15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"አርፏል" - የዶክተር ሰለሞን አሰፋ የቅርብ ሰው
የኢትዮጵያ ኩላሊት እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዬ።
ዶ/ር ሰለሞን በሞት መለየታቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲቃህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። አንድ ቤተሰባቸው በሰጡን ቃል፣ "አዎ አርፏል" ብለዋል።
ቀብራቸው ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸምም ተጠቁሟል።
ዶ/ር ሰለሞን የኩላሊት ህሙማን ከሚገፉት አስከፊ ህይወት እንዲገላገሉ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን በማድረግ ይታወቁ ነበር።
@ThiqahEth
"የሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ባለበት ሁኔታ አንድም የአሜሪካ ባለስልጣን በስብሰባው አይገኝም" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቡድን 20 ስብሰባ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደማይሄዱ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ በሀገሪቱ በነጮች ላይ የዘር ማጥፋት እየተፈፀመ ነው በማለት ነው በስብሰባው ላለመሳተፍ የወሰኑት።
ትራምፕ በትሩዝ ሶቫል ገፃቸው ላይ "የፈረንሳይ፣ የኔዘርላንድ እና ጀርመን ስደተኞች እየተገደሉ፣ የእርሻ መሬታቸውን በህገወጥ መንገድ እየተቀሙ ነው" ብለዋል።
"የሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ባለበት ሁኔታ አንድም የአሜሪካ ባለስልጣን በስብሰባው አይገኝም" ሲሉም ገልጸዋል።
ትራምፕ "ያሳፍራል" በማለት ደቡብ አፍሪካ አመታዊ ጉባኤ ማዘጋጀቷን ተቃውመዋል። #aljazeera
@ThiqahETH
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌዴሌቦ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ተመራማሪው በሞት የተለዩት ባደረባቸው ህመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ87 ዓመታቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለኤፍኤምሲ ገልጸዋል።
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መፅሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የህዝብ ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተነግሮላቸዋል።
የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ስርዓታቸው የፊታችን ማክሰኛ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ/ም እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ #FMC
@ThiqahEth
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ11 ሺሕ 800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በሥርዓተ ትምህርት መሰረት ያስተማራቸው ከ11 ሺሕ 800 በላይ ተማሪዎችን ለ5ኛ ጊዜ በሚሊየም አዳራሽ እያስመረቀ መሆኑን ኢኦቲሲ ዘግቧል።
በመርሃ ግብሩ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምጦስ የመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀድያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተገኝተዋል። #EOTC
@ThiqahETH
#Metema
በመተማ ወረዳ በትራፊክ አደጋ አራት ሰዎቹ ሲሞቱ ሌሎች ተጎዱ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ ባጋጠመው የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን በመተማ ወረዳ የኩመር አፍጥጥ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ውበት መኮነንን ገልጸዋል።
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ 2 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት አንዲሁም የንብረት ውድመት መድረሱን ገልጸዋል።
