መንግስት አስታውቋል።

የፓኪስታን ጦር በበኩሉ፣ 11 አባላቱ እንደተገደሉበት ገልጿል። #cbsnews   #foxnews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#EthiopianAirline

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መልሶ መጀመሩን አበሰረ።

ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በቀን አንድ በረራ በማድረግ መልሶ የተጀመረው ይህ አገልግሎት ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በቀን ወደ ሁለት በረራዎች የሚያድግ መሆኑንም አስታውቋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"እኛ ስልጣን ይዘናል" - የማዳጋስካር ጦር

"ህገወጥ መግለጫ ነው" - የፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት

የማዳጋስካር ጦር የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩን ገለጸ።

የጦሩ ዋና መሪ ኮሎኔል ሚኬል ራኔድሪኒራ በመድናዋ በሚገኘው አንታናሪቮ ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት በሰጡት መግለጫ "እኛ ስልጣን ይዘናል" ብለዋል።

በቅርቡ መንግስት የሚያዋቅሩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንመርጣለን" ሲሉ ተናግረዋል።

የፕሬዝዳንት ራጆሊና ፅህፈት ቤት በበኩሉ የጦሩን እርምጃ፣ "መፈንቅለ መንግስት ተፈፅሟል፣ ህገወጥ መግለጫ ነው" ሲል ተቃውሟል።

ፅህፈት ቤቱ አክሎ፣ "ፕሬዝዳንት ራጆሊና ለደህንነታቸው ሲባል ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ተዘዋውረዋል" ብሏል።  

ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊና ሀገር ጥለው በፈረንሳይ የጦር አውሮፕላን ሸሽተዋል ቢባልም አስተባብለዋል።
#sana

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia

የብር የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል መጨረሻው እስከ የት ድረስ ነው?

"የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ እንዲመራ" ከመደረጉ ጥቂት ቀናት በፊት የአንድ ዶላር ዋጋ Jan 1,2024 ላይ ብር 56.4777 የነበር ሲሆን፣ ከ7 ወር በኋላ July 30,2024 ላይ የአንድ ዶላር ዋጋ ብር 57.8338 ሆኗል።

የአንድ ዶላር ዋጋ በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ ያሳየው ጭማሪ በብር 1.3561 ሲሆን፣ በመቶኛ 2.40% ብቻ ነው።

July 31 2024 ላይ "የውጭ ምንዛሪ በገበያ" እንዲመራ ከተደረገ ከሁለት ቀን በኋላ የአንድ ዶላር ዋጋ በብር 17.59 በመቶኛ ደግሞ 31.15 % እንዲጨምር ተደርጓል።

Octobe 14, 2025 በተደረገው ጨረታ የአንድ ዶላር ዋጋ ብር 148.1007 የደረሰ ሲሆን፣ ከJuly 30,2024 በኋላ ማለትም  "የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ" እንዲመራ ከተደረገ ከ1 ዓመት ከ2 ወር ከ15 ቀን በኋላ 162.23 % ወይም በብር 91.62 ጨምሯል።

ካለፈው ጨረታ June 5, 2025 ላይ ከተደረገው ጋር ሲነጻጸርም በ5 ወር ውስጥ ብር 13.1488 ወይም 9.74% ጨምሯል" ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያው ሙሸ ሰሙ ገልጸዋል።
(ቀሪ ማጣቀሻና ገለጻቸው ከላይ ተያይዟል) #MusheSemu

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ አረፉ።

የኬኔያታና ፕሬዝዳንት ሩቶ ተቀናቃኝ ኦድንጋ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ባሉባት ህንድ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።  

የኬንያ መንግስት በኦድንጋ ህልፈት ዙሪያ እስካሁን የሰጠው ማብራሪያ የለም። #nbstelevision

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ተደብቀው የሚገኙት የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት መንግስታቸው መፍረሱን አወጁ።

የማዳጋስካር ጦር ፓርላማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ጦሩ ፓርላማውን በመቆጣጠሩ የሰጡት አስተያየት የለም ተብሏል። #morningstar #thewashingtontimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካ ከ50 የሚበልጡ የሜክሲኮ ፖለቲከኞችን ቪዛ ከለከለች፡፡

የቪዛ ክልከላው ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንደሆነ ሁለት የሜክሲኮ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ "ዋሽንግተን ደህንነቷን ለመጠበቅ የውጭ ሀገር ዜጎችን ቪዛ ማገዷን ትቀጥላለች" ብሏል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዲፕሎማሲን የፖሊሲ ግቦችን ለማሳካት እየተጠቀሙበት መሆኑ ተገልጿል።

ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም በሜክሲኮ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ቶኒ ዌይን "የትራምፕ መንግስት ሜክሲኮ ላይ ጫና ለማሳደር አዲስ መንገዶችን እየፈለገ ነው" ብለዋል፡፡  #ajiancefrancepress  #reuters

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Ethiopia

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤ ተቀብለው ቃለ መኃላ ፈጸሙ

በጂቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የሹመት ደብዳቤ ተቀብለው የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ ለተሿሚ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና ጂቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋቸዋል።

የቀድሞ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር የነበሩት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በቅርቡ ሥራ መልቀቃቸው ይታወሳል። #MFA

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቤልጅየም ዜጎች የረሃብ አድማ መጀመራቸው ተገለጸ።

በሀገሪቱ የውስጥ በረራዎች እና የየብስ ትራንስፖርት መቆሙ ታውቋል።

የአድማው መንስዔ መንግስት ሲሰጣቸው የነበሩ ድጎማዎችን ማቋረጡና የጡረታ መውጫ እድሜ ዝቅ እንዲል መወሰኑ ነው ተብሏል።

እርምጃው የአውሮፓው ህብረት ድንጋጌዎችን የሚጣረስ እንደሆነ ተነግሯል። #hurriyetdailynews

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በግብፅ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የ450 ሰዎች ህይወት አለፈ፣ 402 አስከሬን ተሰብስቧል።

የግብፅ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ወደ4000 የሚጠጉ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና 402 አስክሬን መሰብሰቡን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ከ200 በላይ ህንፃዎች መፈራረሳቸውን ገልፆ፣ ነገር ግን ህጋዊ ፈቃድ አልነበራቸውም ብሏል።

አለማቀፍ የቀይመስቀል ፌደሬሽን የሟቾቹንና የጠፉ ሰዎችን ቁጥር ከ1000 ይበልጣል ቢልም፣ የግብፅ ባለስልጣናት ግን አስተባብለዋል።

አደጋው የተከሰተው በዋና ከተማዋ ካይሮና ጊዛ ከተማ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ገልጿል።

አደጋው በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተደርጎ ተመዝግቧል ተብሏል። #herald

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

አሜሪካና ቻይና በቲክ ቶክ ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕና ፕሬዚዳንት ዢ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት በመጪው አርብ ቀጠሮ ይዘዋል ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ ለተጨማሪ 90 ቀናት ባስቀመጡት ቀነገደብ መሠረት ቲክ ቶክ በአሜሪካ ስራ የሚያቆመው በዛሬው ዕለት ቢሆንም አገልግሎቱ አልተቋረጠም። #thejapantimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"ሀማስ ካልጠፋ የተሻለው ህይወት አይጀመርም" - ማርክ ሩቢዮ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ማርክ ሩቢዮ እስራኤል ገቡ።

ሩቢዮ ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ሀማስን ለማጥፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከኔታንያሁ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ገልፀዋል።

ማርክ ሩቢዮ "የጋዛ ህዝብ የተሻለ ህይወት ይገባዋል" ብለዋል። ሩቢዮ "ሃማስ ካልጠፋ የተሻለው ህይወት አይጀምርም" ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ ጦርነቱ እንድቆም ጥረት እያደረገች መሆኗን የተናገሩት ሀላፊው "ያልተገደበ ድጋፋችንን መቁጠር ትችላላችሁ" በማለት ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊው "ሀማስ ካልጠፋ የተሻለው ህይወት አይጀመርም" ብለዋል።   #thejapantimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"የኔ ኃላፊነት መረጋጋትን መፍጠር ነው፣ ስልጣን አለቅም" - ፕሬዚዳንት ጄሪ

ከሰባት ቀን በፊት የተሾሙቴ የፔሩ ፕሬዚዳንት ጆሴ ጄሪ ስልጣን እንደማይለቁ አስታወቁ።

ጄሪ "በሙስና ቅሌት" በፓርላማ ተወስኖባቸው ኃላፊነታቸውን በተነጠቁት ድና ቦሎርቴ ምትክ ወደ ስልጣን የመጡት ባሳለፍነው ሳምንት ነው።

ካሁን በፊት በኔፓል እና ማዳጋስካር የተንጸባረቀው የጄን ዜድ ንቅናቄ በፔሩም የተጀመረ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ ጄሪ ከኃላፊነት እንዲነሱ ጠይቀዋል።

