15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"የናይጄሪያ መንግስት በክርስቲያን ዜጎቹ ላይ የሚደርሱ ግድያዎችን ካላስቆመ አሜሪካ እርዳታ ታቆማለች" - ትራምፕ
ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደናይጄሪያ ጦር ሊልኩ እንደሚችሉ ገለጹ።
ትራምፕ "በናይጄሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች የህልውና ስጋት ተጋርጦባቸዋል" ሲሉ ገልጸዋል።
በግል የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ትሩዝ ሶሻል ባሰፈሩት አስተያየት "በናይጄሪያ ክርስቲያኖች በእስላማዊ ታጣቂዎች በገፍ እየተገደሉ ነው" ብለዋል።
ትራምፕ "አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከፔንታጎን አመራሮች ጋር ተወያይተናል" ሲሉ ገልጸዋል።
"የናይጄሪያ መንግስት በክርስቲያን ዜጎቹ ላይ የሚደርሱ ግድያዎችን ካላስቆመ አሜሪካ እርዳታ ታቆማለች" ብለዋል።
ናይጀሪያ በበኩሏ ከአሜሪካ የቀረበባትን ውንጀላ እንደማትቀበል አስታውቃለች። #france24
@ThiqahETH
"በታንዛኒያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው" - የአውሮፓ ሀገራት
ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኖርዌይና ካናዳ ምርጫን ስበብ አድርጎ የተቀሰቀሰው የታንዛኒያ አመጽ መፍትሄ እንዲበጅለት ጠየቁ።
ሀገራቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ "ምርጫ ባስከተለው አመጽ ከፍተኛ የሞትና የጉዳት መጠን መኖሩን ሪፖርቶች ደርሰውናል" ሲሉ ገልጸዋል።
"በታንዛኒያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው" ያሉት ሀገራቱ፣ "ባለስልጣናት የመናገር እና የመሰብሰብ መብትን ማክበር አለባቸው" ብለዋል።
አክለው፣ "ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተቃዋሚዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው አፈሳና እስር በጣም አሳሳቢ ሁኗል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። #gov.uk
@ThiqahETH
ሁሴን አሊ ምዊኒ የዛንዚባር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
ምዊኒ ለሁለተኛ ጊዜ ሀገሪቱን መምራት የሚያስችላቸውን ድምፅ ማግኘታቸውን የዛንዚባር ምርጫ ኮሚሽን (ZEC) አስታውቋል።
ገዥው ቻማ ቻ ማፒንዲ (CCM) ፓርቲ ሀገሪቱ ነፃ ከወጣችበት ከ1964 ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል። #bbc
@ThiqahEth
በታንዛኒያ ምርጫ ሲጀመር ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።
አመጹ መባባሱን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል ተብሏል።
በተቃውሞው እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው እና መጎዳታቸው ተገልጿል።
የፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ መንግስት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን አስሯል ቀሪዎቹንም ከምርጫ አግዷቸዋል ተብሏል።
አመጸኞቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሳይሳተፉ የሚደረግ ምርጫ ፍትሃዊ ባለመሆኑ መደረግ የለበትም በሚል ነው አመፁን የጀመሩት ተብሏል። #news24
@ThiqahETH
በካሪቢያን በተከሰተው አውሎንፋስ የሟቾች ቁጥር 50 ደረሰ።
ከሟቾች ባሻገር፣ ከ16 ሺሕ በላይ ሰዎች የሚኖሩባቸው ከ1000 በላይ ሴቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
"ሜሊሳ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የአውሎንፋስ አደጋ አድማሱን አስፍቶ ከጃማይካ ወደ ኩባ መሸጋገሩ ተገልጿል።
በተለይ በጃማይካ የመገናኛ አውታሮች ተቋርጠዋል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቁሟል ተብሏል።
የጃማይካ መንግስት 735 ሺሕ ዜጎችን አደጋ ከተጋረጠባቸው ሶስት ከተሞች ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።
ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል። #nzherald
@ThiqahETH
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የኑክሌር ሙከራ ማድረግ እንደምትጀምር ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሶስት አስርት አመታት በፊት አቁማው የነበረውን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ በቅርቡ ትጀምራለች ብለዋል።
