15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
በኮርዶፋ ከ1,300 በላይ ዜጎች ያልተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደገጠማቸው ተገለጸ።
የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) ከፍተኛ የጤና ቀውስ መከሰቱን ጠቅሶ፣ አስቸኳይ የሰብዓዊ ቀውስ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
ጥምረቱ ደቡብ ኮርዶፋ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በመያዙ የምግብ እና የህክምና አቅርቦት ለማድረስ አለመቻሉን አስታውቋል።
የሱዳን ዶክተሮች ጥምረት (SDN) ይህን ሪፖርት ይፋ ያደረገው የሱዳን ጦር ከተማዋን በድጋሚ መቆጣጠሩን ከገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ ነው ተብሏል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahEth
ቬትናም እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ ስምምነት ፈጸሙ።
የቬትናም ፕሬዚዳንት ሎንግ ኩዎንግ ከአውሮፓ ካውንስል ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ወገኖች በአለማቀፍ ህግ ላይ የተመሰረተ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር መስማማታቸው ተገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት እና ቬትናም የአለም ኢኮኖሚ በአሜሪካ የታሪፍ ህግ እየተጎዳ ባለበት ወቅት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ወደ ሀኖይ ማቅናታቸው የተሰማው የአውሮፓ ህብረት ባሳለፍነው ማክሰኞ ከህንድ ጋር የንግድ ስምምነት ባደረገ ማግስት ነው። #associatedpress
@EyobTikuye @ThiqahETH
"አሜሪካ በቬኔዙዌላ ተጨማሪ ኃይል መጠቀም አትፈልግም" - ሩቢዮ
ዋሽንግተን ካሁን በኋላ በካራካስ ላይ ጫና ማሳደር እንደማትፈልግ ገለጸች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ፣ "የቬኔዙዌላ አዲስ አስተዳደር ከዋሽንግተን ጋር በቅርበት እየሰራ ነው" ብለዋል።
"አሜሪካ በቬኔዙዌላ ተጨማሪ ኃይል መጠቀም አትፈልግም" ሲሉም ተናግረዋል።
"በቬኔዙዌላ የምታዩት ወታደሮቻችንን ሳይሆን የባህር ጠባቂዎቻችንን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ማርክ ሩቢዮ "ከቬንዙዌላ መሪዎች ጋር ያለን ግንኙነት በጣም በመከባበር ላይ የተመሠረተ እና ውጤታማ ነው" ብለዋል።
በካራካስ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከ2019 ጀምሮ መዘጋቱን አስታውሰው በቅርቡ ለመክፈት ዲፕሎማቶች መላካቸውን ጠቁመዋል። #asiaone
@EyobTikuye @ThiqahEth
በኮሎምቢያ አውሮፕላን ተከስክሶ ባለስጣናትን ጨምሮ የ15 ሰዎች ተቀጠፈ።
በኮሎምቢያ በአውሮፕላን የመከስከስ አደጋ የህግ ባለሙያዎችን፣ የምክር ቤት ተወካይን ጨምሮ ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።
የኮሎምቢያ የትራንስፖርት ሚኒስትር በሰጡት የሀዘን መግለጫ እንዳሉት ከሆነ፣ ከባለሥልጣናቱ በህይወት የተረፈ የለም።
በረራ ላይ የነበረው አውሮፕላኑ የመከስከስ አደጋ ያጋጠመው በሰሜን ምሥራቅ ኮሎምቢያ በቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ ሲሆን፣ ፓለቲከኞችን አሳፍሮ ነበር።
በአደጋው፣ የኮንግረንስ ምርጫ እጩ ካርሎስ ሳልሴዶ፣ የኮሎምቢያ የተወካዮች ምክር ቤት የካታቱምቦ ክልል ተወካይ ዲዮጀነስ ኩንቴሮ ህይወታቸው አልፏል።
የአደጋውን መንስኤ በተመለከተ ከባለስልጣናቱ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ ባይኖርም፣ አደጋው ከመከሰቱ ቀድሞ ግን የአውሮፕላኑ የድንገተኛ አደጋ መብራት እየሰራ እንዳልነበር ተጠቁሟል። #Reuters
@EyobTikuye @ThiqahETH
የኮንግረስ አባል ኢልሃን ኦማር ላይ ጥቃት የፈጸመው አንቶኒ ካዝሚርዛክ እስር ቤት ገባ።
የአሜሪካ ህግ አውጭ በኢልሃን ኦማር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን፣ ጥቃት ፈጻሚው እስር ቤት ገብቶ ክስ ተመስርቶበታል።
የህግ አውጭዎቹ ድርጊቱን ያዘገዙት፣ ከጥላቻ ዘመቻ ጋር በማያያዝ ነው። ታዋቂው የአሜሪካ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ፣ "አሳፋሪ ነው፣ ትራምፕ ድርጊቱን ከማውገዝ ይልቅ ለፖለቲካው እየተጠቀመበት ነው" ብለዋል።