ጆሴ ጄሪ፣ "የኔ ኃላፊነት መረጋጋትን መፍጠር ነው፣ ስልጣን አለቅም" ሲሉ ተናግረዋል።

"መንግስት በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል" ብለዋል።

መንግስትን በመቃወም በተካሄደው በዚህ የጄን ዜድ አመጽ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ከ100 በላይ የሚደርሱት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።   #aljazeera

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

እስራኤልና ሃማስ የፈጸሙት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ፣ 20 ፍልስጤማውያን ተገደሉ

ሁለቱም ወገኖች ለስምምነቱ መጣስ አንዱ ሌላኛውን ተጠያቂ አድርገዋል ተብሏል።

ሃማስ የጋዛ የሰላም ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ 20 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር፣ ሁሉም ታጋቾች አለመለቀቃቸውን ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ያመቻቸችው የሰላም እቅድ እንዲከበር አሳስበዋል።
#time

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ የተሰኘ አዲስ ምርት አስተዋወቀ።

አዲሶቹ የሞባይል ቀፎዎች፣ ታብሌት እና የስራ ጣቢያዎች ምርቶችን በይፋ ተዋውቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ይፋ የሆነው አዲሱ ምርት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል አለም እንድትቀላቀል የማድረግ ሂደት አንዱ አካል  እንደሆነ ገልጸዋል።

"ዘኔክሰስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮጵያን ምርቶች ከሃገር ውጭ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በማለም ነው ብለዋል።

የገጠሩን ማህበረሰብ አካታች ያደረጉ ናቸው ያሉት ስራ አስፈፃሚዋ፣ ያለልዩነት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ የሚያደርግ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

ምርቶቹ የከተማውን ማህበረሰብ ብቻ ያማከለ ብቻ ሳይሆን የገጠሩን ማህበረሰብ አካታች ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው ምርት ከወራት በፊት ይፋ የሆነው የኔክስት ሆራይዘን ስትራቴጂ አካል ነው ብለዋል።  

በ2028 ከ100 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ለማፍራት እቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Madagascar

"ስልጣን ተቆጣጥረናል፣ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሾመናል" - የማዳጋስካር ጦር

"የሀይል የበላይነትን የህግ የበላይነት ሊያሸንፍ ይገባል" - የአፍሪካ ኀብረት

የማዳጋስካር ጦር የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩንና ኮሎኔል ሚኬል ራንድሪያንሪ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾሙን ገልጿል።

የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ፣ የማዳጋስካርን ወታደራዊ መንግስት አግዷል።

የህብረቱ ሊቀመንበር መሀመድ አሊ ዩሱፍ ባወጡት መግለጫ "የሀይል የበላይነትን የህግ የበላይነት ሊያሸንፍ ይገባል" ብለዋል።

እገዳው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የጠቆሙት ዩሱፍ "የሀገሪቱን ህገመንግስት ያማከለ ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።  #trtworld

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

#Gambella

በጋምቤላ ክልል በህዝብ በተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ተኩስ ተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ተኮስ ተከፍቶ በተወሰኑ  ተሳፋሪዎች መድረሱን ክልሉ አስታውቋል።

ስንት ሰዎት እንደተጎዱና የጉዳቱ አይነቱ ምን እንደሆነ አልተለጸም።

በጋምቤላና በአቦል ከተማ መካከል በአውቶቡስ ላይ ተኮስ ከፍተዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኡቾም የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በጊዜያዊነት ተረክበው በጥበቃ ላይ የነበሩ የክልሉ ፖሊስ አባላት ስቶር ተሰብሮ ዕቃ ተዘርፏል በሚል ሁለት የሀገር መከላከያ አባላት ወደ ካምፑ በመግባት ጉዳዩ አጣርተው ሀሰት መሆኑን ካጣሩ በኋላ በሞተር ሳይክል ተመልሶ እንደወጡ በአውቶብስ ላይ ተኮስ በመክፈት ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል።

የክልሉ ፖሊስና የፈደራል የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል የወንጀል ድርጊቱ ከፈጸሙት መካከል ሞተር ሳይክል ሲያሽከረክር የነበረው ተጠርጣሪ ከነሞተር ሳይክሉ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሏል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ኒሳን በአሜሪካ የሚገኙ ከ173 ሺሕ በላይ መኪኖችን "በነዳጅ መሙሊያቸው ሊፈነዱ ይችላሉ" ሲል መልሶ ጠራ፡፡