የኑክሌር ሙከራ የሚደረገው ከሩሲያ እና ቻይና ጋር እኩል ቦታ ላይ እንደምንገኝ ለማሳየት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት ከቻይናው አቻቸው ዥ ጂ ፒንግ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ነው ተብሏል።
አሜሪካ የኑክሌር ሙከራ ያደረገችው በ1992 በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ የስልጣን ዘመን ነበር። #forbes
@ThiqahETH
አይቮሪኮስት ብሄራዊ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።
የወቅቱን ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራን ጨምሮ አምስት እጩዎች በምርጫው እየተወዳደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ከእጩዎቹ መካከል የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጂን ሉዊስ እና በኦታራ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመን የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አሁዋዶን ሜሎ ይገኙበታል ተብሏል።
ሀገሪቱ ካላት 30 ሚሊየን ህዝብ 37% የሚሆነው በድህነት ወለል እንደሚገኝ ተመላክቷል። #france24
@ThiqahETH
በደቡብ ሱዳን 9.3 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ።
አብዛኞቹ እርዳታ ፈላጊዎች በጎርፍ፣ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሀብት ውድቀት የተጎዱ መሆናቸውን ተመድ አስታውቋል።
በደቡብ ሱዳን የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ አኒታ ጌቦ "በተለይ ስድስት ግዛቶች የተለየ ችግር አለባቸው" ብለዋል።
ጌቦ "በቅርቡ በተከሰተው ጎርፍ ብቻ 960,000 ህዝብ በጎርፍ ተጎድቷል" ሲሉ ተናግረዋል።
"በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ችግሩን አባብሶታል" ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለውም በተያዘው አመት ሶስት ሚሊየን ሰዎች እርዳታ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል። #aa
@ThiqahETH
"ከእስራኤል ጋር ያለንን ሁሉንም ግንኙነት እናቋርጣለን" - ትራምፕ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ዌስት ባንክን እንዳትቆጣጠር አስጠነቀቁ።
"እስራኤል ዌስት ባንክን ከያዘች ወሳኝ አጋሯን አሜሪካን ታጣለች" ብለዋል ትራምፕ።
ፕሬዚደንቱ "ከእስራኤል ጋር ያለንን ሁሉንም ግንኙነት እናቋርጣለን" ሲሉ ተደምጠዋል።
"ያ ፈጽሞ አይሆንም ለአረብ መሪዎች ነግሪያቸዋለሁ" ነው ያሉት።
ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው "አትጨነቁ እስራኤል ከዌስት ባንክ ጋር በተያያዘ ምንም አታደርግም" በማለት ገልጸዋል። #thenewarab
@ThiqhETH
ቤልጂየም ምን አለች?
ቤልጅየም የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ድጋፍ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃወመች።
ህብረቱ እንዳይንቀሳቀሱ የታገደው 182 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመተው የሩሲያ ንብረት ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት ጥቅም ላይ እንዲውል ወስኗል።
የቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር ባርት ዌቨር ግን፣ "መፍትሄ መፈለግ ይሻላል ወይስ ዛሬም ለዩክሬን ድጋፍ ማድረግ?" ሲሉ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ይህ ነገር የከፋ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ አለብን" ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በብራሰልስ የሁለት ቀናት ስብሰባ እያካሄዱ ይገኛሉ። #helsinkitimes
@ThiqahETH
40 ስደተኞች በቱኒዚያ ድንበር ህይወታቸው አልፎ ተገኙ።
70 ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገልበጧ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል።
ቀሪዎቹ 30 ስደተኞች በህይወት መትረፋቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ስደተኞቹ በህገወጥ መንገድ አውሮፓ ለመግባት ሲጓዙ ነበር ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት "ህገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር" በሚል በ2023 ለሞሮኮ 127 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተመላክቷል። #anadoluagency
