15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
"ለዚሁ በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 420 ሚሊዮን ዶላር መድቤያለሁ" - ብሔራዊ ባንክ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከታህሳስ መጨረሻ እስከ መጋቢት መጀመሪያ ሳምንት ድርስ ለሚያደርገው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 420 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በተጠቀሰው ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ እንደሚደረግ፣ ለየጨረታው 70 ሚሊዮ ዶላር መመደቡንም ባንኩ ገልጿል።
የውጭ ምንዛሪ ጨረታው በየሁለት ሳምንት እንደሚካሄድም በመግለጫው ያሰፈረው ባንኩ፣ በህዳር 23 እና ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ/ም ለሚያካሂደው ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር መድቤያለሁ ብሏል።
የውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ግልጽና ተገማች አሰራርን ለማጠናከር አለኝ ባለው ቁርጠኝነት በየሩብ ዓመቱ የሚደረጉ የጨረታ ግብይቶችን በየጊዜው ማሳወቁን እንደሚቀጥል ጠቁሟል። #NationalBankEthiopia
@ThiqahETH
ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 25 ሰዎች ሞቱ።
ሩሲያ የሚሳዔል እና ድሮን ጥቃት መፈጽሟን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንት ዘለንስኪ ሩሲያ በ48 ሰዓት ውስጥ 476 ሰው አልባ አውሮፕላን እና 48 ክሩዝና ባለስቲክ ሚሳዔል አስወንጭፋለች ብለዋል።
ዘለንስኪ ጥቃቱ የተፈጸመው በካርኪቭ እና ሌቪቭ ከተሞች መሆኑን ገልጸዋል። #cbsnews
@ThiqahETH
12 ፍልስጤማውያን እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት ተገደሉ።
እስራኤል ሲዶን በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈፀሟን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉ ገልፆ ቁጥራቸውን ግን በትክክል ማወቅ አልተቻለም ብሏል። #middleeastmonitor
@ThiqahETH
ጄምስ ኢጋ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተሾሙ።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጄምስ ኢጋን የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዜዳንት አድርገው ሾሙ።
ፕሬዜዳንት ማያርዲት የቀድሞውን ምክትል ፕሬዜዳንት ቤንጃሚን ሜል ቦልን ባሳለፍነው ሳምንት አርብለት ከሀላፊነት ማሰናበታቸው ይታወሳል።
አዲሱ ምክትል ፕሬዜዳንት የገዥው ኤስፒኤልኤም ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል ተብሏል።
በተመሳሳይ መልኩ የቀድሞው የፕሬዜዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቴን ዌክ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አድርገው መሾማቸው ተገልጿል። #sudanpost
@ThiqahETH
የፀጥታው ምክርቤት አለማቀፍ ሀይል በጋዛ እንዲሰማራ የቀረበውን እቅድ አጸደቀ።
እቅዱ በአሜሪካ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን፣ ከ15 አባላት 13ቱ ሲያጸድቁት ሩሲያ እና ቻይና ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል ተብሏል።
የተመድ የሚመራው አለማቀፍ የሰላም አስከባሪ ሀይል ከወራት በኋላ በጋዛ እንደሚሰማራ ይጠበቃል። #rfi
@ThiqahETH
ዩክሬን 100 ራፋይል ጥይቶችን ከፈረንሳይ ገዛች።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እና ፕሬዚዳንት ማክሮን የተዋጊ ጀት፣ ድሮን እና የተሻሻሉ የጦር መሳሪያዎች ግዥ ስምምነት ፈፅመዋል ተብሏል።
ስምምነቱ እስከ ለአስር አመት ያክል 2035 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
ዘለንስኪ የተደረገው ስምምነት የዩክሬንን የመከላከል አቅም ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።
ሁለቱ መሪዎች "ታሪካዊ" ያሉትን የመከላከያ ስምምነት የፈፀሙት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ወደ ፈረንሳይ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል። #trtworld
@ThiqahETH
የቀድሞዋ የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው።
በሽሽት በህንድ የሚገኙት ሼክ ሀሲና "በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል" ተከሰው በሌሉበት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ተብሏል።