አደጋው የደረሰው አንድ የህዝብ ማመላለሻ አባዱላ መኪና ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም 11 ሰዓት ገደማ ከመተማ ዮሐንስ ወደ ገንደ ውሃ ከተማ አስተዳደር በመጓዝ ላይ እያለ መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ ሰዎችን አሣፍሮ ከገንደውሃ ወደ ኮኪት ከተማ ከሚጓዝ ባጃጅ ጋር በመጋጨት ነው።
የተጎዱ ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም መወሰዳቸውና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑም ዞኑ አስታውቋል። መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ነው።
@ThiqahEth
የሶርያ ፕሬዝዳንት አህመድ አልሻራ አሜሪካ ገቡ።
አልሻራ በአሜሪካ ከሚገኙ የሶርያ ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል ተብሏል።
ጉብኝቱ ከአሜሪካ የሽብር ዝርዝር ውስጥ ከወጡ በኋላ መደረጉን የዲፕሎማሲ ምንጮች ገልፀዋል።
አልሻራ ኖቬምበር 10 ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር የፊት ለፊት ውይይት ያደረጉ የመጀመሪያው የሶርያ ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል ተብሏል። #yenisafaq
@ThiqahEth
"በተመሳሳይ ተልዕኮ ኢትዮጵያ፣ ኢራቅ፣ ሄይቲ፣ ሶሪያ፣ ዩክሬንና ሴራሊዮን ሰርቻለሁ በሱዳን እንደተፈጠረው አይቼ አላውቅም" ጃቢድ አብድልመኒም
በሱዳን ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተባለ።
በሱዳን ንፁሃን ዜጎች የእርስበርስ ጦርነቱን ሸሽተው መጥፋታቸውን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ፕሬዚዳንት ጃቢድ አብድልመኒም ተናግረዋል።
አብድልመኒም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሰጡት መግለጫ "የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የኤልፋሽር ከተማን ሲቆጣጠር ከተማዋን ለቀው የሸሹት እስካሁን ድረስ የት እንደገቡ አይታወቅም" ሲሉ አብራርተዋል።
አብድልመኒም በመግለጫቸው "5000 ታዊላ ከተማ ደርሰዋል፣ ቀሪዎቹ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጠፍተዋል" ብለዋል።
"በተመሳሳይ ተልዕኮ ኢትዮጵያ፣ ኢራቅ፣ ሄይቲ፣ ሶሪያ፣ ዩክሬንና ሴራሊዮን ሰርቻለሁ በሱዳን እንደተፈጠረው አይቼ አላውቅም" በማለት የችግሩን ውስብስብነት ገልፀዋል።
የታዊላ ከተማ ከኤልፋሽር 70 ኪሎሜትር ርቃ እንደምትገኝ ተገልጿል። #thejordantimes
@ThiqahETH
የሱዳን ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ገለጹ።
የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች ከሁለት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተኩስ አቁም ለማድረግ ፍላጎታቸውን አሳይተዋል ተብሏል።
በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች አሜሪካ ላቀረበችው የሰላም እቅድ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ቡድን ስር ከአሜሪካ በተጨማሪ ሳዑዲዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ግብፅ ይገኙበታል። #dw
@ThiqahEth
"ናይጄሪያ የማትፈልገውን ነው የምናደርገው" - ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናይጄሪያን በድጋሚ አስጠነቀቁ።
ፕሬዚደንቱ ከነጩ ቤተ መንግስት ሆነው ባስተላለፉት መልዕክት፣ "የክርስቲያኖች የማያባራ ስቃይና ሞት ለአንዴና ለመጨረሻ መቆም አለበት" ብለዋል።
ትራምፕ አክለው፣ "ናይጄሪያ የማትፈልገውን ነው የምናደርገው" ሲሉ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል።
ፕሬዜዳንቱ ክርስቲያኖች አላግባብ እየተገደሉባት ነው ባሏት ናይጄሪያ ላይ ጦር ሊያዘምቱ እንደሚችሉ መናገራቸው ይታወሳል። #politicsnigeria
@ThiqahETH
በአሜሪካ የጭነት አውሮፕላን ላይ በተፈጠረ አደጋ ቢያንስ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
ኪንታኪ ግዛት ከሚገኘው የሉስቪል አየርማረፊያ የተነሳው አውሮፕላኑ በረራ ሲጀምር እንደተከሰከሰ የከተማዋ ከንቲባ ክራ ግሪንበርግ ተናግረዋል፡፡
በአደጋው ሶስት የበረራ አባላትን ጨምሮ 11 ሰዎች ተጎድተው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል፡፡
