thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

ኢራናዊቷ ኖቬል ተሸላሚ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ፋውንዴሽኗ ጠየቀ።

ኢራናዊቷ የኖቤል ተሸላሚ ናርገስ ሞሀመድ መታሰሯ ተነግሯል።

ናርገስ በአንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መታሰቢያ ላይ በተገኘችበት ወቅት በኢራን መንግስት በቁጥጥር ስር መዋሏን በስሟ የተቋቋመው ፋውንዴሽን አስታውቋል።

በማሻድ ከተማ በደህንነት ሰዎች መያዟን የገለጸው ፋውንዴሽኑ፣ ያለቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ጠይቋል።  #theindependent

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ኢጋድ በኤርትራ ውሳኔ ማዘኑን ገለጸ

ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (IGAD) እራሷን ማግለሏ እንዳሳዘነው የኢጋድ ሴክሬታሪያት አስታውቋል።

ኢጋድ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ፣ ኤርትራ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ራሷን ካገለለች በኋላ በ2023 በጅቡቲ በተካሄደው የተቋሙ 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ለቀጠናዊ አንድነትና ትብብር ድርጅቱን በድጋሚ ለመቀላቀል ያቀረበችውን ጥያቄ በአባል ሀገራቱ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ፣ "ኤርትራ ከ2023 ጀምሮ በተቋሙ  ስብሰባዎች፣ ፕሮግራሞች እና ተግባራት ተሳትፎ አልነበራትም" ሲል ገልጿል።

"ባለፉት ሁለት አመታት በትዕግስት እና በተስፋ መሻሻሎች" እንዲመጡ ሲጠባበቅ እንደነበረ በመግለጫው ጠቅሷል።

ኢጋድ አክሎ ኤርትራ፣ "ተቋሙ ሊያሻሽለው ይገባል" የምትለውን  ሃሳብ ባላቀረበችበትና ከዚያም ባለፈ "ድርጅቱን ለቃ እንድትወጣ ያደረጋትን ምክንያት በግልጽ ባላስቀመጠችበት ሁኔታ ማግለሏን በማሳወቋ ማዘኑን ያሳዝናል" በማለት የኤርትራ መንግስት ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው አሳስቧል።

አሁንም ቢሆን ከኤርትራ መንግስት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ኢጋድ ከኤርትራ መንግስት ጋር ንግግር እንደሚያደርግ ገልፆ፣ "ሀገሪቱ ድርጅቱን በድጋሚ በመቀላቀል በመተማመን እና በቀናነት ለጋራ አላማ፣ ለአካባቢው ለሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማት ለመስራት እንደሚያበረታታ" ገልጿል።

ኢጋድ "ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ቀጠናዊ ትብብርን ለመፍጠር፣ ውይይትን ለማዳበር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ" ሀላፊነቱን እንደሚወጣ በመግለጫው አመላክቷል። #igadsecretariat

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሂዝቦላ ከፍተኛ አመራሩ በእስራኤል ጥቃት መገደሉን ገለጸ።

ከሂዝቦላ አምስት ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ አንዱ የነበሩት ሀይታም አሊ ታባታቢ የተገደለው በመኖሪያ አፓርታማ ውስጥ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።

ታባታቢ የሂዝቦላ ዋና ፀሀፊ ናዒም ቃሲም ምክትል እንደነበር ቡድኑ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።

እስራኤል ትናንት ምሽት በቤሩት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅማለች ተብሏል።   #thenational

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የህፃናትን ማህበራዊ ደህንነት ለመጠበቅ የማህበራዊ ሚዲያ እንዲከፍቱ አይፈቀድላቸውም" - ማሌንዥያ

ማሌዥያ ከ16 አመት በታች የሚገኙ ህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ጣለች።

የማሌዥያ የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ፋህሚ የህፃናትን ማህበራዊ ደህንነት ለመጠበቅ የማህበራዊ ሚዲያ እንዲከፍቱ አይፈቀድላቸውም ብለዋል።

ሚኒስቴሩ አዲሱ የክልከላ ህግ ከ2026 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

ካሁን ቀደም የእድሜ ገደቡ 13 እንድሆን ተወስኖ እንደነበረ ያስታወሱት ፋሀሚ፣ የሀገሪቱ ካቢኔ ወደ 16 አመት ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።