የባንግላዴሽ ከፍተኛ ፍርድቤት ጠቅላይ ሚኒስትሯ በስልጣን በነበሩበት ወቅት በመንግሥታቸው ላይ ተቃውሞ ባስነሱ ዜጎች ላይ ግድያ እንድፈፀም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ተማሪዎች ባስነሱት አመፅ ተገደው ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ወደህንድ ሸሽተዋል።
ከሼክ ሀሲና በተጨማሪ የቀድሞው የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አሳዱዝማን ከማል እና የሀገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ቾውዱሪ አብዱላህ ላይም ተመሳሳይ የሞት ፍርድ ማስተላለፉን ገልጿል። #telegraph
@ThiqahETH
45 ህንዳውያን በሳውዲ አረቢያ ህይወታቸው አለፈ።
ለኡምራ ወደ ጂዳ የተጓዙ ህንዳውያን የተሳፈሩበት መኪና ከሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል።
በአደጋው አንድ ሰው ብቻ መትረፉን የሙፍሪት ከተማ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮሚሽነር ሳጃናር ገልፀዋል። #gulfnews
@ThiqahETH
"ይቅርታ ብቻ በቂ አይደለም" ዶናልድ ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ "ስሜን አጥፍቷል" ባሉት ቢቢሲ ላይ የ5 ቢሊዮን ዶላር ክስ እንደሚመሰርቱ አስታወቁ።
ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ሀሳብ "ቢቢሲ በእኔ ላይ የፈፀመውን ስህተት በሌሎች ላይ መፈፀም የለበትም" ብለዋል።
"ሲጀመር ያን ለምን እንዳደረጉ ለፍርድ ቤት ማብራራት አለባቸው" ያሉት ፕሬዚዳንቱ "እስካሁን ስንት ጊዜ እንደዋሹ ማሳወቅ አለብን" በማለት ተናግረዋል።
"ቢቢሲ ላጠፋው ጥፋት ይቅርታ ብቻ በቂ አይደለም፣ ገንዘብም መቀጣት አለበት" በማለት ክሱ እንደማይቀር ጠቁመዋል።
ስህተት መፈፀሙን ያመነው ቢቢሲ በበኩሉ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የይቅርታ ደብዳቤ መፃፉን ገልጿል። #theweek
@ThiqahETH
ቢቢሲ ዶናልድ ትራምፕን ይቅርታ ጠየቀ።
የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ሳሚር ሻህ ፕሬዚዳንት ትራምፕን በተመለከተ ፓኖራማ በተባለው ፕሮግራም የአርትኦት ችግር መፈጠሩን በፃፉት የይቅርታ ደብዳቤ ገልፀዋል።
ሚዲያው ይህ ፕሮግራም ባስተላለፈበት ወቅት በ2021 በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን አመፅ አስነስተዋል ሲል ተጠያቂ አድርጓቸዋል።
ይህን ተከትሎ የሀሰት ውንጀላ ቀርቦብኛል ያሉት ትራምፕ ጣቢያው ይቅርታ ካልጠየቀ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።
ነገርግን የዩናይትድ ኪንግደም አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሆነው ቢቢሲ የስም ማጥፋት እንዳልፈፀመ አስታውቋል። #thenewarab
@ThiqahETH
ሁለት የዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገለፀ።
ባለስልጣናቱ የፍትህ ሚኒስትር ሄርማን ሀሉሼቼንኮ እና የኢነርጂ ሚኒስትር ስቪትላና ግሬንቾክ ናቸው።
ሚኒስትሮቹ የ100 ሚሊየን ዶላር ሙስና በማጭበርበር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ ነው ለመልቀቅ የወሰኑት ተብሏል።
ባለስልጣናቱ የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የሀይል መሰረተ ልማት የመደበውን ፈንድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ነው የተባለው።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከገባችበት ጀምሮ ከፍተኛ የሙስና አዘቅት መግባቷ ተገልጿል። #theindependent
@ThiqahETH
በሊቢያ ቢያንስ 42 ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
በጀልባዋ ከነበሩት በህይወት የተገኙት ሰባት ሰዎች ብቻ መሆናቸውን አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።
ከአደጋው የተረፉት ለስድስት ቀን በባሕር ዳርቻ ያለ ምግብ እና ውሃ መቆየታቸውን ገልጿል።
ነገርግን ወደትሪፖሊ ተወስደው የህክምናኳ የምግብ እና የውሃ አገልግሎት አግኝተዋል ተብሏል።
በዚህ ጀልባ ላይ ከነበሩት ስደተኞች 29 ሱዳናውያን፣ 8 የሱማሌ ዜጎች፣ ሶስት የካሜሩን እና ሁለት የናይጄሪያ ዜጎች መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
በባለፈው የመስከረም ወር ከሱዳን፣ ባንግላዴሽ እና ፓኪስታን የተውጣጡ 68 ስደተኞች ተመሳሳይ አደጋ ደርሶባቸው እንደነበር የገለፀው አይ ኦ ኤም፣ የ18 ስደተኞች ህይወት አልፏል ብሏል።
የፈረንጆች 2025 ከገባ ወዲህ ባለፉት 11 ወራት ከ1000 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ህይወት ማለፉን አመላክቷል። #abcnews