ኤም ዲ 11 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን የመርከብ ቁሳቁሶችን ጭኖ እንደነበር ከንቲባው ገልጸዋል፡፡#timeslive
@ThiqahETH
የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ዲክ ቼኒ በ84 አመታቸው አረፉ።
በ2003 አሜሪካ ኢራቅ ላይ ወረራ እንድትፈጽም ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሶስት ወር በፊት ቼኒን በዚሁ ውሳኔያቸው ጥፋተኛ ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
ዲክ ቼኒ በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን ለሁለት ዙር ምክትል ፕሬዝዳንት ሁነው አገልግለዋል ተብሏል።
ቼኒ በሳምባ ህመም ምክንያት ለወራት ታመው መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። #aa
@ThiqahETH
"ቤት ለቤት እየዞሩ ጅምላ ግድያ፣ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል፣ ህፃናት በወላጆቻቸው ፊት ተረሽነዋል" - ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት
በሱዳን የተፈጸመው ግድያ የጦር ወንጀል ተደርጎ እንደሚወሰድ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገለጸ።
ፍርድ ቤቱ በኤልፋሽር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የወሰዱት አሰቃቂ እርምጃ " በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል" መሆኑን አስታውቋል።
የጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ታጣቂዎች ኤልፋሽርን ከተቆጣጠሩ በኋላ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ከዓይን እማኞች ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል።
የአይን እማኞቹ "የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ ጅምላ ግድያ፣ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል፣ ህፃናት በወላጆቻቸው ፊት ተረሽነዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ ታጣቂዎቹ በኤልፋሽር ሆስፒታል ላይ በፈጸሙት ጥቃት 460 ሰዎች መገደላቸውንና የህክምና ባለሙያዎች መታገታቸውን አስታውቋል። #france24
@ThiqahETH
ሳሚያ ሱሁሉ የታንዛኒያ ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ።
ፕሬዜዳንቷ ተቃውሞ ባስከተለው አወዛጋቢ ምርጫ 98% ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል ተብሏል።
ፖሊስ ምርጫው ነፃና ገለልተኛ አይደለም በሚል ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ700 በላይ መገደላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲው አስታውቋል። #aljazeera
@ThiqahETH
"ዥ ታይዋንን እንደማይወር ቃል ገብቶልኛል። ምክንያቱም ውጤቱን ያውቁታል" - ትራምፕ
"የታይዋን ጥያቄ የቻይና የውስጥ ጉዳይና ብሄራዊ ጥቅም ነው" - በዋሽንግተን የቻይና ኤምባሲ
ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታይዋን ጉዳይ ከቻይናው አቻቸው ዢ ጂፒንግ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
ፕሬዜዳንቱ "ትራምፕ ፕሬዜዳንት እስከሆንክ ድረስ በታይዋን ላይ ምንም አናደርግም ብለውኛል" ሲሉ ተናግረዋል።
"ዥ ታይዋንን እንደማይወር ቃል ገብቶልኛል" ያሉት ትራምፕ፣ "ምክንያቱም ውጤቱን ያውቁታል" ብለዋል።
በአሜሪካ የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንግዩ ለትራምፕ አስተያየት በሰጡት የአጸፋ ምላሽ "ማንኛውም ግለሰብ ወይም ኃይል ታይዋንን ከቻይና እንዲገነጥል አንፈቅድም" ብለዋል።
"የታይዋን ጥያቄ የቻይና የውስጥ ጉዳይና ብሄራዊ ጥቅም ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
ፔንግዩ "ጥያቄው እንዴት ይፈታ የሚለውን የቻይና ህዝብ ይወስናል" ነው ያሉት።
ቃል አቀባዩዋ ትራምፕ፣ "ቃል ተገብቶልኛል" ስላሉት ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። #euronews