@ThiqahEth
የ92 ዓመቱ ፖል ቢያ የካሜሩንን ሀገራዊ ምርጫ አሸነፉ።
ፕሬዝዳንት ቢያ ምርጫውን ያሸነፉት 53.6% ድምጽ በማግኘት እንደሆነ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሜቴ ገልጿል።
ዋና ተቀናቃኛቸው ኢሳ ባካሪ በ18 በመቶ ነጥብ ርቀው 35% ድምጽ አግኝተዋል ተብሏል።
ይህ ምርጫ ፖል ቢያን ለስምንተኛ የሥልጣን ዘመን እድል የሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
ሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤቱ በመጪዎቹ ቀናት የመጨረሻውን ውጤት በይፋ ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል። #sputnik
@ThiqahETH
142 ግብፃውያን ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
የፀረ ህገወጥ ስደተኞች ኤጀንሲ (AIIA) ባወጣው መግለጫ ስደተኞቹ በኤምሳዒድ ድንበር በኩል በእግራቸው እንድመለሱ መደረጋቸውን ገልጿል።
ስደተኞች ሲመለሱ በቂ የደህንነት ጥበቃ መደረጉን ኤጀንሲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
በድንበር ጠባቂዎችና ወንጀል መርማሪዎች ፍተሻ ተደርጓል ብሏል።
ኤጀንሲው አክሎ፣ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ 37 ህገወጥ ስደተኞች ከደርና ከተማ መመለሳቸውን ገልጿል።
በዚህ ከተማ የባንግላዴሽ፣ ሶማሌ፣ የመንና ቻድ ስደተኞች እንደሚገኙ አስታውቋል። #thelibyaobserver
@ThiqahETH
IMF ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሀገራትን ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ከመጣ ሀገራት ዝርዝር አካተተ።
አለማቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) በተቋሙ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ያስጠናውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል ተብሏል።
በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ኮትዲቫር፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ጠቁሟል።
በዚህ የጥናት ሪፖርቱ ካሁን በፊት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቅሳትን ናይጄሪያን አላካተተም ተብሏል። #legit
@ThiqahETH
ትራምፕ ስለሃማስ ያሉት ምንድን ነው?
"ሀማስ መግደሉን ከቀጠለ አማራጭ አይኖረንም እንገድላቸዋለን" - ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሃማስ በጋዛ ፍልስጤማውያንን ገድሏል መባሉን አወገዙ።
ሃማስ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ "ለእስራኤል ወግነዋል" ባላቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ወስዷል ተብሏል።
ትራምፕ ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ "ሃማስ ከአመፅና ግድያ ድርጊቱ እንድታቀብ ማሳሰብ እፈልጋለሁ" ብለዋል።
"ሀማስ መግደሉን ከቀጠለ አማራጭ አይኖረንም እንገድላቸዋለን" ሲሉም ማስፈራቸውም አነጋጋሪ ሆኗል።
የሰላም ስምምነቱን "ታሪካዊ እድል ነው" ሲሉ የጠሩት ፕሬዝዳንቱ "የምትፈጥሩትን ችግር አቁሙ" በማለት አስጠንቅቀዋል። #jewishtelegraphicagency
@ThiqahETH
ሳሚያ ሱሁሉ 98% ድምፅ በማግኘት የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
ታንዛኒያ ባካሄደችው ምርጫ 32 ሚሊዮን ዜጎች መሳተፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሳውቋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በሀገራዊ ምርጫው እንዳይሳተፉ ማገዳቸው ህዝባዊ ተቃውሞ አስከትሏል።
በታንዛኒያ በምርጫ ውዝግብ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ700 በላይ ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል።
በ2021 ወደስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንቷ ለተጨማሪ አምስት አመት በሀላፊነት መቆየት የሚያስችላትን ድምፅ ማግኘቷን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። #bbc
@ThiqahEth
"በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" - የታንዛኒያ ተቃዋሚ ፓርቲ
በታንዛኒያ በተቀሰቀሰው አመፅ ቢያንስ የ700 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
