thiqaheth | Unsorted

Telegram-канал thiqaheth - THIQAH

15262

ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Subscribe to a channel

THIQAH

አሜሪካ የተከሰተው ከበድ ያለ የበረዶ አውሎ ነፋስ ስላስከተለው ጉዳት ቁጥሮች ምን አሉ?

ቢያንስ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። ሞቱ የተከሰተው በሉዊዚያ፣ በቴነሲ እና በካንሳስ ግዛቶች ነው።

"ፈላይትአዌር" ያወጣው መረጃ ከ11 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል ይላል።

ከ800 ሺሕ በላይ ቤቶች ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል። ይህ እስከ ትናንት ያለ መረጃ ሲሆን፣ ያወጣውም የኤሌክትሪክ መቋረጥን የሚመዘግበው ድረ ገጽ (poweroutage.us) ነው።

አውሎ ነፋሱ በ180 ሚሊዮን አሜሪካውያን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ደቅኗል።

የከዚህ ቀደሙን ዘገባ እዚህ ያንብቡ፣ /channel/thiqahEth/5277

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በደቡብ ፊሊፒንስ አነስተኛ ጀልባ በመስጠሟ 15 ሰዎች ሲሞቱ 28 ጠፉ።

አደጋው የደረሰው ጀልባዋ ከባሲላን ወደ ሱሉ ግዛት እየተጓዘች በነበረበት ወቅት እንደሆነ የፊሊፒንስ የባህር ጠባቂዎች ማህበር (PCG) አስታውቋል።

በጀልባዋ ከ330 ተጓዦች እና 27 የጀልባዋ ሠራተኞች እንደነበሩ ገልጿል።

ማህበሩ 316 ተጓዦችን በህይወት ማዳን ተችሏል ብሏል።

የባሲላን ከተማ አስተዳደር የአደጋውን መንስኤ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።  #bbc

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የእስራኤል በጋዛ የመጨረሻውን ታጋች ለመመለስ "መጠነ ሰፊ ዘመቻ" መጀመሩን አስታወቀ።

ሃማስ በበኩሉ እስራኤል ታጋቹ በሚገኝበት አካባቢ  ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር የፍለጋ ሂደቱን አስተጓጉላለች ሲል ወንጅሏል።

የእስራኤል ጥቃት ማድረስ የተሰማው አሜሪካ እና ሌሎች አሸማጋይ ሀገራት ሁለተኛው ዙር የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲጀመር እየጠየቁ ባሉበት ወቅት ነው ተብሏል።

በፍልስጤም የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት በበኩሉ እስራኤል በተቆጣጠረቻቸው የፍልስጤም ግዛቶች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መቸገሩን ገልጿል። #france24

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ቅጥረኛ ተዋጊዎቹ ከኢትዮጵያ፣ ኮሎምቢያ፣ ቻድ እና ደቡብ ሱዳን የመጡ ናቸው" - ሱዳን

"በግድያ ወንጀል ስለተከሰሱ በእርግጠኝነት የሞት ፍርድ ነው የሚተላለፍባቸው"!

ሱዳን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ "በ122 የውጭ ቅጥረኛ" ባለቻቸው "ተዋጊዎች" ላይ ክስ መሰረተች ተባለ።

"ተዋጊዎቹ በሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) ወግነው የተሳተፉ" መሆናቸውን የሱዳን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ዳይሬክተር እንቲሳር አብዱልሙታር ተናግረዋል።

አብዱልሙታር፣ "ቅጥረኛ ተዋጊዎቹ ከኢትዮጵያ፣ ኮሎምቢያ፣ ቻድ እና ደቡብ ሱዳን የመጡ ናቸው" ሲሉ አብራርተዋል።

ዳይሬክተሯ፣ "በግድያ ወንጀል ስለተከሰሱ በእርግጠኝነት የሞት ፍርድ ነው የሚተላለፍባቸው" ብለዋል።

"ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ቀን ጀምሮ በሱዳን 188 ሺሕ 405 የወንጀል ክሶች ተመስርተዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

አብዱልሙታር በገለፃቸው፣ "135 ህፃናት በግዳጅ ተሰልፈው ሲዋጉ" ከተያዙ በኋላ ለቤተሰቦቻቸው ተላልፈው መሰጠታቸውን አብራርተዋል። #sudantribune

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ በ73 የበይነመረብ "አጭበርባሪ ዜጎቹ" ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣ።