@ThiqahEth
"ብዙ የውይይት አጀንዳዎች አሉ፣ ማዕቀብ ማንሳትን ጨምሮ ግንኙነትን ለማጠናከር ይመከራል" - ቶም ባራክ
የሶርያ ፕሬዜዳንት መሀመድ አልሻራ ወደ አሜሪካ ሊያቀኑ ነው።
የሶርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አልሻይባኒ አልሻራ በህዳር ወር መጀመሪያ እንደሚጓዙ አስታውቀዋል።
በሶርያ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ባራክ የፕሬዚዳንቱ ጉዞ ህዳር 10 ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ባራክ፣ "ብዙ የውይይት አጀንዳዎች አሉ፣ ማዕቀብ ማንሳትን ጨምሮ ግንኙነትን ለማጠናከር ይመከራል" ብለዋል።
ፕሬዜዳንት መሀመድ አልሻራ የአላሳድን መንግስት በሀይል ካስወገዱ በኋላ የሶርያን ግንኙነት ለማደስ ተደጋጋሚ የውጭ ሀገር ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ።
አልሻራ ዶናልድ ትራምፕ ሳውዲ አረቢያ መጥተው በነበረበት ወቅት ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል።
ካሁን በፊት በነጩ ቤተመንግሥት የተጋበዘ የሶርያ ፕሬዝዳንት አለመኖሩ ተገልጿል። #telegraph
@ThiqahETH
የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኡማር ጉሌህ ለስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ተገለጸ።
የብሔራዊ ሸንጎ ፕሬዚዳንት ድሌታ መሀመድ "እሱ (ጉሌህ) በቀጣዩ ምርጫ እጩ ለመሆን ተስማምቷል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በ1999 የጅቡቲ አባት እየተባሉ ከሚጠሩት ሀሰን አፕቲደንን በመተካት ከነፃነት በኋላ ሁለተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆን ችለዋል።
የሀገሪቱ ፓርላማ 75 አመት የነበረውን የፕሬዝዳንትነት የእድሜ ገደብ ከሁለት ሳምንት በፊት አንስቷል። #thisdaylive
@ThiqahETH
#Hawassa
በሀዋሳ በትራፊክ አደጋ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ በስምንቱ ጉዳት ደረሰ።
ከሀዋሳ ወደ ዶሬ ሲጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ ባስከተለው አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉን የከተማው ፓሊስ አስታውቋል።
ይህን ያሉት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮምሽነር ግርማ ማቲዎስ፣ በ5 ሰዎች ላይ ቀላል፣ በ3 ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ፓሊስ እንዳለው ከሆነ፤ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ፍንጫዋ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ባለው 300 ሜትር ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ስቶ በመግባቱ ነው።
ከተሽከርካሪው ጋር በተያያዘ ያለ ችግር በምርመራ ላይ መሆኑና ጉዳት የደረሰባቸው በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ላይ መወሰዳቸውም ተገልጿል።
መረጃው የሀዋሳ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው።
@ThiqahETH
በማሌዥያ የስደተኞች ጀልባ በደረሰባት የተገልበጥ አደጊ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጠፉ።
300 ስደተኞችን ጭና ከማይናማር ጭና ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ማሌዥያን ከታይላንድ በሚያዋስነው ድንበር የመገልበጥ አደጋ አጋጥሟታል ተብሏል።
10 ሰዎች ብቻ በህይወት መገኘታቸው ተገልጿል።
በጀልባዋ ውስጥ የነበሩት አብዛኞቹ የሮሂንጊያ ስደተኞች እና የባንግላዴሽ ዜጎች ናቸው ተብሏል።
የፍለጋ ስራው አሁንም መቀጠሉ ተገልጿል። #outlook
@ThiqahETH
#Dembecha
"የHIT ባለሙያዋ በጦር መሣሪያ ጥቃት ተፈፅሞባታል" - ጽ/ቤቱ
በደምበጫ ወረዳ በአንጀኔ ጤና ጣቢያ በHIT ባለሙያነት ስታገለግል የነበረችው ቤተልሔም አዲስ "በአካቢው የሚንቀሳቀስው ታጣቂ ቡድን አባል በሆነ ግለሰብ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሸቱ 3 ሰዓት ተኩል በጦር መሳሪያ ጥቃት ተፈፅሞባታል" ሲል የደምበጫ ወረዳ ጤና ጽፈት ቤት አስታውቋል።