የሚኒሶታ ተወካይ ኬሊ ማሪሶን፣ "ትራምፕ ጥላቻን ለማስፋፋት እንደ እድል ተመልክቶታል" ሲሉ ገልጸዋል።
የሰሜን ካሮላይና ኮንግረስማን ቫለሪ ፉሼ "የፖለቲካ አመጽ በሀገራችን ቦታ የለውም" በማለት አውግዘዋል።
አንቶኒ ካዝሚርዛክ የአፕል ፈሳሽ ከረጫት በኋላ በፖሊስ ተይዞ በሀኒፐን ካውንቲ እስርቤት እንደገባ ተገልጿል።
የ55 አመቱ ካዝሚርዛክ የኮንግረስ አባል በሆነችው ኢልሃን ላይ ጥቃት በመፈጸም ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል ተብሏል። #rollcall
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ኢራን ወደ ድርድር ትመጣለች አልያ የሚመጣውን ትቀበላለች" - ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን አስጠነቀቁ።
በሎዋ ከተማ በተደረገ ሰልፍ ንግግር ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ "በነገራችን ላይ ሌላ ቆንጆ የአሜሪካ አርማዳ ወደ ኢራን በፍጥነት እየተጓዘ ነው" ብለዋል።
"ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሂደት ላይ ቢሆኑም የአሜሪካ ባህር ሀይል በቀጠናው ግጭት እንዳይከሰት በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው" በማለት ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው "ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛ ትመጣለች አልያ የሚመጣውን ትቀበላለች" ነው ያሉት።
አሜሪካ ከቀናት በፊት ዩኤስኤስ አብረሃም ሊንከን የጦር መርከብ ወደ ምዕራብ እስያ ልካለች። #telegraph
@EyobTikuye @ThiqahEth
ስፔን 500 ሺሕ ስደተኞችን ህጋዊ አደረገች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ "ባለፉት ስድስት አመታት ስደተኞች ለስፔን የኢኮኖሚ እድገት 80% ሚና አላቸው" ብለዋል።
የስፔን ኢሚግሬሽን ሚኒስትር ኢልማ ሴይዝ "ስደተኞች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በየትኛውም ዘርፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ" ብለዋል።
"ከሰብዓዊ መብት ህጎች ጋር የተናበበ ለኢኮኖሚ እድገት እና ማህበራዊ ትስስር የሚረዳ የስደተኞች አያያዝን አጠናክረናል" ሲሉም ገልጸዋል።
በአዲሱ የስፔን አሰራር ተጠቃሚ የሚሆኑት ስደተኞች ቢያንስ አምስት ወራት የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል።
ነገር ግን ባለፈው አመት 2025 ወደ ስፔን የገቡት ስደተኞች ቁጥር ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር 40% ቀንሷል ተብሏል።
ስፔን ከ500 ሺሕ በላይ ስደተኞችን ህጋዊ ማድረጓ ጥብቅ ከሆነው የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ፖሊሲ ጋር የሚቃረን ነው ተብሏል።
አብዛኞቹ ከላቲን አሜሪካ የመጡ ናቸው የተባሉት የስፔን ስደተኞች በ2025 መግቢያ ላይ 840 ሺሕ ሰነድ አልባ ስደተኞች እንደተመዘገቡ የኢሚግሬሽን ሚኒስትሯ ኢልማ ሴይዝ ገልጸዋል።
49.4 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ስፔን ከጠቅላላው ህዝቧ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ዜጎች መሆናቸውን ሴይዝ ጠቁመዋል። #aw
@EyobTikuye @ThiqahETH
በህንድ የግል ጄት ተከስክሶ ባለስጣኑን ጨምሮ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ከሟቾቹ ውስጥ የማሃርሻትራ ምክትል ሚኒስትር አጃት ፓወር እንደሚገኙበት ተገልጿል።
የህንድ አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ (AAIB) የተከሰከሰው የግል ጄት 14 አመት ማስቆጠሩን አስታውቋል።
ጄቱ ከቪሳካፓቱናም ወደ ሙምባይ እየበረረ በነበረበት ወቅት አደጋው መከሰቱንም አስታውቋል።
የአደጋው መንስዔ አለመታወቁን ያመላከተው የምርመራ ቢሮው ምክንያቱን ለማወቅ ገና በምርመራ ላይ መሆኑን ገልጿል። #theindianexpress
@EyobTikuye @ThiqahETH
ቢያንስ 12 ዩክሬናውያን ተገደሉ።
ግድያው የተፈጸመው በሩሲያ ባደረሰችው ጥቃት መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው በባቡር ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በባቡሩ ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ባሻገር በኦዴሳ ግዛት በደረሰ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል።