ድርጅቱ በአሜሪካ የሚገኙ 173 ሺሕ 301 መኪኖችን በነዳጅ መሙሊያቸው ላይ ሊፈነዱ ይችላሉ በማለት መልሶ መጥራቱን የሀገሪቱ ሃይዌይ ትራፊክ ደህንንነት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የተጠሩት የኒሳን መኪኖች የተለያዩ ታዋቂ ሞዴሎችን ያካተተ ሲሆን፣ የትኞቹ እንደሆኑ ግን አላሳወቀም ተብሏል፡፡

ድርጅቱ ከባለስልጣኑ ጋር ባደረገው ውይይት ባለቤቶቹ ባቅራቢያቸው የሚገኙ የኒሳን ቅርንጫፎች ጋር ሄደው ችግሮቹ እንዲመረመሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ድርጅቱ አያይዞም፣ እስካሁን የተከሰቱ ምንም አይነት አደጋዎች አለመኖራቸውን ገልጾ፣ ምርቶቹን የጠራው ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ መሆኑን አስታውቋል። #reuters

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በባንግላዲሽ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ ቢያንስ 16 ሰዎች ሞቱ፡፡

የሀገሪቱ የእሳት አደጋ ባለስልጣን ዳይሬክተር ሞሃመድ ታጁለ ኢስላም እንደገለጹት፣ የሟቾቹ አስክሬን ሙሉ በሙሉ ስለተቃጠለ ማንነታቸውን መለየት አልተቻለም፡፡

የሀገሪቱ ፖሊስም የፋሪካውን ባለቤት ገና በመፈለግ ላይ ሲሆን፣ ፋብሪካው ህጋዊ መሆን አለመሆኑንም ገና እያጣራሁ ነው ብለዋል።

ለፋብሪካው ግብዓት የሚሆኑ ኬሚካሎችን የያዘው ክፍል በእሳት መንደዱንና እሳቱንም ለመቆጣጠር ሶስት ሰዓት መፍጀቱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የፋብሪካው ሰራተኞች ቤተሰቦች በፋብሪካው ዙሪያ ተሰብስበው የጠፉ ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ ይገኛሉ፡፡ #bbc

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ጎግል በህንድ በ15 ቢሊየን ዶላር የኤ.አይ ማዕከል ለመገንባት ማቀዱን ገለጸ፡፡

የጎግል አስተዳዳሪ የሆነው ድርጅት አልፋቤት በሀገረ ህንድ አንድራ ፕራዴሽ ግዛት በአምስት አመት ውስጥ የሚጠናቀቅ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንቨስትመንት ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።

አዲስ የሚገነባው ማዕከል ከአሜሪካ ውጭ ጎግል የሚገነባው ትልቁ የኤ.አይ (AI) ማዕከል እንደሚሆን የጎግል ክላውድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ቶማስ ኩሪያን ተናግረዋል።

ህንድ ለኤ.አይ ማዕከላት መከፈትና ማደግ ቁልፍ ሀገር እየሆነች የመጣች ሲሆን ይህም የሆነው በሀገሪቷ የሚገኘው አነስተኛ የዳታ ክፍያ እና የኢንተርቴት ተጠቃሚ ቁጥር በየግዜው መጨመር ነው ተብሏል።

ከትራምፕ ወደ ስልጣን መመለስ በኋላ ህንድ እና አሜሪካ የታሪፍ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል። #bbc

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#እንድታውቁት!

በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የተካተቱ ተቋማትን ተቋሙ ይፋ አድርጓል።

በዚህም፦
-የንግድ ቢሮ
-የገቢዎች ቢሮ
-የስራ እና ክህሎት ቢሮ
-የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
-የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
-የፕላን እና ልማት ቢሮ
-የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ
-የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
-የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን
-የቤቶች ኮርፖሬሽን
-የኢንቨስትመንት ኮሚሽን
-የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን
-የትራፊክ ማናጅመንት ባለስልጣን
-የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት
-የብሄራዊ መታወቂያ
-ኢትዮ ፖስታ
-ኢትዮ ቴሌኮም
-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና
-ስኬት ባንክ ተካተዋል። @MESOB

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በቬንዙዌላ ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