"በጥቃቱ ወዲያው ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በደምበጫ ጽ/ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብሯ ተፈጽሟል" ነው ያለው።
"የአንጀኔ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ላደረገው መቆርቆርና ለምንወዳት ልጃችን በስራ ቦታ ላይ መሠዋት ያፈሰሰው እምባና ያሳየው ቁጭት ምን ያህል ሰላም ፈላጊ መሆኑን ያየንበት" ነው ብሏል።
"ይህ አይነቱን ሳይመርጥ የሚያጠፋ ገዳይ ሀይልን እንዲያወግዝ እየጠየቅን የጤና ሙያተኞች የሚያገለግሉት ህዝብን በመሆኑ ከእንደዚህ አይነት አሰቃቂ ግድያና ጥቃት ሙያተኞችን እንዲከላከል" አሳስቧል።
መረጃው የደምበጫ ወረዳ ጤና ጽፈት ቤት ነው።
@ThiqahETH
"ለጦርነት ዝግጁ ነን" - ታሊባን
የአፍጋኒስታን እና የፓኪስታን የሰላም ስምምነት ፈረሰ።
የአፍጋኒስታን አስተዳዳሪ ታሊባን ለስምምነቱ መጣስ የፓኪስታንን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል ተብሏል።
ስምምነቱ መፍረሱን ተከትሎ የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቡሂላህ ሙጃሂድ በሰጡት አስተያየት "ሆን ተብሎ ስምምነቱ ተጠልፏል" ብለዋል።
"ሀላፊነት የማይሰማውና ትብብር የማያውቀው የተደራዳሪ ልዑክ በስምምነቱ የመጨረሻ ቀን አፈንግጧል" ሲሉ የወቀሱት ቃል አቀባዩ "ለጦርነት ዝግጁ ነን" ሲሉ ተደምጠዋል።
ሙጃሂድ በገለፃቸው "ጦርነት ከተጀመረ ራሳችንን የመከላከል መብት አለን" በማለት ተናግረዋል።
ፓኪስታን በስምምነቱ መጣስ ዙሪያ እስካሁን የሰጠችው አስተያየት እንደሌለ ተገልጿል።
አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ከአንድ ወር በፊት ወደጦርነት ገብተው የነበረ ቢሆን፣ ግጭቱ በጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ተቋጭቷል። #theweek
@ThiqahEth
ቱርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያም ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣች።
ቱርክ "በጋዛ የዘር ማጥፋት ተሳትፈዋል" ባለቻቸው ኔታንያሁና ሌሎች 36 የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ነው የእስር ትዕዛዝ ያወጣችው ተብሏል።
ከእነዚህም መካከል የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤንጋቪር እና የጦር ሀይል አዛዡ ሌተናንት ጄነራል እያል ዛሚር ይገኙበታል ተብሏል።
እስራኤል "የፖለቲካ አቋምን ያንፀባርቃል" በሚል የእስር ትዕዛዙን መቃወሟ ተገልጿል።
ሀማስ በበኩሉ የቱርክን ውሳኔ በፅኑ እንደሚደግፍ አስታውቋል። #outlooknewsdesk
@ThiqahETH
በአሜሪካ 40 የሚደርሱ አየር መንገዶች በረራ ማቋረጣቸው ተገለጸ።
የአሜሪካ መንግስት ከበጀት ጋር በተያያዘ የሀገር ውስጥ በረራዎች እንድቀንሱ ትዕዛዝ ማስተላለፉ የፌደራል አቪየሺን ባለስልጣን አስታውቋል።
የሀገር ውስጥ በረራዎችን በ4% መቀነሳቸውን የገለፀው ባለሬልጣኑ ይህ ቁጥር ወደ10% ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁሟል።
በዚህ ውሳኔ የተነሳ የደልታ አየርመንገድ 170 በረራዎችን፣ ዩናይትድ አየርመንገድ 200 በረራዎችን፣ አሜሪካ አየርመንገድ 220 በረራዎችን ለመሰረዝ ተገደዋል ተብሏል። #aa
@ThiqahETH
እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።
የእስራኤል ጦር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጦ፣ ሂዝቦላን ኢላማ ማድረጉን ገልጿል።
በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለጸም ተብሏል።
እስራኤል እና ሂዝቦላ ከአንድ አመት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። #ashraqalawusat
@ThiqahETH
በፊሊፒንስ በአውሎ ነፋስ አደጋ የ114 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ፕሬዝዳንት ፈርድናንድ ማርቆስ የአስቸኳይ ጊዜ መታወጁን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ እስካሁን ድረስ የተጎጂዎች ቁጥር በትክክል እንደማይታወቅ ገልፀው፣ 127 ሰዎች መጥፋታቸውን አስታውቀዋል። #yenisafaq
@ThiqahETH
ዞህራን ማምዳኒ የኒዮርክ ከንቲባ ሆነው ተመረጡ።