የሀገሪቱ ዜጎች ረቡዕ መካሄድ የጀመረውን ምርጫ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል ተብሏል።
የቻደማ ተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ጆን ኪቶካ "በመላ ሀገሪቱ ከ700 እስከ 800 ሰዎች ተገድለዋል" ብለዋል።
"በዳሬሰላም ብቻ 350 ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች ጥቃት ህይወታቸው አልፏል" ያሉት ኪቶካ "የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ መብለጡ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።
"ብዙ ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች መረጃ ለመስጠት ፈርተው እየደበቁ ነው" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ለተፈጠረው አለመረጋጋት የፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉን መንግስት ተጠያቂ አድርገዋል። #france24 #ajiancefrancepress
@ThiqhETH
ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም ተስማሙ።
ሁለቱ ሀገራት በቱርክ አሸማጋይነት በኢስታንቡል ውይይት አካሂደዋል።
ሀገራቱ በድንበር አካባቢ የጋራ ቁጥጥር ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የኢስታንቡሉ ውይይት ለሰባት ቀናት መዝለቁን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ባለስልጣናት በቀጣይ ህዳር ወር ላይ ዳግም ተገናኝተው ስለተኩስ አቁም ስምምነቱ ይገመግማሉ ተብሏል። #samma
@ThiqahETH
ሩሲያ 700 ድሮንና ሚሳዔል ወደ ዩክሬን አስወነጨፈች።
በዚህ ከባድ የአየር ላይ ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
ጥቃቱ የሀይል መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ በመሆኑ ውድመት አስከትሏለል ተብሏል። #nzherald
@ThiqahETH
177 ሺሕ ሱዳናውያን ከኤልፋሽር ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ።
ከተማዋ በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ቁጥጥር ስር መዋሏን ተከትሎ የጅምላ ግድያ ይፈፀማል በሚል ስጋት ነው የወጡት ተብሏል።
ቡድኑ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ 2,000 ሰዎች መገደላቸውን ተመድ ገልጿል።
ባለፉት ሶስት ቀናት 36,000 ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን 1000 የሚሆኑት ወደ ታዊላ ከተማ ተሰደዋል ነው የተባለው።
ተመድ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የዘር ማጥፋት ወንጀልና ጭፍጨፋ እየፈፀመ እንደሆነ በተደጋጋሚ አስታውቋል።
በሄመቲ የሚመራው አር ኤስ ኤፍ ንፁሃንን በአንድ ቦታ አሰባስቦ የመረሸን፣ ቤት ለቤት እየዞረ የመግደል እና ፆታዊ ጥቃት ወንጀል ፈፅሟል ተብሏል። #trtworld
@ThiqahETH
በብራዚል በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉት ሟቾች ቁጥር 132 ደረሰ።
በዋና ከተማዋ ሪዮ ድጄናሮ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ በተጀመረው ኦፕሬሽን የሟቾች ቁጥር 132 ደርሷል።
የተተጎጂዎች ቁጥር በውል አይታወቅም ተብሏል።
የሪዮ ከተማ ከንቲባ ቪክቶር ሳንቶስ "ዘመቻው የሚጠበቅ ነው ግን ፈልገነው አይደለም" ብለዋል።
ከንቲባው አክለው፣ "ከአለማቀፍ ስብሰባው ጋር አይገናኝም፣ የተመድ ኮፕ30 ቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል" ብለዋል።
የከተማዋ ፖሊስ በበኩሉ የዘመቻው እቅድ ከሁለት ወር በፊት እንደተጀመረ ገልፆ፣ 2500 ኦፊሰሮች ተሰማርተዋል ብሏል።
በዚህ ኦፕሬሽን ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።#sundaytimes
@ThiqahETH
"ትራምፕ ጦርነት እየፈበረኩ ነው" - ቬንዙዌላ
የቬኔዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በጦርነት ቀስቃሽነት ወነጀሉ።
ማዱሮ "ሀገራችንን ለግጭት እየገፋፉ ነው" ሲሉ ወንጅለዋል።
"ትራምፕ ጦርነት እየፈበረኩ ነው። ጦርነት አንፈልግም ይሉናል ግን ወንጀለኛ አድርገው እየሳሉን ነው" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ መከላከያ ቢሮ ፔንታጎን ትልቁ የጦር አውሮፕላን ወደላቲን አሜሪካ መጓጓዙን ማስታወቁን ተከትሎ ነው። #time
@ThiqahETH
አሜሪካ በኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ላይ ማዕቀብ ጣለች።