በዚህ ጥቃት ከደረሰው የሰብዓዊ ጉዳት ባሻገር በሀይል መሰረተ ልማት ላይ ከባድ ውድመት መድረሱን የግዛቲቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል። #outlookindia
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ለዩክሬን የደህንነት ዋስትና ለመስጠት ቃል አልገባንም" - አሜሪካ
ዋሽንግተን ለኪቭ የደህንነት ዋስትና ትሰጣለች መባሉን አስተባበለች።
የዋይትሐውስ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አና ኬሊ፣ "የተሳሳተ የሚዲያ ዘገባ ነው፤ የሰላም ድርድሩን ይጎዳል" ብለዋል።
"የአሜሪካ ሚና ድርድር ማመቻቸት ነው" ያሉት ኬሊ፣ "የደህንነት ዋስትና በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ የተመረኮዘ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ፣ "የአሜሪካ የደህንነት ዋስትና ተጠናቆ ለመፈረም ዝግጁ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም በሰጡት አስተያየት፣ "የደህንነት ዋስትና መስጠቱን ገና እያሰብንበት ነው" ማለታቸው ይታወሳል። #financialtimes #kyivpost
@EyobTikuye @ThiqahETH
ሶማሊያ የአልሸባብ የገንዘብ ኃላፊ አብዱላሂ ኮሶብሌ "መገደሉን" አስታወቀች።
የሶማሊያ ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ (NISA) ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር በታችኛው ሸበሌ "እርምጃ መውሰዱን" ገልጿል።
ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ፣ "የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው መገደል የአልሸባብን የገንዘብ ምንጭ ያደርቀዋል" ብሏል።
ኮሶብሌ በኩንየ ባሮ ክልል የገለጸው ኤጀንሲው፣ "ከንጹሐን ሶማሊያውያን ገንዘብ ሲመዘብር ቆይቷል" ሲል ወንጅሏል።
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት "አልሸባብ" ላለፉት 16 አመታት የሶማሊያን መንግስት ለመጣልና የራሱን ስርዓት ለመመስረት ሲታገል ቆይቷል።
በአንፃሩ በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የሰላም ተልዕኮ (AUSSOM) እስከ ታህሳስ 2026 ድረስ እንዲቆይ መወሰኑ ይታወቃል። #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
ሰሜን ኮሪያ ሁለት አጭር የባለስቲክ ሚሳዔል አስወነጨፈች።
ሚሳዔሎቹ በጃፓን ባህር ላይ ማረፋቸውን የጃፖን እና ደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት በግልጽ አሳውቀዋል።
ፒዮንግያንግ ሚሳዔል ያስወነጨፈችው የአሜሪካ መከላከያ ፖሊሲ (USDP) ዋና ፀሐፊ ኤልብሪጅ ኮልቢ ሰኞ'ለት በደቡብ ኮሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረጋቸው እና ዛሬ ወደ ጃፓን ማቅናታቸው በተሰማበት ወቅት ነው።
ሴዑል የፒዮንግያንግ እርምጃ የተመድን መመሪያ የሚጥስ እንደሆነ ገልጻለች። ቶኪዮ ደግሞ የጃፓንን ህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል አሳውቃለች።
የደቡብ ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚን ሶንግ ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ "ትራምፕ ብቻ ናቸው ግንኙነታችንን ሊያሻሽሉ የሚችሉትና ፍቃደኛ የሚሆኑት" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አሜሪካ ወደ ሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ መላክ አለባት" ሲሉ ተናግረዋል። #militarty
N.B፥ በኮሪያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከ1950 እስከ1953 የተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት በሰላም ስምምነት አለመቋጨቱን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ላለፉት 70 አመታት መፍትሄ አልባ ሆኖ ዘልቋል።
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ዋሽንግተን በቬኔዙዌላ ፖለቲከኞች ላይ የምታደርሰው ጫና ይብቃ" - ፕሬዚዳንት ሮድሪጌዝ