73 ዜጎች በዚሁ "የማጭበርበር ወንጀል ተይዘው ከካምቦዲያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ተመልሰዋል" ተብሏል።

ፖሊስ "አጭበርባሪዎቹ 33.1 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት አድርሰዋል" ሲል ወንጅሏል።

ካምቦዲያ በነበሩበት ወቅት 229 የደቡብ ኮሪያ ዜጎችን በበይነ መረብ ማጭበርበራቸውን ጠቁሟል።   #yonhapnewsagency

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የመጀመሪያው የሦስትዮሽ ውይይት "ገንቢ ውይይት ነበር" ተባለ።

የሩሲያ ዩክሬን እና የአሜሪካ የመጀመሪያው የሦስትዮሽ ውይይት ተጠናቋል።

ለሁለት ቀናት የቆየው ይህ ድርድር በቀጣይ በአቡዳቢ ሌላ ዙር ውይይት ለማድረግ በስምምነት መጠናቀቁን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል።

ዊትኮፍ ሁለተኛው ዙር ውይይት በቀጣይ ሳምንት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

የሁለት ቀኑ ውይይት በየቀኑ አራት ሰዓታትን የወሰደ እንደነበር ተናግረዋል። #kyivpost

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"በዌስት ባንክ ጊዜ የማይሰጥ ረሃብ ተከስቷል" - ፍሊፕ ላዛርኒ

የፍልስጤም አንዱ ግዛት የሆነው ዌስት ባንክ አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ እያስተናገደ መሆኑ ተሰምቷል።

በፍልስጤም የተመድ ዕርዳታ ስራ ኤጀንሲ (UNRWA) ኃላፊ ፍሊፕ ላዛርኒ፣ "በዌስት ባንክ ጊዜ የማይሰጥ ረሃብ ተከስቷል" ብለዋል።

"ዌስት ባንክ ከ1967 በኋላ ከባድ አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ ተጋርጦበታል" ሲሉ ያጋጠመውን የአቅርቦት ችግር አስረድተዋል።

"33,000 ፍልስጤማውያን በሰሜን ዌስት ባንክ ከሚገኙ የስደተኞች ካምፕ ተፈናቅለዋል" ሲሉም ገልጸዋል።

እንደ ላዛርኒ ገለፃ የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ የፍልስጤም ነዋሪዎችን ማፈናቀል አላቆመም። #gulftimes

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በሱዳን የወርቅ ማዕድን ማውጫ በደረሰ አደጋ 6 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች ተጎዱ።

በደቡብ ኮርዶፋ በተከሰተው በዚህ አደጋ 12 ሰዎች መጎዳታቸው እና በደርዘን የሚቆጠሩ መጥፋታቸው ተገልጿል።

ለተጎጂዎች የህክምና እርዳታ መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን፣ መንግስት ለማዕድን አውጪዎች በቂ ስልጠና እና የደህንነት ዋስትና መስጠት አለበት ተብሏል።

በሀገሪቱ ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ በማዕድን ማውጣት ሙያ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንዳሉ፣ ነገር ግን 80% የሚሆኑት በቂ ስልጠና የሌላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። #trtworld

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የሶማሊያ ጦር "በ59 የአልሸባብ አባላት ላይ እርምጃ" መውሰዱን ገለጸ።

ጦሩ ለ24 ሰዓታት በቆየ ዘመቻ "42 የቡድኑ አባላት መቁሰላቸውን" እና "10 አልሸባብ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች" መያዙን አስታውቋል።

የሀገሪቱ ጦር "ወስጀዋለሁ" ባለው "ጠንካራ እርምጃ የኩዳይ ስትራቴጂክ ግዛት መልሶ መቆጣጠሩን" ገልጿል።

በዚህም ጦሩ ዘመቻውን ያከናወነው በሶማሊያ ከሚገኘው የአሜሪካ ጦር ጋር በመቀናጀት እንደሆነ አስታውቋል። #thenewarab

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ስደተኞች እየተያዙ ያሉት በስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ በገበያ ቦታዎች እና በመኖሪያ ቤታቸው መሆኑ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል" - ቮልከር ተርክ

ተመድአሜሪካ ስደተኞችን የምትይዝበትን መንገድ በብርቱ ተቃውሟል።

የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ፣ "የአሜሪካ ኢምግሬሽንና ጉምሩክ ኢንፎርስመንት (ICE) ስደተኞች የሚይዝበት መንገድ ሰብዓዊነት እንደመንፈግ ይታያል" ብለዋል።