ፋሀሚ ወላጆች ህፃናት ስክሪን ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንድገድቡና ሌሎች የመዝናኛ አማራጮችን እንድያመቻቹ አሳስበዋል። 
#thestraightstimes

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Ertalie

"አመዱ እንደ ድኝ የሚሸት እና ለመተንፈስ አስቸጋሪ ነው። ሌሎች ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል" - ዩኒቨርሲቲው

"ኤርታአሌ" የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ 4 ሰዓት ላይ በአፋር ክልል የተከሰተው ዛሬ ከቀኑ 4 ሰዓት መሆኑን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

ከእሳተ ገሞራው ውስጥ ሰማዩን የሸፍን አመድ እና አቧራ እየወጣ በአቅራቢያ ወደሚገኙት የአፍዴራ ከተማ እና በዙሪያ ያሉ ቀበሌዎች እየደረሰ ነው ብሏል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ መምህሩ ኖራ ያኒሚኦ እንዳሉት፣ አመዱ እንደ ድኝ የሚሸት እና ለመተንፈስ አስቸጋሪ ነው። ሌሎች ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ አፍን፣ አፍንጫን እና አይንን ለመሸፈን የሚያስችሉ የፊት ማስክና ሌሎች መከላከያዎችን በመልበስ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉ ገልጸዋል።

የተከሰተው ፍንዳታ ከፍተኛ መጠን ያለው በመሆኑ በአጎራባች ክልሎችና ከተሞች መሰማቱ ተነግሯል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#Arsi

"በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል፣ አራት ታግተው ተወስዋል" - የዞኑ ሀገረ ስብከት

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሚታና ሂኔሳ ቀበሌ በቀን ህዳር 12 ለ13 አጥቢያ 2018 ዓ/ም ሦስት ምዕመናን ተገድለዋል፤ አራት ታግተው ተውስደዋል" ሲል የዞኑ ሀገረ ስብከት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ለምትተዳደር ቲቃህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በ2018 ብቻ የታገቱትን ሳይጨምር የተገደሉ ምዕመናን ብቻ ብዛታቸው ወደ 40 መድረሱን ሀገረ ስብከቱ አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ በበኩሉ፣ ሦስቱ ተገድለው፣ ሌሎች ታገቱ መባሉ እውነት መሆኑን ነግሮናል።

የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት በበኩሉ በወረዳው ብቻ ባለፉት ሁለት አመታት ከ12ዐ በላይ ምዕመናን መገደላቸውን ገልጾልን ነበር።

በተያያዘ መረጃ፣ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከአዳማ ወደ አቦምሳ በመኪና እየተጓዙ መንገድ ላይ ታገቱ የተባሉ 31 ምዕመናን ያሉበት እንደማይታወቅ ቲቃህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያስረዳል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዜዳንት ዘለንስኪ "ዩክሬን የአሜሪካን ድጋፍ ልታጣ ትችላለች" ሲሉ ተናገሩ።

ፕሬዜዳንቱ ይህን ያሉት ትራምፕ 28 ነጥቦችን ያካተተ የሰላም እቅድ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

ዘለንስኪ ዩክሬን እቅዱን ካልተቀበለች የአሜሪካ ድጋፍ ሊቋረጥ የሚችልበት እድል እንዳለ ጠቁመዋል።

ትራምፕ በበኩላቸው፣ ዘለንስኪን የሰላም እቅዱን በመቀበላቸው አመስግነዋል።

የሩሲያ እና የዩክሬን ሰላም እንዲረጋገጥ ያግዛል ብለዋል ትራምፕ።   #scrippsnees

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አንድ የጋራ ነገር አለን፣ የሁላችንም የሆነችው ኒዮርክን እናሳድጋለን" ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በቅርቡ የኒዮርክ ከተማ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ በዋይትሐውስ የመጀመሪያ ውይይታቸውን አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለአዲሱ ከንቲባ መልካም ምኞታቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ሁለቱም ባለስልጣናት ውይይቱን "ውጤታማ" ሲሉ ገልጸውታል።