በሀገሪቷ ደቡባዊ ክልል በምትገኘው ኤል ካላኦ በተሰኘች መንደር በሚገኘው የወርቅ ማዕድን ማውጫ፣ ከባድ ዝናብ በመጣሉ ነው አደጋው የተከሰተው ተብሏል።

ይህንንም ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጓል ተብሏል፡፡

በኤል ካላኦ መንደርም እ.አ.አ ከ1853 ጀምሮ ወርቅ የማውጣት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዚህ የስራ መስክ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ #aljazeera

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አዲስ አበባን ከሀርጌሳ ጋር የሚያገናኝ አዲስ የመተባበር መንገዶችን ይክፈታል" - ሶማሊላንድ

የሳሞላንድ የሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚደርሱ የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረፋዱን አስታውቋል።

ጉብኝቱ "በትራንስፖርት፣ ንግድ፣ ደኀንነት እና ሌሎች አካላዊ መስኮች ውስጥ መተባበርን ለማስፋፋት ዕድል ይሰጣል፣ እንዲሁም መልካም እድገትን ያግዛል" ብሏል።

"ከደኀንነትና እረፍት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ክልላዊ ጉዳዮችን ለማነጋገር ዕድል ይሰጣል" ሲል ያከለው ሚኒስቴሩ፣ "አዲስ አበባን ከሀርጌሳ ጋር የሚያገናኝ አዲስ የመተባበር መንገዶችን ይክፈታል" ሲልም ገልጿል።

"ይህ ጉብኝት ብቻ የመንግስት የመለኪያ ሂደት አይደለም፤ በተለይ የሁለቱ ሀገሮች ጥልቅ ታሪካዊ ግንኙነቶችን የሚያሳይ መልዕክት ነው፤ በአፍሪካ ቀይ ቦታ ውስጥ ተስፋና ደህንነት ያለው ለወደፊት ግንባር የሚደርስ እንደሆነ ይገልጻል" ነው ያለው።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ኢትዮጵያ የኒክሌየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ዛሬ ሾመች።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ/ም) ጀምሮ አቶ #ሳንዶካን ደበበን የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው መሾመዋል።

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

"በጉብኝት አማካኝነት ወደ አሜሪካ የገቡ ቤተሰቦች ቪዛቸውን ማደስ አይችሉም" - የአሜሪካ ኤምባሲ

የአሜሪካ ኤምባሲ በቱሪስት ቪዛ ወደአሜሪካ ሂደው ለሚወልዱ እናቶች ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "አሜሪካ ሂደው የሚወልዱ እናቶች ለህክምና የመንግስትን እርዳታ ይጠይቃሉ" ሲል ገልጿል።

መንግስትም የህክምና ወጫቸውን እየሸፈነ እንደሚገኝ በማህበራዊ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ኤምባሲው፣ "እነዚህ ወጭዎች በአሜሪካ ግብር ከፋዮች ላይ የሚያልፉ ናቸው" ብሏል።

በመሆኑም "በጉብኝት አማካኝነት ወደ አሜሪካ የገቡ ቤተሰቦች ቪዛቸውን ማደስ አይችሉም" አስጠንቅቋል።
#usembassyaddisabbaba

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

50 ሱዳናዊያን ስደተኞች በሊቢያ ህይወታቸው አለፈ።

በሊቢያ 75 የሱዳን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ መሞታቸው ከተረጋገጡት ውጭ፣ 24 የሚደርሱት በህይወት መትረፋቸውን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

ድርጅቱ ከስደተኞቹ መካከል አንዱ መጥፋቱን አስታውሶ፣ በህይወት ለተረፉት የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል። #thenatiinal

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የኳታሩ አስቸኳይ ስብሰባ የእስራኤልን ጥቃት በማውገዝ ተጠናቀቀ።

በዶሃ በተካሄደው የአረብ እና እስላማዊ ሀገራት አስቸኳይ ስብሰባ እስራኤል የአባል ሀገራቱን ሉዓላዊነት ማቆም እንዳለባት መወሰኑን የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጅድ አልነስሪ ገልፀዋል።

አልነስሪ እስራኤል በጋዛ የምትፈፅመውን የዘር ማጥፋት እና ብሄር የማፅዳት እርምጃ እንድታቆም ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

ስብሰባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን የጋራ መከላከያ ምክርቤት እንድመሰረት አቅጣጫ መቀመጡን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የገልፍ፣ የአረብ እና እስላማዊ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በዶሃ ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።  #thepeninsula

@ThiqahEth

Читать полностью…
Subscribe to a channel