ቮልከር በወቅታዊ የስደተኞች አያያዝ ላይ በሰጡት መግለጫ፣ "የህግ አግባብን ያልተከተለ፣ የቤተሰብ አንድነት የሚንድ እና መሰረታዊ የሰብዓዊ አያያዝ መርህን የጣሰ ነው" ሲሉ ተችተዋል።

"በአሜሪካ ሰነድ አልባ ስደተኞች በግድ መታደናቸው፣ መያዛቸው እና መታገታቸው አሳሳቢ ነው" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ "ስደተኞች እየተያዙ ያሉት በስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ በገበያ ቦታዎች እና በመኖሪያ ቤታቸው መሆኑ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል" ብለዋል።

የአሜሪካ ኢምግሬሽንና ጉምሩክ ኢንፎርስመንት (ICE) ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ የስደተኞች አያያዝን በሚቃወሙ ስደተኞች ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። #theauthiritynews

N.B አሜሪካ በሀገሯ የሚገኙ የየትኛውም ሀገር ሰነድ አልባ ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ካልወጡ እስራት በመፈጸም ጭምር በግዳጅ ለመባረር እንደምትገደድ መግለጿ ይታወሳል። ከ60 ቀናት በኋላም የማሳደድ ዘመቻው ተጀምሯል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አርማዳ የጦር መርከብ ወደ ኢራን እየተጓዘ ነው" - አሜሪካ

"ሁሉን ያቀፈ ጦርነት ይከሰታል። አሜሪካ የኢራንን ሉዓላዊነት ከጣሰች ምላሽ ለመስጠት እንገደዳለን" - ኢራን

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተቃዋሚዎች ግድያ እና በኑክሌር ፕሮግራም "ሰበብ" ወደ ኢራን የጦር መርከብ መላካቸውን ተከትሎ ኢራን አስጠነቀቀች።

ዶናልድ ትራምፕ "አርማዳ የጦር መርከብ ወደ ኢራን እየተጓዘ ነው፣ እንደማንጠቀመው ግን ተስፋ አለኝ" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ "ብዙ ሚሳዔል አውዳሚ መሳሪያዎች በቀጣይ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይላካሉ" ነው ያሉት።

"አስፈላጊ ከሆነ ብቻ ነው የምንጠቀማቸው ሁኔታውን በቅርበት እንከታተለዋለን" በማለት ገልጸዋል።

ስማቸው ያልተጠቀሰ የኢራን ከፍተኛ የጦር አመራር በበኩላቸው፣ "ይህ የጦር ክምችት ለውጊያ ነው ብለን አናስብም፣ ግን የኢራን ጦር ዝግጁ ነው" ብለዋል።

"በዚህ ሰዓት የሚቃጣ የትኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት የሚያስችል ቁመና አለን" ሲሉ አብራርተዋል።

"ሁሉን ያቀፈ ጦርነት ይከሰታል" በማለት ጦርነቱ ቀጠናዊ እንደሚሆን የገለጹት እኒሁ አመራር፣ "አሜሪካ የኢራንን ሉዓላዊነት ከጣሰች ምላሽ ለመስጠት እንገደዳለን" በማለት አስታውቀዋል። #skynews

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ትራምፕ አዲስ ተመድ ለመፍጠር እየሞከረ ነው" - ፕሬዚዳንት ሲልቫ

የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቋቋሙትን "የሰላም ቦርድ" (Peace Boared) አጥብቀው ተቃወሙ።

ሲልቫ፣ "ትራምፕ በብቸኝነት የሚቆጣጠሩት የሰላም ቦርድ ብዝሃነትን የሚያጠፋ አካሄድ ነው" በማለት ተችተዋል።

አክለው፣ "ዓለምን በትዊተር መምራት ነው የሚፈልጉት?" ሲሉ የጠየቁት ፕሬዚዳንቱ "ትራምፕ አዲስ ተመድ ለመፍጠር እየሞከረ ነው" በማለት አካሄዱን ተችተዋል።

ሲልቫ "እሱ (ትራምፕ) በየቀኑ መናገር ይወዳል ዓለም ስለእርሱ ማውራት ይጀምራል እየሆነ ያለው ይህ ነው" ሲሉም ትራምፕን ነቁረውታል።

"ተመድ ማሻሻል ያለበትን ጉዳይ ማሻሻል ይኖርበታል እንጂ ሁሉን ያካተተ ተቋም ንቆ በግለሰቦች የሚመራ ተቋም መገንባት አግባብነት የለም" ሲሉ ማለታቸውን አልጀዜራ ዘግቧል።

ትራምፕ በዳቮስ በተካሄደው የኢኮኖሚ ፎረም ወቅት ራሳቸውን "የቦርድ የመጀመሪያው የዕድሜ ልክ ሊቀመንበር" አድርገው የሾሙበት "የሰላም ቦርድ" ማቋቋማቸው ዘግበን ነበር።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ውይይቱ ዛሬ ሌሊት ላይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ ይካሄዳል"!

አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን የሦስትዮሽ ውይይት ሊያደርጉ መሆናቸው ተነግሯል።

ውይይቱ ዛሬ ሌሊት ላይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የሦስትዮሽ ውይይቱ በ2022 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ ነው።

በዚህ ድርድር ከአሜሪካ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፣ ከሩሲያ በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከሞስኮ በበይነ መረብ እና ተደራዳሪ ልዑካን በአካለሰ፣ ከዩክሬን ዘለንስኪ እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል።

ዘለንስኪ፣ ትራምፕ እና ፑቲን ከወራት በፊት በአላስካ በተወያዩበት ወቅት ድርድሩ ዩክሬንን እንዲያካትት ቢጠይቁም አልተሳካም ሲል የዘገበው ዩፒ ነው።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ለመጨረሻ ጊዜ ለተጨማሪ ለ15 ቀናት ተራዝሟል" - ቢሮው

አመታዊው የንግድ ፈቃድ እድሳት ያለቅጣት የሚታደስበት ጊዜ ካበቃበት ታህሳስ 30/2018 ዓ/ም ጀምሮ የማደሻ ጊዜው ለተጨማሪ 15 ቀናት ተራዝሞ እድሳት ሲከናወን ቆይቷል።

ይሁን እንጂ በተሰጠው ጊዜ እድሳታቸውን ያላጠናቀቁ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን እድሳት ማከናወን እንዲችሉ ለመጨረሻ ጊዜ ለተጨማሪ ለ15 ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሳውቋል።

"በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት ያለቅጣት የሚከናወንበት ጊዜ ጥር 30/2018 ዓም የሚያበቃ ይሆናል"ም ብሏል።

ለቀኑ መራዘም ምክንያት ነጋዴዎች የክሊራንስ አሰጣጥ ላይ መጓተቶች በመኖራቸው ክሊራንስ አለመጨረሳቸውን በመግለጽ ቅሬታ በማቅረባቸው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

አገልግሎት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በቀሩት ቀናት ንግድ ፈቃዳቸውን ያላሳደሱ ነጋዴዎች እንዲያሳድሱ ቢሮው ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የዝምባዋብዌ ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ተገደሉ።

በአምስት ሰዎች ላይ በተሰነዘረው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሦስት ልጆች መገደላቸውን በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የዝምባዋብዌ ኤምባሲ አስታውቋል።

ሟቾቹ አንዲት እህትና ሁለት ወንድማማቾች ናቸው ተብሏል።

የጄብስቪል ከተማ ፖሊስ የግድያ ኬዙን በመመዝገብ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።

ፖሊስ ጥቃቱ የተፈጸመው በእጥፍ ጠፊ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።   #bulawayo24news

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

#ቪዲዮስለየሰነድ አልባ ስደተኞች አያያዝ የመቃወም ጉዳይ፥ በሚኒያፖሊስ የነበረው ተቃውሞ ወደ ቺካጎ መስፋፋቱ ተገለጸ።

በአሜሪካ በሚኒያፖሊስ ከተማ የተፈጸመው ግዲያ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም ቁጣ መቀስቀሱ ተገልጿል።

ተቃዋሚዎቹ የኢሚግሬሽን ፖሊሶች በስደተኞች ላይ የሚወስዱትን ሀይል የተቀላቀለበት እርምጃ አጥብቀው ተቃውመዋል ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደርን ግትርነት የተሞላበት የስደተኞች አያያዝ የሚቃወመው ሰልፍ  ሶስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።

በሚኒያፖሊስ በተደረገው ሰልፍ ብቻ ከ50,000 በላይ ሰዎች መሳተፋቸው ተገልጿል። #novinite

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"አሜሪካ ወደ ሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ መላክ አለባት" - ደቡብ ኮሪያ