ትራምፕ "የከተማዋን ነዋሪዎች ህይወት የሚቀይሩ ስራዎች ይሰራሉ" ብለዋል።

"ትልቅ ውይይት ነበረን፣ አንድ የጋራ ነገር አለን፣ የሁላችንም የሆነችው ኒዮርክን እናሳድጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ማምዳኒ በበኩላቸው፣ "8.5 ሚሊዮን ህዝብ ህይወቱን ለማሻሻል እየታገሉ ነው" ብለዋል።

ከትራምፕ ጋር የተደረገው ውይይት የከተማዋን ችግር ለመቅረፍ እንደሚያግዝ አብራርተዋል። #theweek

@ThiqahET

Читать полностью…

THIQAH

ተመድ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተፈፀመውን የንጹሐን ግድያ አወገዘ።

89 ንጹሐን በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

ጥቃቱን ያደረሱት አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ (ADF) የተባሉት ታጣቂ ሀይሎች መሆናቸውን በስፍራው የተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ገልጿል።   #reuters

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ ባቀረቡት የዩክሬን የሰላም እቅድ ስምምነት የተካተቱ ተጨማሪ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?

-የአሜሪካ እና የሩሲያ የጋራ የፀጥታ ጉዳይ መርማሪ ቡድን ይቋቋማል። ሩሲያ ዩክሬን እና አውሮፓን ለመውረር ያወጣችውን እቅድ ትሰርዛለች።

-አሜሪካ እና ሩሲያ የኑክሌር መሳሪያ ማብላላት ፕሮግራም ስምምነትን ያራዝማሉ። ዩክሬን ኑክሌር አልባ ሀገር ለመሆን ትስማማለች።

-የዛፓሮዢያ የኑክሌር ጣቢያ በአለማቀፍ የኑክሌር ኢነርጂ አሶሴሽን (IAEA) ክትትል ይጀመራል፣ የኤሌክትሪክ ሀይል ክፍፍሉ ለሩሲያና ዩክሬን እኩል 50 ፡ 50 እንዲደርስ ይደረጋል።

-ሁለቱም ሀገራት የትምህርት ፕሮግራሞች መከባበርን የሚያበረታቱ፣ ባህልን የሚያጠናክሩ እና ዘረኝነትን የሚያጠፉ መሆን ይኖርባቸዋል።

-ክሪሚያ፣ ሉሃንስክ እና ዶኔትስክ የሩሲያ ግዛት ሁነው ይቀጥላሉ፤ ኬርሶን እና ዛፓሮዢያ በጊዚያዊነት ከሁለቱም ነፃ ሆነው ይቆያሉ።

-ሁለቱም ወገኖች ግዛቶችን ለመቀማትም ሆነ ለማስለቀቅ ወታደራዊ ሀይል አይጠቀሙም። ሩሲያ ዩክሬን ከዴኒፐር ወንዝ እንዳትጠቀም መከልከል አትችልም።

-ሁሉንም እስረኞችንና ህፃናት ለመለዋወጥ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ይቋቋማል። ዩክሬን በ100 ቀናት ውስጥ ምርጫ ታካሂዳለች። ሀገራቱ በጦርነቱ የተፈጠረውን ሁሉ በይቅርታ ይቋጫሉ፣ ወደፊትም አንዱ በአንዱ ላይ ውንጀላ አያቀርብም።

-ስምምነቱ በህግ አስገዳጅ ይሆናል፣ አፈፃፀሙ ትራምፕ በሚመሩት የሰላም ካውንስል ክትትል ይደረግበታል፣ ስምምነቱን የጣሰ አካል ማዕቀብ ይጣልበታል። ሁሉም ወገኖች ለዚህ ስምምነት ተገዢ ሲሆኑ፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መተግበር ይጀምራል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በተለይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ባሉ አካባቢዎች የግመል ስጋ በድብቅ አስገብተው የሚሸጡ" መኖራቸው ተጋለጠ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ-ወጥ የግመል እርድ መበራከቱንና ድርጊቱ ከወትሮው የተለየና አዲስ ፈተና እየሆነበት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አምኗል።

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ግመሎች ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ታርደው ለሽያጭ እየቀረቡ መሆኑን ገልጸው፣ "በተለይም ወደ ቦሌ ሚካኤል ባሉ አካባቢዎች የግመል ስጋ በድብቅ አስገብተው የሚሸጡ መኖራቸውን" አስረድተዋል።