@ThiqahETH
ፕሬዚዳንት ፔትሮ "ኮሎምቢያ ከአሜሪካ ጋር የደህንነት መረጃ መለዋወጥ አቁማለች" አሉ።
ዋሽንግተን በካሪቢያን ቀጠና በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ካሁን በፊት ጋር ስታደርገው የነበረውን የደህንነት መረጃ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ ማቆሟን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ "የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በካሪቢያን ባህር ጀልባዎች ላይ የሚሳዔል ጥቃት መፈፀሙን አላቆመም" ሲሉ ተናግረዋል።
ፔትሮ በኤክስ ገፃቸው ላይ "ከአሜሪካ የደህንነት ኤጀንሲዎች ጋር የሚደረግ ግንኙነት እንዲቆም ለሁሉም የመንግስት ተቋማት የደህንነት ቢሮ አሳውቂያለሁ" ሲሉ አስፍረዋል።
"በጀልባዎቻችን ላይ የሚደርሰው ጥቃት እስከቀጠለ ድረስ እኛም የአፀፋ እርምጃ እንወስዳለን" በማለት ገልፀዋል።
የህግ ጥሰት ነው ባሉት የአሜሪካ ጥቃት እስካሁን 70 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል። #aljazeera
@ThiqahETH
በፓፑዋ ኒው ጊኒ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
አደጋው የተከሰተው ከዋና ከተማዋ 32 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው የማዳንግ ግዛት ውስጥ መሆኑን የሀገሪቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መከላከያ ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው በደረሰው በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጉዳት አለመመዝገቡን ገልጿል። #volcanodiscovery
@ThiqahETH
"የቡድን 20 ስብሰባ ያለ አሜሪካ ተሳትፎ መካሄድ ይችላል" - ደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካ የገዢው ፖርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ (ANC) ዋና ፀሐፊ ፊክሌ ምባሉላ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ላቀረቡት ወቀሳ የአፀፋ ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ "የደቡብ አፍሪካ መንግስት በነጭ አፍሪካውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው" በማለት ጆሀንስበርግ በሚካሄደው የቡድን 20 አመታዊ ስብሰባ እንደማይገኙ አስታውቀዋል።
ሩቢዮ በበኩላቸው፣ "ነጭ አፍሪካውያን ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑት ሁኔታ አሜሪካ የምትልከው ዲፕሎማት አይኖርም የሚለውን የትራምፕ ሀሳብ እኔም እደግፋለሁ" ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
የፓርቲው ፀሐፊ ታድያ "ይህ የተሳሳተ የኢምፔሪያሊስቶች አስተሳሰብ ነው" በማለት ወቀሳውን ተቃውመዋል።
ምባሉላ "ይህ የለየለት ውሸት ነው፣ በደቡብ አፍሪካ የዘር ጥቃት የለም" ብለዋል።
"የደቡብ አፍሪካ ህግ በአፓርታይድ ዘመን የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት መከለስ አለበት" ያሉት ምባሉላ፣ "ተመድ በጥቁሮች ላይ የተጫነ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል አድርጎ ፈርጆታል" ሲሉም ገልጸዋል።
"ሀገራችን ወደ ፊት መቀጠል አለባት" ያሉት ዋና ፀሐፊው፣ "የቡድን 20 ስብሰባ ያለ አሜሪካ ተሳትፎ መካሄድ ይችላል" ነው ያሉት።
ትራምፕ የደቡብ አፍሪካን ሉዓላዊነት አለማክበራቸውና የዴሞክራሲ መርሆዎችን መጣሳቸው አግባብ እንዳልሆነ አብራርተዋል። #timeslive
@ThiqahETH
ከጋዛ የሰላም ስምምነት በኋላ 280 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ።
እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢፈፀምም በጋዛ የምትፈጸመውን ጥቃት አላቆመችም ሲል የጋዛ ሲቪል ድፌንስ (GCD) ገልጿል።
የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተለው ተቋሙ ጥቃቱ አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብሏል።
በትናንትናው እለት ብቻ እስራኤል አደረሰችው በተባለው ጥቃት 25 ሰዎች ሲገደሉ 77 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል።
እስራኤል ከጋዛው ስምምነት በኋላ 12 የአየር ላይ ጥቃቶችን ፈፅማለች ተብሏል። #middleeastmonitor
@ThiqahETH
"ያ አይፈጠርም" ፕሬዝዳንት ሽንባውም
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሽንባውም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጥቃት እንጸፅማለን ማለታቸውን ተቃወሙ።