ሴዑል ከፒዮንግያንግ ጋር የገባችበትን ልዩነት ለመፍታት የዋሽንግተንን ጣልቃ ገብነት ጠየቀች።

የደቡብ ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚን ሶንግ ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ "ትራምፕ ብቻ ናቸው ግንኙነታችንን ሊያሻሽሉ የሚችሉትና ፍቃደኛ የሚሆኑት" ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አሜሪካ ወደ ሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ መላክ አለባት" ብለዋል።

ሶንግ፣ "በግልጽ ልነግርህ የምፈልገው ማንም ሰው በአሜሪካ በኩል ልዑክ ሁኖ ቢላክ ግንኙነታችን ይሻሻላል" ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ንግግር ከማሰማት ውጭ ለሶንግ ሀሳብ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ የለም ተብሏል። #nknews

(ሰሜን ኮሪያ የምትለው ካለ በዚህ ዘገባ ሀሳቧ ይካተታል።)

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

በ2025 የፓኪስታን የወጭ ንግድ 44% ቀነሰ።

ፓኪስታን ባለፈው አመት ከፍተኛ የንግድ ክፍተት እንዳጋጠማት የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ (SBP) ያወጣው ሪፖርት ያመላክታል።

የውጭ ገበያው የቀነሰው በዋናነት በዓመቱ  ሁለተኛው አጋማሽ መሆኑን የገለጸው ባንኩ ምክንያቱ ደግሞ "ከአፍጋኒስታን ጋር ተከስቶ የነበረው ጦርነት ነው" ብሏል።

ነገር ግን ፓኪስታን ከዘጠኝ ጎረቤት ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ከወጭ ምርት ገቢ ምርት እንደሚበልጥ ተገልጿል።  #gulftimes

@EyobTikuye  @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በቴክሳስ የተከሰተው አውሎንፋስ 160,000 የሚጠጉ ነዋሪዎችን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ አደረገ።

በከተማዋ የተከሰተው ይህ ከባድ አውሎንፋስ ከ4000 በላይ በረራዎችን ማስተጓጎሉም ተገልጿል።

ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የከተማ ነዋሪ በዚህ አደጋ ተጠቂ ሆኗል ተብሏል።

የአሜሪካ ኢነርጂ ዲፓርትመንት (USDE) የቴክሳስ አስተዳደር ጀነሬተር እንዲያሰራጭ አሳስቧል።

የአሜሪካ ብሄራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት (USNWS) በበኩሉ ያልተለመደ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በረዶ ያዘለ ክረምት እንደገባ አስታውቋል። #telegraph

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ካናዳ ከቻይና ጋር ስምምነት ከፈጸመች በ100% ታሪፍ ትቀጣለች" - ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ላይ የ100% ታሪፍ ሊጥሉ እንደሚችሉ  አስጠነቀቁ።

ታሪፍ ለመጣል የገፋፋቸው "ካናዳ ከቻይና ጋር ያደረገችው የንግድ ስምምነት ቅሬታ ስለፈጠረባቸው ነው" ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ፣ "ጠቅላይ ሚኒስትር ካርኔ ካናዳን ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሸቀጦች ማራገፊያ ካደረጋት ተሳስቷል" ብለዋል።

"ቻይና ካናዳን ትውጣታለች፣ የካናዳን ንግዶች ሙሉ በሙሉ ታጠፋቸዋለች" ሲሉ ተናግረዋል።

ትራምፕ አክለው፣ "ካናዳ ከቻይና ጋር ስምምነት ከፈጸመች በ100% ታሪፍ ትቀጣለች" በማለት አስጠንቅቀዋል።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ ከሶስት ሳምንት በፊት ወደ ቻይና አቅንተው ከፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ጋር "አዲስ ስትራቴጂካዊ ስምምነት ፈፅመናል" ሲሉ ገልፀዋል። #france24

@EyobTikuye   @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የሃይማኖት አባቶች በአየር መንገድ ተገኝተን ስደተኞች እንዳይመለሱ ለመማጸን ነው የመጣነው" - ቄስ ቶልጋርድ

"ፖሊስ በሚኒሶታ 100 የሚጠጉ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል" !

በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈፎች የስደተኞች አያያዝን በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

በሚኒሶታ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ ፉሮስ ቶልጋርድ፣ "ፖሊስ በሚኒሶታ 100 የሚጠጉ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል" ብለዋል።

"በከተማዋ 700 የሚደርሱ የንግድ ሱቆችና ትምህርት ቤቶች በአመፁ ምክንያት ተዘግተዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የሀይማኖት አባቶች በአየር መንገድ ተገኝተን ስደተኞች እንዳይመለሱ ለመማጸን ነው የመጣነው" በማለት ገልፀዋል።

"ሚኒሶታ አካባቢ የተፈጠረው ህሊና የማይፈቅደው ነገር ነው" ያሉት ቄስ ቶልጋርድ "በዚህ ሁኔታ መኖር ውስብስብ ችግር ፈጥሮብናል" ነው ያሉት።  

ቄስ ቶልጋርድ "ፖሊስ ወደመጣንበት እንድንመለስ ቢጠይቀንም እኛ ከስደተኞች ጎን መቆማችንን ለማሳየት እዚሁ ድምፃችንን እያሰማን ነው፣ ለውጥ ካላየን አንመለስም" ብለዋል።

የኢምግሬሽን እና ከስተም ኢንፎርስመንት (ICE) ፖሊስ የሁለት እና የአምስት አመት ህፃን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ስደተኞችን ይበልጥ ስጋት ላይ መደቀኑ ተገልጿል። #silive

@EyobTikuye   @ThiqahEth

Читать полностью…

THIQAH

በኢንዶኔዥያ በደረሰ የመሬት መንሸራተት 7 ሰዎች ሲሞቱ 82 ቆሰሉ።

በምዕራብ ጃቫ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ለመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ መሆኑን የኢንዶኔዥያ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ (IDMA) አስታውቋል።

ኤጀንሲው የጠፉትን ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል። #onmanorama

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የ75 አመቱ የቻይና ከፍተኛ የጦር ጀነራል በ"ግልጽ የዲሲፕሊን ጥሰት" ወንጀል ተጠርጥረው ታያዙ።

ቻይና በማዕከላዊ ጦር ኮሚሽን (CMC) የጦር ጄነራሏ ላይ የሙስና ወንጀል ምርመራ ጀምርመራ መጀመራ ታውቋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ጄነራል ዣንግ ዪዢያ፣ "ግልጽ የዲሲፕሊን ጥሰት" በመፈጸም ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።

የ75 አመቱ ጄነራል ዪዢያ ከጦር አመራርነታቸው ባለፈ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ (CCP) ሥራ አስፈፃሚ አባል መሆናቸው ተገልጿል።

ጄነራሉ በቅርቡ በፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ አማካኝነት የተጠራ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል ተብሏል።

ቻይና ባለፈው ጥቅምት ከዪዢያ በፊት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ጄነራል ዣንግ ሸንግሚንን በተመሳሳይ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ማዋሏ ይታወሳል።  #thestraightstimes

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የአውሮፓ ህብረት በግሪንላንድ ጉዳይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።

አስቸኳይ ስብሰባው የተጠራው ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንደሆነ ስማቸው ያልተገለጸ አምስት ዲፕሎማቶች ማረጋገጣቸው ታውቋል።

ህብረቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የታሪፍ እርምጃን ለመቀልበስ "ንግድን እንደ ጦር መሳሪያ ለመጠቀም ማቀዱ" ተገልጿል።

ትራምፕ ግሪንላንድን ለመቆጣጠር የያዙትን ውሳኔ ካልቀለበሱ ህብረቱ ምላሽ መስጠት ግዴታው እንደሆነ ያምናል ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ በውሳኔያቸው ላይ ተቃውሞ ባሰሙ ስምንት የአውሮፓ ሀገራት ላይ ሊጥሉት የነበረውን ታሪፍ ከኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ከተወያዩ በኋላ በጊዜያዊነት መተዋቸውን አስታውቀዋል ሲል ፓለቲኮ ዘግቧል።

ትራምፕ፣ ግሪንላንድን "የአሜሪካ አካል" የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ለዴንማርክ አቻቸው ሜቴ ፍሬድሪክሰን በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ አሜሪካና ግሪንላንድ ብርቱ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተዋል።

በአውሮፓ ፓርላማ የዴንማርክ ተወካይ አንደር ቪስትሰን "ግሪላንድ ለሽያጭ የቀረበች አይደለችም" ሲሉ የትራምፕን ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸውም አይዘነጋም።