ሕገ-ወጥ እርድ የሚፈጸመው አስፈላጊው ምርመራ ባልተካሄደበትና ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲሆን እንደሆነ፣ ይህ የህብረተሰቡን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ድርጅቱ ለማስተካከል እየሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

"ሕብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ ስጋ መውሰድ እንደሚፈልግ እናውቃለን" ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ ለዚህም ሲባል ማኅበረሰቡ ሕገ-ወጥ የግመል እርድን ሲመለከት ወዲያውኑ ጥቆማ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል።

ሕጋዊው የግመል እርድ በቄራዎች ድርጅት በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በስፋት እንደሚከናወንና፣ ስጋውን በስፋት ለሚጠቀሙት የሶማሌና የአፋር ህዝብ ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል።

የቄራዎች ድርጅት በአማካኝ በቀን ከ7 እስከ 10 የሚደርሱ ግመሎችን እርድ እንደሚያከናውን ጭምር ማወቁን የዘገበው #አሐዱሬዲዮ ነው።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለዩክሬን ጦርነት ባለ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ አቀረቡ።

ዶናልድ ትራምፕ የሰላም እቅዱን ለዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ልከውላቸዋል ተብሏል።

አዲሱ የሰላም እቅድ ዩክሬን የተወሰኑ ግዛቶችን አሳልፋ እንድትሰጥ የሚያስገድድ ሲሆን ከአውሮፓ ሀገራት ጠንካራ ትችት ማስተናገድ ጀምሯል ተብሏል።

በሰላም እቅዱ ዙሪያ ከሩሲያ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ እንደሌለ ተገልጿል።

ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአላስካ ከተገናኙ በኋላ ድጋሚ ለመገናኘት ባደረጉት ስምምነት መሰረት በሀንጋሪ ሊካሄድ የነበረው ውይይት ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል። #indiatoday

(ተጨማሪ አለን) 

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

የሕግ ታራሚዎች የርቀት ትምህርት ሊማሩ ነው!

"ሰርተፊኬቱ በኮሚሽኑ በእርምት ላይ የሚገኙ #ከ2ሺሕ በላይ የሕግ ታራሚዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል" - ኮሚሽኑ

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በርቀት ለማስተማር የሚያስችል ፈቃድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አግኝቻለሁ ብሏል።

የኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስመራ አብደታ እንዳሉት ፈቃዱ የተገኘው፦
-የጤና ችግር ላለባቸው፣
-በማረሚያ ቤት ሥራ እየሰሩ ለመማር ለሚፈልጉና ዕድሜያቸው ከፍ በማለቱ በክፍል ወስጥ ተቀምጠው መማር ለማይፈልጉ ታራሚዎችን በርቀት ለማስተማር ነው።

የርቀት ትምህርት ፈቃዱ በማረሚያ ቤት የሚሰጠውን የትምህርት ዕድል እንደሚያሰፋና ሰርተፊኬቱ በኮሚሽኑ በእርምት ላይ ባሉ ከ2 ሺሕ በላይ የሕግ ታራሚዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

-በድሬዳዋ፣
-በዝዋይና በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ማዕከል ያሉ የሕግ ታራሚዎች የርቀት ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር ተቀራርበው እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ጀርመን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዜጎቿ ከፊል የጉዞ እገዳ ጣለች።

የጀርመን ፌደራል የውጭ ቢሮ ጀርመናውያን "በጣም አስፈላጊ" ካልሆነ በስተቀር ከአዲስ አበባ ውጭ መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው ገልጿል።

ምክንያት ያለው ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ አለመሆኑን እና በቅርቡ የተከሰተውን የማርበርግ ወረርሽኝ እንደሆነ ተገልጿል።

በቢሮው መረጃ መሰረት ስድስት ክልሎች ማለትም ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ ክልል አሳሳቢ ችግሮች ያሉባቸው ተብለው ተለይተዋል ተብሏል።

ካናዳም በተመሳሳይ ከሶስት ቀን በፊት ባወጣችው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዜጎቿ ከአዲስአበባ ውጭ እንዳይጓዙ አሳስባለች። #AS