የቬኔዙዌላ የሽግግር ጊዜ ፕሬዚዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ በአሜሪካ የሚደርስባቸውን ጫና መብዛቱን ተናገሩ።
ሮድሪጌዝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቷ ከነዳጅ ሰራተኞች ጋር በነበራቸው ውይይት "ዋሽንግተን በቬኔዙዌላ ፖለቲከኞች ላይ የምታደርሰው ጫና ይብቃ" ሲሉ ተደምጠዋል።
በፖርቶ ላክሩዝ ከተማ በተደረገው በዚህ ውይይት "የቬኔዙዌላ ፖለቲከኞች ልዩነታችንን እና የውስጥ ግጭታችንን እናስወግድ" ብለዋል።
"ይህ መንግስት ፋሽስታዊነት እና ፅንፈኝነትን ሲታገል ቆይቷል" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ሮድሪጌዝ ከአሜሪካ ጋር በትብብር ትሰራለች ካልሆነ መጨረሻዋ እንደ ማድሮ ይሆናል" ማለታቸው ይታወቃል።
የቬኔዙዌላ ፕሬዚዳንት ማድሮ በአሜሪካ መንግስት ወታደሮች ከሀገራቸው ተገደው መወሰዳቸው ይዘነጋም። #Cnn
@EyobTikuye @ThiqahETH
"አውሮፓ ስለግሪንላንድ ከመቆርቆሩ በፊት በሁለት እግሩ መቆሙን ያረጋግጥ" - ኔቶ
የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ የአውሮፓ ሀገራት በአሜሪካ ላይ የሚያቀርቡትን ቅሬታ እንዲያቆሙ አሳሰቡ።
በዚህም በህብረቱ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "አውሮፓ ስለግሪንላንድ ከመቆርቆሩ በፊት በሁለት እግሩ መቆሙን ያረጋግጥ" ሲሉ ተናግረዋል።
"የአውሮፓ ህብረት ያለ አሜሪካ እገዛ ራሱን መከላከል ይችላል ብሎ የሚናገር ህልም ማለሙን ይቀጥል" በማለት ያልተለመደ ንግግር አሰምተዋል።
ሩቴ "አውሮፓ ያለ አሜሪካ ራሱን መከላከል አይችልም" በማለት ገልጸዋል።
ማርክ ሩቴ በዚሁ ንግግራቸው "በኑክሌር ጥላ የሸፈነቻችሁ የደህንነት ዋስትናችሁን አሜሪካን እንዳታጡ" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ዋና ፀሐፊው የኔቶ አባል ሀገራት የመከላከያ በጀታቸውን በእጥፍ ማሳደግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። #thekoreaherald
@EyobTikuye @ThiqahEth
በኮንጎ ቢያንስ 25 ንጹሐን በታጣቂዎች ተገደሉ።
በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ንጹሐን ቢያንስ 25 ንጹሐን በታጠቂዎች መገደላቸው ተገልጿል
ንጹሐኑ የተገደሉት በቤታቸው ውስጥ በነበሩበት ወቅት በተፈጸመባቸው ጥቃት መሆኑን የመብት ተቋማት ድርጅቶች አስታውቀዋል።
ግድያውን የፈጸመው ራሱን ዲሞክራቲክ አላይድ ፎርስ (DAF) እያለ የሚጠራው የእስላማዊ ታጣቂ ቡድን ነው ተብሏል። #newsam
@EyobTikuye @ThiqahETH
የአውሮፓ ህብረት የኢራን አብዮታዊ ዘብን በአሸባሪነት ፈረጀ።
ህብረቱ የኢራን ጦር አካል የሆነውን የኢራን እስላማዊ አብዮት ጠባቂ (IRGC) አልቃይዳ እኩል እና አይኤስ በተካተቱበት የሽብር ድርጊት መዝግቦታል ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ "ጭቆና ምላሽ የለውም፣ ወሳኝ እርምጃ ወስደናል" ብለዋል።
ካላስ በቅርቡ በኢራን በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ህልፈት ተጠያቂ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ፈረንሳይ እና ጣልያን በአብዮታዊ ዘብ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል እቅድ ያቀረቡ ሀገራት ናቸው።
አሜሪካ በ2019 የኢራን አብዮታዊ ዘብን በአሸባሪነት ፈርጃዋለች። #europeanpravada
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ከንቲባው ከእሳት ጋር እየተጫወተ ነው" - ትራምፕ።
በሚኒያፖሊስ ያለው አለመረጋጋት አሁንም መቀጠሉ ተገልጿል።
በዚህም፣ የኢሚግሬሽን ፖሊሶች ከተቃዋሚዎች ጋር መጋጨታቸውን አላቆሙም ተብሏል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን በከተማዋ ለተፈጠረው አለመግባባት ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።
"ከንቲባው ከእሳት ጋር እየተጫወተ ነው" ያሉት ትራምፕ፣ "ከተማዋ የተወሰነ ተረጋግታለች" ሲሉ ገልጸዋል።
"ከንቲባ ፍሬይ ፖሊሶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቡ አስፈላጊ አይደለም" ብለዋል።
በአሜሪካ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከሀገር የማስወጣት እርምጃ ህዝባዊ ቁጣ ከቀሰቀሰ አንድ ሳምንት ተቆጥሯል። #asiaone
@EyobTikuye @ThiqahETH