ትራምፕ ሰሞኑን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን ለመታደም ወደ ስዊዘርላንድ ባቀኑበት ወቅትም "ትራምፕ እንኳን ደኀና መጡ መባል የለባቸውም" የሚል ተቃውሞ ከዙሪክ ከተማ ሰልፈኞች እንደገጠማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የአውሮፓ ህብረት ለዚሁ ጉዳይ ስብሰባ የሰጠራ ሲሆን፣ ስብሰባው ከተካሄደ ውጤቱን በመከታተል ቲቃህ መረጃ ያቀርባል።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

የመካከለኛው ምሥራቅ የፓለቲካ ውጥረት ተከትሎ በዋናነት የተቋረጡ በረራዎች መካከል ተከታዮቹ ተጠቃሽ ናቸው።

ስዊዝ አየር መንገድ (Swiss Airlines) በረራ ካቋረጡት አንዱ ነው። ወደ እስራኤል የሚደረጉ በረራዎችንም ሰርዟቸዋል።

የሆላንድ አየር መንገድ የሆነው KLM ሌላኛው ነው። በዚህም
-ወደሳዑዲ አረቢያ፣
-የተባበሩት አረብ ኢምሬስት
-እስራኤል የሚደረጉ በረራዎችን ሰርዟል።

ብሪቲሽ ኤርዌይስ (British Airways) በረራውን ሰርዟል። የሰረዘውም ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚደረጉ ጉዞዎችን ነው።

ኤር ፍራንስ (Air France) አየር መንገድም በተመሳሳይ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚያደረጉ በረራዎችን አቋርጧል።

ዩናይትድ አየር መንገድ (United Airlines) እና ኤር ካናዳ (Air Canada) በበኩላቸው፥ ወደ እስራኤል እና መካከለኛው ምስራቅ የሚያደጉ በረራዎችን አቋርጠዋቸል።

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ትልልቅ አየር መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርጉትን በረራ ለሳምንት አቆሙ።

ኤርፍራንስ፣ ብሪቲሽ ኤርዌይስ፣ እና ሉፍታንዛ አየር መንገዶች በረራ ለማቆም ከወሰኑት መካከል ይገኙበታል።

አየር መንገዶቹ በረራዎችን ያቆሙት በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በአዲስ መልኩ ውጥረት መንገሱን ተከትሎ አሜሪካ ጥቃት ልትፈጸሸም ትችላለች በሚል የደህንነት ስጋት እንደሆነ ተገልጿል።

በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በበረራው መሰረዝ ምክንያት ተስተጓጉለዋል።

የአየር መንገዶቹ በረራ ማቆም ውሳኔ ለአንድ ሳምንት ፀንቶ እንደሚቆይ ተገልጿል።   #airlive

@EyobTikuye @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የኔቶ ወታደሮች በአፍጋኒስታን ጦርነት ብዙ አልተዋጉም" - ፕሬዚዳንት ትራምፕ

"ስድብ ነው፣ ትራምፕ ይቅርታ ይጠይቅ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር

የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኔቶ በአፍጋኒስታን  ጦርነት ሚና አልነበረውም ማለታቸውን ተቃወሙ።

ትራምፕ "የኔቶ ወታደሮች በአፍጋኒስታን ጦርነት ብዙ አልተዋጉም" ሲሉ አጣጥለዋል። "በጥቂት ግንባሮች ብቻ ነው የተሳተፉት" ነው ያሏቸው።

ለዚህ ስታርመር በሰጡት ምላሽ፣ "ተሳስቼ ከሆነ ይቅርታ፣ ግን የተሰራውን አለማድነቅ ክህደት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በለንደን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ "ስድብ ነው፣ ትራምፕ ይቅርታ ይጠይቅ" በማለት አሳስበዋል።

"ብሪታኒያ ብቻ 457 ወታደሮቿን አጥታለች" ሲሉም ሀገራቸው የነበራትን አስተዋጽኦ አስታውሰዋል።

ኔቶ በ2001 በአሜሪካ የደረሰውን የ9/11 የሽብር ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ መራሹን ዘመቻ በመቀላቀል ከታሊባን ጋር ተዋግቷል። #aa

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"የ3 አመት ህፃን በቢላዋ ቆራርጣ የገደለች ግለሰብ በሞት እንድትቀጣ" ተወሰነባት።

ተከሳሽ ሰንበቴ ታደሰ ግንቦት 27/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት በኮቸሬ ወረዳ ሽፎ ቀበሌ ኤጀርሳ ህዋስ በተሸኘ ቦታ ነው ለመስማት የሚሰቀጥጥ ወንጀሉን የፈጸመችው።