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#CenterlEthiopia

"የተመረዘ ምግብ የተመገቡ" አባት እና 6 ልጆቻቸው ሕይወታቸው አለፈ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ እራት ተመግበው በጠና ከታመሙ 8 የአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ አባትንና 6 ልጆቻቸውን ጨምሮ ሰባት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለው ተመስገን፣ በወረዳው መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ/ም ምሽት 1 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸውን ተናግረዋል።

የቤተሰብ አባላቱ ወደ ሆስፒታል ቢያደርሷቸውም የ5፣ የ7 እና የ17 ዓመት ታዳጊ ወንድማማቾቹ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸው አልፏል።

የቀሪዎቹን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም የ14 እና የ15 ዓመት ሴት እና ወንድ ታዳጊዎች 7 ቀን 2018 ዓ/ም ምሽት 11 ሰዓት አልፏል።

የአንድ ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ደግሞ፣ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም ጥዋት 2 ሰዓት ህይወቱ ሲያልፍ፣ የስድስቱ ሟች ልጆች አባት አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ/ም ሌሊት በሰመመን ውስጥ ሆኖ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ቀርቷል።

የባለቤቷንና የ6 ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችው ወይዘሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል በከፍተኛ የጥንቃቄ ክፍል ውስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

ምግቡ የተመረዘው በማንና እንዴት? የሚለውን እውነታ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ በተጀመረው ምርመራ፣ አስር ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል ፓሊስ አስታውቋል።

መረጃው የክልሉ ፓሊስ ነው።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ የተኩስ አቁም መደረጉን ቢገልጹም የታይላንድ እና ካምቦዲያ ጦርነት አለመቆሙ ተገለጸ።

የካምቦዲያ መንግስት "ታይላንድ ተዋጊ ጄቶችን ጨምሮ ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ ጥቃት እያደረሰች ነው" ብሏል።

ታይላንድ በበኩሏ የካምቦዲያ ጦር "አለማቀፍ ህግን ጥሷል" በማለት የአፀፋ እርምጃ እየወሰደች እንደምትገኝ ተገልጿል።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ትናንት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ ግጭቱን ለማቆም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የነበረ ቢሆን በሰዓታት ልዩነት ጥሰውታል ነው የተባለው። #asiaone

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ሲንጋፖር በአዲስአበባ ኤምባሲ ልትከፍት መሆኑ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን የምትከፍት ከሆነ በአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ እና ግብፅ በመቀጠል ሶስተኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እንደሚሆን ተገልጿል። #asiaone

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በናይጄሪያ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል 50 የሚደርሱት መለቀቃቸው ተገለጸ።

በናይጄሪያ ታጣቂዎች በአንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት በመግባት 12 መምህራን እና 303 ተማሪዎች ማገታቸውን  የናይጄሪያ ክርስቲያን አሶሴሽን (CAN) አስታውቋል።

ነገር ግን ከተያዙት 303 ተማሪዎች 50ዎቹ መለቀቃቸውን አሶሴሽኑ አረጋግጧል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት የታገቱትን መምህራን እና ተማሪዎች ለማስለቀቅ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። #aljazeera

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ ከእስር ሊያመልጡ ሲሉ ተያዙ።

ፕሬዚዳንት ጄር ቦልሴናሮ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ወንጀል የ27 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

በመኖሪያ ቤታቸው በቁም እስር የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ፣ ከቤታቸው ወጥተው ሊሄዱ ሲሉ መያዛቸው ተገልጿል።

የ70 አመቱ ቦልሴናሮ፣ በአርጀንቲና የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም አልተሳካላቸውም ተብሏል።

በ2022 በተካሄደው ምርጫ በሉላዳ ሲልቫ የተሰነፉት ቦልሴናሮ፣ ምርጫውን እንደማይቀበሉ ሲገልፁ ቆይተዋል።  #thekoreatimes

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የማይናማር "ጁንታ" 1600 የውጭ ሀገር አጭበርባሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።

እነዚህ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች በታይላንድ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ ሆነው በበይነ መረብ የታገዘ የማጭበርበር ወንጀል ሲሰሩ ነበር ብሏል።

ከተጠርጣሪዎቹ ጋር 2,893 ኮምፒውተሮች እና 21,750 ስልኮች መያዛቸው ተገልጿል።

የማይናማር ወታደራዊ አስተዳደር እንደገለጸው፣ ለተከታታይ አምስት ቀናት በተደረገ ዘመቻ ተይዘዋል።  #thestraightstimes

@ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በናይጄሪያ የታገቱት ተማሪዎች ቁጥራቸው ከ300 መብለጣቸው ተገለጸ።

በሰሜን ናይጄሪያ የቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የናይጄሪያ ክርስቲያን አሶሴሽን (CAN) አስታውቋል።

ከታገቱት ውስጥ 12 መምህራን እንደሚገኙበት አሶሴሽኑ ገልጿል።

ለእገታው እስካሁን ድረስ ሀላፊነት የወሰደ አካል የለም ብሏል። #itv

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ታጣቂዎች ከ200 በላይ ተማሪዎችና ሠራተኞችን ከትምህርት ቤት አግተው ወሰዱ፤ ፕሬዜዳንቱም የቡድን 20 ጉባዔ ተሳትፏቸውን ሰረዙ።

በማዕከላዊ ናይጀሪያ የናይጄሪያ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደገለጸው አርብ ማለዳ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት 215 ተማሪዎች እና 12 ሠራተኞችን ወስደዋል።

እገታው የተፈጸመው በኒጀር ግዛት ፓፓሪ በሚገኘው የቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ሲሆን፣ ባለሥልጣናቱ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ሁሉም አዳሪ ትምህርት ቤቶች በጊዜያዊነት እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።

የጅምላ እገታው በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው። ሰኞ ዕለት በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አዳሪ ትምህረት ቤት ከ20 በላይ ሴት ተማሪዎች ታግተው ተወስደዋል ተብሏል።

እንዲሁም፣ በክዋራ ግዛት የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስትያን የአምልኮ ሥነ ስርዓቱ በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ምዕመናን ሲገደሉ 38 ደግሞ ታግተው ተወስደዋል።

ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ እነዚህን የጸጥታ ጉዳዮች ለመፍታት በሚል በዚህ ሳምንት መጨረሻ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። #EthioFm #Bbc

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦
-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ፤
-ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
-ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ፤
-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ፤
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል፤ -ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው፤ -ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ፤
-ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል፤
-ከ22 አደባባይ/ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ፤
- ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ፤
-ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል፤
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ)፤
-ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት፤
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ፤
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ፤
-ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ፤
- ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር፤
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ፤
- ከሰንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት፤
-  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር፤
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት፤
-  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን፤ -ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን፤
-ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት ያሉት መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ዝግ ይሆናሉ።

N.B በመስመሮቹ ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#ለጥንቃቄ

በዓለም ዙሪያ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት ዘመቻ ተከፍቷል።

የሳይበር ጥቃት አላማው የዋትስአፕ አካውንቶችን በመጥለፍ ተጠቃሚው #WhatsApp ፕላትፎርም ላይ ያለውን እምነት ማሳጣት እንደሆነ #CTM360 የተባለው የሳይበር ደህንነት ምርት አቅራቢ ኩባንያ ጠቁሟል።

ይህ ዋትሳፕን ኢላማ አድርጎ የተከፈተው ዘመቻ “HackOnChatˮ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

እንዴት ይፈጸማል?
ተመሳስሎ የተሰራ ድረ-ገጽ በመፍጠርና የዋትሳፕ ገጽታን በመላበስ የሚፈጸም ማጭበርበር አጭበርባሪዎች ጥቃታቸውን የሚዘነዝሩበት መንገድ ነው።

የመረጃ መንታፊዎቹ ተጠቃሚው ወደ አካውንቱ ከፍቶ ሲገባ እንዳይጠራጠር ጉዳዩ አስቸኳይ እንደሆነ በማስመሰል ትኩረት የመበተን ታክቲክን ይጠቀማሉ።

“HackOnChatˮ የጥቃት ዘመቻ የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና ቴክኒኮችን የሚጠቀም ሲሆን አለምአቀፍ የዋትሳፕ ተጠቃሚዎችን ለማጥቃት በተለያዩ ቋንቋዎች ሀሰተኛ ገፆችን በመክፈት ተጽእኖውን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማሳደጉ ታውቋል። 

እንዴት እንከላከል?
ቢያንስ ዋትሳፕን ጭምሮ ሌሎች አካውንቶታችንን ከፍተን ስንገባ የምንገባበት ድረ-ገጽ ትክክለኛ ገጽ መሆኑን በማረጋገጥ ሊድርስብን የሚችልን ጥቃት ልንከላከል ይገባል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሃገራችን የዋትሳፕና የቴሌግራም አካውንቶች ጠለፋ እየተበራከተ ይገኛል። #INSA

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ትራምፕ ባቀረቡት የዩክሬን የሰላም እቅድ የተካተቱት የስምምነት ነጥቦች ምን ምን ይዘዋል?