ፕሬዝዳንቱ "በቅርቡ በሜክሲኮ በሚገኙ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንፈፅማለን" ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሽንባውም ለትራምፕ አስተያየት በሰጡት ምላሽ "የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትን አናስተናግድም" ሲሉ ተናግረዋል።
የፕሬዝዳንቱን ንግግር "ያ አይፈጠርም" ሲሉ ትራምፕ እወስደዋለሁ ያሉትን እርምጃ እንደማይፈፀም አስረድተዋል።#trtworld
@ThiqahETH
አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ እና የቴክኖሎጂ ስምምነት ፈጸሙ።
የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ወደአሜሪካ አቅንተዋል።
ትራምፕ እና ቢን ሳልማን ባደረጉት ስምምነት የኑክሌያር ሀይል፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የኤፍ 35 የጦር ጀት ግዥ ተካቷል ተብሏል።
ሁለቱ መሪዎች በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናዊ ሁኔታ፣ በተለይ በጋዛ የሰላም እቅድ ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል።
አልጋ ወራሹ በልዑካን ቡድናቸው ስር ፖርቹጋላዊውን የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶን አካተዋል ተብሏል። #yenisafaq
@ThiqahETH
"ወላጅ አባቱን እና የእንጀራ እናቱን በጦር መሳሪያ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸው ላይ በጥይት ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል" - ፓሊስ
ወላጅ አባቱን እና የእንጀራ እናቱን በጥይት የገደለው ተከሳሽ በእድሜልክ እስራት መቀጣቱን ፖሊስ ገልጿል።
ይህ የሆነው፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላ ጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው ታቦር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ ትዕዛዙ ዋለልኝ ፈንታ በተባለው ግለሰብ ነው።
በዚህም፣ ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3 ሰዓት ገደማ፣ "ለቤት መስሪያ ባህርዛፍ ካልሰጣችሁኝ በሚል ምክንያት ወላጅ አባቱን እና የእንጀራ እናቱን ለስራ በተሰጠው የጦር መሳሪያ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸው ላይ በጥይት ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል" ብሏል ፓሊስ።
ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን በእጅ ከፍንጅ በማጣራት እና መዝገቡን በተገቢው ሁኔታ በማደራጀት ለምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ መምሪያ መላክ ችሏል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ዐቃቢህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀት በማስረጃ አስደግፎ ክስ በመመስረት ተገቢው የህግ ሂደት እንዲታይ አድርጓል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ መሠረት ተከሳሱ ጥፋተኛ መሆኑን በሰው ማስረጃ በመረጋገጡ በእድሜልክ እስራት መቀጣቱን የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ተወካይ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን ስሌማን ሰይድ ገልጸዋል።
መረጃው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ነው።
@ThiqahETH
የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ።
በድሬደዋ ከተማ ዙሪያ አዋሌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ገንደ ሳሊ ተብሎ በሚጠራው መንደር ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12 ሰአት ገደማ የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ መገኘቱን የድሬዳዋ ፓሊስ አስታውቋል።
የቢየ አዋሌ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢ/ር አብዱሰላም መሀመድ እንደገለጹት፣ ሟች ገመዳ አብደላ የተባለው የ10 አመት ታዳጊ ህዳር 7 ቀን ከምሽቱ 12 ሰአት ገደማ ከቤት እንደወጣ ባለመመለሱ ቤተሰቦቹ ምሽቱን ሲያፈላልጉት ቢቆዩም በንጋታው ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በነብር ተበልቶ ሞቷል ብለዋል።