ማዕቀቡ "የአደንዛዥ እፅ ምርትን አስፋፍቷል እና ፀረ ናሮቲክ እርምጃዎችን አደናቅፈዋል" በሚል እንደሆነ ተገልጿል።
የአሜሪካ ገንዘብ ቢሮ ሀላፊ ስኮት ባሰንት በአሜሪካ የሚገኘው የፕሬዝዳንት ፔትሮ ገንዘብ እንዳይቀሰቀስ አግደዋል ተብሏል።
አሜሪካ ከፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሉዊስ ፈርናንዶ ላይም ማዕቀብ ጥላለች። #shafaaqnews
@ThiqhETH
በሱዳን በድሮን ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገደሉ።
ጥቃቱን የፈጸሙት የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መሆናቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።
ጦሩ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው በካርቱም አየርመንገድ አጠገብ መሆኑም ገልጿል። #trtworld
@ThiqahETH
#Ethiopia
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው ለተለያዩ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ምደባ አከናውኗል።
በዚህ መሠረት፦
ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የኢሉባቡር ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮምያ ብሔረሰብ ዞን ኬሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ በሁለተኛ ቀን የጉባኤው ውሎው ወስኗል። #ተሚማ
@ThiqahETH
በካሜሮን ከምርጫ በኋላ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ 20 ሰዎች ሞቱ።
ሀገሪቱ በቅርቡ ባካሄደችው ምርጫ የ92 አመቱ ፖል ቢያ ማሸነፋቸው ይፋ ተደርጓል።
የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪው ኢሳ ባካሪ በበኩላቸው የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት ማሸነፋቸውን አውጀዋል ተብሏል።
የፖል ቢያን ማሸነፍ የተቃወሙ ዜጎች አደባባይ በመዉጣት ተቃውሞ ሲያሰሙ ከሟቾች ውጭ የተረጂዎች ቁጥር አልታወቀም።
ፖሊስ ተቃውሞውን ለማብረድ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል ተብሏል። #worldpoliticsreview
@ThiqahETH
የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ የ5 ዓመት እስር ተፈረደባቸው።
ሳርኮዚ ለምርጫ ዘመቻ ከቀድሞው የሊቢያ ፕሬዚዳንት መሐመድ ጋዳፊ ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የ70 አመቱ ሳርኮዚ ወደማረሚያ ቤት ሲሄዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ ሲያቀርቡላቸው ታይተዋል።
ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ከ2012 እስከ 2017 ፈረንሳይን አስተዳድረዋል። #upi
@ThiqahETH
ጃፓን የመጀመሪያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በይፋ ሾመች፡፡
ወግ አጥባቂ ናቸው የሚባሉት ሳኔ ታካይቺ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ታካይቺ 465 መቀመጫዎች ባሉ የሀገሪቷ ፓርላማ 237 ድምጽ በማግኘት ነው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የቻሉት ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከፓርቲያቸው ነጻ አውጪ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (LDP) ከፍተኛ ድምፅ ማግኘት መቻላቸው ተገልጿል።
ታካይቺ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻንም በከፍተኛ ሁኔታ ትቃወማለች፡፡ #aljazeera
@ThiqahETH
"ፈረንሳይ ትውጣልን" - የማዳጋስካር ተቃዋሚዎች
በዋና ከተማዋ አንታናሪቮ የተሰባሰቡ የሀገሪቱ ዜጎች ፈረንሳይን የሚያወግዝ ተቃውሞ አሰምተዋል ተብሏል።
ተቃዋሚዎቹ፣ "ራጆሊናና ማክሮን ይውጡ" ሲሉ ተደምጠዋል።
በህዝብ ተቃውሞ ከሃገር ሸሽተው የወጡት የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንድሬ ራጆሊና ፈረንሳይ ይገኛሉ።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ልዩ የጦር አውሮፕላን በመላክ ራጆሊና እንዲኮበልል እገዛ አድርገውላቸዋል ተብሏል። #iol
@ThiqahETH
በካሜሩን የገዥው ፓርቲ ቢሮ በእሳት ተቃጠለ።
በቅርቡ ምርጫ ያካሄደችው ካሜሩን ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ነግሶባታል።
የተፎካካሪ ፓርቲ ዕጩ ኢሳ ቶቺራ ቤከሪ ማሸነፋቸውን ቀድመው ማወጃቸው ውጥረቱን አባብሶታል። #morningstar
@ThiqahETH