-የዩክሬን ሉዓላዊነት የተረጋገጠ ይሆናል። በሩሲያ፣ ዩክሬን እና አውሮፓ መካከል ወረራ ያለመፈጸም ስምምነት ይፈጸማል።

-ሩሲያ የጎረቤት ሀገራትን እንደማትወር እና ኔቶ ከተጨማሪ መስፋፋት እንዲቆጠብ ይደረጋል።

-በሩሲያ እና በኔቶ መካከል አለማቀፍ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታትና መረጋጋትን ለመፍጠር፣ ትብብርን በማጠናከር ኢኮኖሚን ለማሳደግ በአሜሪካ የሚመራ ውይይት ይካሄዳል።

-ዩክሬን አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ታገኛለች። የዩክሬን ወታደሮች ቁጥር ከ600 ሺሕ እንዳይበልጥ ውስን ይሆናል። ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል ያላትን ፍላጎት ታስቀራለች። ኔቶም ዩክሬንን አባል ማድረግ አይችልም።

-ኔቶ ወታደሮቹን በዩክሬን ላለማስፈር ይስማማል። የአውሮፓ ተዋጊ ጀቶች በፖላንድ ብቻ እንድሰማሩ ይደረጋሉ።

-አሜሪካ ሀላፊነቱን በመውሰድ ዩክሬን ስምምነቱን ከጣሰች የተሰጣት የፀጥታ ዋስትና ይነሳል፣ ሩሲያም የተነሱላት ማዕቀቦች በድጋሚ ይመለሳሉ። ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል የመሆን መብት አላት፣ የአውሮፓ ገበያ ተጠቃሚ እንድትሆን የአጭር ጊዜ ማረጋገጫ ይሰጣታል፣ ጉዳዩ ከግምት ውስጥ ይገባል።

-ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት "ዩክሬን ዴቨሎፕመንት ፈንድ" የተባለ አለማቀፍ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል። ሩሲያ የተጣለባት ማዕቀብ በሂደት እየታየ ይነሳል፣ ወደ አለማቀፍ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ትመለሳለች።

-ሩሲያ እንዳይንቀሳቀስ የታገደባት 100 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ በዩክሬን ለኢንቨስትመንት ይውላል፣ የአውሮፓ ሀገራት ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር ለመልሶ ግንባታ ይመድባሉ።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

18 ዓመት?

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የ8 ዓመት ህፃን አስገድዶ የደፈሰው ግለሰብ ግለሰብ በ18 ዓመት እስራት መቀጣቱን ወረዳው አስታውቋል።

ተከሳሽ ግዳፍ ሲሳይ ደምሌ በወረዳው በተለምዶ ልዩ ቦታው 06 መንደፈራ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህዳር 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ የግል የ8 ዓመት ህጻንን አስገድዶ ደፍሯል።

የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ሪፖርት ተደርጎለት ጥቆማውን መሰረት በማድረግ አስፈላጊ የሆኑ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል የስራ ሂደት ልኳል።

የወረዳው ፍትህ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ዓቃቤ-ህግ ተጠርጣሪው የወንጀል ቅፅ አንቀጽ 627(1) ተላልፏል በማለት የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አካቶ በወረዳው ፍርድ ቤት ክሱን አቅርቧል።

ተከሳሹም ድርጊቱን መፈፀሙን እና ጥፋተኛ እንደሆነ አምኗል።

ፍ/ቤት ተከሳሹን ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት "ተከሳሹን ያርማል ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን ያስተምራን ያለውን የ18 አመት ፅኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል" ሲል የራያ ቆቦ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በማርበርግ በሽታ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም" ተባለ

አስከሬናቸው እንደማይታጠብና፣ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው እንደማፈጸም፣ ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል።

በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ፣ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ተገቢው ክትትልና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም።

እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፥ ህመሙ በንክኪ እንጅ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል።

ማርበርግ ከኮቪድ በበለጠ ህይወት የሚነጥቅ ነውም ተብሏል። እንደ ወረርሽኙ ክብደት የሞት ምጣኔው ከ24 እስከ 88 በመቶ ይደርሳል።

ይህን መረጃ ያገኘው ከጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በማርበርግ በሽታ ምንነት ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን በመጥቀስ የዘገበው #EthioFm ነው።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ከሦስት እህቶቿ ጋር በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ተወስዳ የነበረች ታዳጊ ከ10 አመት በኋላ ወደ ጋምቤላ መመለሷ ተገጸ።

አበንግ ኡቻላ የተባለችው ኢትዮጵያዊት በ2008 ዓ/ም በ10 ዓመቷ በጆር ወረዳ ኡቱዎል 02 ቀበሌ አቦሮ ሰፈር ከሦስት እህቶቿ ጋር በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ታፍና ተወስዳ ነበር።

በፒቦር ግዛት የእርዳታ እህል ለመውሰድ ባቀናችበት ወቅት የሙርሌ ጎሳ ግለሰብ አግኝታ የአኙዋ ማህበረሰብ ያሉበትን በመጠየቅ ከአኙዋ ተወላጅ ጋር በመገናኘት ወደ ጁባ እንድትሄድ ሁኔታዎችን አመቻቸላት።

ከጁባ ወደ ፑቻላ በማቅናት ከፑቻላ ወደ ጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በወረዳው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አማካኝነት ወደ ጋምቤላ ክልል ተመለሰች።

በታጣቂዎቹ ስለተወሰዱት ሦስት እህቶቿና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ስለመናገርና አለመናገሯ የተባለ ነገር የለም።

ከወላጅ አባቷና ከቤተሰብ ጋር የተቀላቀለች ሲሆን፣ 20 ዓመት ሆኗታል። የልጅቷ አባት አቶ ኡቻላ አኩዎር፣ በ2008 ዓ/ም በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች አራት ልጆቻቸው ታፍነው መወሰዳቸውን ጠቁመዋል ያለው የመረጃው ባለቤት የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

ታዳጊዋ እንደመታደል ሆኖ ተመለሰች እንጅ፣ ጋምቤላ ክልልን ጥሰው በሚገቡ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ታፍነው የሚወሰዱና "ለሽያጭ የሚቀርቡ" ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነው።

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በቬትናም በደረሰ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ የ41 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 9 ጠፍተዋል ተባለ።

በሀገሪቱ ሳምንቱን ሙሉ ሳያቋርጥ የጣለው ከባድ ዝናብ ያልታሰበ የጎርፍ አደጋ ማስከተሉ ተገልጿል።

በዚህ የጎርፍ አደጋ 52 ሺሕ ቤቶች ወድመዋል ተብሏል።

ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች የኤሌክትሪክ ሀይል እንደተቋረጠባቸው ተገልጿል።

ይህ አደጋ በቬትናም ታሪክ ከ1993 በኋላ የተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ ነው ተብሏል።   #bbc

@ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የፈረንሳይ ጦር አዛዥ ፈረንሳይ "መስዋዕትነት ለመክፈል" መዘጋጀት አለባት አሉ።

ጄነራል ፋቢየን ማንዶን የፈረንሳይ ከንቲባዎች ህዝባቸውን "ለወደፊቱ ግጭት" ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።

ማንዶን "ሞስኮን ለማስቆም" መዘጋጀት አለባት ሲሉ ተደምጠዋል።

"ሁሉም እውቀት አለን፣ የኢኮኖሚ እና ዲሞግራፊ ጥንካሬም አለን፣ ሞስኮ ተጨማሪ እድል ከመሞከሯ በፊት ማስቆም ግድ ይለናል" ብለዋል።

ጄነራሉ አክለውም "እኛ የጎደለን ራሳችንን ለመከላከል የሚበቃ የመንፈስ ጥንካሬ ነው" በማለት ተናግረዋል።

የጦር አዛዡ "ካልተዘጋጀን አደጋ ውስጥ ነን" ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። #brusselasignal

@ThiqahETH

Читать полностью…
Subscribe to a channel