የሶርያ ፕሬዚዳንት አህመድ አልሻራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩሲያ አቀኑ።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፕሬዚዳንት አልሻራን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ሩሲያ ለሶርያ የግዛት አንድነት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ተብሏል።
ሶርያን መልሶ ለመገንባት ሩሲያ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት መሀመድ አልሻራ በበኩላቸው፣ ከሞስኮ ጋር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ሩሲያ አደርገዋለሁ ያለችው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ሩሲያ ለረጅም አመታት በመሀመድ አልሻራ ሀይሎች በሀይል የተገረሰሰው የአላሳድ መንግስት ስትደግፍ ከመቆየቷም በላይ፣ ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ በሽሽት ወደ ሞስኮ ሲገቡ ጥገኝነት ሰጥታቸዋለች። #shafaqnews
#ማስተካከያ #ይቅርታ 🙏
ይህ ዘገባ የተወሰነ ማስተካከያ ተደርጎበታል። በዚህም ፕሬዚዳንት አልሻራ ወደ ሩሲያ ያቀኑት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳልሆነ እንድትረዱ እንፈልጋለን።
አህመድ አልሻራ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሩሲያ አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተገናኙት በህዳር 2024 ነበር። ከዚያ በኋላም በኦክቶበር 2025 እንዲሁ ወደ ሞስኮ አቅንተው ነበር።
ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ያቀኑት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የዘገባው ምንጭ #shafaqnews "First official visit" ሲል የገለጸውን ነበር ያስቀመጥነው።
@EyobTikuye @ThiqahETH
በሱዳን ኮርዶፋ በግጭት ከ88 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ።
በደቡብ ኮርዶፋ ግጭቱ መባባሱን ተከትሎ የተፈናቃዮች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩን ተመድ አስታውቋል።
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱዳሪች፣ "በሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ በሆነው ክልል ኮርዶፋ የሰብዓዊ ሁኔታው አሳሳቢ ሆኗል" ብለዋል።
"ከዚያ ያሉት ባለሙያዎቻችን እንደነገሩን ከሆነ መንገዶች በመቋረጣቸው እርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል" ሲሉም ተናግረዋል።
"ጥቂት የሰብዓዊ ረጂ ተቋማት ብቻ በከባድ ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ ነው" ነው ያሉት።
ከግማሽ በላይ የኮርዶፋ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ "ቀሪዎቹ በምግብ፣ የጤና አገልግሎት እና መሰረታዊ ነገሮች አለመሟላት ችግር ውስጥ ናቸው" ብለዋል።
ዱዳራች፣ "ሱዳናውያን ምግብ ይፈልጋሉ፣ ውሃ ይፈልጋሉ፣ መጠለያ ይፈልጋሉ" ሲሉ የሰብዓዊ አቅርቦት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ቃል አቀባዩ በጦርነት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ በመገንዘብ የተኩስ አቁም እንዲደርስ አሳስበዋል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahETH
ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬን ጦርነት ሰለባ ሆነዋል ተባለ።
የስትራቴጂክ እና አለማቀፍ ስተዲስ (CSIS) ሪፓርት እንደሚያሳየው፣ ወታደሮቹ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት እለት ጀምሮ ህይወታቸው አልፏል፣ ቆስለዋል ወይም ደግሞ ጠፍተዋል።
በዚህም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬን ጦርነት ሰለባ መሆናቸውን አስረድቷል።
ይህ የጦርነት ሰለባ አሀዝ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር መሆኑ ተገልጿል።
በ2022 በተጀመረው ጦርነት ሩሲያ 12 በመቶ የዩክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯን የስትራቴጂክ እና አለማቀፍ ስተዲስ (CSIS) አስታውቋል።
ሪፖርቱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ድል መቀዳጀቷ አይቀርም ብሏል። #cnn #TheIndependent
@EyobTikuye @ThiqahETH
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቻይና ገቡ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ የንግድ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
ስታርመር ከስምንት አመት በኋላ ወደ ቻይና ያቀኑ የብሪታኒያ መሪ ሆነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ወደ ቤጂንግ ሲያቀኑ ከ60 በላይ የሚሆኑ የንግድ፣ የትምህርት እና የባህል መሪዎችን በልዑካናቸው አካተዋል ነው የተባለው።
የአውሮፓ ሀገራት ከረጂም ጊዜ አጋራቸው አሜሪካ የሚጣልባቸው ታሪፍ ሌሎች አማራጮችን እንዲያማትሩ አስገድዷቸዋል ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት ከህንድ ጋር "የሁሉም ስምምነቶች እናት" ሲል የጠራውን ትልቅ የንግድ ስምምነት ትላንት መፈጸሙ ይታወቃል። #bbc #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
ታይላንድ ለ1700 ተጓዦች "የኒፓህ ቫይረስ" ምርመራ ማድረጓን ገለጸች።
በህንድ የተከሰተውን የኒፓህ ቫይረስ ተከትሎ አየር መንገድ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች እንደምትገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ምርመራው ያተኮረው ከህንድ ቤንጋል ክልል በሚመጡ ተጓዦች ላይ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።
ይሁን እንጂ ምርመራ ከተደረገላቸው 1700 ተጓዦች ካሁን በፊት በበሽታው የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አስታውቋል።
ምርመራ የሚደረግባቸው ሶስት አየር መንገዶች ሲሆኑ፣ እነሱም ሱባርናቡሚ፣ ዶንሙዋንግ እና ፑኬት ናቸው። #theindependent
@EyobTikuye @ThiqahETH
ሶማሊያዊቷ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ኢልሃን ኡማር ጥቃት ተፈጸመባት። ጉዳት ግን አልደረሰባትም።
የሚኒሶታ ግዛት የምክር ቤት ተወካይ ኢልሃን ዑመር በከተማው አዳራሽ ንግግር እያደረገች በነበረበት ወቅት ነው ጥቃት የደረሰባት ተብሏል።
ኢልሃን ኡማር ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰባት የተገለፀ ሲሆን፣ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብም ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
በኢልሃን ላይ ጥቃት የተፈጸመው በስደተኞች መመለስ ላይ ህዝባዊ ተቃውሞው በበረታበት ሰዓት መሆኑ በዶናልድ ትራምፕ መንግስት ላይ ተጨማሪ ጫና የፈጠረ ክስተት መሆኑ ተገልጿል።
የኮንግረስ አባሏ ጥቃቱ የተፈጸመባት በአሜሪካ የስደትና ጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ከሚኒያፖሊስ መወጣት እንዳለበቸው ንግግር በምታደርግበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አወሳስቦታል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢልሃን ጋር በተደጋጋሚ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። #anadoluagency
@EyobTikuye @ThiqahETH
የደቡብ ሱዳን ግጭት ሀገራዊ የግጭት ስጋት መደቀኑ ተገለጸ።
በሀገሪቱ ሰሜናዊው ክፍል በሚገኘው የጆንግሌ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በአማፂያን መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል ተብሏል።
የደቡብ ሱዳን ጦር አማፂ ኃይሎች ወደ ዋና ከተማዋ ጁባ እንዳይገቡ ለመከላከል ወታደሮችን ወደ ክልሉ ማሰማራቱ ተገልጿል።
አሁን ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመላ ሀገሪቱ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ተቋማት አስጠንቅቀዋል።
ተቋማቱ በ2018 የተፈጸመው የሰላም ስምምነት አንፃራዊ ሰላም ቢፈጥርም አሁን ግን በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት አጥቷል ብለዋል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የሁሉ ስምምነቶች እናት"!