ፖሊስ በበኩሉ በአካባቢው ነብር መኖሩን እና ከአሁን በፊትም በተደጋጋሚ ግዜ ጥቃት ማደረሱን አስታውሶ የአከባቢው ማህበረሰብ በተለይ ልጆችን ብቻቸውን ከመልቀቅ በመቆጠብ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልዕክቱ አስተላልፏል። #Diredawapolice
@ThiqahETH
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ድልድይ ተደርምሶ 32 ሰዎች ሞቱ።
ድልድዩ ካላንዶ በተሰኘው የማዕድን ማውጫ ስፍራ ላይ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር ተብሏል።
የአደጋው መንስኤ ከባድ ጭነት የያዙ ተሽከርካሪዎዎች በማለፋቸው መሆኑ ተገልጿል። #morningstar
@ThiqahETH
"እንደወጣ አልተመለሰም" - ፓሊስ
"የአዕምሮ ጤና እክል ያለበት የ24 ዓመት ወጣት ጠፍቶብናል” የሚል አቤቱታ ተቀብሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ እና የህብረተሰቡን ትብብር እንደሚፈልግ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ካሚል መሃመድ የተባለ የ24 ዓመት ዕድሜ ያለው እና የአዕምሮ ጤና ዕክል እንዳለበት የተገለፀው ወጣት ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ጠዋት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው እፎይታ የገበያ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኝ መኖሪያ ቤቱ እንደወጣ አልተመለሰም፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የግለሰቡን መጥፋት አቤቱታ ተቀብሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ወጣቱን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር #0112733743 በመደወል ወይም አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ጥቆማ እንዲሰጥ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል፡፡
@ThiqahETH
"አሜሪካ ከማዱሮ ጋር ልትደራደር ትችላለች" ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከቬንዙዌላ ጋር ውይይት ልታደርግ እንደምትችል ጠቆሙ።
ፕሬዝዳንቱ "ቬንዙዌላ ንግግር የምትፈልግ ይመስለኛል" ብለዋል።
"አሜሪካ ከማዱሮ ጋር ልትደራደር ትችላለች" ያሉት ትራምፕ "የሚሆነውን በቀጣይ አብረን እናያለን" ሲሉ ተናግረዋል።
አሜሪካ በካሪቢያን ደሴት ህገወጥ የእፅ ዝውውርን ለመግታት በሚል ተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት ውጥረት ውስጥ ገብተዋል።
የቬንዙዌላ መንግስት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስላነሱት የድርድር ጉዳይ የሰጠው ምላሽ የለም ተብሏል። #thekoreaherald
@ThiqahETH
በዳርፉር እና ኮርዶፋ 57,000 የሚደርሱ ሱዳናውያን መፈናቀላቸው ተገለፀ።
የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ በሰሜን ሱዳን በኩል ባደረሰው አዲስ ጥቃት ብዛት ያላቸው ዜጎች ተፈናቅለዋል ሲል የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ቡድን አስታውቋል።
ድርጅቱ ሚሊሺያዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀማቸውን አመላክቷል።
ተፈናቃዮቹ አስቸጋሪ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ እንደሚገኙ ገልጿል። #aa
@ThiqahETH
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት ተነሱ።
ቦል ሜል ከማንኛውም የመንግስት እና የፖለቲካ ኃላፊነት እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ተገልጿል።
ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በፃፉት ደብዳቤ የተባረሩት ሜል፣ ፕሬዜዳንት ሳልቫኪርን አመስግነዋቸዋል ተብሏል።
የ52 አመቱ ቤንጃሚን በመኖሪያ ቤታቸው በነበሩበት ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም የአይን አማኞች ተናግረዋል።
እማኞቹ ቤንጃሚን ቦል ሜል ከኃላፊነት ከተነሱ ከሰዓታት በኋላ የግል ጥበቃዎቹ እንደተቀየሩና የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ዶክመንት ሲወስዱ እንዳዩ ተናግረዋል። #radiotamazuj
@ThiqahETH
"ኪሳራው የራሳቸው ነው" - ፕሬዜዳንት ራማፎዛ
ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ የቡድን 20 ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ ማሳወቋን አጣጣለች።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ "ዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲካን ማግለል መስራት አለመስራቱን ከማረጋገጥ በፊት ማሰብ ይኖርባታል" ብለዋል።