"ምንም የማታውቅ የ3 ዓመት ህፃን በቆጮ መቁረጫ ቢላዋ (ወርሜ) አንገቷን፣ የቀኝ እጇን ሶስት ጣቶች ቆርጣ የደም ቱቦዎች በመቆረጣቸው ደም በመፍሰሱ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጋለች" ተብሏል።

ተከሳሿ እራስዋን የማትከላከለውን ጨቅላ ህፃን በተለየ ጭካኔና ነውረኛነት አንገቷን ቆርጣ የገደለቻት በመሆኗ በ1997 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1 (ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸመችው ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳለች።

ግን፣ ተከሳሷ "ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም" ስትል ክዳ በመከራከሯ ችሎቱ ዐ/ህግ ምስክሮች ቀርበው እንዲያስረዱ በማዘዙ ለሐምሌ 21/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ሦስት ምስክሮች ወንጀሉን ስለመፈጸሟ መመስከራቸውን ዐ/ህግ ሰምቷል።

የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም፣ ጥር 15/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በተከሳሿ ላይ የሞት ፍርድ ፈርዷል። መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው።

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

"ህገወጥ አሰራር እየተፈፀመ ነው" - ሶማሊያዊቷ ኢልሃን ኦማር

የአሜሪካ ኤሚግሬሽን ቢሮ (ICE) የ5 አመት ህፃን መያዙ ቅሬታ አስነሳበት።

ይህ ህፃን የተያዘው በሚኒሶታ ግዛት ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል ተብሏል።

ከኢኳዶር ቤተሰቦች የተወለደው ሊያም ራሞስ አባቱ ሰነድ አልባ ስደተኛ በመሆኑ ከአባቱ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ቢሮው አስታውቋል።

ይህ ድርጊት ብዙዎቹን እያስቆጣ ሲሆን፣ በሚኒሶታ የዲሞክራት ፓርቲ ተወካይ ሶማሊያዊቷ ኢልሃን ኦማር "ህገወጥ አሰራር እየተፈፀመ ነው" በማለት ድርጊቱን አውግዛለች። #aa

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…

THIQAH

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቋቋሙት "የሰላም ቦርድ" ማነው?

ዶናልድ ትራምፕ በዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ዓለምን የሚያነጋግር አዲስ ዓለም አቀፍ ተቋም መስርተዋል።

"የሰላም ቦርድ (Board of Peace)" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ተቋም ከጋዛ መልሶ ግንባታ ጀምሮ እስከ ዓለምአቀፍ ግጭቶችን "ለመፍታት ትልቅ ሚና ይኖረዋል" ተብሏል።

በዚህም፦

- የዕድሜ ልክ ሊቀመንበር፦ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቦርዱ የመጀመሪያው የዕድሜ ልክ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል። 

- የመግቢያ ዋጋ፦ አንድ አገር በቦርዱ ውስጥ "ቋሚ አባል" ለመሆን ለጋዛ መልሶ ግንባታ የሚውል አንድ ቢሊዮን ዶላር መክፈል ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን በየሦስት ዓመቱ የሚቀያየር ተራ አባል ይሆናሉ።

- ተልዕኮ፦ ቦርዱ በዋናነት በጦርነት የወደመችውን ጋዛን መልሶ የመገንባት እና የገንዘብ ድጋፉን የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም ወደፊት የሚፈጠሩ ሌሎች ዓለም አቅፍ ግጭቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ በቻርተሩ ተደንግጓል።

- ቦርዱን የተቀላቀሉ አባል ሀገራት፦  እስካሁን ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ኳታር እና አርጀንቲናን ጨምሮ ከ20 በላይ አገራት ቻርተሩን ፈርመዋል። ክፍያ ፈጽመው ቋሚ አባል የሆኑት እስካሁን በዝርዝር አልታወቁም።

በሌላ በኩል እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ ያሉ አገራት ከመቀላቀል ተቆጥበዋል። ዋነኛ ምክንያታቸው ደግሞ ትራምፕ በግሪንላንድ ላይ የያዙትን አቋም "በመቃወም ነው" ተብሏል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የጂዖፖለቲካ ባለሙያዎች "ይህ የሰላም ቦርድ የተባበሩት መንግሥታትን (UN) ሚና ለመተካት የመጣ ነው"በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛል። #financialexpress #msn #cbcnews

@EyobTikuye  @ThiqahETH

Читать полностью…
Subscribe to a channel