ህንድ እና የአውሮፓ ህብረት "የሁሉ ስምምነቶች እናት" ያሉትን ስምምነት መፈጸማቸው ተገለጸ።
ስምምነቱን የፈጸሙት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የአውሮፓ ህብረት ካውንስል አንቶኒዮ ኮስታ እንዲሁም የህብረቱ ኮሚሽነር ኦርሱላ ቮንደርሊን ናቸው።
በስምምነቱ መሰረት ህንድ በአውሮፓ ምርቶች ላይ የጣለችውን ቀረጥ 96.6% ስትቀንስ፣ የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ወደ አህጉሩ በሚገቡ የህንድ ምርቶች ላይ የ99% ቀረጥ ቅናሽ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።
የሁለቱ ወገኖች ስምምነት 136.5 ቢሊዮን ዶላር የደረሰውን የንግድ ልውውጥ በ2030 ወደ 200 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ህንድ እና የአውሮፓ ህብረት ከኢኮኖሚ ስምምነት ባለፈ የመከላከያ እና የደህንነት ስትራቴጂካዊ ስምምነት ፈጽመዋል ተብሏል።
አሜሪካ የምትጥለውን ቀረጥ ለመከላከል ያግዛል የተባለው ይህ ጠንካራ ስምምነት የነፃ ንግድ ስምምነት (Free trade agreement) መሆኑ ተገልጿል።
ህንድ ከሩሲያ በምትገዛው ነዳጅ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት በግሪንላንድ ውዝግብ ምክንያት ለአሜሪካ የታሪፍ ቅጣት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። #npr
@EyobTikuye @ThiqahEth
#NewsAlert
በህንድ "መከላከያም ሆነ መቆጣጠሪያ የለውም" የተባለ አዲስ ኮቪድ መሰል ወረርሽኝ ተከሰተ።
በህንድ የተከሰተው ይሄው አዲስ "የኒፓህ ቫይረስ" በእስያ ላይ የጤና ስጋት መጋረጡ ታውቋል።
በህንድ ምዕራብ ባንጋል ክልል ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር ተመሳሳይነት ያለው "የኒፓህ" ድንገተኛ ወረርሽኝ መከሰቱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
አዲሱ ወረርሽኝ ከህንድ በተጨማሪ በባንግላዴሽ እና ማሌዥያ መከሰቱ ተረጋግጧል።
በዚህም ታይላንድ፣ ኔፓል እና ታይዋን ከህንድ የሚመጡ መንገደኞችን አየር መንገድ ላይ ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።
"የኒፓህ ወረርሽኝ ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ነው" ያለው ሚኒስቴሩ፣ ወረርሽኙ እንዳይዛመት በመላ ሀገሪቱ የጥንቃቄ መልዕክት መተላለፉን አስታውቋል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHI) በበኩሉ ወረርሽኙን፣ "ከባድ የጤና ስጋት" አድርጎ በመፈረጅ እንዳይስፋፋ የክትትል ስራ ያስፈልጋል ሲል አስጠንቅቋል።
ወረርሽኙ አዲስ በመሆኑ የመከላከያም ሆነ የመቆጣጠሪያ መድኃኒት የለውም ነው የተባለው። #novinite
@EyobTikuye @ThiqahETH
"አይደለም ሩቴ፣ አውሮፓ ለራሷ ደህንነት መስራት አለባት፣ ለራሷ ትበቃለች" ፈረንሳይ
ፈረንሳይ የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ስለ አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ የሰጡትን አስተያየት ነቀፈች።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂንኖዔል ባሮት፣ "አይደለም ሩቴ አውሮፓ ለራሷ ደህንነት መስራት አለባት፣ ለራሷ ትበቃለች" ብለዋል።
ባሮት፣ "አሜሪካ ብትስማማም ባትማማም አውሮፓ የኔቶ አምድ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ሌሊት ላይ በተካሄደው የህብረቱ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር "አውሮፓ ስለግሪንላንድ ከመቆርቆሩ በፊት በሁለት እግሩ መቆሙን ያረጋግጥ" ብለዋል።
ዋና ፀሐፊው "የአውሮፓ ህብረት ያለ አሜሪካ ራሱን መከላከል ይችላል ብሎ የሚናገር ህልም ማለሙን ይቀጥል፣ በኑክሌር ጥላ የሸፈነቻችሁ የደህንነት ዋስትናችሁን አሜሪካን እንዳታጡ" ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር አሰምተዋል።
ሩቴ በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ በአውሮፓ እና በአሜሪካ መካከል ውዝግብ በፈጠረው የግሪንላንድ ጉዳይ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ ግልጽ ያልሆነ ስምምነት ፈጸመው ትራምፕ ሊጥሉት የነበረውን ታሪፍ አስቀርተዋል።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን፣ "ስለስምምነቱ የምናውቀው ነገር የለም እኛን አይመለከትም" ሲሉ ገቢራዊ እንደማይሆን ገልጸዋል። #politico