"ይህ በእኔ ልምድ አይሰራም" ያሉት ራማፎዛ "ኪሳራው የራሳቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንት ትራምፕ ከኖቬምበር 22 እስከ 23 ድረስ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ "የአሜሪካ ልዑካን አባላት አይሳተፉም" ብለዋል።
ምክንያት ያሉት ደግሞ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በነጭ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የንብረት ውድመት እየፈጸመ ነው በሚል ነው ተብሏል። #aljazeera
@ThiqahETH
"ብሩን አንበላውም፤ በመሬት መነገድ ይቁም" - ሰልፈኞች
የኮፕ 30 ጉባኤ በምታስተናግደው ብራዚል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።
በብዛት ከመሬት መብት ጋር የተያያዙ መፈክሮችን ይዘው የወጡት ተቃዋሚዎቹ፤ በቤሌም የሚገኘውንና የዘንድሮው የኮፕ 30 ጉባኤ እየተካሄደ የሚገኝበትን አዳራሽ አቃጥለዋል ተብሏል።
"መሬታችን አይሸጥም፣ የግብርና ንግድ የለም፣ ነዳጅ ማውጣት አይቻልም፣ ህገወጥ የማዕድን ዘረፋ ይቁም" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል። "ብሩን አንበላውም፤ በመሬት መነገድ ይቁም" ሲሉም ጠይቀዋል።
በዚህ ጉባኤ ላይ ከ200 ሀገራት በላይ የተወረጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ አለማቀፍ ልዑካን መገኘታቸው ተገልጿል።
ተቃውሞው የቆመው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ከተበተኑ በኋላ ነው ተብሏል።
የፀጥታ አካላት የስብሰባውን ታዳሚዎች ውስጥ እንዲቆዩ ካደረጉ በኋላ ተቃውሞው ሲበርድ አስወጥተዋቸዋል። #mailonline
@ThiqahETH
ቬንዙዌላ 200,000 ወታደሮችን በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አዘዘች።
ቬንዙዌላ ለወታደሮቿ ጥሪ እንድታቀርብ ያስገደዳት አሜሪካ የጦር አውሮፕላኖችን የጫነውን የዩኤስኤስ ጄራልድ ፎርድ መርከብ ወደ ካረቢያን ሀገራት ማስጠጋቷን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።
ውሳኔው በካሪቢያን ቀጠና የሰፈነው የጂዖ ፖለቲካ ውጥረት መሆኑን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቭላድሚር ፔድሮ ሎፔዝ ተናግረዋል።
ሎፔዝ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት በተላለፈ ንግግራቸው ተደጋጋሚ ወታደራዊ ልምምዶች እየተደረጉ እንደሚገኙ አብራርተዋል። #yenisafaq
@ThiqahETH
"በጦርነት ውስጥ ነው የምንገኘው" - ፓኪስታን
የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ በአጥፍቶ ጠፊ ለተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ተሊባንን ተጠያቂ አደረጉ።
ሚኒስትሩ በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ "ኢስላማባድ ላይ የደረሰው ጥቃት በመላ ሀገሪቱ የማንቂያ ደወል ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
አሲፍ አክለውም "በጦርነት ውስጥ ነው የምንገኘው" ያሉ ሲሆን፣ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደሆነ ግን በግልጽ አላብራሩም።
"በየቀኑ ዜጎቻችንን ለመጠበቅ መስዋዕት እየከፈልን ነው" ሲሉም አብራርተዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ከታሊባን ጋር የሚደረገውን ድርድር "ስህተት ነው" ብለውታል። #thetimes
@ThiqahETH
"መፈንቅለ መንግስት አልፈጸምንም፣ ፕሬዝዳንቱ ራሱ ነው ሀገር ጥሎ ለመውጣት የወሰነው" - ራጆሊናን የተኩት ፕሬዚዳንት
አዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ "መፈንቅለ መንግስት አልተፈጸመም" አሉ።
በኃይል ስልጣን የተቆጣጠሩት ኮሎኔል ሜኬል ራንድሪያኒራ በይፋ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
የማዳጋስካር የቀድሞው ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊናበቅርቡ ወጣቶች ባስነሱት አመፅ ከስልጣን ተወግደዋል።
ራጆሊናን የተኩት አዲሱ ፕሬዚዳንት በሰጡት ሀሳብ "ህዝቡ ተበድሎ ነበር፣ ጥያቄ ሲያነሳም ይገደል፣ ይታሰር ነበር ያ ዘመን ግን አብቅቷል" ብለዋል።
"ጦሩ ህዝቡንና ሀገሩን ነው የደገፈው፣ የርስበርስ ጦርነት አልፈለገም" በማለት የፀጥታ አካላት ህዝባዊ ተቃውሞውን መቀላቀላቸውን አስረድተዋል።
ፕሬዚደንቱ በዚሁ ንግግራቸው "መፈንቅለ መንግስት አልፈጸምንም፣ ፕሬዝዳንቱ ራሱ ነው ሀገር ጥሎ ለመውጣት የወሰነው" በማለት ገልጸዋል።
የመንግስት ለውጥ ባደረገው ተቃውሞ 22 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ቢያንስ 100 የሚሆኑ ቆስለዋል ተብሏል። #skynews
@ThiqahEth