የዲሞክራቱ ተወካይ ማምዳኒ የሪፐብሊካኑን ተወካይ አንድሪው ኩሞን በማሸነፍ ነው የአለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው ኒዮርክ ከንቲባ መሆን የቻሉት ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዲሞክራቱ ማምዳኒ ካሸነፈ ለኒዮርክ የሚመደበውን በጀት አቋርጣለሁ ብለዋል።
ከህንዳውያን ስደተኞች ቤተሰብ የተገኘው ማምዳኒ የመጀመሪያው ሙስሊም ከንቲባ መሆን ችሏል። #thetelegraph
@ThiqahEth
ፔሩ ከሜክሲኮ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጡን ገለጸች።
ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ የገቡት ሜክሲኮ ለቀድሞዋ የፔሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባትሴ ቻቬዝ ጥገኝነት በመስጠቷ እንደሆነ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ በሚገኘው የሜክሲኮ ኤምባሲ ጥገኝነት ጠይቀዋል ተብሏል።
የፔሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁጎ ዘላ "ከቻቬዝ የጥገኝነት ጥያቄ መቀበል ወዳጅ እንዳልሆኑ ማሳየት ነው" ብለዋል።
ዛላ "የመፈንቅለ መንግስት ዋና አስተባባሪ ለሆነ ግለሰብ ዋስትና መስጠቱ ጸጸት ይፈጥራል" ሲሉ ተናግረዋል። #euronews
@ThiqahETH
#Arsi
"አምስት ንጹሐን በታጣቂዎች ትላንት ተገድለዋል፣ ሌሎች በርካቶች ያሉበት አልታወቀም" - አመራር
ሰሞኑን 25 ኦሮቶዶክሳውያን በተገደሉበት ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ታጣቂዎች በድጋሚ ግድያ መፈጸማቸው ተሰምቷል።
በዞኑ መርቲ ወረዳ፣ "በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ አምስት ንጹሐን በታጣቂዎች ትላንት ተገድለዋል፣ ሌሎች በርካቶች ያሉበት አልታወቀም" ሲሉ አንድ የአካባቢው አመራር ነግረውናል።
በዚህ ባለንበት ጥቅምት 2018 ዓ/ም በአርሲ ዞን 25 ኦሮቶዶክሳውያን መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ትላንቶቹ ጋር ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 30 ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል።
በመንግስት በኩል ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰጥ ቤተክርስቲያና ሌሎች ተቋማት ጭምር በመግለጫ ሲጠይቁ ቢስተዋሉም፣ ጉዳዩ መፍትሄ ባለማግኘቱ ግድያው አልቆመም።
@ThiqahETH
የሊቢያ የትምህርት ሚኒስትር በቁጥጥር ስር ዋሉ።
አሊ አል አቤድ ለሁለት ሚሊየን ተማሪዎች የመማሪያ መፅሐፍ ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ተብሏል።
የሊቢያ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሚኒስትሩ "የተማሪዎችን የመማር መብት ጥሰዋል" ሲል ወንጅሏል።
ከአቤድ በፊት የነበሩት ሚኒስትር ሙሳ ማግሪፍ በተመሳሳይ ወንጀል ተከሰው የሶስት አመት ከግማሽ እስር ተፈርዶባቸዋል ተብሏል። #thearabweekly
@ThiqahETH
በአፍጋኒስታን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ 150 ተጎዱ።
በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ኩሉም ከተማ በሬክተር ስኬል 6.3 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂዖሎጂካል ሰርቬይ (USGS) አስታውቋል።
ማዕከሉ ከአደጋው አንፃር የተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል። #reuters
@ThiqahETH
በሜክሲኮ በተከሰተ ፍንዳታ የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
ሱፐር ማርኬት ውስጥ በተከሰተው በዚህ አደጋ 11 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል።
የሳኖራ ግዛት አስተዳዳሪ አልፎንሶ ዱራዞ የፍንዳታው መንስኤ በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ገመድ ላይ የተፈጠረው ቃጠሎ ነው ብለዋል።
የሜክሲኮ ግዥና ንብረት ባለስልጣን በበኩሉ፣ የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ወደስራ መሰማራታቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዜዳንት ክላውዲያ ሽንባውም በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። #sana #afp
@ThiqahETH