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ዩኤኢ (UAE) ከየመን ሙሉ በሙሉ ለመውጣት ተስማምታለች" - ሳዑዲ
የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈይሰል ቢን ፋርሃን ሀገራቸው ከኤምሬት ጋር ያላት ግንኙነት አወንታዊ መሆኑን ተናገሩ።
ሁለቱ ሀገራት ከሁለት ሳምንት በፊት በየመን ጉዳይ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር።
አቡዳቢ በየመን የደቡብ "ተገንጣይ ቡድኖችን ስትደግፍ"፣ ሪያድ ደግሞ "ወታደራዊ ዘመቻ በማድረግ" ሁለት ግዛቶች ወደየመን መንግሥት እንዲመለሱ አድርጋለች።
ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደግሞ፣ "ዩኤኢ ከየመን ሙሉ በሙሉ ለመውጣት ተስማምታለች፣ ይህ ለግንኙነታችን ወሳኝ ነው ብየ አምናለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም "ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር ያለን ግንኙነት ለቀጠናው መረጋጋት ጠቃሚ ነው" በማለት አብራርተዋል።
ቢን ፋርሃን "ትብብራችን የገልፍ ትብብር ካውንስል (GCC) መሰረታዊ አካል ነው" ብለዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ጥያቄ መሰረት ዩኤኢ ወታደሮቿን ከየመን አስወጥታለች ተብሏል። #middleeastmonitor
ከዚህ ቀደም የተዘገበው እዚህ ይገኛል፣ /channel/thiqahEth/5036
@EyobTikuye @ThiqahEth
"30 ኢትዮጵያውያንና አሽከርካሪው ከእነንብረቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ናቸው" - ኮማንደር ምዊምባ
30 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዛምቢያ መያዛቸው የግዛቷ ፓሊስ አስታወቀ።
በህገወጥ መንገድ ወደ ዛምቢያ ለመግባት የሞከሩት ኢትዮጵያውያኑ በትናንትናው ዕለት በምሽት በምስራቃዊ ዛምቢያ የኒምባ ግዛት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
የምስራቃዊ ግዛት ፖሊስ ኮማንደር ሮበርትሰን ምዊምባ፣ "የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ህገወጥ ስደተኞች በአምቡላንስ ተሳፍረው ለመግባት ሲሞክሩ ተይዘዋል" ብለዋል።
ኮማንደሩ፣ "አሽከርካሪው በካቴቴ ግዛት ከሚገኘው ኬኔዲ ፌሪ ሆስፒታል ህመምተኛ እንዳለ አሳውቆ አምቡላንስ እንደሚያስፈልግ መመሪያ የተሰጠው ቢሆንም አምቡላንሱን ይዞ ሲመለስ ሰላሳ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጭኖ ተገኝቷል" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።
ኮማንደር ምዊምባ፣ "30 ኢትዮጵያውያን እና አሽከርካሪው ከእነንብረቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ናቸው" ሲሉ አሁን ያሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል። #lusakatimes
@EyobTikuye @ThiqahETH
በሚኒሶታ የተፈጸመው ተጨማሪ ግድያ በትራምፕ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ትችት አስነሳ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከሀገር የማስወጣት ዘመቻ እንዲያስፈጸሙ ያሰማሯቸው ኃይሎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች በተቃዋሚዎች በኩል ቁጣን ቀስቅሷል።
ክስተቱ ስጋት በመፍጠሩ ህጋዊ ነዋሪዎችን ሳይቀር ድርጊቱን ማውገዛቸው ተገልጿል።
በሚኒሶታ ከሞቱት ሦስት ንጹሐን ዜጎች ውስጥ ሁለቱ እርምጃውን ለመቃወም የወጡ ነጭ አሜሪካዊን ዜጎች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የ37 አመቱ አሌክስ ፔራቲ ግድያ ፖለቲካዊ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት "ትራምፕ በአንድ አመት ውስጥ ህዝባዊ ቅቡልነት እንዲያጡ አድርጓቸዋል ነው" የተባለው።
የሚኒሶታ ገዥ ቲም ዋልዝ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሰማሯቸውን የፌዴራል ኃይሎች እንዲያስወጡ ቢጠይቁም ትራምፕ "ዋልዝ ስህተቱን ለመደበቅ እየሞከረ ነው" ሲሉ ወንጅለዋል።
ብሄራዊ ተቃውሞው የቀሰቀሰው ግድያ ዲሞክራቶች በወቅቱ የትራምፕ አስተዳደር ላይ ጫና ለመፍጠር እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ተብሏል። #cnn
@EyobTikuye @ThiqahETH